TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ እና መጠነ ሰፊ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል። ውሳኔው የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በየዕለቱ ከሚመለከቱት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ተጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በላይ አመልካቾች የሚቀርቡ ከሆነ ጥያቄያቸውን ሳይመለከቱ በቀጥታ ከአገር እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን…
#Update
የአሜሪካ ፕረዚደንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ሲባል የሀገሪቱን ፍልሰተኞች ሕግ አጥብቀዋል።
ይህ የጆ ባይደን ውሳኔ ባለሥልጣናት በሜክሲኮ በኩል ድንበር አቋርጠው የገቡ ስደተኞችን / ጥገኝነት ጠያቂዎችን በቀጥታ በኃይል ወይም በግዳጅ እንዲመልሷቸው ሥልጣን የሚሰጥ ነው።
ጉዳያቸው የሚመዘገቡ ሰዎች ዕለታዊ ኮታ ከተሟላ የተቀሩት ከአሜሪካ በኃይል እንዲወጡ ይደረጋሉ።
ከዚህ ባለፈ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የውጪ ዜጋ ወደ አገር እንዳይገባ " #እንዲታገድ " የሚል ትዕዛዝ ፕሬዜዳንቱ አስተላልፈዋል።
#ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪቃውያን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ እንደሚሻገሩ ይታወቃል።
አሜሪካ የፍልሰተኞችን ፍሰት ለመግታት በሚል ከሜክሲኮ የሚያዋስናትን ድንበር ከማጠር ጀምሮ በርካታ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።
ይህ የአሁኑ የፕሬዜዳንት ባይደን ውሳኔ ስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄያቸው ለሚመለከተው የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ቀርቦ ሳይታይ #በቀጥታ እንዲባረሩ የሚያደርግ ነው ተብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፤ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ግን ሕጉ የስደተኞችን መሰረታዊ መብት ይጥሳል ሲል ተቃውሟል።
መረጃው የጀርመን ዜና አገልግሎት፣ የዶቼ ቨለ እና ቢቢሲ ነው።
@tikvahethiopia

#StateofEmergency #EHRC
" በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (#ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ጋር በተያያዘ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ።
በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “#ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ተፈጻሚነት አብቅቷል።
ይህንን ተከትሎ በእስር የቆዩ ሰዎችን የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥል ኢሰመኮ አሳስቧል።
ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።
ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን ጋዜጣዊ መግለጫ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የክትትልና የምርመራ ሪፖርቶች ይፋ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ አስታውሷል።
በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውቅጥ #በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎችም ማኅበረሰባዊ #አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።
#EHRC #Ethiopia #StateofEmergency

#እንድታውቁት🚨
2 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈቶች አሟልተው ባለመገኘታቸው ምክንያት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቢያ ተላለፈ።
1ኛ. #Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g) , (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56
2ኛ. #Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127
የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶች ያላሟሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስስር ሚኒስቴር አሳስቧል።

Photo
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን #በአዲስ_አበባ ደረጃ ለ7 ቀናት አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደትን ትላንት አጠናቋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም ፥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ጥያቄ እያቀረበ ፤ ማብራሪያም እየጠየቀ ይገኛል።
በብዛት ከሚነሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ ፥ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የተመረጡ 25 ተወካዮች እውነት የወከሏቸውን የአዲስ አበባ ማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎት እና ሀሳብ የማንጸባረቅ ብቃቱ አላቸው ወይ ? የሚል ነው።
እንዲህ ላሉት ጥያቄ አዘል ትችቶች የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ይላል ?
ዶ/ር ዮናስ አዳዬ (ኮሚሽነር) ፦
“ ትችቶቹን #እናከብራቸዋለን። ተችዎቹ በራሳቸው አመለካከት ልክ ናቸው።
እኛ ግን በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ ብለን ያቀድነው 3,500 ሰዎችን ነው በአጠቃላይ።
25 ተመረጡ የተባሉት #አጀንዳውን_የሚያቀርቡልን እንጂ ተመርጠው ወደ #National_dialogue የሚሄዱ አይደሉም።
➡️ አንደበተ ርቱዕ ናቸው ?
➡️ የህብረተሰቡን ጥያቄ ያንጸባርቃሉ ? ለሚለው ጥያቄ ህዝቡ ‘ በአንጻራዊነት እነዚህ #ይሻሉኛል ’ ብሎ ከመረጣቸው መቀበል ነው ” ሲሉ መልሰዋል።
ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-05

#ሞት_ተፈርዶበታል !
ከአባቱ ጋር በገባበት " #የጥቅም_ግጭት " መላው ቤተሰቦቹን በጥይት ገድሎ ሊጨርስ የነበረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተፈረደበት።
ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ ይባላል።
በጋርዱላ ዞን የሃይበና ቀበሌ ነዋሪ ነው።
ግለሰቡ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሠገን ገነት ቀበሌ በመሄድ በ4 ቤተሰቦቹ ላይ የጥይት እሩምታ ይከፍታል።
በዚህም ሶስቱን ሲገድል አንዱን አቁስሏል።
በጥይት እሩምታ የገደላቸው ፦
- #አባቱ
- #እናቱ
- #አጎቱ ሲሆኑ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት የ9 አመት ታናሽ ወንድሙ ነው።
ግለሰቡ ይህን ፈጽሞ ከአካባቢዉ ቢሰወርም የጸጥታ ኃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር ተባብሮ ባደረገዉ ክትትል ከ5 ወራት በኋላ ሊያዝ ችሏል።
ፖሊስም ስራውን አጠናቆ ለፍርድ ቤት አቅርቧል።
ተከሳሹም ፤ ከወላጅ #አባቱ ጋር በገባበት ' የጥቅም ግጭት ' ምክኒያት ወንጀሉን እንደፈጸመ ለፍርድ ቤቱ አምኖ ቃሉን ሰጥቷል።
ይህም ቃሉም ከቀረበበት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ጋር ተዳምሮ የፍርድ ሂደቱን ቀላል እንዳደረገዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።
በዚህም በኃላ ጉዳዩን ሲመረምር የነበረዉ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ #በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።
በተከሳሹ ላይ የተጣለው #የሞት_ፍርድ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው።
#TikvahEthiopiaFamilyHW

#Update #EOTC " የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ ፤ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " - ቅዱስነታቸው ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ። የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ…
#EOTC
የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፦
➡ በቤተ ክርስቲያኗ
➡ በሀገራዊ እንዲሁም በወቅታዊ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ለተከታታይ ቀናት ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ነገ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ ተነግሯል።
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን
#ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፦
➡ በቤተ ክርስቲያኗ
➡ በሀገራዊ እንዲሁም በወቅታዊ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ለተከታታይ ቀናት ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ነገ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ ተነግሯል።
#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን
#ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፦ ➡ በቤተ ክርስቲያኗ ➡ በሀገራዊ እንዲሁም በወቅታዊ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ለተከታታይ ቀናት ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ነገ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ ተነግሯል። #የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን #ኢትዮጵያ…
#ኢትዮጵያ
ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና የግብረ ሰዶማዊነትን #ኃጢአት በተመለከተ አጀንዳ አድርጎ መወያየቱ ተሰምቷል።
በዚህም፥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያኗን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ #ዓለም_አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር የሆነ መግለጫ እንዲሰጥ ወስኗል።
#EOTCTV

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የ4 አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት #እንዲሰረዝ መወሰኑን አሳውቋል።
ሠርተፍኬታቸው የተሰረዘው ፦
1ኛ. ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ➡ ነብይ ኢዮብ ጭሮ
2ኛ. ገዥዋ ዓለም አቀፍ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ➡ መጋቢ ካሳ ኪራጋ
3ኛ. የሰማይቱ ጽዮን ማኅበርተኞች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ➡ መጋቢ ሚስጥሩ መዝገቡ
4ኛ. የእግዚአብሔር መንግስት እውነት ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ ➡ መጋቢ ቢንያም ሽታዬ ... ናቸው።
ውሳኔው የተለለፈባቸው በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ምክንያት ነው።
ካውንስሉ እነዚህ አካላት የተሰጣቸውን የሕግ ከለላ በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮና ጤናማ ሥነ ምግባር ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበሩ ገልጿል።
ከዚህ ተግባራቸው ይመለሱ ዘንድም አስፈላጊውን ትምህርትና ምክር ሲሰጥ ቆይቷል።
ይሁን እንጂ ምክሩ ተቀበለው ሕዝብን ከሚያሳስት ተግባራቸው #ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ሠርተፍኬታቸው እንዲሰረዝ ወስኗል።
(ካንውስሉ ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና የግብረ ሰዶማዊነትን #ኃጢአት በተመለከተ አጀንዳ አድርጎ መወያየቱ ተሰምቷል። በዚህም፥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያኗን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ #ዓለም_አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር የሆነ መግለጫ እንዲሰጥ ወስኗል። #EOTCTV @tikvahethiopia
#Update
የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ተሰጥቷል።
በዚሁ መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ " በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ በመሆኑ በእጅጉ እናዝናለን " ብሏል።
ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በአጽንኦት ጥሪ አቅርቧል።
በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶስ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አካሄድ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳለው ገልጿል።
" ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት አዋጅ መረዳት እንደሚቻለው ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ ሁኔታ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክርና በውይይት ለመፍታት የተቋቋመ መሆኑን ተረድተናል " ብሏል።
ይሁን እንጅ " ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅር አሰኝቶናል " ብሏል።
በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አሳውቋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ውሳኔ አሳለፈ ?
➡️ በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗና በመንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ሰይሟል።
➡️ ቅዱስ ሲኖዶስ የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁም #ከመጽደቁ_በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡
➡️ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ #የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገልጿል። ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ወስኗል።
➡️ #ከሀገር_ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ ፦
- በሙያ ብቃታቸው፣
- በምግባራቸው
- በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት #በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ወስኗል፡፡
ሙሉ መግለጫ ፦ https://www.tg-me.com/tikvahethiopia/88105
@tikvahethiopia
➡️ በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗና በመንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ሰይሟል።
➡️ ቅዱስ ሲኖዶስ የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁም #ከመጽደቁ_በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡
➡️ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠሩ አለመግባባቶች የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች አስመልክቶ እየተላለፉ ያሉ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ መልእክቶችን ቅዱስ ሲኖዶስ #የማይቀበላቸውና በጥብቅ የሚቃወማቸው መሆኑን እየገልጿል። ወደፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ወስኗል።
➡️ #ከሀገር_ውጭ ባሉ አህጉረ ሰብከት መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚላኩ አገልጋዮች በክፍሉ ሊቀጳጳስ ሲጠየቅ ፦
- በሙያ ብቃታቸው፣
- በምግባራቸው
- በመንፈሳዊነታቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮች ከሁሉም አህጉረ ስብከት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቅራቢነት #በውድድር እየተለዩ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲላኩ ወስኗል፡፡
ሙሉ መግለጫ ፦ https://www.tg-me.com/tikvahethiopia/88105
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና የግብረ ሰዶማዊነትን #ኃጢአት በተመለከተ አጀንዳ አድርጎ መወያየቱ ተሰምቷል። በዚህም፥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያኗን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ #ዓለም_አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር የሆነ መግለጫ እንዲሰጥ ወስኗል። #EOTCTV @tikvahethiopia
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ወሰነ ?
ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ፦
➡️ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣
➡️ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ #የተከለከለ፣
➡️ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣
➡️ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣
➡️ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ #እንደሚያወግዝ ገልጿል።
#የተመሳሳይ_ጾታ_ጋብቻ እና #የግብረ_ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።