Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya #Update ሩቶ ካቢኔያቸውን በተኑ። ለሳምንታት በህዝብ ተቃውሞ ስትናጥ የከረመችው ኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውን በተኑ። ሩቶ ዛሬ ነው ይህን እርምጃ የወሰዱት። የፕሬዜዳንቱ እርምጃ በመላው ሀገሪቱ ለተነሳው የፀረ መንግሥት ተቃውሞ እንደምላሽ ነው የተወሰደው። ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ፥ የካቢኔያቸው ተቀዳሚ ዋና ጸሐፊ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ እንዲሁም…
" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በመበተን ሚኒስትሮቻቸውን ከስልጣን ያባረሩት ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑን አሳውቀዋል።

ሩቶ ፥ " ኬንያውያንን በመስማት ካቢኒዬን መርምሬ ነው የወሰንኩት " ብለዋል።

" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።

ከሥራቸው የማይባረሩት ምክትል ፕሬዝዳንቱና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የሚያገለግሉት የካቢኔው ዋና ፀሐፊ ሥልጣናቸው ላይ ይቆያሉ።

ሌሎቹ በጠቅላላ የካቢኔያቸው አባላት ሚኒስትሮች ተባረዋል።

የፋይናንስ ረቂቅ ሕጉን ተከትሎ ፥ " ግብር ሊጨመርብን አይገባም በቃን ! ፣ ተጨማሪ ግብር አንከፍልም፣ ሕጉ ኑሮው ያስወድድብናል " በማለት ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የጀመሩት ተቃውሞ ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተሸጋግሮ የ39 ሰዎች ህይወት ከጠፋ በኋላ ሩቶ ሕጉን ሰርዘውታል።

ምንም እንኳን ሕጉ ሙሉ በሙሉ ቢሰረዝም ተቃውሞው አላበቃም።

ፕሬዜዳንቱ ባልተለመደ ሁኔታ ከተቃዋሚ ወጣቶች ጋር በኦንላይን (X) ምንም አይነት ገደብ የሌለው ግልጽ ሕዝባዊ ውይይት አድርገው ነበር ፤ ያም ቢሆን ሕዝባዊ ጥያቄውን አላስቆመውም።

ፕሬዜዳንቱ በሙስና የተዘፈቁ ሚኒስትሮችን ጠራርገው እንዲያባርሩና ካቢኔውን እንዲበትኑ ጥሪ ሲቀርብ ነበር።

ይህን ተከትሎ ዛሬ ፕሬዜዳንቱ ካቢኔያቸውን በትነዋል።  " የሕዝቤን ድምጽ በመስማት ነው እርምጃውን የወሰድኩት " ብለዋል።

#Kenya
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Somaliland #US

ዛሬ በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ ነበሩ።

አምባሳደር ሪቻርስ ሪሌይ ፤ ሶማሌላንድ ሀርጌሳ ሄደው ከሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ጋር መክረዋል።

ከሌሎችም ከፍተኛ የፖለቲካ መሪዎች ፣ የሲቪል ማህበረሰብ መሪዎችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋርም መወያየታቸው ተሰምቷል።

አምባሳደሩ ፤ አሜሪካ በቀጠናው ብልጽግናን እና የዴሞክራሲ ተቋማትን ለመደገፍ የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት እንዳላት አረጋግጠዋል።

ዲፕሎማሲያዊ እና የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ቀጠናዊ ትብብር እና ውይይትን ያበረታቱም ሲሆን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር የምርጫ ጊዜን በማክበር አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል።

ከግሉ ሴክተር መሪዎች ጋር በመገናኘት ከአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ ጋር ግንኙነት እንዴት እንደሚጠናከር መነጋገራቸው ታውቋል።

የነቃ ሲቪል ማህበረሰብ እና ነፃና ሙያዊ ስርዓቱን ያከበረ ፕሬስ አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል ተብሏል።

ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂም ከአሜሪካው አምባሳደር ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን አሳውቀዋል።

በቀጠናዊ ጉዳዮች ፣ በአፍሪካ ቀንድ ትብብርን ማጎልበት ፣ በምርጫ ጉዳይ ፣ በሶማሌላንድ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

በሶማሊያ፣ ሞቃዲሹ ያለው ኤምባሲ የዛሬውን የአምባሳደሩን የሀርጌሳ ጉብኝት በተመለከተ ያሰራጨውን የጽሁፍ መግለጫን አንዳንዶች ' ያልተለመደ ነው ' ብለውታል።

ሀገሪቱ " ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ ፤ የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት " እያለች መጥራቷ በቋንቋ አጠቃቀም ላይ የታየ ጉልህ ለውጥ ነው ያሉ አልጠፉም።

የአምባሳደሩን ሀርጌሳ ላይ መገኘትን የኮነኑም አሉ። ገለልተኛ አይደሉም ሶማሊያን ይደግፋሉ በሚል።

ሶማሊያውያን ደግሞ በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ አሜሪካን መቃወም ይዘዋል።

" መግላጫው ሶማሌላድ ስለ ተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ምንም ያለው ነገር የለም " በማለት እንዲሁም " ሶማሌላንድ የሶማሊያ ግዛት እንደሆነች ሳይገለጽ መቅረቡ ሌላ ነገር ከጀርባው የያዘ ነው " በሚል ነው የተቃወሙ ያሉት።

#Somaliland
#Hargeisa

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።
 
በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል።

በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል።

ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት ላይ መቆየቱን አሁን ላይ አብዛኞቹ የማጥራት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን አመልክቷል።

በዚህም መሰረት ፥ በተለያዩ ህገወጥ ተግባራት ላይ " እጃቸው አለበት " የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እርምጃ ወደመውሰድ መግባቱን ገልጿል።

በተለይ ዛሬ የብረታ ብረት ስርቆት በመሳሰሉ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን መያዝ መጀመሩን አስታውቋል።

ለጊዜው ምን ያህል ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ በዝርዝር አልታወቀም።

#Tigray
#Mekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፤ አሶሳ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋረጠ 2 ሳምንት አልፏል። የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ አገልግሎት ሊቆም እንደሚችል አሳውቋል። ሆስፒታሉ በየቀኑ ከ400 እስከ 500 ከዞን ፣ ከወረዳ፣ ከአጎራባቹ ኦሮሚያ ክልል ታካሚዎችን ያስተናግዳል። ሆስፒታሉ ከሚሰጠው አገልግሎት አንጻር 24 ሰዓት ሙሉ የማይቋረጥ ኃይል ማግኘት ያለበር ቢሆንም…
🔈 #የሕዝብድምጽ

" ይኸው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ በዋናው ከተማ አሶሳ እና በተለያዩ ወረዳዎች መብራት ከጠፋ ወደ 1 ወር እየተጠጋ ነው። መቼ  ነው ችግሩ የሚፈታው ? ማነው የሚነግረን ? ምንም የሰማነው ነገር የለም። ለበርካታ ቀናት ጨለማ ውስጥ ቁጭ ብለናል። ከዛሬ ነገ መፍትሄ ይሰጠናል ብለን እየጠበቅን ነው። ተሰቃየን የሚመለከታችሁ አካላት ስለፈጠራችሁ መፍትሄ ስጡን !! ህዝቡ ጨለማ ውስጥ ነው መደረግ ያለበት ነገር በፍጥነት ይደረግና ችግሩን ፍቱልን። " - ነዋሪዎች

#TikvahEthiopiaFamilyBG

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እነሆ 500,000 ተጨማሪ የምስጋና ስጦታ፤ በቴሌብር የዕድል ጨዋታ!

በበጀት ዓመቱ በነበረን አስደናቂ ስኬቶች ስለአብሮነትዎ ምስጋና እስከ 250 ሺህ የሚደርስ ኢ-ገንዘብ፣ አይፎን 15 ፕሮማክስ፣ ስማርት ስልክ፣ የዳታ ጥቅልና ኢ-ገንዘብ የሚያሸልሙ 500,000 ስጦታዎችን በቴሌብር ሱፐርአፕ አሰናድተናል!

ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ http://onelink.to/fpgu4m ይጫኑ፤
በየቀኑ አየር ሰዓት ለመሙላት፣ ጥቅል ለመግዛት፣ ለግብይትና ገንዘብ ለማስተላለፍ እየተጠቀሙ ከሐምሌ 5 እስከ 9 ለአምስት ቀናት የሚቆየውን የዕድል ጨዋታ ይሞክሩ!

ለተጨማሪ መረጃ youtube.com/@ethio_telecom ይከተሉ፡፡

ስለ አብሮነትዎ ከልብ እናመሰግናለን!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
@samcomptech

እርሶ ከዘመኑ እኩል መራማድ ከሆነ ምርጫዎ ዘመኑን የዋጁ የላፕቶፕ ምርቶችን አኛ ጋር በተመጣጣኝ ዎጋ ያገኛሉ።

ለቢሮ፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን፣ ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ የተለያዩ ከዉጭ በምናስመጣቸዉ አዳዲስ ላብቶፖች እንታወቃለን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://www.tg-me.com/samcomptech
ቤተሰባዊነት ፣ ተአማኒነት ፣ ገንዘቦቻችን ናቸዉ ! ይምጡ ይሸምቱ!
#Ethiopia

በነዳጅ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መከልከሉ ይታወቃል።

ይኸው ክልከላ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችን እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።

ምንም ዓይነት የሕግ ድንጋጌ ሳይኖር ወይም ግልጽ የሆነ ሕግ ሳይወጣ እና ሕግን የተከተለ ክልከላ ሳይኖር ' ከላይ በወረደ ወይም ተሰጠ ' በተባለ አቅጣጫ ላይ ብቻ በመመሥረት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ መከልከሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችን እያተጓጎለ እንደሆነ ጠቁሟል ኮሚሽኑ።

ኮሚሽኑ ለትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ እንድሂህ ብሏል ፦

- በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከል፣ በሕግ አግባብ ወይም ድንጋጌ የታገዘ አይደለም፡፡

- ለማንኛውም አይነት አገልግሎት የሚውሉ ከባድ የጭነት ተሽከርኮሪዎች፣ የእርሻ ትራክተሮችና ለቱሪስት ማስጎብኛ የሚያገለግሉ አገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎችን መከልከል ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር ነው፡፡

- በግብርና ፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ፣ በሆልቲካልቸር ፣በቱሪዝም ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ በግንባታ እና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ ነው።

- በተለይ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ልዩ ባህሪ የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት እንዲቻል ሚኒስቴሩ ፈቃድ ሊሰጥ ይገባል።


#ReporterNewspaper

@tikvahethiopia
" ክብሯት እና ክብሯን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን ! " - ጆ ባይደን

በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ዴሞክራት ፓርቲያቸውን ወክለው ይወዳደራሉ ተብለው የሚጠበቁት ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የጤናቸው ነገር አሳሳቢ ነው እየተባለ ነው።

" እርጅናም ተጫጭኗቸዋል፣ በትልልቅ መድረኮች የሚነገሯቸውን ነገሮች እየሳቱ ነው ፤ ስለዚህ ምክትላቸው ይተኳቸውና ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ይፎካከሩ " የሚል አስተያየት የሚሰነዝሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።

ባይደን ግን ከጤናቸው ጋር በተያያዘ ለሚነሳው ጥያቄ ፥
- ፍጹም ጤናማ መሆናቸውን ፣
- እንደ ቀድሞው መንቀሳቀስ አቅቷቸው ሥራቸውን መጨረስ ካልቻሉ ብቻ እንደበቃቸው ምልክት እንደሚሆን፣
- አሁን ላይ ምንም ዓይነት የድካም ምልክት እንደሌላቸው ነው የሚመልሱት።

ትላንት በነበረ አንድ የNATO ፕሮግራም የሚዲያ መግለጫ ላይ ፥  የዩክሬኑን ፕሬዜዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪን ለንግግር ሲጋብዙ " ፕሬዝደንት ፑቲን " ብለው መጥራታቸው በሥፍራው የነበረውን ታዳሚ አስደንግጧል።

ዜሌንስኪም ክው ብለው ቀርተዋል።

ወዲያው ግን ጆ ባይደን ፥ " የፑቱን ነገር አሳስቢ ሆኖብን እዛ ላይ ብዙ ስለቆየሁ ነው ፤ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ " ሲሉ ስህተታቸውን አርመዋል።

ዜሌንስኪ " እኔ እሻላለሁ ! (ከፑቱን ማለታቸው ነው) " ሲሉ ተደምጠዋል። ባይደንም ፥ " በእርግጥም በደንብ ትሻላለህ " ሲሉ መልሰዋል።

ከዚህ ቀጥሎ በነበረ አንድ መግለጫ ላይ ደግሞ የገዛ ምክትላቸውን ካማላ ሀሪስን " ምክትል ፕሬዝዳንት ትራምፕ " ብለው ሲጠሩ በርካቶች በድንጋጤ ተመልክተዋቸዋል።

በቅርብ ከሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበረ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ክርክር ወቅት ያሳዩት አቋምም ምርጫውን ለማሸነፍ አጠያያቂ ሆኖ ነበር።

የ81 ዓመቱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ግን " ደህና ነኝ ምርጫውንም አሸንፋለሁ " ባይ ናቸው።

ክስተቶቹን የሚያሳይ ቪድዮ ከላይ ተያይዟል።

#BBC
#CNN

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa.ministry.et/account#/student-result ላይ በመግባት መመልከት ይችላሉ " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ውጤቱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ አድርገዋል።

በዚሁ መሰረት የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።

የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ 85,219  በመንግስት እና በግል ት/ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

ተማሪዎች https://aa.ministry.et/account#/student-result ላይ በመግባት መለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ።

በቀጣይ ጥቂት ቀናት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተመሳሳይ ይፋ የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል።

#AddisAbabaEducationBureau

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የሕዝብድምጽ " ይኸው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ በዋናው ከተማ አሶሳ እና በተለያዩ ወረዳዎች መብራት ከጠፋ ወደ 1 ወር እየተጠጋ ነው። መቼ  ነው ችግሩ የሚፈታው ? ማነው የሚነግረን ? ምንም የሰማነው ነገር የለም። ለበርካታ ቀናት ጨለማ ውስጥ ቁጭ ብለናል። ከዛሬ ነገ መፍትሄ ይሰጠናል ብለን እየጠበቅን ነው። ተሰቃየን የሚመለከታችሁ አካላት ስለፈጠራችሁ መፍትሄ ስጡን !! ህዝቡ ጨለማ ውስጥ ነው…
#Update

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አግኝቷል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ላለፉት 17 ቀናት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ እንደነበር ገልጿል።

ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገቡ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይም ተደጋጋሚ ስርቆት ስለሚፈፀም የተቋረጠውን ኃይል መልሶ የማገናኘት ሥራውን ፈታኝ አድርጎት እንደነበር አስታውቋል።

ለቀናት መስመሩን ለማገናኘት ጥረት ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ተሳክቷል።

ከቀኑ 9:05 ሰዓት ጀምሮ አካባቢዎቹ ኤሌክትሪክ አግኝተዋል።

" በአንድ አካባቢ የሚፈፀም የኃይል መሰረተ ልማት ስርቆት ተፅዕኖው ሰፊ ነው " ያለው መ/ቤቱ " በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኃይል መቋረጥ በግልፅ የታየው ይኸው ነው " ብሏል።

በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ህብረተሰቡ እና የሚመለከታቸው የመስተዳድር አካላት ለመሰረተ ልማቱ ጥበቃ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#EEP

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ ! " - ሩቶ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በመበተን ሚኒስትሮቻቸውን ከስልጣን ያባረሩት ሕዝቡ ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑን አሳውቀዋል። ሩቶ ፥ " ኬንያውያንን በመስማት ካቢኒዬን መርምሬ ነው የወሰንኩት " ብለዋል። " አዲስ እና ሰፋ ያለ መንግሥት ለመመሥረት ከሕዝቤ ጋር ውይይት አደርጋለሁ " ሲሉም አሳውቀዋል።…
የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥራቸውን ለቀቁ።

በሀገሪቱ በተቀጣጠለው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ ጠንካራ ትችት የተሰነዘረባቸው የፖሊስ አዛዥ ጃፌት ኮሜ በዛሬው ዕለት የስንብት ደብዳቤ አስገብተዋል።

የኬንያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤትም የኮሜን የስንብት ደብዳቤ ፕሬዝደንት ዊልያል ሩቶ መቀበላቸውን አረጋግጧል።

ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በቦታቸው ምክትል የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ዳግላስ ካንጃ መተካታቸውን አስታውቋል።

በሀገሪቱ ላይ የተካሄደውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ያደራጀው ጀነሬሽን Z በአጭሩ ጄን Z የተሰኘው የኬንያ ወጣቶች ስብስብ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል ያሉት የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥልጣናቸውን እንዲቀቁ ግፊት ሲያደርግ ነበር።

ሕዝባዊ ተቃውሞ የበረታባቸው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ትላንት ካቢኒያቸውን መበተናቸው ይታወሳል።

#DW
#Kenya

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አካል ጉዳተኛ በመምሰል ስትለምን የነበረች ተጠርጣሪ ከእነ ግብረአበሯ መያዟን አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቀን እስከ 500 ብር ድረስ እንደሚያገኙ ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዋ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይኖራት ነው አካል ጉደተኛ በመምሰል ወገቧን በጎማ በማሰር ዊልቸር ላይ በመሆን ስትለምን ትላንት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው " #መገናኛ " አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ የተያዘችው።

ግለሰቧን ከቦታ ወደ ቦታ ሲያንቀሳቅሳት የነበረው ተጠርጣሪም ተይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ ዊልቸሩን በቀን 35 ብር ተከራይተው ለ8 ወር እንደተጠቀሙና በቀን እስከ 500 መቶ ብር እንደሚያገኙ ከሰጡት ቃል ማወቅ እንደተቻለ ፖሊስ አስረድቷል።

ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሳይኖርባቸው ጉዳተኛ በመስምሰል የሚያታልሉ እንዳሉ ህብረተሰቡ ሊገነዘብ ይገባል ሲል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
" በታሪኬ ከታክስ በፊት ከፍተኛውን ትርፍ አግኝቻለሁ " - ንግድ ባንክ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2016 በጀት ዓመት 135.4 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን አሳውቋል።

በዚህ ዓመት ከታክስ በፊት የተገኘው 25.6 ቢሊዮን ብር ትርፍ እንደሆነ እና በባንኩ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡን ገልጿል።

የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ1.17 ትሪሊዮን ብር የተሻገረ መሆኑን ተናግሯል።

የባንኩ የደንበኞች ቁጥር ደግሞ ከ45 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ አመልክቷል።

የተበላሸ ብድር ክምችቱ 2.6% መደረሱም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፥ ከ218 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ማቅረቡን ጎልጾ 91% ወይም ብር 198 ቢሊዮን የሚበልጠው ለግሉ ሴክተር የተለቀቀ ብድር እንደሆነ አሳውቋል።

#CBE #Ethiopia

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአቢሲንያ ቪዛ ካርድዎን ዲጂታል ቪዛ ካርድ ለማድረግ ቪድዮውን ይመልከቱ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#DigitalVisacard #Visa #ApolloVisacard #BoAVisacard #Visacard #Digitalethiopia #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam አገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል፡፡ ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት ነው እየተሰጠ ያለው። የመጀመሪያ ዙር ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል። ትላንት ሐምሌ 2 በቀድሞ ትምህርት ካሪኩሉም ትምህርታቸውን የተከታተሉ የትግራይ ክልል ተማሪዎች አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና…
#National_Exam

ላለፉት 3 ቀናት በወረቀት እና ኦንላይን ሲሰጥ የቆየው የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

Via @tikvahuniversity
2024/09/30 04:30:21
Back to Top
HTML Embed Code: