Telegram Web Link
🔈#የወላጆችድምጽ #AddisGlobalAcademy

“ ልጆቻችንን የት እናስመዝግባቸው ? ” - ወላጆች

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኘው “ አዲስ ግሎባል አካዳሚ ‘ለኮሪደር ልማት ያስፈልጋል ’ ” በመባሉ ልጆቻቸውን ሌላ ት/ቤትም ማስመዝገብ እንዳልቻሉ ወላጆችና ትምህርት ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ሌላ ት/ቤቶች እንዲያስመዘግቡ የተነገራቸው ሰሞኑን እንደሆነ፣ ሌሎች ት/ቤቶች ምዝገባ በማጠናቀቃቸው ልጆቻቸውን ማስመዝገብ እንዳልቻሉ የተማሪ ወላጆች ተናግረዋል።

“ ልጆቻችንን የት እናስመዝግባቸው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

ውሳኔውን ቀድመው ማወቅ እንደነበረባቸው ገልጸው፣ ምዝገባ እየተገባደደ ባለበት ወቅት ልጆቻቸውን ማስመዝገብ ስላልቻሉ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገረው የትምህርት ቤቱ በበኩሉ፣ ልማቱን ባይቃወምም ቢያንስ የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ፣ የወላጆች ቅሬታ ትክክል መሆኑን ገልጿል።

አንድ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር አካሌ፣ ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ/ም የቦሌ ክፍለ ከተማ አካላት ትምህርት ቤቱ እንደ ት/ቤት እንደማይቀጥል ገልጸው፣ ውሳኔውን ለወላጆች እንዲያሳውቁ ማሳሰቢያ እንደሰጧቸው አስረድተዋል።

ት/ቤቱም ለወላጆች ጥሪ አድርጎ ‘ት/ቤቱ ለልማት ይፈለጋል ባዮቹ’ ራሳቸው ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ማድረጉን፣ የተማሪ ወላጆችም ውሳኔው ዱብእዳ ሆኖባቸው ብዙ ጥያቄዎች እንዳነሱ ገልጸዋል።

የወላጆችም ቅሬታ ውሳኔው የአጭር ጊዜ በመሆኑ ልጆቻቸውን ማስመዝገብ ስለማይችሉ እንጂ ልማቱን መቃወም እንዳልተቃወሙ ያስረዱት እኝሁ አካል፣ “ ብዙ ወላጆች እያቀሱና እያዘኑ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው” ብለዋል።

“ እውነትም ብዙ ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ጨርሰዋል። በጥራት ችግርም ፈቃዳቸው የተወሰደባቸው ብዙ ትምህርት ቤቶች ስላሉ ጫናዎች አሉ ” ሲሉም ተናግረዋል።

“ ለምሳሌ ዛሬ አንዷ ወላጅ አንድ ት/ቤት ልጇን ልታስመዘግብ ሂዳ ስታለቅስ አይቷት ዳይሬክተሩ ደወለልኝ። እጅግ ልብ የሚሰብር ነገር ነው የሆነው ” ነው ያሉት።

“ በትምህርት ቤቱ ወደ 1,300 የሚሆኑ ተማሪዎች፣ ከ200 በላይ ሠራተኞች አሉ ” ብለው፣ መንግስት ወደ ሌላ ትምህርት ቤት እንደሚበተኑ ቢገልጽም በተለይ ተማሪዎቹ ላይ የሚያሳድረው የሥነ ልቦና ጉዳት ሊጠን እንደሚገባ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት ከመንግስት አካላት ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ሙከራው ይቀጥላል።

(ክፍለ ከተማው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ምላሹን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመጽሐፍ ምረቃ ግብዣ!

የአጫር ታሪኮች ሰብስብ የሆነው የደራሲ የሕይወት እምሻው "ለእርቃን ሩብ ጉዳይ" የተሰኘው #አዲስመጽሐፍ ሐሙስ ሐምሌ 25/ 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 11 ሰዓት ጀምሮ አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኘው ኢክላስ ሕንጻ፣ ዋልያ መጽሐፍት መደብር ይመረቃል።

ባለመኪና ታዳሚዎቻችን መኪናችሁን በአብርሆት ቤተ መጽሐፍት ወይም አምባሳደር የገበያ ማእከል እንድታቆሙ እንመክራለን::

በሰዓት ስለምንጀምር በሰዓት ይገኙልን!

[ ሕይወት እምሻው ]
🔈#የእገዛጥሪ

" ወንድማችንን ታደጉልን ! " - ጓደኞቹ

አቤል ተሾመ (ናቲ ) ከ1 አመት በፊት ( 2015 ሀምሌ ) በClinical Pharmacy ከሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በከፍተኛ መዓረግ መመረቁን ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ይናገራሉ።

ከዛሬ 7 ወር በፊት በድንገኛ  አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት (Acute kidney injury) እና የደም ግፊት ፣ ገለምሶ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ወዲያው ወደ ጥቁር አንበሳ ሪፈር ይባላል።

በጥቁር አንበሳ የውስጥ ደዌ ፣ የኩላሊት ስፔሻሊቲ ንዑስ ክፍል (Nephrology Department ) ላለፉት 7 ወራት የህክምና ክትትል ሲያረግ ጎን ለጎንም ላለፉት 3 ወራት በመቻራ ( ዳሮ ለቡ ) ሆስፒታል በተመረቀበት ሞያ ህዝቡን እያገለገለ ነበር።

ከወር በፊት ግን ህመሙ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ክትትል በሚያረግበት ክፍል፣ የኩላሊቶቹ ጉዳት የመጨረሻ ደረጃ End stage renal disease እንደደረሰ እናም የኩላሊት እጥበትና ንቅለ-ተከላ እንደሚያስፈልገው እንደተረገረው አስረድተዋል።

ለዚህም ህክምና ቢያንስ እስከ 2 ሚሊየን እና ከዚያም በላይ እንደሚያስፈልገው ተገልጾለታል።

" አሁን ላይ ወደ ቅዱስ ጷውሎስ ተዘዋውሮ የቅድመ ንቅለ ተከላ ሂደት ጀምሯል " ያሉት ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ " ሆኖም የዚህ ህክምና ወጪ ከአንድ ፋርማሲስት ( Pharmacist ) እና መንግስት ሰራተኛ ቤተሰቡ አቅም በላይ ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቻለው አቅም እንዲደግፈው " ሲል ተማጽነዋል።

የሒሳብ ቁጥር የአባቱ 1000055784772 Teshome Nigusse (CBE)  እንዲሁም የራሱ 1000055874895 Abel Teshome (CBE) እንደሆነ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#NBE

ብሔራዊ ባንክ ወርቅን ከአምራቾች እና አቅራቢዎች በብቸኝነት ይገዛል።

ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም. ጀምሮ በዉጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ላይ ለዉጥ በማድረግ በገበያ የሚመራ የፖሊሲ ማእቀፍን ስለሚከተል ለማንኛዉም ወርቅ አቅራቢ ክፍያ የሚፈጸመዉ የእለቱን ዓለም ዓቀፍ የወርቅ ዋጋ በእለቱ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣዉ የዉጭ ምንዛሪ ተመን ተባዝቶ እንደሆነ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዕለታዊ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዛሬው የምንዛሬ ዋጋ ስንት ነው ? 💵 US Dollar #CASH Buying ➡️ 74.7364 Selling ➡️ 76.2311 #TRANSACTION Buying ➡️ 74.7364 Selling ➡️ 76.2311 💷 Pound Sterling #CASH Buying ➡️ 91.5537 Selling ➡️ 93.3848 #TRANSACTION Buying ➡️ 96.0811 Selling…
#ዕለታዊ : የዶላር ዋጋ ጨምሯል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዱ የአሜሪካ ዶላር በ77 ብር ከ1280 ሳንቲም እየተገዛ በ78 ብር ከ6706 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል።

ፓውንድ ስተርሊንግ በተመሳሳይ ጨምሯል።

አንዱ በፓውንድ በ94 ብር ከ3071 ሳንቲም እየተገዛ በ96 ብር ከ1932 ሳንቲም እየተሸጠ ነው።

ትላንት መጠነኛ መውረድ አሳይቶ የነበረው ዩሮ ዛሬ ጨምሮ አድሯል። አንዱ ዩሮ በ83 ብር ከ3754 ሳንቲም እየተገዛ በ85 ብር ከ0429 ሳንቲም እየተሸጠ ነው።

ከመንግስታዊ ባንክ ውጭ በግል ባንኮችም የዶላር ዋጋ ጨምሯል።

ለአብነት ወጋገን ባንክ አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ77 ብር ከ7401 ሳንቲም እየገዛ በ79 ብር ከ2949 ሳንቲም እየሸጠ ነው።

ዩሮ 82 ብር ከ6591 ሳንቲም እየገዛ በ84 ብር ከ3123 ሳንቲም እየሸጠ ሲሆን ፓውንድ ስተርሊንግ በ93 ብር ከ6991 ሳንቲም እየገዛ በ95 ብር ከ5731 ሳንቲም እየሸጠ ነው።

በአንጻሩ ኦሮሚያ ባንክ ዶላርን ጨምሮ ዩሮ እና ፓውንድ ስተርሊንግ ትላንት ሲጠቀምበት በነበረው ተመን ነው ዛሬም የቀጠለው።

በዚህም አንዱ ዶላር በባንኩ በ74 ብር ከ7382 ሳንቲም እየተገዛ በ76 ብር ከ2329 ሳንቲም እየተሸጠ ነው።

ዩሮ በ81 ብር ከ0386 እየተገዛ በ82 ብር ከ6593 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል።

ፓውንድ ስተርሊንግ በ92 ብር ከ6021 ሳንቲም እየተገዛ በ94 ብር ከ4542 ሳንቲም እየተሸጠ ነው።

በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን / Floating exchange rate ወይም ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር በሚያደርጉ ነጻ ድርድር የውጭ ምንዛሬ መግዛት እና መሸጥ እንዲችሉ የሚፈቅደው አሰራር ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ባንኮች የየራሳቸውን ዕለታዊ ምንዛሬ አውጥተው እየተጠቀሙ ናቸው።

ዝርዝር ዕለታዊ ምንዛሬ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባውን አድርጎ ዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት በማጽደቅ ለሕ/ተ/ም/ቤት እንዲላክ ወስኗል።

ምክር ቤቱ ምን አለ  ?

- የተደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት የ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያስገኝ ነው። ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በእርዳታ፣ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በብድር መልክ የተገኘ ነው፡፡

- የፋይናንስ ድጋፉ ፦
° የኢትዮጵያ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች ለማስፈጸም
° ለሥራ ፈጠራ፣
° የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር፣
° የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ፣
° የመዋቅር ማስተካከያ ለማድረግ እንዲሁም የፌደራል መንግሥት የ2ዐ17 ዓ.ም በጀትን በቀጥታ ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡

- ብድሩ ከወለድ ነፃ ፣ የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው። ከአገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣምም ነው።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግዳሮቶቹ ምንድናቸው ?

ጠንካራ ጎኑን በሚመለከት በስፋት ከብሔራዊ ባንክ ሰነድ ላይ መረዳት ይቻላል።

ስለ ተግዳሮቶቹ ደግሞ የባንክ ጉዳዮች ባለሙያው ሙሴ ሸሙ ተከታዩን ሙያዊ ትንተና አቅርበዋል።


ከአስተያየታቸው መካከል ፦

- ገበያ መር (Free Floating) የውጭ ምንዛሪ ስርዓት በተረጋጋ፣ በቂ አቅርቦት እና ምርታማነት እውን በሆነበት ኢኮኖሚ ላይ ተመስርቶ ካልተተገበረ በስተቀር ውጤታማነቱ አስተማማኝ አይደለም።

- እጅግ የናረ ፍላጎት እና የአቅርቦት እጥረት ያለበት ኢኮኖሚ ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ ተመኑ ላይ ሲተገበር የውጭ ምንዛሪው ዋጋ የሚዋዠቅና በከፍተኝ ደረጃ የሚለዋወጥ ባህርይ ስለሚኖረው የምንዛሬ ተመኑ ከየት ተነስቶ የት ሊያደርስ እንደሚችል መገመት ያዳግታል። 

- እንደሚታወቀው ኢኮኖሚያችን የሚያመነጨው የውጭ ምንዛሪ መጠን ዝቅተኛና ፍላጎታችን የሚያጠረቃ ስላልሆነ የውጭ ምንዛሪውን ተመን ለገበያ ውድድር ብቻ መተዉ፣ የማያቋርጥ የውጭ ምንዛሪ ዋጋ ንረትና ጡዘት ሊያስከትል ይችላል። 

- የብር የመግዛት አቅም መዳከምን ተከትሎ አገልግሎት፣ የጉልበት ዋጋን ጨምሮ፣ አቅርቦት/ ፍጆታ ነዳጅና ማዳበርያ... ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ስለሚያሳዩ ኑሮ በከፍተኛ ደረጃ ሊንር ይችላል። 

- በሰላም እጦት ምክንያት ኢኮኖሚው በምርታማነት፣ በኤክስፓርት፣ በነጻ ግበይትና እንቅስቃሴ ስለማይደገፍ አቅርቦት ተዳክሞ የዋጋ ንረቱ ተባብሶ ሊቀጥል ይችላል። "

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Mushe-Semu-07-31

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የምዝገባ ጊዜን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ በ2017 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና  (NGAT) ምዝገባ ከሐምሌ 24 እከ ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም የሚካሄድ እንደሆነ ገልጿል።

የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መማር ፍላጎቱ ያላቸው የመመዝገቢያው ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት በ
https://NGAT.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዕለታዊ : የዶላር ዋጋ ጨምሯል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዱ የአሜሪካ ዶላር በ77 ብር ከ1280 ሳንቲም እየተገዛ በ78 ብር ከ6706 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል። ፓውንድ ስተርሊንግ በተመሳሳይ ጨምሯል። አንዱ በፓውንድ በ94 ብር ከ3071 ሳንቲም እየተገዛ በ96 ብር ከ1932 ሳንቲም እየተሸጠ ነው። ትላንት መጠነኛ መውረድ አሳይቶ የነበረው ዩሮ ዛሬ ጨምሮ አድሯል። አንዱ ዩሮ በ83 ብር ከ3754…
ዶላር ዛሬ ከሰዓት ጨምሯል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥዋት የነበረው የዶላር ዋጋ ዛሬ ከሰዓት ጨምሯል።

ባንኩ አንዱን ዶላር በ80 ብር ከ0203 ሳንቲም እየገዛ በ81 ብር ከ6207 ሳንቲም እየሸጠ ነው።

በተመሳሳይ ፓውንድ ስተርሊንግም ጨምሯል።

አንዱን ፓውንድ ስተርሊንግ በ97 ብር ከ8436 ሳንቲም እየገዛ በ99 ብር 8005 እየሸጠ ነው።

ዩሮ 86 ብር ከ5019 ሳንቲም እየገዛ በ88 ብር ከ2320 ሳንቲም እየሸጠ ነው።

(ሌሎች የከሰዓት የውጭ ምንዛሬ ዝርዝሮችን ከላይ ተመልከቱ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶላር ዛሬ ከሰዓት ጨምሯል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥዋት የነበረው የዶላር ዋጋ ዛሬ ከሰዓት ጨምሯል። ባንኩ አንዱን ዶላር በ80 ብር ከ0203 ሳንቲም እየገዛ በ81 ብር ከ6207 ሳንቲም እየሸጠ ነው። በተመሳሳይ ፓውንድ ስተርሊንግም ጨምሯል። አንዱን ፓውንድ ስተርሊንግ በ97 ብር ከ8436 ሳንቲም እየገዛ በ99 ብር 8005 እየሸጠ ነው። ዩሮ 86 ብር ከ5019 ሳንቲም እየገዛ በ88 ብር ከ2320…
#ዕለታዊ : የጠዋቱ እና የከሰዓቱ የምንዛሬ ለውጥ ምን ይመስላል ? (በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

💵 የአሜሪካ ዶላር !

➡️ ጠዋት ፦ 1 ዶላር መግዣው 77 ብር ከ1280 ሳንቲም ፤ መሸጫው 78 ብር ከ6706 ሳንቲም ነበር።

➡️ ከሰዓት ፦ 1 ዶላር መግዣው 80 ብር ከ0203 ሳንቲም ፤ መሸጫው 81 ብር ከ6207 ሳንቲም ሆኗል።

💷 ፓውንድ ስተርሊንግ !

➡️ ጠዋት ፦ 1 ፓውንድ ስተርሊንግ መግዣው 94 ብር ከ3071 ሳንቲም ፤ መሸጫው 96 ብር ከ1932 ሳንቲም ነበር።

➡️ ከሰዓት ፦ 1 ፓውንድ ስተርሊንግ መግዣው 97 ብር ከ8436 ሳንቲም መሸጫው 99 ብር ከ8005 ሳንቲም ሆኗል።

💶 ዩሮ !

➡️ ጠዋት ፦ 1 ዩሮ መግዣው 83 ብር ከ3754 ሳንቲም መሸጫው 85 ብር ከ0429 ሳንቲም ነበር።

➡️ ከሰዓት ፦ 1 ዩሮ መግዣው 86 ብር ከ5019 ሳንቲም መሸጫው 88 ብር ከ2320 ሳንቲም ሆኗል።

#UAE ድርሃም !

➡️ ጠዋት ፦ 1 ድርሃም መግዣው 18 ብር ከ7954 ሳንቲም ፤ መሸጫው 19 ብር ከ1713 ሳንቲም ነበር።

➡️ ከሰዓት ፦ 1 ድርሃም መግዣው 19 ብር ከ5002 ሳንቲም ፤ መሸጫው 19 ብር ከ8902 ሳንቲም ሆኗል።

የውጭ ምንዛሬ በገበያው መወሰን / Floating exchange rate / የሚባለው ይኸው ነው። የውጭ ምንዛሬው በፍጥነት መለዋወጥ የሚታይበት ነው።


#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
ተጨማሪ በጀት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ያገኘውን ድጋፍ እና ብድር የያዘ ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ለፓርላማ አቅርቦ እንደሚያስጸድቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል።

ይህ የተናገሩት ዛሬ በነበረው የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ወቅት ነው።

ተጨማሪ በጀቱ ፦

➡️ ለዝቅተኛ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች ለሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፣

➡️ ለነዳጅ ድጎማ፣

➡️ ለዘይት ድጎማ፣

➡️ ለማዳበሪያ እና መድኃኒት ድጎማ የሚውል መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ፎቶ፦ ፋይል

#EthiopianInsider #HoPR #Ethiopia

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

🎁በተወዳጆቹ ሜጋ ጥቅሎች በሽ በሽ እንበል! ለ90 እና ለ180 ቀን የሚቆዩትን ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 500 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት!

🤖 የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
   🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
2024/10/01 13:29:01
Back to Top
HTML Embed Code: