Telegram Web Link
ክፍል 29
የአሸናፊነት ሥነልቡና(ክፍል 2)
በናሁሰናይ ፀዳሉ

አሸናፊነት በራሱ ባህሪይ ነው ለዛውም የምንለማመደውና የምናሳድገው ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እንጂ ከተግባር አይደለም ፡፡ በሀሳቡ ፣ በአዕምሮው የተሸነፈ ሰው በተግባር ቢያሸንፍም ውስጣዊ ደስታ እርካታ ድልን አያገኝም ፡፡ አሸናፊነት የሚለመድ የሚታይ ባህሪይ ነው ፡፡

10ሩ የአሸናፊዎች ባህሪ

ከተራ ቁጥር 1 - 5 ያሉትን ባለፈው በዝርዝር አይተናል፡፡ ዛሬ ከተራ ቁጥር 6-10 ያሉትን እናያለን ፡፡
__
1.ል
ንሆነው/ልንደርስበት ስለምንፈልገው ነገር የጠራ እይታ / አመለካከት
2.ግብ ማስቀመጥ
3.አወንታዊ አመለካከት
4.ቆራጥነት
5.ራስን ማወቅ
__

6.
Self Esteem / ራስን ማክበር

አሸናፊ ሰዎች ለራሳቸው ትልቅ ክብርና አድናቆት ያለቸው ናቸው ፡፡ስለራሳቸው ጥሩ አወንታዊ አመለካከት አላቸው ይህ ማለት ግን ሌሎችን ይንቃሉ / አያከብሩም ማለት አይደለም፡፡ ራስን ማክበርና ሌሎችን ማክበር መነጣጠል የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ተሳካልን ፣ ትልቅ ደረጃ ደረስን አሸነፍን የሚሉ ሰዎች ከታች ያሉ ሰዎቾን የመናቅ ያለማክበር ሁኔታ ይታያል ይህ ግን ትልቅ ችግርና ያልተሟላ አሸናፊነት ብሎም ለወደፊነቱ ወደ ተሸናፊነት የሚወስድ መንገድ ነው ፡፡ አሸናፊ እራሱን ያከብራል ደግሞም ያስከብራል ብሎም ደግሞ ሌሎችን አክብሮ ያስከብራል ፡፡

7.Self Discipline / ስርአት መኖር

ይህ በተግባር የሚገለፅ የአሸናፊነት ባህሪ ነው ። በዚህ ዘመን ብዙ ሰው የወሬ እንጂ የስርአትና የተገባር ሰው አይደለም ከላይ አመራር ጀምሮ እስከታች ድረስ ብዙ ጊዜ ወሬ እንጂ ስርአትና / ተግባር አይታይም ፡፡ ጠንካራ ልምምዶችን እንደ ልምድ አድርጎ በተግባር አለመግለፅ አሸናፊ እንዳንሆን ያረገናል ፡፡ ለምሳሌ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ብንመለከት ልምምዳቸውን በየጊዜው በስርአት ካልሰሩ ብዙ ሽንፈት ሊገጥማቸው ይችላል ፡፡

8.Self Talk / ከራስ ጋር ማውራት (ጊዜ መውሰድ)

አሸናፊዎች ሁልጊዜ የሚራራጡ ፣ እረፍትና እርጋታ የሌላቸው ፣ ሁሌ ሳያቋርጡ የሚሰሩ አይደሉም ፡፡፡ይልቁንስ በቂ ሰአት ስራቸው ላይ የሚያጠፉ እንዲሁም ተመጣጣኝ ጊዜ ደግሞ ለራሳቸው የሚሰጡ ፣ ነገሮችን በትኩረት ረጋ ብለው የሚያስቡ (ሳይጨነቁ ነገሮችን የሚያወጡ የሚያወርዱ) ናቸው ፡፡ ከራሳቸው ጋር በቂ ጊዜ የሚወስዱ ሰዎች ሁሌ ከውጥረት ብሎም ከጭንቀት ራሳቸውን ያስመልጣሉ ፡፡

9.Complete person / ሙሉ ሰውነት

ትክክለኛ አሸናፊ ሰው አንድ ወገን ብቻ ያደገ ፣ ሌላው ጎኑ የጎደለ ሳይሆን በሙሉ ማንነቱ የሞላ ያሸነፈ ነው ፡፡ ሕይወት ትምህርት ጥሩ ውጤት ማምጣት / ሩጦ 1ኛ መውጣት ፣ ተዋግቶ ማሸነፍ ፣ በሀብት ትልቅ ደረጃ መድረስ ብቻ አይደለችም ፡፡ አንዳንድ ሰው በገንዘብ አቅሙ ትልቅ ደረጃ ይደርስና በማህበራዊ ሕይወቱ ደግሞ 0 ይሆናል ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰው ሙሉ ሰው አንለውም ፡፡

#ሙሉ ሰውነት ላይ ወደፊት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይዤ እቀርባለሁ ፡፡

10.Live in the present/ አሁንን መኖር

ይሄ ብዙዎች አሸናፊ እንዳይሆኑ የሚያረግ የአመለካከት ችግር ነው ፡፡ ነገራችንን በሙሉ በነገ ተስፋና በትናንት ፀፀት / ወቀሳ ዛሬ ላይ በደንቡ ሳንኖር በሀዘን እንዘልቃለን ፡፡ አሁንን በአሸናፊነት ሀሳብ/ አመለካከት ሳንኖር የነገን ያልተጨበጠ ድል በማለም በተስፋ ብቻ እንደክማለን ፡፡ ስለዚህ አሸናፊ ለመሆን የሚያስብ ሰው አሸናፊነት ስለ ነገና ስለ ወደፊት ሳይሆን ስለ አሁን ነው ፡፡


አሸናፊነት የሚጀምረው ከአስተሳሰብ ነውና አስተሳሰባችሁን ቀና ፣ በጎ ፣ ጥሩ ጥሩውን ማድረግ ጀምሩ ፡፡ አሉታዊ አስተሳሰባችሁን በአወንታዊ ሀሳቦች ለውጡ ፡፡

ይቀጥላል...

#መልካም_ቀን!
@Psychoet

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
ክፍል 30
የአሸናፊነት ሕይወት (ክፍል 3)
በናሁሰናይ ፀዳሉ

በእርግጥ አሸናፊነት በዋነኛነት ከራሳችን ጋር የሚደረግ ውድድር ቢሆንም በሕይወት ዘመናችን ግን ብዙ ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚደረጉ ውድድሮች ይኖሩናል ፡፡ ለምሳሌ ፦ በትራክ / በጎዳና የሚሮጡ እሯጮች የሚያሸንፋት ከሌሎች ተወዳድረው ቀድመው በመግባት እንጂ ከራሳቸው ጋር ተወዳድረው አይደለም ።
እግር ኳስ ተጫዎቾች አሸናፊ የሚባሉት ከሌሎች ተጋጥመው በሚያስቆጥሩት የበለጠ ጎል እንጂ ባላቸው የኮከብ ተጫዎች ብዛት አይሆንም ፡፡

በጦር ሜዳ ላይም የሚደረግ ፍልሚያ አሸናፊው ማን የበለጠ የጠላትን ድንበር / ወሰን ተቆጣጠረ / ብዙ ሰው ማረከ በሚል ነው ፡፡

በትምህርት ገበታችን 1 ኛ ወጣን የምንለው ከሌሎች በልጠን እንጂ 100 ስላመጣን አይደለም ፡፡

በንግድ ቦታ አሸናፊ የምንሆነው ከሌሎች ተመሳሳይ ነጋዴዎች የተሻለ ብዙ ደንበኛ ፣ ብዙ ሽያጭ ፣ ጥሩ ገቢ ስናገኝ ነው ፡፡

ስለዚህ አሸናፊነት ውድድርም መሆኑን መገንዘብ አለብን ስለዚህ በነዚህ ውድድር እንድናሸንፍ ማረግ ካለብን ዋነኛ ነገሮች ጥቂቱት እንመልከት

1. ራሳችንን እንወቅ፦

ይሄ ዋናውና መሰረታዊው ነገር ነው ፡፡ አብዛኞቻችን ራሳችንን ደካማና ጠንካራ ጎናችንን ምን መስራት ፣ የት መስራት እንዳለብን በደንብ ስለማናውቅ መወዳደር በሌለብን ዘርፍ ስንወዳደር እንገኛለን ፡፡ ከዛም ሁሌ የምንፈልገውን / ያሰብነውን ውጤት ሳናመጣ እንከርምና መጥፎ የተሸናፊነት ስሜት ይሰማናል ፡፡

ለምሳሌ ፦ ጥሩ እግር ኳስ ተጫዎች ሩጫ ቢወዳደር አይደለም ማሸነፍ ላይጨርሰው ይችላል ፡፡ ራሱንና ችሎታውን አውቆ እግሮ ኳስ ቢጫወት ጥሩ ውጤት ሊያመጣ ይችላል ፡፡

ራሳችንን ለማወቅ ማረግ ያለብን ነገሮች በጥቂቱ
ሀ.መጸሐፍቶችን ማንበብና ዕውቀትን ማሳደግ
ለ. በዚህ ጉዳይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን መውሰድ
ሐ. ተረጋግቶ ስለ እራስ ማሰብና ለራስ በቂ ግዜ መስጠት
መ. ሌላ በዘርፉ የተሻሉ ሰዎችን ማማከር ...


ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን በቀጣዩ ክፍል አብራራቸዋለሁ _
2. ተጋ
ጣሚያችንን እንወቅ፦
3.ራሳችንን እናሻሽል
3. ካለንበት ምቹ የሚመስል የተለመደ ቀጠና እንውጣ፦
4. አሸናፊነት ያማልና ራሳችንን ለሕመም እናዘጋጅ፦
_

ይቀ
ጥላል...

#መልካም_ቀን!
@Psychoet

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
ክፍል 31
የአሸናፊነት ሕይወት (ክፍል 4)
በናሁሰናይ ፀዳሉ

ከሳምንት የቀጠለ ፡፡ ማሸነፍ የማይፈልግ ሰው የለምና እነዚህን መንገዶች ትተገብሩ ዘንድ እመክራለሁ ፡፡

2. ተጋጣሚያችንን እንወቅ፦

ይህ ለማሸነፍ አንዱ ወሳኝ ነገር ነው ፡፡ ከዚህ በፊት እንዳፃፍኩት ለማሸነፍ ውድድር ያስፈልጋል ውድድራችን ደግሞ ከራሳችን ጋር ብቻ ሳይሆን በዙሪያችን ካሉ ተመሳሳይ ሙያ ፣ ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ አካሎች ጋርም ጭምር ነው ፡፡ ስለዚህ የማሸነፊያ ሌላው ሚስጥር ስለ ተጋጣሚያችን / ተወዳዳሪያችን ጥሩ ግንዛቤና እውቀት ይዘን ወደ ውድድር መግባት ነው ፡፡ ይሄ ጥበብ አንድም እንዴት ነገሮችን መሰልጠን እንዳለብን ያሳስበናል ሌላው ደግሞ በውድድሩ መስክ ላይ ደግሞ ተጋጣሚያችንን እንዴት ማሸነፍ እንዳለብን እንረዳለን ፡፡

ለምሳሌ ፦ በጦርነት ወቅት ሰላዮች የሚላኩት የተቃራኒው ጦር ስላለው ድክመት እና ጥንካሬ ለመሰለል እንዲሁም ይህን ተጠቅሞ ተቃራኒን ሀይል በቶሎ ለማሸነፍ ነው ፡፡ በንግድም ዘርፍ የሚፎካከረን ነጋዴን ዋጋ በተለያዩ መንገዶች ካወቅን በኀላ በምን መንገድ ገበያውን እንደምንይዝ እናስባለን ፡፡


3.ራሳችንን እናሻሽል

ሌላው ምንም አይነት የችሎታ ፣ የአቅም ሁኔታ ቢኖረን ሁሌ ለመማር ፣ ለመለወጥ ፍላጎትና ተነሳሽነት ይኑረን ፡፡ ብዙ ሰው ለመለወጥ ዝግጁ ስላልሆነ ሁልጊዜ በአንድ መንገድ ሲሰራ ሕይወቱ እየተሻሻለሳይሆን እየደከመ ይሄዳል ፡፡ ስለዚህ ማሸነፍ ከፈለግን ራሳችንን በስልጠናዎች ፣ በትምህርቶች እንለውጥ ፡፡ Software ራሱ ቀየጊዜው Update ይደረጋል ብዙ ሰዎች ግን አንዴ የሆነ መንገድ ከጀመርን Update መሆን ስለማንፈልግ አሸናፊ መሆን ቀርቶ አሸናፊ ከሆንበት መድረክ ተሸንፈን እንወርዳለን ፡፡
         

3. ካለንበት ምቹ የሚመስል የተለመደ ቀጠና እንውጣ፦

4. አሸናፊነት ያማልና ራሳችንን ለሕመም እናዘጋጅ፦
አሸናፊነት ቁጭ ብሎ አልጋ በአልጋ ስለማይመጣ ሁላችንም ምንም ቢከብድ ፣ ቢያስቸግር ጠንክረን እንስራ ሯጮች አንድን ሩጫ ለማሸነፍ ስንት ጉዳት ደርሶባቸው ፣ ስንቴ ወድቀዉ ተሰብረው ስንቴ ተስፋ ቆርጠው ፣ እኛ ለሊት አልጋ ላይ ስንፈላሰስ እነሱ በብርድና በዝናብ በለሊት ሲሮጡ ብዙ ህመም አይተው ነው ለአሸናፊነት የሚደርሱት፡፡ ስለዚህ ተቀምጦ በምኞት ብቻ አሸናፊነት የለም ተነስታችሁ ለአሸናፊነት ጠንክራችሁ ስሩ ፡፡

_
መል
ካም ሳምንት!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ


🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
ስለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን!🙏
PhD in Leadership and Management

“መድረሻህን ሳታልም ጉዞ አትጀምር ፤ መኖርህን ሳታውቅ አትሙት።” ╔ሜ╗╔ሎ╗╔ሪ╗╔ና╗
መልካም የእናቶች ቀን
❖አንባቢ እናት ጥሩ ትውልድን ትገነባለችና ይቺን የመሰሉ እናቶች ይብዙልን ፡፡ ፎቶው የተላከልኝ ከወደ አዋሳ ነው ፡፡
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖
ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ የሕይወት ምክሮችና እውነታዎች
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖

📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

📕በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡

📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡


መልካም የእናቶች ቀን

www.tg-me.com/psychoet
*ሜሎሪና እና ቴሎስ*
በናሁሠናይ ፀዳሉ
በእነሆ መጻሕፍት ያገኟቸዋል።

‹‹ሰው የሚሞተው ሥጋው ነፍሱን መሸከም ሲያቅተው ነው፡፡ ሥጋችን ደግሞ የሚያረጅም የሚበላሽም ነው፡፡ ነፍስ ልትሞት ካልቻለችና የሚሞተው ሥጋችን ከኾነ፣ ለምን ለነፍሳችን የማያረጅና የማይሞት ሥጋ አንሠራላትም? ብለን እየጣርን ነው››፡፡


እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ
4ኪሎ ምኒልክ ት/ቤት ፊት ለፊት ከሮሚና ዝቅ ብሎ።

ሥልክ፦ 0912735000
            0905222224

ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል።

https://www.tg-me.com/enhobooks
https://www.tg-me.com/enhobooks
https://www.tg-me.com/enhobooks
ሰላም ቤተሰቦች፣
ስንጠብቀው የነበረው የ"ሜሎሪና" መጽሐፍ 3ኛ ክፍል በቅርብ ይወጣል። ርዕሱ ምን ይመስላችኋል? በትክክል ለገመተ መጽሐፉ ሲወጣ ከፊርማ ጋር በስጦታ ይበረከትለታል።
"ሜሎሪና -----"
Three stories to boot:
1. Nokia refused Android
2. yahoo rejected google
3. Kodak refused digital cameras
Lessons:
1. Take chances
2. Embrace the Change
3. If you refuse to change with time, you'll become outdated

Two more stories:
1. Facebook takes over whatsapp and instagram
2. Grab takes over Uber in Southeast Asia
Lessons:
1. Become so powerful that your competitors become your allies
2. Reach the top and eliminate the competition.
3. Keep on innovating

Two more stories:
1. Colonel Sanders founded KFC at 65
2. Jack Ma, who couldn't get a job at KFC, founded Alibaba and retired at the age of 55.
Lessons:
1. Age is merely a number
2. Only those who keep trying will succeed

Last but not least:
Lamborghini was founded as a result of revenge from a tractor manufacturer who was insulted by Ferrari founder Enzo Ferrari.
Lessons:
Never underestimate anyone, Ever!
✔️ Just keep working hard
✔️ Invest your time wisely
✔️ Don't be afraid to fail
በቀጣይ ሳምንት ለንባብ ይበቃል
ሜሎሪና ቁጥር 3 💚💛❤️
እየመጣ ነው...
እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችኹ?


እንዲያው በተለምዶ "ሕይወት እንዴት ነው?" ተባብለን እንጠያየቃለን። ግን ለእናንተ 'ሕይወት' ማለት ምን ማለት ነው?

@psychoet
ትልቁ ብቸኝነት ሰውን ማጣት ሳይኾን ራስን ማጣት ነው። በምድር ላይ ራሱን እንዳጣ ሰው ብቸኛ የለም።


ሜሎሪና - ሕይወቴ
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ከሜሎሪና መጽሐፍ የወጡ ሀሳቦች
- መጽሐፉን አንብባችሁ ፎቶዎችሁን ከማስታወሻ ጽሑፍ ጋር ላኩልን

📕‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››
“Dirreen lolaa inni guddaan sammuu namaati, Injifannoo guddaan of mo’uudha

📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡

📕‹‹... በምድር ላይ የሚወዱትን ሰው በሞት እንደመቀማትና ተስፋ ያደረጉትን እንደማጣት ትልቅ ህመም የለም፡፡ ሲደጋገም ደግሞ ሐዘን፣ ሥቃይ፣ ችግርና መከራ እንደመጫሚያና ልብስ አጥልቀዋቸው የሚዞሩ ያህል ይሰማል፡፡››

📕የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡ ለካስ እስር ቤት ቦታ ሳይኾን አስተሳሰብ ነው፡፡ በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል፡፡

@psychoet
ሠላም ወዳጆች፥ "ሜሎሪና- ሕይወቴ" የተሠኘው 3ኛ መጽሐፌ የፊታችን ቅዳሜና እሑድ በራስ አምባ ሆቴል ስለሚመረቅ  እንዲገኙ በአክብሮት እጋብዛለሁ።

ቀን: ነሀሴ 11 ( ከጠዋት 2 - ምሽቱ 2 ሰዓት ) እና ነሀሴ 12 (ከጠዋቱ 4- ምሽቱ 2 ሰዓት) ባመቻችሁ ሰአት በመገኘት መጽሐፉን ከደራሲው በአካል ማግኘት ትችላላችሁ።

ቦታ: ራስ አምባ ሆቴል ( ከ4 ኪሎ ወደመገናኛ በሚወስደው መንገድ ላይ፣ የመጨረሻ ፎቅ ላይ) https://maps.app.goo.gl/V6u4r8vMw2m5cxPH8?g_st=ac

መጽሐፉን በብዛት ለምትፈልጉ 0912664084 መደወል ትችላላችሁ
www.tg-me.com/psychoet
2024/09/26 22:10:36
Back to Top
HTML Embed Code: