Telegram Web Link
#ትግራይ #ኢሮብ

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነቱ በኃላም ቢሆን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የኢትዮጵያ፣ ትግራይ ኢሮብ ወረዳ 23 ት/ ቤቶች በኤርትራ ወታደሮች ስር ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ ተነፃፃሪ የሆነ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ባለባቸው አከባቢዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በቀጣዩ ሃምሌ ወር 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በመዘጋጀት ይገኛሉ።

ለፈተናው እየተዘጋጁ ያሉት ተማሪዎች በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ፤ ትግራይ ክልል በጊዜያዊ አስተዳደር ስር ያሉ ናቸው።

በወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ስር የሚታወቁ እና ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩት አንድ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙባቸው 23 ትምህርት ቤቶች ከ3 ዓመት በላይ #በኤርትራ_ወታደሮች_ቁጥጥር_ስር እንደሚገኙ በኢሮብ ወረዳ የትምህርት ፅህፈት ቤት ተገልጿል።

የትምህርት ቤቶቹ  መምህራን እና ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል። 
 
ቃላቸውን የሰጡ ተማሪዎች ፦
- ጦርነቱ ብዙ ነገሮች እንዳሳጣቸው
- አሁን በወረዳቸው ትምህርት ቤት የኢንተርኔት አቅርቦት ጨርሶ እንደሌለ
- ውሃ ፣ መብራት ፣ ትራንስፓርት የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እንደሌለ ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ በቴክኖሎጂ ታግዞ ከሚፈተኑ ተማሪዎች ጋር ተፈኳኳሪ ለመሆን እንደሚከብድም ገልጸዋል።

ያም ሆኖ ግን አሁን ላይ የተገኘው ዕድል እንዳያመልጥ ለመፈተን ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

መምህራን በበኩላቸው ፥ በወረዳው ያሉት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የክልሉና የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር እገዛ እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች ነፃ ወጥተው የዘወትር አገልግሎት እንዲሰጡ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል።

በወረዳው በጦርነት ምክንያት የትምህርት ሴክተር ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የወደመ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችም ምንም የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት በሌለበት ለመፈተን በዝግጅት ላይ መሆናቸው ግምት ውስጥ በማስገባት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የእገዛ እጃቸው እንዲዘረጉ የወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን መረጃ የትግራይ ቴሌቪዥንን ዋቢ በማደረግ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia            
#ኢሠማኮ

አቶ ካሳሁንን በተመለከተ እውነታው ምንድነው ?

በቅርቡ 112ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) ጉባኤ ተካሂዶ ነበር።

በዚህ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በከፍተኛ ድምጽ የዓለም ሥራ ድርጅት አስተዳደር አካል (Governing Body) አባል ሆነው ተመርጠዋል።

ነገር ግን በማኅበራዊ ሚዲያዎች እና በሌሎች ሚዲያዎች መረጃዎች በተጨባጭ ካለው እውነታ በራቀና #በተዛባ መልኩ መዘገቡን የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ዛሬ በላከልን ደብዳቤ አሳውቋል።

እውነታው ምንድነው ?

አቶ ካሳሁን የዓለም ሥራ ድርጅት የአስተዳደር አካል ምክትል አባል (Deputy member of the Governing Body) ሆነው ተመርጠዋል።

ከዓለም ሠራተኞች 14 መደበኛ ( Regular) እና 19 ምክትል (Deputy) በአጠቃላይ 33 የሠራተኛ ተወካዮች ባላቸው ብቃት እና ልምድ በድምፅ ይመረጣሉ።

ከአሠሪም በተመሳሳይ ይመረጠሉ፡፡

የመንግሥት ከአሠሪና ሠራተኛ /ቁጥራቸው ከፍ ይላል።

ስብሰባቸውም በዓመት 3 ጊዜ በጥቅምት እና በመጋቢት ወራቶች ለአንዳንድ ሳምንት ሲሆን በሰኔ ወር ላይ ከሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ በኃላ ለ1 ቀን ይሰበሰባሉ።

በቋሚነትም አይሠሩም። #ሹመትም_አይደለም

ይህ የአስተዳደር አካል (Governing Body) ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞችን የሚያፀድቅ ነው።

በየዓመቱ በእኤአ አቆጣጣር ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ለሚካሄደው የዓለም ሥራ ድርጅት ጉባዔም (International Labour Conference) አጀንዳ ያዘጋጃል ፤ የበጀት ረቂቅ ያዘጋጃል ፤ እንዲሁም የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ይመርጣል።

እንዲሁም በዓለም ላይ ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍንና በመንግሥት፤ በአሠሪ እና ሠራተኛ መካከል ማኅበራዊ ምክክር እንዲጠናከር ይሰራል።

አቶ ካሣሁን ፎሎ የተመረጡት የዓለም ሠራተኞች በመወከል የአስተዳደሩ አካል (Governing Body) ምክትል አባል ( Deputy member of Governing Body) ነው እንጂ ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር በመሆን የዓለም ሥራ ድርጅትን እንዲመሩ በማንኛውም የሥራ አስፈፃሚ ደረጃ #አልተሾሙም

#ኢሠማኮ

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#DStvEthiopia

⚽️ በላቀ ጥራት በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ እየተዝናኑ በጉጉት የሚጠበቀው የአውሮፓ ዋንጫ የልዩ ስሜት ተካፋይ ይሁኑ!

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር 350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ!
የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/4bVJ8Df

#Euro2024DStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#NewTariff📈

" የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ በሚቀጥሉት ሳምንታት ለሚንስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ ይቀርባል " - የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያዘጋጁትን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ በመገምገም በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ እንደሚያቀርበው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ሽያጭ ታሪፍን በማሻሻል ላይ ያተኮረ ስብሰባ ዛሬ ተደርጎ ነበር።

በዚህም ስብሰባ ላይ ባለፉት ሁለት ዓመታት መከለስ የነበረበት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ያለ ማሻሻያ በመቆየቱ ተቋማቱን ለኪሳራ እንደዳረገ እና የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጫና ማሳደሩ ተነግሯል።

" ለዚህም የታሪፍ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ተብሏል።

ሁለቱ ተቋማት በተናጥል እና በጋራ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ላይ ጥናት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በሌላ አማካሪ ድርጅት ተገምግሞ ማሻሻያው ወደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መቅረቡ ተጠቁሟል።

ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ኃይል ለማመንጨትና ለማሰራጨት የተሰጣቸው ባለፍቃድ መስሪያ ቤቶች ያቀረቡትን የታሪፍ ማሻሻያ ፕሮፖዛል ገምግሞ የውሳኔ ሃሳቡን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ የማጸደቅ ኃላፊነት አለበት።

በነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የኢነርጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አህመድ ሰኢድ ሁለቱ ተቋማት ጥናት በማድረግ ያቀረቡትን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አህመድ ሰኢድ ምን አሉ ?

" መንግስት በሰጠን ስልጣን መሰረት መመሪያ አለን። እነዛን መመሪያዎች ተከትለው ነው ወይ ታሪፉን ያወጡት ? ለምሳሌ ታሪፍ ከጨመረ ገቢ ይጨምራል። ያን ታሳቢ በማድረግ አላስፈላጊ ወጪዎችን ጨምረው ከሆነ እኛ ነን የምንቆጣጠራቸው " ብለዋል።

በተጨማሪ ሁሉቱ ተቋማት ያስጠኑትን የታሪፍ ተመን በባለስልጣኑ መመሪያ መሰረት እንደተሰራ እንደሚገመገም ገልጸው " በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ለሚኒስትሮች ምክርቤት ለውሳኔ ይቀርባል ሲሉ " ተናግረዋል።

የታሪፍ ማሻሻያው አሁን ያለውን ታሪፍ በምን ያህል ይጨምራል ? የሚለውን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አንዱአለም ሲአ " አሁን ላይ እዚህ ላይ ይደርሳል ለማለት አይቻልም " ብለዋል።

" ባለስልጣኑ ነው ቁጥሩን መጨረሻ ላይ አይቶ መርምሮ ለሚኒስትሮች ምክር  ቤት አስገብቶ የሚያፀድቀው " ሲሉ አክለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ደባርቅ

° “ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ተበራክተዋል ” - የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች

° “ ከጥር ወዲህ ወደ 13 ሰዎች ራሳቸውን #መርዘው ሞተዋል ” - ደባርቅ አጠቃላይ ሆስፒታል

በአማራ ክልል ባደባርቅ ከተማ ፣ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች እየተበራከቱ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ነዋሪዎቹ በሰጡት ቃል፣ “ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ተበራክተዋል። የሟቾች ቁጥር በተለይ ከፋሲካ በዓል ወዲህ እየጨመረ ነው ” ብለዋል።

አንድ ሁነቱን በቅርበት የሚከታተሉ ታማኝ ምንጭ ፤ በቤተክርስቲያን አንድ የሃይማኖት አባት “ የሟች ቁጥር 63 መድረሱን ” ሲገልጹ መስማታቸውን ተናግረዋል።

እውነትም ሰዎች ራሳቸውን እያጠፉ ነው ወይ ? ተብሎ የተጠየቀው የከተማው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት፣ “ ራስን የማጥፋት አደጋዎች አሉ ፤ በተደጋጋሚ እየታዬ ያሉ። ኬዙ ግን ወደ ሆስፒታል ነው እየሄደ ያለው ” ብሏል።

ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የከተማው አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አለአምላክ ተስፋ በበኩላቸው፣ “ አዎ ችግሩ አለ። በጣም ብዙ ራሳቸውን ለማጥፋት የሚሞክሩ አሉ ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

“ ከ13 ያላነሱ ሰዎች ራሳቸውን መርዘው እኛ ማገዝ በማንችለው ስለመጡ የሞቱ አሉ ” ብለው፣ ሟቾቹም ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ በማድረጋቸው ምክር ሲሰጣቸው ከነበሩ 59 ሰዎች መካከል መሆናቸውን አስረድተዋል።

“ ከጥር ወዲህ ወደ 13 ሰዎች ራሳቸውን መርዘው ሞተዋል ” ያሉት ኃላፊው፣ ሰዎቹ ለድርጊቱ የሚገፋቸው  የኢኮኖሚ መቃወስ ፣ ቤተሰብ #እንደሞተባቸው ሲሰሙ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዋናነት ግን ምክንያቱ #በጥናት መረጋገጥ አለበት ብለዋል።

ይህን መጥፎ ውሳኔ እየፈጸሙ ያሉት በተለይ ወጣቶች እንደሆኑ አስረድተው፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ቱርክ #ኢትዮጵያም ያለችበትን የBRICS ስብሰብ ትቀላቀል ይሆን ?

ባለፈው ሳምንት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የBRICS አባሏን ቻይናን ጎብኝተው ነበር።

በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይና ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።

በወቅቱ ሀገራቸው ቱርክ የBRICS ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም #እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ብለዋል።

" በእርግጥም ፤ የBRICS አባል መሆን እንፈልጋለን " ያሉት ፊዳን " ስለዚህ በዚህ አመት እንዴት እንደሚሄድ እናያለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ነገር ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።

አናዱሉ እንደዘገበው ደግሞ ቱርክ የBRICS  አባላት ሀገራትን ትብብር እየተመለከተች ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሁለት ቀን በፊትም ወደ ሩስያ አቅንተው ከBRICS አባሏ ሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዝግ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በBRICS አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል።

ፑቲን ከሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ቱርክ ስብስቡን ለመቀላቀል (አብሮ ለመስራት) ያሳየችውን ፍላጎት በደስታ ተቀብለው ፤ ወደ ስብስቡ እንድትቀላቀል ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

የቱርክ መንግሥት BRICS'ን ለመቀላቀል ርምጃ ይወስድ እንደሆነ እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም በይፋ ስብሰቡን ለመቀላቀል ያለውን ፍላጎት በይፋ አሳውቆ አያውቅም።

ቱርክ የ #NATO አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።

#BRICS+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።

#BRICS
#Turkey
#China
#Russia

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በአቢሲንያ አሚን አገልግሎት ውስጥ “መሸ” የሚል ቃል አይታወቅም - ፀሐይም አትጠልቅም! በቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን 24 ሰዓት እርስዎን በሐቅ ለማገልገል ዝግጁ ነን!

አቢሲንያ አሚን ዕሴትዎን ያከበረ!

#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia  #አቢሲኒያአሚን
#Banking #BanksinEthiopia  #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ዘህራ #የሴቶችቁጠባ #አቢሲንያአሚን
#AddisAbaba

° “ መሬቱ በኦዲት ሰበብ ታግዶ የበደል በደል ነው የደረሰብን ” - ማኀበራት

° “ቅሬታ ያላቸው ካሉ በማንኛውም ጊዜ መጥተው ማቅረብ ይችላሉ” - የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር


በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት በማኀበር ተደራጅተው ከቱሉዲምቱ እስከ ዓለም ባንክ ድረስ ቤት እየገነቡ የየበሩ ማኀበራት፣ “መሬቱ በኦዲት ሰበብ ታግዶ የበደል በደል ነው የደረሰብን” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በሰጡት ቃል፣ “እንደ ማኀበር በጋራ ሆነን ጥያቄ አቅርበን እየተከታተልን ነው ከ3 ዓመታት በላይ የቆየነው። ‘ያኔ ለጊዜው ይቁም፣ በፍጥነት ምላሽ ይሰጣል’ ተብሎ ቆሞ ነበር አሁን ስንሄድ ነው የሚያናግረን ሰው ያጣነው” ብለዋል።

ቦታዎቹ #ከቱሉዲምቱ እስከ #ዓለምባንክ እንደሚገኙ አመልክተው፣ “ አጠቃላይ 960 ማኀበራት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 217ቱን ‘ መስተንግዶ ያግኙ ’ ብለው ለቀውላቸዋል። የቀረነው ግን ‘ ይለቀቃል ’ ተብሎ ለረጅም ጊዜ እየታሸን ነው ” ሲሉ አማረዋል።

➡️ ቤት ለመገንባት ከባንክ ገንዘብ የተበደሩ እንዳሉ፣ 
➡️ የባንክ እዳቸውን ከፍለው ባለመጨረሳቸው መሬታቸው ለጨረታ የቀረበ እንዳሉ፣ 
➡️ ቤታቸውን ለመሸጥ የፈለጉ እንዳልቻሉ አስረድተዋል።

ይህ የሆነው ፣ “ ሕገ ወጥ #የመሬት_ወረራ በመኖሩ ኦዲት ይደረግ ” በሚል ሰበብ እንደሆነ፣ እነርሱ ግን መሬታቸው ሕገ ወጥ እንዳልሆነ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጸው፣ ከተማ አስተዳደሩ ኦዲቱን በፍጥነት አጣርቶና አጠናቆ እግዱን እንዲያነሳ ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የቅሬታ አቅራቢዎቹ ሰነድ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቱ ውል ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ የተገባ መሆኑን ፣ ከባንክ #በ100_ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እንደተበደሩ ያስረዳል።

ማኀበራቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ኃላፊዎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

በከተማ አስተዳደሩ የቅሬታና አቤቱታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባይነህ አመርቆ ቅሬታውን በተመለከተ ለመናኸሪያ ሬዲዮ በሰጡት ቃል ግን፣ “ግለሰቦች በሌላ ማኀበር የከተማዋን ሀብት ለግል ጥቅም ለማዋል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ይደረጉ እንደነበር ይታወቃል” ብለዋል።

“ ይህንምን መነሻ አድርጎም የተወሰኑ የታገዱ አሉ ፣ Specific የሚታወቁ ማለት ነው ” ብለው ፣ የእኚሁ አካላት ጉዳይ “ትክክለኛ ነው? ትክክል አይደለም ? የሚለው ነገር ተጣርቶ ውሳኔ የሚሰጣቸው ” እንደሆኑ አስረድተዋል።

“ ከዛ ውጪ ግን ቅሬታ ያላቸው ካሉ በማንኛውም ጊዜ መጥተው ማቅረብ ይችላሉ” ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Info

ዋትስአፕ በድምጽ እና በምስል ጥሪ ላይ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ መጥቷል።

የቪዲዮ ጥሪ ተሞክሮን ለማሻሻል በሚደረገው እንቅስቃሴ ዋትስአፕ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ይዞ መጥቷል።

እነዚህ ማሻሻያዎች ዓላማቸው የዋትስአፕ ቪዲዮ ጥሪን የበለጠ ሁለገብ እና ምቹ ለማድረግ ነው ፣ በተለይ ለትላልቅ ቡድኖች።

ዋትስአፕ አዲስ ይዞ የመጣው አዲስ ነገር ምንድነው ?

▪️የቪድዮ ጥሪ ላይ የሚሳተፍ ሰው ብዛት ጨምሯል።

ዋትስአፕ በሁሉም መሳሪያዎች ማለትም ሞባይል፣ ዊንዶውስ እና ማክ-ኦኤስ ላይ በቪዲዮ ጥሪ ላይ መሳተፍ የሚችሉትን ሰዎች ብዛት ወደ 32 አሳድጎታል። ይህም ትላልቅ የቡድን ስብሰባዎችን ዋትስአፕ ላይ ማድረግን ያስችላል።

▪️ስክሪንን ከድምጽ ጋር ማጋራት እንዲቻል አድርጓል።

ይህ ማሻሻያ በቪዲዮ ጥሪ ጊዜ ስክሪን ላይ የሚታየውን ነገር ከማንኛውም ኦዲዮ ጋር ማጋራትን ያስችላል። ይህ በቀጥታ በዋትስአፕ ውስጥ አብሮ ቪዲዮ ማየትን፣ ወይም አብሮ መስራትን ያስችላል።

▪️ቨዲዮ ጥሪ ላይ ተናጋሪው ሰው ላይ ምልክት ማድረግ እንዲቻል አድርጓል።

በቡድን የቪዲዮ ጥሪ ውስጥ የሚናገረውን ሰው ላይ የተለየ ምልክት መስጠት ጀምሯል። ይህም በቡድን ውስጥ ያሉ ንግግሮችን ለመከታተል ቀላል ያደርገዋል።

የደውል ጥሪን የበለጠ ለማሻሻል በተለይም ደካማ ኔትወርክ ወይም ቆየት ያሉ ስልኮች ላላቸው ተጠቃሚዎች የዋትስአፕ እናት ኩባንያ ሜታ (Meta) የሜታ ሎው ቢትሬት (MLow) አስተዋውቋል።

ይህ ስርአት የተነደፈው ከተገቢው ባነሰ ኔትወርክ ሁኔታ ውስጥ እንኳን የተሻለ ጥራት ለማቅረብ ነው።

#TikvahTechTeam

@tikvahethmagazine
#Tigray
 
ወደ 26 የትግራይ ወረዳዎች ለእርዳታ በመጓጓዝ ላይ ያለ #የተበላሸ የማሽላ እህል ለህዝብ እንዳይከፋፈል ታገደ።

እግዳውን ያስተላለፈው የትግራይ ክልል ምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ነው።

ከማሽላ እህሉ በተወሰደ የናሙና ምርመራ ውጤት መሰረት ፦
- መጥፎ ሽታ ያለው መሆኑ፤
- በነቀዝ የተበላና ወደ ዱቄትነት የመቀየር ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ፤
- በአጠቃላይ የበሰበሰና የተበላሸ በመሆኑ፡
ለምግብነት ቢውል የሚያስከትለው የጤና ጠንቅ እጅግ ከባድ ስለሆነ እህሉ በያለበት መጋዘን እንዲታገድ ተወስኗል።

በመጓጓዝ ላይ ያለውም እንዲቋረጥ ሲል መ/ቤቱ ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለወረዳዎቹ በፃፈው የእግድ ደብዳቤ አስታውቀዋል።

እግድ የተጣለበት የማሽላ እህል ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' በሚል በክልሉ የተቋቋመው በድርቅ እና በሰብአዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች ለማገዝ ከአገር ውስጥና ከውጭ ለጋሾች ባሰባሰው ብር የተገዛ ነው።

ግብረ ሃይሉ ሰነ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚድያዎች በሰጠው መግለጫ  እህሉ በግዢ ጊዜ በናሙና ከቀረበው ውጭ የሆነና የተበላሸ ለጤና ጠንቅ መሆኑ ስለተደረሰበት እንዳይከፋፈል ሲል ገልጿል።

መግለጫው ተከትሎ በማሽላ እህሉ ምርመራ ያካሄደው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥርና ክትትል መ/ቤት ፤ እህሉ የተበላሸና ለምግብነት ውሎ የሚያስከትለው አደጋ ከግምት ውስጥ በማስገባት  በ90 ሚሊዮን ብር በጨረታ የተገዛው የማሽላ እህል #እንዲታገድ ወስኗል።

እግዱን ተከትሎ ' አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ ግብረ ሃይል ' ሰነ 6/2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በሰጠው መግለጫ " እህሉ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ፤ ለመግዣ የተመደበው 90 ሚሊዮን ብር በ26 ወረዳዎች ለሚገኙ ተረጂዎች በጥሬ ገንዘብ እንዲከፋፈል ፤ የጨረታ ሂደቱ ተሰርዞ አህል አቅራቢው ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው 9 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ወስኛለሁ " ብሏል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
#መቐለ

@tikvahethiopia            
በፍቅር እና መተሳሰብ በሚከበረው የኢድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል ልዩ ድምቀት የሆኑትን የሞባይል ጥቅሎች እስከ 25% በሚደርስ ቅናሽ ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው!

በቴሌብር ሱፐርአፕ ከ10% ስጦታ ጋር፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም *999# ለራስዎም ይግዙ፤ በበዓል ስጦታ ወዳጅ ዘመድ ይዘይሩ።

ቴሌብር ሱፐርአፕ ለማውረድ http://onelink.to/fpgu4m ይጠቀሙ!

ኢድ ሙባረክ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን /የትምህርት ካላንደር/ ይፋ አደረገ።

የትምህርት ካላንደሩ በከተማው አስተዳደር ስር ባሉ የመንግስት፣ የግልና በሌሎች የተያዙ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ወጥነት ባለው መልኩ ይተገበራል ተብሏል።

ይፋ በተደረገው በዚህ የትምህርት ሰሌዳ መሰረት ፥ ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ አጠቃላይ የመምህራን ጉባኤ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ከነሃሴ 21-30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የ7ተኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ እንደሚከቅናወን ፤ ከጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው የሚመጡ አዲስ የተማሪዎች ምዝገባ እንደሚከናወን ተመላክቷል።

በከተማው መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ/ም   መደበኛ ትምህርት እንደሚጀምር የትምህርት ሰሌዳው ያሳያል።

ከጥር 19 እስከ 23 ቀን 2017 ዓ.ም አንደኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የ2ኛ ወሰነ ትምህርት እንደሚጀምር ተመላክቷል።

የ2017 ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 3 እስከ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የትምህርት ካላንደሩ (ሰሌዳው) ከሰኔ 9 እስከ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እንደሚሰጥ ይገልጻል።

(ሙሉውን ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
2024/09/27 04:22:28
Back to Top
HTML Embed Code: