Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz • “ የውሃ አቅርቦት ተቋርጦ ችግር ላይ ወድቀናል ” - ነዋሪዎች • “ የመብራት ችግር ነው ” - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ • “ የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው ” - የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት  በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማን ጨምሮ ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ…
#BenishangulGumuz

° “ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ 3 ወር ሆነው። ጨለማ ውስጥ እየኖርን ነው” - የወምበራ ወረዳ ነዋሪዎች

° “ ከወረዳው መንግስት ጋር እየተየጋገርን ነው፤ በቅርቡ እንሰራዋለን ” - የደብረ ዘይት ማዕከል

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ ወምበራ ወረዳ ደብረ ዘይት ከተማ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ ጨለማ ውስጥ ለመኖር መገደዳቸውን ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

“ ኤሌክትሪክ ከተቋረጠ 3 ወር ሆነው። ጨለማ ውስጥ እየኖርን ነው። የፋሲካ በዓል አካባቢ ሁለት ቀን በርቷል ከዚያ በኋላ ምንም የለም ” ብለዋል።

ችግሩ ፦
-  በኑሯቸው ላይ ፈተና እንደሆነባቸው፣
- ተማሪዎች ለመማር፣ ፕሮጀክቶችን ለመስራት እንደተቸገሩ፣ 
- ለስልክ ቻርጅ በጀኔሬተር 20 ብር እንደሚከፍሉ፣ 
- በመስሪያ ቤታቸው ጀነሬተር፣ በቤታቸው Solar Energy ስላላቸው ባለስልጣናቱ ለጉዳዩ ቸልተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

“ ግብር እየከፈልን መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ አለመጠቀም ግን አግባብነት የሌለው ቅሬታን የሚያስነሳ ጉዳይ ነው ” ብለዋል።

በወረዳው የታላቁ ህዳሴ ግድቡ በቅርበት ቢገኝም ተጠቃሚ ባለመሆናቸው የሚመለከተው አካል ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

አቶ የኔሰው የኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ዘይት ማዕከል ኃላፊ አገልግሎቱ ለምን እንደተቋረጠ ጠይቀናቸው በሰጡት ምላሽ፣ ቡለን ላይ ኤሌክትሪክ ስለተቋረጠ መሆኑን አስረድተዋል።

"እንደ ወንበራ ደብረ ዘይት ቅድሚያ የቡለን ማዕከል ራሱን የቻለ አለ። እሱ ከበራ በኋላ ነው እኛ ማብራት የምንችለው። ቡለን ከበራ ይበራል" ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ "ከወረዳው መንግስት ጋር እየተየጋገርን ነው፤ በቅርቡ እንሰራዋለን" የሚል ምላሽ ተሰጥተዋል።

የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ከበደ ሰሞኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ "የተቋረጠው ኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው" ብለው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ “ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው። ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት፤ ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው እየመጡ የሚሰሩት። ይህ ችግር ግን የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ፤ ያንን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት። ” - ዶክተር በሀሩ በዛብህ (የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር የቦርድ አባል - ለቲክቫህ…
#EMA

“ ሀኪሞች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው፤ ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት ” - የኢትዮጵያ ህምክምና ማህበር

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር (EMA) በየዓመቱ ሰኔ 25 ቀን የሚከበረውን “ 7ኛውን የሀኪሞች ቀን ” በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተከብሮ ነበር።

በዚህም በዘንድሮው ' የሀኪሞች ቀን ' ከጌራ የቤት ለቤት ህክምናና የሀኪሞች ቢሮ ተቋም ጋር በመሆን 2,000 ለሚጠጉ የማህበረሰብ ክፍሎች የቤት ለቤትና የጎዳና ላይ ነጻ የህክምና ለመስጠት ማቀዱን አመላክቷል።

ይኸው የነጻ ህክምና ከሐምሌ 1 /2016 ጀምሮ ነው የሚሰጠው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ፣ ከ34 ዓመታት ጀምሮ በአጥንት ቀዶ ህክምና እያገለገሉ የሚገኙትን የማኀበሩ የቦርድ አባልና የአባላት ጉዳይ የሚከታተሉት ዶ/ር በሀሩ በዛብህን ጠይቋል።

እሳቸው በሰጡት ቃል፣ “ ሀኪሞች ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር አለባቸው፤ ኩሽና ተከራይተው ነው የሚኖሩት። ቤት እንኳ የላቸውም። በአውቶብስ ተጋፍተው ነው መጥተው የሚሰሩት ” ብለዋል።

“ ይህ ችግር የጤና እከል የደረሰበትን ማህበረሰብ ከማገልገል አልከለከላቸውም ” ያሉት ዶ/ር በሀሩ፣ “ ያን እያደረጉ ግን ሲታመሙ እንደ ሞያተኛ ሳይሆን ለምነው ነው የሚታከሙት ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ መብራት ኃይል ለአባላቱ መብራት፣ ቴሌ ለአባላቱ የአየር ሰዓት፣ ውሃና ፍሳሽ ለአባላቱ ውሃ ይሰጣሉ። የእኛ ጤና ሲታወክ እንኳ ምንም አይሰጥም። በህግም የተቀመጠ ነገር የለም ” ሲሉ አማረዋል።

“ የሥራ ሁኔታዎች ራሱ አልተመቻቹም ፤ ከሌላ አገር ጋር ሲገጻጸር እየሰራን የሚከፈለን እራሱ ውስን ነው ” ብለዋል።

“ መሬት እንኳን ቢሰጠን ምን ችግር አለው ? መኖር ነው ያቃተን። የሚከፈለን ገንዘብ በጣም ውስን ነው ” ሲሉ አክለዋል።

በዘርፉ የበዙ ችግሮች ከመኖራቸው አንጻር በርካታ ሀኪሞች ከአገር ለመውጣት እየተገደዱ መሆኑን ገልጸው፣  መንግስት ልቦና ሰጥቶት ለሚስተዋሉ ችግሮች ሁሉ መፍትሄ እንዲሰጥ በማኀበሩ ስም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ህክምና ማኀበር / EMA ከተመሠረተ 75 ዓመታትን እንዳስቆጠረ፣ በኢትዮጵያ ከ15,000 እስከ 20,000 ሀኪሞች እንዳሉ ተመላክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🚨 " የበይነ መረብ (ኦንላይን) ተፈታኞች በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ፈተና በበይነ መረብ (ኦንላይ) እንዲሁም በወረቀት እንደሚሰጥ በዛሬው ዕለት በድጋሚ አሳወቀ። በሁለቱም መንገድ ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅት ተደርጓል ብሏል። ትላንት እና ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ያሉ አንዳንድ…
#AddisAbaba #NationalExam

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም ” - ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪ ወላጆችና ከተማሪዎች ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ስለተጠየቀበት የበየነ መረብ (ኦንላይን) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱን ጠይቋል።

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምን አሉ ?

“ ፈተና በሁለት አይነት መልኩ (በኦንላይንና በወረቀት) ይሰጣል።

በኦን ላይን የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲ ላይ ተመድበው የነበሩ አብርሆት ላይብረሪና ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ይሆናሉ።

የተቀሩት ግን በሁሉም በግልም በመንግስም መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩ ት/ቤቶች ሆኖ በተመደቡበት (ድልድል የወጣላቸው ት/ቤቶች ያውቃሉ) መሠረት ፈተናውን በወረቀት ይወስዳሉ።

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱት፦
- በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ 
- በሲቪል ሰርቪስ
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 
- በአዲስ አበባ ሳይንሰና ቴክኖሎጂ
- በጳውሎስ ሚሊኒየም የተመደቡ በዚያ ይወስዳሉ።


እንዲሁም፣ በአብርሆት ላይብረሪ ላይ የተመደቡ ተማሪዎች፣ የሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኦንላይን ይወስዳሉ።

የቀሩት ግን በሌላ መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩት ስለታጠፈ በወረቀት ይወስዳሉ።

በወረቀት የሚወስዱት ዩኒቨርሲቲ ነው የሚገኙት በባለፉት ሁለት አመታት እንደተሰጠው ማደሪያቸውም፣ መዋያቸውም፣ መፈተኛቸውም እዛው ይሆናል። አድረው ሲጨርሱ ነው የሚወጡት።

በኦንላይን የተመደቡት ግን ውሎ ገብ ነው። ተፈትነው ወደ ቤታቸው ሂደው አድረው ተመልሰው በጠዋት መጥተው ይፈተናሉ። ” ብለዋል።

የተፈጠረው ውዝግብ ምንድን ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፥ “ የተፈጠረ ነገር የለም። በድብልቅ መንገድ እንደምንጥ ታሳቦ ነበረ። እሱን ነበር ስንለማመድ የነበረው ” ነው ያሉት።

“ አሁን More እርግጠኛ በተኮነበት መፈተኛ ጣቢያ (ከላይ በተገለጹት) ብቻ ይሰጣል። ” ሲሉ አክለዋል።

ትምህርት ቤቶች “ ቀርቷል ” ሲሉ ተስተውለዋል፤ ታዲያ መረጃውን ከየት አግኝተውት ነው ? ቢሮው ትዕዛዝ አውርዶ ነበር ? ስንል ኃላፊውን ጠይቀናል።

ዶ/ር ዘላለም ፥ “ በዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ጣቢያቸዎች እንደሚሰጥ ነገር ግን ሌሎች ጣቢያዎች የነበሩት፣ በእነርሱ ላይ ካልሆነ በስተቀር ' ቀርቷል ' ተብሎ የተሰጠ መግለጫ አልነበረም ” ብለዋል።

አክለው፣ “ ለሙከራ ስንሞክርባቸው የነበሩ እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ተማሪዎችና ቤተሰብ ላይ እንግልት እንዳይሆን እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ቀንሰናል ” ያሉት ኃላፊው፣ “ በእርግጠኝነት ሊፈጸሙባቸው ተብሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ የተወሰኑት ላይ ግን ተወስኗል ” ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው እንደቀረ ያስተላለፈው መልዕክት ነበር ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ትምህርት ሚኒስቴር እኮ በገጹ ላይ አስታውቋል እንዳልቀረ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም። በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተይዘው የነበሩት በተለያዩ ምክንያቶች ተቀንሰዋል ” ብለዋል።

ቢሮዎ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ጻፈው ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ደብዳቤ (ከላይ ተያይዟል) የቢሮ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ፥ “አዎ። ትክክል ነው !! ” ብለዋል።

“ አሁን ባልናቸው ጣቢያዎች ማለት ነው። በፊት በ153 ጣቢያዎች ብለን ነበር ይዘን የነበረው አሁን ግን በእርግጠኝነት ይሳካል የተባለበት ቦታ ከላይ የተጠቀሱት ጣቢያዎች ብቻ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም በተቀመጠው መርሀ ግብር መሠረት ተማሪዎች ከምንም አይነት ውዢምብር ራሳቸውን ጠብቀው ከቢሮውና ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወርዱ መመሪያዎች ብቻ ተረጋግተው እንዲፈተኑ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
" ልጆቻችን ተረበው ማልቀስ የለብንም ! "

" የአንድ ዓመት ውዙፍ ደመወዝ አልተከፈለንም "  ያሉ የቀድሞ የትግራይ ኃይል አባላት ድምጻቸውን ለማሰማት ሰልፍ ወጡ።

የቀድሞ አባላቱ ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ ሰላማዊ ስልፍ አካሂደዋል።

በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- " የሰማእታት ቃል የሚከበረው የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸው በማገዝ ነው ! "
- " መስዋእት ስለከፍልንና ከሰራዊት ስለተሰናበትን ደመወዛችን ማጣት አይገባንም ! "
- " ልጆቻችን ተረበው ማልቀስ የለብንም ! "
- " ፍትህ ይሰጠን ! "
- " መብታችን ይከበርልን ! "
- " ድምፃችን ይሰማ ! " የሚሉና ሌሎች መፈክሮች አስምተዋል። 

ከሰላማዊ ሰልፈኞቹ አንዱ የሆነው ፀጋይ ገ/ስላሴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጀምሮ ለሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያችን አቅርበን የተሰጠን ምላሽ የለም " ብሏል።

" ፍትሃዊ ጥያቄያችን እስኪመለስ በሰላማዊ መንገድ ሳንታክት እንጠይቃለን " ሲል አክሏል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥያቄያቸው ለማቀረብ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ያመሩ ሲሆን በስብሰባ ምክንያት ጥያቄያቸውን ሰምቶ ያስተናገዳቸው የመንግስት የስራ ሃላፊ እንዳላገኙ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
ዲያቆን ወልደየሱስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ቋሚ ዲያቆን የነበሩት ዲያቆን ወልደየሱስ ማኔዶ ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸውን ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

ዲያቆን ወልደየሱስ በሆሳዕና ሀገረስብከት ሰዳማ የካታኪስት ማዕከል ለካታኪስቶች እና ለወጣቶች በሚሰጡት ሀይማኖታዊ ትምህርት እና ስልጠና ይታወቃሉ።

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ቋሚ ዲያቆን የነበሩም ሲሆን ባደረባቸው ህመም ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በዲያቆን ወልደየሱስ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆች መፅናናትን ተመኝቷል።

@tikvahethiopia
#የጤናባለሞያዎች

➡️ " የ6 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ ካለመከፈሉ በላይ ደመወዝም በአግባቡ ስለማይከፈል ሰራተኛው ስራ እየለቀቀ ነው " - የሀላባ ዞን አቶቴ ኡሎ ወረዳ የጤና ባለሞያዎች

➡️ " የ4 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ ነው ያልተከፈላቸው እንከፍላለን ፤ የሰራተኛ መልቀቅ ግን በስራችን ላይ ችግር አልፈጠረብንም " - የወረዳው ጤና ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን አቶቴ ኡሎ ወረዳ ያሉ የጤና ባለሙያዎች የ6 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ አለመከፈሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ክፍያው ወደ 2017 ከተሸጋገረ እንደሚቃጠልባቸው ባለሞያዎቹ አመልክተዋል።

ጥያቄያቸውን በሚጠይቁበት ጊዜ ጥያቄያቸዉ ወደፖለቲካ እየተጠመዘዘባቸው መሆኑን በመግለፅ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

" በደሞዝ መቆራረጥና ትርፍ ሰአት ስራ ክፍያ ተማሮ የሚለቀቀው ሰራተኛ ለአካባቢው ባለስልጣናት 40 እና 50 ሽህ ብር ተቀብሎ ለመቅጠር መንገድ ከፍቶላቸዋል " የሚሉት ሰራተኞቹ አሁን ላይ " የሰራንበትን ገንዘብ መጠየቅ እንደነውር ተቆጥሮ በደመወዝ በትርፍ ስራና በጉሸማ እየተሰቃየን ነው " ብለዋል።

ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የጤና ባለሙያ በሰጡት ቃል ፥ " በደመወዝ መዘግየትና በትርፍ ሰአት ክፍያ ችግር ምክኒያቶች እኔ በምሰራበት ሆስፒታል ብቻ ከላብራቶሪና ከኢመርጀንሲ አስተባባሪዎች እስከ ዶክተሮች ድረስ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከአምስት በላይ ሰዎች ለቀዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

ነገር ግን " እንዲህ ያለው ከፍተኛ ክፍተት አመራሩን አያሳስበውም " የሚሉት ሰራተኞቹ " እንዲህ ያለው አሰራር ህሊናህን እረፍት ከመንሳቱ በላይ ቅዳሜ እና እሁድ ሰው ሲያርፍ ወገብህ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ የሚጠበቅብህ በላይ ሰርተህ ክፍያዉ ሲቀር ምን ይሰማሀል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በርካታ የጤና ባለሙያዎች አሁን ላይ ኑሮ በእጅጉ መክበዱን ተከትሎ ከ5 እና 6 አመት ትግልና ሙከራ በኋላ ኑሮ ሲያሸንፋቸው ወደቤተሰብ መመለስን አማራጭ እያደረጉ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ ፤ " አሁን ላይ አኗኗራችን ሆነ የምናገኘዉ ገቢ ከቀን ሰራተኛ በታች ሆኗል " ብለዋል።

ባለሙያዎቹን ቅሬታ ይዘን ያነጋገርናቸው የአቶቴ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽህፍተ ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ኬሪ ፥ " ያልተከፈለ የትርፍ ሰአት ክፍያዉ የ6 ወር ሳይሆን የ4 ወር ነው " ብለዋል።

" የሰራተኛዉን ወርሀዊ ደሞዝ በጊዜዉ እየከፈልን ነው " የሚሉት ኃላፊው " የትርፍ ሰአት ክፍያውንም ለማጠናቀቅ ከሚመለከተዉ አካል ጋር እየተነጋገርን ነው" ሲሉ አክለዋል።

" ክፍያው ወደ 2017 ዓ/ም ከተሸጋገረ ሊቃጠል ይችላል " ለሚባለው ሀሳብ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በደመወዝ እና በትርፍ ሰአት ክፍያ ምክንያት ሰራተኛ ይለቃል የሚለውን ሀሳብ በተመለከተ " ሰው የተሻለ ሲያገኝ ነው የሚሄደው ፤ በዚህም ስራ ላይ የታየ ክፍተት የለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ወደ 2017 ከተሸጋገረ ይቃጠላል " የተባለውን የ6 ወር ክፍያና የሰራተኛውን ስራ መልቀቅ እንዲሁም አጠቃላይ በክልሉ ያሉ የህክምና ሰራተኞችን ክፍያ በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ወንጋሮ ጥያቄ እንድናቀርብላቸው እድል ቢሰጡንም በስራ መደራረብ ምክኒያት ምላሽ መስጠት አልቻሉም።

በቀጣይ አነጋግረናቸው ምላሹን የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
STEMpower ከ Embassy of Finland Ethiopia እና IBM በመተባበር Digital Skills Training for Woman, ትጋት በተሰኘ ፕሮግራም ከዚህ ቀደም ያወጣነውን ማስታወቂያ ተመልክተው በርካቶች ተመዝግበው የonline ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ፣ ተመዝግበዉ ስልጠናውን ያልጀመሩ ሰልጣኞች በድህረ ገጻችን https://www.stempower.org/sp-efe-ibm-digital-skills-online-training ያወጣነዉን ዝርዝር በመመልከት ከ IBM SkillsBuild የተላከላችሁን የ ኢሜል መልዕክት በመክፈት የsign-up ሂደቱን በማጠናቀቅ ስልጠናዉን መጀመር ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን https://www.tg-me.com/+YTpmWcxvjcQ0MWZk ይቀላቀሉ
#SafaricomEthiopia

የ 400,000ብር ሽልማት አሸናፊ ይሁኑ! #1Wedefit የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok  ላይ እንፖስት
📲 የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ገጽ ታግ እናድርግ
🏷#የምትኖሩበት ከተማ አድራሻ እና #1Wedefit የሚለውን ማስገባት እንዳንረሳ

እንዝፈን፣ እንወዳደር፣ እንሸለም

#SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether #DigitalMusicChallenge
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎንደር ° “ ውሃ ካጣን ከወራት በላይ ሆነን፤ እንኳን ለመታጠብ ለመጠጥም አልተገኘም ” - የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ° “ ጉድጓድ ስናስቆፍር በ4 ወራት ይደርሳል ብለን አንድ ዓመት ከ8 ወራት ወስዷል ” - የከተማው ውሃና ፍሳሽ  በአማራ ክልል የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ኢንተርን ሀኪሞች፣ የውሃ ችግር እንደፈተናቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። የከተማው ነዋሪዎች…
#Update

“ ‘ የ24 ሰዓት ሙሉ የውሃ አገልግሎት እንሰጣለን ’ የሚለው ውሸት ነው ” - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቅሬታ አቅራቢዎች

“ ሆስፒታል ማለት ለተማሪ አይደለም የምንሰጠው። ሆስፓታሉ ማለት ህክምና የሚካሄድበት ነው ” - የከተማው ውሃና ፍሳሽ ቢሮ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ኢንተርን ሀኪሞች እና ተማሪዎች የውሃ አቅርበት ከተቋረጠ ከወር በላይ ሆኖት እያለ የከተማው ውሃና ፍሳሽ ሰሞኑን የሰጠው ማብራሪያ ትክክል አለመሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በጎንደር ከተማ የውሃ አቅርቦት ችግር እንዳለ ነዋሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ኢንተርን ሀኪሞች ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅነው የጎንደር ውሃና ፍሳሽ ቢሮ ፥ የከተማው ነዋሪዎች ቅሬታ ትክክል እንደሆነ አምኖ ለመፍትሄው መንግስት ርብርብ እንዲያደርግ አሳስቦ ነበር።

ቢሮው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ላይ የተነሳውን ቅሬታ በተመለከተ በሰጠው ምላሽ ግን፣ “ሆስፒታል ላይ ግን 24 ሰዓት ነው የምንሰጠው። መብራትና አጠቃላይ ምርት ቆሞ ካልሆነ አይቋረጥም” ነበር ያለው።

የዩኒቨርሲቲው የኢንተርን ሀኪሞቹ በሰጡት የአጸፋ ቃል፣ ‘የ24 ሰዓት የውሃ አገልግሎት እንሰጣለን’ የሚለው ውሸት ነው። እውነታው ውሃ የለም” ሲሉ ወቅሰዋል።

ውሃ በግቢ ከጠፋ ከወር በላይ እንደሆነው ገልጸው፣ እንኳን ለመጸዳጃ ለመጠጥ እንደተቸገሩና በቦቴ የሚቀርበውም አነስተኛ እንደሆነ አስረድተዋል።

የተነሳውን ቅሬታ በተመለከተ በድጋሚ የጠየቅናቸው የከተማው ውሃና ፍሳሽ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ወርቅነህ አያል፣ "ሆስፒታል ማለት ለተማሪ አይደለም የምንሰጠው። ህክምና ለሚካሄድበት ነው" ብለዋል።

" በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በስኬጁል ነው የሚሰጣቸው ሌላው ማህበረሰብ በወር እያገኘ ለሀኪም 24 ሰዓት ልሰጠው አልችልም። ሆስፒታል ግን 24 ሰዓት ህክምና የሚካሄድበት ስለሆነ 24 ሰዓት ሙሉ ነው አሁንም የምንሰጠው" ነው ያሉት።

" ለሀኪሞች የራሳቸው ፕሮግራም አላቸው እንደሌላው ማህበረሰብ አይደሉም በእርግጥ በሳምንት፤ በ3፤ በ4 ቀናት ነው። ድሮ 24 ሰዓት ነበር የሚሰጣቸው። አሁን ግን የውሃ እጥረት ስላለ አንችልም " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update (ቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ/ም) ስለ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ታጋች ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ? በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ፣ የግቢው የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት እና የታጋች ቤተሰብን ምን አዲስ አለ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬም ጥያቄ አቅርቧል። የታጋች ቤተሰቦች አጋቾቹ ወደ 20 የሚሆኑ ታጋቾችን ከትላንት ጀምሮ ወደ ማያውቁትና ጫካ በበዛበት…
አሜሪካ ምን አለች ?

" ለገንዘብ ተብሎ ተማሪዎች እና ንጹሃንን ማገት ሊቆም ይገባል " - አሜሪካ

አሜሪካ አዲስ አበባ ባሉት አምባሳደሯ ኢርቪን ማሲንጋ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ  ፥ " ለገንዘብ ተብሎ ተማሪ እና ንጸሃንን ማገት ሊቆም ይገባል " ብላለች።

አምባሳደር ማሲንጋ ፦

" ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በተደጋጋሚ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች እየተፈጸሙ ያሉ እገታዎች የተራዘመ ግጭት ወንጀለኞችን እንዳደፋፈረ ፤ የህግ የበላይነትንም እንዳዳከመው ያሳያል።

ለገንዘብ ሲባል በተማሪዎች እና ንጹሃን ላይ የሚፈጸም እገታ ሊቆም ይገባዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ከ100 ተማሪዎች እና መንገደኞች ለገንዘብ ሲባል ታግተዋል። "


በባለፈው ሳምንት አብዛኞቹ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆኑ ሌሎች መንገደኞችን ጨምሮ " ገብረ ጉራቻ " ላይ መታገታቸው ይታወሳል።

#USA
#Ethiopia

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

በኮሪደር ስራ ምክንያት ፦

➡️ ከፊጋ መስመር ወደ ቀኝ ታጥፎ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ

➡️ ከጃክሮስ መስመር በኩል መብራቱን ተሻግሮ ወደ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ

➡️ ከኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስቴር ጫፍ ታጥፎ ወደ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ

ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት አንስቶ ሙሉ ቀን እና ምሽት ለማንኛውም ተሽከርካሪ ዝግ እንደሆኑ ተገልጿል።

ሌላው ፤ ከአያት ወደ መገናኛ እና ከመገናኛ ወደ አያት ቀጥታ ማለፍ እንጂ አደባባዩን መዞርም ሆነ ማቋረጥ የተከለከለ ነው ተብሏል።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙም መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው ከአ/አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
ግብር ለመክፈል መጉላላት ታሪክ ሆኗል!!

ከሥራ ገበታዎ ላይ ሳይነሱ በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ወይም *127# ባሉበት ሆነው በምቾት ይክፈሉ!

ሥራን በክብር
ግብርዎን በቴሌብር!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት በ https://www.tg-me.com/EthiotelecomChatBot 24/7 ያግኙን !

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia
#RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው በኦንላይን እና በወረቀት እየተሰጠ ነው።

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን መስጠት ተግባራዊ ተደርጓል።

በመቐለ ፣ አኽሱም ፣ ዓዲግራት ፣ ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን ብሔራዊ ፈተና አጠቃላይ ከ54,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፈተናው ከሌሎች ክልሎች ለምን ቀድሞ ጀመረ ?

ፈተናውን የሚወስዱት በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተማሪዎች ናቸው።

በ2012 ዓ/ም የ10ኛ ክፍል የነበሩ (code 01) ብዛታቸው ከ31 ሺህ የሆኑ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሀምሌ 2 እስከ 5 /2016 ዓ/ም ፈተና ወስደው ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

ከኮረም ፣ አላማጣ ፣ ዛታ ፣ ኦፍላ ፣ ራያ ጨርጨር ፣ ራያ ዓዘቦ፣ ማይፀብሪ፣ ላዕላይና ታሕታይ ፀለምቲ ሆኖው ትምህርታቸው ሲከታተሉ የነበሩ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሀምሌ 3 አስከ 5 /2016 ዓ/ም ተፈትነው ሀምሌ 6 ና 7 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ተጉዘው ከሀምሌ 9 እሰከ 11/2016 ዓ/ም ተፈትነው ሀምሌ 12 እና 13 ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

በ2012 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል የነበሩ ( Code 07) የሶሻልና የተፈጥሮ ሳይንስ ብዛታቸው ከ23 ሺህ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ሀምሌ 6 እና 7 ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው ከሀምሌ 9 አስከ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ፈተና ወስደው ሀምሌ 13 እና 14 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ።

#TikvahEthiopia
#TigrayEducationBureau

@tikvahethiopia
2024/09/29 22:30:14
Back to Top
HTML Embed Code: