Telegram Web Link
#DStvEthiopia

đŸ’Ĩ አንá‹ĩም ጎል áŖ አንá‹ĩም ደቂቃ áŠĨንá‹ŗá‹ĢመልáŒŖá‰Ŋሁ!

👉 ዛáˆŦውኑ ደንበኝነá‰ĩዎን á‹ĢáˆĢዝሙ áŖ ሁሉንም ጨዋá‰ŗ በላቀ áŒĨáˆĢá‰ĩ ይመልከቱ!

የዲኤáˆĩቲá‰Ē አገልግሎá‰ļá‰Ŋን ለማግኘá‰ĩ ከá‰ŗá‰Ŋ á‹Ģለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይáŒĢኑ ወይም *9299# ይደውሉ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#ሁሉምá‹ĢለውáŠĨኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ወንá‹ļá‰Ŋ በá‰ĩምህርá‰ĩ ሰአá‰ĩ ሁሉ የቀን áˆĩáˆĢ በመáˆĩáˆĢá‰ĩ ርሀá‰Ŗቸውን ለማáˆĩá‰ŗገáˆĩ በáŒĨረá‰ĩ ላይ ሲሆኑ ሴá‰ļá‰Ŋም ላልተገá‰Ŗ á‰Ŋግር ተጋልጠዉ መማር አልá‰ģሉም " - የደቡá‰Ĩ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ መምህáˆĢን ማህበር የደቡá‰Ĩ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ክልል መምህáˆĢን ማህበር አደረኩá‰ĩ á‰Ŗለው ማáŒŖáˆĢá‰ĩ በክልሉ ውáˆĩáŒĨ á‰Ŗሉá‰ĩ የመምህáˆĢን ማሰልጠኛ ኮሌጆá‰Ŋ ለመማር የተመደቡ ዕጩ መምህáˆĢን ሁሉም በሚá‰Ŗል መልኩ  á‰ĩምህርá‰ŗቸውን በፋይናንáˆĩ áŠĨáŒĨረá‰ĩ በአግá‰Ŗቡ áŠĨየተማሩâ€Ļ
" á‰Ŋግሩ በሚá‰Ŗለዉ ደረጃ የተጋነነ á‰Ŗይሆንም ጊዜá‹Ģዊ áŠĨርምጃ ለመዉሰá‹ĩ áŠĨንቅáˆĩቃሴ ጀምáˆŦá‹Ģለሁ " - የደቡá‰Ĩ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ክልል á‰ĩምህርá‰ĩ á‰ĸሎ

ከሰሞኑ በደቡá‰Ĩ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ክልል á‰Ŗሉ መምህáˆĢን ማሰልጠኛ ኮሌጆá‰Ŋ ለመማር የተመደቡ ዕጩ መምህáˆĢን ሁሉም በሚá‰Ŗል መልኩ á‰ĩምህርá‰ŗቸዉን በፋይናንáˆĩ áŠĨáŒĨረá‰ĩ áŠĨየተማሩ አለመሆኑን የደቡá‰Ĩ áŠĸá‰ĩá‹ŦáŒĩá‹Ģ ክልል መምህáˆĢን ማህበር ለቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ መግለጹ ይá‰ŗወáˆŗልáĸ

ወንá‹ļá‰Ŋ á‰ĩምህርá‰ĩ መማር ሲገá‰Ŗቸው የቀን áˆĩáˆĢ áŠĨየሰሩ áŠĨንደሆነና ሴá‰ļá‰Ŋም ላልተፈለገ á‰Ŋግር መጋለáŒŖቸውን ጠቁሞ ነበርáĸ

ተማáˆĒዎቹ በ2015 ዓ/ም ወደ ኮሌጆá‰Ŋ ሲገቡ ከመንግáˆĩá‰ĩ የሚሰáŒŖቸዉ 450 á‰Ĩር በቂ áŠĨንá‹ŗልሆነ áŠĨየá‰ŗወቀ á‰ĸጀመርም áŠĨáˆĩáŠĢሁን አለመáˆĩተáŠĢከሉንና ለዚህም በተከá‰ŗá‰ŗይ ደá‰Ĩá‹ŗቤ መጠየቁን ማህበሩ መግለጹ አይዘነጋምáĸ

ጉá‹ŗዩን በተመለከተ የክልሉ á‰ĩምህርá‰ĩ á‰ĸሎ አáˆĩተá‹Ģየቱን ለቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ሰáŒĨቷልáĸ

የá‰ĸሮው ምክá‰ĩል ሀላፊ á‹ļ/ር á‰ŗምáˆĢá‰ĩ ይገዙ ፤ " ጉá‹ŗዩ በተá‰Ŗለዉ ልክ የተጋነነ á‰Ŗይሆንም የተወሰነ á‰Ŋግር መኖሩን አውቀን áŠĨየሰáˆĢንበá‰ĩ ነው " á‰Ĩለዋልáĸ

" ለá‰Ŋግሩ የአጭር ጊዜ መፍá‰ĩሄ ለመáˆĩጠá‰ĩ áŠĨንቅáˆĩቃሴ ጀምረናል " á‹Ģሉá‰ĩ ሀላፊው " አሁን ላይ ተማáˆĒዎቹ á‹Ģለá‰Ŗቸዉን የቤá‰ĩ áŠĒáˆĢይ á‰Ŋግር ለማቅለል ከዲላ áŠĨና ከአርá‰Ŗምንጭ ዩኒቨርሲቲዎá‰Ŋ ጋር መነጋገር ጀምረናል " á‰Ĩለዋልáĸ

ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር áŒĨሊ መግá‰Ŗá‰Ŗá‰ĩ ላይ መደረሱን የገለጹá‰ĩ á‹ļ/ር á‰ŗምáˆĢá‰ĩ ከአርá‰Ŗምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋርም ሂደቱ áŒĨሊ መሆኑን አመልክተዋልáĸ

" በቋሚነá‰ĩ á‰Ŋግሩን ለማáˆĩተáŠĢከል áŠĨየሰáˆĢን ነውáĸ ምናልá‰Ŗá‰ĩም ለሚቀáŒĨለዉ አመá‰ĩ ሲመጡ የሚከፈላቸዉ ገንዘá‰Ĩም ይጨምáˆĢል á‰Ĩá‹Ŧ አáˆĩá‰Ŗለሁ " ሲሉ ገልጸዋልáĸ

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Ethiopia

" አምá‰Ŗáˆŗደሩ ንግግáˆĢቸው ሀገáˆĒቷን áŠĨንዴá‰ĩ መምáˆĢá‰ĩ áŠĨንá‹ŗለá‰Ĩን á‹Ģልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ ነው " - መንግáˆĨá‰ĩ

የáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ መንግáˆĨá‰ĩ በአሜáˆĒáŠĢ አምá‰Ŗáˆŗደር የተንጸá‰Ŗረቀው ሀáˆŗá‰Ĩ " ሀሰተኛ áŠĨና ተቀá‰Ŗይነá‰ĩ የሌለው ነው " á‰Ĩሎá‰ŗልáĸ

በáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ የአሜáˆĒáŠĢ አምá‰Ŗáˆŗደር ኧርá‰Ēን ማሲንጋ á‰ĩላንá‰ĩ አሜáˆĒáŠĢ áˆĩለ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ á‹Ģላá‰ĩን ፖሊሲ በንግግር ማሰማá‰ŗቸው ይá‰ŗወáˆŗልáĸ

ይህን በተመለከተ ዛáˆŦ የáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ መንግáˆĨá‰ĩ በውጭ ጉá‹ŗይ በኩል መግለáŒĢ አውáŒĨቷልáĸ

በዚህም የአምá‰Ŗáˆŗደሩ ንግግር " በተረጋገጠ መረጃ ላይ á‹Ģልተመሰረተ ነው " á‰Ĩሎá‰ŗልáĸ

" በምርáŒĢ ወደ áˆĩልáŒŖን የመáŒŖን መንግáˆĩá‰ĩ áŠĨንáŒĨላለን በሚል የሚንቀáˆŗቀሱáŖ ንጹሃንን ከሚá‹Ģግቱና ከሚá‹Ģሸá‰Ĩሊ አáŠĢላá‰ĩ ጋር መንግáˆĩá‰ĩን መáŒĨቀáˆŗቸውም ተገá‰ĸ አይደለም " á‰Ĩሏልáĸ

ንግግáˆĢቸው " የáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ መንግáˆĩá‰ĩ ሀገáˆĒቷን áŠĨንዴá‰ĩ መምáˆĢá‰ĩ áŠĨንá‹ŗለበá‰ĩ á‹Ģልተጠየቀ ምክር ለመመምከር የሞከረ ነው " በማለá‰ĩ ገልጾá‰ŗልáĸ

" ከሁለቱ ሀገáˆĢá‰ĩ á‰ŗáˆĒáŠĢዊና ወá‹ŗጅነá‰ĩ ላይ ከተመሰረተው ግንኙነá‰ĩ የተቃረነ ነው " ሲልም አክሏልáĸ

መንግáˆĨá‰ĩ በመግለáŒĢው ላይ ፤ " የተፈጸመው ዲፕለማሲá‹Ģዊ áˆĩህተá‰ĩ ነው " á‹Ģለ ሲሆን በአዲáˆĩ አበá‰Ŗ ከሚገኘው የአሜáˆĒáŠĢ ኤምá‰Ŗሲ ጋር በመáˆĩáˆĢá‰ĩ የተፈጠረውን áˆĩህተá‰ĩ áŠĨንዲá‰ŗረም áŠĨንደሚደርግ ገልáŒŋልáĸ

áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ የሰላምና የጸáŒĨá‰ŗ ጉá‹ŗዮá‰Ŋን ጨምሮ ከአሜáˆĒáŠĢ ጋር ለመáˆĩáˆĢá‰ĩ á‹Ģላá‰ĩን ዝግጁነá‰ĩም ገልáŒŋልáĸ

@tikvahethiopia
" ፖሊáˆĩ ከተማáˆĒዋ ህልፈተ ህይወá‰ĩ ጋር በተá‹Ģá‹Ģዘ ምርመáˆĢ áŠĨá‹Ģደረገ ነው " - አáˆļáˆŗ ዩኒቨርሲቲ

በአáˆļáˆŗ ዩኒቨርሲቲ የጂáŠĻግáˆĢፊ á‰ĩምህርá‰ĩ ክፍል የ4ኛ ዓመá‰ĩ ተማáˆĒ የነበረá‰Ŋው ተማáˆĒ ደáˆĢርቱ ለሜáˆŗ ህይወቷ አልፏልáĸ

ዩኒቨርሲቲው የተማáˆĒዋን ሞá‰ĩ 'á‹ĩንገተኛ ህልፈá‰ĩ'  በማለá‰ĩ በይፋዊ የማህበáˆĢዊ á‰ĩáˆĩáˆĩር ገጹ ላይ የሀዘን መልዕክá‰ĩ አሰáˆĢጭቷልáĸ

ቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ተማáˆĒዋ ' #በጩቤ_ተወግá‰ŗ ህይወቷ áŠĨንá‹ŗለፈ ' የሚገልፁ መረጃዎá‰Ŋን ተመልክቷልáĸ ይህን ተከá‰ĩሎ ዩኒቨርሲቲውን አነጋግሯልáĸ

በጉá‹ŗዩ ላይ áŒĨá‹Ģቄ á‹Ģቀረá‰Ĩንላቸው አንá‹ĩ የአáˆļáˆŗ ዩኒቨርሲቲ አመáˆĢር፤ " ፖሊáˆĩ ከተማáˆĒዋ ህልፈá‰ĩ ጋር በተá‹Ģá‹Ģዘ የጠረጠረውን ግለሰá‰Ĩ በቁáŒĨáŒĨር áˆĩር በማዋል ምርመáˆĢ áŠĨá‹Ģደረገ ይገኛል " á‰Ĩለዋልáĸ

" በዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የማህበáˆĢዊ á‰ĩáˆĩáˆĩር ገáŒŊ ላይ የተሰáˆĢጨው መረጃ ጉá‹ŗዩ ገና በፖሊáˆĩ የተá‹Ģዘ በመሆኑን ነው " ሲሉ አáˆĩረá‹ĩተዋልáĸ

ዩኒቨርሲቲው የተማáˆĒዋን አáˆĩክáˆŦን ወደቤተሰá‰Ļá‰ŋ አሸኛኘá‰ĩ ማá‹ĩረጉንም ለቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ገልፀዋልáĸ

Via @tikvahuniversity
" የ18 ወáˆĢá‰ĩ የዱቲ ክፍá‹Ģ አልተከፈለንም " - የዲላ ዙáˆĒá‹Ģ ወረá‹ŗ ጤና á‰Ŗለሙá‹Ģዎá‰Ŋ

" መሠረá‰ŗዊ á‰Ŋግሩ የበጀá‰ĩ á‰Ŋግር ነው፤ የáŠĢáˆŊ áŠĨáŒĨረá‰ĩ ነው á‹Ģለው " - የጌዴáŠĻ ዞን ጤና መምáˆĒá‹Ģ

በጌዴáŠĻ ዞን ዲላ ዙáˆĒá‹Ģ ወረá‹ŗ በ6 ጤና áŒŖá‰ĸá‹Ģዎá‰Ŋ የሚገኙ ጤና á‰Ŗለሙá‹Ģዎá‰Ŋ የ18 ወáˆĢá‰ĩ የዱቲ ክፍá‹Ģ áŠĨንá‹ŗልተከፈላቸውáŖ áŠĨንዲከፈላቸው á‰ĸጠይቁም መፍá‰ĩሄ áŠĨንá‹ŗላገኙ ለቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ገልጸዋልáĸ

ጤና á‰Ŗለሙá‹Ģዎቹ በሰጡá‰ĩ ቃልáŖ " áŠĨንዲከፈለን ጠይቀን ነበርáĸ ‘#ገንዘá‰Ĩ የለንም áŠĨንከፍላለን’ áŠĨá‹Ģሉ ነው የተበጀተ በጀá‰ĩ áŠĨá‹Ģለ ገንዘቡን ለሌላ ጉá‹ŗይ áŠĨየተጠቀሙ á‹Ģቆዩá‰ĩ " á‰Ĩለዋልáĸ

- áŒĒጩ
- አንá‹ĩá‹ŗ
- áˆĩáˆļá‰ŗ
- ወቸማ
- ኡá‹ļ
- ቱምá‰ĩá‰ģ በተሰኙ የወረá‹ŗው 6 ጤና አጠá‰Ŗበቅ áŒŖá‰ĸá‹Ģዎá‰Ŋ ከ01/06/2015 ዓ/ም ጀምሮ áŠĨáˆĩከ 01/09/2016 ዓ/ም ለ18 ወáˆĢá‰ĩ የዱቲ ክፍá‹Ģ አልተከፈለም ነው á‹Ģሉá‰ĩáĸ

á‹Ģልተከፈላቸውን ገንዘá‰Ĩ መጠን ሲገልጹም አንዷ ቅáˆŦá‰ŗ አቅáˆĢá‰ĸáŖ " የáŠĨኔ ከ80,000 á‰Ĩር በላይ ነውáĸ ከáŠĨኔ በላይ ደመወዝ áŠĨርከን ላላቸው ደግሞ ይጨምáˆĢልáĸ የአንá‹ĩ ሰው ከዚህ በላይ ሲሆንáŖ የ6ቱ ጤና ተቋም á‰Ĩዙ ገንዘá‰Ĩ ነው " ሲሉ አáˆĩረá‹ĩተዋልáĸ

ለተነáˆŗው ቅáˆŦá‰ŗ ምላáˆŊ የጠየቅናቸው የጌዴáŠĻ ዞን ጤና መምáˆĒá‹Ģ ኃላፊ አá‰ļ አንዱዓለም ማሞáŖ " ጉá‹ŗዩ በáŠĨርግáŒĨ á‹Ģለ ነውáĸ መሠረá‰ŗዊ á‰Ŋግሩ የበጀá‰ĩ á‰Ŋግር ነው፤ የáŠĢáˆŊ áŠĨáŒĨረá‰ĩ ነው á‹Ģለውáĸ á‹Ģን ለመፍá‰ŗá‰ĩ በጋáˆĢ áŠĨየሰáˆĢን ነው " á‰Ĩለዋልáĸ

á‰Ŗለሙá‹ĢዎቹáŖ 'የተበጀተ በጀá‰ĩ አለ ግን ለሌላ áŒĨቅም áŠĨá‹Ģዋሉá‰ĩ ነው á‹Ģዘገዩá‰Ĩን' ላሉá‰ĩ ቅáˆŦá‰ŗ በሰጡá‰ĩ ምላáˆŊ ኃላፊውáŖ " áŠĨንደዛ አይደለምáĸ በጀቱ ተይዟል áŠĨውነá‰ĩ ነውáĸ ነገር ግን የáŒĨáˆŦ ገንዘá‰Ĩ áŠĨáŒĨረá‰ĩ áŠĨንጂ ወረá‹ŗውም ለመክፈል ፈቃደኛ áˆŗይሆን ቀርá‰ļ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋልáĸ

የዞኑ የá‰ĨልáŒŊግና áŒŊ/ቤá‰ĩ ኮሚዩኒáŠŦáˆŊን ኃላፊ አá‰ļ አይደፈር áˆŊፈáˆĢው በበኩላቸው ፤ á‰Ŋግሩ የáŒĨáˆŦ ገንዘá‰Ĩ áŠĨáŒĨረá‰ĩ መሆኑን ገልጸውáŖ ለ3 ዓመá‰ŗá‰ĩ የዱቲ ክፍá‹Ģ 6.4 ሚሊዮን á‰Ĩር áŠĨንደተበጀተáŖ ገንዘቡን ለማፈላግለግ áŠĨየተሰáˆĢ áŠĨንደሆነና ዱቲ የሚከፈላቸው የá‰Ŗለሙá‹Ģዎá‰Ŋ á‰Ĩዛá‰ĩ መረጃም áŠĨየተሰበሰበ መሆኑን አáˆĩረá‹ĩተዋልáĸ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ገንዘá‰Ĩ ማáˆĩተላለፍ ሲፈልጉ ከáŠĨሁá‹ĩ áŠĨáˆĩከ áŠĨሁá‹ĩ ለ24 ሰዓá‰ĩ ክፍá‰ĩ በሆነው የቨርቹዋል á‰Ŗንክ ማዕከሎá‰ģá‰Ŋን ይጠቀሙáĸ

#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርáŒĢ
የ ZTE áˆĩልኮá‰Ŋ ከልዩ áˆĩáŒĻá‰ŗ ጋር!

ዘመናዊ የ ZTE áˆĩማርá‰ĩ áˆĩልኮá‰Ŋን በተመáŒŖáŒŖኝ ዋጋ በመግዛá‰ĩ የዩá‰ĩዩá‰Ĩ áŒĨቅልን ጨምሮ ወርሃዊ á‹ŗá‰ŗ ከá‹ĩምáŒŊ áŒĨቅል ጋር በáˆĩáŒĻá‰ŗ á‹Ģግኙ!

በአቅáˆĢá‰ĸá‹Ģዎ በሚገኙ የአገልግሎá‰ĩ ማዕከሎá‰ģá‰Ŋን áŠĨንዲሁም የአዲáˆĩ አበá‰Ŗ ደንበኞá‰ģá‰Ŋን በቴሌገበá‹Ģ á‹ĩረገáŒŊ ጭምር https://telegebeya.ethiotelecom.et/ á‹Ģገኟቸዋል!

የዜá‹ĩ.ቲ.áŠĸ 5ጂ á‰Ĩሌá‹ĩ ኤ73 áŠĨና ዜá‹ĩ.ቲ.áŠĸ á‰Ĩሌá‹ĩ á‰Ē40 ፕሮ ሲገዙ áŠĨáˆĩከ ግንá‰Ļá‰ĩ 23 á‹ĩረáˆĩ የኤርፖá‹ĩ áˆĩáŒĻá‰ŗ á‹Ģገኛሉ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
° “ ልጄ በሕይወá‰ĩ áˆĩለመኖሯ áŠĨርግጠኛ አይደለሁም ” - ልጄ ተጠለፈá‰Ŋ á‹Ģሉ አá‰Ŗá‰ĩ

° “ የልጅቷን አá‰Ŗá‰ĩ መáˆĩለው ቃለ መጠይቅ የሚá‹Ģደርጉ አሉ ” - የኮáˆŦ ዞን አáˆĩተá‹ŗá‹ŗáˆĒ 

° “ በ2015 ዓ/ም á‰Ĩá‰ģ 23 ሴá‰ļá‰Ŋ ጠለፋና አáˆĩገá‹ĩá‹ļ መá‹ĩፈር ተፈáŒŊሞá‰Ŗቸዋል ” - የዞኑ ፍá‰ĩህ á‰ĸሎ

በደቡá‰Ĩ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ክልል ኮáˆŦ ዞን ጠለፋና áŠĨየተáˆĩፋፋ መሆኑንáŖ በዚህም ወላጆá‰Ŋ ልጆá‰ģቸውን ወደ á‰ĩምህርá‰ĩ ቤá‰ĩ መላክ áŠĨንá‹ŗልá‰ģሉ የአáŠĢá‰Ŗá‰ĸው ነዋáˆĒዎá‰Ŋ ይገልáŒģሉáĸ

አá‰ļ ወንá‹ĩሙ ወá‹Ŧáˆŗ የተá‰Ŗሉ የዞኑ ነዋáˆĒ á‰Ŗለፈው ወር የማርá‹Ģም የተá‰Ŗለá‰Ŋ ልጃቸውን “ ጉልበተኞá‰Ŋ ምáˆŊá‰ĩ 3 ሰዓá‰ĩ በáˆĢቸውን ሰá‰Ĩረው ጠልፈው ዱልáŠŦ ” ወደሚá‰Ŗል á‰Ļá‰ŗ áŠĨንደወሰዷá‰ĩáŖ ጠላፊዎቹ ከተá‹Ģዙ በኋላ ከáŠĨáˆĩር áŠĨንደተለቀቁ በማህበáˆĢዊ ሚዲá‹Ģ ሲገልጹ ተáˆĩተውለዋልáĸ

“ ልጄ በሕይወá‰ĩ áˆĩለመኖáˆĢ áŠĨርግጠኛ አይደለሁም ” á‹Ģሉá‰ĩ áŠĨኝሁ አá‰Ŗá‰ĩáŖ የጠላፊ ቤተሰá‰Ļá‰Ŋ ይá‰Ŗáˆĩ á‰Ĩለው áˆŊምግልና áŠĨንደላኩáŖ በዚህም áŠĨኝሁ አá‰Ŗá‰ĩ ለጸáŒĨá‰ŗ አáŠĢላá‰ĩ አáˆŗውቀው á‰ĸá‹Ģáˆŗáˆĩሯቸውም áŠĨንደተለቀቁ áŖ የጠላፊ ቤተሰá‰Ļá‰Ŋም #ፌዝ áŠĨና #ዛá‰ģ áŠĨá‹Ģደረሱá‰Ŗቸው በመሆኑ የዞኑ አáŠĢላá‰ĩ ፍá‰ĩህ áŠĨንዲሰጧቸው ጠይቀው ነበርáĸ

ይህá‰Ŋ ልጅ በጠላፊዎá‰Ŋ áŠĨጅ 2 ወር በላይ ሆኗá‰ŗልáĸ

ከዚህ á‰Ŗለፈ ደáˆĩá‰ŗ ደመቀ የተá‰Ŗለá‰Ŋ ልጃገረá‹ĩ ተጠልፋ የተወሰደá‰Ŋ ሲሆን በጠላፊዎá‰Ŋ áŠĨጅ ከወር በላይ áŠĨንደሆናá‰ĩ ተሰምቷልáĸ

áŠĨንደ አጠቃላይ á‹Ģለውን የጠለፋን ወንጀል በተመለከተ ቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ የጠየቃቸውና áˆĩሜ á‰Ŗይጠቀáˆĩ á‹Ģሉ የዞáˆŦ ዞን ፍá‰ĩህ መምáˆĒá‹Ģ አáŠĢልáŖ “#á‰Ŋግሮቹ አሉáĸ ጠላፋዎቹ ከá‰ĩምህርá‰ĩ ቤá‰ĩ መልáˆĩም ይፈጸማሉ” ሲሉ አረጋግጠዋልáĸ

“ ለሚáˆĩá‰ĩነá‰ĩ የሚጠለፉ አይመáˆĩልምáĸ ጠላፊዎቹ ወደ ሹá‹ŗን በኩል ወርቅ አለ በጅማ በኩል የሚጓዙበá‰ĩ ‘በዚá‹Ģ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ የሚመጡ ሎሌዎá‰Ŋ ናቸው’ ነው የሚá‰Ŗለውáĸ ይህ የሚሆነው ጎርáŠĢ ወረá‹ŗ ነው ” ሲሉ ተናግረዋልáĸ

የየማርá‹Ģምን ጨምሮ በ2016 ዓ/ም የተፈጸሙá‰ĩን የጠለፋ ወንጀሎá‰Ŋ በተመለከተ ገና መረጃ áŠĨá‹Ģሰá‰Ŗሰቡ መሆኑን ገልጸውáŖ “ በ2015 ዓ/ም 23 ሴá‰ļá‰Ŋ የጠለፋና አáˆĩገá‹ĩá‹ļ መá‹ĩፈር ተፈáŒŊሞá‰Ŗቸዋል ” á‰Ĩለዋልáĸ

ተመáˆŗáˆŗይ áŒĨá‹Ģቄ የቀረበላቸው የኮáˆŦ ዞን አáˆĩተá‹ŗá‹ŗáˆĒ አá‰ļ á‰ŗረቀኝ በቀለ በበኩላቸውáŖ “ ሚዲá‹Ģ ላይ የሚá‰Ŗለው መáˆŦá‰ĩ ላይ አለ ወይáˆĩ የለም ? የሚለውን በሚá‰Ŗለው ክላáˆĩተር ላይ ሂጄ የሃይማኖá‰ĩ አá‰Ŗá‰ļá‰ŊንáŖ አረጋዊá‹Ģንን ለማማከር ሞክáˆŦአለሁáĸ አሁን በሚá‰Ŗለው ልክ አይደለም ” የሚል ምላáˆŊ ሰáŒĨተዋልáĸ

“ ‘ከፓሊáˆĩ áŒŖá‰ĸá‹Ģ ሰው áŠĨየተለቀቀ ነው’ የሚለው ነገር áˆĩም ለማáŒĨፋá‰ĩና ዞኑን ለማጠልሸá‰ĩ áŠĨየተደረገ á‹Ģለ ነው ” á‹Ģሉá‰ĩ አá‰ļ á‰ŗረቀኝáŖ “ የልጅቷን አá‰Ŗá‰ĩ መáˆĩለው ቃለ መጠይቅ የሚá‹Ģደርጉ አሉáĸ ቃለ መጠይቅም áˆĢሹ አርáˆļ አደር መáˆĩሎ የሚሰáŒĨ አለ ” ነው á‹Ģሉá‰ĩáĸ

የኮáˆŦ ዞን ሰላምና ጸáŒĨá‰ŗ ዘርፍ ኃላፊ አá‰ļ ተፈáˆĢ á‰Ļንደሮ በበኩላቸውáŖ ከወረá‹ŗው ወደ ዞን የቀረበላቸው ቅáˆŦá‰ŗ áŠĨንደሌለáŖ ጎርáŠĢ ወረá‹ŗ ለመረጃ ሩቅ በመሆኑ ጉá‹ŗዩን áŠĨንá‹ŗልሰሙ ገልጸዋልáĸ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#á‰ĸጂአይ #ፐርፐዝá‰Ĩላክ " ገንዘቡንም አልመልáˆĩም ሲል በደá‰Ĩá‹ŗቤ አáˆŗውቋል " ፐርፐዝ á‰Ĩላክ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ " የመመለáˆĩ አለመመለሱ ጉá‹ŗይ በቀá‰Ĩá‹ĩ ውሉ መሰረá‰ĩ የሚá‰ŗይ ነው " - á‰ĸጂአይ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ áˆĩምንá‰ĩ ወáˆĢá‰ĩን የፈጀውና á‹ĢለáˆĩáŠŦá‰ĩ የተጠናቀቀው የá‰ĸጂአይ-áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ዋና መáˆĩáˆĒá‹Ģ ቤá‰ĩ ህንፃ áˆŊá‹Ģጭ ሂደá‰ĩ አሁን ላይ ወደ ክáˆĩ ሂደá‰ĩ አምርቷልáĸ ገá‹ĸ ሆኖ የቀረበው ፐርፐዝ á‰Ĩላክ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ክáˆĩ áŠĨáˆĩከሚመሰርá‰ĩ á‹ĩረáˆĩâ€Ļ
#Update

á‰ĸጂአይ-áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ áŠĨና ፐርፐዝ á‰Ĩላክ በፍርá‹ĩ ቤá‰ĩ መር አáˆĩማሚ በኩል አለመግá‰Ŗá‰Ŗá‰ŗቸውን በáˆĩምምነá‰ĩ ፈተዋልáĸ
 
የፌዴáˆĢሉ ከፍተኛ ፍርá‹ĩ ቤá‰ĩ በሁለቱ ወገኖá‰Ŋ መáŠĢከል የተፈፀመውን áˆĩምምነá‰ĩ አፅá‹ĩቆ ክሱን በመዝጋá‰ĩ áŠĨግዱም áŠĨንዲነáˆŗ አዟል፡፡
 
በáˆĩምምነቱ መሰረá‰ĩ á‰ĸጂአይ-áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ የተከፈለውን የቀá‰Ĩá‹ĩ ክፍá‹Ģ ለፐርፐዝ á‰Ĩላክ የመለሰ ሲሆን ፐርፐዝ á‰Ĩላክ በፍርá‹ĩ ቤá‰ĩ የጀመረው ክáˆĩም ተቋረáŒĻ áŠĨግዱ ተነáˆĩቷልáĸ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በተማáˆĒ ደáˆĢርቱ ለሜáˆŗ ግá‹ĩá‹Ģ ዙáˆĒá‹Ģ የአáˆļáˆŗ ፖሊáˆĩ ምን አለ ?

የአáˆļáˆŗ ዩኒቨርáˆĩቲ ተማáˆĒ በነበረá‰Ŋው ደáˆĢርቱ ለሜáˆŗ ግá‹ĩá‹Ģ ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰá‰Ĩ በቁáŒĨáŒĨር áˆĩር አውሎ ምርመáˆĢ áŠĨá‹ĢáŒŖáˆĢ áŠĨንደሚገኝ የአáˆļáˆŗ ከተማ ፖሊáˆĩ አáˆĩá‰ŗውቋልáĸ

ፖሊáˆĩ የወንጀል á‹ĩርጊቱ የተፈጸው በአáˆļáˆŗ ከተማ አáˆĩተá‹ŗደር ወረá‹ŗ አንá‹ĩ ልዩ á‰Ļá‰ŗው " ሰላም ሰፈር " ተá‰Ĩሎ በሚጠáˆĢው አከá‰Ŗá‰ĸ ረቡዕ ከጧቱ በግምá‰ĩ 2:45 ላይ áŠĨንደሆነ አመልክቷልáĸ

" በሟá‰Ŋ áŠĨና በተጠርáŒŖáˆĒው መáŠĢከል በተፈጠረ በሀáˆŗá‰Ĩ á‹Ģለመግá‰Ŗá‰Ŗá‰ĩ ምክንá‹Ģá‰ĩ ተጠርáŒŖáˆĒው በአሰቃቂ ሁኔá‰ŗ ጀርá‰Ŗዋ ላይ #በጩቤ_በመውጋá‰ĩ የተማáˆĒዋ ህይወá‰ĩ áŠĨንዲá‹Ģልፍ አá‹ĩርጓል " ሲል ፖሊáˆĩ ገልáŒŋልáĸ

ተጠርáŒŖáˆĒውን ግለሰá‰Ĩ በቁáŒĨáŒĨር áˆĩር አውሎ ምርመáˆĢ áŠĨá‹ĢáŒŖáˆĢ áŠĨንደሚገኝም አáˆŗውቋልáĸ

የከተማው ፖሊáˆĩ የወንጀል á‹ĩርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርáˆĩቲው ግá‰ĸ ውጭ áŠĨንደሆነ አመልክቷልáĸ

ተጠርáŒŖáˆĒው የግá‰ĸ ተማáˆĒ á‹Ģልሆነና ከአዲáˆĩ አበá‰Ŗ ዱከም ከተማ አቋርáŒĻ ወደ አáˆļáˆŗ ከተማ ለáˆĩáˆĢ ጉá‹ŗይ በመምáŒŖá‰ĩ የወንጀል á‹ĩርጊቱን áŠĨንደፈጸመ ገልáŒŋልáĸ

በአንá‹ŗንá‹ĩ ማህበáˆĢዊ ሚá‹ĩá‹Ģዎá‰Ŋ " á‹ĩርጊቱ የተፈጸመው በግá‰ĸ ውáˆĩáŒĨ ነው " በሚል የሚሰáˆĢጨው áŠĨና የá‰Ĩሔር ግጭá‰ĩ አáˆĩመáˆĩለው የሚወáˆĢው ፍጹም ከáŠĨውነá‰ĩ የáˆĢቀ áŠĨና ሁለቱም የአንá‹ĩ á‰Ĩሔር ተወላጅ áŠĨንዲሁም በጓደኝነá‰ĩ አá‰Ĩረው የነበሩ መሆኑን የአáˆļáˆŗ ከተማ ፖሊáˆĩ አáˆŗውቋልáĸ

#AssosaPolice

@tikvahethiopia
áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ለሚገኙ ወáŒŖá‰ĩ ሴá‰ļá‰Ŋ ለ2ተኛ ዙር የቀረበ áŒĨáˆĒ!

áˆĩቴም ፖወር (STEMpower) ከፊንላንá‹ĩ ኤምá‰Ŗሲ (Embassy of Finland Ethiopia) áŠĨና ከአይá‰ĸኤም (IBM) ጋር በመተá‰Ŗበር በáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ከ1,000 በላይ áˆĨáˆĢ አáŒĨ ወáŒŖá‰ĩ ሴá‰ļá‰Ŋን ተግá‰ŖáˆĢዊ የáˆĨáˆĢ ክህሎá‰ĩ ለመáˆĩጠá‰ĩ á‹Ģለመ "á‰ĩጋá‰ĩ" የተሰኘ ፕሮግáˆĢም አáˆĩተዋውቀዋልáĸ

በመጀመá‹Ģ ዙር 700 በላይ ለሚሆኑ ሴá‰ļá‰Ŋ በ Project Management, Web Development , Cyber Security, Digital Marketing , Data Analytics , Information Technology , Job Readiness , Work Readiness áˆĩልጠና የሰጠ ከመሆኑ በተጨማáˆĒ የáˆĩáˆĢ áŠĨá‹ĩል በመፈጠር ተጠቃሚ áŠĨንዲሆኑ áŠĨá‹ĩል አመá‰ģá‰Ŋቷል፡፡

#ነáŒģ በሚሰጠውና ዓለም አቀፍ áŠĨውቅና á‹Ģለው ሰርተፊáŠŦá‰ĩ በሚá‹Ģáˆĩገኘው በዚህ áˆĩልጠና áŠĨነዚህን ኮርáˆļá‰Ŋ ለመውሰá‹ĩ ፍላጎá‰ĩ á‹Ģላá‰Ŋሁ ሴá‰ļá‰Ŋ ምዝገá‰Ŗ የጀመርን መሆኑን áŠĨá‹Ģáˆŗወቅን ምዝገá‰Ŗው የሚቆየው ከ ግንá‰Ļá‰ĩ 7 - 20, 2016 ዓ/ም ሲሆን ቀá‹ĩማá‰Ŋሁ በመመዝገá‰Ĩ የáŠĨá‹ĩሉ ተጠቃሚ áŠĨንá‹ĩá‰ĩሆኑ áŠĨንጋá‰Ĩዛለን፡፡

áŠĨነዚህን ኮርáˆļá‰Ŋ ለመውሰá‹ĩ ፍላጎá‰ĩ á‹Ģላá‰Ŋሁ
👉 https://forms.office.com/r/i0fNZG4021
#Hawassa

➡ī¸ " ንፋáˆĩ በመáŒŖ ቁáŒĨር ጉá‹ŗá‰ĩ áŠĨየደረሰ ነውáĸ áŠĨሎá‰Ĩ የአንá‹ĩ ሰው ህይወá‰ĩ አልፏል " - የሀዋáˆŗ የቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ቤተሰá‰Ĩ አá‰Ŗል

➡ī¸ " ጉá‹ŗá‰ĩ የደረሰበá‰ĩ የáŠĢፌ አáˆĩተናጋጅ ነውáĸ በወቅቱ ወደህክምና ተወáˆĩá‹ļ የህክምና áŠĨርá‹ŗá‰ŗ á‰ĸደረግለá‰ĩም ህይወቱ ግን ሊተርፍ አልá‰ģልም " - የሀዋáˆŗ ከተማ ሰላምና ጸáŒĨá‰ŗ

በሀዋáˆŗ ከተማ ፤ ፒá‹Ģáˆŗ በሚገኘው ንá‰Ĩ á‰Ŗንክ ህንáŒģ ላይ የወደቀ መáˆĩá‰ŗወá‰ĩ የአንá‹ĩ ወáŒŖá‰ĩ ህይወá‰ĩ ቀáŒĨፏልáĸ

ህንáŒģው በዝናá‰Ĩና ንፋáˆĩ ወቅá‰ĩ áŠĨቃ ሲወá‹ĩቅበá‰ĩ የመጀመáˆĒá‹Ģው áŠĨንá‹ŗልሆነ ቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ከሀዋáˆŗ የቤተሰá‰Ĩ አá‰Ŗላቱ áŒĨቆማ ደርáˆļá‰ŗልáĸ

በቅርቡ የተመረቀዉ የንá‰Ĩ ህንáŒģ ከዘጠነኛ ፎቅ ላይ የወደቀ መáˆĩá‰ŗወá‰ĩ የህንáŒģው ወለል ላይ áˆĩáˆĢ ላይ የነበረ ሰáˆĢተኛ ላይ ማረፉን ተከá‰ĩሎ ሰáˆĢተኛው ህይወቱ አልፏልáĸ

በሀዋáˆŗ áŠĨሎá‰Ĩ ከ9 ሰአá‰ĩ በኋላ የነበረው ከá‰Ŗá‹ĩ ዝናá‰Ĩና ውáˆŊንፍር á‰Ŗáˆĩከተለዉ ነፋáˆĩ ከህንáŒģዉ ላይ የወደቀ መáˆĩá‰ŗወá‰ĩ የሰዉ ህይወá‰ĩ ማáŒĨፋቱን ለማረጋገáŒĨ á‰Ŋለናልáĸ

አንá‹ĩ የሀዋáˆŗ የቤተሰá‰Ŗá‰Ŋ አá‰Ŗል ፤ " ንፋáˆĩ በመáŒŖ ቁáŒĨር ከህንáŒģው ላይ በሚወá‹ĩቅ ቁáˆĩ ተደጋጋሚ ጉá‹ŗá‰ĩ በግለሰá‰Ļá‰Ŋ ላይ ሰáˆĢተኞá‰Ŋ ላይ áŠĨየደረሰ ነውáĸ áŠĨሎá‰Ĩ አንá‹ĩ ሰáˆĢተኛ መáˆĩá‰ŗወá‰ĩ ወá‹ĩቆበá‰ĩ áŠĨጁ የመቆረáŒĨ áŖ አናቱ ላይ የመጎá‹ŗá‰ĩ በኃላም ህይወቱ አልፏልáĸ ህንጸው ግልáŒŊ የሆነ የግንá‰Ŗá‰ŗ ጉá‹ĩለá‰ĩ ይá‰ŗይበá‰ŗል " ሲል ቃሉን ሰáŒĨቷልáĸ

በዚህ ጉá‹ŗይ ላይ ለቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ማá‰ĨáˆĢáˆĒá‹Ģ የሰጡá‰ĩ የሀዋáˆŗ ከተማ ሰላምና ጸáŒĨá‰ŗ á‰ĸሎ ሀላፊ አá‰ļ ወንá‹ĩማገኝ á‰ļርá‰Ŗ ፤ ጉá‹ŗá‰ĩ የደረሰበá‰ĩ ወáŒŖá‰ĩ የáŠĢፌ አáˆĩተናጋጅ መሆኑንና በወቅቱ ወደህክምና ተወáˆĩá‹ļ የህክምና áŠĨርá‹ŗá‰ŗ á‰ĸደረግለá‰ĩም ህይወቱ ግን ሊተርፍ áŠĨንá‹ŗልá‰ģለ ገልጸዋልáĸ

ይሁንና " ህንáŒģው ላይ ተደጋጋሚ á‰Ŋግር ተáˆĩተውሏል " ለሚá‰Ŗለዉ ቅáˆŦá‰ŗ áŠĢሁን በፊá‰ĩ የደረሰ አደጋን የተመለከተ áˆĒፖርá‰ĩ የለም ሲሉ ገልጸዋልáĸ

በወቅቱ በዚህ ህንáŒģ ውáˆĩáŒĨ ከደረሰዉ አደጋ  ውጭ በከተማዉ የተከሰተዉ ነፋáˆĩ በርáŠĢá‰ŗ የንá‰Ĩረá‰ĩ ጉá‹ŗá‰ĩ ማáˆĩከተሉንም አáˆĩá‰ŗውሰዋልáĸ

ቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ የህንáŒģዉን አáˆĩተá‹ŗá‹ŗáˆĒዎá‰Ŋ በጉá‹ŗዩ ዙáˆĒá‹Ģ ለማነጋገር á‹Ģደረገዉ ሙከáˆĢ አልተáˆŗáŠĢምáĸ ምላáˆŊ አለም áŠĢሉ መáˆĩተናገá‹ĩ ይá‰Ŋላሉáĸ

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthEthiopiaRegion በደቡá‰Ĩ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ክልል ፤ የáˆļá‹ļ ዙáˆĒá‹Ģ ወረá‹ŗ የመንግáˆĨá‰ĩ ሠáˆĢተኞá‰Ŋ ለወáˆĢá‰ĩ á‹Ģልተከፈለ ውዝፍ ደሞዛቸዉ áŠĨንዲሰáŒŖቸዉ በአደá‰Ŗá‰Ŗይ ሠልፍ ጠይቀዋልáĸ በዎላይá‰ŗ áˆļá‹ļ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ርዕሰ መáˆĩተá‹ŗá‹ĩርና የá‰Ĩልፅግና ፓርቲ áŒŊህፈá‰ĩ ቤá‰ĩ የግá‰ĸ በሮá‰Ŋ ላይ የተሰበሰቡá‰ĩ ሠáˆĢተኞá‰Ŋ áŠĨንደገለጹá‰ĩ áŠĨáˆĩከ 3 ወáˆĢá‰ĩ የሚደርáˆĩ ደሞዝ አልተከፈላቸዉምáĸ ሠáˆĢተኞቹ ደሞዝ áˆĨላልተከፈላቸዉ áŠĨáˆĢáˆŗቸዉንናâ€Ļ
#SouthEthiopiaRegion

➡ī¸ " ... በረሀá‰Ĩ ከምንሞá‰ĩ መá‰Ĩá‰ŗá‰Ŋን áŠĨየጠየቅን አደá‰Ŗá‰Ŗይ ላይ መሞá‰ĩ መርጠን ነው ወደ ርáŠĨሰ መáˆĩተá‹ŗá‹ĩሊ á‰ĸሎ የሄá‹ĩነው " - የáˆļá‹ļ ዙáˆĒá‹Ģ የመንግáˆĩá‰ĩ ሰáˆĢተኞá‰Ŋ

➡ī¸" ማንም መá‰Ĩቱን በነáŒģነá‰ĩ የመጠየቅ መá‰Ĩá‰ĩ አለው " - የደቡá‰Ĩ ክልል ሰላምና ጸáŒĨá‰ŗ á‰ĸሎ ሃፊዉ አá‰ļ ወገኔ á‰Ĩዙነህ

የ2 ወáˆĢá‰ĩ ደሞዛá‰Ŋን ይከፈለን á‹Ģሉ የወላይá‰ŗ ዞን የመንግáˆĩá‰ĩ ሰáˆĢተኞá‰Ŋ አደá‰Ŗá‰Ŗይ መውáŒŖá‰ŗቸዉን ተከá‰ĩሎ  በርáŠĢá‰ŗ á‹Ģልጠበቋቸዉ ጉá‹ŗዮá‰Ŋ áŠĨንደገጠሟቸዉ ገልጸዋልáĸ

ለቲክá‰Ģህ áŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ ቃላቸውን የሰጡ ሰáˆĢተኞá‰Ŋ áĨ " áŒĨá‹Ģቄá‹Ģá‰Ŋን ለመጠየቅ የተገደá‹ĩነዉ ረሀቡ áˆĩለጠናá‰Ĩን ነው " በማለá‰ĩ ላለፉá‰ĩ ወáˆĢá‰ĩ ከፍተኛ á‰Ŋግር ውáˆĩáŒĨ መቆየá‰ŗቸውን ተናግረዋልáĸ

አሁን ላይ ደሞዝ ከወሰá‹ĩን 2 ወáˆĢá‰Ŋን ነዉ የሚሉá‰ĩ ሰáˆĢተኞቹ ከዚá‹Ģ በፊá‰ĩም በፐርሰንá‰ĩ áŠĨየተቆáˆĢረጠ ይሰáŒĨ የነበረው ደሞዝ የማንወáŒŖው áŠĨá‹ŗ ውáˆĩáŒĨ አáˆĩገá‰Ĩá‰ļን ነበር á‰Ĩለዋልáĸ

" በፐርሰንá‰ĩ ሲከፈለን በነበረበá‰ĩ ወቅá‰ĩ á‰Ŋግሩን ለመቋቋም አበá‹ŗáˆĒ ተቋማá‰ĩ ጋር ሂደን የምንበደረው ገንዘá‰Ĩ ወለዱ አሰቸጋáˆĒ መሆኑ áˆŗá‹Ģንáˆĩ ደሞዝ ሲቀርá‰Ĩን ደግሞ ሌላ áŒŖáŒŖ ውáˆĩáŒĨ ገá‰Ŗን " በማለá‰ĩ የá‰ŊግáˆĢቸዉን ውáˆĩá‰Ĩáˆĩá‰Ĩነá‰ĩ አáˆĩረá‹ĩተዋልáĸ

" በዚህ ምክንá‹Ģá‰ĩ በረሀá‰Ĩ ከምንሞá‰ĩ መá‰Ĩá‰ŗá‰Ŋን áŠĨየጠየቅን አደá‰Ŗá‰Ŗይ ላይ መሞá‰ĩ መርጠን ነው ወደ ርáŠĨሰ መáˆĩተá‹ŗá‹ĩሊ á‰ĸሎ የሄá‹ĩነዉ " በማለá‰ĩ ተናግረዋልáĸ

ሰáˆĢተኞቹ " áŠĨáˆĩáŠĢሁን በየደረጃዉ የነበሩ የመንግáˆĩá‰ĩ አáŠĢላá‰ĩን áˆĩንጠይቅ ውክá‰ĸá‹Ģና ማáˆĩፈáˆĢáˆĢá‰ĩ ነበር የሚገáŒĨመን በተለይም መጀመáˆĒá‹Ģ ወደ ዞን አáˆĩተá‹ŗá‹ŗáˆĒ áˆĩናመáˆĢ ፖሊáˆĩ በá‰ĩኖን መልሰን መሰá‰Ŗሰá‰Ĩ ሁሉ ከá‰Ĩá‹ļን ነበር " á‰Ĩለዋልáĸ

" በመጨረáˆģ ወደ ርáŠĨሰ መáˆĩተá‹ŗá‹ĩሊ á‰ĸሎ áˆĩንሄá‹ĩ ሌላዉ á‰ĸቀር ሀáˆŗá‰Ŗá‰Ŋን ሰምተዉ አáŠĢሄዱን በማáˆĩረá‹ŗá‰ĩ ሀáˆŗá‰Ŗá‰Ŋን በደá‰Ĩá‹ŗቤ áŠĨንá‹ĩንገልáŒŊ ፈቅደዉልናል " á‰Ĩለዋልáĸ

" ይሁንና አሁንም áŒĨá‹Ģቄá‹Ģá‰Ŋን ምላáˆŊ አላገኘም " የሚሉá‰ĩ ሰáˆĢተኞቹ ተመልሰን áŒĨá‹Ģቄá‹Ģá‰Ŋን የá‰ĩ ደረሰ áŠĨንá‹ŗንልም áˆĩላልተደáˆĢጀን በየጊዜዉ መሰá‰Ŗሰቡ ከበደን á‰Ĩለዋልáĸ

በመጀመáˆĒá‹Ģዉ ቀን የሰላማዊ ሰልፍ ሙከáˆĢ "  ፖሊáˆĩ ሰáˆĢተኛዉን በá‰ĩኗል " መá‰Ŗሉን በተመለከተ áŒĨá‹Ģቄ á‹Ģቀረá‰Ĩንላቸዉ የክልሉ ሰላምና ጸáŒĨá‰ŗ á‰ĸሎ ሀላፊዉ አá‰ļ ወገኔ á‰Ĩዙነህ በጉá‹ŗዩ ሰáˆĢተኛዉ áŒĨá‹Ģቄ መጠየቁን áŠĨንጅ ከፖሊáˆĩ ጋር ግጭá‰ĩ áŠĨንደገá‰Ŗ መረጃ áŠĨንደሌላቸዉ ገልጸዋልáĸ

á‹Ģም ሆኖ " ማንም መá‰Ĩቱን በነáŒģነá‰ĩ የመጠየቅ መá‰Ĩá‰ĩ አለው " ሲሉ ገልጸው " á‰Ŋግሮá‰Ŋ ተከáˆĩተዉ ከሆነ ወደፊá‰ĩ መረጃ áŠĨንሰáŒŖá‰Ŋኋለን " ሲሉ ቃል ገá‰Ĩተዋልáĸ

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/27 13:27:58
Back to Top
HTML Embed Code: