Telegram Web Link
#ውጤት

የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #1

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
👆የቀጠለ

የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #2

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
👆የቀጠለ የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #2 #TikvahEthiopia @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ውጤት እንዴት ማየት ይቻላል ?

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል።

ውጤት እንዴት ማየት እንደሚቻል በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሰዋል።

እኛም ተፈታኞች እንዴት ነው ውጤታቸውን ማየት የሚችሉት ? ስንል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡

" ተማሪዎች ውጤታቸውን በኦንላይን የሚያዩበትን አማራጭ አድራሻዎች ማምሻውን አገልገሎቱ ይፋ ያደርጋል " ሲሉ ከፍተኛ አመራሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት በድረ-ገፅ፣ በአጭር የፅሑፍ መልዕክት እና በቴሌግራም ቦት ይፋ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል።

አገልግሎቱ አማራጭ አድራሻዎቹን ይፋ እንዳደረገ ወደናንተ እናደርሳለን።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ውጤት እንዴት ማየት ይቻላል ? የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል። ውጤት እንዴት ማየት እንደሚቻል በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሰዋል። እኛም ተፈታኞች እንዴት ነው ውጤታቸውን ማየት የሚችሉት ? ስንል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን…
#ውጤት : የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል።

በሚከተሉት አማራጮች ውጤታችሁን ተመልከቱ፦

በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም ቦት 👉 https://www.tg-me.com/EAESbot

ከውጤት መግለጫ ፖርታል እና ቴሌግራም ቦት ላይ ጊዜያዊ ሰርቲፊኬት ማውረድና ማተም እንደምትችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በውጤት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ካላቸው ወደ አገልግሎቱ ቢሮ በአካል መሔድ ሳያስፈልጋችሁ ከSMS በስተቀር በውጤት መግለጫ አማራጮቹ ላይ Compliant የሚለውን በመጫን የቅሬታቸውን ዓይነት በተዘጋጀ የቅሬታ ፎርም ላይ በትክክል በመሙላት ማቅረብ ትችላላችሁ።

አገልግሎቱ በቅሬታችሁ ላይ ምላሽ ቅሬታቸውን ባቀረቡበት ተመሳሳይ አድራሻ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።

Via @tikvahuniversity
#Tigray

" እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴና መሳሳብ ህዝብ ስላልወደደው አሁኑኑ መቆም አለበት !! " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ም/ ፕሬዚደንትና የሰላምና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ካቢኔ ሃላፊ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ፥ " በአሁኑ ወቅት ለሁለት በተከፈለው ህወሓት መካከል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴና መሳሳብ ህዝብ ስላልወደደው መቆም አለበት " ብለዋል።

ሌ/ጄነራሉ " በተቃውሞ ሆነ በድጋፍ የህዝብ ማእበል ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ህዝቡ ስጋት ውስጥ እየከተተ ስለሆነ ከአሁን ጀምሮ መቆም አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

" ሰላማዊ የአዳራሽ ውስጥ ሰብሰባ ማድረግ ይፈቀዳል " ሲሉ አክለዋል።

ሌ/ጄነራል ታደሰ " አዳዲስ የመንግስት የስራ ምደባዎች እየታዩ ነው ምደባዎች እንዲቆሙ ሁሉም ነገሮች በስከነ አካሄድ እንዲፈፀሙ እንጠይቃለን " ብለዋል።

" የማስማማት ጥረት እየተደረገ ነው (ለሁለት የተከፈሉትን የህወሓት አመራሮች) ፤ ከተቻለ አንድ እንዲሆኑ ካልተቻለ ልዩነታቸው አክብረው በህግ እንዲጓዙ ከዚህ ውጭ ያለው አካሄድ ግን ቀይ መስመር አለው የሚባል ስላልሆነ መገታት አለበት " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል ሌ/ጄነራሉ " የትግራይ እና የአማራ ህዝቦች ዘላቂ ግንኙነት የሚጎዳ ማንኛውም እንቅስቃሴ መቆም አለበት " ብለዋል።

ተመላሽ ተፈናቃዮች ላይ ሰላምን የሚረብሽ እንቅስቃሴ እንዳለ በመጠቆም " ይሄ መቆም አለበት " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ይህንን ዓይነት እንቅስቃሴ ፍሬ ያለው ትርጉም የሌለው መሆኑ ካለፈው እንማር " ሲሉ ገልጸዋል።

" በጠብመንጃ የሚወሰድ መሬትም ሆኖ የሚቀየር ድንበር የለም ስለሆነም በአማራ ክልል በኩል ያሉ ታጣቂዎች ከድርጊታቸው በመቆጠብ ወደ ቀልባቸው ይመለሱ " ሲሉ ማሳሰባቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመግለጫው የአማራ ክልል ስም በመነሳቱ በክልሉ በኩል የሚሰጥ ምላሽ ጠይቆ ያቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ውጤት : የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል። በሚከተሉት አማራጮች ውጤታችሁን ተመልከቱ፦ ► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et ► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284 ► በቴሌግራም ቦት 👉 https://www.tg-me.com/EAESbot ከውጤት መግለጫ ፖርታል እና ቴሌግራም…
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ተማሪዎች እና ወላጆች የፈተናውን ውጤት ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ።

ውጤት የሚታየው ፦

► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

► በቴሌግራም ቦት 👉 https://www.tg-me.com/EAESbot ላይ ነው።

ከፍተኛ የኔትዎርክ መጨናነቅ ስለሚኖር በትዕግስት ይሞክሩት።

በ2016 ዓ / ም ለፈተናው ከተቀመጡት ከ684 ሺህ በላይ ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች (5.4 በመቶ) ናቸው በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን 50% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡት።

ምንም እንኳን በተማሪ ቁጥር ደረጃ ከአምናው የቀነሰ ቢሆንም በቀጣይ የትምህርት ዘመንም የሬሜዲያል ፕሮግራም ይኖራል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ አመት ልዪ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ፣ ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮችን እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡
- Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @ TecnoEt ፣ ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia እና ለ TikTok @ TecnoEt ን  ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።)
- በተጨማሪም #TecnoEt2017 ን keyword መጠቀም እንዳይረሱ)
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ
አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ።

የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
2024/09/30 10:26:48
Back to Top
HTML Embed Code: