Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam " የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል። ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ…
#ATTENTION🚨

" የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ።

በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች " የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተና ቀርቷል " እያሉ ለተማሪዎች መናገራቸውን እና የጽሁፍ መልዕክት በቴሌግራም ላይ መለጠፋቸውን የተማሪ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እንዲህ ያለው ውሳኔ የሚተላለፈው ከማዕከል ከትምህርት ሚኒስቴር ሆኖ ሳለ ፥ ትምህርት ቤቶቹ ውሳኔውን ማን እንዳሳለፈ በይፋ ያሉት ነገር ሳይኖር በደፈናው " ቀርቷል " የሚል ነገር ብቻ ነው የነገሯቸው።

በኋላም እራሳቸው ት/ቤቶቹ ቀድሞ ያሰራጩትን ያልተረጋገጠ መረጃ በማጥፋት የኦላንይን ፈተናው እንዳልቀረ መልሰው ገልጸዋል።

ዛሬ እሁድ ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው በፍጹም እንዳልቀረ በድጋሜ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናውን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ እንደሚገኝም አሳውቋል።

" ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ " ሲልም ገልጿል።

ለተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ባስተላለፈው መልዕክት ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት እንደተማሪዎች የቀደመ ምርጫ መሰረት ይሰጣል ብሏል።

አስቀድመው በወረቀት የመረጡ ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ (ኦንላይን) የመረጡም በተመደቡበት የፈተና ጣቢያ ተገኝተው ፈተናውን እንዲወስዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ እንደተያያዘው አይነት ከሃሰተኛ ወሬ ራሳቸውን በመከላከል ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ለማንኛውም መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ብቻ እንዲከታተሉም አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia
#NationalExam
#MoE

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NationalExam

የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል።

ተፈታኞች ከትናንት ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ናቸው።

ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ይሰጣል።

በትግራይ ክልል ፈተናው ከሐምሌ 2 እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

በትግራይ በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተፈታኞች ናቸው ፈተናቸውን የሚወስዱት።

ትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮውን ብሔራዊ ፈተና በወረቀት እንዲሁም የተመረጡ ተማሪዎች ደግሞ በኦንላይን እንደሚወስዱት አሳውቋል።

ዘንድሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተናው ይቀመጣሉ።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ፈተና ይዘጋጅላቸዋል።

@tikvahethiopia
#Africa

" በኮንፌዴሬሽን ለመዋሃድ ተስማምተናል " - በመንፈንቅለ መንግስት የመጡት የሶስት ሀገራት መሪዎች

ቡርኪናፋሶ ፣ ኒጀር እንዲሁም ማሊ በኮንፌደሬሽ ለመዋሃድ ተስማሙ።

በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት የቡርኪናፋሶ ፣ ኒጀር እና ማሊ ወታደራዊ ሁንታዎች በኮንፌደረሽን ለመዋሃድ ማስማማታቸው ተሰምቷል።

ከምዕራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ ጥምረት (ECOWAS) ፍቺ መፈጸማቸውንም ገልጸዋል።

የ3ቱም ሃገራት ወታደራዊ ሁንታዎች ስልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክቡ ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በተለይ ደግሞ ECOWAS ብርቱ ውትወታ እና ማዕቀብ ሲደረግባቸው ነበረ።

ጥምረቱ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንደሚያደርግ ከገለጸ በኋላም ከሶስቱም ሃገራት ብርቱ ትችት ሲደርስበት ቆይቷል።

ሀገራቱ ECOWASን የቀድሞ ቅኝ ገዢያቸው " የፈረንሳይ ጉዳይ ፈጻሚ " በማለት ክፉኛ ሲወቅሱት ነበረ።

ይህንንም ተከትሎ ከፈረንሳይ ጋር የነበራቸውን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነትን በማቋረጥ ወደ ሩስያ አማትረዋል።

አሁን ደግሞ የስስቱም ሃገራት መሪዎች በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ ባካሄዱት ስብሰባ " የሳሕል ሃገራት ኮንፌደሬሽን መንግስት " በሚል ለመዋሃድ መስማማታቸውን እና መፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሀገራቱ በድምሩ 72 ሚሊዮን ህዝብ ያላቸው ሲሆን 3ቱም በታጣቂ ቡድኖች በሚፈጠር አለመረጋጋት እየተፈተኑ ይገኛሉ።

አሁኑን ስምምነት ተከትሎ በጸጥታ ጉዳዮች አብረው እንደሚሰሩ የኢኮኖሚ ትስስራቸውንም እንደሚያጠናክሩ ይጠበቃል።

ECOWAS በዛሬው ዕለት ስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን ይህ የኮንፌደሬሽን ምስረታ ጉዳይ ዋና የመዋያያ አጀንዳው እንደሚሆን  ተዘግቧል።

መረጃው የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፣ የዶቼቨለ ሬድዮ እና አናዱሉ ነው።

@tikvahethiopia
#ፎቶ

አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲዮም ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ በኋላ እጅግ ከፍተኛ የተመልካች ቁጥር ተገኝቶበታል የተባለለትን የእግር ኳስ ፍልሚያ ዛሬ አስተናገደ።

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ " #የኢትዮጵያ_ዋንጫ " የፍጻሜ ፍልሚያ ተደርጓል።

በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ፥ ወላይታ ዲቻን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።

የአዲስ አበባ ስታዲዮምም ከጫፍ እስከ ጫፍ በእግር ኳስ ተመልካች ተሞልቶ ነበር።

ስታዲዮሙ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ በዚህ ልክ እጅግ የበዛ ተመልካች አላስተናገደም ተብሏል።

ላለፉት ዓመታት እድሳት ሲደረግለትም ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤ ከእድሳቱ በኃላ ለህዝብ ክፍት ተደረጎ በተካሄደው በዛሬው የፍጻሜ ጨዋታ በደጋፊዎች የተወሰኑ ወንበሮች የተነቃቀሉ ሲሆን የተጠባባቂ ተጫዋጮች ወንበሮችም ላይም ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

ከቀናት በፊት ጨዋታውን አስመልክቶ በተዘጋጀ የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ፥ " ስታዲየም ውስጥ ያሉ ንብረቶች የህዝብ ሀብትና የመንግስት ንብረት ናቸው ፤ ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል ስሜታዊነት ባይጎላ " ሲሉ የአደራ መልዕክት አስተላልፈው ነበር።

More : @tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz • “ የውሃ አቅርቦት ተቋርጦ ችግር ላይ ወድቀናል ” - ነዋሪዎች • “ የመብራት ችግር ነው ” - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ • “ የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው ” - የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት  በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማን ጨምሮ ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ…
#BenishangulGumuz

° “ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ 3 ወር ሆነው። ጨለማ ውስጥ እየኖርን ነው” - የወምበራ ወረዳ ነዋሪዎች

° “ ከወረዳው መንግስት ጋር እየተየጋገርን ነው፤ በቅርቡ እንሰራዋለን ” - የደብረ ዘይት ማዕከል

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ወምበራ ወረዳ ደብረ ዘይት ከተማ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ ጨለማ ውስጥ ለመኖር መገደዳቸውን ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

“ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ 3 ወር ሆነው። ጨለማ ውስጥ እየኖርን ነው። የፋሲካ በዓል አካባቢ ሁለት ቀን በርቷል ከዚያ በኋላ ምንም የለም ” ብለዋል።

ችግሩ ፦
-  በኑሯቸው ላይ ፈተና እንደሆነባቸው፣
- ተማሪዎች ለመማር፣ ፕሮጀክቶችን ለመስራት እንደተቸገሩ፣ 
- ለስልክ ቻርጅ በጀኔሬተር 20 ብር እንደሚከፍሉ፣ 
- በመስሪያ ቤታቸው ጀነሬተር፣ በቤታቸው Solar Energy ስላላቸው ባለስልጣናቱ ለጉዳዩ ቸልተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

“ ግብር እየከፈልን መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ አለመጠቀም ግን አግባብነት የሌለው ቅሬታን የሚያስነሳ ጉዳይ ነው ” ብለዋል።

በወረዳው የታላቁ ህዳሴ ግድቡ በቅርበት ቢገኝም ተጠቃሚ ባለመሆናቸው የሚመለከተው አካል ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

አቶ የኔሰው የኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ዘይት ማዕከል ኃላፊ አገልግሎቱ ለምን እንደተቋረጠ ጠይቀናቸው በሰጡት ምላሽ፣ ቡለን ላይ ኤሌክትሪክ ስለተቋረጠ መሆኑን አስረድተዋል።

"እንደ ወንበራ ደብረ ዘይት ቅድሚያ የቡለን ማዕከል ራሱን የቻለ አለ። እሱ ከበራ በኋላ ነው እኛ ማብራት የምንችለው። ቡለን ከበራ ይበራል" ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ "ከወረዳው መንግስት ጋር እየተየጋገርን ነው፤ በቅርቡ እንሰራዋለን" የሚል ምላሽ ተሰጥተዋል።

የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ከበደ ሰሞኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ "የተቋረጠው ኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው" ብለው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ “ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው። ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት፤ ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው እየመጡ የሚሰሩት። ይህ ችግር ግን የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ፤ ያንን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት። ” - ዶክተር በሀሩ በዛብህ (የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር የቦርድ አባል - ለቲክቫህ…
#EMA

“ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው፤ ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት ” - የኢትዮጵያ ህምክምና ማህበር

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር (EMA) በየዓመቱ ሰኔ 25 ቀን የሚከበረውን “ 7ኛውን የሀኪሞች ቀን ” በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተከብሮ ነበር።

በዚህም በዘንድሮው ' የሀኪሞች ቀን ' ከጌራ የቤት ለቤት ህክምናና የሀኪሞች ቢሮ ተቋም ጋር በመሆን 2,000 ለሚጠጉ የማህበረሰብ ክፍሎች የቤት ለቤትና የጎዳና ላይ ነጻ የህክምና ለመስጠት ማቀዱን አመላክቷል።

ይኸው የነጻ ህክምና ከሐምሌ 1 /2016 ጀምሮ ነው የሚሰጠው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ፣ ከ34 ዓመታት ጀምሮ በአጥንት ቀዶ ህክምና እያገለገሉ የሚገኙትን የማኀበሩ የቦርድ አባልና የአባላት ጉዳይ የሚከታተሉት ዶ/ር በሀሩ በዛብህን ጠይቋል።

እሳቸው በሰጡት ቃል፣ “ ሀኪሞች ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው፤ ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት። ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው መጥተው የሚሰሩት ” ብለዋል።

“ ይህ ችግር የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ” ያሉት ዶ/ር በሀሩ፣ “ ያን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ መብራት ኃይል ለአባላቱ መብራት፣ ቴሌ ለአባላቱ የአየር ሰዓት፣ ውሃና ፍሳሽ ለአባላቱ ውሃ ይሰጣሉ። የእኛ ጤና ሲታወክ እንኳ ምንም አይሰጥም። በህግም የተቀመጠ ነገር የለም ” ሲሉ አማረዋል።

“ የሥራ ሁኔታዎች ራሱ አልተመቻቹም ፤ ከሌላ አገር ጋር ሲገጻጸር እየሰራን የሚከፈለን እራሱ ውስን ነው ” ብለዋል።

“ መሬት እንኳን ቢሰጠን ምን ችግር አለው ? መኖር ነው ያቃተን። የሚከፈለን ገንዘብ በጣም ውስን ነው ” ሲሉ አክለዋል።

በዘርፉ የበዙ ችግሮች ከመኖራቸው አንጻር በርካታ ሀኪሞች ከአገር ለመውጣት እየተገደዱ መሆኑን ገልጸው፣  መንግስት ልቦና ሰጥቶት ለሚስተዋሉ ችግሮች ሁሉ መፍትሄ እንዲሰጥ በማኀበሩ ስም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር / EMA ከተመሠረተ 75 ዓመታትን እንዳስቆጠረ፣ በኢትዮጵያ ከ15,000 እስከ 20,000 ሀኪሞች እንዳሉ ተመላክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2024/09/30 04:22:20
Back to Top
HTML Embed Code: