Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል።

አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራ ባደረገው ግለሰብ ላይ የተኩስ መልስ ሲሰጡ ተስተውሏል።

ግለሰቡ የግድያ ሙከራ ባደረገ በሰከንዶች ውስጥ መተገው ገድለውታል።

የግድያ ሙከራውን ያደረገው ማነው ?

- FBI የግድያ ሙከራውን ያደረገው ቶማስ ማቲው የተባለ #የ20_ዓመት_ወጣት እንደሆነ ገልጿል።

- ነዋሪነቱ ምርጫ ቅስቀሳውና የግድያ ሙከራው ከተደረገበት ስፍራ የአንድ ሰዓት ጉዞ የሚፈጅ ቦታ ነው።

- በ2022 ነው ቤተል ፓርክ ከተባለ ሀይስኩል የተመረቀው።

- ወጣቱ በብሔራዊ የሒሳብ እና ሳይንስ ኢኒሼቲቭ ተሸላሚም ነበር።

- የሪፐብሊካን ደጋፊም ጭምር እንደሆነ ተመዝግቧል (የዶናልድ ትራምፕ ፓርቲ ማለት ነው)።

- ቅስቀሳው ከሚደረግበት ቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣራ ላይ ሆኖ ነው ዶላንድ ትራምፕን ለመግደል የሞከረው።

- ለምን ይህን ለማድረግ እንደፈለገ FBI ምርመራ እያደረገ ነው።

#USElection #FBI

@tikvahEthiopia
#Internet

ትላንት ምሽት በተካሄደ የኢንተርኔት የመመለስ ስራ ለበርካታ ወራት ኢንተርኔት ተቋርጦባቸው የነበሩ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኛታቸው ተሰምቷል።

ከሁነኛ ምንጭ በተገኘ መረጃ ኢንተርኔት ተቋርጦ በነበረባቸው 19 ከተሞች አገልግሎት ተመልሷል ተብሏል።

የትኞቹ ከተሞች ናቸው ?
- ባህር ዳር
- ጎንደር
- ደሴ
- ኮምቦልቻ
- ወልዲያ
- ሰቆጣ
- ደብረ ብርሃን
- ደብረ ማርቆስ
- ደብረ ታቦር
- ፍኖተ ሰላም
- ገንደውሃ
- ከሚሴ
- ጋሸና
- ቡሬ
- ባቲ
- ደጀን
- ደባርቅ
- ኢንጅባራ
- ሁመራ ናቸው።

በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን ስለ ተለቀቀው የኢንተርኔት አገልግሎት በተመለከተ ጠይቀናቸው ፍጥነቱ ያን ያህል እንደሆነ እንዲሁም መጨናነቅም እንደሚታይ ነገር ግን እንደተለቀቀ አመልክተዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Raya እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ሪፖርት መሰረት ከራያ አላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ በልጧል። 42 ሺህ ዜጎች ቆቦ ፤ 8,300 ሰዎች ሰቆጣ ይገኛሉ። የተፈናቀሉት ከራያ አላማጣ፣ ዛታ፣ ኦፍላ ነው። አብዛኞቹ ህጻናት ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች እና በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ናቸው። #UNOCHA @tikvahethiopia
🔈 #የተፈናቃዮችድምጽ

ሚያዚያ ወር በተቀሰቀሰው ግጭት ከኮረም፣ ኦፍላ፣ ዛታ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎች ዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞን ይገኛሉ።

እነዚህ ወገኖች ላለፉት ሶስት ወራት ያለ በቂ ሰብዓዊ ድጋፍ በመቆየታቸው የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

አጠቃላይ ተፈናቃዮች ከ22 ሺህ ይልቃሉ።

ተፈናቃዮች ምን አሉ ?

- አሳሳቢ የምግብ እና የመጠለያ ችግር አለ።
- እያንዳንዱ በሰው ቤት ተጠግቶ ነው ያለው።
- ቤተዘመድ እያገዛቸው እንጂ ለ3 ወር የከፋ ችግር ላይ ወድቀው ነው የሚገኙት።
- በ3 ወር ምንም የተደረገ ድጋፍ የለም።
- ዋግኽምራ ዞን የተቻለውን ቢያደርግም ከአቅሙ በላይ ነው። ብዙ ሰው ነው ያለው።
- አብዛኛው በረዳ ወቅዷል።
- ዘመድ ያለውም ዘመዱ ጋር ተቸግሮ ነው የሚኖረው።
- እየለመ የሚበላ አለ፣ ጉልበት ያለውም ተቀጥሮ የሚሰራ አለ።
- አንዳንድ እናቶች መጠለያ ተሰጥቷቸው ነበር ግን ልጆቻቸው ሲታመሙ ቤት ተከራይተው ወጥትተዋል። በዚህ ኑሮ ውድነት መኖር አልቻሉም።
- ተፈናቃዮቹ በቄያቸው ቤት እና ስራ ነበራቸው።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ምን አለ ?

° ከ11 ሺህ ተፈናቃዮች ነው ያሉት።
° አሁን ባለንበት ሁኔታ መጠለያ ማዘጋጀት አንችልም። ድንኳንም የለንም።
° የምንመግበውን ተቸግረን በመጡ ጊዜ ለአንድ ሰው 25 ኪ/ግ ነው  የሰጠነው። ከመጠባበቂያ !
° የሰላሙ ሁኔታ አለ፣ መንገድ ዝግትግት ያለ ነው ሌላ አካል ድጋፍ ላምጣ ቢል እንኳን።
° አካባቢው ዝናብ አጠር ነው። በድርቅ ይጠቃል። የዓምናው ድርቅም ጉዳቱ እንዳለ ነው። ብዙ ሰው ተጎድቷል። አሁን ተፈናቃይ ተጨምሮ ይቅርና በፊትም ብዙ ችግር አለ።
° በህጻናት አድን ድርጅት ካሽ 14 ሺህ በሁለት ዙር ለመስጠት ልየታ እየተደረገ ነው።
° ያሉት ተፈናቃዮች ከኦሮሚያ፣ ከመተማ፣ በሰሜን ጦርነትም ተፈናቅለው ያልሄዱ አሉ።

በአሁኑ ወቅት እርሳቸውም ተፈናቃይ መሆናቸውን የገለጹትና ኮረም ከተማን ለሁለት ዓመት በከንቲባነት የመሩት አቶ ብርሃኑ ኀይሉ፣  የተፈናቀለው ሕዝብ ብዛት ከ22 ሺሕ እንደሚበልጥ ገልጸው ፥ የምግብ አቅርቦቱ እጥረት አሳሳቢ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

" እርዳታ ጠይቀናል። ለ3 ወራት ተከታታይ እርዳታ የለም።  ክልሉ የሰጠን ነገር የለም፤ ጭራሽ አላነገረንም " ብለዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን " መረጃ አለን ፤ ለተፈናቃዮቹ የምግብ አቅርቦት ጥያቄ በቅርቡ ምላሽ ይሰጣል ፤ እርዳታም ይጓጓዛልም " ሲል ገልጸዋል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#DStvEthiopia

የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰ !

ከከባድ ትንቅንቅ በኋላ ስፔን እና እንግሊዝ ለፍፃሜ በጀርመን ኦሎምፒያስታዲዮን ይገናኛሉ!
እንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ታነሳ ይሆን? ስፔንስ የአሸናፊነት መንገዷን ትቀጥል ይሆን? 

⚽️ Spain vs England ሐምሌ 7 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM

👉SS Football ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ
👉SS Euro2024 ቻናል 222 በሜዳ  ፓኬጅ

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ልዩ በቀጥታ ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል። አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራ ባደረገው…
#USA

በትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ሲደረግ የሚያሳዩ ቪድዮዎች ወጥተዋል።

የግድያ ሙከራ ያደረገው ቶማስ ማቲው ክሮክስ የተባለው የ20 ዓመት ወጣት ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ከሚደረጉበት ስፍራ ውጭ ላይ ካለ አንድ ጣራ ላይ ተኝቶ ትራምፕን ለመግደል በተደጋጋሚ ሲተኩስ ታይቷል።

ብዙ ሳይቆይ በሴክሬት ሰርቪስ የስናይፐር ተኳሾች ተመቶ ተገድሏል።

የተለያዩ የአይን እማኞች ለቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሰጠቱ ቃል ፥ የግድያ ሙከራ ያደረገው ወጣት ጣራ ላይ ሲወጣና ከአንዱ ጣራ ወደሌላኛው ጣራ ሲሄድ በኋላም ተኝቶ ትራምፕ ላይ ሲተኩስ መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ድርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት ጣራ ላይ መሳሪያ የያዘ ሰው እንዳለ ለፖሊስ አባላት ጥቆማ ሰጥተው እንደነበር ጠቁመዋል።

የግድያ ሙከራው እስኪደረግ ድረስ ጥቆማቸው ለምን ችላ እንደተባለ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል።

አንዳንድ የደህንነት ባለሞያዎች ሁሉም ጣራዎች ላይ ለምን የሴክሬት ሰርቪስ ሰዎች እንዳልነበሩ እና በሰዓቱ የነበረው የደህንነት ስራው ምርመራ እንዳሚፈልግ ጠይቀዋል።

የአሜሪካ " ሴክሬት ሰርቪስ " ዋነኛ ስራው የአሁን እና ቀድሞ ፕሬዜዳንቶችን ደህንነት ማስጠበቅ ነው።

በሀገሪቱ በአሁን ወይም በቀድሞ ፕሬዜዳንቶች ላይ የግድያ ሙከራ ሲደረግ የአሁኑ ከ43 ዓመታት በኋላ ነው።

ከ43 ዓመታት በፊት ሮናልድ ሬገን በተሞከረባቸው ግድያ ክፉኛ ተጎድተው ለጥቂት ነበር ከሞት ያመለጡት።

#USA
#DonaldTrump

@tikvahethiopia
" ከ2013 ዓ/ም በፊት በአከባቢው ሰላም እና ፀጥታ ሲያስከብሩ የነበሩ ታጣቂ ተፈናቃዮች ከነትጥቃቸው ይመለሳሉ " - ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌ/ ጀነራል ታደሰ ወረደ ትላንት መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ፥ " ለአመታት ከቄያቸው ተፈናቅለው በትግራይ የተለያዩ ከተሞች እና በሱዳን የሚገኙ የምዕራብ ትግራይ ነዋሪዎች እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ወደ አከባቢያቸው ለመመለስ የተያዘው የጋራ እቅድ የዘገየው በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተፈጠረ ችግር አይደለም " ብለዋል።

" የነበረ ክፍተት ተገምግሞ ተፈናቃዮች ድህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቄያቸው ለመመለስ እየተሰራ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ም/ፕሬዜዳንቱ ፥ " የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ አከባቢያቸው የመመለስ ስራ የራያ እና ፀለምቲ ተፈናቃዮች በመመልስ የተገኘው ልምድ መስረት በማድረግ ይፈጸማል " ብለዋል። 

" ተፈናቃዮችን የመመለስ ተግባሩን የሚያቆም አካል የለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የምዕራብ ትግራይ የህዝብ ብዛት እና የኢኮኖሚ የበላይነት ለመያዝ ያለመ የሰፈራ ስራ በአማራ መንግስት ተካሂደዋል " ያሉት ሌ/ጀነራሉ " ከሌሎች አከባቢዎች ወደ ምዕራብ ትግራይ ገብተው እንዲሰፍሩ የተደረጉ ታጣቂዎች እንዲወጡ ይሰራል " ብለዋል።

" ከ2013 ዓ.ም በፊት በአከባቢው ሰላምና ፀጥታ ሲያስከብሩ የነበሩ ታጣቂ ተፈናቃዮች ከነትጥቃቸው ይመለሳሉ "  በማለትም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፥ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ቀላል እና ከባድ ወንጀሎች በመፈፀም ላይ እንዳሉ ተናግረው በአጭር ጊዜ ወንጀል ፈጻሚዎችን ወደ ተጠያቂነት ለመሸጋገር የሚስችል ስራ መጀመሩን አሳውቀዋል።

በከባባድ ወንጀል በተሳተፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አመልክተዋል።

እነማ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ? የሚለውን በዝርዝር አልተናግሩም።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
📷

ዛሬ መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ይጓዝ የነበረ ተሳቢ መኪና ጌዴኦ ዞን፣ ወናጎ ወረዳ ውስጥ ተንሸራቶ ሲወድቅ ከመብራት ሽቦ ጋር ተገናኝቶ እሳት በመነቱ መኪናውን በእሳት ተቀጣጥሎ ወድሟል።

መኪናው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ ተርፈዋል።

ሌላኛው የሰሌዳ ቁጥር ' ኦ.ሮ 27555 ' የህዝብ ማመላለሻ መንገድ ስቶ ተገልብጦ በደረሰ አደጋ ሶስት ሰዎች ተጎድተው ዲላ ሆስፒታል ገብተው ህክምና ላይ ናቸው።

ፖሊስ አደጋ የደረሰው በነበረው ዝናብ ምክንያት በመንሸራተት እንደሆነ ጠቁሞ የክረምት ወቅቱ በመግባቱ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

#ጌዴኦዞንኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሁለት ወራት ከ18 ቀናት ነው መተከል የቆየሁት አንድም ቀን መብራት አልበራም " - ዶክተር መብራቱ አለሙ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሥራ አስፈፃሚ ፣ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ቦሮ) የውጪ እና ዓለም አቀፍ ዘርፍ ኃላፊ ፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር መብራቱ አለሙ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲን ወክለው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በዚህ ቆይታቸው…
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

• “ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚተገበረው ግን መቼ ነው ? ” - የቡለን ወረዳ ነዋሪዎች

• “ ‘ለምን አልመርጣችሁኝም ’ በማለት በበቀል ህዝብን መጉዳት ተገቢ አይደለም ” - ዶ/ር መብራቱ አለሙ


በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ‘ ለምን ፓርቲውን መረጣችሁ ’ በሚል ሰበብ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት እና ፓርቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

በአካባቢው ከዚህ ቀደም በነበረው የጸጥታ ችግር ሳይካሄድ ቀርቶ የነበረው ምርጫ በቅርቡ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ ምርጫውን ያሸነፈው የፓርቲው አባላት ላይ የ ' ቡለን ወረዳ አስተዳደር ' እስራትን ጨምሮ ድብደባ እያደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

“ እኛ የፈለግነውን የመምረጥ መብት አለን። ቦሮን መረጣችሁ በማለት እንዴት እንግልት ይደርስብናል ? ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚተገበረው ግን መቼ ነው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

የፓርቲው የውጪና አለም ዓቀፍ ዘርፍ ኃላፊ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ከፍተኛ አመራር ዶ/ር መብራቱ አለሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ አመራሮች ከምርጫ በኋላ ‘ለምን ቦዴፓን መርጣችሁ’ በሚል ሰበብ ” የሚከተሉትን ድርጊቶች በአባላቱ ላይ እየፈጸሙ መሆኑን ገልጸዋል።

➡️ ከቀበሌ ሚሊሻ አርሶ አደሮች ትጥቅ ማስፈታት
➡️ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ግብር መጫን
➡️ የመንግስት ሠራተኞችን ማዋከብና ፣ ማስፈራራት፣ ማሰርና ማዘዋወር
➡️ ነዋሪዎችን ‘በልማት ስራ አልተገኛችሁም’ በማለት በገንዘብ መቅጣት
➡️ መንግስታዊ አገልግሎት መንፈግ ለአብነት የመታወቂያ እድሳት፣ አዲስ የመታወቂያ ጥያቄ አለማስተናገድ፣
➡️ የድጋፍ ደብዳቤ መከልከል ተጀምሯል ሲሉ ድርጊቶቹን አስረድተዋል።

“ ከነበሩት ቦታ ያለአግባብ የተዘዋወሩ ሁለት የግብርና ባለሙያዎች ቅሬታ በጽሑፍ ሲያቀርቡ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ወርቀቱን ተቀብሎ ቀዶ ከጣለ በኋላ ባለጉዳዮች እንዲታሰሩ አድርጓል ” ሲሉም ወቅሰዋል።

“ የባለጉዳዮችን አቤቱታ ቀዶ የጣለውን ትተው ባለጉዳዮችን አስረዋል ” ነው ያሉት።

“ ህዝቡ የፈለገውን ፓርቲ የመምረጥ መብት አለው። የፈለገውንም መርጧል ” ያሉት ዶ/ር መብራቱ ፥ “ መንግስት ደግሞ የመርጠውንም ያልመርጠውን እኩል የማገልገል ግዴታ አለበት ” ብለዋል።

“ ‘ ለምን እኔን አልመርጣችሁኝም ’ በማለት በበቀል ህዝብን መጉዳት ተገቢ አይደለም። ይህ አካሄድ መልሶ መንግስትን ይጎዳል። ይህ ድርጊት የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል ” ሲሉ አክለዋል።

“ በአጠቃላይ በወረዳው ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ህገወጥ ወከባ የማይቆም ከሆነ በወረዳው ግጭት ሊፈጠር ይችላል ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ቅሬታ ለፈጠረው የመብት ጥሰት ቅሬታ የወረዳውን ምላሽ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የመምህራንድምጽ

" አይደለም ያለ ደመወዝ በደመወዝም እንኳን ኑሮን አልቻልነውም ፤ ደመወዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል " -  መምህራን
 
ከየካቲት ወር 2016 ጀምሮ #እየተቆራረጠ 50% ፣ 30% እየተከፈለ ቆይቶ እስከ የሰኔ ወር ሳይጨምር ውዝፍ ደመወዝ ከ70 እስከ 120% አልተከፈለንም ያሉ በጎፋ ዞን የአይዳ ፣ ገዜ ጎፋ እና ደምባ ጎፋ ወረዳ መምህራን ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" ያለደሞዝ አይደለም በደሞዝም ኑሮን አልቻልነዉም " የሚሉት መምህራኑ " ስቃያችን መች ነዉ የሚያበቃው ? " ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር፥ " የመምህራኑን ድምጽ በተደጋጋሚ ለሚመለከተዉ አካል ሳሳዉቅ ቆይቻለሁ " ብሏል።

መምህራኑም አቤቱታቸውን ለሚመለከተው አካል አቅርበው እንደነበርም አስረድቷል።

ነገር ግን የዞኑ አስተዳደር እና የትምህርት መምሪያው ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ተገቢውን ምላሽ ባለመስጠቱ መምህራኑ የአመራሩን ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከሰምኑ እነዚህ መምህራን ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሠልፍ ለመጠየቅ ሲሞክሩ  የዞኑ መምህራን ማህበር ከአመራሩ ጋር ውይይት እያደረገ በመሆኑ ሠልፍ እንዳይወጡና በትዕግስት እንዲጠብቁ በማድረግ መመለሱን ማህበሩን አሳውቆናል።

ይሁና መምህራኑ ባልተደራጀ ሁኔታም ቢሆን ጥያቄ ለማቅረብ ወደተለያዩ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች መሄዳቸውና በዛም " በዚህ ደረጃ መቀጠል አንችልም ደሞዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል !! " በማለት ድምጻቸዉን ማሰማታቸዉ ተገልጿል።

እንዲህ አይነት ጥያቄዎች ካሁን በፊትም በሌሎች የክልሉ ዞኖች ውስጥም መስተዋላቸውን አንስተን ጥያቄ ያቀረብንላቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊዉ ዶክተር ታምራት ይገዙ ፤ "  ችግሩን እንደ ክልል ከየካቲት ወር ጀምሮ መቅረፍ ተችሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

አሁን ላይ የመምህራንን ደሞዝ በተመለከተ አሰራሩ ዲሴንትራላይዝ ተደርጎ ለየዞኖቹ መሰጠቱን የገለጹት ኃላፊዉ " እኛ ቴክኒካል ድጋፍ እያደረግን ብቻ ነው ያለው " በማለት የደመወዝ ጉዳይ ለነሱ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

" ችግሩ በዚህ ደረጃ ከተስተዋለ ግን ገምግመን ድጋፍ የምንሰጥ ይሆናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#INSA የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ያዘጋጀው የ2016 ዓ/ም “ ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ” ፕሮግራም ምዝገባ እስከ ሰኔ 10/2016 ዓ/ም ድረስ መራዘሙን አሳውቋል። እስካሁን በርካታ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች መመዝገባቸው ተገልጿል። ምዝገባው እስከ ሰኔ 10 ድረስ መራዘሙ ተጠቁሟል። በሳይበር ደህንነት እና በተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶች…
#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ባዘጋጀው የ2016 ዓ/ም “ ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ” ፕሮግራም ላይ ተመዝግበው ለ3ኛ ዙር ፈተና ያለፉ ነዋሪነታቸውም በአዲስ አበባ ከተማ ለሆኑ ፈተናው የሚሰጠው ከማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ዓ/ም እስከ ዓርብ ሐምሌ 12/2016 ዓ/ም መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

ወደ 3ኛው ዙር ፈተና ያለፉ ስም ዝርዝር በ ' INSA የሳይበር ታለንት ማእክል ' የቴሌግራም አድራሻ ➡️ https://www.tg-me.com/cteinsa ላይ በመግባት ማየት እንደሚቻልም ተገልጿል። #INSA

@tikvahethiopia
ከሰማይ እንደመጣ የተነገረለት ' ድንጋይ ' ምንድነው ?

በኦሮሚያ ክልል፤ በጅማ ዞን፤ የቡ ከተማ በቅርቡ ከሰማይ እንደመጣ የተነገረለትን ድንጋይ በተመለከተ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስትቲዩት ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማብራሪያው የሚከተለው ነው ፦

" አስትሮይድ (Asteroid) በህዋ ውስጥ የሚገኙ ድንጋያማ አካላት ናቸው፡፡

በዋነኛነት የስርዓተ ጸሐይ አካል በመሆን በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው ስፍራ የመቀነት ቅርጽ (Asteroid Belt) ፈጥረው ጸሐይን ይዞራሉ፡፡

እነዚህ የሰማይ አካላት ግዙፍ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹም በመቶ ኪሎሜትሮች የሚቆጠር ዲያሜትር ያላቸው ናቸው፡፡

በአንፃሩ ሜትሮይትስ (Meteorites) ወደ ምድር ከባቢ አየር የገቡ የአስትሮይዶች ወይም ኮሜት ቁርጥራጮች ናቸው።

በሌሊት ሰማይ ላይ የምናያቸው የብርሀን ጅራቶች ሜትሮይድ (Meteoroid)፣ ትንሽ የጠፈር አለት ወደ ከባቢ አየር ውስጥ ሲገባና ሲቃጠል የሚፈጠር ነው።

የሜትዮር ሻወር (Meteor Shower) አስደናቂ የብርሃን ትዕይንት በሰማይ ላይ የሚፈጥሩ ሲሆን፤  አብዛኛዎቹ ሜትሮይዶች ጥቃቅን እና መሬት ላይ ከመድረሳቸው በፊት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው የሚጠፉ ናቸው።

በመጠን የገዘፉ እና ጠንካራ የሆኑት አለቶች ከእሳታማው መተላለፊያ እና የመሬት ከባቢ አየር ተርፈው መሬት ላይ ይደርሳሉ።

ከላይ በምስል የሚታየው አለት በጅማ ዞን በየቡ ከተማ የተገኘ ነው።

የተገኘው ድንጋይ ሜትሮይት ወይም ሌላ ዓይነት ከህዋ የተገኘ አለት መሆን አለመሆኑን ለመወሰን የላብራቶሪ ምርመራ አስፈላጊ ነው።

አሁን ባለበት ደረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም።

Meteorites ከተለመዱት የምድር አለቶች የሚጋሩት ነገር ቢኖርም በራሳቸው ደግሞ የተለየ ስሪት እና አወቃቀር ያላቸው በመሆኑ በአይን በማየት ብቻ ለመለየት አዳጋች ይሆናል፡፡

የመስኩ ተመራማሪዎች የሜትሮይትን ስብጥር ለመተንተን የረቀቁ ቴክኒኮችን እና የሳይንስ መመርመሪያ መሳሪያዎችን ይጠቀማሉ።

ይህም የማዕድን ይዘቱን ለመመርመር ከምድር ውጭ ያሉ ንጥረ ነገሮች መኖራቸውን መለየት እና የተረጋጋ የአይሶቶፖች ምጥጥንን (isotope ratio) መለካትን ጭምር ያካትታል።

እነዚህ ትንታኔዎች የሜትሮይትን አመጣጥ እና ስለ መነሻ ምንጫቸው አስመልክቶ ግንዛቤ ለማግኘት ይረዳሉ።

ሜትሮይት በምድር ላይ የሚያስከትሉት ተጽእኖ እና ጉዳት በአንፃራዊነት እጅግ አነስተኛ ነው፡፡

በየዓመቱ ወደ ምድር ገጽ የሚወርዱትም በቁጥር ጥቂት ናቸው፡፡ አብዛኛው አካላቸው በምድር ከባቢ አየር ውስጥ ሲያልፍ ተቃጥሎ ስለሚያልቅ፤  የሚያደርሱት ጉዳት ያነሰ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ጉልህ የሆነ ውድመት ሊያስከትሉ የሚችሉት በሚሊዮን አንዳንዴም በሺህ ዓመታት የሚከሰቱት ብቻ ናቸው፡፡

ከዚህ አኳያ የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ቴሌስኮፖችን በመጠቀም ካለማቋረጥ እንቅስቃሴያቸውን በንቃት በመከታተል ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጡ የሚችሉትን አስቀድሞ በመለየት የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋሉ።

ለምሳሌ ፦ በሀገራችን አቆጣጠር ከ5 ዓመት በኋላ ማለትም በሚያዝያ ወር 2021 ዓ.ም. አፓፊስ (Apophis) የተሰኘ 340 ሜትር ስፋት ያለው አስትሮይድ Geosynchronous ሳተላይቶች ካሉበት 35, 786 ኪ.ሜ. ከፍታ ዝቅ ብሎ ከመሬት በ31, 860 ኪ.ሜ. ከፍታ ላይ እንደሚደርስ ትንበያዎች ያሳያሉ።

የሰው ልጅ የተለያዩ መሳሪያዎችን እና ቴክኒኮችን በመጠቀም ህዋን መመርመር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ይህንን ያክል ግዙፍ አለት ወደ መሬት ሲጠጋ የመጀመሪያው ክስተት እንደሆነ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስትቲዩት በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የአስትሮይድ እንቅስቃሴን ለመከታተል (Asteroid Tracking) የሚያስችል የቴሌስኮፕ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል፡፡ "


#SSGI

@tikvahethiopia
2024/09/30 08:15:52
Back to Top
HTML Embed Code: