Telegram Web Link
በአዲስ አበባ ለብዙሃን ትራንስፖርት ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ መስመሮች ይፋ ሆኑ።

ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ከመጪው እሑድ ጀምሮ በተመረጡ መስመሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

መስመሮቹም ከቦሌ- ፒያሳ፣ ከቦሌ- ሜክሲኮ፣ ከቦሌ- አራት ኪሎ፣ ከቦሌ- አውቶቢስ ተራ፣ ከቦሌ- ሽሮሜዳ፣ ከጀሞ- ፒያሳ እና ከጀሞ- ሜክሲኮ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ከፒያሳ- ቦሌ፣ ከሜክሲኮ- ቦሌ፣ ከአራት ኪሎ- ቦሌ፣ ከአውቶቡስ ተራ- ቦሌ፣ ከሽሮ ሜዳ- ቦሌ፣ ከፒያሳ ጀሞ እና ከሜክሲኮ - ጀሞ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ መሰጠት እንደሚጀምር ተመላክቷል፡፡

ቢሮው " የአገልግሎቱ መጀመር የመንገድ መዘጋጋቱን ለመቀነስ እና ብዙ የሰው ቁጥር ያለው ተጓዥ በአንድ ጊዜ ማመላለስ ያስችላል " ብሏል።

በዚህም ተማሪና መምህራን ብሎም ሌሎች ተገልጋዮች በሰዓታቸው ወደ ሚፈልጉት ቦታ በመንቀሳቀስ አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛል ተብሏል፡፡

" በከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው የተነቃቃ እንዲሆን ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል " ሲልም አክሏል።

ዜጎች የሚያጋጥሟቸውንና የሚስተዋሉ ችግሮችን በአቅራቢያ ለሚገኙ የትራንስፖርት ቁጥጥር ሰራተኞች ወይም በ9417 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ተጠይቋል፡፡

@tikvahethiopia
" ወደ ፖለቲካ ፈጽሞ መመለስ አልፈልግም ! " - የእናት ፓርቲው አቶ ዳዊት ብርሃኑ

የእናት ፓርቲ አባል፣ አመራርና የሕዝብ ግንኙነት ሆነው ያገለገሉት አቶ ዳዊት ብርሃኑ ከዛሬ (መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ/ም) ጀምሮ በፈቃዳቸው ሥራ መልቀቃቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" በተለይም ፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን መጋቢት 30 ቀን 2015  ዓ/ም ባከናወነበት ወቅት በጠቅላላ ጉባኤው በሕዝብ ግንኙነት ከተመረጥኩ በኋላ የተሰጠኝን ኃላፊነት በአግባቡ ስወጣ ቆይቻለሁ " ብለዋል።

" በትብብር ፓርቲዎችም ዘንድ ባለኝ የፀሐፊነት ሚና የበኩሌን ድርሻ ስወጣ ነበር " ነው ያሉት።

" ምንም እንኳ ፓርቲው ከተመሠረተ ያስቆጠረው እድሜ አጭር ቢሆንም የቆየሁባቸው አራት አመታት በሀሳብ ልዕልና እና በሰለጠነ የሀሳብ ጉርብትና ብቻ ፖለቲካ መስራት የሚችሉ አባላትን ያፈራንበትም ወቅት ነበር " ሲሉም አክለዋል።

ከፓርቲው የለቀቁት በምን ምክንያት ነው? በሥራ? ባለመግባባት? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ በምላሻቸው፣ " ከፓርቲው የለቀቁት በግል ውሳኔ ነው " ብለዋል።

በተለይ የፓለቲካ ምህዳሩ እንደ ጠበበ በሚገለጽበት በአሁን ወቅት በፓርቲ ሥራ ውስጥ መቆዬት ተግዳሮቱ ምንድን ነው ? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ፣ " ከባድ ነው። የአገርና ሕዝብን አደራ መሸከም እጅግ በጣም ከባድ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ገዢው ብልጽግና ለሻከረ ግንኙነታቸው መፍትሄው ምንድነው ይላሉ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ምላቸው፣ " ሀቀኛ፣ ሁሉን አቀፍ፣ በአግባቡ የሚመራና ግልጽ የሆነ የፓለቲካ ድርድር ማድረግ " የሚል ነው።

የፓርቲ የሕዝብ ግንኙት አገልግሎትዎ ምን ይመስል ነበር? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ፣ " አስቸጋሪ፣ ፈታኝ እንዲሁም ከፊል ስኬታማ ነበር " ብለዋል።

ካሁን ወዲያ በሌላ ፓርቲ እንጠብቀዎት ወይስ በፓርቲ ሥራ እስከወዲያኛው እየወጡ ነው? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ "ወደ ፓለቲካ ፈጽሞ መመለስ አልፈልግም" ነው ያሉት።

እናት ፓርቲ ለወደፊት ምን ያስተካክል? ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ አቶ ዳዊት አጭር ምላሻቸው፣ "መሠረቱን" የሚል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🔥 ዘመናዊ የእጅ ስልክ ከ1 ዓመት የጥቅል ስጦታ ጋር!!

የጎግል መተግበሪያዎች የተጫኑባቸውን አዳዲሶቹን የ #ZTE_Nubia_Music ዘመናዊ የእጅ ስልኮች በተመጣጣኝ ዋጋ ሲገዙ

▶️ የ2 ጊ.ባ ወርኃዊ የዩትዩብ ጥቅል ለአንድ ዓመት እንዲሁም

🌐+📞 ለ3 ተከታታይ ወራት 3 ጊ.ባ የዳታና 200 ደቂቃ የድምጽ ጥቅል በስጦታ ያገኛሉ!

📍 በአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን እንዲሁም የአዲስ አበባ ደንበኞቻችን በቴሌገበያ ድረገጽ https://telegebeya.ethiotelecom.et/ መግዛት ትችላላችሁ!


#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#ONLF #SOMALIREGION

ከሰሞኑን ተቃዋሚው የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ' የሶማሌ ክልል የዜጎች መብት የሚጣስበት እየሆነ ነው " ሲል ከሷል።

ፓርቲው ክልሉ ሶማሌዎች ማንነታቸውን እንዲክዱ የሚገደዱበት እየሆነ ነው ብሏል።

የክልሉን ስያሜና ሰንደቀላማ የመቀየር እቅድ እንዳለ ከአሉባልታ ከፍ ያለ መረጃ አለን ሲሉም፣ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አብዲራህማን መሀዲ ተናግረዋል።

ባለፉት 6 አመታት በክልሉ የጎሳ ግጭቶች ጨምረዋል ሲሉም ወቀሳ አቅርበዋል።

የክልሉ ርዕሰመስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በበኩላቸው፣ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች " እኛ ሶማሌዎች እንጂ ሶማሊያውያን አይደለንም " ማለታቸው ማንነትን እንደመካድ ሊወሰድባቸው አይገባም ብለዋል።

በቀድሞው አስተዳደር ህግን ባልተከተለ መንገድ ተቀይሮ የነበረውን ስያሜና ሰንደቅ አላማ በመተው በህገመንግስቱ የተቀመጠውን ስያሜ መጠቀም የጀመረው የእርሳቸው አስተዳደር መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ሙስጠፋ የኦብነግ ሊቀመንበር የሚመሩት ቡድን ይህንን መግለጫ ያወጣው በክልሉ ችግር ስላለ ሳይሆን " ሰሞኑን በአፍሪካ ቀንድ እየተስተዋለ ያለውን ጂኦፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ ጥቅም በመፈለግ ነው " ሲሉ ተችተዋል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia
#Tigray

አዲሱ የትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው አነሱ።

በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ  ፊርማ መስከረም 8/ 2017  ዓ.ም የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የዞኑ የመንግስታዊ አገልግሎት ዘርፍና የልማታዊ ዘርፍ አግልግሎት ሃላፊዎች ከስራ ተነስተዋል።

ለሃላፊዎቹ ከዞኑ መንግስታዊ የስራ ሃላፊነት መነሳት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች አልፈፅምም ማለትና ማደናቀፍ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል።

ሁለቱ የዞን የስራ ሃላፊዎች ከመስከረም 8/2017 ዓ.ም ከነበራቸው የስራ ሃላፊነታቸው ተሰናብተው የተሰጣቸው የመንግስት ንብረትና ስራ እንዲያስረክቡ በተፃፉላቸው የስንብት ደብዳቤዎች ተገልፆላቸዋል።

አቶ ፀጋይ ገ/ተኽለ ገ/ክርስቶስ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመሩት ህወሓት በቅርቡ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው የተመረጡት ወ/ሮ ሊያ ካሳ ተክተው  የደቡብ ምስራቅ ዞን ዋና  አስተዳዳሪነት እንዲመሩ በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተሾሙ ናቸው። 

በተመሳሳይ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 6/2917 ዓ.ም " ከአባላትና ከድርጅታዊ ሃላፊነት አባርሪያቸዋለሁ " ብሎ ደብዳቤ የፃፈላቸው የህወሓት ማእካላዊ ኮሚቴ አባልና የትግራይ ማእከላይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰለሙን መዓሾ የአክሱም ከተማ የፀጥታ ሃላፊ ፣  የተምቤን ዓብዩ ዓዲ ከተማ ከንቲባና ሁለት የዞን የስራ ሃላፊዎች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ በማደናቀፍ በሚል ከሃላፊነታቸው ማንሳታቸው መዘገባችን ይታወሳል።  

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እስክንወያይ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ባለበት ይቀጥላል " - ትራንስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ " የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር " በሚል የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ከመጪው እሑድ ጀምሮ በተመረጡ መስመሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቆ ነበር።

መስመሮቹም ከቦሌ- ፒያሳ፣ ከቦሌ- ሜክሲኮ፣ ከቦሌ- አራት ኪሎ፣ ከቦሌ- አውቶቢስ ተራ፣ ከቦሌ- ሽሮሜዳ፣ ከጀሞ- ፒያሳ እና ከጀሞ- ሜክሲኮ እንደሆነ ተመላክቶ ነበር።

በተመሳሳይ  ከፒያሳ- ቦሌ፣ ከሜክሲኮ- ቦሌ፣ ከአራት ኪሎ- ቦሌ፣ ከአውቶቡስ ተራ- ቦሌ፣ ከሽሮ ሜዳ- ቦሌ፣ ከፒያሳ ጀሞ እና ከሜክሲኮ - ጀሞ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ መሰጠት እንደሚጀምር ተገልጾ ነበር።

ቢሮው " የአገልግሎቱ መጀመር የመንገድ መዘጋጋቱን ለመቀነስ እና ብዙ የሰው ቁጥር ያለው ተጓዥ በአንድ ጊዜ ማመላለስ ያስችላል " ነበር ያለው።

ይህን ውሳኔ ለሚዲያ ካሰራጨ በኃላ ሰዓታት ሳይቆይ ውሳኔውን በመሻር " ትራንስፖርት ባለበት ይቀጥላል " ብሏል።

ቢሮው " በቀጣይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እስክንወያይ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ባለበት የቀጥላል " ሲል ነው ያሳወቀው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እስክንወያይ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ባለበት ይቀጥላል " - ትራንስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ " የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር " በሚል የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ከመጪው እሑድ ጀምሮ በተመረጡ መስመሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቆ ነበር። መስመሮቹም ከቦሌ- ፒያሳ፣ ከቦሌ- ሜክሲኮ፣ ከቦሌ- አራት ኪሎ፣ ከቦሌ-…
የሚተላለፉ ውሳኔዎች ?

(አዲስ አበባ)

ከዚህ ቀደም " ጥዋት እና ማታ ያለውን መጨናነቅ ለማስቀረት " በሚል የኮድ 2 ተሸከርካሪዎች በፈረቃ እዲንቀሳቀሱ ሊደረግ መሆኑን ይህም ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር እንደሚገባ አንድ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ኃላፊ ለሚዲያ ይናገራሉ።

ጎዶሎና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 መኪናዎች በፈረቀ እንዲንቀሳቀሱ የህግ ማዕቀፍ ሁሉ መዘጋጀቱን ነበር የተናገሩት።

በራሱ በባለስልጣን መ/ቤቱ ውስጥ በኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉት እኚሁ ግለሰብ ይህን በተናገሩ በሰዓታት ውስጥ መ/ቤቱ በማህበራዊ ሚዲያ ይወጣና " ይሄ ወደፊት በጥናት የሚሆን እንጂ በቅርቡ ተግባራዊ የሚሆን አይደለም ፤ የእኔ አቋም አይደለም " የሚል ምላሽ ሰጥቶ ጉዳዩ በዛው አበቃ።

አሁን ደግሞ የትራንስፖርት ቢሮ " ትምህርት ቤት በመከፈቱ የትራንስፖርት መጨናነቅ እንዳይፈጠር ለብዙሃን ትራንስፖርት (ህዝብ ማመላለሻ) ብቻ የተመረጡ መንገዶች አሉ ከእሁድ ጀምሮም ተግባራዊ ይደርጋል " የሚል መግለጫ ለሚዲያ ያሰራጫል።

መስመሮቹ ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ያለባቸው ናቸው።

ሰዓታት ሳይቆይ ቢሮው " ከባለድርሻ አካላት ጋር እስክንወያይ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ባለበት ይቀጥላል " የሚል ውሳኔ በማሳለፍ የቀድሞውንና ለህዝብ የተሰራጨውን ውሳኔ ቀሪ አድርጎታል።

ቀድሞውንስ እንዴት እንዲህ ያለው እጅግ በርካታ የከተማውን የትራንስፖርት ተገልጋይ የሚመለከት ውሳኔ ያለ ውይይት ሊተላለፍ ቻለ ? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው።

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia
#MPESASafaricom

የሃገር ዉስጥ በረራ ጉዟችን በአዲስ አመት በ M-PESA ያምርበታል ፤ 5% ተመላሽ ሰጥቶን ያሰብንበት ከች እንላለን ፤ በM-PESA ጉዞ ፤ ተመላሽ ይዞ !

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

  #FurtherAheadTogether
#flyethiopia
Hey Mobile !

Tab A9 - 19,500 ETB
•Tab A8 - 29,500 ETB
•Tab A9+ 5G - 31,000 ETB
•Tab S6 Lite - 47,000 ETB
•Tab S9 FE - 59,000 ETB
•Tab S9 +5G - 99,000 ETB
•Tab S9 Ultra - 129,000 ETB

Contact us :
0936222222 @heymobile1
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
#AD

ፋና የወይባ ጡሽ የተመሰረተበትን  22ኛ አመት በአሉንና 4ኛ ቅርንጫፉ የመክፈቻ ስርአት አካሄደ።

በወ/ሮ ፋና ገ/መድህን ከ22 አመት በፊት የተመሰረተው ‘ ፋና የወይባ ጡሽ ’ በደንበኞቹ ዘንድ ያተረፈውን መልካም ስም እና ዝም በመጠበቅ ለአመታት መዝለቅ የቻለ ነው።

በአዲስ አበባ ሳር ቤት ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ገባ ብሎ ካለው የመጀመርያ ቅርንጫፍ በተጨማሪ ቦሌ ከዮድ አቢሲኒያ ፊት ለፊት ፣ በመቐለ ሐውልቲ ፕላኔት ሆቴል ፊት ለፊት እንዲሁም 4ኛ ቅርንጫፉን ሲኤምሲ መሪ አካባቢ ለደንበኞች በሚመች አማካይ ቦታዎች ቅርንጫፎችን በመክፈት አገልግሎቱን አስፋፍቷል።

ቅዳሜ መስከረም 11 ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሀገራዊ በሆነ ግብአት የ22 አመታት አገልግሎት የሰጠው 'ፋና የወይባ ጡሽ ፦
- የበርካቶች የማህፀንና የወገብ ጤና የተመለሰበት ፤
- የቆዳቸው ውበት የተጠበቀበት ፤
- በኑሮ ውጣ ውረድ የደከመ ሰውነታቸው  ዘና ያለበት መሆኑ በደንበኞች ተመስክሮለታል ተብሏል።

ወይባ ፤ ቦለቂያ ፤ ጡሽ እና የመሳሰለው አካባቢያዊ መጠሪያና ስያሜ ተሰጥቶት በተለያዩ የሃገራችን አከባቢዎች ጤናንና ውበትን ለመጠበቅና ለመንከባከብ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፉ በመጡ እና ረጅም ዘመን በዘለቁ ማኅበረሰባዊ እውቀቶች ተፈጥሯዊ የሆኑ እጽዋቶችን የመጠቀም
የቆየ ባህላዊ ሥርዐትና ወግ አላቸው።

ይህን የቆየ ሀገረሰባዊ እውቀት ወደ ከተማ በማምጣት ፣ በማስተዋወቅና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት 'ፋና የወይባ ጡሽ ' ላበረከተው አስተዋፅኦ '' የባህል ጥበባት ለማህበረሰብ ትስስርና ለሀገረ‐መንግስት ግንባታ " በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በተካሄደው ሀገር አቀፍ የባህል ፌስቲቫል፣ ኤግዚቢሽን እና የኪነ-ጥበብ ስነ-ጥበብ ፈጠራ ውድድር እና ትዕይንት ላይ በላቀ ደረጃ ሰኔ 2016 ተሸላሚ ሲሆን ሌሎች ሽልማቶችንም አግኝቷል።

በእለቱ የፋና ወይባ ጡሽ አጀማመርና  ስለአገልግሎት አሰጣጡ የተዘጋጀ መፅሄት ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
" ተለዋጭ መጓገድ ለመገንባት ጥረት እያደረግን ነው " - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ከአዲስ አበባ - ጅማ - መቱ - ጋምቤላ መስመር በቡኖ በደሌ ዞን ደዴሳ ወረዳ ከጅማ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለው መጓገድ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክጓያት መንገዱ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል።

ችግሩ ለመቅረፍ በኢትዮጵያ መንገዶ አስተዳደር የጅማ መጓገድ ጥገና ዲስትሪክት ጊዜያዊ ተለዋጭ መጓገድ ለመገንባት ጥረት እያደረገ እንደሆነ አመልክቷል።

በመኾኑም ተለዋጭ መጓገድ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተጠናቅቆ ለትራፊክ ክፍት እስኪደረግ ድረስ አሽከርካሪዎች በትዕግስት እንይጠባበቁ ጠይቋል።

ከመሃል ሃገር ለሚነሱ _ አሽከርካሪዎች የአዲስ አበባ - ነቀምት - በደሌ - መቱ - ጋምቤላ መሥመርን በአማራጭነት እጓዷጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#TigrayRegion

" የሚሰራጨው ወሬ መሬት ላይ የሌለ ነው " - የምስራቃዊ ዞን አስተዳደር

በትግራይ ዛላኣንበሳና ኢሮብ የኢትዮ-ኤርትራ ደንበር ከቆየው የተለየ እንቅስቃሴ እንደሌለ የምስራቃዊ ዞን አስተዳደር አሳውቋል።

አሁንም ላለፉት 4 ዓመታት አከባቢ በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ስምንት የሚደርሱ የጉሎመኻዳና የኢሮብ ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ላይ የታየ አዲስ ለውጥ እንደሌለ ተመላክቷል።

ከሰሞኑን አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች " በትግራዩ ዛላኣንበሳ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ከቆየው የተለየ እንቅስቃሴ አለ " ዘገባ ሲያሰራጩ ነበር።

የአከባቢው ነዋሪዎችና የትግራይ ምስራቃዊ ዞን አስተዳደር ግን ይህ ሀሰት ነው ሲሉ መልሰዋል።

ነዋሪች እና የዞኑ አስተዳደር " በዛላኣንበሳ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ከቆየው የተለየ እንቅሰቃሴ የለም " ብለዋል።

የምስራቃዊ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህ/ቤት የጉሎመኻዳና ኢሮብ ወረዳ አስተዳደሮች ጠቅሶ ባሰራጨው መረጃ ፥ አከባቢዎቹ ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊትም ሆነ በኋላ በኤርትራ መንግስት ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ገልጿል።

" ሉኣላዊ ግዛት ያለመከበር ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ባላፉት ቀናት በአከባቢው አዲስ ወታደራዊ እንቅሰቃሴ የለም " ብሏል። 

" በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች በዛላኣንበሳና በኢሮብ አከባቢ ከኤርትራ መንግስት በኩል የተለየ እንቅሰቃሴ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው ወሬ መሬት ላይ የሌለና የአከባቢው ነዋሪዎች ይሁንታ ያለገኘ ነው " ሲል አክሏል።

አስከ አሁን ድረስ ዛላኣንበሳ ከተማ ጨምሮ 5 የጉሎመኸዳ ወረዳ የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም ከኢሮብ ወረዳ 4 የገጠር ቀበሌዎች  በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ፅ/ ቤት አስታውሷል።

ዞኑ " በሬ ወለደ ወሬ የሚናፍሱ ሚድያዎችና የማህበራዊ ትስስር ገፅ ፀሃፊያን ከድርጊታቸው እንደዲታቀቡ እናሳስባለን " ሲል አስጠንቅቋል።

በቅርብ እና በረቁ የሚገኙ የዓጋመና አከባቢዋ ተወላጆችና ወዳጆች በየዓመቱ በትግራይ ደረጃ በዓዲግራት ከተማ የሚከበረው የመስቀል በዓል ለማከበር እንዲታደሙ ጥሪ በማቅረብ አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ እንዳለ አመልክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia 
2024/09/29 22:19:51
Back to Top
HTML Embed Code: