Telegram Web Link
#Ethiopia

ውጤቱ በጣም ዝቅተኛ ነው !

" በ2016 ትምህርት ዘመን በወረቀትና በበይነ መረብ የተሰጠው ፈተና ውጤት እንድምታው ሲታይ ከ2014 ዓ/ም 30,034 (3.3%) ፣ ከ2015 ዓ/ም 27,267 (3.2%) ... (ዘንድሮ 5.4%) መሆኑ እያሽቆለቆለ እየሄደ ያለው ጉዞ የተገታ እና መጠነኛ የመሻሻል አዝማሚያ ያሳየ ቢሆንም አሁንም 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተፈታኞች ቁጥር በጣም #ዝቅተኛ ነው። " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር)

@tikvahethiopia
Jasiri is looking for young, motivated and impact driven women entrepreneurs to join our 13 month, fully funded talent investor program.

Apply today for a chance to make a change through high impact entrepreneurship.

👉🏾 https://bit.ly/3A8rxtV

For more information, Join our telegram channel 👉🏾 @Jasiri4Africa
#SafaricomEthiopia

🌻 አንዴ የበዓል ዝግጅታችንን ቆም አርገን 🏃🏼ወደ TikTok ሄደን ተሰጥዖአችንን እናሳይ!
እስከ መስከረም 18 ብቻ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ  እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#1Wedefit #FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
#Oromia : በመሬት ናዳ የሦስት እህትማማቾች ሕይወት አለፈ።

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባላት የነበሩ 3 እህትማማቾች መሞታቸውን የዞኑ አደጋ መከላከል ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ኑራ መሐመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ህይወት የጠፋው በአንድ አባወራ መኖሪያ ቤት አፈር ተደርምሶ ነው።

የእናት እና አባት ህይወት ሲተርፍ ሶስቱ ልጆቻቸው ሞተዋል።

አደጋው የተከሰተው ጷጉሜ 2 ሌሊት ስምንት ሰዓት ላይ ሲሆን አስክሬናቸውን የአካባቢው ማህበረሰብ በነጋታው በማውጣት የቀብር ስነ ስርዓታቸው እንዲፈጸም መደረጉን የዞኑ አደጋ መከላከል ጽ/ቤት ገልጾልናል።

አደጋው በተከሰተባቸው አኮ ጅሩ፣ኢሉ ኩታዬ እና ኡነይ ቀበሌዎች ከሰው ህይወት ህልፈት በተጨማሪ በሰብል የተሸፈነ 20 ሄክታር ማሳ መውደሙ ተነግሯል።

በተጨማሪም ከጅማ ሆሮ ወደ ጊዳሚ የሚወስደው መንገድ በመሬት መንሸራተቱ መዘጋቱን እና ለማስከፈት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ሃላፊው አክለዋል።

ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑ ተጨማሪ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ 10 ቤቶች ላይ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን በማንሳት ወደሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፍሩ እየተሰራ ነው ተብሏል።

Via @tikvahethmagazine
#ውጤት

የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #1

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
👆የቀጠለ

የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #2

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
👆የቀጠለ የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #2 #TikvahEthiopia @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ውጤት እንዴት ማየት ይቻላል ?

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል።

ውጤት እንዴት ማየት እንደሚቻል በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ደርሰዋል።

እኛም ተፈታኞች እንዴት ነው ውጤታቸውን ማየት የሚችሉት ? ስንል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡

" ተማሪዎች ውጤታቸውን በኦንላይን የሚያዩበትን አማራጭ አድራሻዎች ማምሻውን አገልገሎቱ ይፋ ያደርጋል " ሲሉ ከፍተኛ አመራሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ውጤት በድረ-ገፅ፣ በአጭር የፅሑፍ መልዕክት እና በቴሌግራም ቦት ይፋ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል።

አገልግሎቱ አማራጭ አድራሻዎቹን ይፋ እንዳደረገ ወደናንተ እናደርሳለን።

Via @tikvahuniversity
2024/10/01 19:29:38
Back to Top
HTML Embed Code: