Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ሰምቻለሁ " - ጸጋ በላቸው " ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለኔ አዲስ ነው " - ወ/ሮ ወይንሸት ብርሀኑ በሀዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ከሆነችዉ ጸጋ በላቸዉ ጋር በተያያዘ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ  የነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " ለብዙዎች አስተማሪ ይሆናል " በተባለ መልኩ የ16 አመት ጽኑ እስራት…
#Update

" ውሳኔዉ መስተካከሉ አስደስቶኛል ጥንካሬም ሆኖኛል " - ጸጋ በላቸዉ

" የይግባኝ ዉሳኔዉን ተከትሎ ፍርዱ ወደ 10  መቀነሱ ልክ አልነበረም " - የክልሉ ዋና ዐቃቤ ህግ


• ግለሰቡ በ14 ዓመት ከ6 ወር እስራት እንዲቀጣ ተፈርዷል።

በሀዋሳ ፥ የዳሽን ባንክ ሰራተኛዋን ጸጋ በላቸዉ ላይ የጠለፋ ወንጀል የፈጸመዉ የጸጥታ አባሉ ምክትል አስር አለቃ የኋላመብራቱ  ወልደማርያም የጠየቀው ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቶ ፍርዱ ከ16 አመት ወደ 10 መውረዱ ተሰምቶ ነበር።

በወቅቱ በዉሳኔዉ ያዘነችዉ ተበዳይ ጸጋ በላቸዉ ቅሬታ ውስጥ መግባቷን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ ያሳለፈዉ ውሳኔ አግባብ አለመሆኑንና ቅጣቱ በጣም እንዳሳመማት ገልጻ  ቅሬታ ማቅረቧን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህን የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሳኔ በመቃወም ይግባኝ የጠየቀዉ የክልሉ ዐቃቤ ህግ ቅጣቱ መውረዱ ከህግ አንጻር አግባብ አይደለም ብሎ በመከራከር የቅጣት ማቅለያውን ውድቅ በማድረግ ቅጣቱ ተስተካክሎ የ14 አመት ከ6 ወር ውሳኔ ተሰጥቷል።

በዚህ የፍርድ ሂደት አስተያየቷን በመልእክት ያጋራችን ወይዘሪት ጸጋ በላቸዉ በፍርዱ መስተካከል  ደስታ እንደተሰማትና ይህም  ጥንካሬ  እንደሚሰጣት ገልጻልናለች።

" እንደኔ አይነት ጉዳት የደረሰባችሁ እህቶች ሁሉ ወደህግ በመሄድ መጠየቅን አትፍሩ " የምትለው ጸጋ ፥ ከመጀመሪያውም በህግ ላይ እምነት እንደነበራት ተናግራለች።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ኃላፊው አቶ ማቶ ማሩ ፥ " ምንም እንኳን ሚዲያዎች ለዚህ ኬዝ የሰጡት ትኩረት ጉዳዩን ታዋቂ ቢያደርገውም ክልሉ ለሴት ልጅ ጥቃት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ በመሆኑ በርካታ ጠንካራ ውሳኔዎች ተላልፈዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህ የጸጋ በላቸዉ ኬዝ ማህበረሰቡን ያስተምራል ለተጎጅዋም ፍትህ ይሰጣል ብለን ስንከታተለዉ የነበረ ጉዳይ ከመሆኑ በላይ ድርጊቱን የፈጸመዉ ግለሰብ ማህበረሰብ ይጠብቃል ተብሎ ኃላፊነት የተሰጠዉ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተነው ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ማቶ ከወራት በፊት የተሰጠውን የይግባኝ ውሳኔ ህጋዊ ድጋፍ የለውም ብሎ በመቃወም የክልሉ ዐቃቤ ህግ ፍርዱ እንዲስተካከል የጣረው ለዚህ ነበር  ብለዋል።

ቅጣቱ ከ10 ወደ 14 አመት መስተካከሉን ገልጸው " እንደክልል በዚህ አመት ብቻ ከ256 በላይ ሴቶችንና ህጻናትን የተመለከተ ኬዝ በትኩረት ይዘን እየሰራንበት ነው በተወሰኑት ላይም አስተማሪና  ጠንካራ ውሳኔዎች እየተሰጡ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaHawassa

@tikvahethiopia
#National_GAT

ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) መቼ ይሰጣል ?

የ2016 የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT)  ሐምሌ ወር መጨረሻ ሳምንት ይሰጣል።

አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የ3ኛ ዙር አገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) በሐምሌ ወር የመጨረሻ ሳምንት እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።

የ2ኛው ዙር የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና በህዳር 2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

Via @tikvahuniversity
#Somaliland #Turkey

የራስ ገዟ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ሀርጌሳ ካሉት ከቱርክ የቆንጽላ ጄነራል ሌቬንት ቼሪ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ተሰምቷል።

ንግግራቸው ሶማሌላንድ ስለሚያሳስባት ጉዳዮች እና ከቱርክ ጋር ስላላት ግንኙት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር ተብሏል።

ምንም ዝርዝር መረጃ ግን ይፋ አልሆነም።

ንግግሩ ግን በቀጣይ አብሮ ለመጓዝ እና በትብብርም የመስራት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት በመስጠት መጠናቀቁ ተነግሯል።

በሶማሌላንድ ያሉ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቱርክ፣ ሶማሊያን ፦
- የምታስታጥቅ፣
- የምትደግፍ፣
- የምታሰለጥን ሀገር እንጂ የሶማሌላንድ ወዳጅ ሀገር ስላልሆነች ከእሷ ጋር ግንኙነትን ማቋረጥ እንደሚገባ እና ቆንጽላ ጽ/ቤቱ እንዲዘጋ  ጥሪ ሲያደርጉ ተመልክተናል።

ከሰሞኑን የቱርክ ስም ተደጋግሞ እየተነሳ ይገኛል።

ሀገሪቱ ኢትዮጵያና ራስ ገዟ ሶማሌላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ በሶማሊያና ኢትዮጵያ በመካከል የተፈጠረውን መቃቃር መፍትሄ እንዲያገኝ የማሸማገል ስራ እየሰራች እንደሆነ የሚገልጹ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው።

በኢትዮጵያም ይሁን በሶማሊያም በኩል ይፋዊ መረጃ ባይሰጥም በአንካራ የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፊት ለፊት ተገናኝተው ይነጋገራሉ እየተባለ ይገኛል።

ትላንት የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ በX ገጹ ከኢትዮጵያ ጋር ለሚደረግ ንግግር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሚመራ ልዑክ ወደ ቱርክ አንካራ እንዳቀና ከገለጸ በኃላ መረጃውን ከገጹ ላይ አጥፍቶታል።

@tikvahethiopia
#Sidama

በሲዳማ ክልል፣ በሥራ ላይ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ህይወቱ አለፈ።

አንድ ሹፌርም ህይወቱ አልፏል።

ዛሬ ከረፋዱ 3 ሰዓት ላይ በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ የደረሰ የትራፊክ አደጋ አንድ ሾፌርን ጨምሮ በስራ ላይ የነበረ የትራፊክ ፖሊስ ህይወት ቀጥፏል።

አደጋው በወረዳው ' ኤሬርቴ ወንዝ ' አጠገብ ' ቅጥቅጥ ' የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ተነግሯል።

በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃ የሰጡት የሲዳማ ክልል ትራፊክና አደጋ መከላከል ተጠሪ ኮማንደር ከበደ ኮኔራ አደጋው ጠዋት 3:00 ሰዓት አካባቢ በተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር መድረሱን አረጋግጠዋል።

በወቅቱ የአካባቢውን የተሽከርካሪ ፍሰት ሲቆጣጠር የነበረው ትራፊክ ፖሊስ አንድ የሚኒባስ አሽከርካሪን አስወርዶ በመነጋገር ላይ እያለ አቅጣጫውን የሳተ ' ቅጥቅጥ ' የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከዳራቸዉ ከነበረው ሲኖ ጋር እንዳጣበቃቸዉና ሁለቱም ወዲያዉ ህይወታቸዉ እንዳለፈ ገልጸዋል።

" በአካባቢዉ የነበረዉ ብቸኛ የትራፊክ ፖሊስ እና መረጃ አቀባያችን በመሰዋቱ አሁን ላይ ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልቻልንም " ያሉት ኮማንደር ወደቦታዉ ያቀኑት ባልደረቦቻቸው የሚያቀብሉት መረጃ በኋላ ላይ ለህብረተሰቡ  እንደሚያጋሩን ተናግረዋል።

በአደጋዉ የሁለቱ ዜጎች ህይወት ከመጥፋቱ ባለፈ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
ፕሮፌሰሮቹ አባት እና ልጅ 👏

ፕሮፌሰር ባዬ ይማም (አባት) እና ፕሮፌሰር ቃለአብ ባዬ ይማም (ልጅ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሙያቸው እያገለገሉና ተተኪ ምሁራንን እያፈሩ የሚገኙ ፕሮፌሰሮች ናቸው።

ፕሮፌሰር ባዬ 44 ዓመታት ፤ ፕሮፌሰር ቃለዓብ ደግሞ 15 ዓመታት በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ያገለገሉና እያገለገሉ የሚገኙ ምሁራን ናቸው።

2ቱም የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን በሰሩ በ10ኛው ዓመት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አገኝተዋል።

ፕሮፌሰር ቃለዓብ ባዬ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከሰጣቸው ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው።

Credit - AAU

Via @tikvahuniversity
#BenishangulGumuz

• “ የውሃ አቅርቦት ተቋርጦ ችግር ላይ ወድቀናል ” - ነዋሪዎች

• “ የመብራት ችግር ነው ” - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ

• “ የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው ” - የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
 

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማን ጨምሮ ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩ መቸገራቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ገለጹ።

“ የውሃ አቅርቦት ተቋርጦ ችግር ላይ ወድቀናል። ውሃ ካለበት ቦታ በጀሪካ እስከ 30 ብር ለመግዛት ተገደናል ” ሲሉ አማረዋል።

በወንበራ፣ በአሶሳ ከተማና ሌሎችም ቦታዎች የውሃ መብራት ችግር እንዳለ ገልጸው፣ የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸው በአንክሮ ጠይቀዋል።

ቲክባህ ኢትዮጵያም ምን ተፈጥሮ ነው አገልግሎቱ የተቋረጠው ? ሲል የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮን ጠይቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አድማሱ ሞርካ “ የመብራት ችግር ነው። ያለ መብራት አይደለም የሚሰራው ውሃው። ቅሬታቸው ትክክል ነው ” ብለዋል።

“ መንዲ የሚባል አካባቢ ላይ ኤሌክትሪክ ተበላሽቶ ተስካክሎ ነበር። በድጋሚ ተበላሽቶ ነው። በዚህ ምክንያት የከተማው ውሃ የተቋረጠበት ሁኔታ አለ ” ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ አሶሳ ከተማ ላይ የኤሌክትሪክ ችግር ከመከሰቱ ቀድሞም የውሃ አቅርቦት ችግር እንደነበር ተመላክቷል፤ ችግሩን ለመቅረፍ ቢሮው ምን እየሰራ ነው ? ሲል ተጨማሪ ጥያቄ አቅርቧል።

ኃላፊው በምላሻቸው፣ “ ችግሩን ለመቅረፍ ያቀድነው ጉድጓዶችን መጨመር ነው። 4 ነበር ያቀድነው 3ቱ ተቆፍረው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል ” ብለዋል።

“ ሁለተኛ አማራጭ ደግሞ ታንከሮች ናቸው። ከዚህ በፊት ለ500 ሺህ ህዝብ ነው ታንከር የተሰራው። ይሄም በቂ ባለመሆኑ 3 ታንከር ለመጨመር አቅደን አሁን ዝግጁ ሆነዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።

የመብራት ችግሩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ከበደ፣ “ አሶሳ አካባቢ ተቋርጦ ነው ያለው። ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠ መስመር አለ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ቡድን የነቀምት ቢሮ ነው። ከእነርሱ እየገዛን ነው ኤሌክትሪክ ለማህበረሰቡ የምንሸጠው። የተቋረጠው ኤሌክትሪክ እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው። ድጋፍ እያደረግንም ነው ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦ " ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በኋላ እንዲሁም ሰኔ 8 እና 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋናነት በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎች " የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና መሣሪያ በቤታችሁ እንዳለ ተጠቁመናል፤ የደበቃችሁትን መሣሪያ አውጡ " በሚል ምክንያት ሴቶችና የአእምሮ ሕመምተኞችን ጨምሮ ቢያንስ 50 ሲቪል ሰዎች በተናጠል እና በጅምላ ከፍርድ ውጪ መገደላቸውን፣…
#Gambella

ንፁሃንን " መረጃ ሰጥታችኋል " በሚል በአቃቂ ሁኔታ #እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ፤ ግድያው ላይም ተሳትፈዋል ከተባሉ ተከሳሾች ውስጥ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ በተከሰሱበት ክስ #ነጻ መባላቸው ተሰምቷል።

ሌሎች የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የልዩ ኃይል አዛዦችን ጨምሮ 12 ተከሳሾች ግን የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ብይኑን የሰጠው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ-መንግሥት እና በሕገ-መንግሥት ሥርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው። 

ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት እነማን ናቸው ?

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ፣
የቀድሞው ም/ኮሚሽነር ቱት ኮር፣
የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞ ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኮንግ ሬክ
የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞው ምክትል አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡጀዲ ባሬ እና የተለያዩ የፀጥታ አባላትን ጨምሮ አጠቃላይ 15 ተከሳሾች ናቸው።

ተከሳሾቹን ላይ የቀረበው ክስ ምንድነው ?

ሰኔ 7/2014 ዓ/ም በጋምቤላ ከተማ መንግሥት በአሸባሪ ቡድንነት የፈረጀው " ሸኔ " እና የጋምቤላ ነጻ አውጪ ግንባር (ጋነግ) በጋራ ሆነው ቀበሌ 03 በፌደራል ፖሊስ ካንፕ እና በክልሉ ልዩ ኃይል እንዲሁም በሌሎች ፀጥታ አካላት ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከፍተው ነበር።

በኃላም ጥቃት አድራሾቹም በፀጥታ ኃይሎች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።

ከዚህ ክስተት በኋላ ግን ማንነታቸው የተለዩ 35 ሰዎች እና ማንነታቸው ያልተለዩ ሌሎች ንፁሃንን " #መረጃ_ሰጥታችኋል " በሚል በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ  ትዛዝ ሰጥተዋል ፤ በግድያው ላይ የተሳተፉም አሉ የሚል ነው።

የክስ መዝገቡ የተከሳሾች የተሳትፎ ደረጃቸውን በዝርዝር አስቀምጧል።

ፍርድ ቤት ምን ውሳኔ አሳለፈ ?

ከ15ኛው ተከሳሽ ውጭ ሌሎቹ በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ግለሰቦቹ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን አሰምቷል። ማስረጃዎቹን አቅርቧል።

ፍርድ ቤት ፦
° የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ፣
° ቀድሞው ም/ኮሚሽነር ቱት ኮር
° የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞው ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኮንግ ሬክ
° የክልሉ ልዩ ኃይል የቀድሞ ምክትል አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡጀዲ ባሬን ጨምሮ 13 ተሳሾች በተከሰሱበት ድንጋጌ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።

ዛሬ በዋለው ችሎት 12 ተከሳሾች የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በበቂ ሁኔታ መከላከል አለመቻላቸው ተጠቅሶ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከላቸው ተጠቅሶ ነጻ ተብለዋል።

ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉ ተከሳሾችንና የዐቃቤ ሕግን የቅጣት አስተያየት ለመጠባበቅ ለሐምሌ 10/2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከዚህ ቀደም የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል የቀድሞ አባል ኮ/ል አቶሬ ጉር እና የጋምቤላ ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ አባል ረ/ሳጅን ቾድ ቤንግን በተመለከተ ፍ/ቤቱ በቀረበባቸው ክስ ላይ በቂ ማስረጃ አለመሰማቱን ተገልጾ በነጻ እንዲሰናበቱ ተደርጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኤፍቢሲ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

የመጀመሪያው ዲጂታል ቪዛ ካርድ በኢትዮጵያ!

በባንክ ቴክኖሎጂ ፈር ቀዳጅ የሆነው አቢሲንያ ባንክ ዛሬም በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ዲጂታል ቪዛ ካርድ እንሆ ብልዋል።

ይህ ዲጂታል ቪዛ ካርድ ደንበኞች ስልካቸውን እንደ ATM ካርድ መገልገል የሚችሉበት ሲሆን የአፖሎ መተግበሪያን በመጠቀም ቪዛ ካርዳቸውን ወደ ዲጂታል ቪዛ ካርድ በመቀየር ገንዘብ ከATM ለማውጣትም ሆነ POS ማሽኖች ላይ ለመክፈል ስልካቸውን ጠጋ በማድረግ መጠቀም ይችላሉ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#DigitalVisacard #Visa #ApolloVisacard #BoAVisacard #Visacard #Digitalethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ይህ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስም በተለይ በ X መተግበሪያ ላይ እየተራጨ ያለው መግለጫ ሀሰተኛ እና የተቀነባበረ ነው። የሚኒስቴሩን የቀድሞ ሎጎ በመጠቀም እየተሰራጨ ያለው ይህ መረጃ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ፦ - በUN - በEU - BRICS (ኢትዮጵያ እራሷ አባል የሆነችበት) - በኢስላሚክ ሀገራት ከፍተኛ ጫና እንደሰረዘችው…
#Ethiopia #Somalia

" ልዑካኑ የቀጥታ የፊት ለፊት ንግግር / ውይይት አላደረጉም " - የሶማሊያው ፕሬዜዳንት

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት ትላንት አንካራ ውስጥ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

በቱርክ ጋባዥነት በተደረገው ውይይት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞሊም የመሯቸው ልዑካን አንካራ ተገኝተው ነበር። 

ከውይይቱ በኃሏ የሶስቱ ሀገራት የጋራ መግለጫ ወጥቷል።

መግለጫው ፥ ሚኒስትሮቹ ያላቸውን ልዩነቶች ለሁለቱም ተቀባይነት ባለው ማዕቀፍ ውስጥ ለመፍታት ያሉ ሁኔታዎችን እንደዳሰሱ ገልጿል።

ሚኒስትሮቹ በተናጥል በግልጽነት ፣ ወዳጅነት ባለው እና የወደፊቱን ያለመ ውይይት እንደነበራቸው ነው የተመላከተው።

ሁለቱ አገራት ችግሮቻቸውን ለመፍታትና ቀጣናው እንዲረጋጋ የጀመሩትን ውይይት ለመቀጠል ተስማምተዋል የተባለ ሲሆን ለሁለተኛ ዙር ውይይት በአንካራ ነሐሴ 27/ 2016 ዓ.ም እንደሚገናኙ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ራሷን በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር ከ6 ወራት በፊት የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች ወዲህ በይፋ ተገናኝተው ሲመጋገሩ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።

የጋራ መግለጫው ሁለቱ አገራት ልዩነታቸውን ለሁለቱም ተቀባይነት ባለው ማዕቀፍ ለመፍታት ያሉ ሁኔታዎችን እንደዳሰሰ ቢገልጽም እነዚህ ተቀባይነት አላቸው ስለተባሉ ጉዳዮች የተጠቀሰ ጉዳይ የለም።

በሌላ በኩል ፥ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ትላንት ውይይቱ ካበቃ በኃሏ ባሰሙት ንግግር ፦
- ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ከተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ወደኋላ የምትመለስበትን ምንም ምልክት አላሳየችም፤
- ከያዘችው መንገድ እየተመለሳች ስለመሆኑ ምንም ምልክት የለም ፤
- አንካራ ውስጥ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ልዑካን ቀጥተኛ ንግግር አላደረጉም ይልቅም ቱርክ በመሃል እንደ አስታራቂ ሆና እየሰራች ነበር ብለዋል።

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና ከዛም የውጭ ጉዳይ መ/ቤትን ሎጎ በመጠቀም አንካራ ውስጥ በተደረገ ውይይት " ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የገባችውን ስምምነት  ሰርዛለች " የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

#Ethiopia #Somalia #Turkey

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Somalia " ልዑካኑ የቀጥታ የፊት ለፊት ንግግር / ውይይት አላደረጉም " - የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት ትላንት አንካራ ውስጥ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል። በቱርክ ጋባዥነት በተደረገው ውይይት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞሊም የመሯቸው ልዑካን…
ኢትዮጵያ ስለ አንካራው ውይይት ምን አለች ?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአንካራው ውይይት ጉዳይ የፕሬስ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው በቱርኪዬ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ጋባዥነት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ ትላንት ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ተገናኝተው መወያየታቸውን አረጋግጧል።

" በቱርኪዬ መንግስት አመቻቺነት የተካሄደው የሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ላሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ግልፅና ወዳጅነት የተሞላበት የሀሳብ ልውውጥ የተደረገበት ነበር " ብሏል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን አመልክቷል።

የቱርኪዬ መንግስት ውይይቱን ለማመቻቸት ስለተጫወተው ገንቢ ሚናም ምስጋና እንደቀረበ ገልጿል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች መልካም ጉርብትናን እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ከግምት በማስገባት መፍትሄዎችን ለማመላከት ያለሙ ምክክሮችን ለመቀጠልም እንደተስማሙ አረጋግጧል።

ሁለቱም ሚኒስትሮች የቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምከከሩን አገራቸው ለማስተናገድ የወሰዱትን ተነሳሽነት በማድነቅ ሁለተኛ ዙር ውይይታቸውን ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ለመቀጠል እንደተስማሙ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

#Ethiopia🇪🇹

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የትግርኛ እና የአፋን ኦሮሞ የቋንቋ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ አመራሮች የማጠቃለያ ፈተና እንደወሰዱ ተነገረ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለ5 ተከታታይ ወራት የትግርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ትምህርት ሲሰጥ እንደቆየ ተነግሯል።

ትላንትና የማጠቃለያ ፈተና እንደተሰጠ ተገልጿል።

ከክ/ከተማው በተገኘ መረጃ ፥ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ 371 አመራሮች በትግርኛ እና በአፋን ኦሮሞ የቋንቋ ትምህርት ለ5 ወራት ሲከታተሉ ቆይተዋል።

አመራሮቹ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ተጨማሪ ቋንቋ ተምረው ትላንት የማጠቃለያ ፈተና መውሰዳቸው ተገልጿል።

የቋንቋ ትምህርቱ ሲሰጥ የነበረው ከጋራ ጉሪ 1ኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት ጋር በመቀናጀት እንደነበረ ተነግሯል።

ክ/ከተማው ፤ ብልፅግና ፓርቲ በሀገሪቱ አምስት የስራ ቋንቋዎች እንዲሆኑ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል ብሏል።

#AddisAbaba
#LamiKuraCommunication

@tikvahethiopia
2024/09/29 16:34:49
Back to Top
HTML Embed Code: