Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
የቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ጭማሪ ተደረገ። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም ለሊት 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ ፣ የኬሮሲን ፣ የአይሮፕላን ነዳጅ ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #ባለበት_እንደሚቀጥል አሳውቋል። በዚህ መሰረት ፦ - ነጭ ናፍጣ ብር 79.75 በሊትር - ኬሮሲን ብር 79.75 በሊትር…
#እንድታውቁት

ከነገ ግንቦት 28 /2016 ዓ/ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

ስራ ላይ ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?

- ቤንዚን ➡️ ብር 78.67 በሊትር
- ነጭ ናፍጣ ብር 79.75 በሊትር
- ኬሮሲን ብር 79.75 በሊትር
- የአውሮፕላን ነዳጅ ብር 70.83 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ ብር 62.36 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ ብር 61.16 በሊትር ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የአከራይ እና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁ ይታወቃል፡፡

በዚህም አስተዳደሩ አዋጁን በመመሪያ በማስደገፍ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቶቹን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግል ቤት አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር ህጋዊ ሰነዶቻቸውን ይዘው በመቅረብ ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ቤት አከራዮች ፦

➡️ ህጋዊ የምዝገባ ውል ለመፈጸም ወደ ወረዳ ጽ/ቤቶች በሚሄዱበት ወቅት ቤቱ የራሳቸው ስለመሆኑ ወይንም ህጋዊ ተወካይ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተከራዮች ፦

➡️ ማንነታቸውን የሚገልጽ #መታወቂያ ወይም ሌላ ህጋዊ ማንነታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

በስራ ሰዓት መመዘግብ የማይችሉ አከራይና ተከራዮች ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በስራ ቀን ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ ህጋዊ የውል ምዝገባውን መፈጸም ይችላሉ።

#ENA
#Ethiopia
#AddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ የአከራይ እና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መጽደቁ ይታወቃል፡፡ በዚህም አስተዳደሩ አዋጁን በመመሪያ በማስደገፍ ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቶቹን ማጠናቀቁ ተገልጿል። ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ…
#ማስታወሻ

" የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 " ምን ይዟል ?

የመኖሪያ ቤት አከራዮች #በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ መጨመር #አይችሉም

አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪ አካል #በዓመት_አንድ_ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው።

ማንኛውም የቤት ኪራይ ጭማሪ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ 1 ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል።

የቤት ኪራይ ውል ዘመን #ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው።

አከራዮች #ከ2_ወር_የቤቱ_ኪራይ_በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ #አይችሉም

የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው #የመያዝ_ግዴታ አለባቸው።

ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት።

➡️ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል #ከሁለት_ዓመት ሊያንስ አይችልም።

NB. በአዋጁ መሠረት " ተቆጣጣሪው አካል ፣ ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡

More : https://www.tg-me.com/tikvahethiopia/86580

#Ethiopia
#የመኖሪያ_ቤት_ኪራይ_ቁጥጥርና_አስተዳደር_አዋጅ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቡሬ ➡️ “ 15 ተፈናቃዮች ናቸው በሚሊሻ የተወሰዱት ” - በአማራ ክልል የሚገኙ የወለጋ ተፈናቃዮች ➡️“ በቡሬ በኩል ስላለው መረጃ የለኝም ” - አቶ ኃይሉ አዱኛ በ2013 ዓ/ም ከኦሮማያ ክልል #ተፈናቅለው በአማራ ክልል ቡሬ ፣ ቻግኒ ፣ ፍኖተ ሰላም ፣ ባሕር ዳር የነበሩ ተፈናቃዮች ሰሞኑን ወደ ወለጋ ለመመለስ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ሰንቶም ቀበሌና ጣቦ የገጠር ከተማ ላይ ድንገተኛ ችግር…
#Update

“ 12 ሰዎች እስር ላይ ናቸው። 15 ቀናት አለፋቸው ፤ ምግብ አይገባላቸም ” - የታሳሪ ቤተሰቦች

ከወለጋ ተፈናቅለው በአማራ ክልል ፤ ቡሬ እና ሌሎች አካባቢዎች የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ወለጋ እየተመለሱ በነበረበት ወቅት “ ሰንቶም ” የሚባል ቦታ ሲደርሱ በሚሊሻ የተያዙ እንደነበሩ ከዚህ ቀደም ተዘግቦ ነበር።

አሁንስ የተያዙት ተፈናቃዮቹ ከምን ደረሱ ?

ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ በሰጡት ቃል፣ “ ያኔ ከመኪና አስወርደው ‘ቁጫ’ የሚባል ቦታ ላይ ለአንድ ሳምንት አሰሯቸው። በኋላም ከ‘ቁጫ’ ወደ ቡሬ አመጧቸው” ብለዋል።

የቡሬ አካላትን ሲጠይቁም ፥ “ ወደ አገራቸው ይሄዳሉ ብለን ላክናቸው መንገድ ላይ አስቀሯቸው። አሁን እዚህ አምጥተው አሰሯቸው። መከላከየ ነበር የያቸው ” እንዳሏቸው አስረድተዋል።

“ 12 ሰዎች በእስር ላይ ናቸው። 15 ቀናት አለፋቸው ፤ ምግብ አይገባላቸም። ገብቶ መጠየቅም አይቻልም ” ብለው፣ የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ እንዲያሰጧቸው ጠይቀዋል።

ተፈናቃዮቹ ለምን እንደታሰሩ እንዲሁም እንዲለቀቁስ ምን እየተሰራ እንደሆነ የጠየቅናቸው “ ተፈናቃዮቹን ፈርመው የላኩ ” የቡሬ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃይማኖት ሥራ ላይ እንደሆኑ ገልጸው ስልክ ዘግተዋል።

ቆይት ብለው በላኩት የፅሑፍ መልዕክትም ፣ “ በጣም ይቅርታ የፀጥታ ስራ በመስራት ላይ ሆኘ ነው ” ያሉ ሲሆን፣ የማይመቼዎ ከሆነ ለቀረበው ጥያቄ የፅሑፍ ምላሽ ይስጡ ቢባሉም የሰጡት ቃል የለም።

ወደ ወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም የኦሮሚያና አማራ ክልሎች ኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ተጨማሪ ሙከራ ቢደረግም ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

 #TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የአክሱም አፄ  ዮውሀንስ አራተኛ  ኤርፖርት #በተያዘለት_የጊዜ_ሰሌዳ አገልግሎት መስጠት እንዲጀመር የሚያስችሉት የጥገና ስራዎች አሁን ላይ ወደመጠናቀቁ መሆናቸው ተነግሯል። በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት የደረሰበት ኤርፖርቱ የጥገና ስራው ቀን እና ሌሊት እየተሰራ ነበር። የጥገና ተቆጣጣሪ አካል የአውሮፕላን ማረፍያው የሚገባውን ጥራት በያዘ ደረጃ ስራው እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል። በረራው…
#Update #Axum

የአክሱም ኤርፓርት ሰኔ 2/2016 ዓ/ም ዳግም የበረራ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። 

በትግራይ ጦርነት ከፍተኛ  የሆነ ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አፄ ዮውሀንስ አራተኛ  ኤርፖርት ሰኔ 2 የመጀመሪያ ዳግም በረራውን ያደርጋል።

እሁድ ሰኔ 2 በኤርፓርቱ ዳግም መደበኛ የበረራ  አገልግሎት ስነ-ሰርዓት ማስጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸው የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአክሱም ከተማ ኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ እና መጠነ ሰፊ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል። ውሳኔው የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በየዕለቱ ከሚመለከቱት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ተጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በላይ አመልካቾች የሚቀርቡ ከሆነ ጥያቄያቸውን ሳይመለከቱ በቀጥታ ከአገር እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን…
#Update

የአሜሪካ ፕረዚደንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ሲባል የሀገሪቱን ፍልሰተኞች ሕግ አጥብቀዋል።

ይህ የጆ ባይደን ውሳኔ ባለሥልጣናት በሜክሲኮ በኩል ድንበር አቋርጠው የገቡ ስደተኞችን / ጥገኝነት ጠያቂዎችን በቀጥታ በኃይል ወይም በግዳጅ  እንዲመልሷቸው ሥልጣን የሚሰጥ ነው።

ጉዳያቸው የሚመዘገቡ ሰዎች ዕለታዊ ኮታ ከተሟላ የተቀሩት ከአሜሪካ በኃይል እንዲወጡ ይደረጋሉ።

ከዚህ ባለፈ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የውጪ ዜጋ ወደ አገር እንዳይገባ " #እንዲታገድ " የሚል ትዕዛዝ ፕሬዜዳንቱ አስተላልፈዋል።

#ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪቃውያን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ እንደሚሻገሩ ይታወቃል።

አሜሪካ የፍልሰተኞችን ፍሰት ለመግታት በሚል ከሜክሲኮ የሚያዋስናትን ድንበር ከማጠር ጀምሮ በርካታ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።

ይህ የአሁኑ የፕሬዜዳንት ባይደን ውሳኔ ስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄያቸው ለሚመለከተው የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ቀርቦ ሳይታይ #በቀጥታ እንዲባረሩ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፤ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ግን ሕጉ የስደተኞችን መሰረታዊ መብት ይጥሳል ሲል ተቃውሟል።

መረጃው የጀርመን ዜና አገልግሎት፣ የዶቼ ቨለ እና ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#StateofEmergency #EHRC

" በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (#ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ጋር በተያያዘ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ።

በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “#ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ተፈጻሚነት አብቅቷል።

ይህንን ተከትሎ በእስር የቆዩ ሰዎችን የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥል ኢሰመኮ አሳስቧል።

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን ጋዜጣዊ መግለጫ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የክትትልና የምርመራ ሪፖርቶች ይፋ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ አስታውሷል።

በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውቅጥ #በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎችም ማኅበረሰባዊ #አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።

#EHRC #Ethiopia #StateofEmergency

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት🚨

2 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈቶች አሟልተው ባለመገኘታቸው ምክንያት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቢያ ተላለፈ።

1ኛ. #Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g) , (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56

2ኛ. #Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127

የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶች ያላሟሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስስር ሚኒስቴር አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን #በአዲስ_አበባ ደረጃ ለ7 ቀናት አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደትን ትላንት አጠናቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም  ፥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ጥያቄ እያቀረበ ፤ ማብራሪያም እየጠየቀ ይገኛል።

በብዛት ከሚነሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ ፥ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የተመረጡ 25 ተወካዮች እውነት የወከሏቸውን የአዲስ አበባ ማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎት እና ሀሳብ የማንጸባረቅ ብቃቱ አላቸው ወይ ? የሚል ነው።

እንዲህ ላሉት ጥያቄ አዘል ትችቶች የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ይላል ? 

ዶ/ር ዮናስ አዳዬ (ኮሚሽነር) ፦

“ ትችቶቹን #እናከብራቸዋለን። ተችዎቹ በራሳቸው አመለካከት ልክ ናቸው።

እኛ ግን በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ ብለን ያቀድነው 3,500 ሰዎችን ነው በአጠቃላይ።

25 ተመረጡ የተባሉት #አጀንዳውን_የሚያቀርቡልን እንጂ ተመርጠው ወደ #National_dialogue የሚሄዱ አይደሉም።

➡️ አንደበተ ርቱዕ ናቸው ?
➡️ የህብረተሰቡን ጥያቄ ያንጸባርቃሉ ? ለሚለው ጥያቄ ህዝቡ ‘ በአንጻራዊነት እነዚህ #ይሻሉኛል ’ ብሎ ከመረጣቸው መቀበል ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-05

@tikvahethiopia
#ሞት_ተፈርዶበታል !

ከአባቱ ጋር በገባበት " #የጥቅም_ግጭት " መላው ቤተሰቦቹን በጥይት ገድሎ ሊጨርስ የነበረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተፈረደበት።

ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ ይባላል።

በጋርዱላ ዞን የሃይበና ቀበሌ ነዋሪ ነው።

ግለሰቡ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሠገን ገነት ቀበሌ በመሄድ በ4 ቤተሰቦቹ ላይ የጥይት እሩምታ ይከፍታል።

በዚህም ሶስቱን ሲገድል አንዱን አቁስሏል።

በጥይት እሩምታ የገደላቸው ፦
- #አባቱ
- #እናቱ
- #አጎቱ ሲሆኑ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት የ9 አመት ታናሽ ወንድሙ ነው።

ግለሰቡ ይህን ፈጽሞ ከአካባቢዉ ቢሰወርም የጸጥታ ኃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር ተባብሮ ባደረገዉ ክትትል ከ5 ወራት በኋላ ሊያዝ ችሏል።

ፖሊስም ስራውን አጠናቆ ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተከሳሹም ፤ ከወላጅ #አባቱ ጋር በገባበት ' የጥቅም ግጭት ' ምክኒያት ወንጀሉን እንደፈጸመ ለፍርድ ቤቱ አምኖ ቃሉን ሰጥቷል።

ይህም ቃሉም ከቀረበበት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ጋር ተዳምሮ የፍርድ ሂደቱን ቀላል እንዳደረገዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

በዚህም በኃላ ጉዳዩን ሲመረምር የነበረዉ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ #በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

በተከሳሹ ላይ የተጣለው #የሞት_ፍርድ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC የግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፦ በቤተ ክርስቲያኗ በሀገራዊ እንዲሁም በወቅታዊ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ለተከታታይ ቀናት ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የማጠቃለያ መግለጫ ነገ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጧቱ 4፡00 ሰዓት እንደሚሰጥ ተነግሯል። #የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን #ኢትዮጵያ…
#ኢትዮጵያ

ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት 2016 ዓ/ም የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እና የግብረ ሰዶማዊነትን #ኃጢአት በተመለከተ አጀንዳ አድርጎ መወያየቱ ተሰምቷል።

በዚህም፥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያኗን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ #ዓለም_አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር የሆነ መግለጫ እንዲሰጥ ወስኗል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የ4 አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት #እንዲሰረዝ መወሰኑን አሳውቋል።

ሠርተፍኬታቸው የተሰረዘው ፦

1ኛ. ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ነብይ ኢዮብ ጭሮ

2ኛ. ገዥዋ ዓለም አቀፍ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መጋቢ ካሳ ኪራጋ

3ኛ. የሰማይቱ ጽዮን ማኅበርተኞች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መጋቢ ሚስጥሩ መዝገቡ

4ኛ. የእግዚአብሔር መንግስት እውነት ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ መጋቢ  ቢንያም ሽታዬ ... ናቸው።

ውሳኔው የተለለፈባቸው በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ምክንያት ነው።

ካውንስሉ እነዚህ አካላት የተሰጣቸውን የሕግ ከለላ በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮና ጤናማ ሥነ ምግባር ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበሩ ገልጿል።

ከዚህ ተግባራቸው ይመለሱ ዘንድም አስፈላጊውን ትምህርትና ምክር ሲሰጥ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ምክሩ ተቀበለው ሕዝብን ከሚያሳስት ተግባራቸው #ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ሠርተፍኬታቸው እንዲሰረዝ ወስኗል።

(ካንውስሉ ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
2024/09/28 07:32:31
Back to Top
HTML Embed Code: