Telegram Web Link
Forwarded from Jafer Books 📚
በአጭር ጊዜ ተወዳጅነትን ያተረፈውና የተደነቀው " ሜሎሪና " የተሰኘው መጽሐፍ ለ 4ኛ ጊዜ ታትሞ ለንባብ በቃ ።

በወጣቱ ደራሲ ናሁሰናይ ፀዳሉ የተጻፈው ታሪካዊ የሥነልቡና ልብወለድ የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበብ ሚና የሚተርክና የአስተሳሰብ ልዕልናን የሚያሳይ ልብወለድ መጽሐፍ ነው ፡፡

በአቀራረቡም የሥነ- ልቡና ምክሮችንና ሀሳቦችን ከታሪካዊ ክስተቶች ጋር አጣምሮ ይዟል ፡፡

በመጽሐፉ የውስጥ ገጽ እንዲሀ ይለናል !!

‹‹... በምድር ላይ የሚወዱትን ሰው በሞት እንደመቀማትና ተስፋ ያደረጉትን እንደማጣት ትልቅ ህመም የለም፡፡ ሲደጋገም ደግሞ ሐዘን፣ ሥቃይ፣ ችግርና መከራ እንደመጫሚያና ልብስ አጥልቀዋቸው የሚዞሩ ያህል ይሰማል፡፡››

ገጽ 106

“... ያ ሲያስታብየው የነበረው ትልቅ ዕውቀት፣ ጥበብና ኀይል ትንሿን ፍቅር ማሸነፍ እንዳልቻለ ተረዳ፡፡
‹ለካ ነገሮች የሚመዘኑት በብዛታቸው ብቻ ሳይኾን በጥራታቸው ነው› አለ በውስጡ፡፡ “

ገጽ 117

‹‹... የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡ ለካስ እስር ቤት ቦታ ብቻ ሳይኾን አስተሳሰብ ጭምር ነው፡፡ በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል፡፡ ››

ገጽ 179


ሜሎሪና

#ታሪካዊ_የሳይኮሎጂ_ልብወለድ

ጃዕፈር መጻሕፍት ::

ለቴሌግራም - @jafbok
ለዌብሳይት - www.jaferbooks.com
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡
ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

_ሜሎሪና ገጽ 184 _

ሜሎሪና ❤️❤️❤️
ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ
@psychoet
ብዙ ጊዜ ሁላችን በተለያዩ የሕይወት መስተጋብሮች "የመርሳት" ገጠመኝ አለን ፡፡ነገሮችን ማስታወስ አለመቻል በዙሪያችን ባሉ ሰዎች መካከል እንደግዴለሽ የመታየት ፣ በስራችን አመኔታ ማሳጣት ፣ በትምህርታችን ደግሞ ያጠናነውን ያለማስታወስ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ በእርግጥ ነገሮችን መርሳት ሲበዛ እንደ ህመም ይታያል ፡፡ ለዚህም ነው በተለምዶ "የመርሳት ህመም " የሚባለዉ ፡፡ ነገሮችን አለማስታወስ ብዙ ማህበራዊ ጉዳት ካስከተለ ታዲያ እንዳንረሳ ምን እናርግ የሚለው ትልቅ ሙያዊ መልስ ያሻዋል፡፡

መርሳትን ለመቀነስ ምን ማድረግ አለብን ለምትሉ ሳይኮሎጂ እንዲህ ይላል ... ከታች ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ ቪዲዮውን ተመልከቱ
ሌሎችም አድምጠው እንዲጠቀሙበት ሼር አድርጉት
https://youtu.be/2yjs4zk1ZBY
https://youtu.be/2yjs4zk1ZBY
ማኅበራዊ ፍርሃት ማስወገድ
Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet
ይህን ጠቃሚ ትምህርት #Share እናድርገው

ማኅበራዊ ፍርሃት #ብዙ_ሰው_በተሰበሰበበት ቦታ ለመናገር ወይም አንድን ድርጊት ለመፈጸም በተዳጋጋሚ የሚፈጠር በብዙ ግለሰቦች ላይ የሚስተዋል #ምክኒያታዊ_ያልሆነ_ፍርሃት ነው፡፡ ይህ #የጭንቀት ዓይነት ያለባቸው ግለሰቦች ብዙ ጊዜ ንግግር ያለበት ተግባር አጥብቀው #ይሸሻሉ ምክኒያቱም አይደለም ንግግር አድርገው ገና ለማድረግ ሲያስቡ የሚሰማቸው #የፍርሃት ወይም #የጭንቀት_ስሜት ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ፡፡ ከህጻናት በስተቀር ማኅበራዊ ፍርሃት ያለባቸው ሰዎች ፍርሃታቸው ምክኒያታዊ እንዳልሆነ ይረዳሉ ምንም እንኳን ይህ ከፈርሃታቸው ባይታደጋቸውም፡፡
★እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ላይ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ምልክቶች ናቸው፡-

1.ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ አጥብቆ መፍራትና በትምህርት ገበታም ሆነ በስራ ቦታ የተዘጋጁትን በአግባቡ ማቅረብ አለመቻል

2.እንደ ካፌ፣ ሬስቶራንት፣ ቤተ-መጻሕፍትና ሌሌች ብዙ ሰዎች ባሉበት ቦታ ሰዎች እኔን እየተመለከቱኝ ነው ብሎ መሳቀቅ ፣ ከልክ በላይ አንገት አቀርቅሮ መጓዝ

3.ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ በሚያስቡበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ይተቹኛል ብሎ ማሰብ

4.ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ሲያደርጉ በላብ በጠመቅ ወይም ልዋረድ እችላለሁ ብሎ በፍርሃት ማሰብ

5.ብዙ ሰው ባለበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ የሆነ ያልሆነ ምክኒያት በመደርደር እራስን ማቀብ

6.አዲስ ሰው ጋር ለመገናኘት ተደጋጋሞ የሚከሰት ፍርሃት

7.ብዙ ሰው ባለበት ቦታ ምግብ በሚመገቡት ጊዜ ትንታ ወይም መታነቅ እንዲሁም ምግቡ ሊዝረከርክብኝ ይችላል ብሎ መፍራት

8.ከእነዚህ ጋር ተዛምዶ የሚከሰት እንደ የልብ ምት መጨመር፣ ላብ ላብ ማለት፣ የሰውነት መንቀጥቀጥና የመሳሰሉት ፍርሃት ወለድ አካላዊ ለውጦች ናቸው፡፡

፠፠፠ መፍትሄ ፠፠፠

1.የአስተሳሰብ ለውጥ፡-

ብዙ ጊዜ ማኅበራዊ ፍርሃት እንዲከሰት የሚያደርጉ ከበስተጀርባ ያሉ አሉታዊ አመለካከቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ለራስ የሚሰጥ ዝቅተኛ ግምት አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ለዚህ ፍርሃት መከሰት አስተዋጽኦ የሚያበረከቱ ምክኒያታዊ ያልሆኑ አሉታዊ አስተሳሰቦችን ነቅሶ በመለየትና በአዎንታዊ አመለካከት መተካት፡፡

2.መለማመድ፡-

ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ መናገር ስለሚያስፈራን ንግግር የምንሸሽ ከሆነ የፍርሃቱ መጠን እንዲጨምር መፍቀድ ነው፡፡ ከሸሻችሁት በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው መቼም ቢሆን ከዚህ ችግር እንደማትገላገሉ ነው፡፡ ስለዚህ እራስን ቀስ በቀስ ማለማመድ ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡

3.ስራ ላይ ማተኮር፡-

ብዙ ጊዜ የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ከሚሰሩት ስራ ይልቅ ሌሎች ሰዎች ስለሚሰጧቸው አስተያየትና ምላሽ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ እዚህ ላይ መታሰብ ያለበት ከስራው ይልቅ አድማጭ ተመልካች ላይ የምናተኩር ከሆነ መጀመሪያ በተገቢው ስራን መስራት እንችልም ምክኒያቱም ቀልባችን ሌሌች ሰዎች ላይ ነውና፡፡ ሲቀጥ ልሌሎች ሰዎች ላይ ስናተኩር የበለጠ ስለፍርሃት ስሜታችን ላይ እንድናተኩርና የበለጠ አሉታዊ ሃሳቦች እንዲፈጠሩ ይገፋፋል፡፡

4.ጡንቻን ማዝናናት መለማመድ፡-

ከውስጥ ከሆድ መተንፈስ በመለማመድ ጭንቀቱ የሚፈጥረውን የረብሻ ስሜት መቀነስ፡፡ ይህ በጣም ቀላልና የትም ቦታ ሊለማመዱት የሚችሉት ዘዴ ነው፡፡ ለተወሰነ ደቂቃ (እስከ 10 ሴኮንድ) ወደ ውስጥ በመተንፈስ ትንፋሽህን መያዝ ከዚያም መልቀቅ፡፡ እንደገና ወደ ውስጥ ትንፋሽን በመያዝ አሁንም ወደ ውጪ መተንፈስ፡፡በተደጋጋሚ ይህን በማድረግ የጭንቀት ስሜቱን ማቅለል ይቻላል፡፡ ይህን ዘዴ ጭንቀቱ ቀለል እሰከሚልድረስ መከወን ይቻላል፡፡

5.የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና መውስድ፡-

ዓይንን እየተመለከቱ ማውራት፣ ፈገግታ፣ የንግግር ፍሰትን መጠበቅና የመሰሳሰሉት ልምምዶች በንግግርና በሌሎች ማህበራዊ ተግባቦት ላይ ውጤታማነታችንን ሲለሚጨምሩ ለወደፊት የበለጠ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ መናገርና ሌሌች ተግባሮችን ለመፈጸም አወንታዊ ማበረታቻዎች ናቸው፡፡

★★★ከዚህ ጋር በተያያዘ ሥነልቡና ፔጅ የተዘጋጀውን የአንድ ወር ተግባራዊ ልምምድ ስልጠና ብትካፈሉ ብዙ የአመለካከትና የባሕሪ ለውጥ እንደምታመጡ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ ስልጠናው ከ በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል ፡፡
# ★★★

6.ሌላው presentation ሲኖርብን ከመስታወት ፊት በመቆም በደንብ መለማመድ ፣ ስናወራ ምን እንደምንመስል ማየትና ራሳችንን እያረምን ደጋግሞ መለማመድ ፡፡ በተጨማሪ ደፋር ሰዎች ራሱ ብንሆን አንዳንድ ያልተዘጋጀናቸውን ነገሮች ስናቀርብ / ባላሰብነው ሁኔታ ውስጥ ስንገኝ ፍርሀት ሊከሰት ስለሚችል ሁልጊዜ ጠንቃቃ መሆን ይጠበቅብናል ደግሞም ከልክ ያለፈ በራስ መተማመንም ማስወገድ መልካም ነው ፡፡

የፍርሃት ስሜት ወይም ጭንቀት የዕለት ተዕለት ህይዎታችን በደስታ እንዳንመራ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ማኅበራዊ ፍርሃትም እንደዚሁ በህይወታችን ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽኖ ይኖራል፡፡ ለችግሩ መፍትሄ ማፈላለግ እንጂ ለምን ይህ ተከሰተብኝ ብሎ እራስን መኮነንና ጥፋተኛ ማድረግ አይገባም ምክኒያቱም ምንጩ እኛ ሳንሆን አስተዳደጋችን ፣ አካባቢያችን ፣ አስተማሪዎቻችን ፣ ሊሆኑ ይችላሉና ፡፡ ስለዚህ በዚህ ፍረሀት ያላችሁ ሰዎች የጠቀስኳቸውን ነገሮች በደንብ ተግባራዊ አድርጉ ፡፡ ጥያቄ ካላችሁ ጻፉልኝ፡፡

መልካም ቀን ይሁንላችሁ ።
(በአሸናፊ ካሳሁን እና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist

በቴሌግራም በዚህ አግኙኝ www.tg-me.com/Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
የአእምሮ ጤንነትን የሚጠብቁና የሚያሳድጉ 5 ተግባራት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ)

የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡ ሰው እንደ ሰው ፣ ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በተለይም አሁን ባለንበት የኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ ደግሞ ይህ የአእምሮ ጤንነት በመንግስትም ሆነ በዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በዚህ ጊዜም ከወረርሽኙ የተነሳ በአለማችን ሆነ በአገራችን ብዙ ሰዎች ለአዕምሮ (ሥነልቦናዊ) ቀውስ እየተጋለጡ ይገኛሉ በዚህም ብዙዎች ቀናቸውን በድብርት ፣ በፍርሀት ፣ ተስፊ በመቁረጥ ፣ ስለ ነገ አሉታዊ ነገሮችን በማሰብ ያሳልፉሉ ብሎም ብዙ ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል ፣ ከስራተቸው ለቀዋል ፣ ማህበራዊ ህይወታቸውን አቁመዋል ... ብዙ ብዙ ፡፡ ይህ ሁሉ ወረርሽኙ ያስከተለው የሥነልቦና ቀውስ ነው፡፡

ይህ ወረርሽኝ ከሚያመጣው የሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡

1. አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር

አካላዊ ጤንነትና ንቃት ማለት ሁለንተናችን የተመጣጠነ እድገት ሲኖረውና ሰውነታችንን ከተለያዩ በሽታዎች ሲጠበቅ ማለት ነው፡፡ አካላዊ ጤንነት ሁልጊዜ ከአዕምሮ ጤንነት ጋር ይያያዛል ፡፡ በዚህ ንቃት ውስጥ የሚዳብር በራስ መተማመን ፣ ማቀድና መፈፀም እንዲሁም ችግሮችን በስልት መፍታት በሰውነታችን ውስጥ የኬሚካሎች ለውጥ እንዲኖር ያደርጋል ይህም ለኬሚካል ለውጥ በባህሪያችንና በስሜታችን ላይ አወንታዊ ለውጥን ያመጣል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

ባለንበት ቦታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የተለያዩ የሚያስደስቱንን ስራዎች በቤታችን ሁነን መስራት ፣ ጥሩ መጸሐፍትን ማንበብ ፊልሞችን መመልከት ፣በትንሹ እቅድ ማቀድና መተግበርን መለማመድ፡፡

2. አዳዲስ ክህሎቶችን መማር

ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዳዲስ ክህሎቶችን መማር ለአዕምሮ ጤንነትና እድገት ወሳኝ እንደሆነ ነው ፡፡ አዳዲስ ክህሎቶችን መማር በራስ መተማመናችንን ያሳድጋል ፣ የሕይወትን አላማ የቀለጠ እንድንረዳ ያግዛል በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች ጋር የትውውቅና የስራ እድል ይፈጥራል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች
አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር ዩኒቨርስቲ / ኮሌጅ መግባት ፣ ብዙ ገንዘብ ማፍሰስ አይጠይቅም ባሉበት ሆኖ በቅርብ በሚቀኙ ቁሳቁሶች በመጠቀም መማር ይቻላል ፡፡

በዚህ ጊዜ እቤቱ ያለ ሰው የተለያዩ ምግብ አሰራሮችን በየቀኑ መማር ፣ ዩቲዩብ ላይ የተለያዩ ቲቶሪያሎች በማውረድ በነፃ ክህሎቶችን መግኘት ፤ በነፃ ትምህርት የሚሰጡ Online ትምህርቶችን መከታተል በተጨማሪም አዳዲስ ልማዶችን መሞከር ለምሳሌ መጻፍ ፣ መሳል ፣ጥልፍ መስራት አዳዲስ የእስፖርት አይነቶችን መለማመድና እቤት ውስጥ የተበላሸ ነገሮችን መጠገንና ማስተካከል ይቻላል፡፡

በመስሪያ ቤት ያለ ሰው አዳዲስ ሀላፊነቶች
ስራችን ላይ ጨምሮ ቢወጣ ( እዚህ ላይ ግን አብዛኞቻችን ስለምንሰንፍ አሁን ያለኝን ሃላፊነት ራሱ በስነስርአቱ አልተወጣንም ብለን እናስባለን ) ግን አዲስ ሀላፊነት መቀበል የበለጣ የሚከብድ ነገር አይደለም እንዲያውም ቋሚ ሃላፊነቱን የበለጠ እንድንወጣ ይረዳናል፡፡

3. ለሌሎች ማካፈል

ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ደስተኛ ነው ፡፡ ሁሉም ሰው ወይ ለሀይማኖቱ አልያም ለሕሊናው ሲል መለገስ / ማካፈል ይወዳል ፡፡ ይህም የሆነው ሰዎች ከሰጠን / ለሌሎች ካካፈልን በኀላ በውስጣቸን የሚፈጠረው የኬሚካል ለውጥ ምክንያት በጣም ደስተኛ ስለምንሆን ነው ፡፡ መስጠት አወንታዊ አመለካከትን ይፈጥርልናል ፣ ከፈጣሪ ጥሩ መልስ እንድንጠብቅ ያደርጋል ፣ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ያሳድግልናል አላማችንን የበለጠ ለመፈፀም ያተጋናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ሰዎች ላደረጉልን ነገሮች ምስጋናን መለገስ
*በቅርብ ያሉ ሰዎችን ስለውሎአቸው መጠየቅ
*ጊዜያችንን ለሚፈልጉ ሰዎች መገኘት
*ካለን ገንዘብ ፣ ችሎታ ለሌሎች ለተቸገሩ ወገኖች መስጠት
*በመጨረሻም ዋናው መስጠት የምንችለው በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ መሰማራት


4. ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ

ጥሩ ወዳጅነት / ዝምድና አይምሮን ከሚያድሱ ነገሮች ቀዳሚው ነው ፡፡ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር ለራሳችን ያለንን አመለካከት ከማሳደጉ በተጨማሪ አስደሳች ጊዜያቶችን እንድናሳልፍ ዕድል ይሰጠናል ፡፡ ከሰዎችም የድጋ ስሜት እንድንቀበልና እንድንሰጥ ይረዳናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ከቤተሰቦቻችን ጋር ጊዜ ሰተን የጫዎታ ፣ የመወያያ የመመገቢያ ጊዜ ማሳለፍ ፡፡
*ድጋፍ የሚፈልጉ ጓረቤት ዘመዶችን ጊዜ ሰተን መጠየቅ ፣ ሰዎችን በሆስፒታልና በእስር ቤት መጎብኘት፡፡
*ካገኘናቸው ጊዜያት ያስቆጠሩ ወዳጆቻችንን ጋር መደወል።
*በዝንባሌያችን መሰረት በአካባቢያችንም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የተለያዩ ሕብረቶች ውስጥ መሳተፍ፡፡

5. ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት

ከምንም በላይ አሁን ላሉበት ነገር ትኩረት መስጠት የአዕምሮ ጤንነታችን እንዲጠበቅ ያደርጋል ፡፡ ብዙ ሰው አሁን ባገኘው ነገር እንደመደሰትና ፈጣሪን እንደማመስገን ትናንት ስለደረሰበት በደል እያሰበ ያዝናል ፣ ትናንት ስለሰራው ስህተት እየተፀፀተ ይኖራል ። ከዚህም ሲቀጥል ስላልኖረበት ነገ መኖሩን ሳያውቅ ከልክ በላይ "ምን እሆን ?"ብሎ እየተጨነቀ ዛሬውን ያበላሻል ፡፡

ሁልጊዜ አሁን ላይ ትኩረት መስጠት ሕይወትን የበለጠ እንድንረዳና እንድንወድ ያረገናል፡፡

#ማድረግ ያለብን ነገሮች

ትናንት በሕይወታችን የሆኑ መጥፎ ነገሮች መርሳት ባንችልም እነዛ ነገሮች ግን ዛሬ ላይ መተው ሕይወታችንን እንዲረብሹ አለመፍቀድ፡፡


ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

ጽሑፉ ለናንተ ከጠቀማችሁ ሎችም እንዲጠቀሙበት #Share በማድረግ አካፍሉ! ማካፈል ከዚህ ይጀምራል፡፡
www.tg-me.com/psychoet

------ተጀመረ------

ባለፈው አመት ሲሰጥ የነበረውና ብዙ ሰዎች የተጠቀሙበት የሕይወት ማሻሻያ ስልጠና ( በውስጡ የሕይወት አላማን መረዳትና በአላማ መኖርን ፣ የስሜት ብልሀትን፣ በሕይወታችን የሚገጥመን ድብርትን ፍርሃትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣትን ፣ስልታዊ ችግር አፈታትን ፣ ውጤታማ የሰዓትና የገንዘብ አጠቃቀም )የሚያካትተው ስልጠና አሁን ያለውን ኹኔታ በማገናዘብ ተጀምሯል ፡፡ ምዝገባ ከሰኞ የካቲት 22 ጀምሮ ይካሄዳል ፡፡
የስልጠና አድራሻ ፦ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ
የስልጠና ቀናት ቅዳሜና እሑድ በመረጡት ፈረቃ ቅዳሜ (4-6) / ቅዳሜ (10-12) / እሑድ (4-6) /እሑድ (8-10)
#ተጀመረ!
ሲጠበቅ የነበረው ለአንድ ወር የሚቆይ ተግባራዊ የህይወት መምሪያ ስልጠና ተጀምሯል።

-ሳይኮሎጂን መረዳት
-የህይወትን አላማ ማግኘት
-የስሜት ብልህነት
-ውጤታማ እቅድ አወጣጥና ጊዜ አጠቃቀም
-ስልታዊ የሕይወት ችግር አፈታት ዘዴዎች
-ድብርትና ጭንቀትን ማሸነፍ እና ሌሎችም ስልጠናዎችን ያካተተ ነው።

በ#500 ብር ብቻ !

★ልምድ ባላቸው ሳይኮሎጂስቶችና የህይወት ክህሎት አሰልጣኞች ይምጡ ይሰልጥኑ።
★ሁሉንም ለተካፈለ በነፃ የግል የማማከር ጊዜ ፣ የንግግርና የተግባቦት ክህሎት ስልጠና ሰርተፊኬትን ጨምሮ ያገኛል።


#መጋቢት 4 እና 5_ይጀምራል ። ያለው ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድሞ ለተመዘገበ በፈለጉት ፈረቃ የመሰልጠን ቅድሚያ እንሰጣለን ፡፡

በአካል መመዝገብ ያልቻላችሁ በስራ ሰአት ( ሰኞ - አርብ 2-12) በስልክ በመደወልና መረጃዎችን በመላክ መመዝገብ ይቻላል ፡፡0912664084 ይደውሉ።

ያሉን ፈረቃዎች
ቅዳሜ 4-6 ቅዳሜ 10-12
እሑድ 4-6 እሑድ 8-10

አድራሻ 4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ ከቶታል ጀርባ - ህንፃ ቁጥር 219
@Psychoet
#የጥሩ_እንቅልፍ_9_ጠቀሜታዎች
ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው

1. እንቅልፍ ልብዎን ጤናማ ያደርገዋል

እንቅልፍ ማጣት የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ(ስትሮክ) እንደሚያባብስ ተመራማሪዎች ይናገራሉ ይህም የሚሆነው የደም ግፊት እና ኮሌስትሮል መጠንን በመጨመር መሆኑን ይናገራሉ ፡፡በእያንዳንዱ ምሽት ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል እንቅልፍ ካገኙ የልብዎን ጤና የተጠበቀ ይሆናል ፡፡

2. እንቅልፍ ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል

ተመራማሪዎች ለብርሃን መጋለጥ የሜላቶኒንን መጠን እንደሚቀንስ ያምናሉ ፡፡ ሜላተንቲን የእንቅልፍ ና የመንቃትን ዑደትን የሚያስተካክል ሆርሞን ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ዕጢዎችን እብጠት በመቀነስ ካንሰርን ይከላከላል፡፡ ሰውነትዎ የሚፈልገውን ሜላቶኒንን ለማምረት እንዲረዳዎ መኝታዎ ጨለመ ባለ ስፍራ ያድርጉ እንዲሁም ከመኝታዎ በፊት ኤሌክትሮኒክስን ከመጠቀም ይቆጠቡ ፡፡

3. እንቅልፍ ውጥረትን ይቀንሳል

ሰውነትዎ እንቅልፍ እጥረት ሲኖርበት ወደ ውጥረት(ስተርስ) ሁናቴ ይሄዳል ፡፡ ይህም ውጥረት ወየንም ስተርስ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ የመያዝ እድልን ይጨምራል፡፡

4. በቂ እንቅልፍ ማግኘት የበለጠ ንቃትን ይሰጣል

ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ ንቃት እንዲሰማዎት እና በሚቀጥለው ቀን እንዲነቃቁ ይረዳዎታል ፣ በተጨማሪም ጥሩ ስሜት እነዲሰማዎት በማድረግ ሌላ ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ እድልዎተን ይጨምራል።

5. እንቅልፍ የማስታወስ ችሎታዎን ያሻሽላል

ተመራማሪዎች እስካሁኑ ሰዐት ድረስ ለምን እንደምንተኛ ሙሉ በሙሉ አልተረዱም ፣ ነገር ግን እንቅልፍ የማስታወስ ዐቅምን በማጠናር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ደርሰውበታል፡፡
በእንቅልፍ ጊዜ ሰውነትዎ አረፍ ሊል ይችላል ፣ነገር ግን አንጎልዎ ቀንዎን በማቀነባበር የተያዩ ግንኙነቶችን በማድረጉ ሥራ ላይ ነው ፡፡ እነዚሀም ግንኙነቶች በተያዩ ክስተቶች ፣ በስሜት ህዋሳት ፣ ስሜቶች እና ትውስታዎች መካከል ሲሆን በቂ እንቅልፍ ማግኘት ነገሮችን በተሻለ ለማስታወስ እና ለማስኬድ ይረዳዎታል ፡፡

6. እንቅልፍ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል

ተመራማሪዎቹ እንዳሳዩት በማታ ጥቂት ሰዓታት የሚተኙ ሰዎች ከመጠን በላይ ወፍራም ወይም ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው መሆናቸውን ነው ፡፡ የእንቅልፍ እጥረት በሰውነት የምግብ ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሆርሞኖችን መጠን ይጎዳል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት የምግብ ፍላጎትን የሚያስተካክሉ ሆርሞኖች ጋሬሊን እና ሌፕቲን በእንቅልፍ እጥረት ምክንያት ተስተጓጉለው ተገኝተዋል ፡፡ ክብደትን ለማቆየት ወይም ክብደት ለመቀነስ ከፈለጉ ፣ በመደበኛነት በቂ እንቅልፍ ማግኘት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አይርሱ።

7. ማቅለብ ብልጥ ያደርግልዎታል

በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ መውሰድ ለአጠቃላይ ጤናዎ ጥሩ ሲሆን በተጨማሪም የበለጠ ምርታማ እንዲሆኑ አዕምሮዎትን የሚያድስ አማራጭ ነው ፡፡ ጥናቶችእንደሚያሳዩት ከሆነ በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ የሚወስዱ ሰዎች የአዕምሮ ወይንም ኮግኒቲቭ ተግባር እና የ ስሜት መሻሻል ማሳየታቸውን ነው፡፡

8. እንቅልፍ የጭንቀት በሽታ አደጋዎን ይቀንሳል

ሴሮቶኒንን ጨምሮ እንቅልፍ በሰውነትዎ ውስጥ ያሉትን ብዙ ኬሚካሎች ይነካል። የ serotonin ጉድለት ያላቸው ሰዎች በጭንቀት በሽታ የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ትክክለኛውን የእንቅልፍ መጠን እያገኙ መሆኑን በማረጋገጥ ድብርትዎን ለመከላከል በየዕለቱ ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል የዕንቅልፍ ጊዜ ይውሰዱ፡፡

9. እንቅልፍ ሰውነቱን በራሱ እንዲጠገን ይረዳል

እንቅልፍ ዘና የማለት ጊዜ ነው ፤ ሰውነታችን በቀኑ ጊዜ፣ በአልትራቫዮሌት ጨረሮች እና በሌሎች ጎጂ ነገሮች ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ጠንክሮ የሚሠራበት ጊዜ ነው ፡፡ ተኝተው እያለ ሴሎችዎ የበለጠ ፕሮቲን ያመርታሉ ፡፡ እነዚህ የፕሮቲን ሞለኪውሎች የሰውነት ክፍሎችዎን በመገንባትና በማድስ ጉዳቱን ለመጠገን ያስችላቸዋል ፡፡

©በአቤል ታደሰ

ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው
መልካም አዳር
@Psychoet
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት
1. ጥሩ አድማጭ መሆን

ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡

2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን

በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡

3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ

የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡

4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ

ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡

5. አቀማመጥን ማስተካከል

ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡

6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት

እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡

7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ

ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡

8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡

9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር

በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡

ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet

በሚቀጥለው ሳምንት ከሚጀመረው የሕይወት ክህሎት ስልጠናዎች አንዱ የመግባባት ክህሎት /Effective communication አንዱ ነው ፡፡ ይህንን ለሕይወት የሚጠቅም ክህሎት ለማዳበር የምትሹ በቀሩን ጥቂት ቦታዎችና ጥቂት ቀናት ቀድማችሁ እንድትመዘገቡ እናበረታታለን ፡፡
ሙሉ መረጃ በመደወል መጠየቅ ይቻላል 0912664084

ለሌሎች #Share በማረግ እናስተምር
ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet
©Zepsychology
#ሊጀመር_ነው! ጥቂት ቦታዎች ቀርተውናል፡፡
ሲጠበቅ የነበረው ለአንድ ወር የሚቆይ ተግባራዊ የህይወት መምሪያ ስልጠና 4ኛ ዙር ተጀምሯል።

-ሳይኮሎጂን መረዳት
-የህይወትን አላማ ማግኘት
-የስሜት ብልህነት
-ውጤታማ እቅድ አወጣጥና ጊዜ አጠቃቀም
-ስልታዊ የሕይወት ችግር አፈታት ዘዴዎች
-ድብርትና ጭንቀትን ማሸነፍ እና ሌሎችም ስልጠናዎችን ያካተተ ነው።

በ#500 ብር ብቻ !

★ልምድ ባላቸው ሳይኮሎጂስቶችና የህይወት ክህሎት አሰልጣኞች ይምጡ ይሰልጥኑ።
★ሁሉንም ለተካፈለ በነፃ የግል የማማከር ጊዜ ፣ የንግግርና የተግባቦት ክህሎት ስልጠና ሰርተፊኬትን ጨምሮ ያገኛል።

#መጋቢት 4 እና 5_ይጀምራል ። ያለው ቦታ ውስን ስለሆነ ቀድሞ ለተመዘገበ በፈለጉት ፈረቃ የመሰልጠን ቅድሚያ እንሰጣለን ፡፡

በአካል መመዝገብ ያልቻላችሁ በስራ ሰአት ( ሰኞ - አርብ 2-12) በስልክ በመደወልና መረጃዎችን በመላክ መመዝገብ ይቻላል ፡፡0912664084 ይደውሉ።

ያሉን ፈረቃዎች
ቅዳሜ 4-6 / ቅዳሜ 10-12
እሑድ 4-6 / እሑድ 8-10

አድራሻ 4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ( ከቶታል ጀርባ) - ህንፃ ቁጥር 219

ስልጠናውን መካፈል ለሚፈልጉ ጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው @Psychoet
መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ) ©Zepsychology
@Psychoet
#የስሜት_ብልሃትና_ተግባቦት
#Emotional_Intelligence& Communication
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE

የስሜት ብልህነት ማለት ስሜታችንን የማወቅ ፣ የመረዳት የመምራት ችሎታ ነው ፡፡ ጥሩ የስሜት ብልሀት ያላቸው ሰዎች የተመሰገኑ ፣ በማንኛውም ሁኔታ የተረጋጉ ፣ የሩጫ ህይወት የማይመሩ ፣ የበለጠ ደስተኛና ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን የሚመሩ ናቸው ፡፡

በህይወታቸው በጣም ደስተኛና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ያለቸው የስሜት ብልሃት ( Emotional Intelligence ) ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሙያውና ችሎታው እያላቸው በባህሪ ምክንያት ይሰናበታሉ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሀሳብ እያላቸው ባላቸው ባህሪና በተግባቦት እጥረት ምክኒያት ሰሚ ያጡ ፣ ተቀባይነት ያጡ ሰዎች ብዙ ናቸው ፡፡

#ለዛሬ እነዚህ የተግባቦትና የስሜት ብልሃት አለመኖር በሕይወታችን የሚያመጡትን ችግር እንመልከት ፡፡

እኔ አንዱን ድግሪዬን በማኔጅመንት ስሰራ የመመረቂያ ጽሑፌ (Competency development in business areas ) የሚል ነበር ፡፡ በዚህ ጥናት ያገኘሁት አንዱ ግኝት ሰዎች ለቢዝነሳቸው መውደቅና አለማደቅ አንዱና ዋና ምክንያት ያላቸው አነስተኛ #የተግባቦትና #የስሜት_ብልሃት ነው ፡፡

#የስሜት_ብልሃትና_ጥሩ_ተግባቦት_የሌላቸው_ሰዎች_መገለጫዎች

★የራሳቸውን ስሜት አይቆጣጠሩም ( በቀላሉ ይናደዳሉ ፣ ይበሳጫሉ ፣ ከልክ ያለፈ ቁጣ ይታይባቸዋል )

★ከሰው ጋር ተግባቢ አይደሉም ፣ ፍርሀት ጭንቀት ይታይባቸዋል ፣ ስለ ራሳቸው አሉታዊ አመለካከት የላቸውም

★በትንሽ ነገር አብዝተው ያዝናሉ

★በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እና ስሜት ስለማይረዱ ፣ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር በሀሳብ ፣ በወሬ የመጋጨት ሁኔታ ይታይባቸዋል

★ሰው ስለነሱ ስላለው አስተሳሰብ አብዝተው ይጨነቃሉ ፣ ይረበሻሉ ፡፡

★ሃሳባቸውን በድፍረት አይገልፁም ፣ እየተጎዱ ከጉዳቱ መውጣት እየቻሉ ዝምታን ይመርጣሉ ፣

★ለውሳኔዎች ከተገቢው በላይ ይቸኩላሉ፣ በወሰኑት ነገር ለመጸጸት ደግሞ የመጀመሪያ ናቸው

ከላይ የዘረዘርኳቸው መገለጫዎች( የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት ክህሎት አለመኖር) የሚያመጣቸው ጉዳቶችና የባህሪ መገለጫዎች ናቸው ።

በእርግጥ ተግባቦትም ሆነ የስሜት ብልህነት ሳይንሳዊ የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ማሳደግ ይቻላል ፡፡ ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ችግሮች በራሳችሁ ላይ የምታዩ ሰዎች ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ በጥቂት ጊዜ ጥሩ የሆነ ተደጋጋሚ ተግባራዊ ልምምዶችን በማረግ መዉጣት ይቻላል ፡፡
_______________
#በዚህ ሳምንት መጨረሻ /መጋቢት 4 እና 5 በሚጀምረው የሕይወት ክህሎት ስልጠና ላይ እነዚህን ጉዳዮች በስፋት የማነሳቸው ሲሆን በተጨማሪም በየቀኑ የሚሰሩ እነዚህን ክህሎት የሚያሳድጉ ልምምዶችን በተግባር እናያለን፡፡ ለመለወጥ የወሰናችሁ ሰዎች ካሉን ፈረቃዎች በተመቻችሁ መርጣችሁ +251912664084 በመደወል ተመዝገቡ
የስልጠናው ሙሉ ማስታወቂያ ከዚህ በፊት ተለጥፏል ፡፡

ይህ ፅሁፍ ለሌሎችም እንዲደርስና ስልጠናው የሚያስፈልጋቸው እንዲያገኙት ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

@PSYCHOET
#መልካም_መጋቢት_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

አንድ ቀን ነገር ሁሉ ቀላል ይሆናል ! ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ለምትወዱት ጓደኛ #መልዕክቱን አስተላልፉ

@Psychoet
#ማኅበራዊ_ክህሎት
Telegram www.tg-me.com/psychoet

ማኅበራዊ ህይወት ከውልደት እስከ ሞት የሚኖር እና ቀጣይነት ያለው ሂደት ሲሆን በትምህርት እና ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት የሚዳብር ነው፡፡የሰው ልጅ ስለራሱ እና ስለሚኖርበት ማኅበረሰብ የሚኖረውን ዕውቀት በተለያየ መልኩ ማለትም የመግባቢያ ቋንቋ በመማር ፤ አካባቢያዊ ሁኔታውን በመመልከት እንዲሁም ማኅበራዊ ክህሎቶችን በመማር እያሳደገ ይሄዳል፡፡ ይህ የማኅበራዊ ህይወት ክህሎት በአግባቡ መዳበር ለተሟላ ስብዕና እና ዕድገት ወሳኝነት አለው፡፡

 የማኅበራዊ ህይወት አስፈላጊነት

#ለተሟላ አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊ እና ማኅበራዊ ዕድገት እንዲኖር እና የህይወት ቀጣይነት እንዲረጋገጥ፡፡
#ለሁለንተናዊ ሰላም ፤ ጤናና ደስታ፡፡
#ረጅም ዕድሜ ለመኖር፡፡
#ፍቅር ፤ መረዳዳት ፤ ስነ-ምግባር… እነዚህን የአንድ ማኅበረሰብ ህጎች እና ስርዓቶች ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ፡፡
#የሎሎችን ፍቅርና ድጋፍ ለማግኘት፡-

አዎንታዊ የእርስ በርስ ግንኙነት እንቅፋቶች

የግል ባህሪ

ራስ ወዳድነት ፤ ይሉኝታ ማጣት ፤ ግዴለሽነት ፤ሃቀኛና ታማኝ አለመሆን ፤ ኩራት ፤ ንቀት ፤ ያለፈ ጊዜ መጥፎ ተሞክሮ….

የሌሎች ዕሴቶችን እና አመለካከት ልዩነቶችን አለመረዳት

እሴቶች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው ሁኔታዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ዕሴቶችን መረዳት እና የአመለካከት ልዩነቶችን ማክበር ለማኅበራዊ ግንኙነት መሻሻል ወሳኝ ነው፡፡ ይህም ማለት እሴቶቻችንን ወይም በህይወታችን ከፍተኛ ቦታ የምንሰጠውን ነገር ለይቶ ማወቅ ዓላማ ያለው ህይወት ለመምራት ይረዳናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሌሎችን ሰዎች እሴት ማወቅም እንዲሁ ከሰዎች ጋር ለሚኖረን መልካም ግንኙነት ወሳኝነት አለው፡፡ ምክንያቱም ሌሎች ሰዎች በህይወታቸው ዋጋ የሚሰጡትን ነገር ለይተን ካወቅን እና ለፍላጎታቸው አክብሮት ከሰጠን ሰላማዊ ግንኙነት ለመመስረት እንችላለን፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው የሚኖርበትን ማኅበረሰብ እሴቶች በሚጣረስ መልኩ ሲንቀሳቀስ ከማኅበረሰቡ የመገለል ዕጣ ሊገጥመው ይችላል፡፡

በአጠቃላይ ታማኝነት ፤ እውነት ፤ ግልጽነት ፤ ፍቅር ፤ መረዳዳት ፤ ትዕግስት ፤ መቻቻልና ኃላፊነትን መቀበል መቻል የመሳሰሉት በማኅበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ዕሴቶች ናቸው፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
2024/09/29 07:21:42
Back to Top
HTML Embed Code: