Telegram Web Link
#ደመራ

ዛሬ ከሰዓታት በኃላ ለሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅቶች ወደመጠናቀቃቸው ነው።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትላንት በዓሉን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፈው ነበር።

በዚህም በዓሉ በድምቀት ፣ባማረና በሰመረ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ በንቃትና በሕብረት በመሆን ከጸጥታ አካላትና ቤተክርስቲያኒቱ ለዚሁ ዓላማ ካቋቋመቻቸው የኮሚቴ አባላት ጭምር በመተባበር እንዲሰራ አደራ ብለዋል።

የመንግሥት የጸጥታ ተቋማት በዓሉ ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር ተከብሮ መዋል እንዲችል ከጠቅላይ ቤተክህነት ዐቢይ ኮሚቴ ጋር በጥምረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በበዓሉ ወቅት ለሚደረግ ፍተሻ ፍፁም ክርስቲያናዊ ትብብር እንዲያደርግ አደራ ብለዋል።

የጸጥታ አስከባሪዎችም ጨዋነት በተሞላና ክብርን በሚገልጽ አግባብ የፍተሻ ሥርዓቱን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑ ከበዓላችን መንፈሳዊ ሥርዓት ውጪ የሆኑ መልዕክቶች፣ አለባበሶች እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱ መገለጫ ከሆኑ ዓርማዎች ውጭ መያዝ አይገባውም ብለዋል።

በዓሉ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ እንደመሆኑ መጠን ቤተክርስቲያኒቱን ከማይገልጹ ሆታዎችና ጭፈራዎች እንዲርቅ አሳስበዋል።

" የመስቀል ደመራ በሚከበርባቸው ቦታዎች ሁሉ ያልተፈቀዱ ነገሮችን ይዞ መገኘት ፍጹም መንፈሳዊ የሆነውን በዓላችንን የሚያደበዝዘው ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል " ብለዋል።

" ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ልጆቻችን ከሚያቀርቡት መንፈሳዊ ትርኢትና ዝማሬ ጎን ለጎን አካባቢያቸውን በመቆጣጠር በዓላችንን በሰላም እንዳናከብር የሚያደርጉ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ በጥንቃቄ መጠበቅ ይኖርባቸዋል " ብለዋል።

" ብፁዕነታቸው ከንጉሰ ነገስት አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ወዲህ ተደርጎ በማያውቅ ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሦስተኛ ጊዜ የመስቀል ደመራ በዓልን በድምቀት ማክበር የሚያስችል የስቴጅ፣ የድምጽ ማጉያና የክብር እንግዶች ማስተናገጃ ቦታዎችን በማዘጋጀት ተሳትፎ አድርጓል " ሲሉ ገልጸዋል።

ይህን ተሳትፎም አድንቀው የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በራሳቸውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

" በዓሉን ስናከብር ፍቅር ሰላምንና አንድነትን እንዲሁም መግባባትን መርሕ ባደረገ አግባብ መሆን አለበት " ያሉ ሲሆን " በዓሉ ሥጋዊ ፈቃዶቻችንን የምንፈጽምበት ሳይሆን ፦
- ንስሐ ያልገቡ ንስሐ የሚገቡበት
- የተጣሉ የሚታረቁበት
- የተለያዩ አንድ የሚሆኑበት
- የተራራቁ የሚቀራረቡበት
- ፍፁም የደስታና የሰላም በዓል ሆኖ እንዲከበር ማድረግ ይኖርብናል " ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደመራ ዛሬ ከሰዓታት በኃላ ለሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅቶች ወደመጠናቀቃቸው ነው። ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ትላንት በዓሉን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፈው ነበር። በዚህም በዓሉ በድምቀት ፣ባማረና በሰመረ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ በንቃትና በሕብረት…
#EOTC

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፦

" ... አንዳንድ ጊዜ በዓልን ምክንያት በማድረግ መጠጦች ይኖራሉ።

በዓል ለመጠጥ ምክንያት ሊሆን አይችልም።

በዓል ስንል መንፈሳዊ በዓላት ሁል ጊዜ ምክንያቶቻችን ፦
- ለፅድቅ ነው
- ለሰላም ነው
- የተጣላ የምናስታርቅበት ፣
- የራቀውን የምናቀርብበት፣
- የተቸገረውን የምንረዳበት
- ያላመነውን እምነት እንዲኖረው የምናስተምርበት ፣
- ከእግዚአብሔር የራቀውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቅበትን ንስሃ የሚገባበትን ስራ ለመስራት የሚያስፈልጉን ነገሮች የተዘረዘሩ እንጂ መጠጥ አይደለም።

መጠጥ ክፉ ምኞትን ያመጣል፣ የጉልበት ስሜትን ያመጣል፣ መጠጥ ስካርን ያስከትላል፤ ከዚያ በኃላ የሚሰሩትንም የሚናገሩትንም አለማወቅ ይመጣል።

አንዳንድ ጊዜ በምንሰማው በመንፈሳዊ በዓላቶቻችን መንፈሳዊ ተብለው ሲከበሩ በመጠጥ ኃይል አላስፈላጊ ግጭቶች ተፈጥረው የብዙ ንጹሃን ህይወት ደም የሚፈስበት ጊዜ ይኖራል ፤ ይህ በየትኛውም ቦታ ነው ፤ ስለዚህ ይሄ ጥቅም ስለሌለው ጥቅማችን እኛ በዓሉን በማክበር ካላስፈላጊ ክፉ ምኞት ሳይሆን በጎ ምኞት ፦
° ያልቆረበ ለመቁረብ ፣
° ያልሰገደ ለመስገድ፣
° ከእግዚአብሔር የራቀ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ፣
° ሰላምን ያጣ ሰላምን ለማግኘት ፣
° የተጣላ ለመታረቅ ፣
° ያጣ ሰርቶ ጥሮ ግሮ እግዚአብሔር ስራውን ባርኮለት እራሱን ችሎ ከድህነት ተላቆ የሚኖርበትን እግዚአብሔርን የሚማፀንበት ስራ መስራት እስከተቻለ ድረስ ሁሉ ነገር ውጤታማ ያደርገናል። "

#EOTC

@tikvahethiopia
የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል መቼ ይከበራል ?

የዘንድሮ ኢሬቻ መስከረም 25 እና 26 ቀን 2017 ዓ/ም ይከበራል።

የአባገዳዎች ህብረት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም መግለጫ ፥ መስከረም 25 ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በማግስቱ መስከረም 26 ኢሬቻ ሆረ አርሰዴ እንደሚከበር ገልጿል።

#ኢሬቻ2017

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ማስታወሻ : መንገዶቹ ተዘግተዋል።

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ጋር በተያያዘ ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩት መንገዶች ከዚህ ሰዓት አንስቶ ተዘግተዋል።

ከቤት ለስራም ይሁን ለሌላ ጉዳይ የወጣችሁ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ይገኛል።

ከላይ በፎቶው የተያያዘው የማኅበረ ቅዱሳን እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ወደ መስቀል አደባባይ ጉዞ ሲያደርጉ የሚያሳይ ነው።

Photo Credit - TMC

@tikvahethiopia
2024/09/27 11:21:42
Back to Top
HTML Embed Code: