Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya ጎረቤት ኬንያ ታቃውሞ እየናጣት ነው። መንግሥት በታክስ ላይ ጭማሪ ሊያደርግ ማቀዱን ተከትሎ በተለይም ወጣቱ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥቷል። ከወጣቶቹ ሰልፍ ጋራ በተያያዘ ትላንት አንድ ሰው #ተገድሏል፡፡ ግድያው የተፈጸመው በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ነው ተብሏል። ዛሬም በናይሮቢና የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል። ተቃዋሚዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድ የተቃውሞ…
#Update

በነገው ዕለት በኬንያ ምድር አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሏል።

ይህ ሰልፍ የሀገሪቱ መንግስት ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅን የሚቃወም ነው።

የተቃውሞ ሰልፉ አይቀሬ እንደሆነ ያወቀው የሀገሪቱ መንግሥትም በአገር ውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ካቢኔ ሚኒስትር በኩል ሰልፉ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

ዛሬ በሰጠው ይፋዊ መግለጫ ማንኛውም ተቃዋሚ የመንግስትም ሆነ የግል ንብረትን እንዳያወድም ወይም እንዲያወድም እንደማይፈቀድለት አፅንዖት ሰጥቷል።

የተቃውሞ ሰልፈኛው የሚሄድበትን አቅጣጫ ቀደም ብሎ ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ እጅባና ጥበቃ እንዲደረግለት ማድረግ አለበት ተብሏል።

ሰልፈኞቹ ሰልፉን በፍጹም ሰላማዊ መንገድ ማድረግ እንዳለባቸው ያሳሰበው የሀገሪቱ መንግስት ትጥቅ ታጥቆ ሰልፍ መውጣት እርምጃ ሊያስወስድ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ተቃዋሚ ሰልፈኞች ፦
- የውሃ፣
- የኃይል አቅርቦት
- ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጡት ወሳኝ ቦታዎች ላይ እንዳያገኙ ተከልክለዋል።

በተጨማሪ በህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ ተገልጿል።

በምንም መልኩ በየብስ ፣ በባቡር፣ በባህር ፣ በአየር ትራንስፖርት ላይ ጣልቃ መግባት እንደ ሌለባቸው ምንም ይሁን ምን ለሀገሪቱ ህግ የበላይነት ሁሉም ሰው ሊታዘዝ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ሁሉም ተቃዋሚዎች ሰልፉን ሁከት እና ብጥብጥን በማያበረታታ መንገድ እንዲያደርጉ እንዲሁም ደግሞ ፦
° ሰልፉን መሳተፍ የማይፈልጉ / ተቃውሞ ማድረግ የማይፈልጉ
° የፖሊስ አባላትን ፣
° የመንግስት አካላትን ማስፈራራት ፣ ማስጨነቅ እና መተንኮስ እንደሌለባቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

#Kenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ጤፍን ጨምሮ በሌሎች የግብርና ግብዓት ምርቶች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መሆናቸውን የሚወስነዉ መመሪያዉ ተግባራዊ መደረግ እንደጀመረ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። የገንዘብ ሚኒስቴር በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆናቸውን አረጋግጧል። ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ በተጀመረው…
#ያንብቡ #ኢትዮጵያ

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን የወጣው መመሪያ ፤ ' መመሪያ ቁጥር 1006/2016 ' ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

መመሪያው ተግባራዊ የተደረገው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል መሰረታዊ የሆኑ የምግብ አቅርቦቶችን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ እንዲገዛ ለማድረግና የወጪ ጫናውን ለማርገብ ጠቀሜታ ስላለው መሆኑ ተገልጿል።

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሆኑ እቃዎች እና አገልግሎቶች ዝርዝር ምንድናቸው ?

ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በአገር ውስጥ የሚመረቱ እና ከውጭ አገር የሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በአገር ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ናቸው።

1ኛ. እህልና ጥራጥሬ
ጤፍ
ስንዴ
ገብስ
በቆሎ
ማሽላ
ዘንጋዳ
ዳጉሳ
አጃ
አተር ፣ ባቄላ ፣ ምስር፣ አኩሪ አተር፥ ሽምብራ፣ ግብጦ፥ ጓያ እና የመሳሰሉት ጥራጥሬዎች፤
የእነዚህ ዱቄት

2ኛ. የግብርና ግብአቶች
ማዳበሪያ
ጸረ-ተባይ ኬሚካል
የእንስሣት መድሃኒት
የመድሃኒት መርጫ

3ኛ. የበሰሉ ወይም የተዘጋጁ ምግቦች / መጠጦች
👉 እንጀራ
👉 ዳቦ
👉 ወተት

4ኛ. በካፒታል ሊዝ ስምምነት የሚቀርቡ የካፒታል እቃዎች

5ኛ. የወባ መከላከያ አጎበር ፤ ኮንዶም እና ለውሃ ማከሚያ የሚሆኑ ኬሚካሎች

#MinistryofFinance
#MinistryofRevenues

@tikvahethiopia
#EthiopianAirlines🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመባል ክብርን ተቀዳጀ።

በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ' የአቪዬሽን ኦስካር ' ተብሎ በሚጠራው የስካይትራክስ መድረክ ነው ይህን ክብር የተቀዳጀው።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት

🏆 የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ለ6ኛ ተከታታይ ዓመት፣

🏆 በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ በመባል ተደራራቢ ድልን ተጎናጽፏል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በነገው ዕለት በኬንያ ምድር አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሏል። ይህ ሰልፍ የሀገሪቱ መንግስት ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅን የሚቃወም ነው። የተቃውሞ ሰልፉ አይቀሬ እንደሆነ ያወቀው የሀገሪቱ መንግሥትም በአገር ውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ካቢኔ ሚኒስትር በኩል ሰልፉ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል። ዛሬ በሰጠው ይፋዊ መግለጫ ማንኛውም ተቃዋሚ የመንግስትም…
#ኬንያ

" ዉጡ ! ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ወጥታቹ መቃወም ትችላላችሁ " - ኪቱሬ ኪንዲኪ

የኬንያ መንግሥት፤ ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን የሚቃወም የተቃውሞ ሰልፍ " ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ መካሄድ ይችላል " ብሏል።

የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ' ሰላማዊ ይሁን ብቻ ወጥታችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ' ብሏቸዋል።

' ያልተለመደ ነው ' በተባለው እርምጃ ፤ የሀገር ውስጥ የደህንነት ካቢኔ ሚኒስትር ኪቱሬ ኪንዲኪ ፥ " ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ የህግ የበላይነትን እና ህዝባዊ ስርዓቱን እስካከበሩ ድረስ በእቅዳቸውን መሰረት መቀጠል / ወጥተው መቃወም / ይችላሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

" የኬንያ መንግስት ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ በሰላማዊ መንገድ ፤ ትጥቅ ሳይታጠቅ ፦
° የመሰብሰብ ፣
° ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ፣
° የመምረጥ
° አቤቱታዎችን ለባለስልጣናት የማቅረብ የማይገረሰስ ህገ መንግስታዊ መብቱን ያከብራል ፤ እንዲፈጸምም ያደርጋል " ብለዋል።

ሰልፈኞቹ ወደ ሀገሪቱ ቤተ መንግስት ፣ በኃይል ወደ ፓርላማ ህንጻ እንዲሁም ወደ ሌሎችም የመንግሥት አካባቢዎች ለመጠጋት እንዳይዳፈሩ አስጠንቀቀዋል።

- ህግና ስርዓት አክብሩ ፤
- ህዝባዊ ስርዓቱን አክብሩ ፤
- የግል ፣ የመንግስት ንብረት አታውድሙ ፤
- መሰረተ ልማት አካባቢ አትጠጉ ፤
- የተከለከሉ ቦታዎች ጋር አትሂዱ፤
- የህዝባዊ አገልግሎት አታስተጓጉሉ፣
- እናተን የማይደግፏችሁ የተቃውሞ ሰልፍ መውጣት የማይፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን አታስፈራሩ፣ አታዋክቡ፣ አታስጨንቁ
- የጸጥታ ኃይል አባላትን አትተንኩሱ ... ከዚህ ውጭ ግን እንደልባችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ብለዋቸዋል።

ሚኒስትሩ ፤ የጸጥታ ኃይል ጥበቃ እና እጅባ ለማድረግ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሰልፍ ለማድረግ የሚሄዱበትን አቅጣጫ ቀደም እያሉ ማሳወቅ እንዳለባቸው ገልጸው ፀሃይ ከመጥለቋ በፊት ተቃውሞው እንዲያበቃ አደራ ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyKenya

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ " ዉጡ ! ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ወጥታቹ መቃወም ትችላላችሁ " - ኪቱሬ ኪንዲኪ የኬንያ መንግሥት፤ ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው የፋይናንስ ረቂቅ አዋጁን የሚቃወም የተቃውሞ ሰልፍ " ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ መካሄድ ይችላል " ብሏል። የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ' ሰላማዊ ይሁን ብቻ ወጥታችሁ ተቃውማችሁ ግቡ ' ብሏቸዋል። ' ያልተለመደ ነው ' በተባለው እርምጃ ፤ የሀገር ውስጥ የደህንነት…
#ኬንያ

ናይሮቢ፣ ሞምባሳን ጨምሮ በተለያዩ የኬንያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መደረግ ጀምረዋል።

በወጣቶች መሪነት እየተካሄዱ ባሉት በነዚህ ሰልፎች ላይ መንግሥት ተጨማሪ ታክስ ለመጣል ያረቀቀውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅ ሙሉ በሙሉ እንዲተወው እየተጠየቀበት ነው።

መንግሥት በረቂቁ ላይ አንዳንድ ማሻሻያ አደረጋለሁ ቢልም ተቃዋሚዎች ግን " የምን አንዳንድ ነው ? ሙሉ ረቂቁን ተወው " የሚል አቋም እንደያዙ ተሰምቷል።

ከዛሬው ሀገር አቀፉ የተቃውሞ ሰልፍ ጋርም በተያያዘ በናይኖቢ ያለው ሰልፍ ጥሩ እንዳልሆነ እና ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ሰው መጎዳቱ ተሰምቷል።

ባለስልጣናት የተቃውሞ ሰልፉን ለመበተን በ' ኬንያታ ጎዳና ኢመንቲ ህንፃ ' አጠገብ የአስለቃሽ ጭስ ማዘጋጀታቸው ፤ የአድማ ብተና ኃይሎችም ዱላ  እና አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመው ተቃዋሚዎችን ሲያባርሩ እንደነበሩ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት እና ምክትል ፕሬዜዳንት በጋራ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ።

ስራ መልቀቂያውን ያስገቡት ፤ " በፍትህ እና የዳኝነት ሰርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ሁኔታ ማግኘት ስላልቻልን ነው " ብለዋል።

ሰኞ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ በበርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ፤ ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የተፃፈው የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ ትክክለኛ መሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የፕሮቶኮል ሹምን በመጠየቅ አረጋግጧል።

የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፕሬዜዳንትና ምክትላቸው ከደም አፋሳሹ ጦርነት በኃላ በክልሉ በተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር  መሾማቸውን የገለፀው የፕሮቶኮል ሹሙ "  የስራ መልቀቅያ ደብዳቤ ጥያቄው የቀረበላቸው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ለጥያቄው ገና መልስ አልሰጡም  " ብሏል።   

የከፍተኛ ፍርድ ፕሬዜዳንት ፀጋይ ብርሃነ ገ/ተኽለ (ዶ/ር ) እና ምክትላቸው ገብረ ኣምላኽ የዕብዮ በላይ ባቀረቡት ስራ መልቀቅያ ደብዳቤ ፥

" በፍትህና የዳኝነት ስርዓቱ ለውጥ ለማምጣት ያሰብናቸው ፣ ያቀድናቸው የጀመርናቸው እና ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች ለማሳካት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ማግኘት አልቻልንም።

በአጠቃላይ የፍትህ እና የዳኝነት የአስተዳደር ስርአት እያጋጠሙን ያሉ  ያልተሻገርናቸው ችግሮችና ማነቆዎች ለመቀነስ በሌላ መንገድ የበኩላችን እንደምንወጣ በመተማመን ፍላጎታችን ስራችንን ለመልቀቅ መወሰናችንን በትህትና ለማሳወቅ እንወዳለን።

ያቀረብነው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ አስፈላጊው የማስተካከያ እርምጃ እስከሚወሰድ በስራ ገበታችን እንደምንቆይ እናረጋግጣለን "
ብለዋል።

ለ14 ዓመታት የወረዳ የዞን እና የከፍተኛ ፍርድ ዳኛ በመሆን አገልግለው ከወራት በፊት ከከፍተኛ ፍርድ ቤት የስራ ገበታቸው የለቀቁ ዓወት ልጃለም የተባሉ የህግ ምሁር በቅርቡ TPM ለተባለ ሚድያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ፥ " መንግስታዊ ፍርድ ቤቱ ጠንካራና ነፃ አይደለም ፤ ነፃና ጠንካራ የዳኝነት አካል የለም " ያሉ ሲሆን ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኃላ በቻ እሳቸው ጨምሮ ከ 50 በላይ ዳኞችና አቃቤ ህጎች ስራ መልቀቃቸው ተናግረዋል።

አሁን ላይ ፕሬዜዳንቱ እና ምክትላቸው በአንድ ጊዜ የስራ መልቀቅያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ በማህበራዊ የትስስር ገፆች " ፓለቲከኞቹ አላሰራ ካሉዋቸው ስራ መልቀቅ መብታቸው ነው " የሚሉና " ክልሉ ከጦርነት ማግስት በማገገም ሂደት እያለ ይህ መሰል ተግባር ከሙሁራን አይጠበቅም ፣ መታገስና መታገል ነበረባቸው " የሚሉ አስተያየቶች በመንሸራሸር ላይ ናቸው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#Mekelle

" የሴቶች ጥቃትና እገታ ይቁም ! " በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

ሰላማዊ ሰልፉ በራስ ተነሳሽነት በተነሳሱ ወጣት ሴቶች የተደራጀ ሲሆን ዛሬ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በመቐለ ዋና ዋና መንዶች ተካሂዷል።

የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች ፦

➡️ የሴቶች ጥቃት በቃል ሳይሆን በተግባር ይቁም !!

➡️ ፍትህ የማይሰጥ ፍትህ ቢሮ ይዘጋ !! 

➡️ የሴቶች ጥቃትና እገታ ይቁም !!

➡️ መንግስት አጥፊዎች የሚቀጣ ጥርስ ይኑርህ !!

➡️ የእምነት ተቋማት የሴቶች ጥቃትና እገታ አውግዙ !!

➡️ ፆታ ተኮር ጥቃት ይቁም !!

➡️ የዘውዲና የማህሌት ገዳዮች ወደ ፍርድ ይቅረቡ !!

➡️ የሴቶች መብት ይከበር !! 

የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

የሴቶች ጥቃትና እገታ እንዲቆም በራስ ተነሳሽነት በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱት ወጣት ሴቶች፣ ልጃገረዶች ፣ እናቶች አርቲስቶችና ታዋቂ ሴቶች ሲሆኑ በቂ የፀጥታ አካላት ጥበቃና እጀባ እንደተደረገላቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከቦታው ዘግቧል።

በትግራይ ከጦርነቱ ወዲህ ሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትና እገታ መባባሱ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ሲሆን በቅርቡ ከ91 ቀናት እገታ በኃላ ተገድላና ተቀብራ የተገኘችው የተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ብዙዎችን ያስቆጣ እንደሆነ ይታወሳል።

Photo Credit - DW TV

@tikvahethiopia            
2024/10/01 13:42:21
Back to Top
HTML Embed Code: