Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፎቶ ⬆️ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ደረጃ እያካሄደው የሚገኘውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት 3ኛ ቀን መርሀ ግብር ዛሬ አከናውኗል።

ዛሬ በከተማ ደረጃ " #ታዋቂ#ተጽዕኖ_ፈጣሪ " ናቸው የተባሉ ግለሰቦች ተገኝተው በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ስለ ሂደቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል ተብሏል።

በተመሳሳይ በተለየ ቦታ ላይ ከ112 ወረዳዎች ከ11 የህብረተሰብ የተወጣጡ ተሳታፊዎች በየማኅበረሰብ ክፍላቸውን አጀንዳዎችን የለዩ  ሲሆን የሚወክሏቸውን 121 ተሳታፊዎች መርጠዋል።

ነገ ጠቅላይ የሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶችና ዛሬ የተመረጡ 121 ተሳታፊዎች ፤ መግለጫ የተሰጣቸው ተባባሪ አካላት በድምሩ ከ3 ሺ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ሀገራዊ የመክፈቻ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray #TPLF

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የዛሬውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን አወደሱ።

አቶ ጌታቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር በትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው ብለውታል።

ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ " ህወሓት / TPLF / ዳግም እውቅና ሊያስገኝለት የሚያስችለውን መንገድ የሚጠርግ ነው።

@tikvahethiopia
#Adama

ተከሳሽ ቶሎሳ ወይም ፍቅሩ አሸናፊ ይባላል።

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።

ተከሳሹ እናቱን በስለት (ቢላዋ) በአሰቃቂ ሁኔታ ወግቶ ነው ህይወታቸውን እንዲያጡ ያደረገው።

ተከሳሹ ድርጊቱን የፈጸመው #በቁማር_የተበላዉን ገንዘብ እናቱ ያላቸውን ንብረት በመሸጥ እንዲተኩለት ለማድረግ ሲል እየደበደበ ያሰቃያቸው እንደነበር ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ አረጋግጧል።

በዚህ ብቻ ያላበቃው ተከሳሽ ሚያዚያ 21/ 2016 ዓ/ም ጠዋት በአሰቃቂ ሁኔታ የእናቱ ህይወት እንዲያልፍ በማድረጉ ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

ጉዳዩን የተመለከተው የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

በተከሳሹ ላይ የተጣለው #የሞት_ፍርድ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#WKU

" አንድ ተመራቂ ተማሪ እና አንድ  መምህር ጉዳት ካስተናገዱ በኋላ ሁኔታዉ በቁጥጥር ስር ውሏል " - የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አመራር

ከሰሞኑ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንድ ሽጉጥ የታጠቀ ወጣት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተኩስ በመክፈቱ አንዲት ተመራቂ ወጣት እና አንድ መምህር ተጎድተዋል።

የግቢዉ ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በወቅቱ የተፈጠረው የተኩስ ድምጽ እና ሁኔታ እጅግ ረብሿቸው ነበር።

ይሁንና " ታጥቆ ወደ ግቢው የገባው አካል በቁጥጥር ስር መዋሉና ሰላም መሆኑ " ተነግሯቸው ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ መደረጉን አስረድተዋል።

ሁኔታውን በተመለከተ አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የዩኒቨርሲቲው ኃላፊ " ጉዳዩ ድንገት በመፈጠሩ ለጥቂት ሰአታት ግርግር ቢፈጥርም በግቢዉ የጸጥታ ሀይል በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል " ብለዋል።

በወቅቱ " የመመረቂያ ጽሁፍን በዲስፕሊን ምክኒያት እንዳያቀርብ የተከለከለ የነርሲንግ ተማሪ  ሽጉጥ ታጥቆ በመምጣት ጉዳት አድርሷል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የመመረቂያ ወረቀቷን ታቀርብ የነበረዉንና ጓደኛዬ የሚላትን ' እኔ ካላቀረብኩ አንችም አታቀርቢም ' በማለት ሽጉጥ ተኩሶ በማቁሰል በዛ የነበሩትን መምህራን አባሯል " ሲሉ አስረድቷል።

ከዚህ በኋላ ሰዎችን ባይጎዳም ደጋግሞ መተኮሱ በግቢው ውስጥ ችግር መፍጠሩን የሚገልጹት ሀላፊዉ ይህም ተማሪዎችን መረበሹን ገልጸዋል።

በዚህ ወቅት የተሰማዉን የተኩስ ድምጽ የሰማዉ የግቢዉ የጸጥታ ሀይል ወጣቱን በፍጥነት በመቆጣጠር ሁለቱን ተጎጅዎች ወደህክምና ሊወስዳቸዉ እንደቻለና ገልጸዋል።

በወቅቱ ከተከሰተዉ ችግር ለመሸሽ መምህራኑ ባደረጉት ጥረት አንዱ በመስኮት ሲዘል ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰበትና የሁለት እግሮቹ አጥንቶች ተሰብረዉ ከፍተኛ የአጥንት ህክምና በማስፈለጉ የግቢዉ ማህበረሰብ ገንዘብ እያወጣለት መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማወቅ ችሏል።

አንድ ጉዳዩን የምታውቅ ተማሪ ፤ " 1 ወር ከ15 ቀን ልጅ በፊት ደብድቧት ሆስፒታል ገብታ ፤  እሱም 2 ዓመት ተቀጥቶ ነበር። ከዛም በፊት መትቷት ያቃል። ባለፈው ደግሞ ዲፌንስ አቀርባለው ብሎ ሲከለከል ሽጉጥ ይዞ መተኮስ ጀመረ ልጅቷን ተኩሶ ስቷቷል ፤ ከዛ ይዞ ደብድቧታል። ጭንቅላቷ ተፈንክቷል። አንድ መምህርም ከፎቅ ዘሎ ተሰብሯል። አንድ ተማሪም ወድቃ ጭንቅላቷ ውስጥ ደም ፈሶ ሰርጀሪ ተሰርቶላታል " ብላለች።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ አልተከፈለንም " - የዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ባለሙያዎች " መሠረታዊ ችግሩ የበጀት ችግር ነው፤ የካሽ እጥረት ነው ያለው " - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ6 ጤና ጣቢያዎች የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው፣ እንዲከፈላቸው ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ጤና ባለሙያዎቹ በሰጡት ቃል፣…
#Update

“ ክፍያው ሁሉንም የጤና ባለሙያ ያላማከለ ነው ” - የዲላ ዙሪያ ጤና ባለሙያዎች

“ በወቅቱ ሥራ ያላደሩ ልጆች ናቸው ያልተከፈላቸው ” - የጌዴኦ ዞን ጤና መምሪያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች የ18 ወራት የዱቲ ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ቅሬታ አቅርበው የነበረ ሲሆን ፣ አሁን ደግሞ ክፍያው ቢጀመርም ሁሉንም ባለሙያዎች ያላማከለ መሆኑን ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ ክፍያው ሁሉንም የጤና ባለሙያ ያላማከለ ነው” ብለው፣ ክፍያውም የ5 ወራት ብቻ ከመሆኑም ባሻገር ለአንድ ጤና ጣቢያ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

ባሉ መረጃዎች ከ5 ወራቱ ለጤና ባለሙያዎቹ የ1 ወር ብቻ ፣ ለኃላፊዎች ለጪጩ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎቾ ግን የ5 ወራት እንደተከፈላቸው አስረድተዋል።

“ መንግስት #ብሩን_በጅቶ ወጪ እስካደረገው ድረስ ለሁሉም ጤና ባለሙያዎች መብቱን በማስከበር ያቆሙበት ወራት ገንዘብ ሳይቀር ፦
- ለኡዶ፣
- ለስሶታ 
- ለወቸማ
- ለቱምትቻ ጤና ጣቢያዎች ገንዘቡ ይከፈል” ሲሉ ጠይቀዋል።

ለምን ለሁሉም አልተከፈለም ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የጌድኦ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊው አቶ አንዱዓለም ማሞ ፥ “ በወቅቱ ሥራ ያላደሩ ልጆች ናቸው ያልተከፈላቸው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ከ6ቱ ጤና ጣቢያዎች ባለሙያዎች የጪጩ ጤና ጣቢያ ሲያድሩ ነበር። የሌሎቹ ጋ ደግሞ ኃላፊዎች ሲያድሩ ነበር። ስለዚህ የእነርሱ #ባለማደራቸው በዛ ሴኬጁል ውስጥ አልገቡም ፤ እንጂ ሆን ተብሎ አይደለም” ነው ያሉት።

“ የበጀት ችግር ነበር በጋራ ሰርተን የተወሰነ ገንዘብ እንዲከፈላቸው ተደርጓል” ብለው፣ አሁን የተከፈለው ሙሉ የ2015 ዓ/ም የ5 ወራት እንደሆነ፣ የሰሩበት ቀሪው ወራትም በቀጣይ እንደሚከፈል አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ስፖርት : ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻሚዮንስ ሊግ ፍጻሜ ቦሪስያ ዶርትመንድን በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ።

ቡድኑ እጅግ ጠንካራ ነው የሚባለውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን በተደጋጋሚ አሸንፏል።

ቡድኑ በታሪኩ ይህን ዋንጫ ሲያሸንፍ 15ኛ ጊዜ ነው።

ይህ የእግር ኳስ ፍልሚያ በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይ በወጣቶች ዘንድ እንዲሁም በመላው ዓለም በርካታ ሚሊኒዮን ተመልካች ያለው ሲሆን ምርጥ የሚባሉት የአውሮፓ ክለቦች የሚሳተፉበት ነው።

Via @tikvahethsport

@tikvahethiopia
#DStv

✈️ አውሮፓ እንሂድ

⚽️በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአውሮፓ ዋንጫ ሊጀመር ነው! በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

🏆የምትወዱዋቸውን የአውሮፓ ታላላቆችን ዋንጫ ፍልሚያ በወር 350 ብር!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024 #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
“ እናቴን አድኑልኝ፣ የልቧ ሁለቱ ቱቦዎች በመጥበባቸው ደም እየመለሱ ነው ” - ልጅ

የእናቱ ሁለት የልብ ቱቦዎች ጠበው ወደ ሰውነት አካል ክፍላቸው መተላለፍ ያለበት ደም ወደ ኋላ እየተመለሰ በመሆኑ በአስቸኳይ መታከም እንዳለባቸው ሀኪም ማዘዙን የታማሚዋ ልጅ ገልጿል።

የታማሚ ወ/ሮ ትዕግስት ነብሮ ልጅ ናትናኤል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ እናቴን አድኑልኝ፣ የልቧ ሁለቱ ቱቦዎች በመጥበባቸው ደም እየመለሱ ነው ” ይላል።

“ እኔ የአምስተኛ ዓመት አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪ ነኝ። እናቴን ለማሳከም 760,000 ብር ተጠይቀናል። የተገኘው 192,000 ብር ብቻ ነው ” ብሏል።

“ ልቧ ሲመታ ስለሚያማት እናቴ አሁን ምንም አይነት እንቅስቃሴ አታደርግም ” ያለው ተማሪ ናትናኤል፣ “ ኬዙ ቆየት ብሏል፤ ከአንድ ወር በፊት ግን በጣም አሟት ለ17 ቀናት ሆስፒታል ተኝታ ነበር ” ሲል ሁነቱን አስረድተዋል።

ለህክምና 760,000 ብር እንደሚያስፈልግ ከሆስፒታል የተጻፈ ማስረጃ ደብዳቤ አለ ? ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ፣ “ አዎ አለ ” ብሎ የላከ ሲሆን፣ ደብዳቤውም ከላይ ተያይዟል።

ተማሪ ናትናኤል ባስተላለፈው መልዕክት፣ “ከአቅም በላይ ስለሆነ ነው እንጂ እርዳታ አልጠቅም ነበር። ግን ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር አቅም ጠፍቶ ነውና እርዳታ አድርጉልኝ” ሲል ተማጽኗል።

መርዳት ለምትፈልጉ 1000298948935 የNatnael Demelash አካውንት ቁጥር ነው። እንዲሁም 1000032440324 የTigst Nebro አካውንት መጠቀም ይቻላል።

መደወል ለምትፈልጉ 0993655876 ናትናኤል ደመላሽን ማግኘት ይቻላል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2024/09/27 21:26:16
Back to Top
HTML Embed Code: