Telegram Web Link
ለውድ ቤተሰቦቻችን

#melorina_challenge በfacebook ተጀምሯል ፡፡ ከሜሎሪና መጽሐፍ የወደዳችሁትን አባባልና በሃሽ ታግ #melorina_challenge የመጽሐፉን ፎቶ በመለጠፍ ተሸላሚ ይኹኑ ፡፡

ቻሌንጁን አኹኑኑ ይቀላቀሉ ፡፡ ዛሬ ከተለጠፉት ፎቶዎች መካከል እየመሩ ያሉትን ከስር አያይዣለሁ ፡፡ መልካም ቀን

#melorina_challenge
መልካም ምሽት !

@psychoet
እንደምን አመሻችሁ !

ዛሬ ሁላችሁም ይህን የምታነቡ ከመተኛታችሁ በፊት #5 ደቂቃ ወስዳችሁ ይህን እንድታስቡ እጠይቃችኀለሁ ?

📌 ከተወለዳችሁ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ የሰራችሁት #ትልቁ_የደግነት_ስራ ምንድን ነው ?
📌ከተወለዳችሁ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በጣም ትልቅ የምትሉትን ውለታ የዋለላችሁ ሰው ማነው?


ይህን ሳትመልሱ አትደሩ አትዋሉ፡፡ በጣም ወሳኝና የብዙ አመት ባዶ ሩጫን የሚቀንስ ጥያቄ ነው፡፡

@Psychoet
መልካም ምሽት እና አዳር!
በአዲሱ ዓመት (2013) ምን ያህሎቻችሁ ዓመታዊ እቅድ አቅዳችኋል ???

ያቀዳችሁ
ያላቀዳችሁ
ማቀድ የማትፈልጉ ⛔️
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
👉 ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች

ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።

1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።

2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።

3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።

4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።

5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።

6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።

7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።

8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው። በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።

9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው። ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣ ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።

10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
#በቅንነት ሼር አድርጉ

@psychoet
10ኛ ዓመት ሜሎሪና
17/01/2003 -------17/01/2013
-ከራስ ጋር የተደረገ ውይይት

ዛሬ ከመስቀል በዓል በተጨማሪ ለኔ ልዩና ትልቁ ቀን ነው ፡፡ ሜሎሪና መጽሐፍ መጻፍ የተጀመረው የዛሬ 10 ዓመት በዚህች ቀን ነበር ፡፡ ደግሞ ታሪክ ዛሬ ራሱን ይደግምና ከወራት ጥናትና የታሪክ ውቅር በኀላ ሜሎሪና ክፍል ኹለት መጻፍ እጀምራለሁ ፡፡ እንደፈጣሪ ፍቃድ በዚህ ዓመት ምርጫ ፣ ልደቴንና ምርቃቴንና ታክኮ ለአንባቢ ይደርሳል ፡፡

ለወዳጆቼ በተለይም ለኔ ዘመን ወጣቶች ማለት የምፈልገው ባላችሁ ራዕይና እቅድ ተስፋ አትቁረጡ ነው ፡፡ ሕይወትን ከአንዴ በላይ በዚህ ምድር አንኖርምና በደስታ ለአላማችን እንኑረው ፡፡ እኔ ያለፉትን አስር ዓመታት በብዙ ውጣ ውረድ ያለፍኩበት ፣ ራሴን ፈልጌ ያገኘኹበት ደግሜም የፈለኩበት ፣ ብዙ ጓደኞችን ያወኩበት ፣ ሕይወትን በጥቂትም ቢሆን የተረዳሁበት ከኹሉም በላይ ግን የሜሎሪናን Project በደንብ የሰራሁበት ነበር ፡፡ በኹሉም የሕይወት መንገድ ትምህርትን ወስጃለሁ በፈጣሪ ተስፋን ሰንቄያለሁ ፡፡

ሜሎሪና መጽሐፍ ልብወለድ ብቻ ሳይሆን የአለማችን የወደፊት ትልቅ Project እና እጣ ፈንታ ነው ፡፡ የሚረዱኝ ይረዱኛል ቀሪዎች ደግሞ ሲሆን በተግባር ያያሉ ፡፡ ሃሳቤ ስለ ዓለም ህዝብ በሙሉ ነውና ፡፡ በሜሎሪና ኑሬ መሞትን ሳይሆን ሙቼ መኖርን ፣ ዜጋዊ ሳይኾን ሰዋዊ ማንነትን ፣ መድረሻን ብቻ ሳይኾን መንገድን ተረድቻለሁ ፡፡

ለሜሎሪና ❤️❤️❤️ መልካም 10ኛ ዓመት እመኛለኹ ፡፡ በዚህ ሶስት አመት( ፳፻፲፭ ከመጠናቀቁ በፊት) የዓለማችንን ኹሉም ሃገራትና ሚዲያዎችን የሚያነጋግርና የሚያስደንቅ ነገር በኢትዮጵያ ይከሰታል ፡፡ እንዴት መቼና በማን የሚለውን እናያለን ፡፡ ፈጣሪ የዛ ሰዎች ይበለን ፡፡

#2050
👉ጠቃሚ ምክሮች👈

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

#መልካም_ቀን !
#Share #Like
@Psychoet
ሜሎሪና 3ተኛ ዕትም በገበያ ላይ

"ሜሎሪና" ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ ለአንባቢያን በቀረበ ሦስት ወር ሳይሞላው #ሦስተኛ_ዕትም ገበያ ላይ ውሏል ፡፡ አንብባችሁ ስለወደዳችኹት ደግሞም አስተያየታችሁን በተለያዩ መንገዶች እያደረሳችሁኝ ስላላችሁ አመሠግናለሁ ፡፡

መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው ስነ-ልቦናዊ ልቦለድ ሲሆን የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበባዊ ሚና የሚተርክና ከፍተኛ የአስተሳሰብ ልዕልናችንን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው ፡፡

ከመጽሐፉ የተወሰደ

አብዛኞቻችን ሕይወታችንን የምንመራው ነገን በመፍራት ነው፡፡ በተለይም በማይመች አካባቢ ስንኖር ሕይወታችን እንዲሁ የሚያልቅ ስለሚመስለን ሐዘናችን ይጨምራል ሕይወትም ትጨልምብናለች፡፡ ምንም እንኳን ለመሥራት እስከተነሣን ድረስ በሕይወታችን ረፈደ የሚባል ጊዜ ባይኖርም፣ እኛ የሰው ልጆች ግን ከሕይወት ይልቅ ለሞት፣ ከደስታ ይልቅ ለሐዘን፣ ከመቀጠል ይልቅ ለማቆም የቀረብን ፍጡር ነን፡፡

****

በሕይወት ከመኖር ይልቅ መሞት ይቀላል፡፡ ለመኖር፣ መሥራትና መጣር፣ መውጣትና መውረድ ሲያስፈልግ፣ ለመሞት ግን ምንም ሳይሠሩ ቊጭ ማለት በቂ ነው፡፡ ምክንያቱም ከአፈር የተሠራው ሥጋ ለመኖር አፈር ይፈልጋልና፡፡ እኛ ሰዎች አሳባችን ከምንኖርበት ዓለም የሰፋና የጠለቀ ቢኾንም፣ እኛ ግን ይህንን ዘንግተን በተቈጠረው የሕይወት ዘመናችን ከሰፊው ራሳችን ይልቅ ወደ ጠባቡ ውጪ በመመልከት በሙሉ ማንነታችን ባዶነትን የምንላበስ፣ በክቡር ሥጋችን ውርደትን የምንከናነብ፣ በምክንያት በመጣንባት ምድር በዋዛ ኖረን በዋዛ የምናልፍ ነን፡፡

-ሜሎሪና-


ያላነበባችሁ መጽሐፋን በተመጣጣኝ ዋጋ በጃዕፈር መጽሐፍ መደብር ታገኛላችሁ ፡፡

#
አንባቢ_ልበ_ብርሃን_ትውልድ
በኢትየጵያ የሚወጡ አዳዲስ መጽሐፎችን በቀላሉ ለማግኘት የጃዕፈርን መጽሐፍ መደብር ቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ
@Jafbok
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሜሎሪና 3ተኛ ዕትም በገበያ ላይ "ሜሎሪና" ታሪካዊ የሳይኮሎጂ ልብወለድ ለአንባቢያን በቀረበ ሦስት ወር ሳይሞላው #ሦስተኛ_ዕትም ገበያ ላይ ውሏል ፡፡ አንብባችሁ ስለወደዳችኹት ደግሞም አስተያየታችሁን በተለያዩ መንገዶች እያደረሳችሁኝ ስላላችሁ አመሠግናለሁ ፡፡ መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው ስነ-ልቦናዊ ልቦለድ ሲሆን የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው ትግል ውስጥ የኢትዮጵያውያንን ቀደምት ጥበባዊ…»
የአሸናፊነት ሳይኮሎጂ
በናሁሰናይ ፀዳሉ

አሸናፊነት በራሱ ባህሪይ ነው ለዛውም የምንለማመደውና የምናሳድገው ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እንጂ ከተግባር አይደለም ፡፡ በሀሳቡ ፣ በአዕምሮው የተሸነፈ ሰው በተግባር ቢያሸንፍም ውስጣዊ ደስታ እርካታ ድልን አያገኝም ፡፡ አሸናፊነት የሚለመድ የሚታይ ባህሪይ ነው ፡፡

10ሩ የአሸናፊዎች ባህሪ

1. Self Projection
ይህ ማለት ወደፊት ልንሆነው ፣ ልንደርስበት እና ሊኖረን ስለምንፈልገው ነገር ጥርት ያለ እይታ / አመለካከት መኖር ነው ፡፡ የመጨረሻ መዳረሻ ግባችንን አስበን ወደዛ ለመጓዝ የምናረገውን ሂደት በአይነ ሕሊናችን መሳል / መመልከት ነው ፡፡

2.Setting Goals

ይህ ደግሞ በአይነ ሕሊናች የሳልናቸው የመጨረሻ ውጤቶች ጋር ለመድረስ የምናበጀው ግብ ነው ፡፡ የምናዘጋጃቸው ግቦች ተግባራዊ የሚሆኑ ፣ በጊዜ የተወሰኑ ፣ ሊደረስባቸው የሚችሉ ፣ ሊለኩ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡ አለበለዚያ ግቡን ማሳካት አንችልም / እጅጉን ይከብደናል ፡፡

3.Focus positive side

ፍርሀት ጭንቀትንና ውጥረትን ይወልዳል ፡፡ ፍርሀት ደግሞ በአብዛኛው የሚመነጨው ከአሉታዊ አመለካከት ነው ይህ አመለካከት ደግሞ በሕይወታችን አሸናፊዎች እንዳንሆን ይይዘናል ፡፡ ስለዚህ አሸናፊዎች ሁልጊዜም ቀና / አወንታዊ አሳቢዎች ናቸው ፡፡

4.power of self determination

ቆራጥነት ሌላው የአሸናፊነት ሥነልቡና መነሻ ነው ፡፡ ብዙ ሰው ለሚሰራው ስራ ፣ ለሚወዳደረው ውድድር ፣ ለሚያጋጥመው ፍልሚያ ቆራጥ አይደለም ፡፡ የምንሰራውን ስራ የምንሰራው ግድ ስለሆነ ፣ ገንዘብ ለማግኛ ብቻ እንጂ በሕይወታችን ደስታን ለማግኚያ አይደለም ፡፡ ስለዚህ የአሸናፊነት ሥነልቡና ለማዳበር በስራችን ቋራጥና የምናረገውን ነገር ሁሉ ለሌላ ሰው ብለን ሳይሆን ለራሳችን ብለን ማድረግ አለብን ፡፡

5.Self Awareness

በዚህ ምድር አንድም ፍፁም ሰው የለም ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ ፍፁምነት / ሁሉን አዋቂነት ሳይሆን በምንወዳደርበት ነገር ተሽሎ (በልጦ) መገኘት ነው ፡፡ ለዚህ ደግሞ ራስን ማወቅ ( ደካማና ጠንካራ ጎናችንን) ወሳኝነት አለው፡፡

የሚቀጥሉትን 5 ባህሪያት በቀጣዩ ቀን እንመለከታለን ፡፡

👍 #Like ▶️ #Share በማረግ ሁላችንም ባለንበት ቦታ አሸናፊ እንሁን !

መልካም እሑድ!
@psychoet
#መልካም_ጥቅምት_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

አንድ ቀን ነገር ሁሉ ቀላል ይሆናል ! ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ለምትወዱት ጓደኛ #መልዕክቱን አስተላልፉ

@Psychoet
የአሸናፊነት ሥነልቡና
#ክፍል_2
በናሁሰናይ ፀዳሉ

አሸናፊነት በራሱ ባህሪይ ነው ለዛውም የምንለማመደውና የምናሳድገው ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እንጂ ከተግባር አይደለም ፡፡ በሀሳቡ ፣ በአዕምሮው የተሸነፈ ሰው በተግባር ቢያሸንፍም ውስጣዊ ደስታ እርካታ ድልን አያገኝም ፡፡ አሸናፊነት የሚለመድ የሚታይ ባህሪይ ነው ፡፡

10ሩ የአሸናፊዎች ባህሪ

ከተራ ቁጥር 1 - 5 ያሉትን ባለፈው በዝርዝር አይተናል፡፡ ዛሬ ከተራ ቁጥር 6-10 ያሉትን እናያለን ፡፡
______________________________
1.ልንሆነው/ልንደርስበት ስለምንፈልገው ነገር የጠራ እይታ / አመለካከት
2.ግብ ማስቀመጥ
3.አወንታዊ አመለካከት
4.ቆራጥነት
5.ራስን ማወቅ
______________________________

6.Self Esteem / ራስን ማክበር

አሸናፊ ሰዎች ለራሳቸው ትልቅ ክብርና አድናቆት ያለቸው ናቸው ፡፡ስለራሳቸው ጥሩ አወንታዊ አመለካከት አላቸው ይህ ማለት ግን ሌሎችን ይንቃሉ / አያከብሩም ማለት አይደለም፡፡ ራስን ማክበርና ሌሎችን ማክበር መነጣጠል የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ተሳካልን ፣ ትልቅ ደረጃ ደረስን አሸነፍን የሚሉ ሰዎች ከታች ያሉ ሰዎቾን የመናቅ ያለማክበር ሁኔታ ይታያል ይህ ግን ትልቅ ችግርና ያልተሟላ አሸናፊነት ብሎም ለወደፊነቱ ወደ ተሸናፊነት የሚወስድ መንገድ ነው ፡፡ አሸናፊ እራሱን ያከብራል ደግሞም ያስከብራል ብሎም ደግሞ ሌሎችን አክብሮ ያስከብራል ፡፡

7.Self Discipline / ስርአት መኖር

ይህ በተግባር የሚገለፅ የአሸናፊነት ባህሪ ነው ። በዚህ ዘመን ብዙ ሰው የወሬ እንጂ የስርአትና የተገባር ሰው አይደለም ከላይ አመራር ጀምሮ እስከታች ድረስ ብዙ ጊዜ ወሬ እንጂ ስርአትና / ተግባር አይታይም ፡፡ ጠንካራ ልምምዶችን እንደ ልምድ አድርጎ በተግባር አለመግለፅ አሸናፊ እንዳንሆን ያረገናል ፡፡ ለምሳሌ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ብንመለከት ልምምዳቸውን በየጊዜው በስርአት ካልሰሩ ብዙ ሽንፈት ሊገጥማቸው ይችላል ፡፡

8.Self Talk / ከራስ ጋር ማውራት (ጊዜ መውሰድ)

አሸናፊዎች ሁልጊዜ የሚራራጡ ፣ እረፍትና እርጋታ የሌላቸው ፣ ሁሌ ሳያቋርጡ የሚሰሩ አይደሉም ፡፡፡ይልቁንስ በቂ ሰአት ስራቸው ላይ የሚያጠፉ እንዲሁም ተመጣጣኝ ጊዜ ደግሞ ለራሳቸው የሚሰጡ ፣ ነገሮችን በትኩረት ረጋ ብለው የሚያስቡ (ሳይጨነቁ ነገሮችን የሚያወጡ የሚያወርዱ) ናቸው ፡፡ ከራሳቸው ጋር በቂ ጊዜ የሚወስዱ ሰዎች ሁሌ ከውጥረት ብሎም ከጭንቀት ራሳቸውን ያስመልጣሉ ፡፡

9.Complete person / ሙሉ ሰውነት

ትክክለኛ አሸናፊ ሰው አንድ ወገን ብቻ ያደገ ፣ ሌላው ጎኑ የጎደለ ሳይሆን በሙሉ ማንነቱ የሞላ ያሸነፈ ነው ፡፡ ሕይወት ትምህርት ጥሩ ውጤት ማምጣት / ሩጦ 1ኛ መውጣት ፣ ተዋግቶ ማሸነፍ ፣ በሀብት ትልቅ ደረጃ መድረስ ብቻ አይደለችም ፡፡ አንዳንድ ሰው በገንዘብ አቅሙ ትልቅ ደረጃ ይደርስና በማህበራዊ ሕይወቱ ደግሞ 0 ይሆናል ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰው ሙሉ ሰው አንለውም ፡፡


10.Live in the present/ አሁንን መኖር

ይሄ ብዙዎች አሸናፊ እንዳይሆኑ የሚያረግ የአመለካከት ችግር ነው ፡፡ ነገራችንን በሙሉ በነገ ተስፋና በትናንት ፀፀት / ወቀሳ ዛሬ ላይ በደንቡ ሳንኖር በሀዘን እንዘልቃለን ፡፡ አሁንን በአሸናፊነት ሀሳብ/ አመለካከት ሳንኖር የነገን ያልተጨበጠ ድል በማለም በተስፋ ብቻ እንደክማለን ፡፡ ስለዚህ አሸናፊ ለመሆን የሚያስብ ሰው አሸናፊነት ስለ ነገና ስለ ወደፊት ሳይሆን ስለ አሁን ነው ፡፡


👍 #Like ▶️ #Share በማረግ ሁላችንም ባለንበት ቦታ አሸናፊ እንሁን !

አሸናፊነት የሚጀምረው ከአስተሳሰብ ነውና አስተሳሰባችሁን ቀና ፣ በጎ ፣ ጥሩ ጥሩውን ማድረግ ጀምሩ ፡፡ አሉታዊ አስተሳሰባችሁን በአወንታዊ ሀሳቦች ለውጡ ፡፡

#መልካም_ሳምንት!
@Psychoet
ባንተ ውስጥ ያንተን እድገት የሚቃወም ጭራቅ አለ፡፡ከድህነት እንድታመልጥ አይፈልግም፡፡ከመጥፎ ጓደኞችህ ስትሸሽ ያመዋል፡፡ከሱስ ስትርቅ ይጨንቀዋል፡፡ፍላጎቱ ለጊዛዊ ደስታ ጊዜና ሐይልህን በከንቱ እንድታባክን ነው፡፡
+
በተለይ አዲስ ነገር ስትሞክር ይንጫጫል፡፡
"ይህን ማድረግ አደጋ አለው!! ጎመን በጤና! ዋ! ትከስራለህ !ይሳቅብሃል!!" በማለት አዛኝ መስሎ እንደ ሐውልት ያስቆምሃል፡፡በጊዜ ሂደትም ወደኃላ ጎትቶ ይጥልሃል፡፡በገዛ ራስህ ህይወት አቅም ታጣለህ፡፡እሱ ንጉስ አንተ ባርያ ትሆናለህ::
+
ባርነት አልሰለቸህም? የራስህ ህይወት ንጉስ መሆን አላመማረህም? ከጭራቁ እስር ቤት ነጻ መውጣትስ? በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ነገር ማድረግስ? የራስህን ህይወት መኪና መሪ መጨበጥስ? ህልምህን አሳክተህ ከስኬት ተራራ ጫፍ መሆንስ? አያጓጓህም? መልስህ "አዎ!" ከሆነ በመጀመርያ በውስጥህ ያንቀላፋውን ጀግና ቀስቅሰው፡፡
+
ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡፡ይህ ጀግና ፈጣሪን የሚመስል ገራሚ ሐይል ነው፡፡ይህንን ሐይል ማድመጥ ጀምር፡፡የጭራቁን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡
+
ጭራቁ ማንነትህ ፈሪ ነው፡፡ጀግናው ማንነት #አማኝ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡፡ጀግናው ማንነትህ #ለፊ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ "ሰው ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ስህተት ይፈራል፡፡ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡ጀግናው ማንንትት ግን "እኔ ራሴን ምን እላለው? ፈጣሪስ ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡፡ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል።
©ከFB የተገኘ

#SHARE
@psychoet
2024/09/29 19:26:50
Back to Top
HTML Embed Code: