Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
" አረጋዊ ካህኑ ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት መ/መ/ቀ/ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ አረጋዊ ካህን ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል። መ/መ/ቀ/ወ/ኢየሱስ…
#EOTC

በአረጋዊው መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌውና አራት ቤተሰባቸው ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያን በልዩ  ሁኔታ እንደሚከታተለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አሳውቋል። 

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ (ሞጆ )  ወረዳ ቤተ ክህነት  በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ  ለ41 ዓመታት ያህል ከድቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትኅትና ሲያገለግሉ የቆዩት መልአከ /መ/ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ባሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ይታወቃል።

ግድያው " ማንነታቸው ለጊዜው አልታወቀም " በተባሉ ኃይሎች መፈጸሙን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከትን ዋቢ በማድረግ ያመለከተው ጠቅላይ ቤተክህነት ግድያው በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸመ ነው ብሏል።

ጠቅላይ ቤተክህነት በዚህ አሰቃቂ ግድያ ሕይወታቸውን ባጡ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮችና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

" ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደረሰውን አስደንጋጭ ሀዘን ከሰሙ ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩን በልዩ ትኩረት እየተከታተሉት ይገኛሉ " ብሏል።

ዝርዝር ሁኔታውን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገርና እስከ መጨረሻው ጫፍ በመድረስ ሕጋዊ እልባት  እንዲያገኝ እንደሚደረግ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የዋጋ ጭማሪ የተደረገባቸው አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ጭማሪ አድርጓል።

ተቋሙ በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ያደረገው የዋጋ ጭማሪ ከፍ ያለ ነው።

ለአብነት ፦

° የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ማሳወቅ አገልግሎት 500 ብር የነበረው 1,000 ብር ገብቷል።

° የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ለሽያጭ አገልግሎት 2,310 ብር የነበረው 4,000 ብር ገብቷል።

° የተሽከርካሪ የባለቤትነት ስም ዝውውር አገልግሎት 3,000 ብር የነበረው 5,000 ብር ገብቷል።

° ለዓመታዊ ምርመራ ተለጣፊ ምልክት (ቦሎ) ግልባጭ ለመጀመሪያ ጊዜ 1,010 ብር የነበረው 2,500 ብር ተደርጓል።

° የተሽከርካሪ ባለቤት ማረጋገጫ ሊብሬ 300 ብር የነበረው 1200 ብር ተደርጓል።

° ሊብሬ ሲበላሽ ወይም ሲጠፋ ምትክ ፣ የማደሻ ቦታው ሲያልቅ መስጠት 3,000 ብር የነበረው 3,500 ብር ሆኗል።

° መረጃ መስጠት 300 ብር የነበረው 700 ብር ተደርጓል።

° አዲስ መንጃ ፍቃድ መስጠት 680 ብር የነበረው 1500 ብር ተደርጓል።

° ለጠፋ መንጃ ፍቃድ ማፈላለጊያ ለፖሊስ ወይም ለፕሬስ የሚሰጥ መረጃ 100 ብር የነበረው 700 ብር ተደርጓል።

° ከ3 ጊዜ በላይ የፅሁፍ ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት 100 ብር የነበረው 300 ተደርጓል።

° ከ3 ጊዜ በላይ የተግባር ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት ከ300 ብር ወደ 600 ብር ጨምሯል።

° የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እድሳት ከ620 ብር ወደ 1000 ብር ገብቷል።

° ለጠፋ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ምትክ መስጠት 620 ብር የነበረው 5,000 ብር ገብቷል።

(ተጨማሪ በተለያዩ አገልግሎቶች ላይ የተደረገውን የታሪፍ ጭማሪ ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

ማንቸስተር ዩናይትድ እሁድ ከምሽቱ 12፡30 ወደ ሜዳ ይመለሳል🔥
Man United vs Tottenham በSS Premier League ቻናል 223
🤔ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት መንገድ ይመለሳል?

እንዳያመልጥዎ…
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራትም፣ በብራንድም፣ በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ  በፈለጉት ስክሪን መጠን ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን።

ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፊት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ። በላፕፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!
!
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ° " እርባና የሌለው ልዩነታችንን ትተን ለህዝባችን ሰላምና እፎይታ እንስጠው " - አቶ ጌታቸው ረዳ   ° " ሰላማዊ ፓለቲካዊ ትግላችን ማጠናከር ይገባል " - የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል ዛሬ በትግራይ ፣ መቐለ ጮምዓ ተራራ ሲከበር የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ሌ/ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ተገኝተው…
#Tigray

" ስም በማጥፋት የሚፈታ የትግራይ ችግር የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ መስከረም 19/2017 ዓ.ም ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ተወካዮች ጋር  በመቐለ የሰማእታት ሃወልት አዳራሽ ተወያይተዋል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ " ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተልእኮዎቹ በአግባቡ እንዳይወጣና እንዳይፈፅም ከቅርብና ከሩቅ የሚያጋጥሙት መሰናክሎች በመመከት በትኩረት ይሰራል "
ብለዋል።

" ስም በማጥፋት የሚፈታ የትግራይ ችግር የለም " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " የህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ የምንሰራዎች የጋራ ስራዎች በአንድነት መፈፀም አለባቸው " ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ዛሬ ከደቡባዊ ምስራቅ ዞን ተወካዮች በመቐለ የሰማእታት ሃወልት አዳራሽ ያካሄዱት ህዝባዊ ውይይት የነበረው መልክ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታዝቧል።

" በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና በአቶ  ጌታቸው ረዳ የሚመራ ህወሓት " ተብሎ ለሁለት ከተከፈለ በኋላ ዛሬ በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው መሪነት በመቐለ የተካሄደው ህዝባዊ ውይይት ከባድ ድባብ ነበረው።

ውይይቱ መስከረም 13/2017 ዓ.ም ሊካሄድ  ታቅዶ ይፋ ባልሆነ ምክንያት ወደ መስከረም 19 / 2017 ዓ.ም የተሸጋገረ ነድ።

ዛሬ በህዝባዊ ውይይቱ ለመሳተፈ በመቐለ ዙሪያ ከሚገኙ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ወረዳዎች ዶግዓ ተምቤን ፣ እንደርታ ፣ ሕንጣሎ ወጀራት ፣ ሳምረ ሳሓርቲ የተውጣጡ የህዝብ ተወካዮች በአራት አቅጣጫ ወደ መቐለ ሲገቡ በከተማዋ መግብያ የፓሊስ ፍተሻ ገጥሟቸው ነበር።

በተያያዘ ህወሓት ለዓመታት በብቸኝነት ለፓለቲካዊ ስብሰባዎቹ ሲጠቀምበት የነበረውን የሰማእታት ሃወልት አዳራሽ ለመግባት የተሰበሰበው ህዝብ የአዳራሹ ቁልፍ በሰአቱ ባለመከፈቱ ከአዳራሹ ውጭ ፀሐይ ላይ እንዲቆይ ተገዷል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ከተምቤን ፣ ዓዲግራት ፣ ማይጨውና ፣ መኾኒ ቀጥለው በእንዳስላሰ ሽረ ሊያካሂዱት ያቀዱት ህዝባዊ ውይይት በአዳራሽ ውስጥ በተፈጠረ አለመደማመጥና ግርግር ተቋርጦ ነበር።

ዛሬ በመቐለ ከደቡባዊ ምስራቅ ዞን ተወካዮች ያካሄዱት ውይይት " ተጨማሪ ድጋፍ ያስገኝላቸዋል ፤ የሚታየው ህዝባዊ መነቃቃት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅና የመሰብሰብ ዴሞክራሲ መብቶች ያጎለብታል " የሚሉ ብዙሃን አስተያየት ሰጪዎች ጎን ለጎን " ፕሬዜዳንቱ የሚታይ የሚዳሰስ  ነገር ሳይሰሩ በህዝብ ደጋፍ እየሰከሩ ነው " የሚሉ አልታጡም።   

በመቐለ ዙሪያ የሚገኘው የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዶ/ር ደብረፅዮን በሚመሩት ህወሓት የፓሊት ቢሮ አባል የሆኑት ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ አቶ ፀጋይ ገብረተኽለ ዋና አስተዳዳሪ ሆኖው እንዲሰሩ በጊዚያዊ አስተዳደሩ በቅርቡ መሾማቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ መሪነት ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ተወካዮች  በተከናወነው ህዝባዊ ውይይት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

@tikvahethiopia 
2024/10/01 02:20:47
Back to Top
HTML Embed Code: