Telegram Web Link
በምድር ላይ ስትኖሩ በምን ስራችሁ ስትታወሱ መኖር ትፈልጋላችሁ ?

በምድር ላይ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ ።
1. የመጀመሪያዎቹ ጥሩ ነገሮችን በመስራት ታዋቂ የሆኑ ናቸው ፤
2. ኹለተኛዎቹ ደግሞ መጥፎ ነገሮችን በመስራት ታዋቂ የሆኑ ናቸው ፤
3. ሦስተኛዎቹና አብዛኛው የምድራችን ሰዎች ግን ከላይ የተጠቀሱትን ሰዎች ሲከተሉ የራሳቸውን ስራ ሳይሰሩ የሚያልፉ ናቸው ፡፡

ከሶስቱም አይነት ሰው የመኾን ምርጫ የእኛ ነው ፡፡

ሜሎሪና በዚህ ክረምት መነበብ ያለበት ድንቅ ዐይን ገላጭ ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ
@PSYCHOET
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
👉 ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች

ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።

1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።

2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።

3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።

4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።

5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።

6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።

7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።

8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው። በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።

9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው። ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣ ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።

10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
#በቅንነት ሼር አድርጉ

@psychoet
ሜሎሪናን ሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ እያነበባችሁ አስተያየት እየሰጣችሁኝ ያላችሁን የፔጃችን ቤተሰቦችን ላመሰግን እወዳለሁ ፡፡ ያላነበባችሁም እንድታነቡት እጋብዛለሁ ?

ጃዕፈር ፣ ሀሁ እንዲሁም ሌሎች መደብሮችና ከአዟሪዎች እጅ ያገኛል ፡፡

መጽሐፉን ማግኘት ካልቻላችሁ በዚህ አሳውቁኝ @cdimage
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «የሜሎሪና ተከታታይ ልብወለድ መጽሐፍ ዳሰሳ በኢቢኤስ - ቅዳሜ ከሰዓት ፕሮግራም ። "ሰው እንዳያረጅም እንዳይሞትም ማረግ ይቻላል ወይ? ምድር እስር ቤት ነች ወይ? ትልቁ የጦርነት ስፍራ አእምሮ ነው ወይ? ... " ከተወያየንባቸው ሀሳቦች በጥቂቱ ናቸው ፡፡ ብዙዎች አንብበውት ቀጣዩን በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡ በቲቪ ያልተከታተላችሁ በዩቲዩብ ታገኙታላችሁ መጽሐፉን በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች…»
ሜሎሪና መጽሐፍ አንድ ወር ሳይሞላው
ከአንጋፋ የኢትዮጵያውያ መጽሐፎች ተርታ በአንባቢያን ተወዶ እየተሸጠ በመሆኑ ታላቅ ክብር ይሰማኛል ፡፡

መጽሐፉን በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች መጽሐፍት መደብሮች እየተሸመተ ነው ፡፡
@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_26
#ሜሎሪና
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

አብዛኞቻችን ሕይወታችንን የምንመራው ነገን በመፍራት ነው፡፡ በተለይም በማይመች አካባቢ ስንኖር ሕይወታችን እንዲሁ የሚያልቅ ስለሚመስለን ሐዘናችን ይጨምራል፡፡ ሕይወት ትጨልምብናለች፡፡ የሕይወት ጥያቄዎችም መነሣት የሚጀምሩት በዚህ ጊዜ ነው፡፡ አኹን ለመሥራት እስከተነሣን ድረስ በሕይወታችን ረፈደ የሚባል ጊዜ ባይኖርም፣ የሰው ልጅ ግን ከሕይወት ይልቅ ለሞት፣ ከደስታ ይልቅ ለሐዘን፣ ከመቀጠል ይልቅ ለማቆም የቀረበ ፍጡር ነው፡፡ ለዚህ ነው በሕይወት ዘመኑ ሲለፋ፣ ሲዳክርና ሲባዝን የሚታየው፡፡


በሕይወት ከመኖር ይልቅ መሞት ይቀላል፡፡ ለመኖር፣ መሥራትና መጣር፣ መውጣትና መውረድ ሲያስፈልግ፣ ለመሞት ግን ምንም ሳይሠሩ ቊጭ ማለት በቂ ነው፡፡ ምክንያቱም ከአፈር የተሠራው ሥጋ ለመኖር አፈር ይፈልጋልና፡፡ እኛ ሰዎች አሳባችን ከምንኖርበት ዓለም የሰፋና የጠለቀ ቢኾንም፣ እኛ ግን ይህንን ዘንግተን በተቈጠረው የሕይወት ዘመናችን ከሰፊው ራሳችን ይልቅ ወደ ጠባቡ ውጪ በመመልከት በሙሉ ማንነታችን ባዶነትን የምንላበስ፣ በክቡር ሥጋችን ውርደትን የምንከናነብ፣ በምክንያት በመጣንባት ምድር በዋዛ ኖረን በዋዛ የምናልፍ ነን፡፡

❖_____________________________❖

ሜሎሪና መጽሐፍን በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች የመጽሐፍ መደብሮችና ከአዟሪዎች ይገኛል፡፡

ነገ ከ 8:00 - 10:00 ሰዓት የሜሎሪና መጽሐፍ ዳሰሳ ከዮናስ ዘውዴ ጋር በአሃዱ ሬድዮ (94.3) የማደርገውን የቀጥታ ስርጭት ውይይት እንድታዳምጡ እጋብዛለሁ፡፡
❖__________________________________❖

@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
ስብሃት ገብረእግዚአብሄር አንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፥

"በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ፤ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ፤ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ፤ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፤ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።

"በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።

"ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"

አንድ ነገር ልንገራችሁ፥ በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ፤ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡልችሀል፤ መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑችሁዋል። ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆናቹኋል፤ ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑላችሁዋል።

በዚህ ሀሳብ የሚስማማ #ሼር ያድርግ
@Psychoet
የሜሎሪና መጽሐፍ ውይይት #3

በአሐዱ ሬዲዬ 94.3 ላይ ዛሬ (እሑድ) ከ 8:00 - 10:00 በሚካሄደው የፍኖተ ጥበብ ፕሮግራም ላይ በቀጥታ ስርጭት ከዮናስ ዘውዴ ጋር የማደርገውን ውይይት እንድትከታተሉ እጋብዛለሁ?
ዛሬ - እሑድ ከ 8 - 10 ሰዓት

መልካም ሠንበት
@psychoet
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት
1. ጥሩ አድማጭ መሆን

ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡

2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን

በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡

3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ

የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡

4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ

ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡

5. አቀማመጥን ማስተካከል

ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡

6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት

እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡

7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ

ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡

8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡

9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር

በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡

ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet

የቻናሉ ቤተሰቦች በቅርቡ የኅትመት ብርሃን ያየውና በአስገራሚ የታሪክ ፍሰቱና ስነልቦናዊ ምክሮቹ የቀረበው የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ተከታታይ ልብወለድ መጽሐፍ "ሜሎሪና" እንድታነቡ እጠይቃለሁ ፡፡ ያነበቡት ኹሉ ወደውታል ፣ ተምረውበታል ፣ ሕይወትን ዘወር ብለው አይተውበታል ፡፡ መጽሐፉን ( በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች መደብሮች ያገኙታል ) ።

ለሌሎች #Share በማረግ ተግባቦታችንን እናሳድግ
ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet
©Zepsychology
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ግጭትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት
Telegram www.tg-me.com/psychoet

ግጭት የአንድ ሰው ድርጊት ወይም አመለካከት ሌላውን ሲረብሽ የሚፈጠር ሲሆን ይህም በቤተሰብ ፤ በጓደኛ ፤ በስራ ቦታ፤ በጋብቻ.. ወዘተ መካከል ሊከሰት ይችላል፡፡ የግጭቱ ሁኔታ መክረር ወይም በቀላል መፈታት  እንደተጋጪዎቹ ባህርይ ፤ግንኙነትና  የግጭቱ ዓይነት ይለያያል፡፡ የተለያዩ የግጭት ዓይነቶችን በአራት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት (Intra-personal)

ምንም እንኳን የተለያዩ የግጭት ዓይነቶች ቢኖሩም በማኅበረሰባችን ውስጥ የላቀ ትኩረት የሚሰጣቸው ከውጫዊ አካላት ጋር ለሚፈጠሩ ግጭቶች ነው፡፡ ይሁንና ሰው ከራሱ ጋር የሚፈጥረው ግጭት ከሌሎች ግጭቶች በተለየ መልኩ አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና ማኅበራዊ ቀውሶችን እንደሚያስከትል ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ከራስ ጋር የሚፈጠር ግጭት በተለያዩ  ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው ሰው በህይወት ዘመኑ በሚፈጽማቸው ስህተቶች ከህሊናው ጋር የሚፈጥረው ግጭት ነው፡፡

ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር ግጭት (Inter-personal)

በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው የግጭት ዓይነት ከሌላ ሰው ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ሲሆን ይህም በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከዋነኛዎቹ የዚህ ግጭት መንስኤዎች መካከል በሃሳብ አለመግባባት ፤ ግትርነት ፤ ነገሮችን በትዕግስት አለማሳለፍ ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡

በአንድ ቡድን አባላት መካከል የሚፈጠር (Intra-group)

ይህ የግጭት ዓይነት በግለሰቦች ደረጃ የሚፈጠር ሳይሆን ለአንድ ዓላማ በተመሠረተ ቡድን ውስጥ ባሉ አባላት መካከል ምክንያታዊና ምክንያታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች የራስን አቋም በማጣት የሌላውን ሃሳብ ተከትሎ በመሄድና የተዛባ መረጃ በመያዝ ከሌሎች የቡድን አባላት ጋር የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡

በቡድኖች መካከል የሚፈጠር ግጭት (Inter-group)

የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውኑ ሁለትና ከዚያም በላይ የሆኑ ቡድኖች በሚያገናኟቸው ጉዳዮች ላይ ተስማምተው መስራት ሳይችሉ ሲቀር ወይም አንዱ ሌላውን በበላይነት ማስተዳደር ሲፈልግ የሚፈጠር የግጭት ዓይነት ነው፡፡

በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው የግጭት ዓይነቶች በሚከተሉት ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

*የአመለካከት ልዩነት
*የባህል ፤ አስተዳደግ ፤ የባህርይ ልዩነት
*የዓላማ እና የፍላጎት ልዩነት
*የስልጣን/የኃይል ልዩነት
*እውነታና ፍላጎት አለመስማማት

★የግጭት አፈታት ዘዴዎች

ማንኛውም ዓይነት ግጭት ለማኅበራዊና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ሊዳርግ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ በመሆኑም በማንኛውም ጊዜ የሚያጋጥሙትን ለግጭት የሚዳርጉ ሁኔታዎችን ከግጭት በራቀ መልኩ የመፍታት ክህሎትን ማዳበር ስኬታማ የሆነ ህይወት ለመምራት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ግጭትን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት የሚያስችሉ ነጥቦች

1.የግጭቱን መንስኤ ለይቶ ማወቅ፡–

ግጭቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ መንስኤያቸውን ለይቶ ማወቅ ግጭቱ እንዳይባባስ ለማድረግና በቀላሉ መፍትሄ ለማፈላለግ ይረዳል፡፡ ለምሳሌ አንድ  ግጭት በሃሳብ አለመግባባት ቢፈጠር ይህ ሁኔታ ሊከሰት የቻለው ተጋጪው ካለው የአስተሳሰብ፤ የባህል ፤ የአስተዳደግ ፤ ወይም ከግለሰቡ የግል ባህርይ የተነሳ ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ መቻል ግጭቱን በቀላሉ ለመፍታት ይረዳል፡፡

2.አማራጭ መፍትሄዎችን ማየት

ለተከሰተው የሃሳብ ልዩነት ወይም ግጭት እንደመፍትሄ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጭ መንገዶችን ማየት ግጭትን በቀላሉ ለመፍታት ያስችላል፡፡

3.ስሜታዊነትን ማስወገድ

አብዛኛውን ጊዜ በስሜታዊነት የሚወሰዱ እርምጃዎች ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው የጎላ ነው፡፡

በመሆኑም ግጭት በሚነሳበት ወቅት እራስን ለመቆጣጠር እና ከስሜታዊነት የጸዳ ውሳኔ ለመወሰን ይቻል ዘንድ ግጭቱ ከተነሳበት አካባቢ በመራቅ ረጋ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

4.ስምምነት መፍጠር

 የተፈጠረውን አጋጣሚ አንስቶ ፊት ለፊት በግልጽ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር እንደ አስፈላጊነቱ ሌላ ሦስተኛ አካል ገብቶ የሚያነጋግርበትን መንገድ በመፈለግ ከግጭት ይልቅ ስምምነት የሚፈጥርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል ፡፡

መልካም ቀን ተመኘሁላችሁ ፤ ሰላም!
©zpsychologist


Telegram www.tg-me.com/psychoet
ይህ ምስል ከፔጃችን ቤተሰብ (ከAmerica Los Angeles) የደረሰን ነው ፡፡ ሜሎሪና ከሀገር ተሻግሮ በብዙ የዓለማችን ክፍሎች መነበብ በመጀመሩ ደስታ ይሰማናል ፡፡

ሜሎሪናን እያነበባችሁ በተለያየ መንገድ አስተያየት እየሰጣችሁን ያላችሁ ቤተሰቦቻችን እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን ፡፡

ሜሎሪናን እስካሁን ያላነበባችሁ መጽሐፉን በጃዕፈር ፣ በሀሁ እንዲሁም በሌሎች መደብሮች ታገኛላችሁ ፡፡

‹‹በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡ በምድር ላይ ሰዎች በኹለት ነገር ሲታወሱ ይኖራሉ፤ አንዱ በሚፈጥሩት ችግር ሲኾን፣ ሌላው ደግሞ በሚፈቱት ችግር ነው፡፡ ስለዚህ ሁሌ የችግር ፈቺ እንጂ ፈጣሪ አትኹን›› እያለች ትመክረው ነበር፡፡

ሜሎሪና ❤️❤️❤️
@Psychoet
የተለያዩ የማነቃቂያ ንግግሮችና የስነልቡና ምክሮችን ለማግኘት ሌላ አማራጭ በወጣቱ ተመስገን ዐቢይ
▶️ እንድትመለከቱት እጋብዛችኀለሁ
@psychoet
http://www.youtube.com/BePlusMotivation/channel
Forwarded from Jafer Books 📚 (Zee - Se)
በናሁሰናይ ጸዳሉ አበራ የተደረሰው ' ሜሎሪና ' የተሰኘው መጽሐፍ ተነባቢ ሆኗል ::

/

መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው ስነ-ልቦናዊ ልቦለድ ሲሆን የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበባዊ ሚና የሚተርክና ከፍተኛ የአስተሳሰብ ልዕልናችንን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው ፡፡

አቀራረቡም አዝናኝና የሥነልቦና ምክሮችንና ሀሳቦችን ከታሪካዊ ክስተቶች ጋር ደምሮ የያዘ ነው፡፡

የታሪኩ መቼት 1960 - 1994 ሲሆን
መተማ ፣ ጎንደር ፣ ዐዲስ አበባ ፣ ትግራይ (ደብረዳሞ ገዳም ፣ አል ነጃሽ መስጂድ ) ፣ አሜሪካ ( ዋሽንግተን ፣ ኒውዮርክ ፣ ኮሎራዶ) ፣ እንዲሁም እግረመንገድ እስራኤል ድረስ ይዘልቃል ::

//

ጃዕፈር መጻሕፍት ::

ለቴሌግራም:- @jafbok

ለዌብሳይት :- www.jaferbooks.com

መገኛችን :- ለገሃር ኖክ ተወልደ ሕንጻ ስር ::
‹‹ኢትዮጵያዬ ቅደሚ፣ አንቺ ስትቀድሚ ልጆችሽ ደስ ይለናል፡፡ አንቺ ስትለሚ ከስደታችን እናርፋለን፤ አንቺ ስትበለጽጊ ዓለም ሁሉ ወዳንቺ ይመጣል›› እያለች ስታለቅስ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ታቤል በልጅነት አእምሮው ‹ኢትዮጵያ› የሚለውን ስም የያዘው፡፡ ታቤልም ‹‹እንዲህ የምትወድድ፣ የሚታዘንላትና የሚለቀስላት ኢትዮጵያ ማን ነች?›› እያለ መጠየቅ የጀመረው ከዚያ በኋላ ነው....

ሜሎሪና

በአንድ ወር ኹለተኛ ህትመት ተሰቷል ፡፡ ሜሎሪና ተከታታይ ልብወለድ መጽሐፍ የሃገራችንና የዓለማችን የወደፊት መፃኢ እድል ነፀብራቅ ነው ፡፡

ያላነበባችሁ መጽሐፉን በጃዕፈር ፣ በሀሁ፣ በብራና፣ በኢዞፕ፣ በጦብያ ... እንዲሁም በሌሎች መደብሮችና አዟሪዎች እጅ ታገኛላችሁ ፡፡

ሜሎሪና ❤️❤️❤️
የታሪክና የሳይኮሎጂ ልብወለድ
@Psychoet
2024/09/29 23:29:07
Back to Top
HTML Embed Code: