Telegram Web Link
#ጭንቀትን_መቀነሻ_ቴክኒኮች

ይህም በሥልጠናና በባለሙያ የካውንሰሊንግ አገልግሎት ሊገኝ ይችላል፡፡ ሁለት ቴክኒኮችን ብቻ እንመልከት (በርካታ ቴክኒኮች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል)፡-

1⃣ #ABCDE_ቴክኒክ :

ይህ ቴክኒክ አልበርት ኤሊስ (Albert Ellis) በተባሉ የስነልቦና ባለሙያ የተገኘ ዘዴ ነው፡፡

አልበርት ኤሊስ ሰዎች ወደ ጭንቀት የሚገቡት አግባብ ያልሆነ አስተሳሰቦችና እምነቶች (Irrational beliefs and thoughts) ሲጠናወቷቸው ነው ብለው ያምናል።

ለምሳሌ:-

👉ሰው ሁሉ ይጠላኛል፣
👉ሰው ሁሉ ይወደኛል፣
👉ከሰው ሁሉ ተቀባይነትን ማግኘት አለብኝ፤
👉በምሰራው ስራ ሁሉ መሳሳት የለብኝም...ወዘተ የሚሉ እምነቶችና አስተሳሰቦች ለጭንቀት እንደሚዳርጉ ያሰምሩበታል።

እኚህ ሰው እንደሚሉት፥

✔️አሉታዊ ነገሮችን አጋኖ ማየት (Awfulising)

✔️ጥቁርና ነጭ እሳቤ (Black and White thinking 👉ይህ እንግዲህ አንድን ነገር ጥሩ ወይም መጥፎ ብሎ መመደብና በውስጡ ሊኖር የሚችለውን የተወሰነውን ጥሩ ነገር አለማየት ነው።

✔️ጠቅላይ እሳቤ(Over generalizing) 👉ሁልጊዜ፣ ሁሉም ሰው፣ በፍፁም.....ወዘተ የሚሉ ቃላትንና ሃሳቦችን መጠቀም፤
(ሁሉም የሚል አባዜ አለባቸው)

✔️Personalizing የማይመለከተንን ነገር ከራሳችን ጋር አቆራኝቶ ማየት፤

✔️Filtering በሁኔታዎች ውስጥ አሉታዊን ነገር ብቻ መርጦ ማየት፤

✔️Mind reading ይህንን አስቦ ነው ብሎ ያለምንም ማስረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ፤

✔️Blaming 👉ሰዎችን መተቸትና መውቀስ

✔️Labeling 👉ለራስ ስያሜ መስጠት

ለምሳሌ: ደካማ ነኝ፤ዋጋ ቢስ ነኝ...ወዘተ ማለት አግባብ ላልሆኑ አስተሳሰቦች ምክኒያት ናቸው ይሉናል፡፡

ቴክኒኩን ተንትነን ለማየት እንሞክር

#Antecedent (Activating event, Stimulus)፡

ይህ ማለት ጭንቀትን የሚቀሰቅሰው ሁኔታ ወይም ነገር ነው (ተንኳሽ እንበለው)፡፡
" ይህ ተንኳሽ የኛን ምላሽ (Response) ይጠይቃል።

ለምሳሌ:- ከስንት አንድ ቀን ቀጠሮ ብናረፍድ ጭንቀት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት ጭንቀትን የሚፈጥርብን ጉዳይ ማርፈዳችን ነው ማለት ነው፡፡

#Belief_our_cognition_about_the_situation ፡-

ይህ እንግዲህ ስለ ተንኳሹ ያለን ሃሳብና እምነት ነው፡፡

ለምሳሌ ማርፈዴ ያለኝን ተቀባይነት ያሳጣዋል፣ በምንም አይነት ምክኒያት ቢሆን ማርፈድ አሳማኝ አይደለም...ወዘተ የሚል እምነት ማለት ነው፡፡

#Consequences- the way that we feel and behave፡

ይህ ውጤት ነው - ጭንቀታችን፡፡ ይህ ምን ባህሪ ይፈጥራል? ቶሎ ለመድረስ አላግባብ ጣልቃ እየገባን መኪናችንን መንዳትን፣ በእጃችንም በአንደበታችንም የተንቀረፈፈ የመሰለንን ሾፌር መስደብ፣ መቆጣት፤ ከአስፋልት ወጥቶ በእግረኛ መንገድ መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

እዚህ ላይ አልበረት ኤሊስ ይሞግታሉ “ያስጨነቀን ማርፈዳችን ነው ወይስ ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው?”

አሳቸው እንደሚሉት፤ ውጤቱን የፈጠረው ማርፈዳችን (stimulus) ሳይሆን ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው ባይ ናቸው፡፡

#Dispute:- is the process of challenging the way we think about situations:

ይኸኛው አስተሳሰባችንን የምንሞግትበት ዘዴ ነው። እሳቸው አግባብነት የሌለውን አስተሳሰብና እምነት መሞገት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

ለምሳሌ ከላይ የጠቀስነውን ማርፈድ ብንወስድ እምነታችንን ስንሞግተው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
“ብዙ ጊዜ በሰዓቱ የምገኝና ቀጠሮ አክባሪ የሆንኩ ሰው ነኝ፡፡ አንድ ዛሬን ባረፍድ ተቀባይነቴን አያሳጣም”፣ “ለማርፈዴ ምክኒያት የሆነኝ የትራፊክ መጨናነቅና ያልጠበቅሁት የመንገዶች መዘጋጋት ነው፡፡ ስለዚህ በቂ ምክኒያት ሊሆን ይችላል፡፡” እነዚህን ምክኒያቶች በማሰብ ነባሩን ሃሳብ መሞገት እንደሚገባ ይጠቁማሉ፤ አልበርት ኤሊስ፡፡

#Effect : ይሄ አዲሱ ውጤት ነው።
አስተሳሰባችንን ከሞገትነውና በአዲስ አስተሳሰብ ከተካነው በኋላ የሚፈጠር ባህሪ ነው፡፡ የላይኛውን ምሳሌ ብንከተል ተረጋግቶ መንዳት፤ ተራ መጠበቅ፤ በተፈቀደው አስፋልት መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

👉ማስተዋል ያለብን ሃሳብ ስሜታችን እና ባህሪያችን ላይ ተፅእኖ ይፈጥራል፡፡ ማወቅና አስተሳሰብን መለወጥ ደሞ አስፈላጊ ነው፡፡

#share

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
Telegram : www.tg-me.com/psychoet
youtube : youtube.com/thenahusenai
መልካም ቀን!
#ተሰሚነት
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ብዙዎቻችን የሚጎለን ክህሎት ስለሆነ ሌሎችም እንዲማሩ አንብበን #Share እናርገው

“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡ ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡

ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡

ቅለት

ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡

ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ

“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡

በራስ መተማመን

አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ ጉልበት አላቸው፡፡

በሌሎች ዓይን ማየት

ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣ ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ መቼም አይጠፋም፡፡

ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡

እጥረትን መፍጠር

ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣ የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣ በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡

ዝግጅት

ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመናችንንም ይገነባል፡፡

ለምሳሌ እነዚህን በሙሉ ክህሎቶች ዶ/ር ምህረት ላይ እናገኛለን ፡፡ የመሰማቱ አንዱ ሚስጢር ይሄ ነዉ ፡፡ ሲያስተምር አይታችሁ ከሆነ የሚያስተምረውን ነገር ቀለል አርጎ ፣ በራስ መተማመን ለአድማጭ በሚስብ መልኩ ያደርጋል ፡፡ ይህ በሁላችን አድማጮቹ ዘንድ ተሰሚነትን ፈጥሮለታል ፡፡ በሌላ በኩል አንድ ሰፈር /ስራ ቦታ የምናውቀውን ሳያቋርጥ የሚያወራ ፣ ንግግር የማያስጨርስ ሰው ስናስብ እንኳን ለመስማት ከሱ ጋር ለማውራት ይቀንቀናል ፡፡ እንግዲህ ሚስጥሩ ይሄው ነው ፡፡

በሰዎች ዘንድ ለመሰማት በዕውቀትና በጥበብ እናውራ !
(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
#Share & #Like oue page - fb.com/psychologyet
_________________________
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#መራር_እውነታዎች

ዶ/ር ምህረት ደበበ

#ምንም ነገር ለዘላለም አይቆይም፡፡ ችግሮችህ፣ የከበቡህ ሰዎች፣ ስራህ፣ ትዳርህ እና ግንኙነቶችህ ሁሉ ለጊዜዉ ነዉ፡፡ የሁሉም ነገር ፍፃሜ የሆነ ቀን ላይ ሲሆን ታየዋለህ፡፡ በህይወቴ ሁሉ አብረዉኝ ይኖራሉ ያልካቸዉ ነገሮች እንኳን ሳይቀሩ ሲፈረካከሹ ታያቸዋለህ።

#ለሁሉም ነገር ተራ አለዉ፡፡ ሰዉን ብትጠቅም ጊዜዉን ጠብቆ አምላክህ ይከፍልሃል፡፡ ብትጎዳም እንዲሁ። በሰፈርከዉ ማንነት ጊዜዉ ሲደርስ ትሰፈራለህ።

#ማንም ሰዉ ስላንተ አይጨነቅም፡፡ 20 ፐርሰንቱ ብቻ ስላንተ ሲጨነቁ (እነሱም የቅርብ ጓደኞችህና ቤተሰቦችህ መሆናቸዉን አትዘንጋ) 80 ፐርሰንቱ ግን ኑር አትኑር አንዳች ቅንጣት ስላንተ አያስቡም፡፡ ችግሮችህን ለነዚህ ለ 80 ፐርሰንት መናገር እራስህን ማባከን ነዉ ምክንያቱም ችግርህ ለነሱ ምናቸዉም አይደለምና! የራሳቸዉ ጉዳይ ብቻ ያሳስባቸዋልና ቆጠብ በል።

#ሰዎች በህይወትህ ይመጣሉ ደግሞም ይሄዳሉ፡፡ አንድ ቀን ለብቻህ ሰዉ በሌለበት ልትሞት ትችላለህና ሰዎችን አትደገፍ።

#ከ5-6 የልብ የምትላቸዉ ሰዎች በቀር ፌስቡክ ላይ ያሉት የጓደኛ ጋጋታ ምንም አይጠቅሙህም፡፡ ብትሞት እንኳ ቀብርህ ላይ የማይመጡ ብዙዎች መሆናቸዉን እወቅ።

#የስራ አለቃህ እንድታድግና የተሻለ ቦታ እንድትይዝ ሊመኝ ይችላል ግን መቼም እንድትበልጠዉ አይፈልግም፡፡ ምንም ሽልማትና ጭብጨባ ቢበዛልህ ከሱ እንደምትበልጥ ካሰበ አንተን ለመገፍተር ወደኋላ አይልም።

#98 ፐርሰንቱ ሰዉ መቼ እንደተወለድክ እንኳን አያዉቅም (2 ፐርሰንቱ መቼም እነማን እንደሆኑ መገመት አያቅትህም)፡፡ ካላመንከኝ ሞክረህ እየዉ!

#የዉሸት ጓደኞችህ የተሻለ ህይወት እንድትመራ በፍጹም አይፈልጉም፡፡ ነገሮች መልካም ሲሆኑ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሊያስገርምህ አይገባም! አንድ ቀን ህልምህ 'ወለም' ብሎ ካዩ እጃቸዉን ቀስረዉ ይስቁብሃል፡፡ የዛኔ ያልሳቁብህን የልብ ጓደኞችህ አድርጋቸዉ።

#ገንዘብ ያለዉና ፀዳ ብሎ የሚመላስን ሰዉ ብዙዎች ሲያከብሩት ትመለከታለህ ፡፡ የማያዉቅህ እንኳን ቢሆን ፀዳ ካልክበት ሊያከብርህ ሲዳዳዉ ታየዋለህ።

#ለሰዎች ምክር መስጠት በጣም ቀላል ነዉ ነገር ግን ምክርን ወደተግባር መቀየር ከባዱና አስቸጋሪዉ ነገር ነዉ፡፡ አንዳንዴ ሰዉን ካለበት ማጥ ለማዉጣት ካሰብክ ከምክር በላይ የሆነ ስብዕና ሊኖርህ ይገባል፡፡

#አንድ ዉሸታም ጓደኛህ ከ 100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል፡፡ ጠላቶችህን ተከታተላቸዉ ጓደኞችህን ደግሞ በጣም ተከታተላቸዉ።

#ነገሮች መልካም እንዲሆኑና እንዲሳኩ ያለ የሌለ ጥረትህን አድርገህ ሳይሳካልህ ቀርቶ ይሆናል፡፡ ይሄ ያንተ ደካማነት ሳይሆን ህይወት እንዲህ አይነት ገፅታም ስላላት ነገሩን ተቀበለዉ።

#ለመወደድ ልዩ ሰዉና ሁሉንም ሞካሪ መሆን አይጠበቅህም፡፡ እንዳንዴ ሰዉ ሁሉ ባይወድህ እንኳን ይሄ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተረዳ፡፡

#በሰዎች መጠላትንም ቀለል አድርገህ ዉሰደዉ ምክንያቱም እንዴት እራስህን ማሳደግ እንዳለብህ ማጤን ወሳኙ ነገር ሲሆን የሰዎችን ስሜት እያዳመጥክ ከፍና ዝቅ እያልክ መኖር አይጠበቅብህም፡፡

#የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎች በሀሳብህ አለመስማማታቸዉ አንተነትህ ላይ የሚያመጣዉ ነገር የለም፡፡ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትዉጣ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ።

#ይቺ አለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነዉ፡፡ ባጠቃላይ አለም እራስ ወዳድ ናት።

#ሰዎች ስለ ደስታ አጋነዉ ሲያወሩ ትሰማ ይሆናል፡፡ በኣጭሩ ደስታ ማለት ስሜትህ ሳይሆን አእምሮህ ያለበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ደስተኛ ሆነህ በሰዎች ልትጎዳ ትችላለህ፡፡

#ህይወት እኩል አይደለችም፡፡በሆነ ነገር ጎበዝ ብትሆን ካንተ የበለጠ በጣም ጎበዝ ሰዉ አለ...እኩልነት ዉሸት ነዉ፡ ስለዚህ በመኖርህ ብቻ ተደሰት፡፡

...................................................................
@Psychoet
# የአለም__እውነታወች
1. የሚከተልህ ሁሉ አድናቂህ አይደለም

2. ውሻ ጭራውን የሚቆላው ላንተ ሳይሆን
በእጅህ ላለው ዳቦ ነው፣ አስመሳይና
ተለማማጭ ሰውም እንዲሁ ነው።

3. ሕይወት ድልድይ ናት፣ አቋርጣት እንጂ
በላይዋ ላይ ቤት አትስራ።

4. ውሀ ቅርፁን ከመያዣው ጋር እንደሚስማማ
ሁሉ ብልህም ራሱን ከሁኔታው ጋር ይስማማል።

5. ምንም ያህል ርቀት በተሳሳተ መንገድ
ብትጓዝም ወደኋላ ተመለስ።

6. ዝቅ ብለህ ብትመለከት ምን ያክል ከፍ
እንዳልክ ታውቀዋለህ።

6. አንድ ሰው ስትተዋወቀው በልብሱ
ልትመዝነው ትችላለህ፣ ስትለየው ግን
በአስተሳሰቡ ትመዝነዋለህ።

7. ሠርግ እና ቀብር አንድ ናቸው። ልዩነቱ
የሠርግ አበባን ባለቤቱ ማሽተት መቻሉ ብቻ
ነው።

8. አምላክህን ደስታህን በቅንነት ብትጠይቀው
ይሰጠሀል። ብቻ በቤትህ በሀቀኝነት ኑር።

9. ማንክያ የሾርባን ጣዕም እንደማያውቅ ሁሉ
ለስሙ የተማረም የጥበብን ጣዕም አያውቅም።

10. ሀገር እንዳትጠፋ ትልቅ ነገርን አታጥፋ።
"ሰው ሆይ በትዕቢትና በንቀት መወጠርህን
አቁም። የውሸት መኖርህን፣ ሰዎችን መበደልህን፣
ፈጣሪህን ማሳዘንህን አቁምና መልካም ነገርን
አድርግ። ልብ በል ሺህ ጊዜ የውሸት ብትኖር
አንድ ጊዜ የእውነት መሞትህ አይቀርም።

ስንት ቁጥር ተመቻችሁ. ?
ፔጁን ሼር፣ ላይክ ያድርጉ
@psychoet
🔥👉 ጭንቀትን_ድብርትንና_አሉታዊ ስሜቶችን_ለመከላከል የሚረዱ_ዘዴዎች🔥👈

🎈ባለፈ ጥፋት ወይም ውድቀት ላይ በማተኮር #ፀፀት# ውስጥ አለመግባት። ከባለፈው ስህተት በመማርና አሁን/ዛሬ ላይ ማተኮር።

🎈 ማህበራዊ ተሳትፎዎችን ማድረግ።

🎈 ከተለያዩ እፆችና አልኮል #ሱሰኝነት# መቆጠብ።

🎈 ግጭቶችን፣ ቅራኔዎችንና አለመግባባቶችን በአግባቡ መፍታት።

🎈 ውጥረትንና ጭንቀትን የሚፈጥሩብዎትን ነገሮችና ሁኔታዎችን መለየትና ከእነሱ መራቅ።

🎈 በጎ ማድረግና ምላሹን ከሰዎች አለመጠበቅ።

🎈ጭንቀትና ድብርት ሲሰማዎ ለቅርብ ወዳጅ፣ ጓደኛ ወይም ቤተሰብ ማጋራት።

🎈ድንገተኛ ችግር ሲያጋጥምዎ፤ ራስን ማረጋጋት።

🎈ሌሎች ሰዎች ስለእርስዎ በሚሰጡት ትችት እና አስተያየት አለመረበሽ።

🎈 የህይወትን ጥሩ ገፅታ ማየት።

🎈በአላማና በእቅድ መኖር ፤ ጊዜን በስራ ማሳለፍ።

🎈የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ንፅህናን መጠበቅ እና ጤናማ የአመጋገብ ስርአትን መከተል።

🎈ለራስ ጊዜን መስጠትና እረፍት ማድረግ።

🎈ከሁሉም በላይ በፈጣሪ መታመንና እኛ ልንፈታ የማንችላቸውን ነገሮች ለእርሱ መተው።

መልእክቱ ለብዙዎች እንዲደርስ Share & Like አይርሱ።

© Psych ጤና Fb ፔጅ
👉በመአዛ መንክር
ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

@psychoet
💙ኦትዝም/ Autism/ASD💙

📌📌 📌 ኦቲዝም የወረርሽኝን ያህል በልጆች ላይ እየተከሰተ ያለ የእድገት ችግር ነው።

🔷 ኦትዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ልጆች ላይ በብዛት የሚታይ የተዛባ የባህሪ አይነት ልንለው እንችላለን።

🔷 ኦትዝም ከሌሎች በልጅነት ከሚከሰቱ የአእምሮ እክሎች የሚለየው በጨቅላ እድሜ የሚታይ አካላዊ የሆነ ምልክት ብዙም የለውም።

🔷 ኦትዝም ያለባቸው ሰዎች የተለያዬ ባህሪ፣ ትምህርት የመቀበል አቅም፣ የቋንቋ ችሎታ፣ ከሰው ጋር የመቅረብ ፍላጎት፣ የማስታወስ ችሎታ እና ልዩ ልዩ ተሰጥኦዎች አላቸው።

🔷📌አንድ ልጅ ኦትዝም አለበት የምንለው፡
ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ምልክቶች፡🔷📌

📌 ከሰዎች ጋር ብዙ የአይን-ለአይን ምልከታን የማያደርግ ከሆነ

📌 ከእድሜ እኩዮቹ ጋር ጓደኝነትን መመስረት ካልቻለ

📌 በዙሪያው ያሉ ሰዎች የሚያስቃቸው እና የሚያስደስታቸው ነገር ብዙም ትርጉም የማይሰጠው ከሆነ

📌 የልጅነት ምናባዊ የሆኑ ጨዋታዎችን የማያደርግ ከሆነ ለምሳሌ: እርሳስ ቢያገኝ በሱ ለመፃፍ ከመሞከር ይልቅ እርሳሱን እንደመኪና መንዳት፣ ማሽከርከር ወይም ደጋግሞ መወርወር ሊያሳይ ይችላል

📌 በእድሜ የሚጠበቀውን የቋንቋ ክህሎት ምንም አለመኖር ወይም ትንሽ ቃላት ብቻ መጠቀም

📌 ድግግሞሽ ያለው እንቅስቃሴ ማድረግ እና ያልተለመዱ ባህሪያትን ማሳየት ማለትም በአንድ እቃ ሁሌ መጫወት፣ አንድ ጨዋታ ብቻ መፈለግ፣ ያልተለመደ የእጅ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ያልተለመደ ድምፅ ማውጣት....መንጠላጠል፣ ከሰው ይልቅ እቃ ላይ ማተኮር፣ ቴክኖሎጅን ከእድሜያቸው በላይ መጠቀም መቻል. ......እና ሌሎችም

📌 ለህክምና 📌
0946417368 ይደውሉ

በመአዛ መንክር
ክሊኒካል ሳይኮሎጅስት
@Psychoet
@psychoet

#Share #share #share


https://youtu.be/a_InVAsOMoM
"ሜሎሪና" መጽሐፍን በተመለከተ እንዲኹም የወጣቶች የጊዜ አጠቃቀም ምን መምሰል አለበት በሚል ጥቂት ቆይታ በኢትዮ FM 107.8 ከ ሀበሻን Meme Radio ፕሮግራም ጋር አድርጌያለሁ ፡፡
ሙሉ ፕሮግራሙ ከጥቂት ደቂቃዎች በኀላ ዛሬ ሀሙስ ማታ በ FM 107.8 ከምሽቱ 3:00 - 4 :00 ይቀርባል ፡፡

እንድታዳምጡት እጋብዛለሁ ፡፡
👉🎈ድብርት/ድባቴ/Depression🎈👈

🧠ድብርት ማለት ቢይንስ ለ2 ሳምንት የቆዬ አስተሳሰብንና ባህሪን የሚያዛባ፤ የሰዎችን የእለት ተለት እንቅስቃሴንና ምርታማነትን የሚያውክ የአእምሮ ህመም አይነት ሲሆን መገለጫዎቹም:

🔥 ደስታ ማጣት🔥 ማዘንና መከፋት🔥 ተስፋ መቁረጥ፣🔥 ብቸኝነት🔥ብስጩነት🔥 ምንም ነገር ለማድረግ ፍላጎት ማጣት🔥 የህይወት ትርጉም ማጣትና ከዚህም የተነሳ ራስን ለማጥፋት ማሰብ/ ማቀድና መሞከር🔥 ከወትሮው የተለየ የምግብ ፍላጎት/ የእንቅልፍ ሁኔታና የክብደት መጨመር ወይም መቀነስ🔥 ትኩረት ለማድረግ መቸገር🔥 አልረባም ማለትና🔥 ከፍተኛ የጥፋተኝነት/የፀፀት ስሜት🔥 ዋናዎቹ የድብርት ምልክቶች ናቸው።📌📌

የተለያዩ የድብርት አይነቶች አሉ። ከላይ የተገለፁት ምልክቶቹ ግን 🧠Major Depression እና Chronic Depression (Dysthymia--ሁለት አመትና ከዛ በላይ የቆዬ ድብርት)🧠 ናቸው።

📌📌 የድብርት መንስኤ

👉 በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ለውጦች

🎈ወሊድ፣
🎈የቅርብ የቤተሰብ አባል/ ወዳጅ ሞት፣
🎈ፍች፣
🎈የገንዘብ ችግር፣
🎈በስራ ላይ ወይም በትምህርት ላይ
የሚያጋጥሙ ችግሮችና ማረጥ

👉 ከመድሃኒቶች ጋር የተያያዙ መንስኤዎች

🎈የደም ግፊት፣
🎈 የhepatitis C፣
🎈የአስምና የአርትራይተስ መድሃኒቶችም ድብርትን ሊያመጡ ይችላሉ።

👉 ከበሽታዎች ጋር የተያያዙ መንስኤዎች

🎈 ከስኳር በሽታ፣
🎈ከካንሰር፣ ከልብ በሽታና
🎈ከስትሮክ ጋርም ተያይዞ ሊከሰት ይችላል።

💥🗝 ህክምና🗝💥

👉 ስሜትን ለማስተካከል የሚረዱ መድሀኒቶች (Antidepressants) እና Cognitive Behavior Therapy ጥሩና ውጤታማ ህክምናዎች ናቸው

👉© በመአዛ መንክር - Psych ጤና
ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት
"ሜሎሪና" መጽሐፍን በተመለከተ እንዲኹም የወጣቶች የጊዜ አጠቃቀም ምን መምሰል አለበት በሚል ጥቂት ቆይታ በኢትዮ FM 107.8 ከ ሀበሻን Meme Radio ፕሮግራም ጋር ያደረኩት ቆይታ ፡፡ 👇👇👇

እንድታዳምጡት እጋብዛለሁ ፡፡
ማስታወስ /Memory /
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE

ብዙ ጊዜ ሁላችን በተለያዩ የሕይወት መስተጋብሮች "የመርሳት" ገጠመኝ አለን ፡፡ነገሮችን ማስታወስ አለመቻል በዙሪያችን ባሉ ሰዎች መካከል እንደግዴለሽ የመታየት ፣ በስራችን አመኔታ ማሳጣት ፣ በትምህርታችን ደግሞ ያጠናነውን ያለማስታወስ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ በእርግጥ ነገሮችን መርሳት ሲበዛ እንደ ህመም ይታያል ፡፡ ለዚህም ነው በተለምዶ "የመርሳት ህመም " የሚባለዉ ፡፡ ነገሮችን አለማስታወስ ብዙ ማህበራዊ ጉዳት ካስከተለ ታዲያ እንዳንረሳ ምን እናርግ የሚለው ትልቅ ሙያዊ መልስ ያሻዋል፡፡
______________________________

እንዴት የማስታወስ ችሎታዬን እጨምራለሁ
መርሳትን እቀንሳለሁ የሚሉትን መፍትሔዎችን፡_____________________________________
ማስታወስ / ትዝታ በብዙ መንገዶች መጨመር እንችላለን በዋነኛነት የሚመጡት ግን እነዚህ ናቸው ፡፡

Pay attention (ለነገሮች ትኩረት መስጠት ) : ከዚህ ክፍል 4 እና 5 እንዳስተማርኩት አንድ መረጃ ወደ አዕምሮአችን ገብቶ ለረጅም ጊዜ የሚቀመጠው በስነስርአቱ መረጃው ሲገባ ነው ስለዚህ ነገሮችን ለማስታወስ መጀመሪያውንም ወደ ውስጥ ስናስገባው በጥንቃቄና በአትኩሮት መሆን አለበት ፡፡ በብዛት የሚረሱ ሰዎች መጀመሪያውኑም ለፈተና ከላይ የሚያጠኑ ፣ የምንላቸውን ከላይ ከላይ / በግዴለሽነት የሚሰሙ ናቸው ፡፡

Add meaning ፦የምንሰማውን ፣ የምናየውን ነገሮች እንዳንረሳ ከዚህ ቀድም ከምናውቃቸው ጋር ማቆራኘትና ከመሸምደድ ይልቅ ትርጉሙን መረዳት ፡፡

Take your time ፦ በአንድ ጊዜ ነገሮችን ለመያዝ / ለማገባት ከመሞከር ጊዜ ወስደን እያረፍን ወደ አዕምሮአችን እናስገባ ፡፡

over learn፦ አንድን ነገር እንደምናውቀው ብናውቅም ደጋግሞ ማንበብ ፣ መስማት ፣ ማየት ለብዙ ጊዜ እንዳንረሳው ይረዳል ፡፡

Monitor your learning ፦ ያወቅነውን እንዳንረሳ ደጋግሞ በቃል ማለት በጥያቄ መፈተሽ ፡፡ በተለይሞ ተማሪ የሆናችሁ አንድን ነገር ስላነበባችሁ ብቻ በቂ አይደለም ይልቁንስ ያነበባችሁትን ወረቀት ዘግቶ ማሰብ እንዲሁም እውቀታችንን / ትውስታችንን በተለያዩ መንገዶች መመዘን ፡፡ አርቲስቶችን ብንመለከት (በቲያትር / ሙዚቃ ሙያ ያሉ ሰዎች) አንድን ገፀ ባህሪ አንብበው ያወቁ ቢመስላቸውም ከመድረክ በፊት ግን ብዙ ጊዜ ደጋግመው ይሉታል ይለማመዱታል ፡፡ ይህን የሚያረጉት የሚናገሩት ከራሳቸው ጋር እንዲዋሀድ እና እንዳይረሱት ነው፡፡

_______________________________
እንዲሁም መርሳትን ለመቀነስ ባለፈው ትምህርት እንደተመለከትነው በተጨማሪ *
★የግል ምክር ነገሮችን እየረሳችሁ ላላችሁ !

በጣም ብዙ ሰዎች ሳማክር አንዱ የሚነግሩኝ ችግራቸው የመርሳት ጉዳይ ነው ፡፡ ምንም እንኳን ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የመርሳት (የአለማስታወስ) ችግር ቢኖርም በወጣቶች/ታዳጊዎች ላይም በተለያዩ ምክንያቶች መርሳት ያጋጥማል፡፡

ስለዚህ በመርሳት ለተቸገራችሁ ምክሬ እነሆ ፡- ነገሮችን መርሳት መጀመራችሁን ስትረዱ / የቅርብ ሰው ሲነግራችሁ መጀመሪያ ተረጋግታችሁ ለራሳችሁ ግዜ በመውሰድ እነዚህን አርጉ

1. በወቅቱ በብዙ ስራ / ተግባር ተወጥራችሁ ከሆነ ሀሳባችሁን በመሰብሰብ የምትሰሩትን ስራ ለመቀነስ ሞክሩ ከቻላችሁም ዋና መስራት ካለባችሁ 1/2 ስራ በስተቀር ሌሎቹን ተዋቸው ምክንያቱም መርሳት አንዱ ምክንያት በብዙ ስራ / ሃሳብ መወጠር ነው፡፡

2. ለጊዜው ለውጥ እስክታሳዩ ድረስ መስራት/ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች በሙሉ አንድ በአንድ ወረቀት ላይ በመጻፍ ተከታተሉ ፡፡በሀገራችን "በቃል ያለ ይረሳል በፅሁፍ ያለ ይወረሳል" የሚባለውን እንደምሳሌ እንኳን ብንወስድ እንኳን ተማሪዎች የሆናችሁ ክፍል ውስጥ የምትማሩት አልቆ ስትወጡ የምታስታውሱት 50% ነው ከአንድ ቀን በኀላ ደግሞ ወደ 10% ይወርዳል ፡፡ይህም ማለት የምንማረውን ሳይቀር በአንድ ቀን 90% እንረሳለን ማለት ነው ስለዚህ ነገሮችን መጻፍ ለማስታወስ ዋነኛ መሳሪያ ነው ፡፡

3. በአንድ ጊዜ አንድ ብቻ ስራ ስሩ ይህም ማስተዋላችሁን (Concentration ) ስለሚጨምር የመርሳት ችግር ይቀንሳል ፡፡

4. (Quantity) በአንዴ ጥቂት ነገር ብቻ ይማሩ / ያጥኑ ፡ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ለተከታታይ 5 ሰአት ከሚያጠና ሰው ይልቅ በቂ እረፍት በየመሀሉ እየወሰደ 3 ሰአት የሚያጠና ሰው የበለጠ የማስታወስ / ያለመርሳት አቅሙ ይጨምራል ፡፡

5. ለብቻችሁ በየቀኑ በቂ እረፍት ውሰዱ ፦ ይህ እረፍት ወደ አዕምሮአችን የሚገባውን መረጃ ፍሰት ለጊዜው ስለሚቀንሰው አዕምሮአችን እንዳይጨናነቅ ይረዳል፡፡

ሌላውና ዋነኛው ነገር #በጣም እየረሳችሁ ከተቸገራችሁ ከአዕምሮ ጤና ጋር ሊገናኝ ስለሚችል ወደ ህክምና ጣቢያ እንድትሄዱ እመክራለሁ ምክንያቱም የዚህ አይነች ችግር የሚታከመው በመድኃኒትም ጭምር ነው ፡፡

፠፠______________________________፠፠
፠፠______________________________፠፠

ምንጭ ፦ ካለኝ ዕውቀት ማለትም ከዚህ በፊት ከሰማኀቸው ፣ ከተማርኩት እንዲሁም ካነበብኩት ለአንባቢ እንዲቀር አድርጌ በአማረኛ የጻፍኩት ነው ።

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

TELEGRAM 🚙 www.tg-me.com/Psychoet 👍
ሥነ ልቡና - Psychology

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የአእምሮ ጤንነትን የሚጠብቁና የሚያሳድጉ 5 ተግባራት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ)

የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡ ሰው እንደ ሰው ፣ ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በተለይም አሁን ባለንበት የኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ ደግሞ ይህ የአእምሮ ጤንነት በመንግስትም ሆነ በዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በዚህ ጊዜም ከወረርሽኙ የተነሳ በአለማችን ሆነ በአገራችን ብዙ ሰዎች ለአዕምሮ (ሥነልቦናዊ) ቀውስ እየተጋለጡ ይገኛሉ በዚህም ብዙዎች ቀናቸውን በድብርት ፣ በፍርሀት ፣ ተስፊ በመቁረጥ ፣ ስለ ነገ አሉታዊ ነገሮችን በማሰብ ያሳልፉሉ ብሎም ብዙ ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል ፣ ከስራተቸው ለቀዋል ፣ ማህበራዊ ህይወታቸውን አቁመዋል ... ብዙ ብዙ ፡፡ ይህ ሁሉ ወረርሽኙ ያስከተለው የሥነልቦና ቀውስ ነው፡፡

ይህ ወረርሽኝ ከሚያመጣው የሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡

1. አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር

አካላዊ ጤንነትና ንቃት ማለት ሁለንተናችን የተመጣጠነ እድገት ሲኖረውና ሰውነታችንን ከተለያዩ በሽታዎች ሲጠበቅ ማለት ነው፡፡ አካላዊ ጤንነት ሁልጊዜ ከአዕምሮ ጤንነት ጋር ይያያዛል ፡፡ በዚህ ንቃት ውስጥ የሚዳብር በራስ መተማመን ፣ ማቀድና መፈፀም እንዲሁም ችግሮችን በስልት መፍታት በሰውነታችን ውስጥ የኬሚካሎች ለውጥ እንዲኖር ያደርጋል ይህም ለኬሚካል ለውጥ በባህሪያችንና በስሜታችን ላይ አወንታዊ ለውጥን ያመጣል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

ባለንበት ቦታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የተለያዩ የሚያስደስቱንን ስራዎች በቤታችን ሁነን መስራት ፣ ጥሩ መጸሐፍትን ማንበብ ፊልሞችን መመልከት ፣በትንሹ እቅድ ማቀድና መተግበርን መለማመድ፡፡

2. አዳዲስ ክህሎቶችን መማር

ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዳዲስ ክህሎቶችን መማር ለአዕምሮ ጤንነትና እድገት ወሳኝ እንደሆነ ነው ፡፡ አዳዲስ ክህሎቶችን መማር በራስ መተማመናችንን ያሳድጋል ፣ የሕይወትን አላማ የቀለጠ እንድንረዳ ያግዛል በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች ጋር የትውውቅና የስራ እድል ይፈጥራል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች
አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር ዩኒቨርስቲ / ኮሌጅ መግባት ፣ ብዙ ገንዘብ ማፍሰስ አይጠይቅም ባሉበት ሆኖ በቅርብ በሚቀኙ ቁሳቁሶች በመጠቀም መማር ይቻላል ፡፡

በዚህ ጊዜ እቤቱ ያለ ሰው የተለያዩ ምግብ አሰራሮችን በየቀኑ መማር ፣ ዩቲዩብ ላይ የተለያዩ ቲቶሪያሎች በማውረድ በነፃ ክህሎቶችን መግኘት ፤ በነፃ ትምህርት የሚሰጡ Online ትምህርቶችን መከታተል በተጨማሪም አዳዲስ ልማዶችን መሞከር ለምሳሌ መጻፍ ፣ መሳል ፣ጥልፍ መስራት አዳዲስ የእስፖርት አይነቶችን መለማመድና እቤት ውስጥ የተበላሸ ነገሮችን መጠገንና ማስተካከል ይቻላል፡፡

በመስሪያ ቤት ያለ ሰው አዳዲስ ሀላፊነቶች
ስራችን ላይ ጨምሮ ቢወጣ ( እዚህ ላይ ግን አብዛኞቻችን ስለምንሰንፍ አሁን ያለኝን ሃላፊነት ራሱ በስነስርአቱ አልተወጣንም ብለን እናስባለን ) ግን አዲስ ሀላፊነት መቀበል የበለጣ የሚከብድ ነገር አይደለም እንዲያውም ቋሚ ሃላፊነቱን የበለጠ እንድንወጣ ይረዳናል፡፡

3. ለሌሎች ማካፈል

ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ደስተኛ ነው ፡፡ ሁሉም ሰው ወይ ለሀይማኖቱ አልያም ለሕሊናው ሲል መለገስ / ማካፈል ይወዳል ፡፡ ይህም የሆነው ሰዎች ከሰጠን / ለሌሎች ካካፈልን በኀላ በውስጣቸን የሚፈጠረው የኬሚካል ለውጥ ምክንያት በጣም ደስተኛ ስለምንሆን ነው ፡፡ መስጠት አወንታዊ አመለካከትን ይፈጥርልናል ፣ ከፈጣሪ ጥሩ መልስ እንድንጠብቅ ያደርጋል ፣ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ያሳድግልናል አላማችንን የበለጠ ለመፈፀም ያተጋናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ሰዎች ላደረጉልን ነገሮች ምስጋናን መለገስ
*በቅርብ ያሉ ሰዎችን ስለውሎአቸው መጠየቅ
*ጊዜያችንን ለሚፈልጉ ሰዎች መገኘት
*ካለን ገንዘብ ፣ ችሎታ ለሌሎች ለተቸገሩ ወገኖች መስጠት
*በመጨረሻም ዋናው መስጠት የምንችለው በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ መሰማራት

4. ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ

ጥሩ ወዳጅነት / ዝምድና አይምሮን ከሚያድሱ ነገሮች ቀዳሚው ነው ፡፡ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር ለራሳችን ያለንን አመለካከት ከማሳደጉ በተጨማሪ አስደሳች ጊዜያቶችን እንድናሳልፍ ዕድል ይሰጠናል ፡፡ ከሰዎችም የድጋ ስሜት እንድንቀበልና እንድንሰጥ ይረዳናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ከቤተሰቦቻችን ጋር ጊዜ ሰተን የጫዎታ ፣ የመወያያ የመመገቢያ ጊዜ ማሳለፍ ፡፡
*ድጋፍ የሚፈልጉ ጓረቤት ዘመዶችን ጊዜ ሰተን መጠየቅ ፣ ሰዎችን በሆስፒታልና በእስር ቤት መጎብኘት፡፡
*ካገኘናቸው ጊዜያት ያስቆጠሩ ወዳጆቻችንን ጋር መደወል።
*በዝንባሌያችን መሰረት በአካባቢያችንም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የተለያዩ ሕብረቶች ውስጥ መሳተፍ፡፡

5. ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት

ከምንም በላይ አሁን ላሉበት ነገር ትኩረት መስጠት የአዕምሮ ጤንነታችን እንዲጠበቅ ያደርጋል ፡፡ ብዙ ሰው አሁን ባገኘው ነገር እንደመደሰትና ፈጣሪን እንደማመስገን ትናንት ስለደረሰበት በደል እያሰበ ያዝናል ፣ ትናንት ስለሰራው ስህተት እየተፀፀተ ይኖራል ። ከዚህም ሲቀጥል ስላልኖረበት ነገ መኖሩን ሳያውቅ ከልክ በላይ "ምን እሆን ?"ብሎ እየተጨነቀ ዛሬውን ያበላሻል ፡፡

ሁልጊዜ አሁን ላይ ትኩረት መስጠት ሕይወትን የበለጠ እንድንረዳና እንድንወድ ያረገናል፡፡

#ማድረግ ያለብን ነገሮች

ትናንት በሕይወታችን የሆኑ መጥፎ ነገሮች መርሳት ባንችልም እነዛ ነገሮች ግን ዛሬ ላይ መተው ሕይወታችንን እንዲረብሹ አለመፍቀድ፡፡

በዚህ ርዕስ (5ኛው ላይ) መጸሐፌ ውስጥ ወሳኝ የሆነ ስለጊዜና አስተሳሰብ ያለንን አመለካከት የሚቀይር አጭር ሀሳብ አካትቻለሁ ፡፡ ሲወጣ ታገኙታላችሁ ፡፡

ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

ጽሑፉ ለናንተ ከጠቀማችሁ ሎችም እንዲጠቀሙበት #Share በማድረግ አካፍሉ!


በCovid-19 ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው የሕይወት ክህሎት ስልጠና በቅርቡ በጥቂት ሰዎች ስለሚጀመር ፍላጎቱ ያላችሁ ለስልጠናው ተዘጋጁ ፡፡ ከሚመጣው ሳምንት ጀምሮ ስለ ስልጠናው ሙሉ መረጃ እለጥፋለሁ ፡፡

www.tg-me.com/psychoet
💪በራስ መተማመንን ማጎልበት💪
Developing Self Confidence

በራስ መተማመን ማለት ሰው ባለው ችሎታ፣ አካላዊ ውበትና ሁለንተናዊ ማንነት አለመፍራት እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ራስን መቀበል ማለት ነው፡፡

ትእቢት ፣ ትምክህት፣ ያልተገባ አውቃለሁ ባይነት እና ከመጠን ያለፈ ድፍረት በራስ መተማመን አይደለም።

በራስ መተማመንን የሚያጎለብቱ ብልሀቶች

🔥 ራስዎን ከሌሎች ጋር አለማነፃፀር።

🔥 ያለዎትን ክህሎት እና ድክመት መለየት።

🔥 የአካላዊ ገፅታ ውበትን መጠበቅ ደግሞም የሰውን ትኩረት ከልክ ባለፈ ሁኔታ የሚስቡ ጌጣጌጦችንና ሜካፖችን አለመጠቀም።

🔥 ጥሩ እና ምቹ አለባበስ መልበስ።

🔥 ነቃና ቀልጠፍ ብሎ መራመድ ።

🔥 በሰው ፊት ሀሳብዎን መግለፅ ሲኖርብዎ ቀድመው በቂ ዝግጅት ማድረግ።

🔥 መልካም በሆነ የህይወት እንቅስቃሴ የበኩልዎን አስተዋፅዖ ማድርግ።

🔥 ጥሩ የሚሰሩ ሰዎችን ማድነቅ/ ማበረታታት።

🔥 ሰዎች የተቃወሙዎት ወይም የናቁዎት ሲመስልዎ በእርጋታ ምላሽ መስጠት።

🔥 ሰዎች ስህተትዎን ሲነግሩዎ በቀና ማየት(ስለሚጠሉኝ ነው አለማለት)።

🔥 እርዳታ ሲያስፈልግዎ ያለፍርሀት መጠይቅ።

🔥 ሰአት ማክበር።

©በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት
YouTube: Dink Mikir

#Like #Share
@Psychoet
🔥በራስህ እምነት ይኑርህ!

የበታችነት ስሜትን ለማሸነፍ መጀመር ያለብን የራሳችንን እምነት በመገንባት ነው።
በራስህ የማይናጋ እምነት ሊኖርህ ይገባል ምክንያቱም አንተ በራስህ እምነት ከሌለህ ማንም በአንተ እምነት ሊኖረው አይችልም።

🔥 Believe in yourself !

The first step in raising your self-esteem is to believe in yourself. You have to create this unshakeable belief in yourself because one thing is clear: If you don’t believe in yourself, nobody elses.

💥 አፈፃፀምህን ከማንነትህ ለይ!

ያንተ ማንነት በምታገኘው ውጤት አይለካም። አንተ ሰው ብቻ ነህ። ማንነትህ በምንም አይጨምርም አይቀንስምም።

💥 Separate your value from your performance!

Who you are as a person is not determined by what you accomplish as a performer.

©InsideOut- ኢንሳይድአውት

•════••• •••════
👉TG: www.tg-me.com/InsideOutEth
👉FB:https://m.facebook.com/InsideOutEt
👉YT:https://bit.ly/36h1mOA
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈
አጠቃላይ _ የአእምሮ_ህመም_ምልክቶች
Symptoms of Mental_Illness

📌📌🧠 በእለት ተለት እንቅስቃሴያችን በሚያጋጥሙን ምክንያቶች ልንናደድ ወይም ልንጨነቅ እንችላለን። ነገር ግን ምንም ምክንያት ሳይኖረን የምንጨነቅ፣ የምንረበሽ እና ከልክ ያለፈ ፍርሃት የሚሰማን ከሆነ

📌📌🧠 ምክኒያቱ ያልተረዳነው ጭንቀት እና መረበሽ በስራችን፣ በትምህርታችን፣ በውጤታማነታችን እና በማህበራዊ ግንኙነታችን ላይ ተፅእኖ ካመጣ

📌📌🧠 የመረበሽ እና የመጨነቅ ስሜቱ ለረጅም ጊዜ ከቆየ

📌📌🧠 በዙሪያችን ያሉ የቅርብ ቤተሰቦች፣ ጓደኛ እና የትዳር አጋር የምናሳየውን አዲስ ስሜት አይተው-ሁኔታህ ጥሩ አይመስልም ምንሆነሃል/ሻል ብለው እስኪጠይቁ የሚያደርስ ሁኔታ ላይ ከደረስን

📌📌🧠 የሚሰማዎት ጭንቀት ከልክ በላይ ሆኖ እርሱን ለመርሳት የአልኮል መጠጥ እና የእንቅልፍ መድሃኒቶችን መፈለግ ከጀመሩ

📌📌🧠 ከሚሰማዎት ጭንቀት ብዛት "አሁንስ ብሞት ይሻላል" የሚል ሀሳብ ከጀማመሮት እና

📌📌🧠 ያልተለመደ ሃሳብ ማለትም ሰዎችን መጠራጠር እና ያልተለመዱ ድምፆችን መስማት ከጀመሩ ---በግዜ የአእምሮ ሀኪም ጋር በመሄድ የንግግር ወይም የመድሃኒት ህክምና ያግኙ።

#MentalIllnessAwareness

👉👉የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ለማስፋፋት ይህንን ፅሁፍ Share ያድርጉ።📌📌

👉 በመአዛ መንክር
ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት Watch "Dink MiKir ድንቅ ምክር" on YouTube
@psychoet
2024/09/29 15:27:36
Back to Top
HTML Embed Code: