Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
“ የልጅነት ልጄን አድኑልኝ። ሁለት የልብ ክፍተት ህመም አለበት ፤ ለህክምና 665 ሺህ ብር ተጠይቄአለሁ ” - የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህር የ2 ዓመት ከ5 ወር ልጃቸው የታመመባቸው አቶ ገ/መድህን መብርሃቱ የተባሉ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ለህክምና የተጠየቁት ገንዘብ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ እርዳታ እንዲደረግላቸው ተማጸኑ። ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የህፃኑ አባት፣ “ ህፃኑ ሁለት የልብ ክፍተት…
"ገንዘቡ ስላልሞላልኝ ልጄ በህመም እየተሰቃዬ ይገኛል " - ልጃቸው በጠና የታመመባቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህር

የሁለት ዓመት ልጃቸው በሁለት የልብ ክፍትት ህመም በጠና የታመመባቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህር ገ/መድህን መብርሃቱ ለህክምና 665 ሺህ ብር ተጠይቀው ከዚህ ቀደም እናንተኑ እርዳታ ጠይቀው ነበር።

ላደረጋችሁላቸው እርዳታም በቅድሚያ ልባዊ ምስጋና አቅርበውላችኋል።

ሆኖም ልጃቸው በቶሎ መታከም እንዳለበት ቢነገራቸውም የተጠየቁት ገንዘብ ስላልሞላላቸውና ከሰርጄሪ በኋላ ከ5 በላይ መድኃኒት በማስፈለጉ  በድጋሚ እርዳታ እየጠየቁ ነው።

ከ150 ሺሕ ብር እንደሚያስፈልጋቸው፣ ገንዘቡ ካልተሟላ ደግሞ ህፃኑን ማሳከም እንደማይችሉ አስረድተዋል።

" የጎደለውን ገንዘብ በመሙላትና ሁሉም በየእምነቱ በፀሎት በማገዝ የልጅነት ልጄን እንድታድኑልኝ በእግዚአብሔር ስም እማጸናለው " ብለዋል።

መረዳት ለምትሹ 1000543793508  የአቶ ገብረ መድህን መብራቱ ኣብርሃ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር ነው።

በተጨማሪ ለመደወል 0914178980 (አባት)፣
0946482480 (እናት)።

@tikvahethiopia
🔈#የጤናባለሙያዎችድምፅ

" ከ15 ወራት በላይ የዱቲ ገንዘብ አልተከፈለንም በዚህ ኑሮ ውድነት በብድር በዬ ወሩ ተሰቃየን " - ጤና ባለሙያዎች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፣ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ15 ቀናት የዘመቻ አበልና ከአንድ አመት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመፈጸሙ ችግር ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ ዝርዝር ቅሬታ ምንድን ነው ?

" እኛ ጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ የምንገኝ ጤና ባለሙያዎች በጣም ተቸግረናል። በሰራነውና በለፋነው ልክ ክፍያ እየተከፈለን አይደለም።

አሁን ላይ ትልቁ ችግራችን ቢግ ካቻፕ ተብሎ በመጣ ዘመቻ ላይ ከ15 ቀናት በላይ ስራ ላይ ያሳለፍን ሲሆን፣ ለጤና ባለሙያ የክፍያ ገንዘቡ መጥቷል።

ክትባቱ ከ5 ዓመት በታች ላሉ ሕፃናት የሚሰጡ Rota፣ Ipv፣ Mcv፣ Vitamin A፣ Vermox፣ BCG፣ Opv የመሳሰሉት የክትባት አይነት ነው።

በዘመቻ ሰዓት ODK ተብሎ በሁሉም ቤት እየገባን ልክ እንደ ቤት ቆጠራ ከኪሳችን እያዋጣን የሞላነው ገንዘብ ጭምር አልተከፈለንም።

የቢግ ካቻፕ የክትባት ዘመቻ በሁሉም በጌዴኦ ዞን ባሉት ወረዳ ላይ ገንዘቡ ቢሰጥም ሁሉንም ወረዳ ያማከለ አይደለም።

ለምሳሌ ይ/ጨፌ፣ ወናጎ፣ ራጴ፣ ገደብ ላይ ከ6,500 ብር በላይ ተሰጥቷል። ዲላ ዙሪያ ወረዳ ግን 1, 800 ብር ለመስጠት፣ ለማስፈረም ሲሉ ጤና ባለሙያ እያቀረበ ያለውን ቅሬታ ሰሚ አካል ለማግኘት አልቻለም።

በሌላ በኩል ከ15 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም በዚህ ኑሮ ውድነት በብድር በዬ ወሩ ተሰቃዬን" የሚል ነው ቅሬታቸው።

ለተነሳው ለዚህ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ ወደ ጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ ብንሞክርም ስልክ ለማንሳትም ሆነ መልዕክት ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ትግራይ

በአንድ ሳምንት ብቻ የክረምቱ ከባድ ዝናብና ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የሰው ህይወት ጠፍቷል። አዝርእት ወድሟል። በርካታ እንስሳት በጎርፍ ተወስደዋል። 26 አባወራዎች አፈናቅሏል።

በያዝነው ሳምንት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በከባድ ዝናብና ጎርፍ ከፍተኛ የተባለ አደጋ ደርሷል።

በአጠቃላይ 25 ሰዎች እንደሞቱም ተነግሯል።

በአፅቢ ወረዳ ያጋጠመው አደጋ ግን የከፋ ነው ተብሏል።

በአፅቢ ወረዳ " ስዩም ቀበሌ ገበሬ ማህበር " ሃይለኛ ዝናብ ቤት አፍርሶ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው አልፏል።

ቤቱ በውድቅት ሌሊት መፍረሱ አደጋውን የከፋ አደርጎታል።

ቤተሰባቸው ያጡ እማወራ እንዳሉት ፥ ባለቤታቸውና ሁለት ልጆቻቸው በአደጋው ምክንያት በማጣታቸው የመኖር ተስፋቸው ጨልሞ ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

የአደጋው ሰለባ የመኖር ተስፋቸው ዳግም እንዲያንሰራራ መንግስትና አቅም ያለው ሁሉ እንዲያግዛቸው ጥሪ አማቅረባቸውን ከዞኑ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተያያዘ በቀጠለው ሃይለኛ ዝናብና ከባድ ክረምት በተለያዩ አከባቢዎች የመሬት መንሸራተት እየተስተዋለ ነው።

በአምባላጀ ፣ በእንትጮ ከተማ ዙሪያ ሃይለኛ ዝናብ ያስከተለው የመሬት መንሸራተት 31 ቤቶች አፍርሶ 31 ሄክታር መሬት ላይ የነበረውን አዝርእት ከጥቅም ውጭ በማድረግ ዘጠኝ አባወራዎች አፈናቅሏል።

እንስሳትም በጎርፍ ተወስደዋል። 

በመቐለ ዙሪያ የሚገኘው የገረብ ግባ ግድብ ከልክ በላይ ሞልቶ በመፍሰሱ ምክንያት በ 138 ሄክታር መሬት የተዘራ እህል ላይ ጉዳት አድርሷል።

በአደጋው የተጎዱ 270 የእንደርታ ወረዳ አርሶ አደሮች ጊዚያዊ  አስተዳደሩ ግብረ ሃይል አቋቁሞ እንዲያግዛቸው ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
" ኢትዮጵያ አሁን ያላትን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት 10 ወደቦች ያስፈልጓታል " - ጅቡቲ

ጅቡቲ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ በሚል ከኢትዮጵያ 100 ኪ/ሜ ርቆ የሚገኘውን የ ' ታጁራ ወደብ ' ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት የሚል የመፍትሄ ሀሳብ አቅርባለች።

ለጊዜው በምን መልኩ ፤ እንዴት ነው የምትጠቀመው የሚለው በዝርዝር አልታወቀም።

ኢትዮጵያ ይህን የጅቡቲ ጥያቄ ትቀበለው አትቀበለው እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም።

የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዩሱፍ ምን አሉ ?

" ይሄ ለኢትዮጵያ በጣም የሚጠቅም ነገር መሆኑን እናውቃለን።

ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ ሸማቾች ያሏት ትልቅ ሀገር እንደመሆኗ ኢትዮጵያ ከ3 እና 4 በላይ ወደቦች ያስፈልጓታል።

ኢትዮጵያ አሁን ያላትን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት 10 ወደቦች ያስፈልጓታል።

እኛ እነዚህን የኢትዮጵያን ፍላጎቶች እንረዳለን። የሚጠበቀውን ለማድረግም እንሞክራለን።

ኢትዮጵያ የባህር ኃይል ጦር ሰፈር መገንባት አትችልም ግን ኢትዮጵያ ከአንድ በላይ ወደብ እንዲኖራት ለመርዳት እንፈልጋለን።

ኢትዮጵያ ከአንድ በላይ መተላለፊያ እንዲኖራት በማገዝ የተፈጠረውን ውጥረት በማርገብና ሁሉም እንዲረጋጋ በማድረግ በዋናው ቁምነገር ላይ ማተኮር አለብን።

እንደ ጅቡቲ ያለን ሚና ያ ነው። ላለፉት ዓመታት ስናደርግ የነበረውም ያንን ነው። አሁንም በነዚህ መርሆች ላይ መስራታችንን እንቀጥላለን።

እኛ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የነበረው መልካም ግንኙነት ወደነበረበት እንዲመለስ እንፈልጋለን " ብለዋል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል።

ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት የአፍሪካ ግዝፏ ሀገር #ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ ስትሆን ያላት ፍትሃዊ ጥያቄዋ ላለፉት በርካታት አመታት እንደ ሀገር አጀንዳ ሳይሆን ቆይቷል። ጉዳዩም በዚህ ልክ ተነስቶ አያውቅም ነበር።

ከወራት በፊት ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ ግን ጉዳዩ የዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኗል።

ምንም እንኳ ስምምነቱን ተከትሎ ሶማሊያ አኩርፋ ግንኙነቷን ብታሻክርም ችግሩን ለመፍታት በሚል የተለያዩ የመፍትሄ ሀሳቦች መቅረብ ጀምረዋል።

ሀገሪቱ (ሶማሊያ) ከ " ኢትዮጵያ ጋር አልነጋገርም " ብትልም ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ ያላትን አቋም ከተመለከተች በኃላ በአሸማጋዮች አማካኝነት ወደ ውይይት ጠረጴዛ መጥታለች። ምንም እንኳ እስካሁን ውይይቶቹ ፍሬ አልባ ቢሆኑም።

#ETHIOPIA

@tikvahethiopia
ወጋገን ባንክ !

ልዩ የአውድ ዓመት ስጦታ ከወጋገን ባንክ

ወጋገን ባንክ መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከውጭ ሀገር ከወዳጅ ዘመድዎ በደሀብሽል፣ ዌስተርን ዩኒየን፣ መኒ ግራም እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል እና በባንኩ ስዊፍት አድራሻ WEGAETAA እስከ መስከረም 30 የሚላክልዎትን ገንዘብ ከወጋገን ባንክ ሲቀበሉና የውጭ ሀገር ገንዘብ ሲመነዝሩ ከመቼውም ጊዜ ከፍ ባለ የምንዛሬ ዋጋ ገንዘብዎን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ያስረክብዎታል፡፡

September 5, 2024 Thursday Exchange Rate
#WegagenBank #ExchangeRate #Currency
Follow us and get more information...
www.tg-me.com/WegagenBanksc
#DStv

🌼አዲሱን አመትን ምክንያት በማድረግ የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ800 ብር ቅናሽ እስከ መስከረም 20 ለተጨማሪ አንድ ወር መራዘሙን እንገልፃለን!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በመግዛት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፣ ቻምፒዮንስ ሊግ ፣ ላሊጋ ፣ ሴሪ አ ጨዋታዎችን ጨምሮ የሚወዱትን ክለብ በሚመርጡት ፓኬጅ ላይ እንደየምርጫዎ በዲኤስቲቪ ይዝናኑ!

ሁሉንም ታላላቅ ሊጎች፣ ሁሉንም የቡድን ወኔ፣ ሁሉንም ትንታኔዎች ... ሁሉም በዲኤስቲቪ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስአበባ #መታወቂያ “ የትምህርት ቤት ምዝገባው ሲጠናቀቅ አገልሎቱን መስጠት እንጀምለራለን ” - CRRSA ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው አዲስ አበባ ከተማ ለመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት “በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን” መባሉን ከወራት በፊት ነግረናችሁ ነበር። አሁንስ ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትሰጡ ከዚህ ቀደም ገልጻችሁ ነበር፤…
መታወቂያ መስጠት መቼ ይጀመራል ?

" አሁን ማጣራት ጀምረናል የገቡትን መረጃዎች፣ አሰራሮችና ማኑዋሎች ጭምር ተዘጋጅቷል " - CRRSA

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከክልል ከተሞች መሸኛ ለሚያመጡ ዜጎች የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ መስጠት መቼ እንደሚጀምር ጠይቀነው የሰጠንን ምላሽ በተደጋጋሚ አድርሰናችሁ ነበር።

ኤጀንሲውን ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ መቼ ይጀመራል ? ብለን ጠይቀን በሰጠን ምላሽ፣ በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጾ ነበር።

ከቆይታ በኋላ ላቀረብንለት ተመሳሳይ ጥያቄ ቀሰጠው ምላሽ፣ " የትምህርት ቤት ምዝገባ ሲጠናቀቅ አገልግሎቱን መስጠት እንጀምራለን " ነበር ያለው።

የትምህርት ቤት ምዝገባው ሲጠናቀቅ መቼ መሰጠት እንደሚጀመር በወቅቱ ስንጠይቅም፤ ከነሐሴ አጋማሽ 2016 ዓ/ም በኋላ እንደሚሰጥ መግለጹ አይዘነጋም።

አሁንስ አገልግሎቱ መሰጠት ተጀመረ ?

አሁንስ አገልግሎቱን መስጠት ተጀምሯል ? ስንል የጠየቅናቸው አንድ የኤጀንሲው አካል፣ " ገና ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ የሚጀመር ይመስለኛል፡፡ ግን ገና ነው " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ከነሐሴ አጋማሽ በኋላ አገልግሎቱን እንደምትሰጡ ገልጻችሁ ነበር ብለን አስታውናቸዋል።

እኝሁ አካልም፣ " አዎ። አሁን ማጣራት ጀምረናል የገቡትን መረጃዎች፣ አሰራሮችና ማኑዋሎች ጭምር ተዘጋጅቷል፡፡ ገና መስጠት አልተጀመረም " ነው ያሉት።

አሁንስ መቼ መሰጠት ይጀምራል ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡት ምላሽ፣ እሳቸው ትክክለኛ ቀኑን እንደማያውቁት አስረድተዋል።

አክለውም፣ " መቼ ቀን እንደሚጀመር እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ በቅርብ ጊዜ ሊጀምር እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ "  ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል። የነሀሴ ወር 2016 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ሃምሌ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል። የነዳጅ ማደያዎችም ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ እንደታዘዙ አመልክተዋል። @tikvahethiopia
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የመስከረም ወር 2017 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ነሃሴ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ ፥ የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
2024/09/30 22:28:03
Back to Top
HTML Embed Code: