Telegram Web Link
Welcome to the membership registration page of RAEY Financial Institution!
እንኳን ወደ ራዕይ የፋይናንስ ተቋም የአባልነት ምዝገባ ገጽ በደህና መጡ!


Purpose:

"RAEY Financial Institution works together with the community towards building a mutual tomorrow - where society cooperates - by becoming a good role model in focusing-on people's potential capabilities!"


ዓላማ፡

"ራዕይ የፋይናንስ ተቋም ወገን ለወገን የሚተባበርበትን የጋራ ነገን በጋራ ለመገንባት ሰዎች ያላቸው እምቅ ሀብት ላይ ትኩረት በማድረግ መልካም አርአያ በመሆን ይሰራል!"

Introduction

RAEY Financial Institution works towards developing a way for people to help each other through strengthening their capacity to help themselves and other vulnerable community members who are disadvantaged, so that our society does not lose hope and sustainable solutions due to poverty. In order to help achieve this goal, a partner charitable institution called RAEY Foundation is being established side by side.

መግቢያ

ራዕይ የፋይናንስ ተቋም የኅብረተሰባችን ክፍል ከድህነት የተነሳ ተስፋና ዘላቂ መፍትሔ በማጣት እንዳይባክን ሰዎች በትብብር መንፈስ ለማደግ እና ከራሳቸው አልፈው ሌሎች የተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት የሚችሉበትን አቅም በማጎልበት ወገን ለወገን የሚረዳዳበትን መንገድ ለማዳበር የሚሰራ ሲሆን ይህንን ዓላማ ደግሞ ለማሳካት ይረዳ ዘንድ ራዕይ ፋውንዴሽን የተባለ አጋር የበጎ አድራጎት ተቋም ጎን ለጎን አብሮ በመቋቋም ላይ ይገኛል፡፡

RAEY Foundation’s Purpose:

RAEY Foundation is a social work venture that aims to contribute towards social solidarity by addressing livelihood problems (psycho-social and economic difficulties) faced by the most vulnerable members of our community.

የራዕይ ፋውንዴሽን ዓላማ፡

ራዕይ ፋውንዴሽን በማህበረሰባችን የሚገኙ በእጅግ ከፍተኛ ችግር የሚኖሩ ወገኖችን የሕይወት መሰናክሎች (ማለትም የስነ-ልቦና ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን) በመፍታት ሕብረተሰባዊ ትስስርን በማጎልበት ዙሪያ የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግን ዓላማ ያደረገ የማህበረሰብ ተኮር እንቅስቃሴ ነው፡፡

Membership Registration Criteria of RAEY Financial Institution:

Donate a 50 ETB contribution monthly and participate in charitable activities that support the purpose through one’s capability by being a member of RAEY Foundation

የራዕይ ፋይናንስ ተቋም አባልነት ምዝገባ መስፈርት፡

የራዕይ ፋውንዴሽን አባል በመሆን ወርሃዊ 50 ብር ማዋጣት እና በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ዓላማውን የሚያጎለብት ተሳትፎ አቅም በፈቀደ ማድረግ

https://forms.gle/EfYQVYFxaWpECnRo7
RAEY Life Center & Services (RLCS) pinned «Welcome to the membership registration page of RAEY Financial Institution! እንኳን ወደ ራዕይ የፋይናንስ ተቋም የአባልነት ምዝገባ ገጽ በደህና መጡ! Purpose: "RAEY Financial Institution works together with the community towards building a mutual tomorrow - where society cooperates…»
2024/06/26 00:41:56
Back to Top
HTML Embed Code: