Telegram Web Link
አስተማሪ አጭር ታሪክ .!

አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡

ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ
እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ።

ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥ አሰራር ጥበብ ተካነ ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ ፡፡

ይሄኔ ባለሱቁ "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡ ብሎ ይልከዋል ፡፡ ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡

ወደ ሱቅ ይመለሳል ፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም ?አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው ፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡

ሜሎሪና የሳይኮሎጂ ልብወለድ መጽሐፍ ላይም መሰል ምክሮችና ስነልቦናዊ ሀሳቦችና በታሪክ ተዋዝቶ ታገኛላችሁ ፡፡ ሜሎሪና ስውር ጥበብ❤️❤️❤️
# ሼር ይደረግ 👇
©በትልቁ ማሰብ
❀꧁ @psychoet Channel꧂❀
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡
ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

_ሜሎሪና ገጽ 184 _

ሜሎሪና ❤️❤️❤️
ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ
ያነበቡት ኹሉ ወደውታል

ለቅዳሜና እሑድ መጽሐፍ ሸመታችሁ ፡፡ሜሎሪና መጽሐፋን በጃዕፈር እንዲሁም በሌሎች መደብሮች ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡ ያነበቡት ኹሉ በአስደናቂው የታሪክ ፍሰቱና ትስስሩ ወደውታል፡፡

መልካምና ደስ የሚል ቀን ይኹንላችሁ ፡፡😀 ራሳችሁን ከኮሮና ጠብቁ ፡፡
@Psychoet
በሕይወት ከመኖር ይልቅ መሞት ይቀላል፡፡ ለመኖር፣ መሥራትና መጣር፣ መውጣትና መውረድ ሲያስፈልግ፣ ለመሞት ግን ምንም ሳይሠሩ ቊጭ ማለት በቂ ነው፡፡ ምክንያቱም ከአፈር የተሠራው ሥጋ ለመኖር አፈር ይፈልጋልና፡፡ እኛ ሰዎች አሳባችን ከምንኖርበት ዓለም የሰፋና የጠለቀ ቢኾንም፣ እኛ ግን ይህንን ዘንግተን በተቈጠረው የሕይወት ዘመናችን ከሰፊው ራሳችን ይልቅ ወደ ጠባቡ ውጪ በመመልከት በሙሉ ማንነታችን ባዶነትን የምንላበስ፣ በክቡር ሥጋችን ውርደትን የምንከናነብ፣ በምክንያት በመጣንባት ምድር በዋዛ ኖረን በዋዛ የምናልፍ ነን፡፡
@Psychoet

❖_____________________________❖
ማንኛዉም ሰዉ ስለ IQ ማወቅ ያለበት ነጥቦች።

የአዕምሮ አቅም (Intelligence) ትርጓሜዎች ዘርፋቸዉ እጅጉን ብዙ ቢሆንም፣ ባጠቃላይ የማመዛዘናችን፣ የማቀድ፣ ችግሮችን የመፍታት፣ በፍጥነት የመማር፣ በራሳችን ማሰብ፣ ዉሳኔዎችን መወሰን እና በዚህ አለም ላይ ኑሮን ተቋቁመን እንድንኖር መቻላችን የአዕምሮአችን አቅም (Intelligence) እንለዋለን።

የ አዕምሮ አቅም መለኪያ (Intelligence Quotient, IQ) አልፍረድ ቢነት እና ቲዎዶር ሳይመን የተሰኙ ሁለት የስነልቦና ባለሙያዎች እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ የዘመን ቀመር በ 1905 በ ሀገረ ፈረንሳይ በትምህርት ገበታቸዉ ላይ ለሚቸገሩ ልጆች መመዘኛ እሳቤ አዘጋጁት። ይሄንን መለኪያ ያዘጋጁበትም ምክንያት ከተማሪዎቹ መካከል የትኞቹ የተለየ ክትትል እንደሚያስፈልጋቸዉ ለመለየት በማለም ነበር፤ ይህም መለኪያ የዛሬዉን IQ test ወለደዉ።

ከ 19 ኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ፣ ተመራማሪዎች የአዕምሯችን ንግግር የመረዳት (verbal reasoning) ፣ የተለያዩ ቅርጾችን መለያየት (visual-spatial skills) እና መረጃዎችን የማገናዘብ ፍጥነት(working memory) አጠቃላይ የ አንድን ሰዉ አዕምሮ አቅም መለካት እንደሚችል ንድፈ ሃሳብ አስቀምጠዉ ነበር።

ከእነርሱም መካከል ሳይመን እና ቢነት በየዘርፉ የተወሰኑ ጥያቄዎችን በማዘጋጀት እና ከዚያ ለጥያቄዎች በትክክል ምላሽ የተገኘዉን ዉጤት በአንድ ላይ በመደመር መለኪያዉን ጀመሩት። ጥያቄዎቹም በእድሜ ቡድን የታሰቡ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ልጅ የሚያመጣዉ ዉጤት ከሌሎች እኩዮቹ የሚነጻጸረዉ ያመጣዉን ዉጤት ለ እድሜዉ በማካፈል እና ከዚህም የተገኘዉን ዉጤት በ መቶ በማባዛት የሚገኘዉን ዉጤት የ IQ መለኪያ አድርገዉ ወሰዱት።

ዛሬ 100 ተብሎ የሚወሰደዉ የ IQ ዉጤት የሚያመለክተዉ አማካይ ዉጤት፣ 68 በመቶ የሚሆነዉ ሰዉ ያመጣዉ ዉጤት ከ 85 እስከ 115 ድረስ የሆነበትን ስሌት ነዉ። ሳይመን እና ቢነትም በመመዘኛዉ ጥያቄዎች የሚለኩት ክህሎቶች የ አጠቃላይ አዕምሮን አቅም (General Intelligence) ሊገልጽ እንደሚችል አስበዉ ነበር።

ነገር ግን ያኔም ሆነ አሁንም ድረስ ቢሆን ሁሉንም ተመራማሪዎችን የሚያስማማ የ አጠቃላይ አዕምሮ አቅምን የሚለካ ሙከራ ወይም ምዘና የለም። ይህም ደግሞ መመዘኛውን ሰዎች እንደፈቃዳቸዉ በራሳቸዉ የአዕምሮ አቅም አመለካከት መሰረት እንዲጠቀሙበት እድሉን ክፍት አድርጎታል የተለየ ክትትል የሚያስፈልጋቸዉን ልጆች ለመለየት አገልግሎት የታሰበዉ መለኪያ እጅጉን ለተሳሳተ ጉዳዮች ጥቅም ላይ በፍጥነት መዋል ጀመረ። ከዋነኞቹ የተሳሳቱ የ IQ መለኪያ ጥቅም ላይ ከዋለባቸዉ ሁኔታዎች መካከል አንዱ የነበረዉ በሀገረ አሜሪካ መጀመሪያዉ የአለም ጦርነት ሰዓት ወታደሮችን ለስልጠና ለመምረጥ በዚህ መለኪያ መጠቀማቸዉ ነበር። በዚያም ወቅት ብዙ ሰዎች በ ዩጄኒክስ ያምኑ ነበር (ዩጀኒክስ(Eugenics): ማለት እንዲበዛ የሚፈለግ እና የማይፈለግ የሰዉ ዘር ቁጥጥር ይደረግበት የሚል አስተሳሰብ ነዉ)።

ይሄ አስተሳሰብ ችግር ያለበት ከመሆኑም በላይ የአዕምሮ አቅም የማይቀየር መሆኑ ብቻ ሳይሆን በሰዉየዉ ዘር እንደሚወሰንም መታሰቡ ነበር። በዩጄኒክስ አስተሳሰብ ምክንያት ተመራማሪዎች ከወታደሮቹ ምልመላ የተገኘዉን ዉጤት መሰረት በማድረግ የተወሰኑት የሰዉ ዝርያዎች ከሌሎቹ ይልቅ በአዕምሮ አቅም የበላይ እንደሆኑ ተቀብለዉ ነበር። በጊዜዉ መመዘኛውን የወሰዱቱ አብዛኞቹ ወደ አሜሪካ በቅርብ ጊዜ በስደት የገቡ መሆናቸዉ እና በቂ የሆነ መደበኛ ትምህርት ያለገኙ እና የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ያላዳበሩ መሆናቸዉን ከግምት ባለማስገባት በሰዉ ዝሪያም መካከል በዘር የበላይነት እና የበታችነት በመከፋፈል አስቀመጡ።

የዩጄኒክስ አስተሳሰብ ከ IQ መለኪያ ጋር መጣመሩ ሳይንሱን ብቻ ሳይሆን ፖሊሲ ጭምር ላይ ጫናዉን አሳድሮ ነበር። እንደጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ1924 የቨርጂኒያ ግዛት የ IQ መጠናቸዉ ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች መዉለድ እንዳይችሉ መሃን እንዲሆኑ የሚያስገድድ ህግ በ አሜሪካዉ ፍርድ ቤት ድጋፍ ተላለፈ። በናዚ ጀርመን ደግሞ የ IQ መጠናቸዉ ትንሽ የሆኑ ህጻናት እንዲገደሉ መንግስት ወሰነ። ከሆሎኮስት እና ሰብዓዊ መብቶች እንቅስቃሴዎች በኋላ የ IQ መጠንን መሰረት ያደረገ መድልዎ በሞራልም ሆነ ሳይንሳዊ መሠረት ተቃዉሞ ገጠመዉ።
ተመራማሪዎችም አንድ ሰዉ የሚኖርበት አካባቢ በአዕምሮ አቅሙ (IQ) ላይ ያለዉን ተጽዕኖ ማጥናት ጀመሩ። ለምሳሌ የ IQ ምዘናዎች በ 20ኛዉ ክፍለ ዘመን በየጊዜዉ ይስተካከሉ ነበር። አዳዲስ ይመጡ የነበሩ ትዉልዶች በአሮጌዉ መለኪያ እጅግ የላቀ የ IQ ዉጤት ከቀዳሚዎቻቸዉ ይልቅ ያስመዘግቡ ነበር። ይህም ሁኔታ ፍልን ኢፌክት (Flynn Effect) በመባል ይታወቃል። ነገር ግን የሁኔታዉ በፍጥነት መከሰት ከዘረመል ዝግመታዊ ለዉጥ ይልቅ ከትምህርት መሻሻል፣የተሻለ ጤና እንክብካቤ እና የተሻለ አመጋገብ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ያመለክታል።

በመካከለኛዉ 20ኛ ክፍለ ዘመን የስነ ልቦና ባለሙያዎች የ IQ መለኪያን ከአዕምሮ አቅም መለኪያነት ለሌላም ጥቅም ሲያዉሉ ተስተውለዋል፤ ለከባድ አዕምሮ ህመም ወይም እስኪዞፍሬኒያ፣ ድባቴ እና ለሌሎች የአዕምሮ ህመሞች ምርመራ ተጠቅመዉበታል። ይሄም የምርመራ ሂደት በመርማሪዎቹ ህክምና ዉሳኔ ላይ በከፊሉም ቢሆን የተደገፈ እና የተወሰኑ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ያካተተም የነበረ ቢሆንም ከዚያ በኋላ የተደረጉ ጥናቶች ጠቃሚ የሆነ መረጃ እንደማይገኝበት አሳይተዋል።
የዛሬዎቹም የ IQ መለኪያዎች በብዛት እንደ መጀመሪያዎቹ አይነት አወቃቀር እና የጥያቄ አይነት ቢኖራቸዉም፣ አሁን ላይ በመለኪያዉ ላይ ሊከሰት የሚችለዉን ስህተት ለመለየት የሚያስችሉ ቴክኒኮች አሉን ተብሎ ይታመናል። አሁን ላይ ማንኛዉም የአዕምሮ ህመሞችን ለመመርመርም ጥቅም አይዉሉም። ነገር ግን በብዙ የሙያዉ ኤክስፐርቶች ተቃዉሞ ቢኖረዉም ተቀራራቢ የሆኑ መለኪያዎች የየዘርፉን ዉጤት በመጠቀም የመማር ያለመቻልን ጉድለት ለመለየት ዛሬም ቢሆን አገልግሎት ላይ ሲዉሉ ይታያሉ።

በአለማችን አብዛኞቹ የስነ ልቦና ባለሙያዎችም ይሄንን መለኪያ መሠረት በማድረግ የአዕምሮ አቅም ውስንነትን ለመለየት እና ዉጤቱን በመጠቀም ልዩ የትምህርት ክትትል፣ ስልጠና እና ኑሮ ድጋፍ ለማድረግ ይገለገሉበታል
የ IQ መለኪያ በሳይንሱ መሰረት የሌላቸዉን አስተሳሰቦች እና አሰቃቂ ፖሊሲዎች ማስፈጸሚያ ጥቅም ላይም ቢዉልም፣ መለኪያዉ ምንም ጥቅም የለዉም ማለት ግን አይደለም። ሊመዝን የታሰበለትን የአዕምሯችን ንግግር የመረዳት (verbal reasoning)፣ የተለያዩ ቅርጾችን መለያየት (visual-spatial skills)፣ መረጃዎችን የማገናዘብ ፍጥነት (working memory) መመዘን ይችላል። ነገር ግን ይህ ማለት የአንድን ሰዉ ፍጹም አዕምሮአዊ አቅም መለካት ያስችላል ማለት አይደለም። የተወሳሰቡ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሳይንሳዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች ከ IQ መለኪያ ጋር የሚነሱ ቢሆንም፤ እየጨመሩ የሚመጡ የተመራማሪዎች አካል ግን ሰዎችን በአንድ መለኪያ ቁጥር ዉጤት ብቻ መከፋፈልን አይቀበሉም።

ከአንድ እናት ተወልደው አንድ ቤት እየኖሩ የተለያየ ብቃት ያላቸውን ሰዎች በምናይበት ዘመን ላይ እንዲህ አይነት ሙከራዎችን ሀገርን ለመፈረጅ ጥቅም ላይ መዋሉ ትልቅ ችግር ያለበት እንደሆነ አምናለሁ።
ችግሩን ለማሳየት መጠየቅ ካለባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ውስጥ፡
1.ማነው የወከለን?
2. ባህል ከግንዛቤ ውስጥ ገብቷል?
3. የኑሮ ደረጃቸዉ?
4. የመመዘኛዉስ ቋንቋ፤ እነዚህ እና የመሳሰሉ ጉዳዮች በዉጤቱ ላይ የሚያደርሱት ተጽዕኖ በምን ያህል ተስተካከለ የሚሉት ጉዳዮች ዉጤቱን ጥያቄ ዉስጥ ያስገቡታል።

በኔ በኩል የ IQ መመዘኛ የእንድን ሰዉ የአዕምሮ አቅም በትክክል የሚለካ፣ የማይቀያየር እና የዚያን ሰዉ መጨረሻ ወሳኝ ነዉ ብዬ አላምንም። ይልቁንም ማንኛዉም ረሃብ ያልቀጣዉ፣ ፍቅር የጠገበ፣ ጤነኛ አዕምሮ ያለዉ፣ ተገቢ መረጃ እና ጥበብ በሚነፍስበት አከባቢ በቂ ጊዜ ያሳለፈ የትኛዉም አዕምሮ የሰዉ ልጅ የደረሰበት የልቀት መጠን ሊደርስ ይችላል ብዬ አምናለሁ።
“አማካይ የአዕምሮ አቅም የሚባል ነገር የለም… ጤነኛ አዕምሮ ካለህ የበላይ ነህ!” የሚለዉን የጥቁር አሜሪካዊዉን፣ በህጻንነቱ እጅጉን ሰነፍ በመባል ይሰደብ የነበረዉ፣ ነገር ግን በዓለማችን የመጀመሪያዉ ከባዱን የ ህጻናት አንጎል ቀዶ ህክምና ያደረገዉ፣ በ አራት የተለያዩ የህክምና ዘርፎች ፕሮፌሰር የሆነዉ፣ የ Gifted Hands መጽሃፍ እና ፊልም ባለታሪክ እና ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ምርጫ ውድድር ጀምሮ የነበረዉ ዶክተር ቤን ካርሰንን ሃሳብ እጅጉን የሚያሳምን ሆኖ አገኘሁ።

እንዲህ አይነቱ ፍረጃ ህዝባችን ማሰብ አልችልም ችግር አለብኝ ብሎ እንዲያምን ፣ ታዳጊዎችም አለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን እንዳይችሉና የዝቅተኝነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል። ይሄንን ወሬ ያናፈሱት ጋዜጠኖቻችንም ማስክ የለበሰዉን አፋቸዉን ከማንቀሳቀሳቸዉ በፊት ክፍት በሆነዉ አይናቸዉ ተጠቅሞ ስለጉዳዩ በቂ መረጃ መመርመር ተገቢ ነዉ ብዬ አምናለሁ።
ጥያቄዎች: ሃሳብዎን በ comment ላይ ያካፍሉን።
1. ከዚህ በፊት የ IQ ምዘና ወስደዉ ያዉቃሉ?
2. የአዕምሮን አቅም በትክክል ይለካል ብለዉ ያምናሉ?
አመሰግናለሁ።
ዶ/ር ተመስገን እንዳለዉ
በቅዱስ ጳዉሎስ ሚ/ህ/ኮሌጅ መምህር፣ የ Hakim Consultancy ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር እና ኮንሰልታንት SMM
FM 107.8 ላይ በቀጥታ ስለ ውይይት ስለለኝ እንድታደምጡ እጋብዛለሁ ፡፡

እሑድ 12:00 - 12:30
ጥሩ የመወያያ መድረክ በዶ/ር ኤልያስ ገብሩ ተከፍቷል፤

https://www.tg-me.com/joinchat-GDFVjxqBS4ex2iY4jIPoCA

ገብታችሁ ቤተሰብ በመሆን ጥሩ ጥሩ ሀሳብ እርስ በእርስ እንድትጋሩ እጠይቃለሁ ፡፡

በተጨማሪም ወደዚህ "የኔ ትውልድ አብርሆት" የቴሌግራም ግሩፕ ብዙ ሰዎችን add ማድረግ፤
ለማወዳደር ግሩፑ ላይ ያለውን invite ሊንክ ሼር በማድረግ አልያም ከታች ያለውን ሊንክ ተጭኖ ለጓደኞች በመላክ የካርዱ ተሸላሚ መሆን ይቻላል።

1ኛ ለወጣ 300 ብር
2ኛ ለወጣ 150 ብር
3ኛ ለወጣ 50 ብር

መልካም እድል፤

@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#አራቱ የሰው ባህሪ አይነቶች
www.tg-me.com/psychoet

በዛሬው ርዕስ ለሰው ልጆች ተግባቦትና የቀን ተቀን መስተጋብር ወሳኝ ስለሆነው አመል ( Temperament) እንመለከታለን፡፡ እንደሚታወቀው ማንኛውም ባህሪ መነሻ ምክኒያት አለው ፡፡ ምክንያቶቹ ደግሞ #ተፈጥሮአዊ ወይም #አካባቢያዊ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡

1. ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ :- ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ ስንል በዘር ከወላጆቻችን የምንወርሰው ሲሆን

ለምሳሌ ፦ አንድ ልጅ እናቱ ወይም አባቱ ያላቸውን ባህሪ ሲወርስ

2. አካባቢያዊ :- ከቤተሰብ ጋር ባለ ግንኙነት ፣ በጓደኛ ተፅዕኖ ፣ በትምህርት ቤት ቆይታና በምንኖርበት ባህል የምንወርሳቸውን ባህሪያቶች ያጠቃልላል

ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው በጣም ተሳዳቢ ቢሆን ( ያን ስድብ የወረሰው በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አልያም ከሰዎች በተለያዩ መንገድ ከተመለከታውና ከሰማው ሊሆን ይችላል )


የስነልቦና ተመራማሪዎች የሰውን ተፈጥሮአዊ አመል (Temperament ባህሪ) በአራት በመክፈል ያስቀምጡታል

1 .📌ሳንጊዊን (Sanguine)
ሳቂታና ተጫዎች ...
#ተግባቢና ምክኒያታዊ ናቸው

2.📌ኮለሪክ (Choleric)
ተነጫናጭ/ አዛኝና አኩሪፊ ...
#ተግባቢና ስሜታዊ ናቸው

3 .📌ሜላንኮሊክ (Melancholic)
አይናፋር ...
#ጭምቶችና ስሜታዊ ናቸው

4. 📌ፊላግማቲክ (Phlegmatic)
ግትር...
#ጭምተኛና ምክኒያታዊ ናቸው

እነዚህ አራት የሰው አመሎች የየራሳቸው መገቸጫ አላቸው

📌ሳንጊዊን
❇️አየር ⭕️ማሕበራዊ ሰዎች

ሳንጊዊን አመል ያላቸው ዋናው መገለጫቸው አብዝቶ ተጫዎችና ወሬኛነት ፣ ነገሮችን ለመስራት ፈጣንነት ፣ ማሕበራዊነት ይገኙበታል ፡፡ ሳንጊዊኖች በጣም ተግባቢና የሕብረት ነገር የሚወዱ ናቸው፡፡ ይህ አመል ያላቸው ሰዎች ሁልጊዜም ለራሳቸው ሳይሆኑና ምንም ሳይሰሩ ኑሮአቸውን የግል ሳይሆኖ የጋራ ያረጋሉ፡፡

📌ኮለሪክ
❇️ እሳት ⭕️አስተዳዳሪዎች
ኮለሪኮች በጣም ተግባቢ ሲሆኑ የሚገለፁበት ባህሪ በውሳኔ ሰጭነታቸው ፣ በግብ ተኮርነታቸው ፣ በምኞታቸው ፣ በኢጥገኛነታቸው ነው፡፡ በተጨማሪም ኮለሪኮች ቁጡዎች ቂም የሚይዙ ለስሜት ቅርቦች ናቸው፡፡

📌ሜላንኮሊክ
❇️መሬት ⭕️ሰዎችን ከሕይወታቸው አግላይ

ሜላንኮሊክ ሰዎች አስተዋያዮችና ዝርዝር ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጪዎች ደግሞም ጥልቅ አሳቢዎችና ጭምቶች ናቸው ፡፡ ከዛ በተጨማሪ ራሳቸውን ብዙ ሰዉ ካለበት ቦታ ማግለል / ማሸሽ የሚመርጡ ናቸው ፡፡ እነዚህ አይነት ሰዎች ሁሌም ፍፁም ለመሆን የሚሞክሩና የሚፈልጉ ናቸው፡፡ይህ ባህሪ ሰዎችን ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ የሚገፋፋ ፣ ቁጥብ እንዲሆኑ የሚያረግ ነው ፡፡

📌ፊላግማቲክ
❇️ውሀ ⭕️ሰዎችን ከወደሕይወታቸው አቅራቢ

ፊላግማቲክ ሰዎች ረጋ፣ ፈታ ያሉና ከሁሉ ጋር እንደውሀ የሚራመዱ ናቸው ፡፡ ለሌሎች በጣም የሚያዝኑ ግን የራሳቸውን ስሜት በማፈን የማይገልፁ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሰዎች  የተለያዩ ሀሳቦችን እና ችግሮችን ወደአንድ በማምጣት ለመፍታት የሚሞክሩ ናቸው ፡፡


አንዳንድ ሰዎች ከነዚህ ባህሪያት ሁለቱን ወይንም ከዛ በላይ ሊያሳዩ ይችላሉ ፡፡ በቅርብም የተጠኑ ጥናቶች ከ4ቱ አመሎች ላይ አንድ ጨምረው 5 አድርሰውታል ፡፡ አምስተኛው ደግሞ የሁሉም ቅልቅል ያለበት ከሁሉም መሀል የሆነ ሲሆን (SUPINE )ብለው ጠርተውታል፡፡

የናንተ ባህሪ ከየትኛው ይመደባል ? በ #Comment አሳውቁኝ ?

❖__________________________________❖

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
የማስታወስ አቅምን መጨመር! /Memory /
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

ብዙ ጊዜ ሁላችን በተለያዩ የሕይወት መስተጋብሮች "የመርሳት" ገጠመኝ አለን ፡፡ነገሮችን ማስታወስ አለመቻል በዙሪያችን ባሉ ሰዎች መካከል እንደግዴለሽ የመታየት ፣ በስራችን አመኔታ ማሳጣት ፣ በትምህርታችን ደግሞ ያጠናነውን ያለማስታወስ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ በእርግጥ ነገሮችን መርሳት ሲበዛ እንደ ህመም ይታያል ፡፡ ለዚህም ነው በተለምዶ "የመርሳት ህመም " የሚባለዉ ፡፡ ነገሮችን አለማስታወስ ብዙ ማህበራዊ ጉዳት ካስከተለ ታዲያ እንዳንረሳ ምን እናርግ የሚለው ትልቅ ሙያዊ መልስ ያሻዋል፡፡
______________________________

ማስታወስ / ትዝታ በብዙ መንገዶች መጨመር እንችላለን በዋነኛነት የሚመጡት ግን እነዚህ ናቸው ፡፡ መፍትሔዎች ፦

Pay attention (ለነገሮች ትኩረት መስጠት ) : ከዚህ ክፍል 4 እና 5 እንዳስተማርኩት አንድ መረጃ ወደ አዕምሮአችን ገብቶ ለረጅም ጊዜ የሚቀመጠው በስነስርአቱ መረጃው ሲገባ ነው ስለዚህ ነገሮችን ለማስታወስ መጀመሪያውንም ወደ ውስጥ ስናስገባው በጥንቃቄና በአትኩሮት መሆን አለበት ፡፡ በብዛት የሚረሱ ሰዎች መጀመሪያውኑም ለፈተና ከላይ የሚያጠኑ ፣ የምንላቸውን ከላይ ከላይ / በግዴለሽነት የሚሰሙ ናቸው ፡፡

Add meaning ፦የምንሰማውን ፣ የምናየውን ነገሮች እንዳንረሳ ከዚህ ቀድም ከምናውቃቸው ጋር ማቆራኘትና ከመሸምደድ ይልቅ ትርጉሙን መረዳት ፡፡

Take your time ፦ በአንድ ጊዜ ነገሮችን ለመያዝ / ለማገባት ከመሞከር ጊዜ ወስደን እያረፍን ወደ አዕምሮአችን እናስገባ ፡፡

over learn፦ አንድን ነገር እንደምናውቀው ብናውቅም ደጋግሞ ማንበብ ፣ መስማት ፣ ማየት ለብዙ ጊዜ እንዳንረሳው ይረዳል ፡፡

Monitor your learning ፦ ያወቅነውን እንዳንረሳ ደጋግሞ በቃል ማለት በጥያቄ መፈተሽ ፡፡ በተለይሞ ተማሪ የሆናችሁ አንድን ነገር ስላነበባችሁ ብቻ በቂ አይደለም ይልቁንስ ያነበባችሁትን ወረቀት ዘግቶ ማሰብ እንዲሁም እውቀታችንን / ትውስታችንን በተለያዩ መንገዶች መመዘን ፡፡ አርቲስቶችን ብንመለከት (በቲያትር / ሙዚቃ ሙያ ያሉ ሰዎች) አንድን ገፀ ባህሪ አንብበው ያወቁ ቢመስላቸውም ከመድረክ በፊት ግን ብዙ ጊዜ ደጋግመው ይሉታል ይለማመዱታል ፡፡ ይህን የሚያረጉት የሚናገሩት ከራሳቸው ጋር እንዲዋሀድ እና እንዳይረሱት ነው፡፡

_______________________________
እንዲሁም መርሳትን ለመቀነስ ባለፈው ትምህርት እንደተመለከትነው በተጨማሪ *
★የግል ምክር ነገሮችን እየረሳችሁ ላላችሁ !

በጣም ብዙ ሰዎች ሳማክር አንዱ የሚነግሩኝ ችግራቸው የመርሳት ጉዳይ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የመርሳት (የአለማስታወስ) ችግር ቢኖርም በወጣቶች/ታዳጊዎች ላይም በተለያዩ ምክንያቶች መርሳት ያጋጥማል፡፡

ስለዚህ በመርሳት ለተቸገራችሁ ምክሬ እነሆ ፡- ነገሮችን መርሳት መጀመራችሁን ስትረዱ / የቅርብ ሰው ሲነግራችሁ መጀመሪያ ተረጋግታችሁ ለራሳችሁ ግዜ በመውሰድ እነዚህን አርጉ

1. በወቅቱ በብዙ ስራ / ተግባር ተወጥራችሁ ከሆነ ሀሳባችሁን በመሰብሰብ የምትሰሩትን ስራ ለመቀነስ ሞክሩ ከቻላችሁም ዋና መስራት ካለባችሁ 1/2 ስራ በስተቀር ሌሎቹን ተዋቸው ምክንያቱም መርሳት አንዱ ምክንያት በብዙ ስራ / ሃሳብ መወጠር ነው፡፡

2. ለጊዜው ለውጥ እስክታሳዩ ድረስ መስራት/ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች በሙሉ አንድ በአንድ ወረቀት ላይ በመጻፍ ተከታተሉ ፡፡በሀገራችን "በቃል ያለ ይረሳል በፅሁፍ ያለ ይወረሳል" የሚባለውን እንደምሳሌ እንኳን ብንወስድ እንኳን ተማሪዎች የሆናችሁ ክፍል ውስጥ የምትማሩት አልቆ ስትወጡ የምታስታውሱት 50% ነው ከአንድ ቀን በኀላ ደግሞ ወደ 10% ይወርዳል ፡፡ይህም ማለት የምንማረውን ሳይቀር በአንድ ቀን 90% እንረሳለን ማለት ነው ስለዚህ ነገሮችን መጻፍ ለማስታወስ ዋነኛ መሳሪያ ነው ፡፡

3. በአንድ ጊዜ አንድ ብቻ ስራ ስሩ ይህም ማስተዋላችሁን (Concentration ) ስለሚጨምር የመርሳት ችግር ይቀንሳል ፡፡

4. (Quantity) በአንዴ ጥቂት ነገር ብቻ ይማሩ / ያጥኑ ፡ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለተከታታይ 5 ሰአት ከሚያጠና ሰው ይልቅ በቂ እረፍት በየመሀሉ እየወሰደ 3 ሰአት የሚያጠና ሰው የበለጠ የማስታወስ / ያለመርሳት አቅሙ ይጨምራል ፡፡

5. ለብቻችሁ በየቀኑ በቂ እረፍት ውሰዱ ፦ ይህ እረፍት ወደ አዕምሮአችን የሚገባውን መረጃ ፍሰት ለጊዜው ስለሚቀንሰው አዕምሮአችን እንዳይጨናነቅ ይረዳል፡፡

ሌላውና ዋነኛው ነገር #በጣም እየረሳችሁ ከተቸገራችሁ ከአዕምሮ ጤና ጋር ሊገናኝ ስለሚችል ወደ ህክምና ጣቢያ እንድትሄዱ እመክራለሁ ምክንያቱም የዚህ አይነች ችግር የሚታከመው በመድኃኒትም ጭምር ነው ፡፡

፠፠______________________________፠፠
ቴሌግራም ቻናሌ www.tg-me.com/psychoet

ምንጭ ፦ ካለኝ ዕውቀት ማለትም ከዚህ በፊት ከሰማኀቸው ፣ ከተማርኩት እንዲሁም ከማሰለጥነው ስልጠና ለአንባቢ እንዲቀል አድርጌ በዐማረኛ የጻፍኩት ነው ።

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

መልካም ቀን
#ተስፋ_መቁረጥ_ከየት_ይመጣል ?

በጣም ጠቃሚ ስለሆነ #ሼር አድርጉት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ሁነው ተስፋ የለኝም ፣ ተስፋዬ ተሟጧል ፣ የመሳሰሉትን ቃላት በቀን ተቀን ሕይወታቸው ይጠቀማሉ ፡፡

ተስፋ መቁረጥ ወደ ግባችን / ፍላጎቶቻችን እንዳንደርስ የሚያረገን ባህሪ ነው ፡፡ በሕይወቱ ብዙ ጊዜ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ወደግቡ/እቅዱ የመድረሱ እድል በጣም አነስተኛ ነው ፡፡ ወደ ጠቃሚ የሕይወት ግባችን አለመድረስ ደግሞ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት ፣ የበደለኝነት ስሜት ያመጣብናል ፡፡

ሳይኮሎጂ ችግር የመፍቻ ዋና መንገዱ የችግሩን ምክንያት መረዳት እንደሆነ ያትታል ፡፡ስለሆነም የተስፋ መቁረጥ ዋና ዋና ምክንያቶች እንመለከታለን፡፡
_______________________
1.Environmental Factor (አካባቢያዊ ምክንያት)

በአካባቢያችን ያሉ የተለያዩ ሁኔታዎችና ገጠመኞች ፍላጎቶቻችንንና እቅዳችንን እንዳናሳካ ይከለክሉናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ማድረግ የምንፈልገውን ነገሮች " አትችለውም ፣ ይከብድሀል ፣ ከዚህ በፊት አልተሞከረም ፣ ሰው ምን ይልሀል" በማለት ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ያደግንበት ባህል ፣ የምንኖርበት አካባቢ ለማድረግ ያቀድነውን ነገር እንዳናሳካ በራሱ ሊይዘን ይችላል ፡፡ ይሄ በሕይወታችን ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል ፡፡

2.Personal inadequency Factor (ግላዊ ብቃት/ክህሎት ማጠር )

ይህ ደግሞ ፍላጎቶቻችንን እንዳናደርግ የሚገድበን አለመሙላት (ብቃት አልባነት) ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድን እቃ በጣም ወደነው ለመግዛት ስንፈልግ ከተወደደብንና ያለን ገንዘብ አነስተኛ ከሆነ ተስፋ ቆርጠን ላንገዛ እንችላለን ፡፡ እዚህ ጋር ነገሩን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አለመኖር የራሳችን የሆነ ጉድለት ይሆናል፡፡ ሌላው አንድን ነገር ለመስራት አስበን የግል ችሎታ / ብቃት/ ክህሎት ሲያንሰን እሱ " በቃ አልችልም " በማለት ተስፋ ለመቁረጥ መንስኤ ይሆነናል ፡፡

3. Conflict of interest ( የፍላጎት ግጭት )
የመጨረሻው የግላዊ ፍላጎቶች/ ግቦች እርስ በእርስ ሲፃረሩ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችላል ፡፡ ተስፋ መቁረጡ የሚመጣዎ ሁለቱንም ግቦቻችንን ልናሳካ ባለመቻላችን ነው ፡፡ አንዱን ግብ ብናሳካ ራሱ ሌላውን ስላላሳካን የመወላወል ተስፋ የመቁረጥ ( የማዘን ) ስሜት ይሰማናል፡፡

ከነዚህ ሶስቱ ዎና ዎና ምክንያቶች እግጅ በጣም ብዙ ሰው የሚያጋጥመው የመጨረሻው (.Conflict of Motives / የፍላጎት ግጭት ) እንደሆነ ሳይኮሎጂ ይጠቁማል፡፡
______________________________
እነዚህ Conflict of motives ( የፍላጎት ግጭት ) ደግሞ በ አራት ይከፈላሉ ፡፡
______________________________
ሀ. Approach - Approach Conflict
(ፍላጎት ፥ ፍላጎት ግጭት)

ይህ ግጭት ሁለት ነገሮችን በእኩል ፈልገን ነገር ግን መምረጥ የምንችለው አንዱን ብቻ ሲሆን ማለት ነው ፡፡ ለምሳሌ :- ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኅላ Department ሲመርጡ ብዙ ተማሪዎች በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ የdepartment ምርጫዎች ይወጠራሉ ነገር ግን መምረጥ የሚችሉት የወደዱትን ሁሉ ሳይሆን አንዱን ብቻ ስለሚሆን ግጭት ውስጥ ይገባሉ ፡፡ ሌላው ገበያ ሂደን ሁለት ሱሪዎች በጣም ወደናቸው ነገር ግን መግዛት የምንችለው አንዱን ብቻ ከሆነ ይህ አይነት ግጭት ከራሳችን ጋር ይገጥመናል፡፡

ለ. Avoidance - Avoidance Conflict (የማስወገድ ፥ የማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ ከሁለት የማንፈልጋቸው ነገሮች የግድ አንዱን መምረጥ ግድ ሲለን ነው ፡፡
ለምሳሌ ፦ ልጃችን በሰዎች ታግቶ ብር ካልከፈላችሁ ይገደላል ቢሉን ፤ እዚህ ጋር ልጁ እንዲሞትም አንፈልግም ለአጋቾቹ ብር መክፈልም አንፈልግም ፡፡ ግን አንዱን መምረጥ ግድ ይለናል ፡፡ ሌላ ምሳሌ ፦

ሐ. Approach - Avoidance Conflict (የፍላጎትና ማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ በአንድ ግብ ላይ የፍላጎትም የማስወገድም ስሜት ሲሰማን ነው ፡፡

መ. Multiple Approach - Avoidance Conflict (ብዙ የፍላጎት ማስወገድ ግጭት)

ይህ ሁላችንም በሕይወት ቆይታችን የሚያጋጥመን የለት ተለት ግጭት ነው ፡፡ እያንዳንዱ የሚገጥመን ነገር #ብዙ_አወንታዊና_አሉታዊ ነገሮች ይይዝና እሱን #መምረጥና #አለመምረጥ ችግር ይሆናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው መልኩን ፣ ገቢውን ወደን ፀባዩ አመለካከቱ ካላማረን ይሆነኛል አይሆነኝም ብለን ከራሳችን እንጋጫለን ፡፡ሌላው አንድን ስራ ስንሰራ በዉስጡ ያሉ የተለያዩ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ስገፉን ሲስቡን እንደዚህ አይነት ግጭት ውስጥ እንገባለን ፡፡


ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው
Melorina.bin
8.6 MB
ከሜሎሪና መጽሐፍ የተቀነጨበ ንባብ

በአጭር ጊዜ በአንባቢያን የተወደደው የታሪክና የሳይኮሎጂ መጽሐፍ "ሜሎሪና- ስውር ጥበብ " ንባብ

"ሜሎሪና" መጽሐፍ በሑሉም መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል ፡፡

ደራሲ ናሁሰናይ ፀዳሉ
አንባቢ ዘላለም ሸምሱ
@psychoet
ራስን በመቆጣጠር ድብርትን መከላከልና መጋፈጥ
ይህን ጠቃሚ መልዕክት #Share እናድርግ

የራስ ቁጥጥርና (self-regulation) የድብርት ስሜት ተዛማጅና ግንኙነት ያላቸው የስነ-ልቡና ክስተቶች ናቸው፡፡ ራስን መቆጣጠር ማለት አንድን ነገር ከግብ ለማድረስ ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብንና ጠባይን መግራት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራስን መቆጣጠር ከግብ ወይም አላማችን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ለምሳሌ ግባችን መማር፤ጥሩ ስራ መያዝ፤ የፍቅር ጓደኛ መያዝ፤ትዳር መመስረትና ልጆች ማፍራትና የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል፡፡ እናም አላማችን ከትናንሽ የዕለተለት ግቦች እስከ ላቅ ያሉ ለህይወታችን ከፍተኛ ትርጉም ያላቸው ግቦች ድረስ ሊሆን ይችላል፡፡

ራስን መቆጣጠርና የድብርት ስሜትን ምን አገናኛቸው?

ራስን መቆጣጠር ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብና፣ጠባይንና ከአላማነችን አንጻር መግራት ነው በሚለው ከተስማማን፤ የግባችን የስኬት መጠን ከድርጊታችን በኋላ ለሚሰማን ሰሜት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ያሰብነውና ያቀድነው ነገር በተሰካ ጊዜ ደስታ፣እርካታ፣ተሰፋና ለነገ የተነሳሽነት ስሜት ይፈጥርልናል፡፡ ያሰብነውና ያለምነው ነገር ሳይሳካ ሲቀር በተቃራኒው የድብርተና ተዛማጅ አሉታዊ ስሜቶች ሊፈራረቁ ይችላሉ፡፡ በዚህም ምክኒያት ራስን መቆታጠርና ድብርት የጠለቀ ግንኙነት አላቸው፡፡

የድብርት ስሜት ለራስ ቁጥጥር ያለው እንድምታ

ምንም እንኳን የድበርት ስሜት ምችት የማይሰጥ ቢሆንም ሳይንሳዊ መላምቶችና ምርምሮች እንደሚያመላክቱት ከሆነ እራሳችን ለመቆጣጠር የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ለምሳሌ ለፍቅረኛችን ታማኝ መሆን ሲገባን በስህተት ተማኝነታችንን ብናጎድል ከፈጸምነው በኋላ የድብርት ስሜት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ነገ ተደጋጋሚ ስህተት ላለመፈጸም ለእራሳችን ግበረ-መልስ (feedback loop) ነው:: ስለዚህ አላማችን ያማረ የፍቅር ህይወት መመስረት ከሆነ ለዚህ አላማችን መሳካት የእራሳችንን ጠባይ እንድንቆጣጠር የድብርት ስሜቱ አስተዋጽኦ ያበረክታል ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ሁሌም ታማኝነታችንን እያጎደልን ከፈጸምነው በኋላ ፌሽታና ደስታ የሚሰማን ከሆነ በዛው እምነት አጉዳይነታችን የመቀጠላችን እድል የሰፋ ነው፡፡ በተመሳሳይም በትምህርታችን ጥሩ ውጤት የማስመዝገብ አላማ ቢኖረንና ጊዜያችንን በአግባቡ ሳንጠቀም የፈለግነው ውጤት ባይመጣ አሁንም የድበርት ስሜት ሊከስት ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ለእራሳችን ጠባይ ከሰነቅነው አላማ አንጻር ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ አእምሯችን እራሱን የሚገመግምበት ግብረ-መልስ ሲሆን፤ ለወደፊት ይህ እንዳይከሰት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ በአጭሩ በዚህ የአረዳድ ድባብ መሰረት የድብርት ስሜት መፈጸም በምንፈለግገውና በፈጸምነው መካከል ልዩነት ሲፈጠር የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡

ተደጋጋሚ ውድቀትና ድብርት

በተደጋጋሚ ያሰብነውና ያቀድነው ነግር በማይሳካ ጊዜ የድብርት ስሜቱም እየጠነከረ በተደጋጋሚ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት፣መንስኤና ውጤት አትኩሮት ሰጥተን እንድናሰላስል በር ይከፍታል፡፡ ይህም ክስተት rumination በመባል ይታወቀል፡፡ ይህ አጥብቆ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት ማንሰላሰል ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ አብዛኞቹ በዚህ ዙሪያ የሚያጠኑ የስነ ልቡና ጠበብቶች አጥብቆ ከልክ በላይ ማሰቡ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አጽኖት ሰጥተው ይናገራሉ፡፡

ስለዚህ ከድብርት እራሳችን ለመካከልና ለመቋቋም ምን እናደርግ?

❖ተግባራዊ ግብ

በተደጋጋሚ ነገሮች ሳይሳኩ ሲቀሩ የድበርት ስሜት የሚከሰት ከሆነ፣ በተደጋጋሚ ላለመውደቅ ሊተገበር የሚችል ግብ ማውጣት፡፡ የነገሮች አለመሳክት ሁልጊዜ የችሎታ ማነስ፣እድለቢስነትና የሌሎች ተዛማጅ ነገሮች እጥረት ሳይሆን፤ በህይወታችን የምንሰነቃቸው ግቦች ሊተገበሩ የማይችሉና የራስ ቁጥጥራችን ደካማ ስለሆነ ሊሆን ይችላል፡፡

❖ግባችን ለመምታት አስፈላጊ ግብዓቶቸን ማፈላለግ

ተግባራዊ እቅዶችን ከነደፍን በኋላ ወደዚያ ጎዳና ለመድረስ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ከእራሳችንንና ከአካባቢያችን ማፈላለግ፡፡ ተሰጥኦቻችንን ማበልጸግ፤ ድክመታችንን ማሻሻልና የሚጎድለንን መሙላት፡፡

❖ጽናት

ተግባራዊ ግቦችን ካስቀምጥንና ወደ አላማችን የሚያደርሱንን ግብዓቶችንን ካመቻቸንን፤ ቀጣዩ የአላማ ጽናት (persistence) ነው፡፡ ሁሌም አዲስ ነገር ሲጀመር በወረትና በመነሳሳት መንፈስ ማደርግ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ድርግጊቱ መሃል ሲገባና ጫና ሲበዛ መፍረክረክ ግባችንን እንዳናሳካ ያደርገናል፡፡ ፈተና ሊበዛ ይችናል፡፡ ነገር ግን ካለ ተግዳሮትና ፈተና የሚገኝ የቤተሰብ ውርስ ብቻ ነው፡፡ የራሳችን ነገር፣ በእራሳችን ብርታት የምንፈልግ ከሆነ ፈተናና ተግዳሮት አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም ከፈተናና ተግዳሮት ልምድ መቅሰምና እራሳችንን እንዲጠቅመን መቀየር ነው፡፡ ለዚህም ራስን ማዘጋጀት፡፡ ሁሉም ነገር አልጋባልጋ ይሆናል ብለን ከተነሳን፤ በኋላ ተግዳሮቶች ሲከሰቱ የመንፈስ ስበራቱ ያለምነው ግባችን ላይ እንዳንደርስ መሰናክል ይሆናል፡፡ ስለዚህ ለተግዳሮቶችና ፈታናዎች ራስን በማዘጋጀት የአይበገሬነት መንፈስ መቀናጀት፡፡

❖አንዴ አልተሳካም ማለት ህይወት አከተመላት ማለት አይደለም

ህይወት መስመሯ አባ ጎርባጣ እነደመሆኑ መጠን ዛሬ ያቀድነው ነገር አልተሳካም ማለት አጠቃላይ ህይዎታችን አለቀላት ማለት አይደለም፡፡ እንደዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ለድበርት ስሜትና ለሌች የስነ ልቡና ችገሮች መከሰት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ምክኒያታዊ ያልሆነ አስተሳሰብ (irrational belief) ነው፡፡ ዛሬ ያፈቀርካትን ልጅ ስላላገኘሀት አጠቃላይ የፍቀር ህይዎትህ ዜሮ ሆነ ማለት አይደለም፡፡ ዛሬ የፈለግኸውን ስራ ስላላገኘህ የነገ መንገድህ ተቆረጠ ማለት አይደለም፡፡ ያለተሳካው ከብዙ የህይወት ግብ ውስጥ እንዱ ወይም የተወሰኑት ናቸው፡፡ ህይወት ደግሞ በአንድና ሁለት እቅድ አትመዘነም፡፡ ይህም የህይወትንና የተፈጥሮን ታላቅንት ማሳነስ ነው፡፡

❖ራስን መቆጣጠር ልምምድ ይፈልጋል

እንግዲህ ተግባራዊ ግብ ማስቀመጥና አስተሳሰባችንን፤ውስጠ ስሜታችንንና ጠባይያችንን ከዚህ ግብ አንጻር መግራት የራስ ቁጥጥር አንኳር መገለጫዎች ናቸው፡፡ የማይተገበር ግብ ማስቀመጥም ለውድቀት ይዳርጋል፤ ተግባራዊ ግብ ቢኖረንም በጽናት ጠባይያችንንና nአስተሳሰባችንን ካልገዛነውም ለውድቀት እንዳረገልን፡፡ ስለዘህ እራሳችንን የመቆጣጠር ክህሎት ለመካን ከትናንሽ ነገሮች ጀምረን እንለማመደው፡፡ ያኔ የስብእናችን ዋነኛ ምሰሶ ይሆናል፡፡

(በአሸናፊ ካሳሁን)
©Zepsychology

www.tg-me.com/psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
እንኳን ለ 2013 ዐዲስ አመት አደረሰን!
#ሜሎሪና መጽሐፍ ለዐዲሱ አመት ስጦታ፡፡

በብዙ አንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሜሎሪና ልብወለድ መጽሐፍ ለአንባቢያን በቀረበ በኹለት ወር ውስጥ ሦስተኛ ህትመት የተሰጠና ብዙዎች አንባቢዎችን ቀጣዩን በጉጉት እንዲጠብቁ ያደረገ መጽሐፍ ነው፡፡

መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው ሥነልቡናዊ ልቦለድ ሲሆን የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው የማያቋርጥ ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበባዊ ሚና የሚተርክና ከፍተኛ የአስተሳሰብ ልዕልናችንን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው ፡፡ አቀራረቡም አስተማሪ የሥነልቡና ምክሮችንና ሀሳቦችን ከታሪካዊ ክስተቶች ጋር ደምሮ የያዘ ነው፡፡

|ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብ ወለድ|

ከመጽሐፉ የተወሰዱ ሀሳቦች
~~~~~~~~~~~~~~~
‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››
______
‹‹ኢትዮጵያዬ ቅደሚ፣ አንቺ ስትቀድሚ ልጆችሽ ደስ ይለናል፡፡ አንቺ ስትለሚ ከስደታችን እናርፋለን፤ አንቺ ስትበለጽጊ ዓለም ሁሉ ወዳንቺ ይመጣል›› እያለች ስታለቅስ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ታቤል በልጅነት አእምሮው ‹ኢትዮጵያ› የሚለውን ስም የያዘው፡፡ ታቤልም ‹‹እንዲህ የምትወድድ፣ የሚታዘንላትና የሚለቀስላት ኢትዮጵያ ማን ነች?›› እያለ መጠየቅ የጀመረው ከዚያ በኋላ ነው፡፡
______
‹‹ዐይን አላችሁ? ተመልከቱ! ጆሮ አላችሁ? እንግዲያውስ ስሙ! ልብ አላችሁ? አስተወሉ! ገንዘብ ምድራዊ ሕይወት እንጂ እውነተኛን ደስታን አይገዛላችሁም፡፡ ደስታን የሚገዛላችሁ እረፍት የሚሰጣችሁ ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ የሌለው ላይመጣ ያለው ላይሄድ ዕድሜያችሁን ሙሉ ከመባዘን ተጠበቁ!›› ይሉ ነበር አበምኔቱ፡፡
_____
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡ ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

~~~~~~~~~~~~~~~
በተለያዩ ሚዲያዎች የቀረቡ የመጽሐፉ ዳሰሳ

በEBS ቅዳሜን ከሰዓት
https://youtu.be/pCMLIRgFKdM

በETV ፈታኝ ሳጥን
https://youtu.be/XNBsOMgrd4o

በNahoo መዝናኛ
https://youtu.be/hb_7RyK203c

በአሐዱ ራዲዬ ፍኖተ ጥበብ ፕሮግራም
https://youtu.be/ULetSbHlRSI
https://youtu.be/DZWWNEP1Po4

በFana ራዲዬ ጥበባት ፕሮግራም
https://youtu.be/I07rjVHMKM0

በመጽሐፍ መደብሮችና አዟሪዎች እጅ ይገኛል!
_____________________________
በዐዲስ አበባ

ለገሀር ✿ጃፋር (ኖክ አጠገብ - ተወልደ ህንጻ)

ሜክሲኮና ስታዲየም ናሽናል ታወር ✿ሀሁ (ደብረ ወርቅ ህንፃ አጠገብ)

ጥቁር አንበሳ ✿እነሆ (ትራኮን ታወር)

ካዛንቺስ ✿ጦቢያ መጽሐፍ ቤት

ቦሌና አራት ኪሎ ✿BOOK LIGHT

በተጨማሪም ከሌሎችም መጽሐፍ መደብሮችና መጽሐፍ አዟሪዎች ላይ ታገኙታላችሁ
_____________________________
በክልሎች
በአዳማ +251923736714

በአዋሳ +251916617743
+251940479245

በሌሎች ችልሎች የምትገኙ አንባቢያን መጽሐፉን ከየመደብሩ ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡
_____________________________
ከኢትዮጵያ ውጭ

አሜሪካ +12022947117

ኢንግላድ +447577009720
_____________________________
በዐዲስ አበባ ሜሎሪና ቤታችሁ ድረስ እንዲመጣ ከፈለጋችሁ +251939115238 ደውላችሁ እዘዙ ።
መጽሐፉን በብዛት ማከፋፈል የምትፈልጉ 0912664084 መደወል አሳታሚውን ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡

መልካም ንባብ !
ለምትወዱት ሰው ለዐዲስ ዓመት የምትሰጡት ግሩም ስጦታ

ሜሎሪና 💚💛❤️

መልዕክቱን ለሌሎችም በማጋራት እናድርስ
@psychoet
2024/09/29 19:31:14
Back to Top
HTML Embed Code: