Telegram Web Link
#Kenya

የኬንያው ፕሬዝዳንት ተቃውሞ በተደራጀባቸው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርበው ከወጣቶች ጋር ተወያዩ።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ያዘጋጁትን የፋይናንስ ሕግ ውድቅ እንዲያደርጉ ያስገደዳቸው የወጣቶች ተቃውሞ የተደራጀበት ማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ለውይይት መቅረባቸው ታሪካዊ ነው ተብሏል።

ሩቶ ትላንትና ከሰዓት በ ' X ' ስፔስ ላይ ቀርበው ከህዝብ ለሚነሳው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

' X ' ላይ ከተቃዋሚ ወጣቶቹ ጋር ለጥያቄ እና መልስ መቅረባቸው ፍጹም ያልተጠበቀ እንደነበር ተነግሯል።

ፕሬዝዳንቱ በውይይቱ ቀጥተኛ እና መሸፋፈን ያልታየባቸው ጠንካራ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ነበር።

መጀመሪያ ውይይቱ በጽህፈት ቤታቸው ይፋዊ ገጽ አስተናጋጅነት ሊካሄድ ነበር በኋላ ባገጠመ እክል ከፕሬዝዳንቱ ተቃዋሚዎች አንዱ በሆነ ኦሳማ ኦቴሮ በተባለ ግለሰብ ገጽ ገብተው ነው ምላሽ የሰጡት።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ያለ ከልካይ የፈለጉትን ሲጠይቁ፣ ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩ መሃል ላይ እየገቡ ሲመላለሱና ማብራሪያ ሲጠይቁ ነበር።

ተቃዋሚዎቹ ምን አሏቸው ?

መንግስታቸው እስካሁን ያስመዘገበውን ነገርና ባህሪያቸውን በተመለከተ አንስተው አብጠልጥለዋቸዋል።

በርካታ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በፖሊስ በጭካኔ መገደላቸውን አመልክተው " በሽብርተኛ አገር ውስጥ ነው እንዴ ያለነው? " በማለት ጠይቀዋቸዋል።

የመረጣችሁ ሰው በመሆኑ ቅድሚያ ለሰው ግድ ሊሰጣችሁ ይገባል ብለዋቸዋል።

ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ ሥራ አጥ የሆነ አንድ የውይይቱ ተሳታፊ " በካቢኔዎት ውስጥ ብቃት የሌላቸው በርካታ ባለሥልጣናት አሉ " ብሏቸዋል።

➡️ ሙሰኛ እና የተቀመጡበት ቦታ የማይገባቸው በርካታ ሰዎች በመንግስት ውስጥ እንዳሉ ነግረዋቸዋል።

የተገደሉ ወይም የተጎዱትን ሰዎች ቤተሰቦች ለማነጋገር ሞክረዋል ወይ? ሲሉም ጠይቀዋል።

አንዳንዶች ውሸታም እና ሐዘኔታ የሌላቸው በሚል ከሰዋቸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ምን መለሱ ?

● በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ባለሥልጣናትን በሙሉ ለማባረር ቃል ገብተዋል።

● " እውነት ነው ፤ አንዳንድ ባለሥልጣኖቻችን አስጸያፊ ድርጊቶችን እንደሚያሳዩ እስማማለሁ ፤ እራሳቸውን እንዴት እንደሚያስተካክሉ እኔም ጉዳዩን በግሌ አንስቼላቸዋለሁ። ከዚህ የበለጠም አደርጋለሁ " ብለዋል።

● በተቃውሞው የተገደሉ ሰዎችን አሃዝ በማጋነን አንዳንዶችን " ግድየለሽ " ሲሉ ከሰው ቁጥሩ 25 መሆኑን ተናግረዋል።

● በጥይት የተገደለ የ12 ዓመት ህፃን እናት ማነጋገራቸውን ገልጸዋል።

● በተቃዋሚዎች ላይ ሲተኩስ በካሜራ እይታ ውስጥ የገባ የፖሊስ አባል ክስ እንዲመሰረትበት እንዳዘዙ ተናግረዋል።

NB. የኬንያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ እንደሆነ አሳውቋል።

● ሩቶ አምባገነን እንዳልሆኑ ተናግረዋል። " እኔ ፕሬዝዳንት ነኝ ትክክል !! ግን ፕሬዜዳንቱ ፍጹም ስልጣን የለውም ለዛም ነው ዴሞክራሲያዊ ሀገር የሆነው ቼክ ኤንድ ባላንስ አለ። ፕሬዝዳንቱ አምባገነን አይደለም " ብለዋል።

● ረቂቅ ሕጉን ማንሳታቸውን በማረጋገጥ ፣ ሕጉን በተመለከተ ግን የተሳሳተ ግንዛቤ መፈጠሩን ጠቅሰዋል። የሕጉ ዓላማ የኬንያውያንን ንግድ ማጠናከረ ነበር በማለተ የተካተቱትን ዕቅዶች ጠቃሚነት አብራርተዋል።

ታሪካዊ ነው በተባለውና ምንም አይነት ቁጥጥር ባልነበረው የ ' X ' ህዝባዊ ግልጽ ውይይት መድረክ ላይ ከ150,000 በላይ ሰዎች ታድመው ነበር። 

ከዚህ በፊት አንድ ፕሬዝዳንት ይህን ያህል በይፋ ወጥቶ እራሱን በማጋለጥ ከሕዝቡ በቀጥታ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠበት ጊዜ ባለመኖሩ ምክንያት ነው ታሪካዊ የተባለው።

ፕሬዝዳንት ሩቶ ሁልጊዜ በሚያስቆጡ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮችን በሚመለከት ክርክር ውስጥ ሲሳተፉ ይታያል።

በፖለቲካ ሕይወታቸው ፈታኝ ጥያቄዎችን እና ሁኔታዎችን ከመጋፈጥ ወደ ኋላ ሲሉም ታይተው አይታወቅም።

በመገናኛ ብዙኃን ዘንድ ከቀደምት ፕሬዝዳንቶች በበለጠ በራቸው ክፍት መሆኑ ይነገራል።


#BBCNEWS
#Kenyans
#CitizenTV

@tikvahEthiopia
#እንድታውቁት  #አዲስአበባ

ነገ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች ይኖራሉ።

ስለሆነም ነገ ለስራ፣ ለቤተሰብ ለጓደኛ ጥየቃ ለሌላም ጉዳዮች ፕሮግራም የያዛችሁ ፕሮግራማችሁን ከልሱ።

መንገድ የሚዘጋው " ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም " በሚል የጎዳና ላይ ሩጫ ስለሚካሄድ ነው።

ሩጫው መነሻውን መስቀል አደባባይ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ከዛም በባምቢስ፣ ዑራኤል አደባባይ ወደ ቀኝ፣ ፒኮክ መናፈሻ ፣ ሰላም መንገድ ፣ በወሎ ሰፈር ፣ ደንበል ፣ ፍላሚንጎ በማድረግ መስቀል አደባባይ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

በዚህም  ፦
- ከ22 ወደ ዘሪሁን ህንፃ
- ከዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ
- ከአትላስ መብራት ወደ ዑራኤል አደባባይ
- ከቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ወደ ወሎ ሠፈር
- ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ
- ከኤግዚብሽን ወደ ፊላሚንጎ
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቴሌ ማቋረጫ (ክቡ) ባንክ ወደ ስታድየም
- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከካዛንቺስ ሼል (ኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል) ወደ ባምቢስ
- ከዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:30 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ከዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በተጠቀሱ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#ArbaMinch

በኢትዮጵያ ግዙፍ ነው የተባለለት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ተመረቀ።

ሆስፒታሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተመረቀው።

ስለ ሆስፒታሉ ፦

- የሆስፒታሉ ግንባታ የተጀመረው በመጋቢት 29 /2007 ዓ/ም ነው።

- ለግንባታ 1.4 ቢሊዮን ብር ወጪ ወጥቶበታል።

- 25 ሺህ ካሬ ላይ ነው ያረፈው።

- አሁን ላይ እጅግ ዘመናዊ የተባሉ የሕክምና መስጫና የምርምራ ቴክኖሎጂዎች አሉት።

- 600 ደረጃቸውን የጠበቁ አልጋዎች አሉት።

- የሄሊኮፕተር አምቡላንስ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ አለው።

- የውስጥ ደዌ ፣ የቀዶ ጥገና ፣ የሕጻናትና እናቶች ፣ የማህጸን ጽንስ ፣ ከአንገት በላይ፣ የአጥንትና የስነ አእምሮ ... ሌሎችም ህክምናዎች ይሰጡበታል።

- ኦክሲጅን የሚመረትበት ክፍል / ኦክሲጅኑም በየክፍሉ የሚያዳርስ መስመር ፣ የዲጅታል ኤክስሬይ ማሽን ፣ ሲቲ ስካን ፣ ኤም አር አይ ፣ ዘመናዊ አልትራ ሳውንድ ማሽኖች አሉት።

- በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 100 ስፔሻሊስት ሐኪሞች እና ከ2 ሺህ በላይ ሰራተኞች አገልግሎት ይሰጡበታል።

- ከ7 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የአካባቢውና የአጎራባች ክልሎች፣ ዞኖች ነዋሪዎች በአጠቃላይና በስፔሻሊቲ ደረጃ አገልግሎት ይሰጣል።

#SouthEthiopiaRegion
#ArbaMinch

Photo Credit - PM Dr. Abiy Ahmed

@tikvahethiopia
#ስፖርት #ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ።

ቡድኑ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ፍጻሜውን እስካገኘበት የሊጉ የመጨረሻ መርሃግብር ድረስ ከመቻል የእግር ኳስ ቡድን ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ ነው ሻምፒዮን የሆነው።

ዛሬ በተካሄደ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ መድህንን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

በዓመቱ 64 ነጥብ በመሰብሰብም ከመቻል በ1 ነጥብ በልጦ አጠናቋል።

መቻል በዓመቱ የፍጻሜ መርሃግብር ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ተፋልሞ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም በ1 ነጥብ ተበልጦ ዋንጫውን ተነጥቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በመጣበት አመት በታሪኩ የመጀመሪያው የሆነውን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ማሳካት ችሏል።

ቲክቫህ ስፖርት👇
https://www.tg-me.com/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport    
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia “... የፌደራል ፓሊስ በፓትሮል መንገድ ላይ ወጥቶ እንዲሰራ ሁሉ ተደርጓል ” - ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር የድንበር ተሻጋሪ የከባድ መኪና #አሽከርካሪዎች አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በታጠቁ ኃይሎች እስከ ግድያ የሚድረስ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው መግለጻቸውን በተደጋጋሚ መረጃ ተለዋውጠን ነበር። አሽከርካሪዎቹ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እየሰጠ እንዳልሆነ…
“ ባለፉት 10 ቀናት 5 አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ” - ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር

የአሽከርካሪዎች ግድያ፣ የተሳፋሪዎች እገታ፣ የህግ አግባብ የሌለው የ‘ኮቴ’ ክፍያ እንዳልቆመ ጣና የከባድ መኪና የአሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

“ በቅርቡ በአማራ ክልል ፤ ማክሰኝት አካባቢ አንድ ሹፌር ተገድሏል። ከዚያ በፊትም እዚያው ሌላ አሽከርካሪ ተገድሏል ” ሲል አመልክቷል።

ጥቃቱ በተለያዩ ክልሎች ሲፈጸም እንደሚስተዋል ጠቁሞ፣ “ በኦሮሚያ ክልል ‘55’ ተብሎ የሚጠራው አካባቢም አንድ አሽከርካሪ ተገድሏል ” ነው ያለው።

ከግድያው በተጨማሪ እገታም እንዳልቆመ ያስረዳው ማኀበሩ፣ “ በአጠቃላይ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል 3 አሽከርካሪዎች ተገድለው፤ በታታ የነበሩ ተሳፋሪዎች ታፍነው መወሰዳቸው መረጃ ደርሶናል (ጫንጮ ወጣ ብሎ) ” ብሏል።

ማኀበሩ፣ ከዚህ ቀደምም ጥቃቱ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲፈጸም እንደተስተዋለ አስታውሶ፣ “ ቅርብ ቀንም እነዚህ (ከላይ የተዘረዘሩት) ጥቃቶች ተፈጽመዋል ” ሲል አስረድቷል።

“ የአሁኑ ጥቃት የቅርብ ጊዜ ጥቃት ነው። ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ 5 አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ” ያለው ማኀበሩ፣ ባለፉት ዓመታት ከ120 የሚበልጡ አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች እንደተገደሉ አስታውቋል።

በተያያዘም፣ የ ‘ኮቴ’ እየተባለ የሚጠየቀው ከህግ አግባብ ውጪ የሆነ ከ2,000 ብር በላይ ክፍያ ኦሮሚያ ክልል ላይ አሁንም እንዳልቆመ፣ ከክልሉ ሳይወጡ ራሱ እስከ 5 ጊዜ ለመክፈል እንደሚገደዱ ሹፌሮች ተናግረዋል።

ማኀበሩ በበኩሉ፣ ይሄው ቅሬታ ትክክል መሆኑን አረጋግጦ፣ “ ከጂቡቲ ለሚጫን እቃ የ ‘ኮቴ’ የሚለው ቃል ራሱ ከአፍ ሊወጣ አይገባም ነበር” ሲል ወቅሷል።

በመንገድ ላይ ስለሚፈጸም የታጣቂዎች ጥቃት ምን እየሰራ እንደሆነ ከዚህ ቀደም የጠየቅነው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር፣ “ ከሚኒስቴር መ/ቤታችንም ሌላም አካል ዳይሬክሽን ተሰጥቶ፣ እንዲያውም ፌደራል ፓሊስ በፓትሮል መንገድ ላይ ወጥቶ እንዲሰራ ሁሉ ተደርጓል ” ማለቱ ይታወሳል።

የ‘ኮቴ’ ክፍያውን ቅሬታ በተመለከተም ችግሩ መኖሩን አምኖ፣ “ ከኦሮሚያ ክልል መንግስትም ጋር አውርተን መፍትሄ የምንሰጥ ይሆናል ” ነበር ያለው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#KUWAIT

ኩዌት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተገኘባቸውን ሰራተኞች " በህገወጥ መንገድ ያገኙትን ገንዘብ ሁሉ መመለስ አለባቸው " አለች።

" በሕግ ፊት አቆማቸዋለሁ " ብላለች።

ኩዌት፣ ከዚህ ቀደም ባደረገችው ሲቪል ሰራተኞች ያቀረቡትን የትምህርት ሰነድ የማጣራት ስራ የበርካታ ሰራተኞች መረጃ ሀሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

ይህን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ሰራተኞች በህገወጥ መንገድ ያገኙትን የመንግስት ገንዘብ ሙሉ በሙሉ እንዲመልሱ ለማዘዝ ማቀዱን የኩዌት ጋዜጣ ዘግቧል።

በዚህም ሀሰተኛ ዲግሪ ፣ ማስተርስ ፣ ዶክትሬት ሆነ ሀሰተኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሰነድ ያለው ሰራተኛ ስራውን ሙሉ በሙሉ መልቀቅና በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃው በማታለል ከተቀጠረበት ጊዜ ጀምሮ ያገኘውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መመለስ ይጠበቅበታል ተብሏል።

እነዚህ ሰዎች ገንዘቡን መመለስ ብቻ ሳይሆን ወደ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ ተደርጎ በሕግ እንደሚጠየቁ ተነግሯል።

Via @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የሩዋንዳ እቅድ (ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ መላክ) ገና ከጅምሩ ሞቶ የተቀበረ ነው " - አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር

ከሰሞኑን ዩናይትድ ኪንግደም (UK) አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር አግኝታለች።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኪር ስታርመር ናቸው።

ፓርቲው የሪሹ ሱናክን የወግ አጥባቂ (ኮንሰርቫቲቭ) ፓርቲ በከፍተኛ ብልጫ ነው ዘርሮ ያሸነፈው።

በከፍተኛ ብልጫ የተሸነፉት ሱናክ ፥ " የሕዝቡን ቁጣ ሰምቻለሁ። ለዚህ ሥራ ያለኝን ነገር ሁሉ ሰጥቻለሁ። ይሁን እንጂ የዩናይትድ ኪንግደም (UK) መንግሥት መለወጥ እንዳለበት ግልጽ የሆነ መልዕክታችሁን አስተላልፋችኋል፤ የሚተካኝም ሲገኝ ከፓርቲ መሪነት እለቃለሁ " ብለዋል።

በሌላ በኩል የምርጫ ውጤቱን ተከትሎ ስልጣን የተረከቡት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ዛሬ የመጀመሪያ መግለጫቸውን ሰጥተዋል።

በዚህም ፥ በጥገኝነት ጠያቂዎች / ስደተኞች ጉዳይ የቀድሞው የወግ አጥባቂ መንግሥትን ፖሊሲ እንደማያስቀጥሉ በይፋ አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " የሩዋንዳ እቅድ (ጥገኝነት ጠያቂዎችን /ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ) ገና ከጅምሩ ሞቶ የተቀበረ ነው " ብለዋል።

መንግስታቸው ፥ የቀድሞው አገዛዝ በህገወጥ መንገድ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም የገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎች / ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የጀመረውን ስራ እንደማይቀጥሉበት ተናግረዋል።

" ከሩዋንዳ ጋር የተደረሰው ስምምነት አይቀጥልም ውድቅም ይሆናል " ያሉት ጠ/ሚ ስታርመር  በዚህ የስደተኞች ጉዳይ ላይ የቀድሞው መንግስት ፖሊስ አይቀጥልም ብለዋል።

#UK
#Rwandascheme

@tikvahethiopia
2024/09/30 10:23:47
Back to Top
HTML Embed Code: