Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_27
#ሜሎሪና #ተስፋ_ማድረግ
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

‹‹ልጄ ያሬድ፣ የሰው ልጆችን መከራ ማሸነፊያ መሣሪያ ስለኾነው ነገር ልንገርህ፡፡ ችግሮችን ሁሉ የምናሸንፍበትና ከገባንበት አረንቋ የምንወጣበት አንድ ትልቅ መሰላል አለ፤ እሱም መልካም ተስፋ ነው፡፡ ተስፋ፣ ከምንኖርበት ቦታና ካለንበት አካባቢ አልፈንና ተሻግረን አርቀን እንድናስብ የሚረዳን ነው። ተስፋ አሳብ ነው፤ ተስፋ ምኞት ነው። ዛሬያችንን፣ ከተወረሰበት ጨለማ አራግፈን የምናወጣበት ነው፡፡ ይቺ ዓለምም ብትኾን ለተስፈኞች የተለየ ቦታ ያላት ትመስላለች፡፡ ምክንያቱም ምንም ነገር ሳይታይ፣ ሳይሰማ፣ ሳይዳሰስና ሳይጨበጥ በፊት በአሳብ ደረጃ እያለ የማይታየውን እንዲታይ፣ ያልተጨበጠውን እንዲጨበጥ የሚያደርጉት ትላልቅ ተስፈኞች
ናቸው፡፡ ተስፋ በርግጥ የወደቀውን ያነሣል፤ የተሰበረውን ይጠግናል፡፡

‹‹ስለዚህ ዛሬን በደስታ እየኖርህ ነገ የተሻለ ቦታ መድረስ እንደምትችል በፈጣሪ መልካም ተስፋ አድርግ፡፡ ኹኔታዎች ምቹ ባይመስሉም ተስፋህን ግን አታርቀው፤ ሁሌ ለችግርህና ለሐዘንህ ተስፋን አሳያቸው፡፡ ሕይወትህ መከራ፣ ችግር፣ ሐዘን ውስጥ ቢገባም በቅርቡ ወደ በለጠ ደስታ፣ ድልና ስኬት እንደምትሸጋገር እመን፡፡ በምታልፍበት የሕይወት ችግር ውስጥ የምትኖረው ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደኾነ ለችግርህ ንገረው፡፡ በነገ መልካም ተስፋ ዛሬን በደንብ ጠንክረህ ሥራ በደስታም ኑር፡፡››

-ሜሎሪና 172-

❖_____________________________❖

ሜሎሪና መጽሐፍን በጃዕፈር ፣ በሀሁ፣ በብራና፣ በኢዞፕ፣ በጦብያ ... እንዲሁም በሌሎች መደብሮችና አዟሪዎች እጅ ታገኛላችሁ ፡፡

❖__________________________________❖

@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
የሰው ልጆችን ቀልብ የሚስቡና ልብ የሚገዙ ወሬዎች ባይነት ባይነቱ ቢሰሙም፣ ‹‹ሞቼ ተነሣሁ›› የሚልን ሰው ወሬ እንደመስማት ግን የሚያጓጓ አይገኝም፡፡ ‹‹የማያውቁት አገር አይናፍቅም›› ቢባልም ስለማያውቁት አገር ለመስማት የሚናፍቁ ብዙዎች ናቸው፤ የማይቀርለት አገር ምን እንደሚመስል እንደማወቅ ልብ የሚሰቅል ነገር የለምና፡፡
ሜሎሪና ❤️
ቸር ሠንበት
@Psychoet
ምስጋና እና ዘርፈ ብዙ ጥቀሞቹ
Telegram : www.tg-me.com/psychoet

በርካታ ጥናቶችም የምስጋና ባህል በተቻለ መጠን መዳበር እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ ጥናቶች መካከል የ “Positive Psychology” መስራች ሴሊግማን 411 ሰዎች ላይ ያካሄደው ጥናት ቀዳሚ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው የተለያዩ አዎንታዊ ሀሳቦች እና ድርጊቶች ያላቸውን ውጤት በመለካት (Testing) ሲሆን ምስጋና ከሁሉም የላቀ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ታውቋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሕይወታችን ትልቅ ቦታ አለው የሚሉትን እና በሚገባ አመስግነው ለማያውቁት ሰው የምስጋና ደብዳቤ ፅፈው በራሳቸው እጅ እንዲያደርሱ ከተደረገ በኋላ ውጤቱን ተጠንቶ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ተሳታፊዎቹ ላይ ታይቷል፡፡ ለውጡ ይበልጥ አስደናቂ ሊሆን የቻለው የተፈጠረው የደስታ ስሜት ለብዙ ወራት መቆየት በመቻሉ ጭምርም ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከየትኛውም ድርጊት በበለጠ መልኩ ምስጋና አመስጋኙን ደስተኛ የማድረግ ኃይል እንዳለው ታውቋል፡፡

የምስጋና ጥቅሞች

#ደስተኛ_ያደርገናል
በቀን ለአምስት ደቂቃ ያህል ማመስገን ከአማካይ ጤንነት በላይ 10% ሁለንተናዊ ጤንነትን ያሻሽላል፡፡

#ሰዎች_እንዲወዱን_ያደርጋል
በሁለት የተለያዩ ጥናቶች ከአብዛኘው ሰው 10 % በላይ የሚያመሰግኑ ሰዎች 17.5 % ከሌሎች የበለጠ የሰው መውደድ እንዳላቸው ታውቋል፡፡ ምስጋና ሰዎች እምነት እንዲጥሉብን፣ እንዲቀርቡን እና እንዲወዱን ያደርጋል፡፡

#በሥራ_ቦታ_ስኬታችንን_ይጨምራል
ምስጋና የተሻለ መሪ፣ ተግባቢ፣ የውሳኔ ሰው እና ስኬታማ እንድትሆኑ ያግዛል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ምስጋና ጤናማ ስሜት እንዲኖረን፣ ቁሳዊ አመለካከታችን (Materialism) እንዲቀንስ፣ ራስ ወዳድነት እንዲቀንስ፣ ለራሳችን ያለን አመለካከት እንዲሻሻል፣ ጥሩ እንቅልፍ እንድንተኛ፣ ረጅም እድሜ እንድንኖር ወዘተ ያደርጋል፡፡

ምስጋና ባህል እንደመሆኑ መጠን ደግመን ደጋግመን እስከተለማመድነው ድረስ ይሻሻላልም፡፡ ይህንን ለማድረግ የምስጋና ደብዳቤ መጻፍ፣ ጊዜ ቢታጣ እንኳ በልቦናችን ማመስገን፣ የምስጋና የግል ማስታወሻ መፃፍ፣ በረከቶቻችንን መቁጠር፣ ፀሎት የመሳሰሉት የምስጋና ባህላችንን ለማሻሻል የሚረዱ ልምምዶች ናቸው፡፡

_______________
ይህን ካነበባችሁ አይቀር የማመስገን ባሕልን ዛሬውኑ መለማመድ ጀምሩ ፡፡ ሕይወታችሁ ሲለወጥ ታዩታላችሁ ፡፡

አንድ ምሳሌ ልጨምርላችሁ ፦ አንድ ዳቦ ይዛችሁ ሶስት የተቸገሩ ሰዎችን ተመለከታችሁ ፡፡ ከዛ ዳቦውን እኩል ቦታ ቆርሳችሁ አካፈላችኀቸው፤ ሰዎቹም ሲበሉም ቆይተው ሲጨርሱ
#አንዱ ይሄ ምን ያጠግባል ፣ ደግሞ የማይጣፍጥ ዳቦ ነው ብሎ ተነስቶ ሄደ
#ሌላው ደግሞ ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ሄደ
#የቀሪው ግን እጅግ አመስግኖ እያለቀሰ ምግብ ከበላሁ 1 ቀኔ ነበር በማለት ሰጪውን ደጋግሞ አመሰገነ

እናም በዚህ ሁኔታ ሰጪው ላይ ምን አይነት አስተሳሰብ የሚጎለብት ይመስላችኀል? ተቀባዮቹስ ላይ?

ሰጪው በጣም የሚያስደስተው የሰጠው ጥቂት ዳቦ ሳይሆን ያመሰገነንውና እሱ በሰጠው ጥቂት ዳቦ ከርሀብ የወጣው ሰው ታሪክ ነው ፡፡ አማሮ ለሄደው ሰው ግን ለወደፊቱ ሞልቶ ቢተርፈውም ላይሰጠው ያስባል ስለ ሶስተኛው ሰው ግን እንዴት ምንም ሳይል ይሄዳል በሚል ብዙ ጥያቄዎችን ያወጣል ያወርዳል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ስንባል ምንም ነገር ስናደርግ ምላሽ እንጠብቃለን ፡፡

ስለዚህ ለመልካም ግንኙነት ስንል መልካም ነገር መናገር አማራጭ የሌለው ነገር ነው ፡፡ ካልተቻለ ግን መጥፎ ነገር ከመናገር ዝም እንበል ፡፡ መልካም ነገር የሚጀምረው ደግሞ ከቀላል ምስጋና ነው፡፡

Like & Share
fb.me/psychologyet
ሰላም ቤተሰቦቼ ፣

ቀናችሁ እንዴት ነበር?

ጥሩ ❤️
መካከለኛ 😏
ደስ የማይል 😢
#ህይወትን_በአዲስ_እይታ
www.tg-me.com/psychoet

ብዙዎቻችን ህይወትን የምንደርስበት ግብ አድርገን ፣ነገ የምናገኘው፣ ከልፋት በኋላ የምንቀዳጀው፣ ከአድማስ ባሻገር ያለ የቅርብ ሩቅ አድርገን እንስለዋለን። ይህ ግን ዛሬን እንደ መራራው ኮሶ መድኃኒት እየተጋትን ነገን በሰማይ እናዳለችው ወተቷን እንደማናየው ላም እየናፈቅን የቅዠት ኑሮ፣ በተስፋ መቁረጥ የታጨቀ፣ መፍጨርጨር የተሞላበት ግቡን ቀና ብሎ የሚያይ ግን የችግሮች እንቅፋት የሚያገላድፈው እይታችን ነው። ይህንን እይታ የኑሮ መሰረታቸው አድርገው የትዳር አጋራቸውን ያለፍቃዳቸው የራቁ፣ ልጆቻቸውን የማይንከባከቡ፣ ለእራሳቸው በቂ ጊዜ የማይሰጡ፣ ነፍሳቸው የወደደችውን ነገር ማድረግ እንደ ቅንጦት የሚቆጥሩ ሞልተዋል። ይህ ደግሞ በስተመጨረሻ ቁሳዊ የሆነ ማንነት አሳቅፎ ብቻችንን ያስቀረናል።

ግን እስኪ ደግሞ በዚህ በኩል እንመልከተው! ህይወት ግብ ሳይሆን መንገድ ነው። እራሳችንን እያወቅን የምንጓዝበት፣ በመኖራችን ለውጥ የምናመጣበት፣ በስህተታችን ተምረን የምንቀየርበት፣ በገጠመኞች የተሞላ ወደ ተሻለ ማንነት የሚደረግ ጉዞ። ይህን እይታ ከያዝን ለነገ መኖርን እናቆማለን ማለት ሳይሆን ነገን እያሰብን ዛሬን እስከነ ጭራሹ ከመዘንጋት እንላቀቃለን። ግለኝነትን ያተኮረ የራሴ ጥቅም ብቻ እያልን በሰዎች ጫንቃ ላይ በመወጣጣት እኔን ብቻ ላኑር ከሚል ርካሽ አስተሳሰብ ከላያችን ላይ አራግፈን በዛሬ ውስጥ እራሳችንን ማግኘት ያስችለናል።

ዛሬ ጊዜ ያልሰጠናቸው ቤተሰቦቻችን ነገ “እንደዛ ስለፋ የነበረው አንተ የሻለ ኑሮ እንድትኖር በማሰብ ነው” “እንዲህ እንድትንደላቀቂ ብዬ ነው ቀን ከለሊት ስለፋ የነበረው” የሚል የየዋህነት አስተሳሰብ ያሳጣናቸውን ፍቅር እና አብሮነት አይተካም። ገንዘብ ለልጆቻችን ጃኬትን እንጂ ማቀፍ የሚሰጠውን የደህነትን ስሜት አይገዛም። ገንዘብ ውድ የሆነ ስጦታን እንጂ ከትዳር አጋራችን ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ አይገዛም፣ ገንዘብ አልጋን እንጂ እንቅልፍን አይገዛም፣ ገንዘብ ምግብን እንጂ የምግብ ፍላጎትን አይገዛም። ስለዚህ በእኛነታችን የምንሰጣቸውን፣ የገንዘብ ቁልል የማይገዛቸውን፣ የመኖር ሃብቶች፣ የህይወት ስጦታዎች የሆኑትን እኚህን የዛሬ ውጤቶችን አሳጥተናቸው ነገ ገንዘብ ብንሰጣቸው ዋጋው ምንም ነው።

ህይወታችንን ግብ አድርገን ከምንስለው በዕለት ተዕለት ኑሮዋችን ውስጥ የምናደርጋቸው ማናቸውም ቁርኝቶች ድምር መሆኑን ብናምን ይህ አዲስ እይታ የብርሃን ጮራ በህይወታችን ላይ ይፈነጥቅልናል።

(ዘመነ ቴዎድሮስ) ©psychologist
www.tg-me.com/psychoet
የሜሎሪና መጽሐፍ ውይይት #3

በአሐዱ ሬዲዬ 94.3 በሚካሄደው የፍኖተ ጥበብ ፕሮግራም ላይ ከዮናስ ዘውዴ ጋር ያደረኩትን ውይይት ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡
https://youtu.be/ULetSbHlRSI

መልካም ቀን
በእነዚህ ቀናት ያለፍን ሰዎች እድለኞች ነን
01/01/01
02/02/02
03/03/03
04/04/04
05/05/05
06/06/06
07/07/07
08/08/08
09/09/09
10/10/10
11/11/11
12/12/12

ተመሳሳይ ቀናት ከ 100 ዓመትታ በኀላ ይመጣሉ ፡፡ ያኔ ልጆቻችንና ቅድመ ልጆቻችንም ሊያዩት ይታደሉ ይሆናል - ግን ጥያቄው እነዛን ቀን ለማየት የታደሉ ሰዎች እኛ በዚህ ጊዜ በምንሰራቸው ስራዎች እኛን ያመሰግኑን ይሆን ወይስ ይረግሙን ?

ናሁሰናይ ፀዳሉ
@psychoet
፨በ12/12/12

በኢቶዮጽ መጽሐፍ የምናውቀው ደራሲና ሀኪም ኤሊያስ ገብሩ ለክረምቱን መውጫ መልካም የጆሮ ስጦታ በ "አንድ ፍቅር" የግጥም አልበም ሲዲ መቷል ፡፡

የአልበሙን ሲዲ ለማግኘት በአገር ውስጥ ያላችሁ በ0966060708 በመደወል አልያም በአካል አብርሆት አሳታሚዎች ለም ሆቴል ፊትለፊት በመሄድ ወይም ቤታችሁ ድረስ እንዲመጣ በ0939115238 በመደወል ልታዙ ትችላላችሁ ።
በተጨማሪ በአውታር መተግበሪያ ላይ ማግኘትም ይቻላል። በውጭ አገራት ላላችሁ ደግሞ ቀጣዮቹን ሊንኮች ልታገኙት ትችላላችሁ

Amazon Music

https://www.amazon.com/gp/product/B08F9VNNP2/ref=dm_ws_sp_ps_dp

ITunes

https://music.apple.com/us/album/aned-feqer-ethiopia/1526401947?uo=4&app=itunes

Apple Music

https://music.apple.com/us/album/aned-feqer-ethiopia/1526401947?uo=4&app=apple+music

Google Play

https://play.google.com/store/music/album/Dr_Elias_Gebru_Aned_feqer_Ethiopia?id=Bidtvyix5manurdpxuya3lxi3hm

(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)
ደስታ ከውጭ የሚገኝ ብቻ ሳይሆን ከውስጥም የሚፈልቅም ጭምር ነው ፡፡ ደስታችሁ ኹሌም ይብዛ ፡፡

መልካም አዳር
@Psychoet
የ3 ደቂቃ ስራ ናት እናንብባት ረጅም አይደለችም አጭር ፅሁፍ ናት

*አንድ የ78 ዓመት አባት እራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል ይወሰዳሉ ። ለ24 ሰዓት የሚያቆያቸው የመተንፈሻ ኦክስጅን ተሰጣቸው ። ከጥቂት ግዜ በኃላ ተሻላቸውና ዶክተሩ የተጠቀሙበትን ሂሳብ የ500 ዶላር ደረሰኝ ሰጣቸው ።
*እኝህ አባትም የተሰጣቸውን ደረሰኝ በተመለከቱ ግዜ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ። ዶክተሩም ስለ ገንዘቡ ማልቀስ አይገባዎትም በአንድ ግዜም ባይሆን ቀስ እያሉ መክፈል እንደሚችሉ ነገራቸው ። *ሆኖም እኝህ አባት " እኔ የማለቅሰው ስለዚህ ገንዘብ አደለም ገንዘቡን በሙሉ የመክፈል አቅም አለኝ ፤ የማለቅሰው 24 ሰኣት ለተነፈስኩበት ኦክስጅን 500 ዶላር ልከፍል በመሆኑ ነው ፤
*ነገር ግን ላለፋት 78 አመታት የእግዚአብሔርን ንፁ አየር በነፃ ስተነፍስ ኖሬያለው ለእነዚ ሁሉ ግዜያት መክፈል ቢኖርብኝ ምን ያህል የእግዚአብሔር እዳ እንዳለብኝ መገመት ትችላለህ ?? " በማለት መለሱለት
*አሁን ይሄንን ወደምታነቢው እህት ወይም ወንድም ልመለስ ፤ የእግዚአብሔር ንፁህ አየር ያለ አንዳች ክልከላና ክፍያ ይሄን ያህል ስትተነፍሺ ኖረሻል ወይም ስትተነፍስ ኖረሃል ።
==========================
ከተመቸችህ አስተማሪ ናት ካልክ ሼር አድርጋት
©Selam yehune

@Psychoet
የዶ/ር ኤልያስ ገብሩ የግጥም አልበም በአውታርም ተለቋል። 18 ሥራዎቹን ከአውታር መተግበሪያ ላይ በ15 ብር ካርድ ብቻ ማውረድና ማዳመጥ ትችላላችሁ።

አንድ ፍቅር❤️❤️❤️
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
25 ሕይወት ቀያሪ አባባሎች
#Share

1. አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡
-ፍራንክ ኦሽን

2. በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሀል ፡፡
-ቶማስ ጄፈርሰን

3. ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ ነው ፡፡
-ዶናልድ

4. አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡
-ኢማም አሊ

5. በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው ፡፡
-ዋልተር ባግሆት

6. ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡
-ጂም ዋትኪንስ

7. ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም ፡፡
-አርል ኒተንጋል

8. ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው ፡፡
-አዚም ፕሪሚጂ

9. ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡
-ዚግ ዚግላር

10. ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ ፡፡
-አልበርት አንስታይን

11. አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም ፡፡
-ካርል ጉስታቭ

12. ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡
-ሪያኖር ሮዝቪልት

13. እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡
-ኮንፊሺየስ

14. ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
-ቲም ኖትኪ

15. ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል ፡፡
-ሱዚ ካስም

16. እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር ፡፡
-ብሩስ ሊ

17. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
-ካረን ላንብ

18. ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል ፡፡
-ስቴፈን ማክክሬን

19.ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው ፡፡
-ሮቢን ሻርማ

20. አለም የምትቀየረው በአንተ አስተያየት ሳይሆን በአንተ ተግባራዊ ስራ ነው ፡፡
-ፖል ኮኢልሆ

21. መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል ፡፡
-ኤሪክ ቶማስ

22. ፊትህን ወደ ፀሀይ ስታዞር ጥላህ ከኀላህ ይወድቃል ፡፡
-የማዎሪ አባባል

23. 99% የሚሆኑ ሰዎች ሀሳብህን ከተጠራጠሩህ ፣ እጅጉን ስተሀል አልያም ታሪክ ልትሰራ ነው ፡፡
-ስኮት ቤልስካይ

24. ፈፅሞ አትድከም ምክንያቱም አሁን እጅግ ከባድ የሆነብህ ስራ ከጥቂት ጊዜያት በኀላ ለሌላ ስራ መሟሟቂያ ይሆናል ፡፡
-ያልታወቀ ሰው

25. ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ ፡፡

ለሌሎች ወዳጆቻችንም #ሼር እናርጋቸው
ባለንበትም የፌስ ቡክ ግሩፖች #በማጋራት መልካም ሃሳብ እናስተላልፍ

የፔጃችንም Like በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
ሥነ ልቡና - Psychology

fb.com/psychologyet

ከሁሉም የቱ ተመቻችሁ?
(በናሁሰናይ ፀዳሉ) የተሰበሰቡ ድንቅ አባባሎች
@psychoet
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፈታኝ ሳጥን
እሑድ ነሐሴ 17 ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በኢቲቪ መዝናኛ

❖ በሜሎሪና መጽሐፍ ያነሳኀቸውን አንዳንድ ነጥቦች በተጨማሪም በግላዊ የሕይወት ተሞክሮዬ ላይ ከዴቭ ጋር ውይይት አድርገናል ፡፡
እንድትከታተሉና ሌሎችም ወጣቶች እንዲመለከቱት እንድትጋብዙልኝ እጠይቃለሁ ፡፡

የሰው ልጆችን ቀልብ የሚስቡና ልብ የሚገዙ ወሬዎች ባይነት ባይነቱ ቢሰሙም፣ ‹‹ሞቼ ተነሣሁ›› የሚልን ሰው ወሬ እንደመስማት ግን የሚያጓጓ አይገኝም፡፡ ‹‹የማያውቁት አገር አይናፍቅም›› ቢባልም ስለማያውቁት አገር ለመስማት የሚናፍቁ ብዙዎች ናቸው፤ የማይቀርለት አገር ምን እንደሚመስል እንደማወቅ ልብ የሚሰቅል ነገር የለምና፡፡

ለቅዳሜና እሑድ መጽሐፍ ሸመታችሁ ፡፡ሜሎሪና መጽሐፋን በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች መደብሮች ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡ ያነበቡት ኹሉ በአስደናቂው የታሪክ ፍሰቱና ትስስሩ ወደውታል፡፡

መልካምና ደስ የሚል ቀን ይኹንላችሁ ፡፡😀 ራሳችሁን ከኮሮና ጠብቁ ፡፡
www.tg-me.com/Psychoet

ናሁሰናይ ፀዳሉ
ሰላም ቤተሰቦቼ!
የሜሎሪና መጽሐፍ ዳሰሳ ዛሬ እሑድ

በናሁ ቲቪ እሑድ መዝናኛ ከ 9:00 ጀምሮ
በETV መዝናኛ ከ 2:10 እንድትከታተሉ እጋብዛለሁ ፡፡

መልካም ሠንበት!
@PSYCHOET
የደስታ ሳምንት !
ሳምንታችንን እኛ እንሰራዋለን ፡፡ እያንዳንዱ ቀን በራሱ ጥሩ ወይንም መጥፎ ሁኖ አይመጣም ይልቁንስ ኹለቱንም እድል ይዞ ወደእኛ ይመጣል ፡፡ ስለዚህ ደስታና ሀዘን ባብዛኛው የውሳኔያችን ውጤት ስለሆነ በየቀኑ ባለን ነገር ለመደሰት እንወስን ፡፡ ባለንበት ዕምነት ደግሞ ምስጋና ማድረግ ትልቁ የደስታ ምንጭ ነውና ፈጣሪን በየቀኑ እናመስግን ፡፡

ሜሎሪና መጽሐፋችን በሀገር ውስጥ በየክልሉ ስለተሰራጨ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ እየገዛችሁ እንድታነቡና ብዙ የሕይወት ቁም ነገሮችን ቆም ብላችሁ እንድታስታውሱ አሳስባለሁ ፡፡

መልካም ቀንና ሳምንት ይሁንላችሁ
#Share #Like
@Psychoet
የሜሎሪና ተከታታይ ልብወለድ መጽሐፍ ዳሰሳ

በኢቢኤስ - ቅዳሜ ከሰዓት ፕሮግራም ። "ሰው እንዳያረጅም እንዳይሞትም ማረግ ይቻላል ወይ? ምድር እስር ቤት ነች ወይ? ትልቁ የጦርነት ስፍራ አእምሮ ነው ወይ? ... " ከተወያየንባቸው ሀሳቦች በጥቂቱ ናቸው ፡፡ ብዙዎች አንብበውት ቀጣዩን በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡

በቲቪ ያልተከታተላችሁ በዩቲዩብ ታገኙታላችሁ

መጽሐፉን በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች መደብር እየተሸመተ ይገኛል ፡፡
በክልል ከተሞችም ስለተላከ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ታገኙታላችሁ ፡፡

በቲቪ ያልተከታተላችሁ በዩቲዩብ ታገኙታላችሁ
https://youtu.be/pCMLIRgFKdM
#የጥሩ_እንቅልፍ_9_ጠቀሜታዎች
ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው

1. እንቅልፍ ልብዎን ጤናማ ያደርገዋል

እንቅልፍ ማጣት የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ(ስትሮክ) እንደሚያባብስ ተመራማሪዎች ይናገራሉ ይህም የሚሆነው የደም ግፊት እና ኮሌስትሮል መጠንን በመጨመር መሆኑን ይናገራሉ ፡፡በእያንዳንዱ ምሽት ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል እንቅልፍ ካገኙ የልብዎን ጤና የተጠበቀ ይሆናል ፡፡

2. እንቅልፍ ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል

ተመራማሪዎች ለብርሃን መጋለጥ የሜላቶኒንን መጠን እንደሚቀንስ ያምናሉ ፡፡ ሜላተንቲን የእንቅልፍ ና የመንቃትን ዑደትን የሚያስተካክል ሆርሞን ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ዕጢዎችን እብጠት በመቀነስ ካንሰርን ይከላከላል፡፡ ሰውነትዎ የሚፈልገውን ሜላቶኒንን ለማምረት እንዲረዳዎ መኝታዎ ጨለመ ባለ ስፍራ ያድርጉ እንዲሁም ከመኝታዎ በፊት ኤሌክትሮኒክስን ከመጠቀም ይቆጠቡ ፡፡

3. እንቅልፍ ውጥረትን ይቀንሳል

ሰውነትዎ እንቅልፍ እጥረት ሲኖርበት ወደ ውጥረት(ስተርስ) ሁናቴ ይሄዳል ፡፡ ይህም ውጥረት ወየንም ስተርስ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ የመያዝ እድልን ይጨምራል፡፡

4. በቂ እንቅልፍ ማግኘት የበለጠ ንቃትን ይሰጣል

ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ ንቃት እንዲሰማዎት እና በሚቀጥለው ቀን እንዲነቃቁ ይረዳዎታል ፣ በተጨማሪም ጥሩ ስሜት እነዲሰማዎት በማድረግ ሌላ ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ እድልዎተን ይጨምራል።

5. እንቅልፍ የማስታወስ ችሎታዎን ያሻሽላል

ተመራማሪዎች እስካሁኑ ሰዐት ድረስ ለምን እንደምንተኛ ሙሉ በሙሉ አልተረዱም ፣ ነገር ግን እንቅልፍ የማስታወስ ዐቅምን በማጠናር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ደርሰውበታል፡፡
በእንቅልፍ ጊዜ ሰውነትዎ አረፍ ሊል ይችላል ፣ነገር ግን አንጎልዎ ቀንዎን በማቀነባበር የተያዩ ግንኙነቶችን በማድረጉ ሥራ ላይ ነው ፡፡ እነዚሀም ግንኙነቶች በተያዩ ክስተቶች ፣ በስሜት ህዋሳት ፣ ስሜቶች እና ትውስታዎች መካከል ሲሆን በቂ እንቅልፍ ማግኘት ነገሮችን በተሻለ ለማስታወስ እና ለማስኬድ ይረዳዎታል ፡፡

6. እንቅልፍ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል

ተመራማሪዎቹ እንዳሳዩት በማታ ጥቂት ሰዓታት የሚተኙ ሰዎች ከመጠን በላይ ወፍራም ወይም ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው መሆናቸውን ነው ፡፡ የእንቅልፍ እጥረት በሰውነት የምግብ ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሆርሞኖችን መጠን ይጎዳል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት የምግብ ፍላጎትን የሚያስተካክሉ ሆርሞኖች ጋሬሊን እና ሌፕቲን በእንቅልፍ እጥረት ምክንያት ተስተጓጉለው ተገኝተዋል ፡፡ ክብደትን ለማቆየት ወይም ክብደት ለመቀነስ ከፈለጉ ፣ በመደበኛነት በቂ እንቅልፍ ማግኘት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አይርሱ።

7. ማቅለብ ብልጥ ያደርግልዎታል

በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ መውሰድ ለአጠቃላይ ጤናዎ ጥሩ ሲሆን በተጨማሪም የበለጠ ምርታማ እንዲሆኑ አዕምሮዎትን የሚያድስ አማራጭ ነው ፡፡ ጥናቶችእንደሚያሳዩት ከሆነ በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ የሚወስዱ ሰዎች የአዕምሮ ወይንም ኮግኒቲቭ ተግባር እና የ ስሜት መሻሻል ማሳየታቸውን ነው፡፡

8. እንቅልፍ የጭንቀት በሽታ አደጋዎን ይቀንሳል

ሴሮቶኒንን ጨምሮ እንቅልፍ በሰውነትዎ ውስጥ ያሉትን ብዙ ኬሚካሎች ይነካል። የ serotonin ጉድለት ያላቸው ሰዎች በጭንቀት በሽታ የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ትክክለኛውን የእንቅልፍ መጠን እያገኙ መሆኑን በማረጋገጥ ድብርትዎን ለመከላከል በየዕለቱ ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል የዕንቅልፍ ጊዜ ይውሰዱ፡፡

9. እንቅልፍ ሰውነቱን በራሱ እንዲጠገን ይረዳል

እንቅልፍ ዘና የማለት ጊዜ ነው ፤ ሰውነታችን በቀኑ ጊዜ፣ በአልትራቫዮሌት ጨረሮች እና በሌሎች ጎጂ ነገሮች ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ጠንክሮ የሚሠራበት ጊዜ ነው ፡፡ ተኝተው እያለ ሴሎችዎ የበለጠ ፕሮቲን ያመርታሉ ፡፡ እነዚህ የፕሮቲን ሞለኪውሎች የሰውነት ክፍሎችዎን በመገንባትና በማድስ ጉዳቱን ለመጠገን ያስችላቸዋል ፡፡

©በአቤል ታደሰ

ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው
መልካም አዳር
@Psychoet
2024/09/29 21:27:18
Back to Top
HTML Embed Code: