Telegram Web Link
ኮርና ለሲዳማ ቡና
ይገዙ ቦጋለ ጎል የሚያስቆጥርበትን አጋጣሚ መጠቀም አልቻለም
በጨዋታዉ የዉጤት ለዉጥ የለም

ሲዳማ ቡና 2-0 ጂማ አባጂፋር
ይገዙ
ኦዚል
ጨዋታዉ ቀዝቀዝ ብሏል😑
እየመራን ነዉ ምን አገባኝ😁
ጨዋታዉ ደብዘዝ ብሏል ተኝቼ ሊነሳ😁

ጎል ከገባ ንገሩኝ
👇👇👇👇👇
@yonasofficial
@yonasofficial
በመጀመሪያ አጋማሽ ተቀይሮ የገባዉ ብርሃኑ አሻሞ በመሃል መስመር መልካም እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።
ኳስ መጫወት አስጠልቷቸዋል ሁላ እየጠለዙ ነዉ።
ኦኦኦኦ ሲዳማ ቡና የሚያስቆጭ እድል አጥፍተዋል
ይገዙ ለብሩክ ያሻማዉን ኳስ ብቻዉን ነበር ግን በረኛዉ ያዘበት
ይገዙ ቦጋለ ወጣ አቤኔዘር ገባ
አምስት ደቂቃ ጭማሪ
ተዎድሮስ ማስቆጠር የሚችልበትን እድል ነበር ግን ግብ ጠባቂዉ ያዘበት
ተጠናቀቀ
ሲዳማ ቡና 2-0 ጂማ
ይገዙ ቦጋለ ስምንተኛ ግቡን አስቆጥሯል።
እስቲ ለአጥቂያችን👍
📷Aku
ባለ ብዙ አላማ ባለቤቶች

ከእነርሱ መካከል ወደፊት ብዙ ትላልቅ የሲዳማ ቡናን ስም ለማስጠራት ብዙ ህልም ያላቸዉ ልጆች አሉ ፤ የእነርሱን ህልም ብትጠይቋቸዉ አንድ እና አንድ ትልቅ ተጫዋች ሆነዉ ቤተሰቦቻቸዉን ፣ ከተማቸዉን እና ሀገራቸዉን ማሳደግ እና መለወጥ ብቻ ነዉ።

ለዚህም ጉዞ በሲዳማ ቡና ቤት አምና በኢትዮጵያ ከሀያ አመት በታች የዋንጫ አሸናፊ መሆናቸዉ የሚታወሰዉ ክለቡ አምና የቡድኑ አሰልጣኝ የሆነዉ ወንድማገኝ ተሾመ ወደ ዋናዉ ቡድን ምክትል አሰልጣኝነት ተመልሶ በርሱ ቦታ ተስፋዬ ሀንቻቻን በዋና አሰልጣኝነት ከቀጠረ በኋላ የመጀመሪያ የዉድድር ዘመኑን በአሰልጣኝነት ይጀምራል።

ሀሙስ ወደ ጎንደር የሚሄደዉ ቡድኑ የአምናዉን አቋማቸዉን ለመድገም ሙሉ እምነት እንዳላቸዉ አሰልጣኞቹ ተናግረዋል ፤ ዛሬም የአቋም መለኪያ ጨዋታቸዉን ከለኩ ከተማ ጋር ጨዋታቸዉን አድርገዉ ማሸነፍ ችለዋል።

ከጨዋታዉ በኋላ የለኩ ከተማ አሰልጣኝ ሀብታሙ መንግስቱ ክለቡ ባሳየዉ አቋም ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል ፤ ክለቡ ሀሙስ ወደ ጎንደር የሚያቀና ይሆናል።

ሲዳማ ቡና ከሀያ አመት በታችእግርኳስ ክለብ
ሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ
Sidama Bunna F.c
Sidama coffee F.C
የያኩቡ የሲዳማ ቡና ቆይታ..........

ሲዳማ ቡና በ2011 ከነበረዉ የሰንደይ ሙቱኩ እና ፈቱድን ጀማል ጥምረት በኋላ ብዙ የመሃል ሜዳ ተጫዋቾችን ሞክሯል ፤ ከብዙ ሙከራዎች በኋላ አሁን ላይ በመሃል ስፍራ ተከላካይ ቦታ የሚጫወቱት ያኩቡ መሃመድ እና ጊት ጋት ኩት የሲዳማ ቡና ቀዳሚ ተመራጭ የመሃል ተከላካይ ( Central Defence) ተጫዋቾች ናቸዉ።

ስለ ያኩቡ አንድ አንድ እዉነታ ለመናገር ያህል ተጫዋቹ በተለይም የአየር ላይ ኳስ የማዉጣት ስራዉ የሚደነቅለት ሲሆን የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች ኳስ በመግፋት ሲቀርቡት ባለዉ የሰዉነት ግዝፈትም በመጠቀም ኳሶችን የሚጨናገፍ ስራዉ መልካም የሚባል ነዉ።

አንድ አንድ ጊዜ ደግሞ ኳስ ሲያገኝ ለአጥቂ አማካዮች እና የተከላካይ አማካዮች ኳስ በማቃበል የቀማዉን ኳስ ለሲዳማ ቡና ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እና ግብ ለማስቆጠር በሚደረግ ጥረት ሊሳተፍ የሚችል ተጫዋች ነዉ።

ስለ ያኩቡ አንድ የምናገረዉ ነገር ቢኖር የሚያገኛቸዉን ኳሶች Long pass ወይም ረጅም ኳሶችን ለማቃበል ቢሞክር ሲዳማ ቡና ከኦዚል ወይም ታፈሰ ሰለሞን ከሚያገኛቸዉ እድሎች በተጨማሪ ያኩቡ በተከላካይ ቦታ ሆኖ የመስመር አጥቂ ለሆነዉ ሀብታሙ ገዛኸኝ ረጅም ኳስ የሚጥልለት ከሆነ በመስመር ፈጣን የሆነዉ ሀብታሙ በቶሎ ማጥቃት የጎል አድሎችን መፍጠር ይችላል።

ያኩቡ እና ጊት ተግባቦት ያላቸዉ እና አሁን ላይ ደግሞ ጊት እጅግ ልምድ ያለዉ ተጫዋች በመሆኑ በመናበብ ስህተቶች ግብ እንዳይቆጠሩቅን ያደርጋሉ ፤ ለዚህም በልምምድ ወቅት በሚሰሩት ማይነር ጌሞች ላይ በብዙ ቢፈተኑ ባይ ነኝ።

በተረፈ ያኩቡ በሲዳማ ቡና ቤት እንደሚሳካለት እርግጠኛ ነኝ ፤ ቀሪዉን አብረን የምናይ ይሆናል።

@Sidamacoffe
ሳላዲን ሰይድ ሲዳማ ቡናን ከተቀላቀለ በኋላ 260 ያህል ደቂቃዎች ሜዳ ዉስጥ ተጫዉቶ ሶስት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።🔥

ሲዳማ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በሚያደርገው ቀጣይ የቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሳላዲን የቀድሞ ክለቡን የሚገጥም ይሆናል ፤ ሲዳማ ቡና ያንን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ በርግጠኝነት ለዋንጫዉ ጉዞ መንገዱን ያሳምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ተጫዋቹ አቋሙ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ዳግም በብሔራዊ ቡድናችን የምንመለከተዉ ተጫዋች ይሆናልቸ።

@sidamacoffe
@sidamacoffe
የዘጠኝ ጎሎች ባለቤት አጥቂዉ ይገዙ ቦጋለ ነገ ሲዳማ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ላይ አይጫወትም ፤ ተጫዋቹ በተከታታይ በተመለከታቸዉ አምስት ቢጫ ካርዶች ጨዋታዉ እንደሚያልፈዉ ሲገለጽ የርሱን ቦታ ብሩክ ሙልጌታ ይሸፍነዋል።

@sidamacoffe
@sidamacoffe
ሰላዲን ሰይድ የቀድሞ ክለቡን የሚገጥምበት የዋንጫዉን ጉዞ የሚወስነዉ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ጨዋታዉን ለማድረግ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ይቀራሉ።

@sidamacoffe
@sidamacoffe
ሲዳማ ቡና በሀብታሙ እና ፍሬዉ አማካኝነት በማጥቃት ላይ ይገኛል
2024/11/16 02:02:37
Back to Top
HTML Embed Code: