Telegram Web Link
#እጅግ_በጣም_ስኬታማ_የሆኑ_ሰዎች_7_ልምዶች
በጣም አስተማሪ መልዕክት ነው #SHARE
Telegram www.tg-me.com/psychoet

ከአስራ አምስት ሚሊዮን ቅጂ በላይ ተሽጧል፤ በሰላሳ ቋንቋዎች ተተርጉሞም ለንባብ በቅቷል፤ በእኛው አማሪኛ ቋንቋም ተተርጉሞ መታተሙንም አውቃለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ “The 7 Habits of Highly Effective people” ይባላል:: “እጅግ በጣም ስኬታማ የሆኑ ሰዎች 7 ልምዶች” ብለን ቃል በቃል እንተርጉመው፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ ይባላል፡፡ ይህ መጽሐፍ በግለሰብ ደረጃ ብልፅግናን (Personal development) ለመፍጠር እንዲረዱ ታስበው እስከ ዛሬ ድረስ ከተጻፉ መጽሐፍት መካከል ወደር የማይገኝለት ነው፡፡ ካላነበባችሁት እንድታነቡት እመክራለሁ፡፡ ያነበብነውም ደግመን ልናነበው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

የዚህ ድንቅ መጽሐፍ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ “ውስጣዊ ድል ከውጫዊ ድል ይበልጣል” ይላል፡፡ እዚህ ምድር ላይ ማግኘት የምንፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ ለማግኘት አስቀድመን ራሳችንን ማሸነፍ፤ የህይወታችን ሾፌር መሆን፤ ውስጣዊ ማንነታችንን መቆጣጠር ወዘተ አለብን ማለት ነው፡፡ “ከተማን ከሚመራ ሰው ይልቅ ራሱን የሚመራ ሰው ይበልጣል” ይላል ጠቢቡ ሰለሞን፡፡ ራስን ማሸነፍ ሌሎች ውጫዊ ነገሮችን የማሸነፊያ ቁልፍ ነው፡፡ በመቀጠል በቅደም ተከተል የምንመለከታቸው 7 ልምዶች ማንኛውም ሰው የግል ህይወቱ መሪ እንዲሆን በእጅጉ የሚያግዙ ናቸው፡፡ አሁን ቦታውን ለእነዚህ ልምዶች ለቀቅ እናድርግ እስኪ፡፡

1. ኃላፊነት ውሰዱ

ጅብ ከሄደ በኋላ የውሻ መጮህ ምንም ውጤት አያመጣም፤ ትርፉ ድካም ነው፡፡ ውጤት የሚያመጣው ጅቡ ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ በማነፍነፍ ድምጽ ማሰማት ነው፡፡ ሁኔታዎችን፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ዓለምን ወዘተ የሚወቅሱ ሰዎች በህይወታቸው የረባ ቁም ነገር አያከናውኑም፤ ሁልጊዜም ኃላፊነትን የሚያሸክሙት ከእነሱ ውጪ ላለ ሌላ አካል ነው፡፡ ኃላፊነትን መሸከም ስንችል ነው የህይወታችንን ጉዞ አቅጣጫ መወሰን የምንችለው፡፡ የተሸከርካሪውን መሪ ለሌላ አካል አሳልፈን ሰጥተን የምፈልገው ቦታ አይደለም የደረስኩት፤ በፈለኩት ፍጥነት አይደለም እየተጓዝኩ ያለሁት ወዘተ ልንል አንችልም፤ ብንልም ዋጋ የለውም፡፡ የጉዞውን አቅጣጫ፣ ፍጥነት እና አድራሻ የሚወስነው አሽከርካሪው ነው፡፡ ልምዳችን መውቀስ፣ ጣት መጠቆም፣ ራስን መከላከል ወዘተ ከሆነ እውነቱን ለመናገር የሚወቀስ ነገር ማግኘት አይከብድም፡፡ ዘወትር የእናቴ መቀነት አደናቅፎኝ ነው ማለት ህይወታችን ባለህበት እርገጥ እንዲሆን በር ወለል አድርጎ ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ለውጥ ለማምጣት፣ የራሳችን ሰዎች ለመሆን፣ ውስጣችንን ድል ለማድረግ ወዘተ ሁልጊዜም ለገዛ ራሳችን ህይወት ሙሉ ኃላፊነት እንውሰድ፡፡ ቃላችንን የምናከብር፤ በአልንበት ቦታ የምንገኝ፤ በገዛ ራሳችን ጥረት የምንፈልገውን ማንኛውንም ዓይነት ነገር እጃችን ለማስገባት መጓዝ ያለብንን ያህል ርቀት መጓዝ የምንችል ሰዎች እንሁን፡፡ “ስራ እኮ ጠፋ! እኔ ምን ላድርግ?!” ከማለታችን በፊት ስራ ለማግኘት የምንችለውን ድንጋይ በሙሉ መፈንቀላችንን እርግጠኛ እንሁን፤ ቀጣሪዎች የሚፈልጉትን ዕውቀት እና ክህሎት ይዘን ለመገኘት ጥረት እናድርግ፤ የተለመደውንም ያልተለመደውንም አማራጭ እንፈትሽ፡፡ ሳይኮሎጂስቶች “Life is 10 % what happens to us and 90 % how we react to it” ይላሉ፡፡ የህይወታችንን አብዛኛውን (90 %) ክፍል በምንፈልገው መልኩ መስራት እንችላለን ማለት ነው፡፡ የምናጭደው የዘራነውን ነው፡፡

2. የምትፈልጉትን ነገር አስቀድማችሁ እወቁ

ስቴቨን ኮቬይ “ነገሮች ሁለት ጊዜ ይፈጠራሉ” ይላል፡፡ የመጀመሪያው ፈጠራ የሚጠናቀቀው አእምሮአችን ውስጥ ነው፡፡ ከቤት ከመውጣታችን በፊት የምንሄድበትን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ከአንድ እና ሁለት፣ አምስት እና አስር ዓመት ወዘተ በኋላ ምንድን ነው ማግኘት፣ ማድረግ፣ መሆን ወዘተ የምንፈልገው? ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ መስጠት ነገሮቹ በተጨባጭም ወደ ህይወታችን የሚመጡበትን ዕድል ከፍ ያደርጋል፡፡ “We rise to the level of our expectations” ይባላል፡፡ የምናገኘው የምናስበውን ነው፤ የምንደርሰው እንደርሳለን ብለን የምናስበው ከፍታ ድረስ ነው፡፡ ግባችንን ማወቃችን ትኩረታችንን ለመሰብሰብ ይረዳናል፤ ከነፈሰው ጋር አንነፍስም፤ በፈተና መካከል ጸንተን እንቆማለን፡፡ ሳይኮሎጂስቶች የህይወታችንን ግብ በቅጡ ለመለየት የሚረዳን አንዱ ሁነኛ መንገድ “የቀብራችን ዕለት እንዲነበብ የምንፈልገውን የህይወት ታሪካችንን መወሰን ነው” ይላሉ፡፡ ቁጭ ብለን ልናስብበት ይገባል፡፡

3. ቅድሚያ ለሚገባቸው ነገሮች ቅድሚያ ስጡ

“ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት” ይባላል፡፡ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገሮች ቅድሚያ መስጠት አለብን፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም፡፡ ኮቬይ እንዲህ ይላል፡- “ራሳችሁን ከእነዚህ ሶስት አጉል ልምዶች በአንዱ መውቀስ ቢኖርባችሁ በየትኛው ነው የምትወቅሱት? (1) መስራት ያለብኝን ነገር በቅደም ተከተል መለየት አልችልም፤ (2) በአስቀመጥኩት ቅደም ተከተል መሰረት መስራት አልችልም፤ (3) በወሰንኩት ቅደም ተከተል መሰረት ለመስራት አስፈላጊው ቁርጠኝነት የለኝም፡፡ ብዙ ሰዎች ቁርጠኝነቱ የለኝም ነው የሚሉት፡፡ ጠለቅ ብለን ከመረመርነው ግን እውነቱ ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እውነቱ ቅደም ተከተሉ ውስጣችን በጥልቀት አለመስረጹ ነው፡፡ ልምድ 2ን ማለትም የህይወት ግባችንን አስቀድመን በሚገባ ለይተን በሚገባ ውስጣችንን መቅረጽ አለመቻላችን ነው”::

4. በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ ተመሩ

ከተቃራኒ ፆታ ጀምሮ እስከ የንግድ ስራ ግንኙነት ድረስ በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ መመራት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ “አዎ! በሚገባ አምንበታለሁ፡፡ በእኩል ተጠቃሚነት መርህ ነው ህይወቴን የምመራው፡፡” ትሉ ይሆናል፡፡ እንደምትሉት እንደምትኖሩ ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ለማሸነፍ ከመጣር ይልቅ እንዴት በጋራ እኩል ተጠቃሚ ለመሆን ጥረት አድርጉ፡፡ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ከሌላው ከፍ ብሎ ለመታየት፣ ልክ ሆኖ ለመገኘት ወዘተ ከመጨነቅ ይልቅ በጋራ እኩል እንዴት ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ማሰብ እና ይህንን መርህ በየትኛውም የግንኙነታችን መረብ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ይበልጥ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

5. መጀመሪያ ለመረዳት ጥረት አድርጉ

መጀመሪያ ስንረዳ የሚረዱንን እናገኛለን፡፡ ብዙ ጊዜ ግን በአንጻሩ ጊዜያችንን የምናጠፋው ሰዎች እንዲረዱን በመፍጨርጨር ነው፡፡ ቆም ብለን  “ምንድነው እስኪ እያሉ ያሉት? ልክ ይሆኑ ይሆን? በየትኛው ማዕዘን ነው እነሱ ጉዳዩን ያዩት?” ወዘተ ብሎ በቀናነት ማሰብ እና ሰዎችን ለመረዳት ጥረት ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ሰዎችን የመረዳት ችሎታችን ጥሩ ሲሆን የሚረዱንን ሰዎች ቁጥርም ይጨምራል፡፡

6. 1 + 1 = 3

“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ትልቅ መልዕክት ያለው አባባል ነው፡፡ በጋራ የሚሰሩ ስራዎች በግል ከሚሰሩ ስራዎች ይልቅ የላቀ ውጤት ያመጣሉ፡፡ አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብም፡፡ ሩጫን በመሰለ የግል ጥረትን በከፍተኛ ሁኔታ በሚጠይቅ የውድድር ዘርፍ እንኳን አትሌቶቻችን ሲተባበሩ የሚያስመዘግቡትን አንጸባራቂ ድል እናውቀዋለን፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ በጋራ የመስራትን መንፈስ ማዳበር ጠንካራ ያደርጋል፤ የበዛ ፍሬም ያፈራል፡፡ አብረን መብላት ብቻ ሳይሆን አብረን መስራትንም ባህላችን እናድርግ፡፡ ስቴቨን ኮቬይ እንደሚለው “አንድ
ሲደመር አንድ ከሁለት በላይ ነው”፡፡

7. መጋዛችሁን ሳሉ

ስቴቨን ኮቬይ መጽሐፉ ውስጥ ግሩም አፈ ታሪክ አለ፡፡ አንድ ተጓዥ መንገደኛ በአንድ ጫካ ውስጥ አቋርጦ ሲያልፍ አንድ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ላቡ ጠፍ እስከሚል ድረስ ያለምንም እረፍት እንጨት ሲቆርጥ ይመለከታል፡፡ ተጓዡ መንገደኛ ቆም ይልና የመጋዙን መደነዝ አስተውሎ ኑሮ “ወዳጄ! ለምን መጋዝህን ዕረፍት ወስድህ አትስለውም?” ይለዋል፡፡ ልፋ ያለው እንጨት ቆራጭ “አይ ለሱ እንኳን ጊዜ የለኝም” የሚል የዋህ ምላሽ ይሰጠዋል፡፡ ይኼ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ዕረፍት ወስዶ መጋዙን ቢስል በተሻለ ቅልጥፍና ብዙ እንጨት መቁረጥ እንደሚችል አልተረዳም፡፡

የተራ ቁጥር ሰባት ልምድ መልዕክት ቀላል እና ግልጽ ነው፡፡ በቂ ዕረፍት ምንጊዜም አድርጉ ነው፡፡ ከስራ በኋላ ራሳችሁን ዘና የማድረግ ልምምዱ ይኑራችሁ፡፡ መዝናናት ለጊዜው ከሚሰጠው ደስታ ባሻገር ለቀጣይ ስራ ያዘጋጃል፡፡ ሁልጊዜም እንደምለው ትልልቅ ኩባንያዎች ወጪ ችለው፣ ወርሃዊ ደሞዝ መክፈላቸውን ሳያቋርጡ ሰራተኞቻቸውን የሚያዝናኑት በጣም ቸር ስለሆኑ አይደለም፡፡ ይልቁንም የተዝናና ሰራተኛ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚሆን እና እነሱንም ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡

አንድ አንድ ሰዎች “እኔ መዝናናት አይሆንልኝም” ይላሉ፡፡ “መዝናናት ራሱን የቻለ ችሎታ ነው” ይላል አንድ ሌላ ወዳጄም፡፡ በመሆኑም “እንዴት እንዝናና?” የሚል ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች እነዚህን የመዝናኛ አማራጮች እንድትፈትlቸው እጋብዛለሁ፡- ዋና ዋኙ፤ ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር አስደሳች ጊዜ አሳልፉ፤ ዮጋ ስሩ፤ ዳንስ ደንሱ፤ ከከተማ ከተቻለም ከሀገርም ወጣ ብላችሁ ጎብኙ፤ ደስታ ይሰጠኛል ብላችሁ የምታስቡትን የትርፍ ጊዜ የመዝናኛ አማራጭን (Hobby) ሞክሩ፡፡

ቸር እንሰንብት!

(በነጋሽ አበበ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

📕በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡

📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡

📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖
ከሜሎሪና መጽሐፍ የተወሰዱ ሃሳቦች
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖

@psychoet
መልካም ቀን
ናሁሰናይ ፀዳሉ
#ክፍል_22
#አራቱ የሰው ባህሪ አይነቶች
www.tg-me.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

እንደምን ሰነበታችሁ የፔጃችን ቤተሰቦች !
ተቋርጦ የነበረው ሳምንታዊ የሳይኮሎጂ ትምህርታችን ዛሬ ጀምሯል፡፡

በዛሬው ርዕስ ለሰው ልጆች ተግባቦትና የቀን ተቀን መስተጋብር ወሳኝ ስለሆነው አመል ( Temperament) እንመለከታለን፡፡ እንደሚታወቀው ማንኛውም ባህሪ መነሻ ምክኒያት አለው ፡፡ ምክንያቶቹ ደግሞ #ተፈጥሮአዊ ወይም #አካባቢያዊ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡

1. ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ :- ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ ስንል በዘር ከወላጆቻችን የምንወርሰው ሲሆን

ለምሳሌ ፦ አንድ ልጅ እናቱ ወይም አባቱ ያላቸውን ባህሪ ሲወርስ

2. አካባቢያዊ :- ከቤተሰብ ጋር ባለ ግንኙነት ፣ በጓደኛ ተፅዕኖ ፣ በትምህርት ቤት ቆይታና በምንኖርበት ባህል የምንወርሳቸውን ባህሪያቶች ያጠቃልላል

ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው በጣም ተሳዳቢ ቢሆን ( ያን ስድብ የወረሰው በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አልያም ከሰዎች በተለያዩ መንገድ ከተመለከታውና ከሰማው ሊሆን ይችላል )


የስነልቦና ተመራማሪዎች የሰውን ተፈጥሮአዊ አመል (Temperament ባህሪ) በአራት በመክፈል ያስቀምጡታል

1 .📌ሳንጊዊን (Sanguine)
ሳቂታና ተጫዎች ...
#ተግባቢና ምክኒያታዊ ናቸው

2.📌ኮለሪክ (Choleric)
ተነጫናጭ/ አዛኝና አኩሪፊ ...
#ተግባቢና ስሜታዊ ናቸው

3 .📌ሜላንኮሊክ (Melancholic)
አይናፋር ...
#ጭምቶችና ስሜታዊ ናቸው

4. 📌ፊላግማቲክ (Phlegmatic)
ግትር...
#ጭምተኛና ምክኒያታዊ ናቸው

እነዚህ አራት የሰው አመሎች የየራሳቸው መገቸጫ አላቸው

📌ሳንጊዊን
❇️አየር ⭕️ማሕበራዊ ሰዎች

ሳንጊዊን አመል ያላቸው ዋናው መገለጫቸው አብዝቶ ተጫዎችና ወሬኛነት ፣ ነገሮችን ለመስራት ፈጣንነት ፣ ማሕበራዊነት ይገኙበታል ፡፡ ሳንጊዊኖች በጣም ተግባቢና የሕብረት ነገር የሚወዱ ናቸው፡፡ ይህ አመል ያላቸው ሰዎች ሁልጊዜም ለራሳቸው ሳይሆኑና ምንም ሳይሰሩ ኑሮአቸውን የግል ሳይሆኖ የጋራ ያረጋሉ፡፡

📌ኮለሪክ
❇️ እሳት ⭕️አስተዳዳሪዎች
ኮለሪኮች በጣም ተግባቢ ሲሆኑ የሚገለፁበት ባህሪ በውሳኔ ሰጭነታቸው ፣ በግብ ተኮርነታቸው ፣ በምኞታቸው ፣ በኢጥገኛነታቸው ነው፡፡ በተጨማሪም ኮለሪኮች ቁጡዎች ቂም የሚይዙ ለስሜት ቅርቦች ናቸው፡፡

📌ሜላንኮሊክ
❇️መሬት ⭕️ሰዎችን ከሕይወታቸው አግላይ

ሜላንኮሊክ ሰዎች አስተዋያዮችና ዝርዝር ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጪዎች ደግሞም ጥልቅ አሳቢዎችና ጭምቶች ናቸው ፡፡ ከዛ በተጨማሪ ራሳቸውን ብዙ ሰዉ ካለበት ቦታ ማግለል / ማሸሽ የሚመርጡ ናቸው ፡፡ እነዚህ አይነት ሰዎች ሁሌም ፍፁም ለመሆን የሚሞክሩና የሚፈልጉ ናቸው፡፡ይህ ባህሪ ሰዎችን ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ የሚገፋፋ ፣ ቁጥብ እንዲሆኑ የሚያረግ ነው ፡፡

📌ፊላግማቲክ
❇️ውሀ ⭕️ሰዎችን ከወደሕይወታቸው አቅራቢ

ፊላግማቲክ ሰዎች ረጋ፣ ፈታ ያሉና ከሁሉ ጋር እንደውሀ የሚራመዱ ናቸው ፡፡ ለሌሎች በጣም የሚያዝኑ ግን የራሳቸውን ስሜት በማፈን የማይገልፁ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሰዎች  የተለያዩ ሀሳቦችን እና ችግሮችን ወደአንድ በማምጣት ለመፍታት የሚሞክሩ ናቸው ፡፡


አንዳንድ ሰዎች ከነዚህ ባህሪያት ሁለቱን ወይንም ከዛ በላይ ሊያሳዩ ይችላሉ ፡፡ በቅርብም የተጠኑ ጥናቶች ከ4ቱ አመሎች ላይ አንድ ጨምረው 5 አድርሰውታል ፡፡ አምስተኛው ደግሞ የሁሉም ቅልቅል ያለበት ከሁሉም መሀል የሆነ ሲሆን (SUPINE )ብለው ጠርተውታል፡፡

የናንተ ባህሪ ከየትኛው ይመደባል ? በ #Comment አሳውቁኝ ?

በዩቲዩብ የምንለቃቸውን ትምህርቶች ለማግኘት ቻናላችንን Subscribe አድርጉ
youtube.com/thenahusenaipsychology
❖_____________________________❖
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

የሳምንት ሰው ይበለን!
❖__________________________________❖

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡
ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

_ሜሎሪና ገጽ 184 _

ሜሎሪና ❤️❤️❤️
ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ
ያነበቡት ኹሉ ወደውታል

ለቅዳሜና እሑድ መጽሐፍ ሸመታችሁ ወደ ጃዕፈር @jafbok መደብር ጎራ ብላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ ያላችሁ በየክፍለ ሀገሩ ስለተሰራጨ ከሚቀርባችሁ መደብሮች ማግኘት ይቻላል፡፡
ይኽን ፎቶ ከተነሳሁት ሰንበትበት ብሏል ይኹን እንጂ ትራንኘ የተናገረውን የሞኝነት ቃል ሰማሁና ለመለጠፍ ወሰንኩ ፤ ይንንም ለመጻፍ ተነሳሁ ፡፡

በእኔ እድሜ ኢትዮጵያ ቀሪውን ዓለምን ትረዳለች ፡፡ ይሄ ቅዠት ፣ ምኞት ፣ አልያም አጉል ተስፋ ሳይኾን ታሪክን በአግባቡ ለሚያጠናና ለሚከታተል ወለል ብሎ የሚታይ ሃቅ ነው ሌላው ደግሞ ከልጅነቴ ጀምሮ ምን አይነት system እየሰራሁ እንደሆነ አውቃለሁ 😉። ስለዚህ ኢትዮጵያ ቀሪውን ዓለምን ትረዳለች የምለው በምክንያት ነው ፡፡

በውጭ ትራንፕና ትራንፕን የመሠሉ ሰዎች ስለ ኢትዮጵያ ያፍራሉ ፡፡ በሃገር ውስጥ ያሉ ( የፖለቲካ ፣ የሃይማኖት ... ) ባንዶዎችም ተስፋቸው አልቦ ይሆናል ፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ስልጣንን አግኝተው በምንአለብኝና በማንአለብኝነት ሌሎችን ሰዎች በሀገራቸው ኹለተኛ ዜጋ እንደሆኑ እንዲሰማቸው የሚያረጉ ፣ ፍትህንና ፍርድን በሕዝብ ላይ ለሚያዛቡ ፣ በታሰረ አእምሮዋቸው ነፃ ሰዎችን ለሚያስሩ፣ እነሱ ከሌሉ ሃገር የሚቀጥል ለማይመስላቸው ፣ ከ "ሰውነት" የወረደ ስራ የሰሩና እየሰሩ ያሉ እነርሱም እውነትንና ፍትህን የሚያዩበት ጊዜ ቀርቧል ፡፡ እንደ ሃገር አምስትና አሥር አመታት ነገ ማለት ናቸው፡፡

#Historywillneverforget
ከአድማስ ማዶ ኹና የማያት የተስፋይቷ ምድር
@psychoet
የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡ ለካስ እስር ቤት ቦታ ሳይኾን አስተሳሰብ ነው፡፡ በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል፡፡

ሜሎሪና ❤️ ሜሎሪና ❤️ ሜሎሪና
#share
@Psychoet
የደስታ ቀን !
ቀናችንን እኛ እንሰራዋለን ፡፡ እያንዳንዱ ቀን በራሱ ጥሩ ወይንም መጥፎ ሁኖ አይመጣም ይልቁንስ ኹለቱንም እድል ይዞ ወደእኛ ይመጣል ፡፡ ስለዚህ ደስታና ሀዘን ባብዛኛው የውሳኔያችን ውጤት ስለሆነ በየቀኑ ባለን ነገር ለመደሰት እንወስን ፡፡ ባለንበት ዕምነት ደግሞ ምስጋና ማድረግ ትልቁ የደስታ ምንጭ ነውና ፈጣሪን በየቀኑ እናመስግን ፡፡

መልካም ቀን ይሁንላችሁ
#Share #Like
@Psychoet
#ይህ_ሲያለቅስ_የምትመለከቱት_ሰዉ_ዶክተር_ነዉ ፡፡ በእርግጥም የሚያለቅሰዉ ተቸግሮ አሊያም የሚበላዉ አጥቶ አይደለም ፡፡ ነገር ግን ለበጎ ፈቃድ ሲሪያ ምግብ እያደለ ሳለ የምታዩት ህፃን ልጅ የተናገረዉ ቃል ነዉ፡፡ ልጁ ምግብ የሚሰጠዉ ሰዉ ዶክተር እንደሆነ ሲያዉቅ በኮልታፋ አንደበቱ "እባክህ ሁለተኛ እንዳይርበኝ መድሀኒት ስጠኝ ወይም መርፌ ዉጋኝ? " አለዉ ፡፡
ይህ ምን ያህል አሳዛኝ ታረክ እንደሆነ የሰዉ ልጅ የሆነ ሁላ መፍረድ ይችላል፡፡ እኔ ግን ዛሬ አንድ ነገር ልበላችሁ ፡፡
❀❀❀አሁን ያለችዉን ሀገር በሰላም መጠበቅ ካልቻልን ወደፊት የሀገራችን እጣ የልጆቻችን ጥያቄ ከዚህ አይለይም ፡፡ ሰዉ የኔ ዘር ብቻ ፣ የኔ ሀይማኖት ብቻ ሲል ሀገር ትረበሻለች ፡፡ ነገር ግን በአንድ ሀሳብ ባንስማማ እንኳን ልዩነቶቻችንን ተቻችለን መኖር ይገባናል፡፡

☞እኔስ ዛሬ አዘንኩ ፣ አነባዉ ለሀገሬ
☞ምንም የማያዉቅ ሰዉ ሲገደል እንዳዉሬ ፤

#በ face book ማንኛዉም መጥፎ ሀሳብ የሚያሰራጩ ሰዋችን #block #unfriend #unfollow በማረግ ራሳችንን ከመጥፎና አሉታዊ ሀሳቦች እንከላከል፡፡ ለልጆቻችን #መልካምን_ሀገርን_እናዉርስ !
#ዘረኝነትን_እንቃወም !

የሚስማማ #Share ያድርግልኝ
@Psychoet
ጠቃሚ መረጃ ስለሆነ #share እናድርገው

@Psychoet
ወጣቱ ደራሲ ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ ዛሬ በማዕከላችን በመገኘት በቅርቡ ያሳተመውን “ሜሎሪና” የተሰኘ የበኩር መፅሀፉን ዕትሞች እና የ15 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጎልናል፡፡
ልብ የሚሹ ሕፃናትን ለመደገፍ ካለህ ላይ ስላበረከትክልን ከልብ እናመሰግንሀለን፡፡
#nahusenaytsedaluabera | #CHFE | #CCE
#6710_A_B_C_D
ይህን ለማድረግ በመታደሌ እጅግ ደስ ይለኛል ፡፡ ትልቁ የደስታ ሚስጥር ካለን ማካፈል ነው እንጂ ሲተርፈን ማካፈል አይደለም ፡፡ ኹላችንም ለነዚህ ህፃናት የቻልነውን እንድናካፍል እጠይቃለሁ ። መልካም ቀን!

@cardiaccenterethiopia
#መልካም_የሕዳር_ወር !
T.me/psychoet #Share

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

ቆሞ የነበረው የሥነልቦናና የሕይወት ክህሎት የማሕበራዊ ሚዲያ ትምህርታችን ከዛሬ ጀምሮ በዐዲስ መልክ ይቀጥላል ፡፡

Telegram : www.tg-me.com/psychoet
Facebook : fb.com/psychologyet

መልዕክቱን #Share #Like በማረግ ለሌሎችም እናጋራ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#አሁንም_አልረፈደም ! #Share
www.tg-me.com/psychoet

እኔ ማንም አይደለሁም ፤ እራሴንም ከሌላው ለማወዳደርና እሻላለሁ ብዬ ለመናገር ሞራሉም ብቃቱም የለኝም፡፡ ግን ግን ሰው ነኝና አንዳንድ ሁኔታዎች ይገርሙኛል፤ የሚገርመኝንና የምታዘባቸውን ነገሮች ለሌላው ባካፍል መመጻደቅ አይሆንብኝም፡፡ ህይወት ትምህርት ቤት ናት ፤ በህይወት ትምህርት ቤትነት ያወቅነውን ወይም የታዘብነውን ለሌሎች ማሳወቅና ማካፈል ሞራላዊ ግዴታም ጭምር ነው ብዬ አምናለው፡፡ ይህንን ጽሑፍ ከእዚህ መንፈስና አንድምታ ተረድታችሁልኝ እንድታነቡ አስቀድሜ ላሳስባችሁ እወዳለሁ፡፡

ተወልጄ ባደጉበት አካባቢ አንድ “አፒዮ” የሚባል ሰው ነበር፡፡ አፒዮ የቀን ሰራተኛ ሲሆን ፤ ለቤት መስሪያ የሚሆን እንጨት ከተቆረጠበት እስከሚፈለግበት ቦታ ድረስ በትከሻው ተሸክሞ ደከመኝ ሳይል የፈጀበትን ጊዜና ቀን ያህል ቢፈጅበትም እንጨቶቹን ተሸክሞ እያመላለሰ ከምር በተባለበት ስፍራ ይከምራል፡፡ ለድካሙ ዋጋ ብር አይቀበልም ጥቂት ዝርዝር ሳንቲምና ምግብ ብቻ በቂው ነው፡፡ አፒዮ እኔ እስከማውቀው ድረስ ዘመድ የለውም እንዲሁም በአካባቢው መኖሩን እንጂ ከየት እንደመጣ ማንም አያውቅም፡፡ ከሰው ጋር አይነጋገርም በአጠቃላይ ከማኅበራዊ ህይወት የተገለለ በእራሱ ዓለም የሚኖር ሰው ነው፡፡ ቤት የለው ፤ አንዲት ቃል ትንፍሽ አይል ብቻ ዝም ብሎ የጸጥታን ባህር የሚቀዝፍ ለሰውም ለራሱም ባይተዋር የሆነ ምስኪን ሰው፡፡ ቢርበው ራበኝ ብሎ ምጽዋት አይጠይቅም ፤ ውሃ ቢጠማው እሩቅ ተጉዞ ወንዝ ሄዶ ይጠጣል እንጂ ከማንም ጋር ግንኙነት መፍጠር አይፈልግም፡፡ የቀን ስራ ሰርቶ የሚያገኛትን ሳንቲም በድሪቶ ልብሱ ላይ ይቋጥራል፡፡ በላዩ ላይ ያለው ልብስ ድሪቶ ቢመስልም ብዙ ገንዘቦችን ቋጥሮ ይገኛል፡፡ “ግን አፒዮ ዘመድ ፤ ሚስትና ልጅ የለው ገንዘብ ምን ሊያደርግለት ያጠራቅማል?” ልጆች ሳለን ብዙዎቻችን የምንጠይቀው ጥያቄ ነበር፡፡ ታዲያ ምስኪን አፒዮ በዓመት ወይም በሁለት ዓመት አንዴ በከተማው ማዘጋጃ ቤት ጸጥታ አስከባሪዎች በግድ (አፒዮ እንደ ዝምተኛነቱ ሳይሆን አንድ ሰው አጠገቡ ደርሶ በመተናኮል ገንዘቡን ሊዘርፈው ቢነሳሳ ዘውትር ከአጁ በማትለው ቀመጥ እንካ ቅመስ ብሎ ያስገባለታል፡፡) ይያዝና ድሪቶ ልብሱ ከላዩ ላይ ይገፈፍል በእራፊ ጨርቆች የቋጠራቸው ሳንቲሞች ይፈታሉ ፤ ጸጉሩ ይቆረጣል ፤ አዲስ ጥብቆና ልብስ ይገዛለታል (ቀሪው ገንዘቡ ምን እንደሚደረግበት ፈጣሪ ይወቀው!)፡፡ እርሱ ግን በዚህ ምንም ደስተኛ አይሆንም እንዲሁም ለምን ንብረቴን ነካችሁብኝ ብሎ ያዝናል ፤ ይተክዛል ከፍ ሲልም ያለቅሳል፡፡ በአዲስ ገጽና ልብስ ለጥቂት ሳምንታት ከቆየ በኋላ ቀስ በቀስ አዲስ ገጽታውና ልብሶቹ እያደፉ ወደ ቀድሞ ማንነቱ ይመለሳል፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ህይወቱ በእንዲህ ቀጥላለች አሁን ይኑር አይኑር ባለውቅም፡፡

በአዲስ መስመር ሃሳባችንን ስናጠናክር በስራና በትምህርት ገበታ ብዙ አፒዮችን አውቃለው፡፡ እነኚን ከዋናው አፒዮ የሚለያቸው የተማሩ የሚባሉ ፤ በአንጻሩ የተሻለ ገቢ የሚያገኙ ናቸው፡፡ ነገር ግን በትክክል ከታየ ህይወታቸው ከአፒዮ የሚለይበት ምንም መስመር የለውም፡፡ በአፒዮ ላይ ምንም መፍረድ አንችልም ምክንያቱም ለሰው ቀርቦ የማያዋየው ወይም ሌሎቻችን ልንረዳው ያልቻልነው ብዙ ግላዊ ሚስጥሮችና እንቆቅልሾች ይኖሩታል፡፡ እነኚህን ግን ምን ልላቸው እንደምችል አላውቅም (ልፈርድባቸው ሳይሆን የህይወት ትርጉም ለእነሱ ምንድን ናት የሚለውን ለማንሳት ያህል ነው፡፡) ይሰራሉ ማንም የሚያገኘውን (አንዳንዴ እንዲሁም ከማናችንም በላይ ያገኛሉ) ደመወዝ ያገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ ከማኅበራዊና ዘመድ የተገለሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን ገንዘብ ማጠራቀም ትልቁ ስራቸው ነው፡፡ ለምን ገንዘብ ያጠራቅማሉ ለማለት አይደለም ገንዘብ ልንገለገልበት እንጂ ሊገለገልብን አይገባም፡፡ ልብሳቸውንና ገላቸውን አይታጠቡ አንዲት ልብስ እላያቸው ላይ እስኪወይብና እስኪያረጅ ማልያ አድርገው ይለብሳሉ፡፡ ትንሽ ገንዘብ አውጥተው ምግብ ለመብላት ለገንዘባቸው ይሳሱለታል፡፡

ብቻ እዚህ ልገልጸው የማልችላቸው ነገሮችን ሁሉ አይባቸዋለው፡፡ ባልፈርድባቸውም ያሳዝኑኛል ገንዘብ አስፈላጊ ነው ነገር ግን ገንዘብ ብቻ አያኖረንም፡፡ እንደው ይቅር ምንም አታውጡ ማኅበራዊ ህይወትን እንኳን እንጋራ ሲባሉ አሻፈረኝ የሚሉ፡፡ እራስን እየበደሉ ገንዘብ ማጠራቀም አሁንም ማጠራቀም፡፡ ይህ በእውነት ጤነኝነት አይደለም ለዚህ ነው ዓለም ዓቀፉ የጤና ድርጅት “አለመታመም ጤነኝነት አይደለም” ብሉ ጤናን በተለያየ አኳሃን የሚተረጉመው፡፡

የሚገርመው ነገር እነኚህ ሰዎች ገንዘባቸውን አጠራቅመው ኋላ ላይ ጤናቸውን በገንዘብ ለመሸመት ለዘመናት ያጠራቀሙትን ገንዘብ ለህክምና ያውሉታል፡፡ “የቆጣቢን ይበላል ቆርጣሚ!” እንደሚባለው አስቀድመን ያልተንከባከብነውን ጤና በኋላ ላይ ገንዘብ ብቻ አይታደገውም፡፡ ድህነት አስቀያሚ ነገር ነው ክብርንና ማንነትን ያዋርዳል ነገር ግን የሚበላ የሚጠጣ ሳይጠፋቸው ከድህነት ጠለል በታች የሚኖሩ ሰዎች በፍጹም የጤነኝነት አይደለም፡፡ ሰው ምግብ ካልበላ ውሃ ካልጠጣ እንዴት ነው የሚኖረው ፤ ለነገስ ብለን የምናጠራቅመው ገንዘብ ነገ እንደሚያኖረን እንደምን እርግጠኛ እንሆናለን!?

ከስነ-ልቦና አንጻር ከተመለከትነው ይህ እራሱን የቻለ ትልቅ ችግር ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች በገንዘብ እጦት ምክንያት ብዙ መሰረታዊ ጉዳዮቻቸው ሳይሟሉ ካደጉ በኋላ ዘመን ያንን የማጣትን ዘመን ለመበቀል ሲሉ እራሳቸውን እየቀጡ ገንዘብ ማጠራቀምን ትናንትን እንደማሸነፊያ መንገድ አድርገው ሊወስዱት ይቻላሉ፡፡

ያለነን ነገር ሁሉ ደፍፍተን ዛሬን ብቻ እንኑር ማለትም አደጋ አለው፡፡ ዛሬን በአግባቡና በመጠኑ በመኖር ነገን ማለም ብልህነት ነው፡፡ ሰው እንደ ፀሐይ ነው በጊዜ ጀምበር ይወጣል በጊዜ ጀንበር ይጠልቃል፡፡ ጀንበር ወጥታ ለመጥለቅ እንደ ወቅቶች ሁኔታ ቢለያይም ቢያንስ አስራ ሁለት ሰዓት ያህል ይፈጅባታል ሰው ግን የራሱን ህይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ጀንበሩ በእጁ ላይ ነች፡፡ የህይወት ጀንበር ከመጥለቋ በሚፊት እራስን መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት ማንም ሌላውን ይምሰል ወይም የሌላውን ኑሮ ይኑር ሳይሆን በአቅሙ ለመኖር ይብላ ይልበስ ሳይቸግረው እራሱን በእራሱ ቀጥቶ አያጥፍ ለማለት ነው፡፡ በገዛ እጅ እራስን አጎሳቅሎ የተጠራቀመን ገንዘብ ለህክምና ከማውጣት ጀምበር ከመጥለቋ በፊት መንቃት፡፡ ሻሎም!

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©Zepsychologist
2024/09/29 17:29:26
Back to Top
HTML Embed Code: