Telegram Web Link
ሰላም ቤተሰቦች የስልጠና ፕሮግራሞቻችን ባለፈው ሳምንት ጀምረዋል ፡፡
በመጀመሪያው ቀን ስለ ስልጠናው ሂደትና ስለ ስልጠናዎቹ ርዕሶች የተወያየን ሲሆን

ቅዳሜ 3-5 | ቅዳሜ 5-7 | ቅዳሜ 8-10
እሑድ 3-5 | እሑድ 5-7
ባሉን ፈረቃዎች በእያንዳንዱ የ 2 ሰው ቦታ ስላለን በተመቻችሁ ፈረቃ መመዝገብ የምትፈልጉ 0912664084 በመደወል ቦታ ማሲያዝ ትችላላችሁ፡፡ በተጨማሪም ከሰኞ - አርብ ባሉት ቀናት በግል ለብቻችሁ መሰልጠን የምትፈልጉም ደውላችሁ መረጃ መጠየቅ ትችላላችሁ ፡፡

#የስልጠና ርዕሶች

-ሳይኮሎጂን መረዳት
-የህይወትን አላማ ማግኘት
-የስሜት ብልህነት
-ውጤታማ እቅድ አወጣጥና ጊዜ አጠቃቀም
-ስልታዊ የሕይወት ችግር አፈታት ዘዴዎች
-ድብርትና ጭንቀትን ማሸነፍ እና ሌሎችም ስልጠናዎችን ያካተተ ነው።

በ#500 ብር ብቻ !

★ሁሉንም ለተካፈለ በነፃ የግል የማማከር ጊዜ ፣ የንግግርና የተግባቦት ክህሎት ስልጠና ሰርተፊኬትን ጨምሮ ያገኛል።


አድራሻ 4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ( ከቶታል ጀርባ) - አራት ኪሎ የገበያ ማዕከል ህንፃ ቁጥር 219

ስልጠናውን መካፈል ለሚፈልጉ ጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው @Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሰላም ቤተሰቦች የስልጠና ፕሮግራሞቻችን ባለፈው ሳምንት ጀምረዋል ፡፡ በመጀመሪያው ቀን ስለ ስልጠናው ሂደትና ስለ ስልጠናዎቹ ርዕሶች የተወያየን ሲሆን ቅዳሜ 3-5 | ቅዳሜ 5-7 | ቅዳሜ 8-10 እሑድ 3-5 | እሑድ 5-7 ባሉን ፈረቃዎች በእያንዳንዱ የ 2 ሰው ቦታ ስላለን በተመቻችሁ ፈረቃ መመዝገብ የምትፈልጉ 0912664084 በመደወል ቦታ ማሲያዝ ትችላላችሁ፡፡ በተጨማሪም…»
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ምስጋና እና ዘርፈ ብዙ ጥቀሞቹ

በርካታ ጥናቶችም የምስጋና ባህል በተቻለ መጠን መዳበር እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ ጥናቶች መካከል የ “Positive Psychology” መስራች ሴሊግማን 411 ሰዎች ላይ ያካሄደው ጥናት ቀዳሚ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው የተለያዩ አዎንታዊ ሀሳቦች እና ድርጊቶች ያላቸውን ውጤት በመለካት (Testing) ሲሆን ምስጋና ከሁሉም የላቀ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ታውቋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሕይወታችን ትልቅ ቦታ አለው የሚሉትን እና በሚገባ አመስግነው ለማያውቁት ሰው የምስጋና ደብዳቤ ፅፈው በራሳቸው እጅ እንዲያደርሱ ከተደረገ በኋላ ውጤቱን ተጠንቶ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ተሳታፊዎቹ ላይ ታይቷል፡፡ ለውጡ ይበልጥ አስደናቂ ሊሆን የቻለው የተፈጠረው የደስታ ስሜት ለብዙ ወራት መቆየት በመቻሉ ጭምርም ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከየትኛውም ድርጊት በበለጠ መልኩ ምስጋና አመስጋኙን ደስተኛ የማድረግ ኃይል እንዳለው ታውቋል፡፡

የምስጋና ጥቅሞች

#ደስተኛ ያደርገናል

በቀን ለአምስት ደቂቃ ያህል ማመስገን ከአማካይ ጤንነት በላይ 10% ሁለንተናዊ ጤንነትን ያሻሽላል፡፡

#ሰዎች እንዲወዱን ያደርጋል

በሁለት የተለያዩ ጥናቶች ከአብዛኘው ሰው 10 % በላይ የሚያመሰግኑ ሰዎች 17.5 % ከሌሎች የበለጠ የሰው መውደድ እንዳላቸው ታውቋል፡፡ ምስጋና ሰዎች እምነት እንዲጥሉብን፣ እንዲቀርቡን እና እንዲወዱን ያደርጋል፡፡

#በሥራ ቦታ ስኬታችንን ይጨምራል

ምስጋና የተሻለ መሪ፣ ተግባቢ፣ የውሳኔ ሰው እና ስኬታማ እንድትሆኑ ያግዛል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ምስጋና ጤናማ ስሜት እንዲኖረን፣ ቁሳዊ አመለካከታችን (Materialism) እንዲቀንስ፣ ራስ ወዳድነት እንዲቀንስ፣ ለራሳችን ያለን አመለካከት እንዲሻሻል፣ ጥሩ እንቅልፍ እንድንተኛ፣ ረጅም እድሜ እንድንኖር ወዘተ ያደርጋል፡፡

ምስጋና ባህል እንደመሆኑ መጠን ደግመን ደጋግመን እስከተለማመድነው ድረስ ይሻሻላልም፡፡ ይህንን ለማድረግ የምስጋና ደብዳቤ መጻፍ፣ ጊዜ ቢታጣ እንኳ በልቦናችን ማመስገን፣ የምስጋና የግል ማስታወሻ መፃፍ፣ በረከቶቻችንን መቁጠር፣ ፀሎት የመሳሰሉት የምስጋና ባህላችንን ለማሻሻል የሚረዱ ልምምዶች ናቸው፡፡

_______________
ይህን ካነበባችሁ አይቀር የማመስገን ባሕልን ዛሬውኑ መለማመድ ጀምሩ ፡፡ ሕይወታችሁ ሲለወጥ ታዩታላችሁ ፡፡

አንድ ምሳሌ ልጨምርላችሁ ፦ አንድ ዳቦ ይዛችሁ ሶስት የተቸገሩ ሰዎችን ተመለከታችሁ ፡፡ ከዛ ዳቦውን እኩል ቦታ ቆርሳችሁ አካፈላችኀቸው፤ ሰዎቹም ሲበሉም ቆይተው ሲጨርሱ
#አንዱ ይሄ ምን ያጠግባል ፣ ደግሞ የማይጣፍጥ ዳቦ ነው ብሎ ተነስቶ ሄደ
#ሌላው ደግሞ ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ሄደ
#የቀሪው ግን እጅግ አመስግኖ እያለቀሰ ምግብ ከበላሁ 1 ቀኔ ነበር በማለት ሰጪውን ደጋግሞ አመሰገነ

እናም በዚህ ሁኔታ ሰጪው ላይ ምን አይነት አስተሳሰብ የሚጎለብት ይመስላችኀል? ተቀባዮቹስ ላይ?

ሰጪው በጣም የሚያስደስተው የሰጠው ጥቂት ዳቦ ሳይሆን ያመሰገነንውና እሱ በሰጠው ጥቂት ዳቦ ከርሀብ የወጣው ሰው ታሪክ ነው ፡፡ አማሮ ለሄደው ሰው ግን ለወደፊቱ ሞልቶ ቢተርፈውም ላይሰጠው ያስባል ስለ ሶስተኛው ሰው ግን እንዴት ምንም ሳይል ይሄዳል በሚል ብዙ ጥያቄዎችን ያወጣል ያወርዳል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ስንባል ምንም ነገር ስናደርግ ምላሽ እንጠብቃለን ፡፡

ስለዚህ ለመልካም ግንኙነት ስንል መልካም ነገር መናገር አማራጭ የሌለው ነገር ነው ፡፡ ካልተቻለ ግን መጥፎ ነገር ከመናገር ዝም እንበል ፡፡ መልካም ነገር የሚጀምረው ደግሞ ከቀላል ምስጋና ነው፡፡
 
Share
@psychoet
ብዙውን ጊዜ እጅግ በጣም የጎዱህ ነገሮች
🔽
🔽
🔽
ትሎቁን ትምህርት ያስተምሩሀል፡፡
@psychoet
ሰላም ቤተሰቦች ለአንድ ወር የሚቆየው የሕይወት ክህሎት ማዳበሪያ ስልጠናችን 4ኛ ዙር ተጠናቆ 5ኛ ዙር ምዝገባ ጀምረናል፡፡ ስልጠናው በቀጣዩ ሳምንት ሚያዝያ 9 እና 10 ይጀምራል፡፡

-ሳይኮሎጂን መረዳት
-የህይወትን አላማ ማግኘት
-የስሜት ብልህነት
-ውጤታማ እቅድ አወጣጥና ጊዜ አጠቃቀም
-ስልታዊ የሕይወት ችግር አፈታት ዘዴዎች
-ድብርትና ጭንቀትን ማሸነፍ እና ሌሎችም ስልጠናዎችን ያካተተ ነው።

በ#500 ብር ብቻ !

★ልምድ ባላቸው ሳይኮሎጂስቶችና የህይወት ክህሎት አሰልጣኞች ይምጡ ይሰልጥኑ።
★ሁሉንም ለተካፈለ በነፃ የግል የማማከር ጊዜ ፣ የንግግርና የተግባቦት ክህሎት ስልጠና ሰርተፊኬትን ጨምሮ ያገኛል።

ያሉን ፈረቃዎች
ቅዳሜ 3-5 | ቅዳሜ 8-10 | ቅዳሜ 10-12
እሑድ 3-5 | እሑድ 5-7

★ያለው ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድሞ ለተመዘገበ በፈለጉት ፈረቃ የመሰልጠን ቅድሚያ እንሰጣለን ፡፡

በአካል መመዝገብ ያልቻላችሁ በስራ ሰአት ( ሰኞ - አርብ 2-12) በስልክ በመደወልና መረጃዎችን በመላክ መመዝገብ ይቻላል ፡፡0912664084 ይደውሉ። በተጨማሪም ከሰኞ - አርብ ካሉት ቀናት ውስጥ በግል (VIP) ለብቻችሁ መሰልጠን የምትፈልጉም ደውላችሁ መረጃ መጠየቅ ትችላላችሁ ።

አድራሻ: 4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ( ከቶታል ጀርባ) - አራት ኪሎ ንግድ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 219

ስልጠናውን መካፈል ለሚፈልጉ ጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው @psychoet
#መልካም_ሚያዝያ_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ለወዳጅ ጓደኛችሁ #መልዕክቱን ያጋሩ

@Psychoet
አስተሳሰብንና ኑሮን የመለወጫ ትልቅ እድል!
የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን በያዝነው ሳምንት ሚያዝያ 9 እና 10 ይጀምራል፡፡

-ሳይኮሎጂን መረዳት
-የህይወትን አላማ ማግኘት
-የስሜት ብልህነት
-ውጤታማ እቅድ አወጣጥና ጊዜ አጠቃቀም
-ስልታዊ የሕይወት ችግር አፈታት ዘዴዎች
-ድብርትና ጭንቀትን ማሸነፍ እና ሌሎችም ስልጠናዎችን ያካተተ ነው።

★አሰልጣኝ ፦ ናሁሰናይ ፀዳሉ በተጨማሪም ሌሎች ተጋባዥ ባለሙያዎች
★ሁሉንም ለተካፈለ በነፃ የግል የማማከር ጊዜ ፣ የንግግርና የተግባቦት ክህሎት ስልጠና ሰርተፊኬትን ጨምሮ ያገኛል።

ያሉን ፈረቃዎች
ቅዳሜ 3-5 | ቅዳሜ 8-10 | እሑድ 4-6

★በአንድ ፈረቃ ጥቂት ሰዎች ብቻ ይሰለጥናሉ
በ#500 ብር ብቻ !

በሚመችዎት ፈረቃ አንዱን በመምረጥ በ0912664084 በመደወል ይመዝገቡ መረጃ ይጠይቁ። በተጨማሪም ከሰኞ - አርብ ካሉት ቀናት ውስጥ በግል (VIP) ለብቻችሁ መሰልጠን የምትፈልጉም ደውላችሁ መረጃ መጠየቅ ትችላላችሁ ።

አድራሻ: 4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ( ከቶታል ጀርባ) - አራት ኪሎ ንግድ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 219

ስልጠናውን መካፈል ለሚፈልጉ ጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው @psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «አስተሳሰብንና ኑሮን የመለወጫ ትልቅ እድል! የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን በያዝነው ሳምንት ሚያዝያ 9 እና 10 ይጀምራል፡፡ -ሳይኮሎጂን መረዳት -የህይወትን አላማ ማግኘት -የስሜት ብልህነት -ውጤታማ እቅድ አወጣጥና ጊዜ አጠቃቀም -ስልታዊ የሕይወት ችግር አፈታት ዘዴዎች -ድብርትና ጭንቀትን ማሸነፍ እና ሌሎችም ስልጠናዎችን ያካተተ ነው። ★አሰልጣኝ ፦ ናሁሰናይ ፀዳሉ በተጨማሪም ሌሎች ተጋባዥ ባለሙያዎች…»
ካገባሁ ኹለት አመት ሁኖኛል ፡፡ ሚስቴን በጣም እወዳታለሁ ግን አሁን ግራ ገብቶኛል ፡፡

ያለ አባት ያላሳደገችኝ እናቴ እጅጉን ደክማ ሞት አፋፍ ላይ ነች ፡፡ የኹል ጊዜ ጥያቄዋ የኔን ብቸኛው ልጇን ልጅ ወልዶ ማቀፍና ማየት ነው እና ኹል ጊዜ ባየችኝ ቁጥር እባክህ ወልደህ አሳቅፈኝ ትለኛለች ፡፡ እናቴ በዚህ ምድር ትልቅ ቦታ የምሰጣት ሰው ነች ፡፡ ካገባሁ ሰሞን የልጅ ልጇን ለመሳም ተስፋ ሰንቃ ነበር ግን ሁለት አመት አልፎ ምንም የተፈጠረ ነው ፡፡

ከሚስቴ ጋር ከመውለድ ርዕስ ውጪ በሰላም ነው የምንኖረው ፡፡ ግን ደግሞ ሌላ የምትወደኝ ልጅ አለች እና የእናቴን ጥያቄ ስለምታውቅ "ከእኔ ውለድ" እያለች ትጨቀጭቀኛለች፡፡ በዚህ በኩል ደግሞ ባለቤቴ በዚህ ጊዜ ልጅ አልወልድም፣ ኑሮ ተወዷል እያለች ታስጨንቀኛለች ፡፡ እናቴ ደግሞ እንደዚህ እየለመነችኝ ልጄን ሳታይ ብትሞት ለዘለአለም ነው የሚቆጨኝ ፡፡
እባካችሁ ግራ ገብቶኛል ሃሳባችሁን አጋሩኝ ? ሚስቴን ፈትቼ ከሌላ ልውለድ ወይስ የእናቴን ፀፀት ይዤ ልቀመጥ ?
T.me/psychoet
ለ5ኛ ዙር ስልጠና #1 ቀን ብቻ ቀርቷል
አሁኑኑ ባሉበት ሆነው በመደወል ይመዝገቡና ሕይወትዎን ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ያስተካክሉ

ያሉን ፈረቃዎች
1. ቅዳሜ 3-5
2. ቅዳሜ 8-10
3. እሑድ 4-6

የስልጠና አድራሻችን በመሀል አዲስ አበባ 4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ
0912664084
እኛ_እራሳችንን እና ሌሎች_እኛን ምን ያህል ያውቁናል?
The 4 selves within us

አንዳንድ ግዜ ሰዎች እኔ እራሴን በደንብ አውቀዋለሁ ወይም እከሌን በደንብ አውቀዋለሁ ሲሉ ይደመጣል ነገር ግን የስነ-ባህሪ አጥኝዎች ሰው ራሱንም እንዲሁም ሌሎችን ሙሉ በሙሉ እንደማያውቅ እንደሚከተለው ያስረዱናል።

4ቱ ማንነቶቻችን

📌📌 1.Open- ግልፅ ሆኖ የሚታየው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን እና ሌሎች እኛን የሚያውቁት ግልፅ የሆነው ማንነት ክፍል ነው።

📌📌 2. Hidden- ድብቅ የሆነው የማንነት ክፍል ሲሆን እኛ ራሳችን የምናውቅው ሌሎች ግን ስለእኛ የማያውቁት ክፍል ነው

📌📌 3. Blind- ሰዎች ስለኛ የሚያውቁት እኛ ግን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል እና

📌📌 4. Unknown- ሌሎች ሰዎችም ሆኑ እኛ ራሳችን ስለራሳችን የማናውቀው የማንነት ክፍል ነው።

ስለዚህ:

👉 ከሰዎች ጋር መልካም እና ሚዛናዊ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን ከላይ የተዘረዘሩትን የማንነት ክፍሎች ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

👉 ካልሆነ ግን እከሌን አውቀዋለሁ ብለው ሲያስቡ አንድ ቀን ድብቁ/ የማያውቁት ማንነት ሲገለጥ ሊጎዱ ይችላሉ። እንዲሁም ራስዎትን ራሴን በደንብ አውቀዋለሁ በማለት ሌሎች ከሚሰጥዎት ምክር ባለመማር ራስዎትን ከማሳደግ እና ከማሻሻል እንዳይገደቡ ጥንንቃቄ ያድርጉ።

📌 ለማንኛውም የሕፃናት የአእምሮ ህክምና 📌
For Child_Mental_Health_Care_Service
📱0946417368

መልእክቱ ለብዙዎች እንዲደርስ Share & Like አይርሱ።

👉 በመአዛ መንክር
ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

@Psychoet
መልካም ዜና!
የአንድ ወር ሕይወት ክህሎት ስልጠናችንን መሳተፍ ለምትፈልጉ !

አሁንም ጥቂት ቦታዎች ስለሚቀሩን ባሉበት ሆነው በመደወል ይመዝገቡና ሕይወትዎን ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ያስተካክሉ

ያሉን ፈረቃዎች
#ቅዳሜ 3-5 ወይም #እሑድ 4-6

የስልጠና አድራሻችን በመሀል አዲስ አበባ 4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ
0912664084

💎💎💎የስልጠናው ውጤት በሰልጣኞቻችን ያየነው የአኗኗር ለውጥ ነው ፡፡
@psychoet
ከኢትዮጵያ ውጭ ለምትኖሩ መልካም ዜና፡፡ ሜሎሪና መጽሐፍን ከሶደሬ.ኮም በቀጥታ ማግኘት ትችላላችሁ

https://soderestore.com/%E1%88%98%E1%8D%83%E1%88%85%E1%8D%8D%E1%89%B5-Books-c35241255
ተመስገን | አልሃምዱሊላህ
#መልካም_ግንቦት_ወር !
ለወዳጅ ጓደኛችሁ #መልዕክቱን ያጋሩ
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ የተሳካ ምርጫ ፣ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

@Psychoet
VERY IMPORTANT❗️❗️❗️

This msg is for everyone .
If u find any child crying on the road showing his/her address on a piece of paper and asking u 2 take him/her to that address, please if u're so sympathetic, take that child 2 the Police Station and don't take him/her to that address. It is a new way of gang Stealing, Raping & Kidnapping. Pls, forward 2 all Ur loved ones. One msg from u may save a life or property. Plz circulate. Let us b security conscious.

4wrded as received
@Psychoet
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው የዒድ-አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
#ኢድ_ሙባረክ
#Eid_Mubarak
2024/09/29 01:23:42
Back to Top
HTML Embed Code: