Telegram Web Link
#GondarUniversity

ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ #በተለያየ_ጊዜ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ #አንጋፋ የሚባሉ ምሁራን ፤ መምህራንን ፣ ሰራተኞችን ፣ ተመራቂ ተማሪ እና የዩኒቨርሲቲው ታላቅ #ባለውለታ የሆኑ አባትን በሞት ተነጥቋል።

አንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እነማንን #በሞት ተነጠቀ ?

🕯አባሆይ አሰፋ ዘለቀ🕯

የመሬት ርስታቸውን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያ ካበረከቱት 59 አርሷደሮች መካከል አንዱ ነበሩ። በ1963 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲው የተማሪው ቁጥር መጨመር እና የሚሰጠውም የትምህርት ዓይነት እየሰፋ በመምጣቱ ግቢውን ወደ ማራኪ አካባቢ ማስፋፋት ሲፈልግ አባሆይ አሰፋ ዘለቀ ከሌሎች ልበቀናዎች ጋር በመሆን በማራኪ ከፍተኛ ቦታ አካባቢ የነበራቸውን የመሬት ይዞታ ለማስፋፊያ እንዲሆን በመፍቀድ ትውልድ እንዲቀረጽበት በማድረግ ዘመን ማይሸረው አበርክቶ አድርገዋል፡፡ በ94 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

🕯ፕሮፌሰር ሞገስ ጥሩነህ🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ መምህር ፣ ተመራማሪ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልጋይ ነበሩ።

🕯ዶ/ር ሰለሞን ይርዳው🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ ባልደረባ ነበሩ። ከ1988 ዓ/ም ጀምሮ በህክምናው ሙያ በመተማ ሆስፒታል አገልግለዋል። ከ1992/93 ዓ.ም ጀምሮ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ውስጥ በረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሙያቸው አገልግለዋል። በማስተማርም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። በጤና እክል ህይወታቸው አልፏል።

🕯መምህር ደመቀ ደሱ 🕯

አንጋፋ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህር ነበሩ። በጡረታ እስከተገለሉበት ድረስ ለ40 ዓመታት ገደማ  በማስተማር ሙያ እንዲሁም በትምህርት ክፍል እና በዲን ኃላፊነት አገልግለዋል።

🕯አቶ ፍስሃ ሞሴ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም Nutrition & Dietetics Department ውስጥ የChief laboratory Technical Assistant ባለሙያ ነበሩ። ቤተሰብ ለመጠየቅ በሄዱበት በደንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ተቀጥፏል።

🕯አቶ አታለል ምስጋናዉ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በፊዚዮሎጂ ት/ክፍል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ መምህርና በአሁኑ ሰዓት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ ነበሩ። በ31 ዓመታቸው በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

🕯ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ🕯

የኪነህንፃ / #Architecture / ተመራቂ ተማሪ ነበር። የትንሳዔ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር ባሄደበት ከፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ከሚመረቁት ተማሪዎች መካከል ነበር።

🕯አቶ ሙሉአለም ይትባረክ🕯

በህክምናና በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተማሪዎች አገልግሎት ውስጥ የተማሪዎች ምኝታ ቤት አስተባባሪ ነበሩ። በህመም ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ አጠቃላይ 8 አንጋፋ ምሁራን ፣ መምህራን ፣ ሰራተኞች ፣ ተማሪ እንዲሁም የተቋሙን ባለውለታ ታላቅ አባት በሞት ተነጥቋል።

የጤና እክል ፣ ድንገተኛ አደጋ ፣ የመኪና አደጋ የህልፈተ ህይወት መንስኤዎቹ እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዩኒቨርሲቲው ካገኘው መረጃ ተረድቷል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
" እጆቼን ማዘዝ ችዬ እኔን ለማገዝ የሚደክሙትን ሁሉ ከድካማቸዉ ባሳርፋቸዉ  ደስ ይለኝ ነበር " - ጠንካራው የይቅርታ ሰዉ ዳግማዊ አሰፋ (ዳጊ)

የህግ ባለሞያና ደራሲ ዳግማዊ አሰፋ ከዓመታት በፊት በሀዋሳ ከተማ በእሱ እና በጓደኛው እጅ ላይ ከነበረ የፍትህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ " ጉቦ አንቀበልም !! " በማለቱ በአንድ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መጎዳቱ ይታወሳል።

በዚህ አደጋ ጠንካራ የወጣት እጆቹ አልታዘዝልህ ብለዉታል። በአከርካሪዉ ዙሪያ ያሉ ነርቮች መጎዳትም ቆሞ እንዳይሄድ እንቅፋት ሆነዉበታል።

በዚህ ምክኒያት በሰው እጅ መብላቱ መልበሱ እና መንቀሳቀሱ ፈተና ቢሆንበትም ዛሬም ተስፋው ከሱ አልፎ ለሰዎች ይደርሳል።

ያልተሰበረው መንፈሱ የተሰበሩትን ይጠግናል ፤ ያልወደቀው ምራሉም የወደቁትን ያነሳል።

በዚህ ትጋቱ ያልተገታዉ ዳግማዊ ከህመሙ ጋር እየታገለ ስቃዩን እየተሰቃዬም ቢሆን አርፎ መቀመጥን አልወደደም ሁለት መጽሀፍት ለተደራሲያን አብቅቶ ለብዙዎች ህይዎት መቃናት ምክኒያት ሆኗል።

በዚህ ዓመትም ሌላ መጽሀፍ ሊያስመርቅ እየሰራ ነው። የቀደሙ ሁለቱ መጽሀፍትም በአፋን ኦሮሞ ታትመዉ ለመዉጣት ጫፍ መድረሳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ከምንም በላይ ለሰዎች መትረፍ ሲችል የሰዎችን ድጋፍ ይፈልግ ዘንድ ብርቱ ክንዶቹ ዝለው ስራዎቹን መከወን ያቅታቸው ዘንድ ምክኒያት የሆነውን ሰው " ይቅር ብየሀለሁ " ማለቱ ለትንንሽ ጥፋት ይቅርታ ማድረግ ለከበዳቸዉ ሁሉ ታላቅ ትምህርት የሰጠ ሰው ነው።

ጠንካራው ዳግማዊ ከሁለት ዓመት በፊት ውጭ ወጥቶ መታከም ከቻለ መዳን እንደሚችል ሀኪሞች ማብሰራቸውን ተከትሎ በርካታ ወዳጆቹ ተደስተዉ ጎ ፈንድሚ ቢያቋቁሙም ወቅቱ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሀገራችን ችግር ላይ የነበረችበት ወቅት  በመሆኑ እንዳስቆመው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።

" አሁን ላይ  ' ጎፈንድሚውን እንጀምር  ዘንድ ፈቃድህን ብቻ ስጠን 'ላሉኝ ጓደኞቼ ፈቃዴን ሰጥቻለሁ "  ብሏል።

ድኖ ለብዙዎች መትረፍ ሲችል ' ሀገሬ ችግር ላይ ናት " ብሎ የዘገየዉ ዳግማዊ ምንም እንኳን ብዙ ችግሮቹን " ወዳጆቼን አላስጨንቅም " ብሎ ቢደብቅም በቶሎ መታከም እንዳለበት ግን አሁን ላይ ብዙ ምልክቶችን አሳይቷል።

ይህ ተከትሎም ሁሉም ደጋግ ኢትዮጵያውያን እገዛ እንዲያደርግለት ወዳጆቹ እየተረባረቡ ይገኛሉ።

ዳግማዊ ፥ " ' 2 ሺህ የፌስቡክ ጓደኞቻችን ሁለት ሁለት መቶ ሰው ይዘዉ የአንድ ማኪያቶ የሚሆን 57 ብር በማዉጣት ያሳክሙሀል ' ብሎ ወዳጄ መምህር ወሌ ሀሳቡን ጀምሮታል " ብሏል።

" ዳግማዊ ገንዘቡ ተሰብስቦልህ ታክመህ ስትድን በእጆችህ ቀድመህ ልትሰራ የምታስበዉ ምንድን ነው ? " በማለት የቲክቫህ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል ጥያቄ አቅርቧል።

ከረዥም ዝምታ በኋላ ፦

" አይገርምህም አስቤዉ አላዉቅም ... ግን እጆቼን ማዘዝ ችዬ እኔን ለማገዝ የሚደክሙትን ሁሉ ከድካማቸዉ ባሳርፋቸዉ  ደስ ይለኝ ነበር። "

ዳግማዊ አሰፋን ማገዝ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ ያላችሁ ደጋግ ኢትዮጵያዉያን ፦
በጎፈንድሚ 👉 https://gofund.me/d93d0840
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 👉1000310977938
በዳሽን ባንክ 👉 5016527877077
በአቢሲንያ ባንክ 👉 39796821 በኩል ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

ስልክ እንፈልጋለን ለምትሉም ፦ 0909888857 ላይ መደወል ትችላላችሁ።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ትላንትና ማክሰኞ #ከሀዋሳ ወደ #አዲስ_አበባ በመብረር ላይ እያለ የደኅንነት ችግር ሊያስከትል የሚችል ክስተት በገጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ቁጥር #ET154 ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጥልቅ የሆነ የደኅንነት ምርመራ ሊያደርግ እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ትላንት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን…
#Update

ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ።

ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም ደግሞ አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መስፍን ጣሰዉ  ፥ " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መቃጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ " ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር " ET154 " ሚያዝያ 29/2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን እና አውሮፕላኑ በሰላም ቦሌ ኤርፖርት ማረፉን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል።

የዚህ መረጃ ባለቤት ካፒታል ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
“ 20 እናቶች በደም እጦት ሕይወታቸው አልፏል ” - ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል

ከ60 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሕዝቦች የሚገለገሉበት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ባጋጠመው ከፍተኛ የደም እጥረት ሳቢያ በተለይ እናቶች ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን ሆስፒታሉ ገልጿል።

ላጋጠመው የደም እጥረት ምክንያቱ የደም ባንክ አለመኖር መሆኑን የገለጸው ሆስፒታሉ በዚህም ደም የሚሹ ታካሚዎች ለሕልፈተ ሕይወት እየተዳረጉ መሆኑን አስረድቷል።

የዩኒቨርሲቲው የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ኢያሱ ታደሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያና ለሌላ አንድ ሚዲያ በሰጡት ቃል ፣ “ በ6 ወራት ውስጥ በተከሰተው የደም እጦት ሳቢያ 20 እናቶች ሕይወታቸው አልፏል ” ብለዋል።

የደም ባንክ እንዲቋቋም ሆስፒታሉ ለጤና ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ደም ባንኩን ማቋቋም እንዳልተቻለ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ከደም እጥረቱ ባሻገር በሆስፒታሉ በርካታ የወባ ታካሚዎች በመኖራቸው መጨናነቅ እንደፈጠረ፣ ሆስፒታሉ የምርመራ ግብአቶችን ጨምሮ የኦክስጂን እጥረት እንደፈተነው ተመላክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቃቸው አንድ የጤና ሚኒስቴር ፒአር ባለሙያ ጉዳዩን ከሰሙ በኋላ፣ “ እኔ የፒአር ባለሙያ ነኝ የሚመለከተውን ነው እንጂ የማገናኝህ መልስ አልሰጥህም ” ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች የተቋሙ አካላት ለጊዜው ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#EARTHQUAKE

" ብዙዎቻችን በህይወት እንተርፋለን ብለን አልጠበቅንም ነበር " - አቶ ኦይታ ኡኖ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ፣ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ትናንት ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ36 ደቂቃ ላይ ነው የተከሰተው።

ክስተቱ በደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል " ወይጦ ድልድይ ፖሊስ ጣቢያ " አካባቢ መከሰቱን ጠቁሟል።

ኢንስቲትዩቱ ይህ መጠን (4.8) ዝቅተኛም ሆነ ከፍተኛ የሚባል እንዳልሆነና " መካከለኛ " የሚል ደረጃ የሚሰጠው እንደሆነ ገልጿል።

የሚያስከትለው ውድመት እና ጥፋት እንደ አካባቢው ቅርበት እንደሚወሰን ፤ ከተማ ውስጥ ቢፈጠር ብዙ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል አስረድቷል።

" ወይጦ " የተባለው አካበቢ የሚገኝበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ ብራይሌ ታዳጊ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ኦይታ ኡኖ ትናንት ሌሊት የመሬት መንቀጥቀጥ ማጋጠሙን አረጋግጠዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በተከታታይ ሁለት ጊዜ መከሰቱን እና ክስተቱም አስደንጋጭ እንደነበር ገልጸዋል።

" ብዙዎቻችን በህይወት እንተርፋለን ብለን አልጠበቅንም ነበር " ብለዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ካሉት ስድስት ወረዳዎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር ውስጥ በስድስቱ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ አረጋግጧል።

እስካሁም መረጃ በተገኘባቸው መዋቅሮች ጉዳት አልተመዘገበም።

አሪ ዞንም የመሬት መንቀጥቀጡ መሰማቱን የዞኑ የመንግስት አሳውቋል።

ጂንካን ጨምሮ በአራት ወረዳዎች እና 2 የከተማ መስተዳድሮች ክስተቱ ማጋጠሙን አረጋግጧል።

በሁሉም መዋቅሮች የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ጠቁሟል።

ባለፈው ሳምንት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን በወረዳ ሁሉም መዋቅሮች 3 ሬክተር ስኬል የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሞ ነበር።

የትናንትናው የመሬት መንቀጥቀጥም እስከ ዳውሮ ድረስ መሰማቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
#HibretBank

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም ቅሬታ ወደ 995 የጥሪ ማእከላችን በመደወል ፣ በኢሜል [email protected] በመላክ ወይም በዋናው መ/ቤት 3ኛ ፎቅ በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡ አዳዲስ መረጃ እንዲርሶ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጫኑ፡፡
ቴሌግራም- https://www.tg-me.com/HibretBanket
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር

ዘመናዊ እና ጥራት ያላቸውን እቃዎች ከብዙ አማራጮች ጋር ከዮናታን ቢቲ ያገኛሉ !

የውበት፣ የጥራት እና የምቾት ዳር ድንበር
ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር !

አድራሻችን ፦
1. ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር (ከኢቲዮ ሴራሚክ ዝቅ ብሎ)
+251957868686
2. ከዊንጌት አደባባይ አለፍ ብሎ ከአቢሲኒያ ባንክ ፊትለፊት +251995272727
3. ከሲኤምሲ አደባባይ ወደ ሀያት መንገድ መሪ ሳይደርስ (ዘመን ባንክ አጠገብ) +251993828282
#Amhara

➡️ “ በአጠቃላይ 7 ሰዎች ሞተዋል። በተለይ ሕፃናት ተርበዋል ” - ደባርቅ የሚገኙ የትግራይ ተፈናቃዮች 

➡️ “ በድርቁም ችግር አለ፤ ተፈናቃዮች ላይም ችግር አለ ” - የሰሜን ጎንደር ዞን

በ2013 ዓ/ም ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል ፤ በሰሜን ጎንደር ዞን ፤ ደባርቅ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች እርዳታ እየተደረገላቸው ባለመሆኑ የምግብ እጥረት እንደተጋረጠባቸው፣ በዚህም የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ገልጸዋል።

ተፈናቃዮቹ ሁኔታውን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል “ ኬንዳውን (መጠለያውን) አፈረሱብን። በየመስሪያ ቤቱ ብንገባም ተቀባይነት አጣን ” ብለዋል።

“ የትግራይ ተፈናቃዮች በየመስሪያ ቤቱ፣ በየመስጂዱ (በተለይ ሕፃናት፣ ሕሙማን፣ እናት አባት የሞቱባቸው) ናቸው ” ያሉ ሲሆን “ ባይሆን ለእነርሱ እንኳን እርዷቸው ብለን እንኳ ብንለምን ‘ ምንም የለም፤ ለእናንተ አይሰጥም ’ አሉን ” ሲሉ አማረዋል።

“ ሕዝቡ ግን ረሃብ ሞተ። በተለይ ሕፃናት ፣ መድኃኒት ተጠቃሚዎች። ከ2016 ዓ/ም መስከረም ወር ወዲህ 4 ሰዎች ሞተዋል። ከዚያ በፊት ደግሞ 3 ሰዎቸ ሞተዋል። በአጠቃላይ 7 ሰዎች ሞተዋል ” ነው ያሉት።

መጠለያውን ያፈረሱት ግንባታ ሊገነቡበት እንደሆነ ፣ የተፈናቃዮቹ ብዛት 403 አባውራ፣ በአጠቃላይ ደግሞ 1,244 መሆናቸውን፣ የተፈናቀሉት በ2013 ዓ/ም እንደሆነ ፣ የተፈናቀሉት ከመቐለ ፣ ከዓዲግራት ፣ ሽረና ሌሎች የተለያዩ ቦታዎች እንደሆነም አስረድተዋል።

“ እኛ እዚህ ተቀባይነትን ካጣን ሌላ ቦታ ተቀባይነት ካገኘን ዜግነታችንንም ቢሆን ቀይረን ፈርመን አብረን እንሄዳለን ተረካቢ ድርጅት ካገኘን ” እስከማለት የደረሱት እኚህ ተፈናቃዮች ይህን የወሰኑት የሚረዳቸው ስላጡ መሆኑን ገልጸዋል።

የእለት ደራሽ ምግብ እርዳታ እንዲሰጣቸውም አጥብቀው ጠይቀዋል።

በተፈናቃዮች በኩል ለቀረበው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቅናቸው አንድ የሰሜን ጎንደር ዞን ባለስልጣን፣ “ የክልሉ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ‘ከእኔ ውጪ መረጃ እንዳይሰጥ’ ብሎ በክልሉ መንግስት አሳውጇል። እኔማ እንዴት ብዬ ልስጥህ። ‘መረጃ በአንድ ማዕከል ይሁን’ ብለው አቅጣጫ ስለሰጡ ” ብለዋል።

እኝሁ አካል “ በድርቁም ችግር አለ። ተፈናቃዮች ላይም ችግር አለ። የሰላም ተመላሽ ላይም ችግር አለ። ይህን ለማለት ግን እቸገራለሁ። መረጃ ሰጥተናል ለክልሉ መንግስት ” ከማለት ውጪ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ተቆጥበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
° ለተናቃዮቹ ለምን እርዳታ አልተደገላቸውም ?
° መጠለያውስ ለምን ፈረሰ ? በማለት የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተቢበሪያ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌታን ጠይቋል።

ጉዳዩን #ከፍተኛ_የመንግስት_አካላት እንደያዙት እና እሳቸው ማብራሪያ መስጠት እንደማችሉ ከመግለጽ ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

#TikvahEthopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2024/09/27 11:17:48
Back to Top
HTML Embed Code: