Telegram Web Link
ዝም ማለትን ብንለምድ!

“ለሰው ልጅ አንደበቱን ከፍቶ መናገርን ለመማር ሁለት አመት ብቻ ነው የሚፈጅበት፣ ይህንን አንደበቱን መዝጋትን ለመማር ግን ከ60 አመታት በላይ ይፈጅበታል” – Ernest Hemingway

1. በተናደድን ጊዜ በረድ እስከምንል ድረስ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

2. የአንድን ሁኔታ ሙሉ ታሪክ በማናውቅበት ጊዜ በግምት ከመናገር ይልቅ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

3. መናገር የፈለግነውን ነገር ብንናገረው የተፈጠረውን ሁኔታ ለመለወጥ ምንም መዋጮ እንደማይኖረው ሲገባን ዝም ማለትን ብንለምድ፣

4. ስሜታዊነታችን ከምክንያታዊነታችን በልጦ ሲገኝ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

5. በተናገርነው ቁጥር የተናገርነውን ነገር በመጠቀም ሁኔታውን የሚያባብስ ሰው ሲያጋጥመን ዝም ማለትን ብንለምድ፣

6. አንዴ የተነገረ ነገር የት ሊደርስ እንደሚች ስለማናውቅ በሰዎቹ ፊት የማናወራውን ነገር ሰዎቹ የሌሉበትን እየጠበቅን ከማውራት ይልቅ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

7. በማያገባንና ባልገባን የሰው ነገር ላይ ዝም ማለትን ብንለምድ፣

አብዛኛው ችግራችን ይቀረፍ ይሆን?

©Dr eyob
#ክፍል_10
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE
#LOVE_Styles / #የፍቅር_አይነቶች
___
ዛሬ የሳይኮሎጂ 10 ኛ ትምህር
ታችንን ወጣ ባለ ርዕስ ላይ ነገር ግን ለሁላችን አስፈላጊና ወሳኝ ስለሆነው ስለ ፍቅር እንወያያለን ፡፡

ፍቅር በተለያዩ ሙያዎች አንፃር በተለያየ መንገድ ተተርጉሟል ፡፡ Social psychology (በማህበራዊ ሳይኮሎጂ ) አንዱን ትኩረቱን በዚህ ላይ በማረግ የተለያዩ የፍቅር ትርጉም ፣ አይነት ... ላይ ያተኮሩ ጥናቶችን ያበረክታል ፡፡

በአጠቃላይ ስናየው ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ቶሎ በፍቅር ይወድቃሉ ሴቶች ደግሞ ተግባራዊ ጓደኛነትን መሰረት ባደረገ ፍቅር ይሳባሉ ፡፡ ፍቅር በብዙ መንገድ ተተርጉሟል ። ከነዚህ በጥቂቱ

*ለሰው ከዝምድና / ከቅርበት የተነሳ ያለን ጥልቅ ስሜት
*ከፆታዊ ፍላጎት ምክንያት ያለ መሳሳብ ወዘተ ......
___
ይህ ብዙ ትርጓሜ ያሉት ፍቅር
ስድስት አይነት የፍቅር አይነቶች /ዘይቤዎች / እንዳሉት ማህበራዊ ሳይኮሎጂስቶች ይናገራሉ ፡፡ እነዚህም

1.Eros-ኤሮስ ፦ለኛ ልዩ ውበት ያለውን ሰው በማየት የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ።

በዚህ ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ገና እንዳዩ የሚሰማ ጥልቅ የፍቅር ስሜት ነው ፡፡

2.Storge-ስቶርጄ :- ይህ ደግሞ ከጓደኛነት የተነሳ የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር የሚመነጨው በመለማመድ ፣ በመቀራረብ ፣ አብሮ ጊዜ በማሳለፍ ነው ፡፡

3. Ludus-ሉደስ ፦ ፍቅርን በጨዋታ መልክ የሚገለፅበት ዘይቤ ነው ፡፡

በዚህ #ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር በብዛት በማማለል የሚፈጠር ሲሆን ስራዬ ተብሎ ያልተያዘ ፍቅር ነው ፡፡


4. Mania-ማኒያ ፦ እጅጉን በኔነት ስሜት የሚያፈቅሩና ፍቅራቸውን በብዙ መከራ ራሱ የማይጥሉበት የተወሰነ ጊዜ የተቆጠረበት የፍቅር ግንኙነት ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።


5. Pragma- ፕራግማ ፦ ይሄ ደግሞ በምክንያት የተደገፈ ፍቅር ሲሆን በባሕሪ ፣ ባስተሳሰብ የሚመስለንን ሰው የምናፈቅርበት ዘይቤ ነው ፡፡

በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።

6. Agape- አጋፔ፦ይህ የፍቅር አይነት ያለአንዳች ምክንያት የምናፈቅረውን ሰው ከራሳችን በላይ የምናስቀምጥበት ነው ፡፡
ይህ የፍቅር ብዙ ጊዜ ከእምነት ጋር ይያያዛል ፡፡ እንደዚህ የሚያፈቅሩ ሰዋች ፍቅረኛዬ ከሚጎዳ እኔ ልጎዳ ፣ ከሚቸገር እኔ ልቸገር የሚሉ ናቸው ፡፡

#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

__

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet 👍

፠፠__፠፠

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet 👍

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠__፠፠
ማንን እንደምናፈቅር የምናውቅበት መለኪያ ፡፡ ባሉት ክፍት ቦታዎች የሚሆነውን ስም ብቻ ጻፉና ብዙ ስሙን የጻፋችሁትን ሰው ❤️ አለ ማለት ነው ፡፡
እስኪ መልሱልኝ ወዳጆቼ?
🚫
ከጥቂት አመት በፊት በካንሰር ምክኒያት ያረፈች ጓደኛዬ ከመሞቷ በፊት የጻፈችልኝ ነበር።

መኖራችን ለሌሎች ድጋፍ ምክኒያት ሲኾን ደስ ይላል። በቅርብ ከክፍያ ነጻ በአካል የማማከር ጊዜ ስለማመቻች ምክር የምትፈልጉ ወዳጆቼ ወደፊት በማስቀምጠው አድራሻ የምታገኙኝ ይኾናል። ሕይወትን በጋራ በሳቅና በለቅሶ እንታገላለን። ❤️

እወዳችኋለሁ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_11   #SHARE
#በቤተሰብ አባል ውስጥ የሥነ-ልቦና መታወክ ሲያጋጥም ምን እናድርግ?

የስነ-ልቦና ወይም የስነ-ባህሪ መታወክ በሀገራችን ትኩረት ካልተሰጠባቸውና የህክምና ዘዴው (psychotherapy) ካልተስፋፋባቸው ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በባህላዊና በሃይማኖታዊ ድጋፎች ማኅበረሰባችን ከዚህ ችግር ጋር እየተጋፈጠ ቢሆንም፣ ዋናው ጫና የዚህ ችግር ተጠቂ ከሆኑ የቤተሰብ አባላት ላይ ነው፤ምክኒያቱም እንደሰለጠነው ዓለም የህክምና ፤ ድጋፍና እንክብካቤ ሰጪ  ቦታዎች ስለሌሉን ነው፡፡ ይህን ችግር ለማቃለል እየተንቀሳቀሱ ካሉት አገር በቀል ድርጅቶች ውስጥ አንዱ መቄዶኒያ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ስለሚሰሩት ስራ ያለኝን አድናቆት ሳልጠቅስ አላልፍም፡፡እናንተም የተቻላችሁን ድጋፍ አድርጉላቸው፡፡

ከዚህ በመቀጠል የስነ-ልቡና መታወክ ችግር ያጋጠማቸው የቤተሰብ አባላት ይህን ተግዳሮት ለመቋቋም ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን በዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽሐፍ መነሻነት ይጠቅማሉ ያልኳቸውን ነጥቦች አነሳለሁ፡፡ መልካም የንባብ ጊዜ!
___
#ለበሽታው_ያለንን_ግንዛቤ_ማሳደግ ፡-

ስለታመመብን ሰው የስነ-ልቡና መታወክ አይነት፣ መንስኤ፣ ምልክቶች፣ ስለሚያባብሱ ሁኔታዎችና ነገሮች እራስን ማስተማር፡፡ ስለታመመው ሰው የስነ-ልቡና ወይም የስነ-ባህሪ ችግር የተሳሳተ መረጃ ካለን ወይም ስለ ምልክቶቹና ስለሚያባብሱ ጉዳዮች ዝቅተኛ ግንዛቤ ካለን ግለሰቡንና ቤተሰቡን በአጠቃላይ ሊጎዳ የሚችል ተግባር ልንፈጽም እንችላለን፡፡

#ለምሳሌ እስኪዞፍሬኒያ (Schizophrenia) ያለባቸው ግለሰቦች ስለሚታያቸው አስፈሪ ግን በገሃዱ አለም የለለ ምስል (hallucination) ምንም ግንዛቤ ከሌለን፤ በተገቢው ተጠቂዎችን ላንረዳቸውና አግባብነት ያለው ምላሽ ላንሰጥ እንችላለን፡፡

#በለሌላ ምሳሌ በከፍተኛ ድባቴ (Depression) ውስጥ ያሉ ግለሰቦች አጥብቀው እራስን ስለማጥፋት (suicidal ideation) ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ይህ ሃሳብ በዝርዝር እራሳቸውን እንዴት፣በምን፣የትና እራሳቸውን እነደሚያጠፉና የመሳሰሉትን በዝርዝር ማሰላሰልና ሙከራ ማድረግን ሊያካትት ይችላል፡፡ ስለዚህ እድብታ ወደ እንደዚህ አይነቱ የስነ-ልቡናና የስነ-ባህሪ ዝንባሌ ሊወስድ እንደሚችል በቂ እውቀት ከሌለን፤ በዚህ የሚሰቃይ ቤተሰባችን፣ጓደኛችን፣ፍቅረኛችንን እንዲሁም የስራ ባልደረባችንን በተገቢው መንገድ መርዳት አንችልም፡፡ አንዳንዴም ለምን ስለማይጠቅም ነገር ታስባለህ እና የመሳሰሉትን ትችቶች በመስጠት ግለሰቡን እንኮንናለን፡፡ ስለሆነም በግለሰቡ ላይ የምናያቸው እንግዳ ባህሪያትና አስተሳሰቦች ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጭ ስለመሆናቸው መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ግለሰቡ የስነ-ልቡና ችግር ያለን ግንዛቤ ለግለሰቡ ለምንሰተጠው እርደታ፣ግለሰቡን የምንረዳበትን እይታ፣እንዲሁም ለራሳችን ደህንነት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ምክኒያቱም የቤተሰብ አካል ጓደኛ ወይም ፍቀረኛ የስነ-ልቡና ችግር ሲያጋጥም የኛ ደህንነት ላይም ተጽዕኖ ስለሚያደርስ፡፡

➋ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን ማፈላለግ፡-

ስለ ግለሰቡ የስነ ልቡና ችግር ሳይንሳዊ ግንዛቤ ለመጨበት ትክክለኛ ምንጮችን መከተል ይገባናል፡፡ ምንም እንኳን በሀገራችን ቋንቋንዎች የተጻፉ ሳይንሳዊ መሰረት ያላቸው መጽሀፍት ባይኖሩም፣ የእንግሊዚኛ ችሎታ ካለን በእንግሊዚኛ የተጻፉ ሳይንሳዊ መጽኃፍትን ወይም ታእማኝነት ያለቸውን ድህረ-ገጾች መጠቀም፡፡ እንዲህ ስል በእንግሊዚኛ ስለተጻፈ ብቻ ጠቃሚ ነው ማለቴ ሳይሆን እነደ ዕድል ሆኖ ሳይንሱ በምዕራቡ አለም ስለተስፋፋ ብዙ ሳይነሳዊ የሆኑ መጽሀፍት በእንግሊዚኛ ቋንቋ ስለተጻፉ ነው፡፡ ስለዚህ የሀገራችን ሳይኮሎጂስቶችና ሳይካቲሪስቶች ብዙ የቤት ስራ አለብን፡፡ ምርምር ከመመረቂያ ጽሁፍ በላይ መሆን አለበት፡፡ (እዚህ ጋር ላቋርጣችሁና… የኛ አላማ ይህን ክፍት መሙላት  የሚችል በስነ-ልቡና ችግሮችን፣ ትዳርን፣ ፍቅር፣ የልጅ አስተዳደግን፣ ትምህርት ነክና ለሌች የስነ-ልቡና ጉዳዮችን የሚዳስስ ሳይንሳዊ መሰረት ያለቸውን መረጃዎች ለናንተና በውጭ ሀገር ላሉ አዳማጭ ላጡ ወገኖቻችን አማራጭ ማቅረብ ነው፡፡ ስለዚህ ለወደፊት ስለተለያዩ የስነ-ልቡና ችግሮች መንስኤ፣ምልክት፣የመጀመሪያ እርዳታ እንዲሁም ዕርዳታ እንዴት ማግኘት እነደምትችሉ የተደራጀ መረጃ በዌብሳይታችን እናቀርባልን)፡፡ወደ ወናው ሃሳብ ስመለስ ስለስነ-ልቡና ችግሮችና መፍትሄዎች የተነገሩ ወይም የተጻፉ ነገሮች ሁሉ ትክክል ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በጋዜጦችና መጽሄቶች የሚነገሩ ነገሮችን በባለሙያተኞች የሚነገሩ ከሆኑ እንደ ግብአት መውሰድ ይቻላል፡፡ በጥቅሉ ሳይንሳዊ ዳራ ያለቸውን ታማኝ ምንጮችን ተጠቀሙ ምክሬ ነው፡፡

➌የእርዳታ ምንጮችን መፈለግ፡-

የስነ-ልቡና ችግርን በሀገራችን ካሉ ሌሎች በሽታዎች ለየት የሚያደርገው የበሽታው ተጠቂዎች ላይ የሚደርሰው አድሎና መገለል አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ምክኒያት ከማህበረሰቡ ከሚገኙ ድጋፍ ይልቅ አድሎው የሚያመዝንበት ሁኔታ አለ ምንም እንኳ የተለያዩ የሀይማኖት ተቃማት የራሳቸውን ድጋፍና እንክብካቤ ለተጠቂዎች የሚያደርጉ ቢኖሩም፡፡ በዚህም ምክኒያት የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስለ በሽታቸው ከሌሎች ግለሰቦች የመወያየትና ድጋፍ የማግኘት እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ እናም የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ግለሶቦች ቤተሰቦች ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ሌሎች ቤተሰቦች ጋር መወያየትና ሀሳብ መለዋወጥ ልምድ ከማካፈል በዘለለ ስለሚደርስባቸው ተግዳሮቶች ማውራታቸው የተወሰነም ቢሆን ስለጉዳዩ የሚሰማቸው ጭንቀት ቅልል ሊልላቸው ይችላል፡፡ ይህ እንግዲህ ፈረንጆቹ support group የሚሉት አይነት ነገር ነው፡፡ እዚህ ጋር ማንኛቸውም ሊጠቅሙ የሚችሉ ባህላዊና፣ ሀይማኖታዊ፣መንግስታዊ እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ከስነ-ልቡና ችግር ጋር በተገኘ እርዳታ የሚሰጡ ተቋማትን ማፈላለግ፡፡

__
(በአሸናፊ ካሳሁን)
🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀
🎊🎉🎀🎊🎉🎀

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በመንግሥት ከተመደቡለት ተማሪዎች በተጨማሪ ባሉት ክፍት ቦታዎች በተወሰኑ የትምህርት መስኮች #የግል_አመልካቾችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

አመልካቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦

1. በ2015 አና 2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ፣

2. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) በመውሰድ የሚቀመጥን መቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ፣

3. በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተምራችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ፣

4. ዩኒቨርሲቲዉ በ12ኛ ብሔራዊ ፈተና ውጤት መሠረት ድልደላ ሲያካሒድ አመልካቾች በመረጡት የትምህርት ፕሮግራም አማራጮች ውስጥ ለመደልደል ውጤታቸው ካላበቃቸው ዩኒቨርሲቲው ወደፊት በሚያደርገው ድልደላ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ተወዳድረው ለመደልደል ፈቃደኛ የሆኑ፣

5. ለጤና የትምህርት ዘርፎች ዩኒቨርሲቲው የሚጠይቀውን ተጨማሪ ምዘና ማለፍ የሚችሉ፡፡

የማመልከቻ ቀናት፦ ከህዳር 20 እስከ 26/2016 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ፦ ህዳር 28 እና 29/2016 ዓ.ም

የቅድመ-ምረቃ የትምህርት መስኮችን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፦
http://www.aau.edu.et/blog/admission-of-self-sponsored-students-in-the-regular-undergraduate-program-for-the-2023_24-academic-year/

ለተጨማሪ መረጃ፦
http://aau.edu.et or https://portal.aau.edu.et
ሀሙስ #10

የቤት በርዎን መቆለፍና አለመቆለፍዎን ከልክ በላይ ያረጋግጣሉ?

Obsessive compulsive disorder (OCD) ከ anxiety(ጭንቀት) የስነ-ባህሪ መዛባት ክፍል የሚመደብ ሲሆን፤ ከቁጥጥር ውጭ ተደጋግሞ በሚከሰት አስጨናቂ ሀሳብና፤ ይህ ምክኒያታዊ ያልሆነ ሀሳብ የሚፈጥረውን ስጋት ለመከላከል በሚደረግ ድርጊት፣ባህሪ ወይም የአእምሮ ምላሽ ይታወቃል፡፡

ለምሳሌ ከብዙ በትንሹ፤ የዚህ አይነት ዝንባሌ ያለባቸው ግለሰቦች ከልክ በላይ በበሽታ እለከፋለው ብሎ በመስጋት በተደጋጋሚ እጅን መታተጠብ፡፡ በቀን ከ60ና ከዛ በላይ እጃቸውን በሳሙና ሊታጠቡ ይችላሉ፡፡ እዚህ ጋር ንጽኅናቸውን የሚጠብቁ ሰዎች ሁሉ በዚህ መዛባት ውስጥ ይመደባሉ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ፍርሀት ወለድ የሆነ ከልክ በላይ የሆነውን ነው፡፡ ከዚህ አይነቱ የስነ-ባህሪ መዛባት ጋር ተዛማጅነት ያለው የስብዕና መዛባት አይነትም አለ፡፡ በጥቅሉ አብዛኞቻቸን መጠኑ አይብዛ እንጅ የዚህ አይነት ባህሪ ሊኖረን ይችላል፡፡ ለምሳሌ የቤት በራችንን መቆለፍና አለመቆለፋችንን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል፡፡

እንዲህ አይነቱ ባህሪ የእለት ተለት ህይዎታችን ላይ ጣልቃ የሚገባ ከሆነ መፍትሄ መፈለግ ይበጃል፡፡ መጠኑ የበዛ ሲሆንና ኑሯችንን በአግባቡ መምራት እንዳንችል ጣልቃ ሲገባ የተላያዩ የህክምና ዘዴዎች አሉት፡፡ በተለይ ሳይኮቴራፒ ይመከራል፡፡ እንደዚህ አይነቱን የባህሪ መዛባት ለመቀልበስ በሳይኮቴራፒ ከሚመከሩ ተግባሮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው፤ ከቁጥጥር ውጭ የሆነው አስጨናቂ ሀሳብ በሚመጣ ወቅት፤ ሀሳቡን ከመሸሽ ይልቅ መጋፈጥና ምንም አይነት ምላሽ አለመስጠት መፍትሄ ነው፡፡

ለምሳሌ ፦ ከምግብ በኋላና በፊት ልክ እንደማንኛውም ሰው ከታጠብን እንዲሁም ምንም ለጤና አስጊ ነገር በእጃችን እስካልነካን ድረስ፤ በበሽታ እለከፋለሁ የሚለው ከቁጥጥር ውጭ የሆነው ሀሳብ ሲመጣ፤ በፍጹም አለመታጠብ ማለት ነው፡፡የቤት በራችንንም አንዴ ከቆለፍን እንደዛው ደጋግመን አለማረጋገጥ ማለት ነው፡፡

ጥናቶች እነደሚያሳዩት ይህ በሚሆን ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ በሆነው በአስጨናቂው ሀሳብና በምንሰጠው ምላሽ መካከል ያለውን ቁርኝት ይቀንሰዋል ወይም ያላላዋል፡፡ በተጨማሪም ሀሳቡን መጋፈጣችን (exposure) ለሀሳቡ ያለንን ፍራቻ ይቀንሰዋል፡፡ የፍርሃት መጠኑ በሚቀንስበት ጊዜ ሀሳቡ በአምሯችን ላይ ያለው ሀይል ይቀንሳል፡፡ በዚህም ምክኒያት በሀሳቡ ላይ ያለን ትኩረትም በዛው ልክ ይቀንሳል፡፡ አንድ ሀሳብ ለሌላ ሀሳብ መሰረት ሲሆን ፤ የዚህ ቅጥልጥሎሽ አጠቃላይ ስሜታችንን ይወስናል፡፡

©zepsychologist
አሸናፊ ካሳሁን

@Psychoet
#ክፍል_12
(በአሸናፊ ካሳሁንና ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ ) #SHARE
#በቤተሰብ አባል ውስጥ የሥነ-ልቦና መታወክ ሲያጋጥም ምን እናድርግ?

........ከቅዳሜው የቀጠለ
የስነ-ልቡና መታወክ ችግር ያጋጠማቸው የቤተሰብ አባላት ይህን ተግዳሮት ለመቋቋም ምን ማድረግ አለባቸው ፦
___________
➍ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ተስፋ መሰነቅ
፡-

የስነ-ልቡና ችግር ላለበት ግለሰብ ካለን ፍቀር አንጻር ግለሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልካም ባህሪ አሳይቶ ወደ ጤናማ የዕለት ተለት እንቅስቃሴው ቢመለስ የሁላችንም ፍላጎት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፍላጎትና ለግለሰቡ የአእምሮ ጤና መሻሻል ያለንን ተስፋ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያላገናዘበና ከልክ ያለፈ መሆን የለበትም፡፡ ምክኒያቱም የስነ-ልቡና መታወክ በአብዛኛው ቀስ በቀስ እየተሻሻለ የሚሄድ እንጅ እነደ ሌሎች አካላዊ በሽታዎች በቅጽበት ስለማይድን ነው፡፡ ስለዚህ ለግለሰቡ መሻሻል ያለን ጉጉት ከልክ በላይ ከሆነ ግለሰቡ ላይ ሌላ ጫና በማሳደር የማባባስ ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ እንደጠበቅነው ሳይሆን ሲቀር ለኛ ለቤተሰቦችና ጓደኞችም ያለው የመንፈስ ስብራት ቀላል አይሆንም፡፡ ስለዚህ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገበናዘበ ከሆነ ለወደፊት ለሚከሰቱ ችግሮች የስነ-ልቡና ዝግጁነት ይኖረናል ማለት ነው፡፡

➎የእራስ ቁጥጥር መንፈስን ለግለሰቡ ማጎናጸፍ፡-

እንደየ ግለሰቡ የስነ-ልቡና ችግር መሰረት ግለሰቡ የእራሱን ህይወት እንዲቆጣጠር መገፋፋት፡፡ ግለሰቡ መፈጸም የሚችላቸውን ተግባራት በተቻለ መጠን እራሱ እንዲያከናውን መገፋፋት፡፡ ከሁሉም በላይ ግለሰቡን በክብርና ሰባዊነት በተመላበት ሁኔታ ማዋራት፡፡ ምንም እንኳን ግለሰቡ የሚያሳያቸው እንግዳ የሆኑ ምልክት ወለድ ባህሪያት ቢኖሩም ለሌሎች ሰዎች የምናሳያቸውን ሰብአዊነት የስነ-ልቡና ችግር ላለባቸው ሰዎችም ማሳየት ይኖርብናል፡፡ አንድ ጥያቄ ለእናንተ… አንድ ሰው የጨጓራ ህመም ቢያመው ትስቁበታላሁ፣ትሳለቁበታላችሁ? ታዳያ ለምን የስነ-ልቡና ችግር ላለባቸው ግለሰቦች ላይ?

➏ገደብ ማበጀት፡-

ምንም እንኳን ግለሰቡ የራሱን ህይወት በተቻለ ቁጥጥር እንዲመራ ቢበረታታም የምንሰጠው ነጻነት እንደየ ግለሰቡ ለማህበረሰቡና ለእራሱ ባለው ስጋት መሰረት ሊወሰን ይገባል፡፡ ግለሰቡ እራሱንና ሌሎች የማህበረሰቡ ክፍሎችን ሊጎዳ የሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ክብር የተመላበት ገደብ ማበጀት መልካም ነው፡፡

➐ የእኩልነት መንፈስን በቤተሰብ ውስጥ ማዳበር፡-

በቤተሰብ ውስጥ ባሉ ተግባራት ውስጥ ግለሰቡ በሚችል ከሆነ እንዲሳተፍ ማድረግ፡፡ ለምሳሌ የቤተሰብ አባላት ግለሰቡን ለመርዳት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውስጥ ግለሰቡን ከማግለል ይልቅ አሱም እንዲሳተፍ ማድረግ፡፡

➑እራስን ማረጋገት፡-

እራሳቸንን ካላረጋጋን ሌሎችን መርዳት ስለማንችል በተቻለን መጠን እራሳችንን ማረጋጋት ግድ ይለናል፡፡ የራሳችንን ህይወት በአጠቃላይ መዘንጋት ለምንረዳው ግለሰብና ለቤተሰባችን ጥሩ ውጤት አይኖረውም፡፡ ለዚያም ነው አንዳንዴ የቤተሰብ አባላት ተከታትለው ለዚህ ችግር የሚወድቁት ምንም እንኳን በዘር የሚተላለፉና በጋራ የቤተሰብ ሁኔታ ምክኒየት ሊሆኑ ቢችሉም፡፡ ስለዚህ እውነታወን በመቀበል ልክ እንደ ግለሰቡ ሁሉ ለእራሳችሁም ጊዜ መስጠት፡፡ ምክኒያቱም እናንተ ጤነኛ ካልሆናችሁ ሌሎችን መርዳት አትችሉምና፡፡

ማንኛውም ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ #Comment ላይ ጻፉልኝ?
__________

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀
🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet

ምንጭ ፦ Emotional survival guide for care givers ከሚለው የዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽኃፍ መነሻነት የቀረቡ

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀
#መልካም_ታህሳስ_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

አንድ ቀን ነገር ሁሉ ቀላል ይሆናል ! ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ለምትወዱት ጓደኛ #መልዕክቱን አስተላልፉ

@Psychoet
ሀሙስ #11

ሚዛናዊ ጤነኛ ሰው
#Share #Share በጣም ጠቃሚ የሆነ መልዕክት ነው

አለም አቀፉ የጤና ድርጅት WHO አለመታመም የጤነኝነት ምልክት አይደለም ይልና ጤናን እንዲህ ሲል ይተረጉመዋል፡፡ ሙሉ (Complete) አካላዊ ፤ አእምሮአዊ ፤ ማኅበራዊ ፤ ውስጠ ስሜታዊ (Emotional) እና መንፈሳዊ ደህንነት ነው ይለናል፡፡ ከተጠቀሱት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ ቢስተጓገል የጤና መታወክ እንዳለም ያስረዳናል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች እንዳሉ ሆነው የፖዘቲቭ ሳይኮቴራፒ ጽንሰ-ሃሳብ አመንጪ ፕ/ር ኖስራት ፖዘሽኪያን የሰው ልጅ ዕለት ተዕለት በሚኖረው ህይወት ውስጥና በዚህች ምድር ላይ እስካለ ድረስ ጤናማ ፤ ደስተኛና ስኬታማ ሆኖ እንዲኖር አራት መሰረታዊ ሚዛንነት ያላቸው ጉዳዮች ያስፈልጉታል፡፡ ውጤታማ ለመሆንም ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላው ሳይሸጋገር የምኞቱንና የፍላጎቱን ውጥን ማሳካት ይችላል ይላል፡፡ ከአብርሃም ማስሎ የፍላጎት ደረጃ በተቃራኒ (Hierarchy of needs)፡፡ አሁን ያለበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የአኗኗር ዘይቤን መቀየር ብቻ ወሳኝ መሆኑን ያስረዳል፡፡ እሳቤውም ሰዎች የዛሬውን ድካም ፤ አለመሳካት ፤ ጭንቀት ፤ ሰላም ማጣትን ብቻ እንዲያስቡ ሳይሆን የዛሬ አለመሳካትን ፤ ጭንቀትንና ጨለምተኝነትን እንደ አንድ ግብአት በመውሰድ ኃይልና ብርታትን አግኝተው ወደፊት ወይም ወደ ሚፈልጉበት አቅጣጫ መጓዝ እንደሚችሉ ነው፡፡ የዛሬ የጭንቀት ፤ የድካምና የልፋት እሳት የነገ ብርሃን እንደሆነ በማስረዳት፡፡

ፖዘቲቭ ሳይኮቴራፒ ሶስት መሰረታዊ የመርህ አምዶች ሲኖሩት ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሚዛናዊነት መርህ ነው (Principles of Balance)፡፡ ከተነሳንበት ነጥብ ጋር ተያያዥነት ስላለው የሚዛናዊነት መርህ ምን እንደሆነ በቀላሉ ለማስረዳት እሞክራለው፡፡

የሚዛናዊነት መርህ አራት ዋና ዋና ክፍሎችን በውስጡ አካቶ ይይዛል (አካል ፤ ስኬት ወይም ስራ ፤ ማኅበራዊነትና መንፈሳዊነት/ተስፍ)፡፡ አራቱም ክፍሎች በእኩል ሚዛናዊነታቸውን ጠብቀው ያለተቃርኖ አንዱ አንዱን እያገዘና እየደገፈ የግለሰቡን ማንነት ፤ ፍላጎት ፤ ደስታ ፤ ስኬት ጤነኝነት…ወዘተ ያስገኙለታል፡፡

ሀ. አካል (Body)

ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ሮጦ ህይወትንና ኑሮን ለመምራት አካላዊ ጤና ወሳኝነቱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ግን ስለ አካልህ ምን ይሰማሃል (ወፍራም ፤ ቀጭን ፤ ረጅም ፤አጭር፤ ብርቱ ፤ ደካማ ፤ አካል ጉዳተኛ ፤ ጤናማ…ወዘተ)? አካላዊ ማንነትህን ትቀበለዋለህ ወይስ የሆነ ለውጥ እንደሚያስፈልግህ ታስባለህ? አካልህን ትንከባከበዋለህ ወይስ ለዚህ ፈራሽ ገላ ብለህ ደንታ ቢስ ሆነሃል? ያገኘውትን ልብላ ዛሬ የሆንኩትን ልሁን አካሌ ኖረ አልኖረም አይደንቀኝም ትል ይሆናል፡፡ አካላዊ ሰላምና ጤና የሌለህ (ጉዳትም ካለብህ እውነታውን ተቀበልና ባለህበት ደስተኛና ውጤታማ መሆን ትችላለህ፡፡ በመጀመሪያ እራስህንና ማንነትህን ተቀበለው) ቢሆን እንኳ ግድ የለህም እራስህን መቀየርና መለወጥ ትችላለህ፡፡ አካላዊ ማንነትህ ሰላምና ጤናማ ሲሆን አእምሮህም መልካም ነገር ማሰብና መስራት ይጀምራል፡፡ ወይም በተቃራኒው እዩኝ ባይ ተሽቀርቃሪ ለአካላዊ ማንነትህ የምትኖርና የምትጨነቅ ብቻ መሆን የለብህም፡፡ አካልህ የማንነትህ አንድ መገለጫ እንጂ ሁለንተናህ እንዳልሆነ ተረዳ፡፡ በአጭሩ አካልህን ውደደው ተቀበለው ተንከባከበው መቀየር ወይም መለወጥ ያለበት አካላዊ ገጽታ ካለህ ጠንክረህ በመስራት ገጽታህን ለውጠው (በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወይም ለጤናህ ቅድሚያ በመስጠት)፡፡ አንተ ጡንቻ ብቻ ሳትሆን አእምሯዊ፤ መንፈሳዊ፤ ማኅበራዊም ሰው መሆንህን ልብ በል፡፡ ግን አሁንም አካልህን መንከባከብን አትዘንጋ (በሚዛናዊነት)

ለ. ስኬት/ስራ (Achievement)

በምትሰራው ስራ ወይም በተሰማራህበት ነገር ሁሉ ስኬታማ መሆንን ትሻ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ህይወት ስኬት ብቻ አይደለችም፡፡ የምትፈልገው የስኬት ወይም ውጤት ላይ ስትደርስ ምናልባት አእምሮህ ፤ አካልህ ፤ ማኅበራዊነትህና ተስፈኝነትህ ተዳክሞ ሊሆን ይችላል የደረስከው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛው ስኬት ላይ እንዳልደረስክ እወቅ፡፡ አንዱን ለማግኘት ስትል ሌላው ማንነትህን አጥተሃልና፡፡ ዛሬ ለብር ብቻ ብትሮጥ ብትለፍ ውሎ አድሮ ብርን ታገኝና በገንዘብህ ደግሞ ጤናን ለመሸመት ወደ ኋላ መሄድህ አይቀርም፡፡ ስራ መስራትና ገንዘብ ማጠራቀም ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን እራስን ጎድቶ ለገንዘብ ማደር ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ገንዘብህ ዋጋ የሚኖረው መጀመሪያ አንተ ስትኖር ነው፡፡ አንዴ አንተ ከጠፋህ ገንዘብ ሊያኖርህ አይችልም፡፡ ታመህ ጤናን ለመሸመት ከመሯሯጥ ሳትታመም አስቀድመህ ባለህ ነገር ጤናን መንከባከብ ይሻላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ስኬትንም ለማግኘት ደፋ ቀና ስትል በሚዛናዊነት መሆን አለበት፡፡ ትምህርትን ስታስብ መማርህን ብቻ ሳይሆን እየተማርክ በተጓዳኝ ማስኬድ ያለብህ ነገር ምን አንዳላ ተረዳና ከውነው (ጊዜህን ሙሉ በትምህርት ብቻ አሳልፈህ ወደ ኋላ ተመልሰህ ልታገኛቸው የማትችላቸው የህይወት ዘይቤዎቸ ስላሉ አስተውላቸው) ስኬት አካላዊ ፤ አእምሮዊ ፤ማኅበራዊና መንፈሳዊ/ተስፍ ዕድገትን አካታ ካልተገኘች ትናንት የቋመጥክለት ስኬት እርባና ቢስ ይሆንብሃል (ቤተሰብ የመመስረቻ ጊዜ….በነገራችን ላይ ቤተሰብ አለመመስረትም አንዱ የህይወት ዘይቤ ነው) ምክንያቱም በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ሁሌም ዕድገትና ለውጥ ስላለ የትናንት ወርቃማ መርሆችህና የኑሮ ዘይቤዎችህ ከአስር ዓመት በኋላ ምንም ማለት እንዳልሆኑ ስትረዳው ትናት ያባከንከው ጊዜና ኃይል መልሰህ ላታገኘው ነገር ይቆጭሃል (Robert J. Havighurst’s Developmental Task)፡፡ ስለዚህ ለጊዜና ለስኬትህ ሚዛናዊነትን አስቀምጥ፡፡ ስኬት ወይም ስራ አስፈላጊ ነው ነገር ግን በተጓዳኝ ምን ያስፈልገኛል የሚለውን ባለመርሳት፡፡

 

ሐ.ማኅበራዊ (Social)

ሰውን ሰው ያሰኘው ስራው ብቻ ሳይሆን ማህበራዊነቱም ጭምር ነው፡፡ አገርኛ ዘይቤው ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው እንዲል፡፡ ያለ ማኅበራነት ህይወት ትርጉም ታጣለች፡፡ ስትደሰት ደስታህን ተካፍይና ስታዝን አጽናኝ ያስፈልግሃል፡፡ በብቸኝነት ደስታ ጤነኝነትንና እርካታን ማግኘት አይቻልም ቢገኝም ጊዜአዊ ነው የሚሆነው፡፡ ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ ደሴት አይደለም፡፡ ደሴት ደሴት ይባል ዘንድ ዙሪያውን በውሃ አካል መከበብ አለበት፡፡ ማኅበራዊ ህይወት ስንል ሺህ ሰማኒያውን ሰው ግር አድርጎ መጓተትና መግተልተል ሳይሆን ጥራቱን ነው የምናወራውና ትኩረት የምንሰጠው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በብዙ ሰዎች ተከበህም ምንም የማይፈይዱህ ከሰው ጋር ሆነህ ብቸኝነት እንዲሰማህ የሚያደርጉህ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ህይወትህን ቀለል የሚያደርጉና ደስታና ሃዘንህን ሊጋሩህ የሚችሉ ወዳጆች ያስፈልጉሃል፡፡ ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስር ያላቸው ሰዎች ደስተኛና ጤነኛ ይሆናሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጥሩ ማኅበራዊ ህይወት ያላቸው ሰዎች ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ፡፡ ከማኅበራዊ ሚዲያ አምስት ሺህ ጓደኞችህ (በአወንታዊው መልኩ ይታይልኝ፡፡ የማኅበራዊ ሚዲያን ጓደኝነት ማሳነሴና ዋጋ ለማሳጣት እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡ እኛም በማኅበራዊ ሚዲያ አይደል እየተማማርን ያለነው!) ይልቅ በሳምንት አንዴ በአካል የምታገኘው ወዳጅህ ትልቅ አስተዋጽኦ ላንተነትህ አለው፡፡ ሳይበዛም ሳያንስም ማኅበራዊ ህይወት ደስታንና ሃሴትን ከማጎናጸፉ ባሻገር የሌላውን ልምድና ተሞክሮ እንድንጋራ ይረዳናል፡፡
 

መ. መንፈሳዊነት/ተስፋ (Spirituality or Hope)

ትናንትን አትመልሰውም ወይም አትኖረውም፡፡ ግን ትልቅ ቤተ-መጽሐፍና ትምህርት ቤት ሊሆንህ ይገባል፡፡ የትላንት መንነትህ ዛሬነትህን አይገልጸውም፡፡ ብትወድቅ ብትነሳ ፤ ህይወት ቢሰምርልህ ቢያማርርህ ትናንት ነበር ነው፡፡ ላትመልሰው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብቶህ ሄዶአል፡፡ ዛሬ የአንተ ናት በእጅህ ላይ ነው ያለችው፡፡ የስኬትንም የውድቀትም ካርድ ልትመዝባት ትችላለህ፡፡ ግድ የለህም ዛሬ እንኳ ባይሆንልህ ነገ ደግሞ አለልህ፡፡ ነገን ታስበው ዘንድ ተስፍ የሚሉት ስንቅ ያስፈልግሃል፡፡እዚህ ላይ መንፈሳዊነት/ተስፍ ስንል ሃይማኖተኝነትህን ለመግለጽ ሳይሆን ዛሬን እንደ ግብአት ተጠቅመህ ነገን እንደምትኖር ለማሳየት ነው፡፡ ተስፍ እንዲኖርህ ደግሞ መንፈሳዊ ሰው መሆን አለብህ፡፡ ነገሮችን በቅንነት በመልካምነት የሚመለከት አእምሮ ፤ የዛሬ ውድቀትህ ጠንክሮ በመስራት ትምህርትና የነገ ስኬትህ እንደሚሆን የሚያስብ፡፡ እንዲያ ሲሆን በአሉታዊ ህይወትና መንገድ ውስጥ አወንታዊ የሆነውን ነገር ማየት ትችላለህ (አወንታዊ= ጠንካራ ጎን + ደካማ ጎን )፡፡ ነገን ለማየት ግን ምንም ዋስትና ባይኖርህም በተስፍ ታየዋለህ፡፡ ካለማመን ማመን ይሻላል ብለህ ስለምታስብ ነገን በዛሬ መነጽር ታያትና ሐሴት ታደርጋለህ፡፡ ግላዊ እምነትህ ምንም ይሁን ምን ተስፈኝነትን/መንፈሳዊነትን ከአንተ በፍጹም ማራቅ የለብህም፡፡ ሌሎች “ተስፍ/መንፈሳዊነት የሞኞች መጽሐፍ ቅዱስ/ቁራን ነው” ቢሉህ አትስማቸው፡፡ ሰው ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም ኗሪ ነው ፤ አንድም በምናብ አንድም በአካል፡፡ ታላቁ የሰላም ታጋይ ማህተመ ጋንዲ ብዙ ጊዜ ስለ ሃይማኖቱ ሲጠየቅ ምላሹ ስለዚህ ጉዳይ አስቤበት አላውቅም ነበር መልሱ፡፡ ከሃማኖተኝነቱ ይልቅ መንፈሳዊነቱ/ተስፈኝነቱ ስለሚያደላበት፡፡ ያለተስፍ ሁሉም ነገር ከንቱና ብላሽ ነው፡፡ መሽቶ ስንተኛ ነግቶ ጠዋት እንደምንነሳ በተስፋ ነው፡፡ ሰው እንስሳ ስላልሆነ ተስፍና ተስፈኝነት ያስፈልገዋል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው አካል ፤ ስኬት/ስራ ፤ ማኅበራዊነትና መንፈሳዊነት/ተስፍ የፒራሚድ ቅርጽ በመስራት አንዱ አንዱን ሳይጎዳና ሳይጫን በሚዛንነት ተጠባብቀው የሚሄዱ ከሆነ ህይወት ቀላልና ምቹ ትሆናለች፡፡ የሰው ጤነኛነቱም (From Positive Psychotherapy point of view) በዚሁ ልኬት ይታያል ይዳሰሳል፡፡ ስለዚህ ጤነኛና ደስተኛ ሰው የአራቱ ድምር ውጤት ነው በእኩልነት (1+1+1+1=4 (ሙሉ ጤናማ ሰው))፡፡ ከላይ በተቀመጡት መስፈርቶች አንተስ እንዴት ነህ የጎደለህና ማስተካከል ያለብህ ነገር አለ? እንግዲያውስ አትዘናጋ ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ስራህን በሚዛናዊነት ለመከወን ተነሳ፡፡ ያን ጊዜ ጤነኛና ደስተኛ ሰው ትሆናለህ:: ሻሎም!

(በአንቶኒዩ ሙላቱ)
©zepsychologist
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_13
#ሶስቱ_የስብዕና/ማንነት_አካላት
www.tg-me.com/psychoet
(በአቤል ታደሰ እና ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

#ኢድ(id)፣
#ኢጎ(Ego) እና
#ሱፐር-ኢጎ(Super ego)

በታዋቂው ሲግመንድ ፍሮይድ የስነ-ልቦና ጽንሰ-ሀሳብ The Psychoanalytic Theory መሠረት የሰዎች ስብዕና ውስብስብ እና ከአንድ በላይ በሆኑ ክፍሎች ነው፡፡

እነዚህ ሦስቱ የስብዕና ወይንም የማንነት አካላት ኢድ(id)፣ ኢጎ(Ego) እና ሱፐር-ኢጎ(Super ego) ተብለው ሲጠሩ ውስብስብ የሆነውን የሰዎች ባህሪ ለመፍጠር አብረው ይሰራሉ ​​፡፡ ሦስቱም የስብዕና አካላት በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በተለያየ መልኩ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡

በፍሮይድ ጽንሰ-ሀሳብ መሠረት የስብዕናዎ የተወሰኑ ክፍሎች በመሰረታዊ ፍላጎቶችዎ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ግፊት ሲያደርጉ ሌሎች የስብዕናዎ ክፍሎች ደግሞ እነዚህን ፍላጎቶች ወይም ምኞቶች ለመግታት እና ከእውነተኛ ፍላጎቶችዎ ጋር እንዲስማሙ ለማድረግ ይጥራሉ።

እያንዳንዳቸው እንዴት በተናጥል እንደሚሠሩ እና እንዴት እንደሚነጋገሩ እንመልከት ፡፡

#ኢድ(id)

ከተወለደንበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ብቸኛው የስብዕናችን አካል ሲሆን፡፡ይህ የስብዕናችን አካል ሙሉ ለሙሉ የማይታወቅ እና በደመ ነፍስ የሚመራ ባህሪያትን አካቷል ፡፡ ኢድ(id) ሁሉንም ፍላጎቶች ወዲያውኑ ለማሟላት ከሚሠራው የሰውነት የመደሰት መርህ የሚመነጭ ነው፡፡እነዚህ ፍላጎቶች ወዲያውኑ ካልተሟሉ የስብዕና ውጥረት ይፈጠራል ፡፡
ለምሳሌ ፣ የረሀብ ወይም የጥማት ፍላጎት ለመብላት ወይም ለመጠጣት አፋጣኝ ሙከራን እንድናደረግ ይገፋፋናል : ነገር ግን እነዚህን ፍላጎቶች ወዲያውኑ ማሟላት ሁልጊዜ ተጨባጭ እና የሚቻል አይደለም ፡፡ ይህ የሰውነት የመደሰት መርህ በሙሉ የሚገዛን ከሆነ ፣ ሁልጊዜ የራሳችንን ፍላጎቶች ለማርካት ስንኖር አንገኛለን፡፡
እንደ ፍሮይድ ገለፃ ኢድ(id) የሚፈልገውን ፍላጎትን ለማርካት የአእምሮ ምስል በመፍጠርና የመጀመሪያ ደረጃ(ስጋዊ) ስሜትን በመጠቀም የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት ይሞክራል ፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ውሎ አድሮ የኢድን(id) ደመ- ነፍሳዊ ፍላጎት መቆጣጠርን ቢማሩም ፣ ይህ የባህሪይ አካል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ተመሳሳይ ሆኖ ይኖራል፡፡

#ኢጎ(Ego)

ራስን ከፍ ከፍ በማድረግ ከእውነታው ወይም ከገሀዱ አለም ጋር ለመገናኘት የሚየግዘን የስብዕና ክፍል ሲሆን እንደ ፍሩድ ገለጻ ኢጎ(Ego) ከ ኢድ(id) የሚዳብር ሲሆን የኢድ(id) ግፊቶች በእውነተኛው ዓለም ተቀባይነት ባለው መልኩ እንዲገለፁ ያደርጋል ፡፡
ኢጎ የሚሠራው በእውነተኛው መርህ ላይ በመመርኮዝ ነው ፣ ስለዚህ የኢድ(id) ፍላጎቶችን በተጨባጭና በማህበራዊ እይታ ተገቢው በሆነ መንገድ ለማርካት ይጥራል ፡፡

ለምሳሌ ፣ በሥራ ቦታ ረዥም ስብሰባ ላይ ተቀምጠው ቆዩ እንበል፡፡ ስብሰባው እየቀጠለ ሲሄድ ረሀብዎ እየጨመረ ሲሄድ ይሰማዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ ኢድ(id) ከመቀመጫዎ ላይ እንዲወጡ እና ለምግብ እንዲወጡ ሲገፋፋዎት ኢጎ(Ego) በጸጥታ ስብሰባው እስኪያበቃ ድረስ እንዲቀመጡ በተቃራኒው ይገፋፋዎታል፡፡

#ሱፐር-ኢጎ

የመጨረሻው የሰዎች ስብዕና ክፍል ሱፐር-ኢጎ(Superego) ነው። ሱፐር-ኢጎ(Superego) ከወላጆችና ከማህበረሰብ የምናገኛቸው፡ በውስጣችን የተቀመጡ የሥነ-ምግባር መርህና አመለካከቶችን የሚይዝ የስብዕና ክፍል ሲሆን፡፡ ሱፐር-ኢጎ ውሳኔና መመሪያዎችን ይሰጣል ፡፡ ሱፐር-ኢጎ(Super ego) ባህርያችንን ፍጹም እና ስልጡን ለማሳደግ ይሠራል።

እንደ ፍሮይድ ገለጻ ፣ ለጤነኛ ስብዕና ቁልፍ የሆነው ነገር በ ኢድ(id)፣ ኢጎ(Ego) እና ሱፐር-ኢጎ(Super ego) መካከል ያለው ሚዛናዊ መስተጋብር ነው ፡፡

www.tg-me.com/psychoet
www.tg-me.com/wikihabesha
_❖
So
urce:- From Personality Psychology books & verywellmind (web)

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!
እወዳችኅለሁ
__❖

ለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
15 Lessons from "Make Your Bed: Little Things That Can Change Your Life...And Maybe the World" by Admiral William H. McRaven:

1. Start Small, Make Your Bed: Discipline starts with small, consistent actions. Making your bed every morning creates a sense of accomplishment and sets the tone for a productive day.

2. Embrace the Challenge: Don't shy away from difficulties. View challenges as opportunities to grow, learn, and build resilience.

3. Never Give Up: Persistence is key. Learn from your mistakes, keep moving forward, and never give up on your dreams.

4. Find Your Motivation: Discover what fuels your passion and commitment. Your "why" will sustain you through challenges and inspire you to achieve your goals.

5. Find Your Tribe: Surround yourself with positive, supportive people who challenge you and help you grow. A strong team can achieve more than any individual.

6. Communicate Effectively: Open and honest communication is essential for building trust and fostering collaboration. Learn to listen actively, express your ideas clearly, and resolve conflict constructively.

7. Lift Others Up: Celebrate the successes of your teammates and support them through their challenges. Positive energy and mutual respect are key ingredients for success.

8. Lead by Example: Be the change you want to see in the world. Your actions speak louder than your words, so lead with integrity and dedication.

9. Serve Others: Focus on serving those around you, both in big and small ways. Making a positive impact on others brings true fulfillment and purpose.

10. Do the Right Thing, Even When It's Hard: Stand up for what you believe in, even when it's difficult or unpopular. Integrity and courage are essential for effective leadership.

11. It's Not All About You: Learn to see the bigger picture and understand how your actions impact others. Humility and perspective are crucial for effective leadership and collaboration.

12. Embrace Failure: View failure as a learning opportunity, not a setback. Learn from your mistakes, adapt, and keep moving forward.

13. Never Stop Learning: Continuous learning and personal growth are essential for success in any field. Cultivate a curious mind and stay open to new ideas and experiences.

14. Find Humor in the Darkest Moments: Laughter is a powerful tool for overcoming challenges and maintaining a positive outlook. Learn to find humor even in difficult situations.

15. Make Your Bed, Change the World: By starting with small, disciplined actions and focusing on service and leadership, you can create a ripple effect that can positively impact your community and the world.

Remember, Admiral McRaven's message is one of empowerment and hope. By embracing these lessons and incorporating them into your daily life, you can transform your own life, strengthen your relationships, and contribute to a better world.
#ሀሙስ 12

#ተሰሚነት
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ብዙዎቻችን የሚጎለን ክህሎት ስለሆነ ሌሎችም እንዲማሩ አንብበን #Share እናርገው

“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡ ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡

ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡

ቅለት

ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡

ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ

“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡

በራስ መተማመን

አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ ጉልበት አላቸው፡፡

በሌሎች ዓይን ማየት

ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣ ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ መቼም አይጠፋም፡፡

ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ  

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡

እጥረትን መፍጠር

ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣ የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣ በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡

ዝግጅት

ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመናችንንም ይገነባል፡፡

ለምሳሌ እነዚህን በሙሉ ክህሎቶች ዶ/ር ምህረት ላይ እናገኛለን ፡፡ የመሰማቱ አንዱ ሚስጢር ይሄ ነዉ ፡፡ ሲያስተምር አይታችሁ ከሆነ የሚያስተምረውን ነገር ቀለል አርጎ ፣ በራስ መተማመን ለአድማጭ በሚስብ መልኩ ያደርጋል ፡፡ ይህ በሁላችን አድማጮቹ ዘንድ ተሰሚነትን ፈጥሮለታል ፡፡ በሌላ በኩል አንድ ሰፈር /ስራ ቦታ የምናውቀውን ሳያቋርጥ የሚያወራ ፣ ንግግር የማያስጨርስ ሰው ስናስብ እንኳን ለመስማት ከሱ ጋር ለማውራት ይቀንቀናል ፡፡ እንግዲህ ሚስጥሩ ይሄው ነው ፡፡

በሰዎች ዘንድ ለመሰማት በዕውቀትና በጥበብ እናውራ !
(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
#Share & #Like oue page - fb.com/psychologyabc
_________
2024/07/01 08:36:30
Back to Top
HTML Embed Code: