Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹 ከነገ ግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ቀናት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል። ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃን። የስብሰባው ሥርዓቶች ምንድናቸው ? 1. ማንኛውም ተሳታፊ #በነጻነት ሀሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ሆኖም ተሳታፊዎች ከጥላቻ፣ ከአዋራጅ እና ከተንኳሽ ንግግሮችመቆጠብ፤ 2. በምክክሩ ጊዜ መደማመጥን…
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

በአዲስ አበባ የተጀመረው የአጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ምን መልክ አለው?

በአዲስ አበባ የተጀመረው የአጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ከዛሬ ግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል። በሂደቱ ከ2,500 በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፋሉ።

በዋናነት ከዚህ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ምን ይጠበቃል?

- 2,500 ከሚሆኑት ተሳታፊዎች በቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ምክክር አዲስ አበባን ወክለው የሚሳተፉ ተወካዮች ይመረጣሉ

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ጉባኤ ይሰየማል

- በአዲስ አበባ ደረጃ በሀገራዊ ምክክሩ ላይ መቅረብ አለባቸው የሚባሉ አጀንዳዎች ይዘጋጃሉ።

በእነዚህ 7 ቀናት ምክክር ኮሚሽኑ ምን ሊያከናውን አቅዷል?

#ቀን_1 እና #ቀን_2

- በመጀመሪያው ቀን በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ የምክክር ምዕራፉ መክፈቻ ሥነ-ስርአት ይካሄዳል። (ይሄ መርሐግብር ዛሬ ጠዋት በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል)

ከመጀመሪያው ቀን የከሰዓቱ መርሐግብር ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ቀን መጨረሻ ድረስ፦

- 11 የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች  ከ100 በማይበልጥ ቡድን ተከፍለው ይወያያሉ።

- እያንዳንዱ ቡድን ህበረተሰቡን ወክሎ በሚቀጥሉት የምክክር ሂደቶች ሊሳተፉ
የሚችሉ 22 እጩዎችን ይለያሉ።

#ቀን_3

- በቡድን ሲደረግ የነበረው ምክክር ውጤት በየተራ ለቤቱ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይካሄድበታል።

- ከተለዩ እጩዎች ውስጥ 11 የህብረተሰቡ ወኪሎች በሚስጥር ድምጽ አሰጣጥ ይመርጣሉ፡፡

በዚሁ ቀን በተጓዳኝ በከተማ አስተዳደር ደረጃ የተወከሉ ቁጥራቸው 1,220 የሚደርሱ ባለድርሻ አካላት ውይይት ይደረጋል። (ባለድርሻ አካላት የሚባሉት ታዋቂ ሰዎች፤ ፖለቲከኞች ከተቋማትና ማኅበራት የሚሳተፉ አካላት ናቸው።)

#ቀን_4

ዋናው የመክፈቻ  ሥነ-ስርዓት (Launching Ceremony) ይከናወናል

- ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችን ጨምሮ 3,500 ተሳታፊዎች በዋናው የመክፈቻ  ሥነ-ስርዓት ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ።

#ቀን_5

- ተሳታፊዎቹ በ5 ቡድን ( ከወረዳ የተወከሉ (ብዛት 121 )፤ መንግስት፤ የፖለቲካ ፖርቲዎች፤ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት፤ ታዋቂ ሰዎች (ብዛት 1220) ተከፍለው የአጀንዳ ምክክራቸውን ይቀጥላሉ፤ አጀንዳዎቻቸውን ይለያሉ።

በተጨማሪ ከአምስቱ ቡድኖች በተናጠል የምክክር ውጤቶችን የሚያጠናክሩና የሚያዳዳብሩ 5 ተወካዮች በድምሩ 25 ተወካዮች ይመረጣሉ።

#ቀን_6

- ጠዋት 1,340 ተሳታፊዎችን የያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ጉባኤ ይሰየማል፡፡ 

- 5ቱም ቡድኖች ለጉባኤው የምክክራቸውን ውጤት ሪፖርት ያቀርባሉ፤ በሪፖርቱ ላይም ውይይት ይደረጋል።

- ከየቡድኑ የተመረጡ 25ቱ ሰዎች በጋራ የ5ቱን ቡድኖች አጀንዳ አንድ ላይ በማምጣት ኮሚሽኑ ባስቀመጠው መሰፈርት መሰረት ያደራጃሉ፡፡

#ቀን_7

- 25ቱ ወኪሎች ያደራጆቸውን አጀንዳዎች ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርቡና ሙሉ ቀን ውይይት ይደረግበታል፡፡  

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አጀንዳ ግብዓት ተለይቶ ለኮሚሽኑ ይሰጣል፡፡

- 25ቱ ተወካዮች የከተማ አስተዳደሩን የተጠቃለለ እጀንዳ ለማደራጀት ሦስት መስፈርቶች ይጠቀማሉ። እነዚህም አስቸኳይ ፤ አስፈላጊ እና  ከፍተኛ ውክልና ያለው በሚል የሚለዩ ይሆናሉ።

#TIKVAHETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢንተርን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተር ሀኪሞች ከስራ ሰዓትና ክፍያ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ኢንተርን ሀኪሞቹ ምን አሉ ? “ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሆስፒታሉ የኢንተርን ሀኪሞች የሥራ ሰዓት ወደ 24 ሰዓታት ዝቅ እንዲል ተደርጎ ነበር። ነገር ግን የኮሌጁ ግለሰብ / #ዳይሬክተር ሲቀየር በራሱ ውሳኔ የራሱን መላምት በመፍጠር መልሶ ወደ 36 ሰዓታት ከፍ አድርጎታል።…
#ኢንተርን #UoG

“ በኢንተርን ምዘና የተጻፈ መስፈርት የለም ” - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተርን ሀኪሞች

“ ቢሮ መጥተው ይጠይቁ ” - ዩኒቨርሲቲው

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2016/17 ዓ/ም ኢንተርን ሀኪሞች ፦
- በኢንተርንሽፕ ምን ያህል መስራትና መማር እንዳለብን፣
- ምን መስራትና ምን እውቀት ማምጣት እንዳለብን፣
- በኢንተርን ምዘና የተፃፈ ሰዓትና መስፈርት ባለመኖሩ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በተያያዘ በዩኒቨርሲቲዎቲው ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው ለህክምና መስጫ ተረኛ አዳሪ እረፍት (Day off) እንዲሰጣቸው ኢንተርን ከመጀመራቸው ከሳምነት በፊት በደብዳቤ በመጠየቃቸው የ3 ወራት ደመወዝ እንደተቆረጠባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

“ ሥራ ከመጀመራችን ከ3 ቀናት በፊት በሥራና ትምህርት ገበታችን ላይ እንደማንገኝ በደብዳቤ አሳውቀን ከትምህርት ገበታችን ሳንገኝ ቀርተናል ” ብለው ፣ በዚህም የ3 ወራት ደመወዛቸው እንደተቆረጠና ሥራ ቢጀምሩም እንዳልተከፈላቸው አስረድተዋል።

ለተከታታይ 34 ሰዓታት ያለ እረፍት መስራት፣ በሳምንት ከ90 - 94 ሰዓታት መስራት፣ አለፍ ሲልም እስከ 118 ሰዓታት በመስራት አስቸጋሪና ከአቅም በላይ የሆነው አሰራር ካልተቀየረ፦
📌 የአእምሮ መዛል፣ የመንፈስ መቃወስ የሚስከትል
📌 የህክምና ስህተት የሚፈጥር
📌 ከሥራ በቂ እውቀት የማያስገኝ
📌 የእኩልነት መብት የሚጥስ መሆኑን በማስረዳት ሥራና ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ጠይቀው በሥራ ጫናና በሌሎች ምክንያቶቾ ጥያቄውን ክትትል ሳያደርጉበት እንደቆዩ አስረድተዋል። 

“ ሆኖም ግን በጥያቄው ዙሪያ ተወያይተን መፍትሄ እናገኛለን ብለን ስንጠብቅ ቅጣት ተጣለብን ” ብለው፣ ለ4 ቀናት ከቆዩ በኋላ ወደ ሥራ ገበታ ቢመለሱም የ3 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል።

የኢንተርን ምዘና መስፈርቱን፣ የሥራና መማሪያ ሰዓት ገደብ አለመቀመጡን በተመለከተ ለተነሳው ቅሬታ ምላሽ የጠየቅናቸው የጤና ሳይንሱ አካል ዶክተር ሙሉጌታ፣ “ ይህን ጥያቄ ካላቸው ቢሮ መጥተው ይጠይቁ ” ብለዋል።

“ ተገቢ ዶክሜንት አለ። ስርዓተ ትምህርቱ አለ። ይህን የሚያስፈጽሙ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች አሉ። በእነርሱ በኩል መልስ እንሰጣለን ” ሲሉ አክለዋል።

የደመወዝ መቆረጡን በተመለከተ በሰጡት ቃልም፣ “ ነገሩን ለማሳጠር ያህል ባለፈው ዶክተር አይንሸት የሰጠው መልስ ተገቢ ነው። የተለዬ መልስ ተጨማሪ መረጃ የለኝም ” ነው ያሉት።

ዶ/ር አይንሸት የደመወዝ ቅሬታውን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ የኢንተርን ሀኪሞቹ ጥያቄ አቀራረብ ልክ ባለመሆኑ የ3 ደመወዝ እንደተቆረጠባቸው ገልጸው ነበር።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#Attention ⚠️

" ራኒቲዲን #ካንሰርን ሊያመጣ የሚችል ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ምክንያት #ታግዷል " - የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን

ለጨጓራ ተያያዥ ህመሞች በመድኃኒትነት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው ' ራኒቲዲን ' የተባለው መድሃኒት በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል #ማገዱን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የባለስልጣኑ የመድኃኒት ደህንነት ክትትልና የሕክምና ሙከራ መሪ ስራ አስፈጻሚ አስናቀች ዓለሙ ፤ " በመጀመሪያ ደረጃ በሌሎች ሀገር የወጡ ሪፖርቶችን አይተን ነበር። ስለዚህ በሀገራችንስ ይሄ መድሃኒት እንዴት ነው ? የሚለውን በማገናዘብ የላብራቶሪ ምርመራ አድርገናል " ብለዋል።

በዚህም መድሃኒቱ ካንሰር ሊያመጣ የሚችል ' N-nitrosodimethylamine ወይም NDMA ' የተሰኘ ንጥረ ነገር እንደተገኘበት መሪ ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።

" በመሆኑም ይህንን መድሃኒት ከምዝገባ ፋይላችን አውጥተናል። የተሰራጩ መድሃኒቶችም #እንዲሰበሰቡ እና ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መልእክት አስተላልፈናል " ብለዋል።

" በዚህ በሰረትም ጥቅም እንዳይውል #ታግዷል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

" የጤና ባለሙያዎችም፣ የጤና ተቋማትም ሌሎች አማራጭ መድሃኒቶችን እንዲያዙ እና እንዲጠቀሙ ይህንን መድሃኒት #እንዳይጠቀሙ " ሲሉም አሳስበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#DStvEthiopia

🏆 የአውሮፓ ቻምፒዮን ማን ይሆን

⚽️ ሪያል ማድሪድ አይኑን ሌላ ዋንጫ ላይ ጥልዋል! ዶርትመንድ ከሞት ምድብ ድኖ ፒኤስጂን በመጣል ቅዳሜ ግንቦት 24 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በለንደን ዌንብሊ ለፍፃሜው ይገናኛሉ!

🔥 ዋንጫው የማን ነው?

👉 ይህንን ደማቅ ፍልሚያ በSS Football 222 በሜዳ ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DARMA

ግሬስ ኮንስትራክሽን ኬሚካልስ " DARMA " በሚባል ብራንድ የሚታወቁ ከ 15 በላይ የውሀ ስርገት መከላከያ፤ የወለል እና ግድግዳ ፊኒሺንግ አንዲሁም ከ ኮንክሪት ጋር የተያያዙ ማንኛውንም አይነት ኬሚካሎችን ከ8 አመታት በላይ በጥራት፤በፍጥነት እና በታማኝነት በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ 

ተጠቃሚዎች ላላቸው ጥቄዎች በነጻ የሚያማክር በመሀንዲሶች የታገዘ ቴክኒክ ክፍል መኖሩም ለብዙዎች መተማመንን ፈጠሮላቸዋል፡፡

ግሬስ ኮንስትራክሽን ኬሚካልስ ከግንቦት 22 እስከ 24 በሚሊኒየም አዳራሽ በሚካሄደው የBIG 5 CONSTRUCT ETHIOPIA አለምአቀፍ ኤግዚቢሽን የወርቅ ደረጃ ስፖንሰር መሆኑንና ምርቶቹንም እንዲጎበኙ ሲጋበዝዎ በታለቅ ደስታ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በ ስ.ቁ 0964234444 ወይም 0929337886 ይደውሉ ወይም ወሎ ሰፈር አይቤክስ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው ዋና ቢሮ ብቅ ይበሉ፡፡
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " አሁን ላይ ያሉ ችግሮች ምፍትሄ እስካላገኙ  ስለ ምርጫ ማሰብ #ቀልድ ነው " - አቶ ግርማ በቀለ የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሕብር) ሊቀ መንበር አቶ ግርማ በቀለ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድረገዋል። Q. የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት ጥሰትን በተመለከተ ስለሚነሱ ጉዳዮች የፓርቲዎ ግምገማ ምን ይላል ?   አቶ ግርማ…
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል።

የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

Q. ከዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት አንፃር የፓርቲዎን ግምገማና መፍትሄውን ቢገልጹ ?

አቶ ጀሚል ሳኒ፦

“ ሰዎች በተደጋጋሚ ሕይወታቸውን እያጡ ነው። በዋና ከተማዋ ሲይቀር ሰዎች እየታሰሩ፣ እየታገቱ ነው።

የትኛውም ዜጋ የደህንነት ስሜት እየተሰማው አይደለም። 

መንግስት #በዋነኛነት የተመሠረተበትና እንዲሰራው ኃላፊነት የተሰጠው ስራ ከየትኛውም ቅድሚያ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የተዘነጋ የሚመስልበት ዘመን ላይ ነን።

በመወያየትና በመነጋገር ጦርነትን ማስቆም ይገባል።

ሰላምን ከማስፈን ይልቅ #ስልጣንን_የመጠበቅ ፣ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራት ነው አብዛኛው አቅም እየባከነ ያለው።

ከዚያ ይልቅ አገሪቱን በሚያሻግሩ ሀሳቦች ላይ አተኩሮ መስራት ያስፈልጋል።

ያለፉትን ዘመናት እንደ ቅንጦተ እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው። ”

Q. በሙስና ተዘፍቀው ስለሚገኙ ባለስልጣናት እንዲሁም በአጠቃላይ ስለብልሹ አሰራር ፓርቲዎ ምን ይላል ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ አሁን ላይ #ሀዘኔታዎች_የጠፉበት ፣ ሌላው ይቅርና የዜጎች ቤቶች ‘ሕገ ወጥ ናቸው’ ተብለው ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ላይ ገንዘብ የሚጠየቅበት ሁኔታ ነው ያለው። 

ከኢትዮጵያ Norm ሁላ ያፈነገጠበት ወቅት ላይ ነው ያለነው። በአብዛኛዎቹ መስሪያ ቤቶች የተለመደውን አይነት አሰራር ከመስራት ይልቅ ከእግሮች እጆች እየቀደሙ ነው።

#ሙስና_በግልጽ_እየተጠየቀ ፣ ቢሮ ውስጥ ሥራ አስፈጻሚዎች #በግልጽ_ድርድር እያደረጉበት ያለበት ሂደት ነው አሁን ያለው።

አለ የተባለ የትኛውም ችግርን ለመቅረፍ ላይከብድ ይችላል ፤ ነገር ግን ከተንሰራፋ የትኛውንም ችግር ልቅረፍ ማለት የማይታሰብ ይሆናል። 

ሙስና የሀገር ተቋርቋሪነትን፣ ስሜትን ያጠፋል።

እያየነው ያለውም ይሄው ነውና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።”

Q. እንደ ፓርቲ የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ የምስረታ ጉባዔ ባደረግንበት፣ የጉባዔውን ውጤትና የምርጫ ቦርድ ኮሮጆ ጭምር ይዘን በነበረበት ሰዓት ነው እስር የተጀመረው። ክፍለ አገርም አዲስ አበባም እስሮች አሉ። 

በአባል ደረጃ አንድ የፓርቲው አባል ከ5 ወራት በላይ ያለ ክስና ዋስትና በእስር ላይ ይገኛሉ። ከአባላቶች እስራትና ተንቀሳቅሶ ከመስራት ጋር ዘተያያዘ ያለፉትን ዘመናት እንደ ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው።

ፓርቲውን የሚደግፉ አባላት #ወጣቶች_እየተላኩ ማስፈራሪያ ያደርሱባቸዋል።

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ሕገ መንግስቱን ያልከተለ በመሆኑ ምስረታው እንዲታገድ፣ ኢ - ሕገ መንግስታዊ ስራዎች በሰሩ ባለስልጣናት ላይ የመሰረትነው ክስ በቀጠሮ እየተጉላላ ነው ያለው። ”

Q. ሕዝቡ በኑሮ ውድነቱ ተማሯል። ለዚህም “ መንግስት ትኩረት አልሰጠም  ” የሚሉ ወቀሳዎች ይቀርባሉ። የፓርቲዎ ግምገማ ምንድን ነው ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ የኑሮ ውድነት በራሱ የሚፈጠር ነገር አይደለም። እስካሁን ከላይ የተነጋገርንባቸው ነገሮች ናቸው እየገፉ የሚያመጡት። 

አንዲት አገር #በጦርነት ላይ ሆና ሚሊዮን ዶላሮችም ለጦርነት እያወጣች ፣ አርሶአደር ማምረትና በሰላም ወጥቶ መግባት ባልቻለበት ፣ የመልካም አስተዳደር ፣ የአቅም ፣ የብቃት ጉዳዮች የመጨረሻ ውጤታቸው የኑሮ ውድነቱ ማምጣት ነው።

እነዚህን ችግሮች ማጥፋት፣ መቀነስ ካልተቻለ የኑሮ ውድነቱን ማረጋጋት፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ማስፈን አይቻልም። ”

Q. ስለምርጫ ያላችሁ አስተያዬት ምንድን ነው ? በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?


“ ከምርጫ ጋር በተገናኘ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራው፣ አጀንዳውም የሚያዘው ከሚደረገው #የፓርላማ እና #የክልል_ምክር_ቤቶች ጋር በተገናኘ ነው። 

ይሄ ስርዓቱን ለመቀየር የሚያስችል ብቸኛው መንገድ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ምርጫ በየአካባቢው ማድረግ ያስፈልጋል። የአካባቢ ምርጫ የተደረገው ከ8 ዓመታት በፊት ነው።

የአካባቢ ምርጫ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

አሁን ባለንበት ሁኔታ ላይ #ምርጫ ሊደረግ ይችላል ብሎ ማለት ትንሽ አዳጋች ነው። ”

◾️በቀጣዩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፓርቲ የሰጠው ቃል ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
2024/09/27 21:31:33
Back to Top
HTML Embed Code: