Telegram Web Link
#Event Addis/ሁነት አዲስ

#አሁን በኢትዮጵያ ማህበራዊ ትስስር ገፆች!

#የዜግነትክብር
#ቀይአሻራ
#በቃ

የተሰኘ የተቃወሞ ዘመቻ ቀኑ ከ6:00 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

ሼር!

https://www.tg-me.com/EventAddis1
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
👉 ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች

ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።

1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።

2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።

3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።

4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።

5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።

6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።

7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።

8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው። በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።

9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው። ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣ ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።

10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
#በቅንነት ሼር አድርጉ

@psychoet
የበታችነት ስሜትን የማሸነፊያ መንገዶች
#Share

ማንም ከበታችነት ስሜት ጋር የተወለደ ወይም የሚወለድ ሰው የለም፡፡ የበታችነት ስሜት ተፈጥሮአዊ ሳይሆን በአካባቢ ተጽእኖ የሚመጣ ውጤት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሰዎች ስለራሳቸው የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ከአካባቢያቸው ይማራሉ፡፡ የተማሩትን ነገር ደግሞ ትተው፣ አዲስ ነገር መማር ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የበታችነት ስሜት ሊለወጥ የሚችል አስተሳሰብ ነው፡፡

እያንዳንዱ ሰው በተፈጥሮ እንዲሁም ካደገበት አካባቢ አንጻር ልዩ በመሆኑ የበታችነት ስሜትን የሚያሸንፍበት አንድ ወጥ የሆነ አካሄድ ላይኖር ይችላል፡፡ ሆኖም በዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱ ምክሮችን ተግባራዊ ቢያደርጉ ስለራሳቸው ጤናማ/ትክክለኛ የሆነ እይታ ሊያሳድጉ ይችላሉ፡፡

በሌሎች ሰዎች አስተያየት ላይ ጥገኛ አለመሆን

 በልጅነት ወቅት አንድ ነገር ሰርተን፣ ወላጆቻችን ወይም ትልልቆች ብለን የምናስባቸው ሰዎች ጥሩ ነው፣ ትክክል ነው፣ ጎበዝ .… እንዲሉን እንፈልጋለን፡፡ በጎልማሳነት ጊዜ እንዲህ ያለውን የልጅነት ወቅት ባህርይን መተው አስፈላጊ ነው፡፡ ከሰዎች ተገቢውን አስተያየት መጠየቅና ስራችንን መገምገም ጠቃሚ ቢሆንም፣ በእነርሱ አስተያየት ላይ ጥገኛ መሆን  ዞሮ ዞሮ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ይጎዳል፡፡

ራሳችንን ከአሉታዊ አስተሳሰቦች መለየት

 በተቻለ መጠን ራሳችንን/ ማንነታችንን በአእምሮአችን ውስጥ ከተከማቸው አሉታዊ አስተሳሰብ መለየት አለብን፡፡ በሌላ አነጋገር በእነዚያ አሉታዊ አስተሳሰቦች ራሳችንን መመዘን ስንተው፣ እነዚያ አስተሳሰቦች ኃይል ያጣሉ፡፡ በእርግጥ ከእኛ ጋር ለረጅም ጊዜ የቆዩ ከሆኑ፣ ከእነርሱ ጋር ዝምድና ስለፈጠርን በቀላሉና ቶሎ ላይሄዱ/ላይለዩን ይችላሉ፡፡ ሆኖም ከእነርሱ ጋር ላለመኖር ከወሰንን፣ ቀስ በቀስ ስፍራውን ይለቃሉ፡፡ በእነርሱ ስፍራ ደግሞ ተገቢ የሆኑ ሃሳቦችን እናስገባለን፡፡ እነዚያ ቀስ በቀስ ገብተው ስፍራ እንደያዙ ሁሉ፣ አዲሱና መልካም የሆነው አስተሳሰብም ዕድል ከሰጠነው ቀስ በቀስ ወደ አእምሮአችን ገብቶ ሥፍራውን ይይዛል፡፡

በውድቀታችን ራሳችንን ከመኮነን ከውድቀታችን መማር

 ስህተት የማይፈጽም ሰው የለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው ስህተታችንን የምናስተናግድበት ሁኔታ ነው፡፡ በስህተታችን ራሳችንን እየወቀስን የምንሄድ ከሆነ፣ ራሳችንን ለመቀበል እንቸገራለን፡፡ ከስህተታችን ተምረን ወደፊት ማሻሻል የሚገባንን ነገር የምናስብ ከሆነ ደግሞ ራሳችንን ተቀብለን ወደፊት እንሄዳለን፡፡ ስለሆነም በህይወታችን በእኛም ሆነ በሌሎች ሰዎች በደረሰቡን ችግሮች፣ ውድቀቶች፣ አለመሳካቶችና መልካም ያልሆኑ ነገሮች ሁሉ ራሳችንን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን ከመኮነን፣ ከክፉ ነገሮች መልካምን ነገር ተምረን ወደፊት መሄድ የተሻለ አማራጭ መንገድ ነው፡፡

ራሳችንን በፉክክር ውስጥ አለማስገባት

እያንዳንዱ ሰው ልዩ ሆኖ የተፈጠረ ፍጡር ነው፡፡ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለው እምቅ ችሎታ አንድ ዓይነት ላይሆን ይችላል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ያደገበትና ያለበት ዓውድ ልዩነት አለው፡፡ ስለዚህ ከሌሎች ጋር ሁልጊዜ መፎካከርና ራሳችንን ከሌሎች አንጻር ከመገመት ይልቅ እኛ ዘንድ ያለውን መልካም ነገር በመለየት በተሻለ መንገድ መጠቀም የምንችልበትን መንገድ መቀየስ ይረዳናል፡፡ ከሌሎች ሰዎች ስኬት፣ ብርታት፣ መልካም ነገሮች፣ አሸናፊነት ለራሳችን መልካም ቁምነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ ስለዚህ የፉክክር የህይወት ዘይቤን በመተው ከሌሎች መማርን መልመድ ጠቃሚ ነው፡፡

ስጦታችንን በመለየት ማሳደግ

 እያንዳንዱ ሰው ስጦታ እንዳለው ሁሉ እኛም ስጦታ አለን፡፡ ስለዚህ በውስጣችን ያለውን እምቅ ችሎታ፣ ፍላጎታችንንና ምቹ ሁኔታዎችን በመለየት ስጦታችንን በዕውቀትና በክህሎት ማሳደግ እንችላለን፡፡ ጎበዝ በሆንበት ወይም መስራትና መሆን በምንፈልገው ጉዳይ ላይ የበለጠ ዕውቀትና ክህሎትን በማጎልበት የበለጠ ፍሬያማ መሆን እንችላለን፡፡  በችሎታችን ራሳችንና ሌሎች ሰዎችን መጥቀም ስንችል ደግሞ እርካታና ደስታን እናገኛለን፡፡ ለሰዎችም አንድ በጎ ነገር ማድረግ መቻላችን ደግሞ ስለራሳችንም በጎ አስተሳሰብ እንዲኖረን ያግዘናል፡፡

ባለሙያን ማማከር

እንግዲህ ራሳችንን የመቀበል ችግር ሲኖረን በአብዛኛው ከበጎ ነገር ይልቅ በህይወታችን ውስጥ ባሉ ድክመቶች፣ ጉድለቶችና ስህተቶች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ የበታችነት ስሜት መንስኤ የሆኑ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ ተገቢውን መፍትሔ ለመፈለግ እጅግ ያግዛል፡፡ ምክንያቶቹ ከሰው ወደ ሰው የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ራሳችንን የማንቀበል ከሆነ እኛው ለራሳችን ጠላቶች ሆንን ማለት ነው፡፡ ሁልጊዜ ከራሳችን ጋር እንጣላለን፡፡ ጠላትን በውስጣችን ተሸክመን እንዞራለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራሳችንን በመቀበል በሰላም በመኖር የበታችነት ስሜትን ማስወገድ እንችላለን!

ገንቢ ያልሆኑ መንገዶች

በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት እንዲሁም ስለራሳችን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን እንከን የለሽ ስራዎችን ለመስራት ጥረት ማድረግ የማይጠቅም አካሄድ ነው፡፡ ማንም ሰው በንግግሩና በስራው ፍጹም መሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ይህን ዓይነት መንገድ መከተል የበለጠ ራስን ለውድቀት ብሎም ለበለጠ የበታችነት ስሜት እንዲሰማን ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይሆናል፡፡

በቅናት መንፈስ ውስጥ ሆኖ ከሌሎች ሰዎች በልጦ ለመገኘት ጥረት ማድረግ የበታችነት ስሜትን አያጠፋም፡፡ ጤናማ ያልሆነ ፉክክር በማሸነፍና በመሸነፍ ሚዛን ውስጥ ያስገባናል፡፡

ብዙ ጊዜ በአሉታዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ የበታችነት ስሜታችን እንዲኖር እንዲሁም እንዲያድግ ያደርጋል፡፡

ከሌሎች ሰዎች በችሎታ፣ በብቃት፣ በትምህርት ደረጃ፣ በገንዘብና በሌሎች ነገሮች እኩል ብንሆን ስለራሳችን ያለን አስተሳሰብ በጎ እንደሚሆን ማሰብ ሁልጊዜ ትክክል አይደለም፡፡ ስለዚህ ትኩረት መደረግ ያለበት ደረጃን በማሻሻል ላይ ሳይሆን በማንኛውም ደረጃ ላይ ብንሆን ራሳችንን ተቀብለን መኖር መማር ላይ ነው፡፡ ስለራሳችን ያለንን አሉታዊ ስሜት ማስወገድ ይገባናል፡፡

#Share
©Zepsychology
@psychoet

ያላችሁን ጥያቄ / አስተያየት በ Comment አሳውቁን
ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች፣

በቅርቡ በተለያዩ የሕይወት ጉዳዮች ላይ የምንወያይበትና የተለያዩ አማካሪ ባለሙያዎች የሚካተቱበት የቴሌግራም ግሩፕ ስለከፈትን ማንኛውም የሕይወት ጥያቄ ያላችሁ ፣ ምክር የምትፈልጉ ይህን ግሩፕ በመቀላቀልና ጓደኞቻችሁንም በመጋበዝ ልታገኙን ትችላላችሁ፡፡
ከሥነልቡና / Psychology / አንጻር እንድንጽፍላችሁ የምትፈልጉትን ርዕስ በ comment አሳውቁን!
@ethiodiscussion
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች፣ በቅርቡ በተለያዩ የሕይወት ጉዳዮች ላይ የምንወያይበትና የተለያዩ አማካሪ ባለሙያዎች የሚካተቱበት የቴሌግራም ግሩፕ ስለከፈትን ማንኛውም የሕይወት ጥያቄ ያላችሁ ፣ ምክር የምትፈልጉ ይህን ግሩፕ በመቀላቀልና ጓደኞቻችሁንም በመጋበዝ ልታገኙን ትችላላችሁ፡፡ ከሥነልቡና / Psychology / አንጻር እንድንጽፍላችሁ የምትፈልጉትን ርዕስ በ comment አሳውቁን! @ethiodiscussion»
#መልካም_የሀምሌ_ወር_ይኹንላችሁ!

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በኹሉም አካባቢዎች ሰላምን የምንሰማበት ፣ ፍትህን የምናይበት ይሁንልን ፡፡

ከአንድ ወር እረፍት በኀላ ተመልሰናል። ቆሞ የነበረው የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት የማሕበራዊ ሚዲያ ትምህርታችን ከዛሬ ጀምሮ በዐዲስ መልክ ይቀጥላል ፡፡

ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ።
Telegram : www.tg-me.com/psychoet
Group : www.tg-me.com/ethiodiscussion
Facebook : fb.com/psychologyabc

መልዕክቱን #Share #Like በማረግ ለሌሎችም እናጋራ
የመወያያ ጥያቄ?

➊እልህ አወንታዊ ወይስ አሉታዊ ስሜት ነው? ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ ስሜት(ባህሪ)?

ሀሳባችሁን አጋሩን?
📌 👉 አደገኛው ስብእና/ Narcissism👈📌

🔥ለትዳር፣ ለጓደኝነትና አብሮ ለመስራት ስንመርጣቸው አብዝተን ልንጠነቀቃቸው የሚገባ አስቸጋሪ ማንነት ያላቸው ሰዎች።🔥

📌👉 ሁል ጊዜ ጥፋተኛ እንደሆናችሁ እንድታስቡ የሚያደርጉትን። ለሚሰጧችሁ መጥፎ ምላሽ ተጠያቂው/ዋ አንተ/አንቺ ነሽ የሚሉትን።

📌👉 የእነሱን ችግር እንጂ ፈፅሞ የእናንተን ማዳመጥና መረዳት የማይፈልጉትን።

📌👉 ለጥፋታቸው ሀላፊነት መውሰድ የማይፈልጉ፣ ሁል ጊዜ ትክክል ነኝ ብለው የሚያስቡና ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ምክንያቱ እናንተ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ የሚያደርጉትን።

📌👉 ጉራቸው ከልክ ያለፈ። ታላቅነታቸውን፣ ችሎታቸውን፣ ተፈላጊነታቸውን እና የበላይነታቸውን ሁሌ የሚናገሩትን። ከእናንተ የወሰዱትን ሀሳብ ጭምር የራሳቸው አድርገው የሚነግሯችሁን።

📌👉 የሰውን ትኩረት ለመሳብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በእያንዳንዱ ንግግራቸው እኔ....እኔ....እኔ የሚሉትን።

📌👉 ለሌላ ሰው ችሎታ እውቅና የማይሰጡና የሚቀብሩትን።

📌👉 ሌሎችን በጣም የሚያሳንሱ። የእነሱ ትልቅነት የሚጎላው የሌላውን ውድቀት፣ ድክመትና አለመሳካት ሲያወሩ የሚመስላቸውን።

📌👉 ፈፅሞ አክብሮት የላቸውም። ተሳስቻለሁ....ይቅርታ የሚባል ነገር አይታሰብም። ለጥፋታቸው ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ የሚያሸማቅቁትን።

📌👉 እነሱ የሚፈልጉትን ሀሳብ እንድትቀበሉና በነሱ ቁጥጥር ስር እንድትሆኑ የሚያደርጉትን።

📌👉ምንም አይነት ፍቅርና ርህራሄ የሌላቸውን።

📌👉 ክፋታቸውን ነቅታችሁ ስትርቋቸው ስማችሁን የሚያጠፉ። ሚስጥርና ድክመታችሁን ለሰው የሚያወሩተን። በሚችሉት ሁሉ ሊጎዷችሁ የሚሞክሩትን።

🔥ይህንን ካነበቡ በኋላ ግንኙነቶችዎን ደግመው ይመርምሩ። ለሌሎችም እንዲጠቅም ሼር ያድርጉ🔥

👉 ©በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

@Psychoet
የትብብር ጥያቄ!

ከላይ የምትመለከቱት ኢትዮጲያዊ ሞዴል በአለምአቀፍ ደረጃ በሞዴሊንግ እየተወዳደረ የሚገኝ ሲኾን በSocial media እየገባችሁ ድምጻችሁን እንድትሰጡት በአክብሮት ይጠይቃል፡፡
እንደምን አላችሁ፣
በጣም የምትጠሉትን የሰው ባህሪ Comment ላይ ጻፉልን?

ብዙ ሰው የጻፈው ባህሪ ላይ ሥነልቦናዊ ማብራሪያ እናቀርባለን፡፡
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
እንደምን አላችሁ፣ በጣም የምትጠሉትን የሰው ባህሪ Comment ላይ ጻፉልን? ብዙ ሰው የጻፈው ባህሪ ላይ ሥነልቦናዊ ማብራሪያ እናቀርባለን፡፡
ከተሰጡት ከ 50 በላይ የኾኑ አስተያየቶች በብዙ ቤተሰቦች የተመረጡት 3 የሚጠሉ ባህሪዎች እነዚህ ናቸው፡፡
በነዚህ ርዕሶች በዚህና በቀጣዩ ሳምንት የተወሰነ ሥነልቦናዊ ማብራሪያ እናቀርባለን
1. የሚዋሽ (ውሸት)
2. የሚያስመስልና የሚለዋወጥ (ማስመሰልና መቀያየር)
3.ሰዎችን የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያረግ

@Psychoet
#ውሸት
#ክፍል_1
ለምን እንዋሻለን ???

በግል የምንዋሸው እንዳለ ኾኖ አሁን አሁን በትልልቅ ሚዲያዎች ሳይቀር ቀርቦ ውሸት መናገር እየተለመደ የመጣ መጥፎ ተግባር ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ውሸትን ለብዙ ነገራቸው አየተጠቀሙት ልምድ አርገውታል፡፡ ግን
ውሸት ምንድነው?
ባለሙያዎች ውሸትንና ውሸታሞችን እንዴት ያዮቸዋል? ከታች የቀረበው ጽሑፍ ብዙ ነገሮችን ያስዳስሰናል፡፡


ውሸትን የተለያዩ ምሁራን ትርጓሜና እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል በዚህም ነጋሪውን ለመጥቀም የታሰበ ሐሰታዊ የሆነ ግንኙነት የሚለው መጀመሪያው ሲሆን ይህም ብዙ ውዝግቦችን አስነስቶ ነበር፡፡ ምክንያቱም ነጋሪውን ብቻ ለመጥቀም  ውሸት አይነገርም የሚሉ፣ ውሸት ሆን ተብሎ የሚደረግ እውነትን የመደበቅ ስራ ነው ብለው መልስ የሰጡ ብዙ ወገኖች ነበሩ፡፡ በሁለተኛው የውሸት ማብራሪያ ወይም ፍቺ መሰረትም ሰዎች ሳያውቁት የተሳሳተ መረጃ ከተናገሩ እንደ ውሸት አይቆጠርም ማለት ነው፡፡ በርገን እና ቡለር የተባሉ ሁለት ምሁራን ደግሞ ውሸት ማለት መልዕክት ላኪው ለመልዕክት (መረጃ) ተቀባዩ ሆን ብሎ የተሳሳተ መረጃ በማቀበል መልዕክት ተቀባዩን መጉዳት ነው ይሉናል፡፡ እኛ ደግሞ የእራሳችን የሆነ የውሸት ትርጉም ወይም ፍቺ ይኖረናል፡፡

ውሸት ብዙ ጊዜ በቃላት ብቻ የሚገለጽ አይደለም በድርጊትም ጭምር እንጂ  ለምሳሌ ያልተጎዳ አትሌት እግሩን እንደተጎዳ አድርጎ እያነከሰ ከውድድር ወይም ከስልጠና ካቋረጠ ዋሽቷል ማለት ነው፡፡ መረጃን ሆን ብሎ መደበቅ ለምሳሌ የገቢን መጠን በመደበቅ ግብርን ለመቀነስ የሚደረግ ጥረትም ውሸት ነው፡፡ እኛ ሰዎች ውሸትን ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእራሳችንም እንዋሻለን ለአብነትም ማሳካት የፈለግነውን ነገር በራሳችን በሆነ ምክንያት ካላሳካን ችግሩን በውጪ ኣካል በማሳበብ (Externalize) ለራሳችን ውሸት እንነግራለን፡፡ እንደ ዲፓውሎ እና ሌሎችም ምሁራን መሰረት ሶስት  የውሸት ዓይነቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው outright lie (falsification) ሲሆን በግርድፉ አማርኛ ፍጹም ውሸት የሚባለው ነው ይህም ውሸት ተናጋሪዎች ከእውነታው ፍጹም ተቃራኒ የሆነ መረጃን ወይም መልዕክት ይናገራሉ ወይም ያስተላልፋሉ፡፡ ሁለተኛው Exaggeration ወይም ማጋነን ሲሆን በዚህም ውሸት ተናጋሪዎች እውነታውን በማጋነን ያቀርባሉ ለምሳሌ ቀጠሮ ላይ አርፎዶ የሚመጣ ተቀጣሪ የመንገዱን መዘጋጋት ከዕውነታው በተጋነነ መልኩ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ሶስተኛው የውሸት ዓይነት subtle lie ሲሆን በዚህም የሚነገረው የውሸት ዓይነት ጥቂት ሆኖ ከብዙ እውነታዎች ጋር በማቅረብ ሰዎችን ለማማሳት የምንጠቀምበት ነው፡፡

ለምን እንዋሻለን ?

ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡–  ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡

ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡

ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች  በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና  እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ  (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው  ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-

ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡

ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን  ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡

ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡

ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡

ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡


ቀጣዩ ክፍል ነገ ይቀጥላል ...... ያላችሁን ጥናቄና አስተያየት በ Comment አሳውቁን
©በቁምላቸው ደርሶ
@Psychoet
#ውሸት
#ክፍል_2
ውሸታም ሰዎችን እንዴት እናውቃለን?

ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን የሚለካ እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
#ስሜታዊነትን (emotional state)፣
#የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity)  እና
#ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡

የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን  የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ያደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና  ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም  ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡

ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………..

©(በቁምላቸው ደርሶ)
@Psychoet
እንኳን ደስ አለን!
ሲጠበቅ የነበረው የክረምት የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሊጀምር ነው!

ስለ ሳይኮሎጂ ለማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ በተጋባዥ የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎችና ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች።

📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖ለሕይወታችን ምን ይፈይደል?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
📖Counseling ምንድነው?
🔖ችግር አፈታትና ውሳኔ አሰጣጥ
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖የሕይወት አላማ መረዳት
🔖በራስ መተማመን እና ሌሎችም

ለሰልጣኞቻችን የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን ቅዳሜና እሑድ አልያም ከሰኞ እሮብ አርብ በጠዋት ፣ በከሰአትና በማታ ፈረቃ መከታተል ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡
www.tg-me.com/psychoet
‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››

በሕይወታችሁ አሁን ምን ላይ ናችሁ? ወደፊትስ የት መድረስና ምን ማድረግ ትፈልጋላችሁ? የምትፈልጉት ቦታ እንዳትደርሱ ምን ያዛችሁ?

በሕይወታችን ትልቅ ጦርነት የምናደርገው ከራሳችን ጋር ነው ፣ እያንዳንዱ ውሳኔዎቻችን ከራሳችን ጋር በሚደረግ ትግልና ትንቅንቅ የሚወሰኑ ናቸው ፡፡ ትልቁ ጠላታችንም አስተሳሰባችን ፣ ልማዳችን ፣ ምከላችን ነው ፡፡ ኹሉም ግጭት ደግሞ አእምሮአችን ውስጥ ከራሳችን ጋር ይካሄዳል ፡፡

ራሳችንን ካሸነፍን በምንም አንሸነፍም፡፡ ትልቁ ጠላታችን የኛ ሌላኛው ማንነታችን ነው፡፡

ከተስማማችሁ #ላይክና #ሼር በማድረግ ለሌሎችም እናድርስ

የሕይወትና የአስተሳሰብ ለውጥ ላይ የሚያተኩረው ስልጠናችን ላይ ለመመዝገብ 0912664084 ይደውሉ፡፡
2024/09/27 23:27:39
Back to Top
HTML Embed Code: