Telegram Web Link
መስከረም 2፣ 2016
ሰላም ቤተሰቦች
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በየሳምንቱ ለሁለት ቀን ቋሚ የኾነ ከእናንተ ከሚነሱና ወቅቱን ያገናዘቡ #የሳይኮሎጂ #የአመራርና ማህበራዊ #የስራ ፈጠራ ጉዳዮች ዙሪያ #እፅፋለሁ ስለሆነም በየትኛው ቀን እንዲሆን እንደምትፈልጉ ከታች ምረጡ?

#የተሰጠው ድምፅ #የሚቆጠረው እስከ #ቅዳሜ ማታ 6:00 ያለውን ነው ፡፡

በዛውም ወደ ቻናሉ ሰዎችን በመጋበዝ የሚፈልጉትን እንዲመርጡና እንዲማሩ እንርዳ ፡፡

✿ Vote : #በTelegram_ብቻ@psychoet
1️⃣ ሰኞ
2️⃣ ማክሰኞ
3️⃣ ረቡዕ
4️⃣ ሀሙስ
5️⃣ አርብ
6️⃣ ቅዳሜ
እንወያይበት!

1. ዕቅድ ማውጣት ተገቢ ነው ወይስ ህይወት ባመራችን እንጓዝ?

@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
አስገራሚ እውነታዎች ስለእንቅልፍ
*****

• የሰው ልጅ የዕድሜውን አንድ ሦስተኛ የሚያሳልፈው በእንቅልፍ ነው። ይህም በአማካኝ 25 ዓመት ይሆናል።

• በቀን ከ7 ሰዓት በታች መተኛት የሰዎችን አማካኝ የመኖሪያ ዕድሜ ይቀንሳል።

• አላርም (የሚያነቃ ሰዓት) ከመፈጠሩ በፊት እንግሊዝ እና አየርላንድ ውስጥ ሰዎችን ከእንቅልፍ በመቀስቀስ የሚተዳደሩ ሠራተኞች ነበሩ። ሠራተኞቹ ማልደው ተነስተው በር እያንኳኩ ደምበኞችን ከእንቅልፍ ያስነሱ ነበር።

• ቀንድ አውጣ ያለማቋረጥ ለ3 ዓመት መተኛት ይችላል።

• ድመቶች የዕድሜያቸውን 70 በመቶ የሚያሳልፉት በእንቅልፍ ነው። ድመቶች በቀን እስከ 16 ሰዓት ይተኛሉ።

• አሜሪካን ለ1 ቀን ብቻ ያስተዳደሩት ፕሬዝዳንት ዴቪድ አቹሰን፤ ከ24 ሰዓት የስልጣን ዘመናቸው ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፉት በእንቅልፍ ነበር። ጊዜውም እ.ኤ.አ መጋቢት 4 ቀን 1894 ነው።

• ማይግሬን (ከባድ የራስ ምታት)፣ ዝቅተኛ የደም ግፊት እና የእንቅልፍ መቆራረጥ፣ የቅዥት ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው።

• በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ፓል ከርን የተባለ የሀንጋሪ ወታደር የፊት ግንባሩን በጥይት ተመቶ እንቅልፍ የሚቆጣጠረው የአይምሮው ክፍል ላይ ከባድ ጉዳት ይደርስበታል። በዚህም ወታደሩ ለ40 ዓመታት ያህል (ቀሪ ዕድሜውን) ያለ እንቅልፍ አሳልፏል።

• ቀጭኔዎች ንቁ ለመሆን በቀን ከ5 እስከ 30 ደቂቃ ብቻ መተኛት በቂያቸው ነው። ቀጭኔዎች በቀን በአማካኝ እስከ 5 ሰዓት ይተኛሉ።

• ሞርፊን የሚለው ቃል የመጣው ሞርፈስ ከተባለው የጥንት ግሪኮች የእንቅልፍ እና የህልም አምላክ ነው። ሞርፊን የከባድ በሽታዎች የህመም ማስታገሻ ሲሆን በታማሚዎች ላይም የእንቅልፍ ስሜት ይፈጥራል።

• ምሽት ላይ ካፌን ያላቸው እንደ ቡና ፤ ሻይ እና ኮካ ያሉ (የሚያነቃቁ) መጠጦችን መጠጣት ፤ አይምሯችን ሜላቶኒን የተባለውን የእንቅልፍ ሆርሞን የሚለቅበትን ጊዜ እንዲዘገይ ያደርገዋል። ይህም መደበኛውን የእንቅልፍ ስርዓት በአማክኝ እስከ 40 ደቂቃ ድረስ ያዛባል።

• የመተኛት ፍርሃት ሶምኒ ፎቢያ ይባላል።

• አብዛኛው ሰው አልጋ ላይ ከወጣ በኃላ በ7 ደቂቃ ውስጥ እንቅልፍ ይወስደዋል።

• ስራን በወቅቱ የማይሰሩ ሰዎች ለእንቅልፍ ችግር (ኢንሶምኒያ) የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው።

• በተደጋጋሚ በነውጥ (ሁከት) የተሞሉ ህልሞችን ማየት፤ እንደ ፓርኪንሰን (የሚያንቀጠቅጥ በሽታ) እና ድሜንሻ (የመርሳት በሽታ) ያሉ የአይምሮ ህመሞች ምልክት ሊሆን ይችላል።

• ህልም እያዩ ህልም መሆኑን መረዳት እና የህልሙን ትዕይንት በተወሰነ መልኩ መቆጣጠር መቻል ሉሲድ ድሪም ይባላል። በተለይ ቪዲዮ ጌም መጫወት የሚያዘወትሩ ሰዎች እንዲህ አይነት ህልሞችን በተደጋጋሚ ያያሉ።

• ከ80 በላይ በሳይንስ የተለዩ የእንቅልፍ ችግሮች አሉ።

• የዓለም ህዝብ ቁጥር አንድ የእንቅልፍ መስተጓጎል ምክንያት ኢንተርኔት ነው።

• ከመተኛታችን ከ2 ሰዓት በፊት ቴሌቭዥን ማየት እንዲሁም ስልክ እና ኮምፒዩተር መጠቀም እንቅልፍ ያስተጓጉላል።

• የሰው ልጅ በአማካኝ የዕድሜውን 6 ዓመት የሚያሳልፈው ህልም በማየት ነው።

• ዳክዬዎች የሚተኙት አንድ አይናቸው ሳይከደን ነው።

• ስሉዝ የተባሉት እንስሳቶች 80 በመቶ የሚሆነውን የዕድሜያቸውን ከፍል የሚያሳልፉት በእንቅልፍ ነው። ዓለም ላይ ቁጥር አንድ እንቅልፋም እና ዘገምተኛ እንስሳቶች ስሉዝዎች ናቸው።

• ከየብስ እንስሳቶች በሙሉ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ያላቸው ዝሆኖች ናቸው። ዝሆኖች በቀን እስከ 2 ሰዓት ብቻ ይተኛሉ።

• በእንቅልፍ ልብ የሚበሩ ወፎች አሉ። በተለይ ስደተኛ ወፎች (ወቅት እየጠበቁ ከሀገር ሀገር የሚጓዙ) አየር ላይ ለአጭር ጊዜ ያሸልባሉ።

በኢዮብ መንግሥቱ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሰላም ቤተሰቦች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በየሳምንቱ ለሁለት ቀን ቋሚ የኾነ ከእናንተ ከሚነሱና ወቅቱን ያገናዘቡ #የሳይኮሎጂ #የአመራርና ማህበራዊ #የስራ ፈጠራ ጉዳዮች ዙሪያ #እፅፋለሁ ስለሆነም በየትኛው ቀን እንዲሆን እንደምትፈልጉ ከታች ምረጡ? #የተሰጠው ድምፅ #የሚቆጠረው እስከ #ቅዳሜ ማታ 6:00 ያለውን ነው ፡፡ በዛውም ወደ ቻናሉ ሰዎችን በመጋበዝ የሚፈልጉትን እንዲመርጡና እንዲማሩ እንርዳ…»
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ via @like
ሰላም ቤተሰቦች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በየሳምንቱ ለሁለት ቀን ቋሚ የኾነ ከእናንተ ከሚነሱና ወቅቱን ያገናዘቡ #የሳይኮሎጂ #የአመራርና ማህበራዊ #የስራ ፈጠራ ጉዳዮች ዙሪያ #እፅፋለሁ ስለሆነም በየትኛው ቀን እንዲሆን እንደምትፈልጉ ከታች ምረጡ? #የተሰጠው ድምፅ #የሚቆጠረው እስከ #ቅዳሜ ማታ 6:00 ያለውን ነው ፡፡ በዛውም ወደ ቻናሉ ሰዎችን በመጋበዝ የሚፈልጉትን እንዲመርጡና እንዲማሩ እንርዳ…
ሰላም ቤተሰቦች
በመረጣችሁት መሠረት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በየሳምንቱ #ሀሙስና #ቅዳሜ ለሁለት ቀን ቋሚ የኾነ ከእናንተ ከሚነሱና ወቅቱን ያገናዘቡ #የሳይኮሎጂ #የአመራርና ማህበራዊ #የስራ ፈጠራ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንጀምራለን። እንደመነሻ የተለያዩ #የሳይኮሎጂና #ማህበራዊ ሀሳቦች ላይ ማብራሪያ የምሰጥ ሲኾን በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ የምትሉትን በ#comment ላይ አሳውቁኝ? በተጨማሪ ወደ ቻናሉ ሰዎችን እንጋብዝ፡፡

#በTelegram_ብቻ@psychoet
የተመረጡ ቀናት
1️⃣ ቅዳሜ
2️⃣ ሀሙስ
መልካም ሠንበት ለሁላችሁ
#ይቻላል
JOIN TELEGRAM @psychoet

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
@psychoet

መልካም ቀን!
#Share_it
አንዳንድ ሰዎች የሚገፉህ ስላነስክ ሳይኾን ስለምትበዛባቸው ነው።

ስለዚህ #ሁሌ ብዛ😁
@psychoet
#በአንድ_ደቂቃ_ዉስጥ_አንብቡትና #አስተሳሰብዋን_ቀይሩ፡፡
ሁለት በጠና የታመሙ ሰዋች በሆስፒታል ዉስጥ በአንድ ክፍል ተኝተዉ ይታከሙ ነበር፡፡ አንዱ ታካሚ በቀን ለአንድ ሰአት በአልጋዉ ላይ እንዲቀመጥ የተፈቀደለት ሲሆን አልጋዉ ከክፍሉ ብቸኛዉ መስኮት አጠገብ ነበር፡፡ ሌላኛዉ ታካሚ ግን ካለበት ህመምና ፖራላይዝ ከመሆኑ የተነሳ ቀኑን ሙሉ ተኝቶ ግሉኮስ ብቻ እያገኘ ይቆይ ነበር፡፡ ሁለቱ ታካሚዋች ቀኑን ሙሉ ስለ ልጆቻቸዉ ፣ ስለ ስራቸዉ ፣ ወታደር እያሉ ስላሳለፋት ህይወት ሲያወሩና ሲጫወቱ ነበር የሚዉሉት፡፡

በየቀኑም አንዱ ታካሚ አልጋዉ ላይ በሚቀመጥበት ሰአት በመስኮቱ አሻግሮ ስለሚያየዉ ድንቅ የከተማዉ ገፅታ፣ ከሩቅ ስለሚታየዉ ሀይቅና በዉስጡ ስላሉ ዳክዬዋች ፣ በአካባቢዉ ስለሚጫወቱት ህፃናትና እጅ ለእጅ ተያይዘዉ ስለሚሄዱ ወጣት ፍቅረኛሞች ለሌላኛዉ ታካሚ ሲያብራራ ነበር የሚቆየዉ፡፡ በዚህ አንድ ሰአት ዉስጥ ሌላኛዉ ታካሚ አይኑን ጨፍኖ ዉጭ ያለዉን ነገር በአይነ ህሊናዉ ሲስል ጊዜዉን በደስታ ያሳልፍ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሌላኛዉ ታካሚ አገላለፅ እጅግ በጣም ማራኪ ስለነበር ሁሌ እሱም እነዚህን ነገሮች ለመመልከት እንዲጓጓና ህይወቱን እንዲወዳት ያረገዉ ነበር፡፡

እንዲህ እያረጉ ቀናት ፣ ሳምንታት ፣ ወራት አለፋ ፡፡ አንድ ቀን እንደተለመደዉ ነርሷ የሚታጠቡበትን ዉሀ ይዛ ስትመጣ ከመስኮቱ አጠገብ የነበረዉ ታካሚ ላይመለስ አሸልቦ ነበር ፡፡ በጣም አዝና ለሆስፒታሉ አስተዳደሮች ካመለከተች በኀላ ሰዉየዉ በክብር ተወስዶ ተቀበረ፡፡ ካጠገቡ የነበረዉ ታካሚ ግን እጅግ አብዝቶ አዘነ ከህመሙ በላይ ጓደኛዉን ማጣቱ የበለጠ አመመዉ፡፡ ሰዉየዉ በየቀኑ ይነግረዉ የነበረዉ የዉጭ ገፅታ ሁሌ ወደ አይምሮ ይመጣል ፡፡

ከዛም ነርሷ ስትመጣ ጠብቆ አልጋዉ በዛኛዉ በኩል እንዲቀየርለት ጠየቀ ፡፡ ነርሷም ዶክተሩን አማክራ በመስኮቱ በኩል አልጋዉን አስጠጋችለት፡፡ ካስተካከለችዉም በኅላ ጤንነቱን ጠይቃዉ ከክፍሉ ጥላዉ ወጣች ፡፡ ታካሚዉ እንደምንም ብሎ አንገቱን መለስ አርጎ ወደ መስኮቱ ዞሮ የዉጭዉን አለም ለመመልከት ሞከረ፡፡ ከብዙ ጥረት በኅላ አንገቱ ወደ መስኮቱ በጥቂት ሲዞር ግን ያየዉ ባዶ ግድግዳ ነበር፡፡ ከዛም ነርሷ ስትመጣ የሞተዉ ሰዉየ የሚነግረዉ እንዴት አርጎ ከመስኮት ዉጭ እያየ እንደሆነ ጠየቃት? ነርሷም እያለቀሰች እንዲህ ስትል መለሰችለት "በእርግጥ ሰዉየዉ ያን ሁሉ ያደረገዉ አንተን ለማቀረታታት ነበር እንጂ ሆስፒታል ሲገባ ሁለቱን አይኖቹን በጦርነት አጥቶ ማየት አይችልም ነበር" አለችዉ ፡፡ ይህን የሰማዉ ታካሚ በዚያዉ ላይመለስ አሸለበ ፡፡ 😢😢😢

#ትምህርት
በሕይወታችን በምንም መንገድ እንኳን እያለፍን ቢሆን ለሌላዉ መኖርና መደሰት ምክንያት እንሁን !
@psychoet
⚠️⚠️⚠️⚠️
ይሄን ሰሞን በከተማችን የተለያዩ ቦታዎች ራስን ማጥፋት በዝቷል።

በተለይ በአፍላው እድሜ በሚገኙ ወጣቶች ዘንድ ራስን ማጥፋት በጣም እየጨመረ ነው።

እባካችሁ ራሴን ላጠፋ ነው ወይም መሮኛል ብሎ ለፖሰተ ሰው ብታቁትም ባታውቁትም አብሮነታችሁን ድጋፋችሁን አሳዩ እንጂ ቀልድ አትቀልዱ። ለቀልድና ጨዋታ ብዙ የተሻለ ቦታ አለ።

በቅርብ የምናቃቸው ሰዎች መሞታቸው ሲገለፅ የአብዛኛው ጓደኞቻቸው ምላሽ "እኔ መች ጠረጠርኩ... ደብሮኛል እያለኝ.. " ምናምንም በሚሉ ፀፀቶች የተሞላ ነው።

በዙርያችሁ ላለ ሠው ሁሉ ትኩረት ስጡ!


--------------------------------------------------------
በዓመት እስከ 800,000 ሰዎች ራሳቸውን እንደሚያጠፉ የWHO ሪፖርት ያመለክታል፡ ከዚህ ቁጥር በላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ራሳቸውን የማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ ።
እድሜያቸው ከ 15 እስከ 29 ዓመት በሆኑ ወጣቶች ሁለተኛው ከፍተኛ ሞት የሚመዘገብበት ችግር ነው ፡ እንዲሁም 79% ያህሉ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ላይ የሚስተዋል ነው ። ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት መርዝ መጠጣት መታነቅ ፣የጦር መሳሪያ መጠቀም፣ በዋናነት ይጠቀማሉ ።

አጋላጭ ሁኔታዎች
-----------------------------------------------------------------
የተለያዩ የአዕምሮ ህመሞች በተለይም ድባቴ (Depression) ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ ችግር ፣ከባድ አካላዊ ህመም ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ፣ ጭንቀት፣ ድንገተኛ ግጭትና ብቸኝነት ዋና ዋና በአጋላጭ ችግሮች ናቸው ። እንዲሁም ቀደም ባለ ጊዜ ያልተሳካ ራስን የማጥፋት ሙከራ ከነበረ ዋነኛ አጋላጭ ችግር ሊፈጥር ሊሆን ይችላል ።

መከላከያ መንገዶች
-----------------------------------------------------------------
ራስን የማጥፋት ችግር በሚገባ መከላከል ይቻላል
በተለይም ራስን ለማጥፋት የሚረዱ ምቹ ሁኔታዎችን መቀነስ፣ ተደጋጋሚ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን በመገናኛ ብዙሃን በመስጠት፣ ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ ማዕከል በማደራጀት ለመምህራን ለወላጆች እንዲሁም ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ በቂ የቅድመ ጥንቃቄ መረጃና ትምህርት መስጠት እንዲሁም ለተማሪዎች የማማከር አገልግሎት ማመቻቸት፣ የአልኮል መጠጥ አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ የአእምሮ ህመሞችን ቶሎ መለየትና በቂ ህክምና ማድረግ እንዲሁም ተገቢውን ክትትል ማድረግ፣በቂ የሱስ ማገገሚያ ማዕከላትን ማቋቋም።
================================

ብዙ ሰዎች ህመማቸውን መከፋታቸውን የሚያወሩለት ወዳጅ አጥተው ሶሻል ሚዲያ ላይ ነው ሚገልፁት። እንዲህ አይነት ፖስቶችና መልእክቶች ስታዩ ረጋ ብላችሁ ምላሽ ስጡ። ቀልድ ነው ብላችሁ በምታላግጡበት ሰአት ያ ሰው ወደሞት እየቀረበ ይሆናል።

በዚህ ርዕስ ሰፋ ያለ ፅሁፍ ይዤ እቀርባለሁ።

ባላችሁበት የቴሌግራም ግሩፖች #share አድርጉ @psychoet
💪በራስ መተማመንን ማጎልበት💪
Developing Self Confidence

በራስ መተማመን ማለት ሰው ባለው ችሎታ፣ አካላዊ ውበትና ሁለንተናዊ ማንነት አለመፍራት እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ራስን መቀበል ማለት ነው፡፡ ትእቢት ፣ ትምክህት፣ ያልተገባ አውቃለሁ ባይነት እና ከመጠን ያለፈ ድፍረት በራስ መተማመን አይደለም።

በራስ መተማመንን የሚያጎለብቱ ብልሀቶች

🔥 ራስዎን ከሌሎች ጋር አለማነፃፀር።

🔥 ያለዎትን ክህሎት እና ድክመት መለየት።

🔥 የአካላዊ ገፅታ ውበትን መጠበቅ ደግሞም የሰውን ትኩረት ከልክ ባለፈ ሁኔታ የሚስቡ ጌጣጌጦችንና ሜካፖችን አለመጠቀም።

🔥 ጥሩ እና ምቹ አለባበስ መልበስ።

🔥 ነቃና ቀልጠፍ ብሎ መራመድ ።

🔥 በሰው ፊት ሀሳብዎን መግለፅ ሲኖርብዎ ቀድመው በቂ ዝግጅት ማድረግ።

🔥 መልካም በሆነ የህይወት እንቅስቃሴ የበኩልዎን አስተዋፅዖ ማድርግ።

🔥 ጥሩ የሚሰሩ ሰዎችን ማድነቅ/ ማበረታታት።

🔥 ሰዎች የተቃወሙዎት ወይም የናቁዎት ሲመስልዎ በእርጋታ ምላሽ መስጠት።

🔥 ሰዎች ስህተትዎን ሲነግሩዎ በቀና ማየት(ስለሚጠሉኝ ነው አለማለት)።

🔥 እርዳታ ሲያስፈልግዎ ያለፍርሀት መጠይቅ።

🔥 ሰአት ማክበር።

©በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

#Like #Share በማረግ ለሌሎችም እናስተምር

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
www.tg-me.com/psychoet
ሀሙስ #1
#ተስፋ_መቁረጥ_ከየት_ይመጣል ?
___

ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ሁነው ተስፋ የለኝም ፣ ተስፋዬ ተሟጧል ፣ የመሳሰሉትን ቃላት በቀን ተቀን ሕይወታቸው ይጠቀማሉ ፡፡

ተስፋ መቁረጥ ወደ ግባችን / ፍላጎቶቻችን እንዳንደርስ የሚያረገን ባህሪ ነው ፡፡ በሕይወቱ ብዙ ጊዜ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ወደግቡ/እቅዱ የመድረሱ እድል በጣም አነስተኛ ነው ፡፡ ወደ ጠቃሚ የሕይወት ግባችን አለመድረስ ደግሞ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት ፣ የበደለኝነት ስሜት ያመጣብናል ፡፡

ሳይኮሎጂ ችግር የመፍቻ ዋና መንገዱ የችግሩን ምክንያት መረዳት እንደሆነ ያትታል ፡፡ስለሆነም የተስፋ መቁረጥ ዋና ዋና ምክንያቶች እንመለከታለን፡፡
___
1
.Environmental Factor (አካባቢያዊ ምክንያት)

በአካባቢያችን ያሉ የተለያዩ ሁኔታዎችና ገጠመኞች ፍላጎቶቻችንንና እቅዳችንን እንዳናሳካ ይከለክሉናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ማድረግ የምንፈልገውን ነገሮች " አትችለውም ፣ ይከብድሀል ፣ ከዚህ በፊት አልተሞከረም ፣ ሰው ምን ይልሀል" በማለት ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ያደግንበት ባህል ፣ የምንኖርበት አካባቢ ለማድረግ ያቀድነውን ነገር እንዳናሳካ በራሱ ሊይዘን ይችላል ፡፡ ይሄ በሕይወታችን ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል ፡፡

2.Personal inadequency Factor (ግላዊ ብቃት/ክህሎት ማጠር )

ይህ ደግሞ ፍላጎቶቻችንን እንዳናደርግ የሚገድበን አለመሙላት (ብቃት አልባነት) ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድን እቃ በጣም ወደነው ለመግዛት ስንፈልግ ከተወደደብንና ያለን ገንዘብ አነስተኛ ከሆነ ተስፋ ቆርጠን ላንገዛ እንችላለን ፡፡ እዚህ ጋር ነገሩን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አለመኖር የራሳችን የሆነ ጉድለት ይሆናል፡፡ ሌላው አንድን ነገር ለመስራት አስበን የግል ችሎታ / ብቃት/ ክህሎት ሲያንሰን እሱ " በቃ አልችልም " በማለት ተስፋ ለመቁረጥ መንስኤ ይሆነናል ፡፡

3. Conflict of interest ( የፍላጎት ግጭት )
የመጨረሻው የግላዊ ፍላጎቶች/ ግቦች እርስ በእርስ ሲፃረሩ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችላል ፡፡ ተስፋ መቁረጡ የሚመጣዎ ሁለቱንም ግቦቻችንን ልናሳካ ባለመቻላችን ነው ፡፡ አንዱን ግብ ብናሳካ ራሱ ሌላውን ስላላሳካን የመወላወል ተስፋ የመቁረጥ ( የማዘን ) ስሜት ይሰማናል፡፡

ከነዚህ ሶስቱ ዎና ዎና ምክንያቶች እግጅ በጣም ብዙ ሰው የሚያጋጥመው የመጨረሻው (.Conflict of Motives / የፍላጎት ግጭት ) እንደሆነ ሳይኮሎጂ ይጠቁማል፡፡
__
እነዚ
ህ Conflict of motives ( የፍላጎት ግጭት ) ደግሞ በ አራት ይከፈላሉ ፡፡
__
ሀ.
Approach - Approach Conflict
(ፍላጎት ፥ ፍላጎት ግጭት)

ይህ ግጭት ሁለት ነገሮችን በእኩል ፈልገን ነገር ግን መምረጥ የምንችለው አንዱን ብቻ ሲሆን ማለት ነው ፡፡ ለምሳሌ :- ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኅላ Department ሲመርጡ ብዙ ተማሪዎች በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ የdepartment ምርጫዎች ይወጠራሉ ነገር ግን መምረጥ የሚችሉት የወደዱትን ሁሉ ሳይሆን አንዱን ብቻ ስለሚሆን ግጭት ውስጥ ይገባሉ ፡፡ ሌላው ገበያ ሂደን ሁለት ሱሪዎች በጣም ወደናቸው ነገር ግን መግዛት የምንችለው አንዱን ብቻ ከሆነ ይህ አይነት ግጭት ከራሳችን ጋር ይገጥመናል፡፡

ለ. Avoidance - Avoidance Conflict (የማስወገድ ፥ የማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ ከሁለት የማንፈልጋቸው ነገሮች የግድ አንዱን መምረጥ ግድ ሲለን ነው ፡፡
ለምሳሌ ፦ ልጃችን በሰዎች ታግቶ ብር ካልከፈላችሁ ይገደላል ቢሉን ፤ እዚህ ጋር ልጁ እንዲሞትም አንፈልግም ለአጋቾቹ ብር መክፈልም አንፈልግም ፡፡ ግን አንዱን መምረጥ ግድ ይለናል ፡፡ ሌላ ምሳሌ ፦

ሐ. Approach - Avoidance Conflict (የፍላጎትና ማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ በአንድ ግብ ላይ የፍላጎትም የማስወገድም ስሜት ሲሰማን ነው ፡፡

መ. Multiple Approach - Avoidance Conflict (ብዙ የፍላጎት ማስወገድ ግጭት)

ይህ ሁላችንም በሕይወት ቆይታችን የሚያጋጥመን የለት ተለት ግጭት ነው ፡፡ እያንዳንዱ የሚገጥመን ነገር #ብዙ_አወንታዊና_አሉታዊ ነገሮች ይይዝና እሱን #መምረጥና #አለመምረጥ ችግር ይሆናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው መልኩን ፣ ገቢውን ወደን ፀባዩ አመለካከቱ ካላማረን ይሆነኛል አይሆነኝም ብለን ከራሳችን እንጋጫለን ፡፡ሌላው አንድን ስራ ስንሰራ በዉስጡ ያሉ የተለያዩ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ስገፉን ሲስቡን እንደዚህ አይነት ግጭት ውስጥ እንገባለን ፡፡

፠፠__፠፠

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙
www.tg-me.com/Psychoet 👍

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠__፠፠
ሳምንት ሰው ይበለን!
#ክፍል_1
ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አርጉት !   

Psychology - ሥነ ልቡና /Ψ/
ሥነልቡና በታሪኩ ውስጥ የተለያየ ትርጓሜ ይዞ የመጣ ሲሆን አሁን በደረሰበት የዕድገት ደረጃ ግን አብዛኞቹ ተመራማሪዎች የሚስማሙበት ትርጉም ይህን ይመስላል ፡፡

ሳይኮሎጂ ከሁለት የግሪክ ቃላት ሳይኪ እና ሎጎስ (Psyche & logos ) የሚሉ ቃላቶች የተወሰደ ነው ፡፡
❖(Psych )ሳይኪ | Mind (ነፍስ - አዕምሮ - መንፈስ) ሲሆን
❖(Logos) ሎጎስ | Disclosure (ገለፃ /ጥናት) ማለት ነዉ ፡፡

በዚህም መሰረት ሥነልቡና ማለት፦
ስለ #ባህሪይ እና #የአዕምሮ አሰራር ሂደት የሚያጠና #ሳይንስ ነው ፡፡

#ባህሪይ ስንል ማናቸውም የምናረጋቸዉና በአይን የሚታዩ ነገሮች ሲሆኑ
#የአዕምሮ አሰራር ሂደት ደግሞ በአይን የማይታይ ግን በተግባር የሚገለፅ ነዉ ፡፡
#ሳይንስ ስንል ሳይንስ የሚያልፍባቸውን ሂደቶች ስለሚያልፍ ነዉ እነርሱም (Emperical / በሙከራ የተረጋገጠና መመልከት የምንችለው ,
Objective / ከግል ስሜት ጋር ያልተያያዘና ከገሀዱ አለም ጋር የተገናኘ ,
Systematic / በስርአት የተቀረፀና የሚሰራ ,
Replicable / ውጤቱ ሆነ ሂደቱ በሌላ ሰው መደገም የሚችል) ናቸው ፡፡

ሌላው ሥነልቡና ማህበራዊ ወይስ ተፈጥሮአዊ ሳይንስ ነው የሚለው ጥያቄ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ባለንበት ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም የትምህርት ተቋም እንደማህበራዊ ሳይንስ የሚታይና የሚሰጥ ሲሆን ባብዛኞቹ ባደጉት ሀገራት ግን ከህክምና ትምህርት ክፍል ስር የሚሰጥ በተፈጥሮአዊ ሳይንስ ስር ያለ ትምህርት ነው ፡፡
Social science is the scientific study​ of human society and social relationships. Whereas natural science deals with the physical world. By these definitions then psychology would fall under the category of a natural science.
https://www.thestudentroom.co.uk/showthread.php?t=4949812

ሥነ ልቡና አዕምሮን አያጠናም ይልቁንስ ስለ አዕምሮ አሰራር ሂደት እንጂ። (ስለአዕምሮ የሚያጠኑት ኒውሮሎጂስት እና ሳይካትሪስቶች ናቸዉ ፡፡ )

የሥነልቦና ትምህርት ዋና አላማ / ግብ (goal) አራት ናቸው እነርሱም ፦
1.ባህሪን መግለፅ (Describe )
2.ባህሪን ማብራራት (Explain)
3.ባህሪን መተንበይ (predict)
4.ባህሪን መምራት /መቆጣጠር (control )

ሥነልቡና (Psychology ) መገለጫ ምልክት (Symbol) ያለዉ ሲሆን ምልክቱ  የግሪኩ 23ኛ ካፒታል ሊተር Ψ ሳይ (Psi ) ነዉ፡፡ የ ሳይ ምልክት የተገለበጠ "ሐ" ይመስላል ፡፡ በዚህ ምልክት  ' Ψ ' ላይ ያሉት ሶስት አምዶች አንዳንድ ጠቢባን በነዚህ ሶስት ነገሮች ይመስሏቸዋል
1. ነፍስን #Soul
2. ሀሳብን(አዕምሮ) #Mind
3. መንፈስን #Spirit

❖❖❖❖

በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል፡፡ ማንኛውም ጥያቄ / ተጨማሪ ሀሳብ Comment ማረግ ይቻላል ፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት እንዚህን እናያለን ፦
1. በሥነልቡና ስር ያሉ ዋና ዋና ሙያዎች (Sub fields )
2. የሥነልቡና ታሪካዊ አመጣጥ ፣ ከፍልስፍና ጋር ያለው ቁርኝትና በዘርፉ ብዙ ሚና ያበረከቱ ሰዎች
3. እንዴት ነገሮችን እንደምናስታውስና እንደምንረሳና ከዚህ ጋር ተያይዞ መርሳት የሚባል ነገር በሥነ ልቡና አለ ወይ
4.ሥነ ልቡና ስለ ህልም ምን ይላል ብለን እንመለከታለን

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው  💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!

Join
@psychoet
@psychoet
@psychoet
#መልካምነት
አንድ የ 24 አመት ወጣት ከሚጓዝበት ባቡር አሻግሮ በሚያያቸዉ ነገሮች ተገርሟል፡፡ ከዛም ጮክ ብሎ "አባቴ ፥ ዛፎቹን እያቸዉማ ወደኀላ እየሆዱኮ ነዉ! " ሲለዉ አባትየዉ #ፈገግ አለ ፤ በቅርብ ያሉ ተሳፋሪዋች ግን የ 24 አመት ወጣቱን በሀዘን ስሜት እንደ ልጅና #ህመምተኛ ተመለከቱት፡፡
ወጣቱ በድንገት በመደነቅ ደግሞ "አባቴ ፥ ተመልከት ደመናዉ እኮ አብሮን እየሄደ ነዉ!" አለዉ፡፡ አባትየዉ አሁንም ልጁን #በፈገግታ ተመለከተዉ ፤ በቅርብ ያለ አንድ ሰዉዬ ግን ወጣቱ በሚያሳየዉ የልጅ ፀባይ አላስችል ብሎት በንዴት ...
"ለምን ልጅህን ወደ ጥሩ የአዕምሮ ሆስፒታል አትወስደዉም?" አለዉ ለወጣቱ አባት፡፡
አባትየዉ በአንዴ ፊቱ በሀዘን ተሞላ ፣ አይኖቹ እንባ እየተናነቀዉ በእርጋታ እንዲህ ብሎ መለሰለት..."ሆስፒታል ወስጄዋለሁ... ፥ አሁን ራሱ ከዛ እየተመለስን ነዉ ፥ ልጄ ከልጅነቱ ጀምሮ ማየት አይችልም ነበር ለወራት ከታከመ በኀላ ዛሬ ነዉ ታክሞ አይቶ ከሆስፒታል የወጣዉ" አለዉ ፡፡

#ትምህርት

በዚህ ምድር እያንዳንዱ ሰዉ የራሱ የሆነ ታሪክ አለዉ፡፡ የሰዉን ታረክ ሳናዉቅ ሰዉ ላይ ለመፍረድ አንቸኩል፡፡ ምክንያቱም እዉነታዉን ስንሰማና ስናዉቅ ሁሌ የተናገርነው ይቆጨናልና፡፡

#የሳምንት_ሰዉ_ይበለን ♥️♥️♥️
#ለሰዋች_የደስታ_ምንጭ_መሆን_ባንችል_የሀዘን_ምክንያት_አንሁን
#ፈጣሪ_ሀገራችንን_ይጠብቅልን_ሰላም_ያርግልን

መልዕክቱ የተመቸዉ ደግሞ #share የሚለዉን በመጫን ሌሎችን ያስተምራል !

Nahu|ናሁ
ሀሙስ #2

ግጭትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት
Telegram www.tg-me.com/psychoet

ግጭት የአንድ ሰው ድርጊት ወይም አመለካከት ሌላውን ሲረብሽ የሚፈጠር ሲሆን ይህም በቤተሰብ ፤ በጓደኛ ፤ በስራ ቦታ፤ በጋብቻ.. ወዘተ መካከል ሊከሰት ይችላል፡፡ የግጭቱ ሁኔታ መክረር ወይም በቀላል መፈታት  እንደተጋጪዎቹ ባህርይ ፤ግንኙነትና  የግጭቱ ዓይነት ይለያያል፡፡ የተለያዩ የግጭት ዓይነቶችን በአራት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት (Intra-personal)

ምንም እንኳን የተለያዩ የግጭት ዓይነቶች ቢኖሩም በማኅበረሰባችን ውስጥ የላቀ ትኩረት የሚሰጣቸው ከውጫዊ አካላት ጋር ለሚፈጠሩ ግጭቶች ነው፡፡ ይሁንና ሰው ከራሱ ጋር የሚፈጥረው ግጭት ከሌሎች ግጭቶች በተለየ መልኩ አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና ማኅበራዊ ቀውሶችን እንደሚያስከትል ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት በተለያዩ  ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው ሰው በህይወት ዘመኑ በሚፈጽማቸው ስህተቶች ከህሊናው ጋር የሚፈጥረው ግጭት ነው፡፡

ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር ግጭት (Inter-personal)

በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የግጭት ዓይነት ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ሲሆን ይህም በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዋነኛዎቹ የዚህ ግጭት መንስኤዎች መካከል በሃሳብ አለመግባባት ፤ ግትርነት ፤ ነገሮችን በትዕግስት አለማሳለፍ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡

በአንድ ቡድን አባላት መካከል የሚፈጠር (Intra-group)

ይህ የግጭት ዓይነት በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጠር ሳይሆን ለአንድ ዓላማ በተመሠረተ ቡድን ውስጥ ባሉ አባላት መካከል ምክንያታዊና ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች የራስን አቋም በማጣት የሌላውን ሃሳብ ተከትሎ በመሄድና የተዛባ መረጃ በመያዝ ከሌሎች የቡድን አባላት ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡

በቡድኖች መካከል የሚፈጠር ግጭት (Inter-group)

የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሁለትና ከዚያም በላይ የሆኑ ቡድኖች በሚያገናኟቸው ጉዳዮች ላይ ተስማምተው መስራት ሳይችሉ ሲቀር ወይም አንዱ ሌላውን በበላይነት ማስተዳደር ሲፈልግ የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡

በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው የግጭት ዓይነቶች በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

*የአመለካከት ልዩነት
*የባህል ፤ አስተዳደግ ፤ የባህርይ ልዩነት
*የዓላማ እና የፍላጎት ልዩነት
*የስልጣን/የኃይል ልዩነት
*እውነታና ፍላጎት አለመስማማት

★የግጭት አፈታት ዘዴዎች

ማንኛውም ዓይነት ግጭት ለማኅበራዊና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ሊዳርግ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ጊዜ የሚያጋጥሙትን ለግጭት የሚዳርጉ ሁኔታዎችን ከግጭት በራቀ መልኩ የመፍታት ክህሎትን ማዳበር ስኬታማ የሆነ ህይወት ለመምራት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ግጭትን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት የሚያስችሉ ነጥቦች

1.የግጭቱን መንስኤ ለይቶ ማወቅ፡–

ግጭቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ መንስኤያቸውን ለይቶ ማወቅ ግጭቱ እንዳይባባስ ለማድረግና በቀላሉ መፍትሄ ለማፈላለግ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ አንድ  ግጭት በሃሳብ አለመግባባት ቢፈጠር ይህ ሁኔታ ሊከሰት የቻለው ተጋጪው ካለው የአስተሳሰብ፤ የባህል ፤ የአስተዳደግ ፤ ወይም ከግለሰቡ የግል ባህርይ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ መቻል ግጭቱን በቀላሉ ለመፍታት ይረዳል፡፡

2.አማራጭ መፍትሄዎችን ማየት

ለተከሰተው የሃሳብ ልዩነት ወይም ግጭት እንደመፍትሄ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጭ መንገዶችን ማየት ግጭትን በቀላሉ ለመፍታት ያስችላል፡፡

3.ስሜታዊነትን ማስወገድ

አብዛኛውን ጊዜ በስሜታዊነት የሚወሰዱ እርምጃዎች ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው የጎላ ነው፡፡

በመሆኑም ግጭት በሚነሳበት ወቅት እራስን ለመቆጣጠር እና ከስሜታዊነት የጸዳ ውሳኔ ለመወሰን ይቻል ዘንድ ግጭቱ ከተነሳበት አካባቢ በመራቅ ረጋ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

4.ስምምነት መፍጠር

 የተፈጠረውን አጋጣሚ አንስቶ ፊት ለፊት በግልጽ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር እንደ አስፈላጊነቱ ሌላ ሦስተኛ አካል ገብቶ የሚያነጋግርበትን መንገድ በመፈለግ ከግጭት ይልቅ ስምምነት የሚፈጥርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል ፡፡

መልካም ቀን ተመኘሁላችሁ ፤ ሰላም!
በአንቶኒዮ ሙላቱ ©zpsychologist

Telegram www.tg-me.com/psychoet
#ክፍል_2
ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አርጉት !
የፔጃችን ቤተሰብ ያልሆናችሁ ፔጁን Like በማረግ ጥሩ ትምህርት በነፃ ያግኙ ።

የሥነ ልቡና ሳይንስ ትምህርት እንዴትና በማን ተጀመረ ?

ሥነ ልቡና ከሰው ልጅ ፍጥረት ጀምሮ (በ Evolution ለሚያምኑ ደግሞ አሁን ያለው የሰዉ ዘር Evolv ካረገበት ጊዜ ጀምሮ ) በተለያየ የህይወት መስተጋብር ሲጠና ሲገለጥ ሲታወቅ የመጣ ሙያ ነዉ ፡፡ ይሁን እንጂ ሥነልቡና እራሱን እንደቻለ ትምህርት / ሳይንስ መጠናት የጀመረው ከ 19ነኛው ክፍለ ዘመን በኀላ ነው ፡፡
Wilhelm Wundt የሚባል ሰው በጀርመን ሀገር 1879 የመጀመሪያውን የሥነ ልቡና የሙከራ (ምርምር) ተቋም በ Leipzig ዩኒቨርስቲ ከፈተ ፡፡ ይህ በታሪክ የመጀመሪያው የሥነልቡና ምርምር ቤተሙከራ ለመሆን በቅቷል ፡፡ በዚህም ሳቢያ አቶ Wundt አብዛኛውን ጊዜ የሥነልቡና አባት በመባል ሊጠራ ችሏል ለዘመናዊ ሥነልቡና ጥናት መጀመርም መሰረት ሆኗል ፡፡

ከዚህ በፊት የፈረንሳዩ ፈላስፋ ሬኒ ዴካርት (1596 -1650) በስነልቡና ሙያ እድገትና ሙያውን ከፍልስፍና ትምህርት ራሱን ችሎ እንዲወጣ ብዙ ሚና የተጫወተ ነው ፡፡ በ Interactive dualism Theory ( በበይነግንኙነታዊ ሁለትዮሽ ፅንሰ ሀሳቡ ) የሰውን ልጅን አዕምሮ /አስተሳሰብ ከ ስጋው በመነጠል ያላቸውን መስተጋብር ለማጥናት የሞከረ ፈላስፋ ነው ፡፡ በ 17 ክፍለ ዘመንም ጆን ሎክ እና ቶማስ ሆብስ ለዚህ ሙያ እድገት ከፍልስፍናው ጎን ብዙ ሚና ተጫውተዋል ፡፡

#የሥነልቡና_ታሪካዊ_አመጣጥ

ሥነልቡና በታሪክ ዉስጥ በፍልስፍና ስር የሚጠና ሙያ የነበረ ሲሆን ትርጓሜውም ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋና እየተስተካከለ እራሱን ችሎ ወቷል ፡፡ የሥነልቡና ትምህርት እድገት በታሪክ ውስጥ በአራት ተከፍሎ ይታያል ። እነርሱም
1 ፡ Ancient Greekperiod / በጥንታዊ የግሪክ ክፍለጊዜያት
2 ፡ per-modern period / ቅድመ ዘመናዊነት ጊዜ
3 ፡ modern period / በዘመናዊነት ጊዜ
4 ፡ current status / አሁን ያለንበት (ድህረ ስልጣኔ እንዲሁም ተሻጋሪያዊ ስልጣኔ ) ዘመን

1.በጥንታዊ የግሪክ ክፍለጊዜያት የግሪክ ፈላስፎች ለዕድገቱ ብዙ ሚና አበርክተዋል ፡፡ ከነዚህም በጉልህ ተጠቃሾቹ ሶቅራጥስ ፣ ፕሌቶና አርስቶትል ናቸው ፡፡
በዚህ ጊዜ ሥነልቡና የሚጠናው ከነፍስ / አዕምሮ አንፃር ብቻ ነበረ ፡፡ እነዚህ ፈላስፎችም በስራቸው የሚያነሱት ስለ አዕምሮ እንጂ ስለ ባህሪ አልነበረም ፡፡

2.ቅድመ ስልጣኔ ዘመን በፊት ፡ ሥነልቡና ከፍልስፍና ተነጥሎ ለብቻው የወጣው በዚህ 1800ዋቹ ጊዜ ነበር ፡፡ ለዚህ ትልቅ ሚና ያበረከቱት Wilhelm Wundt and William James ናቸው ፡፡

3.በዘመናዊነት ጊዜ : በዚህ ዘመን ብዙ የስነባህሪ ተመራማሪዎች የመጡበት ጊዜ ሲሆን ሥነ ልቡናን ከአዕምሮ /ነፍስ በተለይ #ከባህሪ አንፃር ለማየት የተሞከረበት ጊዜ ነው ፡፡

4.አሁን ያለንበት ጊዜ ፡ ከዚህ በፊት የነበሩት የሥነ ልቡና ትርጓሜዎች ሙሉ ያልነበሩ ሲሆኑ በዚህ ጊዜ ግን ሥነ ልቡና የአዕምሮ አሰራር ሂደትንና ባህሪን አጠቃሎ የሚያጠና ሳይንስ ተብሎ ተተርጉሟል ፡፡

#በሥነልቡና ስር ያሉ ዋና ዋና ሙያዎች (Sub fields )

ዘርፉ እራሱን ችሎ እንደ ሳይንስ ከወጣ ገና 140 አመት በመሆኑና በዚህ ጊዜም በጣም ብዙ በስሩ ያሉ የሙያ አይነቶች እየታወቁና እየተጠኑ በመሆናቸው ትክክለኛ ቁጥሩ አሻሚ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ የሥነ ልቡና ተቋማች ውስጥ ያሉ ሰዎች ያሉት ሙያዎች በዚህ ጊዜ ከ 100 እንደሚያልፉ ይነገራሉ ፡፡
ካሉት ሙያዎች ውስጥ በጣም የሚታወቁትን ጥቂቶች መርጬ እንደሚከተለው አቀርባለሁ

1. Clinical (ክሊኒካል ሳይኮሎጂ ) :- ከቀላል እስከ አስከፊ የአዕምሮ የስሜትና የባህሪይ ህመሞችን (ችግሮችን) የሚያጠናና የሚያክም ነው ፡፡

2.Counseling psychology
የሰው ልጅ የሚገጥሙትን የቀን ተቀን ግላዊ / ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት የሚሞክር ነው ፡፡ሰዎችንም ችግርን ለመቋቋምና ለመፍታት እንዲረዳቸው ያላቸውን ጥንካሬ እንዲያውቁ ይረዳል፡፡

3.Cognitive and Perceptual psychology
የሰዉን የመረዳት ፣ የማሰብ ፣ የመገንዘብና የማስታወስ ሁኔታ የሚያጠና ነው፡፡ በዚሀሸ ስር አዕምሮአችን እንዴት ዕውነታን እንደሚረዳ ? ሰዎች ነገሮችን እንዴት እንደሚማሩ ? ሰዎች ቋንቋን እንዴት እንደሚረዱና እንደሚያወጡ ? ሰዎች እንዴት እንደሚወስኑ ፣ እንደሚፈርዱ እምክንያታዊ ሀሳብ እንደሚያመነጩ ያጠናል ፡፡

4.Neuropsychologists and Behavioral neuropsychologists
በአዕምሮና በባህሪይ መካከል ስላለው ግንኙነትና የአሰራር ዘዴ ያጠናል ፡፡

5.Health psychology
እንዴት ስነህይወት ፣ ሥነልቡናና ማህበራዊ ጉዳዮች የሰው ልጅ ጤናን አፊክት እንዳሚያረጉ ያጠናል ፡፡

6.Developmental psychology
የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ የሚያሳልፋቸውን የተለያዩ የእድገት ደረጃዎች ያጠናል ፡፡

7.Social psychology
የሰው ልጅ እርስ በርሱ በሚያረገው ማህበራዊ ግንኙነትና መስተጋብር ያሚደርስበትን ተፅዕኖዎች ያጠናል ፡፡

8.School & Educational psychology
ከመማር ማስተማር ጋር የተያያዙ እያንዳንዳቸው ጉዳዮች የሚጠኑበት ነው ፡፡

9.Industrial-Organizational Psychology
በአንድ የስራ ቦታ ላይ የሚገኙ የሰዎችን ግንኙነት ፣የሥራ ተዛምዶና ባህሪይ የሚያጠና ነው ፡፡

??????????
#ከዚህ በላይ ከዘረዘርኳቸው ጥቂት የሥነልቡና ሙያዎች ( Sub fields ) የቱን ወደዳችሁት ? ወደፊትስ የቱን አተኩረን እንድንማማር ይፈልጋሉ? #Comment አርጉ

❖❖__❖__❖❖
Source:-

http://psychology-hari.blogspot.com/2012/01/brief-historical-background-of.html?m=1

https://opentextbc.ca/introductiontopsychology/chapter/1-2-the-evolution-of-psychology-history-approaches-and-questions/

http://colfa.utsa.edu/psychology/subfields_of_psychology

በሚቀጥለው ሳምንት ይቀጥላል፡፡
ማንኛውም ጥያቄ / ተጨማሪ ሀሳብ Comment ማረግ ይቻላል ፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት እንዚህን እናያለን ፦
1.በብዙ ሰው ከተመረጠው ሙያ ውስጥ ፤ በሙያዉ ስር ያሉ መሰረታዊያንን እንመለከታለን
በተጨማሪ የሰው ልጅ እንዴት ነገሮችን እንደሚማርና እንደሚያውቅ በአስደናቂ መንገድ እንማራለን

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!


🎡@🎡መልካም ቀን
    #Join   #Join     #Join
      🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
             🚗 @Psychoet👍
             🚕 @Psychoet👍
2024/09/28 17:30:27
Back to Top
HTML Embed Code: