Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስአበባ #መታወቂያ “ የትምህርት ቤት ምዝገባው ሲጠናቀቅ አገልሎቱን መስጠት እንጀምለራለን ” - CRRSA ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው አዲስ አበባ ከተማ ለመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት “በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን” መባሉን ከወራት በፊት ነግረናችሁ ነበር። አሁንስ ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ አገልግሎቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትሰጡ ከዚህ ቀደም ገልጻችሁ ነበር፤…
መታወቂያ መስጠት መቼ ይጀመራል ?

" አሁን ማጣራት ጀምረናል የገቡትን መረጃዎች፣ አሰራሮችና ማኑዋሎች ጭምር ተዘጋጅቷል " - CRRSA

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከክልል ከተሞች መሸኛ ለሚያመጡ ዜጎች የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ መስጠት መቼ እንደሚጀምር ጠይቀነው የሰጠንን ምላሽ በተደጋጋሚ አድርሰናችሁ ነበር።

ኤጀንሲውን ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ መቼ ይጀመራል ? ብለን ጠይቀን በሰጠን ምላሽ፣ በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጾ ነበር።

ከቆይታ በኋላ ላቀረብንለት ተመሳሳይ ጥያቄ ቀሰጠው ምላሽ፣ " የትምህርት ቤት ምዝገባ ሲጠናቀቅ አገልግሎቱን መስጠት እንጀምራለን " ነበር ያለው።

የትምህርት ቤት ምዝገባው ሲጠናቀቅ መቼ መሰጠት እንደሚጀመር በወቅቱ ስንጠይቅም፤ ከነሐሴ አጋማሽ 2016 ዓ/ም በኋላ እንደሚሰጥ መግለጹ አይዘነጋም።

አሁንስ አገልግሎቱ መሰጠት ተጀመረ ?

አሁንስ አገልግሎቱን መስጠት ተጀምሯል ? ስንል የጠየቅናቸው አንድ የኤጀንሲው አካል፣ " ገና ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ የሚጀመር ይመስለኛል፡፡ ግን ገና ነው " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ከነሐሴ አጋማሽ በኋላ አገልግሎቱን እንደምትሰጡ ገልጻችሁ ነበር ብለን አስታውናቸዋል።

እኝሁ አካልም፣ " አዎ። አሁን ማጣራት ጀምረናል የገቡትን መረጃዎች፣ አሰራሮችና ማኑዋሎች ጭምር ተዘጋጅቷል፡፡ ገና መስጠት አልተጀመረም " ነው ያሉት።

አሁንስ መቼ መሰጠት ይጀምራል ? ስንል ጠይቀናቸው በሰጡት ምላሽ፣ እሳቸው ትክክለኛ ቀኑን እንደማያውቁት አስረድተዋል።

አክለውም፣ " መቼ ቀን እንደሚጀመር እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ በቅርብ ጊዜ ሊጀምር እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ "  ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል። የነሀሴ ወር 2016 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ሃምሌ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል። የነዳጅ ማደያዎችም ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ እንደታዘዙ አመልክተዋል። @tikvahethiopia
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የመስከረም ወር 2017 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ነሃሴ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ ፥ የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
#Tecno
ቴክኖ በአይነቱ አዲስ የሆነ እና ሶስት ጊዜ የሚታጠፍ PHANTOM ULTIMATE 2 የተሰኘ የስልክ ዲዛይን ንድፈ ሀሳብን ይፋ አድርጓል፡፡  ይህ የስልክ ዲዛይን ንድፈ ሃሳብ በአለም ገበያ ላይ ከሚገኙ ታጣፊ ስልኮች ቀጭን ዲዛይን ያለው ሲሆን ስልኩ ሶስት ጊዜ የመታጠፍ ብቃት ሲኖረው 11 ሚሊ ሜትር ውፍረት ብቻ  እንዲኖረው ሆኖ ዲዛይን ተደርጓል፡፡

PHANTOM ULTIMATE 2  ሲታጠፍ 6 ነጥብ 48 ኢንች ሙሉ በሙሉ ሲዘረጋ ደግሞ 10 ኢንች የስክሪን ስፋት ይኖረዋል ከዚህ ባለፈም ሁለት ስራዎችን እንደ አንድ ለመከወን እና የተለያዩ ቋንቋዎችን ለመተርጎም የሚያስችል ብቃትም አለው፡፡

ይህ የስልክ ዲዛይን ንድፈ ሃሳብ በቅርብ ለአለም ገበያ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AAU #GAT

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መስከረም 3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡ 

በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 1/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡

Via @tikvahuniversity
#Ethiopia ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆነውን የኤሌክትሪክ እና የውሀ ፍጆታ መጠን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 1021/2016 ከላይ ተያይዟል።

#MinistryofFinance

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OLF 🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ መንግስት በተለዬ መልኩ ጫና እያደረሰብን ነው ” ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲ ወቀሰ። ፓርቲው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርጓል። በዚህም በወቅታዊ እና በአገራዊ ጉዳዮች እንደ ፓርቲ ያለውን ግምገማና የመፍትሄ ሀሳብ አጋርቷል። Q. ስለ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፓርቲው ግምገማ ምንድን ነው ? ኦነግ ፦ የአገራዊ ምክክር…
ፎቶ ፦ ባለፉት አራት አመታት እስር ላይ የነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ተለቀዋል።
➡️ አብዲ ረጋሳ፣
➡️ ሚካኤል ቦረን፣
➡️ ኬነሳ አያና፣
➡️ ለሚ ቤኛ፣
➡️ ዶክተር ገዳ ኦልጅረ፣
➡️ ገዳ ገቢሳና ዳዊት አብደታ ዛሬ ማምሻውን ከእስር ቤት በዋስ መለቀቃቸውን የግንባሩ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ለሚ ገመቹ ለኦኤምኤንገልፀዋል።

#OMN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ባለፉት አራት አመታት እስር ላይ የነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ተለቀዋል። ➡️ አብዲ ረጋሳ፣ ➡️ ሚካኤል ቦረን፣ ➡️ ኬነሳ አያና፣ ➡️ ለሚ ቤኛ፣ ➡️ ዶክተር ገዳ ኦልጅረ፣ ➡️ ገዳ ገቢሳና ዳዊት አብደታ ዛሬ ማምሻውን ከእስር ቤት በዋስ መለቀቃቸውን የግንባሩ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ለሚ ገመቹ ለኦኤምኤንገልፀዋል። #OMN @tikvahethiopia
#OLF

" ለ4 ዓመታት ያህል በግፍ ታስረው የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ከእስር መለቀቃቸውን " የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ አወደሱ።

ፖለቲከኛው ፥ በአመራሮቹ መፈታት እጅጉን እንደተደሰቱ ገልጸዋል።

" መንግስት የቀሩትን የፖለቲካ እስረኞች በመፍታት የትጥቅ ግጭቶችን ሁሉ በውይይት እንዲቆሙ በማድረግ ይህንን በጎ እርምጃ ማሳደግ ይኖርበታል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የተፈጠረው ልዩነት ያለ ግጭት እንዲፈታ እንሰራለን " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ " ያሉት ልዩነቶች ያለ ግጭት እንዲፈቱ እንሰራለን " ብለዋል።

ይህን ያሉት ዛሬ ማይጨው ከተማ ህዝባዊ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

አቶ ጌታቸው የሚመሩትና ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ያሉበት የከፍተኛ አመራሮች ቡድን ከሰሞኑን በትግራይ እየተንቀሳቀሰ ህዝባዊ ውይይት እያደረገ ነው።

ከቀናት በፊትም በዓዲግራት ውይይት አድርጎ ነበር።

ዛሬ ደግሞ በማይጨው ከተማ ህዝባዊ ውይይት አድርጓል።

አመራሮቹ ወደ ማይጨው ባደረጉት ጉዞ በየመንገዱ ህዝቡ እየወጣ ተቀብሏቸዋል ፤ ማይጨው ላይም ከፍተኛ የሰው ቁጥር በአጀብ ተቀብሏቸዋል።

ከህዝብ ጋር ባደረጉት ውይይት የተለያዩ ጉዳዮች ተነስተው ነበር።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

- በአመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ህዝቡን ይከፋፍላል ስለዚህ በአስቸኳይ መቆም አለበት።
- በአመራሮች መካከል የተፈጠረው እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይብቀል ዓይነት አካሄድ ይቁም።
- በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ ፤ የተመለሱት ክትትልና ድጋፍ ይደረግላቸው።
- አመራሮች ሰላም ቀዳሚ የህዝብ ምርጫ መሆኑ ሊረዱና ሊያስቀጥሉ ይገባል።
- በዲፕሎማሲ እንጂ በአፈሙዝ አይመራም።
- የትግራይ ሉግዛት የማስከበር ጉዳይ ችላ መባል የለበትም።
- የሚታዩ የፀጥታ ስጋቶች የሚቀርፍ ቀጣይ ስራ ይሰራ።
- ፍትህ እየተጓደለ ነው ፤ በፍርድ ቤቶች ፍትህና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ይሰራል። 
- በሴቶች የሚደርሰው ጥቃት ይቁም።
- የሰማእታት ቤተሰቦች ትኩረት ይደረግላቸው።
- አቅም ያላቸው ሰዎች ወደ አመራር ይወጡ። - ተጀምረው የተቋረጡ መሰረተ ልማቶች ይቀጥሉ።
- ህገወጥ የወጣቶች ፍልሰት የሚከላከል መንግስታዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ተግባራዊ ይሁን።
- ከአግባብ ውጭ በሙስናና ህገ-ወጥ መንገድ ለኢንቨስትመንት ማስፋፍያ ተብሎ የሚሰጥ መሬት ይቁም ... ሲሉ አሳስበዋል። 

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ የህወሓት ህጋዊነት ለህዝብ በሚመጥንና የፕሪቶሪያ ውል በሚያስከብር መልኩ ለመመለስ እንደሚሰሩ ገልፀዋል። 

እርሳቸው በሚመሩትና በዶ/ር ደብረፀዮን በሚመራው ህወሓት መካከል የተፈጠረው ልዩነት ያለ ግጭት እንዲፈታ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

" ከዚህ ውጭ የፕሪቶሪያ ውል ለማፍረስ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ጦርነትን መጥራት መሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

" የተፈጠረው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ከማድረግ ጎን ለጎን ተፈናቃዮች በአጭር ጊዜ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ እናደርጋለን " ሲሉ አክለዋል።

ፎቶ፦ ድምጺ ወያነ

@tikvahethiopia 
2024/10/01 09:33:36
Back to Top
HTML Embed Code: