Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «እንኳን ለ 2013 ዐዲስ አመት አደረሰን! #ሜሎሪና መጽሐፍ ለዐዲሱ አመት ስጦታ፡፡ በብዙ አንባቢያን ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ሜሎሪና ልብወለድ መጽሐፍ ለአንባቢያን በቀረበ በኹለት ወር ውስጥ ሦስተኛ ህትመት የተሰጠና ብዙዎች አንባቢዎችን ቀጣዩን በጉጉት እንዲጠብቁ ያደረገ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ ታሪካዊ ይዘት ያለው ሥነልቡናዊ ልቦለድ ሲሆን የሰው ልጅ ሞትን ለማሸነፍ በሚያረገው የማያቋርጥ ትግል ውስጥ…»
ከ"ሜሎሪና" መጽሐፍ የተወሰዱ የሕይወት ምክሮችና እውነታዎች

📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

📕በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡

📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡

📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖
ከሜሎሪና መጽሐፍ የተወሰዱ ሀሳቦች
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖

❖አንባቢ እናት ጥሩ ትውልድን ትገነባለችና ይቺን የመሰሉ እናቶች ይብዙልን ፡፡ ፎቶው የተላከልኝ ከወደ አዋሳ ነው ፡፡

መልዕክቱን ለሌሎችም ወዳጆቻችን #Share እናድርግ

"ሜሎሪና" መጽሐፍን በጃዕፈር ፣ በሀሁ ፣ በእነሆ ፣ Book Light ጨምሮ በሀገራችን በኹሉም ክልሎች በሚገኙ የመጽሐፍ መደብሮች ይገኛል ፡፡ ለዐዲስ ዓመት ለወዳጅዎ የሚሰጡት ትልቅ ስጦታ ፡፡ ሜሎሪና ❤️❤️❤️

መልካም ቀን
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
www.tg-me.com/psychoet
አንዳንዴ እንዳሰብነው ባይሆን እንኳን እንዳሰበልን አኑሮን ከዘመን ዘመን አድርሶናል መጪውንም እሱ አብሮን ይሁን 😍 ፈጣሪ 🙇🏽

እነዚህ የጳጉሜ ቀናት የይቅርታ ፣ የምስጋና እንዲሁም የሚያልፈውን ዓመት የምንገመግምበት የሚመጣውን የምናቅድበት ቀናት ናቸው ስለሆነም

ሳላውቅ በስህተት
💙አውቄ በእህል💔
አስቀይሜ
አሳዝኜ
አስከፍቼ
💜ከሆነ ከጉልበቴ
በርከክ ብዬ💗
💞
💞
💞
💞ታ እጠይቃለው💕
🖤በችግሬ በሃዘኔ ስከፋ ተከፋታችሁ ሳዝን አዝናችው💘
💖በደስታዬ ተደስታችው ሃሳቤን በመካፈል መፍትሄ ለሰጣችውኝ
💚ስሜታዊ ሆኜም
💙መታገስን ላስተማራችሁኝ💜💗
💖💕💞በዙሪያዬ
💓💗💖ያላችው
💙💜ኹሉ
💝
💝
💝
💝
💝
💝
💝
💝💕💞💓💗 መልካም አዲስ አመት 🌻🌻🌻🌻💐💐💐🌼🌼🌼ላንተ/ቺ ይሁንላችሁ ለጓደኞቻቹ ኣድርሱ እኔም🙋🙌 ከነዛ ውስጥ ከሆንኩ forward ኣድሩጉልኝ😙💕💕💕💕💕💕💕💕💕
@Psychoet
በእንግሊዝና በአሜሪካ ያላችሁ የፔጃችን ቤተሰቦች ሜሎሪናን ስትፈልጉ በእነዚህ ስልኮች በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡

★★★ አሜሪካ
+12022947117

★★★ ኢንግላድ
+447577009720


በአዲስ አበባ ያላችሁ ደግሞ እቤታችሁ ድረስ በዋጋው እንዲመጣ በዚህ +251939115238 ደውሉ ፡፡

በዚህ ፔጅ ከ 16,700 በላይ ቤተሰቦች አላችሁ ፡፡ ምን ያህሎቻችሁ ሜሎሪናን አንብባችኀል?

@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «በእንግሊዝና በአሜሪካ ያላችሁ የፔጃችን ቤተሰቦች ሜሎሪናን ስትፈልጉ በእነዚህ ስልኮች በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡ ★★★ አሜሪካ +12022947117 ★★★ ኢንግላድ +447577009720 በአዲስ አበባ ያላችሁ ደግሞ እቤታችሁ ድረስ በዋጋው እንዲመጣ በዚህ +251939115238 ደውሉ ፡፡ በዚህ ፔጅ ከ 16,700 በላይ ቤተሰቦች አላችሁ ፡፡ ምን ያህሎቻችሁ ሜሎሪናን አንብባችኀል? @Psychoet»
Forwarded from Jafer Books 📚 (Zee - Se)
በአጭር ጊዜ ተወዳጅ የሆነው " ሜሎሪና " የተሰኘው መጽሐፍ ሁለተኛ ዕትም ለንባብ በቃ ::
መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ) ©Zepsychology
@Psychoet
ኹል ጊዜ ደጋግሜ ሳነበው የሚያፅናናኝ ቃል

በሕይወታችን አንዳንድ ጊዜ ለፍተን፣ ጥረን፣ ደክመን ምንም ውጤት እናጣለን ፡፡ ይባስ ብሎ በአቅማችን የሰራነው ነገር ደግሞ ወዲያው ሲበላሽ፣ ሲወድም፣ ሲጠፋ እንመለከታለን ፡፡ በሕይወት ትግል ኹል ጊዜ ተሸናፊዎች የኾንን እስኪመስለን ድረስ ተስፋ ቆርጠን ፣ ነገር ጨልሞብን በድንግዝግዝ እንመላለሳለን ፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ ፈጣሪ የሚባል ነገር ራሱ መኖሩን እንጠራጠራለን ፤ በቃ ሕይወት ራሱ ግራ ትገባናለች፡፡

ግን እኔ ይህን አምናለሁ ፡፡ የእኛነታችን ዋንኛው ጥንካሬ የሚፈተሸው በዚህ ስሜትና ኹኔታ ውስጥ ነው ፡፡
መልካም ቀን ይኹንላችሁ ፡፡
ጷግሜ 2 ፣ 2012
@psychoet
በሌለን ነገር ከማማረር ባለን ነገር ማመስገን ጤናማ ያደርጋል ፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ ፡፡
ሀሳቡን ለሌሎችም አጋሩ
@psychoet
በፈታኝ ሳጥን #Show
ስለ ሜሎሪና መጽሐፍ ያደረኩት ውይይት

ናሁሰናይ ፀዳሉ | ሜሎሪና

https://youtu.be/t-vrVH351EM
🐘🐘🐘 እና 🐕🐕🐕
#ከለታት_በአንድ_ቀን_አንድ_ዝሆንና_አንድ_ዉሻ_በተመሳሳይ_ቀን_አረገዙ፡፡
ከሶስት ወር በኀላ ዉሻዋ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኀላም ዉሻዋ በድጋሜ አረገዘች እናም በዘጠነኛዉ ወር ሌሎች ብዙ ቡችሎችን ወለደች ፡፡ ዉሻዋ እንዲህ እያለች ብዙ ቡችሎችን ወለደች፡፡

በ18ኛዉ ወር ግን ግራ የገባት ዉሻ ወደቀድሞ ዝሆን ጓደኛዋ ሂዳ እንዲህ ስትል ጠየቀቻት "እርግጠኛ ነሽ ግን ማርገዝሽን? " ካስታወሽ የ ዛሬ 18 ወር እኩል ነበር ያረገዝነዉ ይሁን እንጂ ባለፋት ወራት እኔ ብዙ ቡችሎችን ወልጄ አሁን ትላልቅ ሁነዋል፡፡ አንቺ ግን እስካሁን የምር እርጉዝ ነሽ? ምን እየሆነ ነዉ ስትል ጠየቀቻት፡፡

ይህን የሰማችዉ ብልህ ዝሆን በእርጋታ እንዲህ ስትል መለሰች ፡፡ ዉድ ጓደኛዬ፥ እንድታዉቂዉ የምፈልገዉ አንድ ነገር አለ፡፡ ያረገዝኩት እኮ ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡ በሁለት አመት አንድ ዝሆን ብቻ ነዉ እኔ ልወልድ የምችለዉ፡፡ ነገር ግን ልጄን በወለድኩ ጊዜና ልጄ መሬት ሲረግጥ መሬት ራሱ ትናወጣለች ፡፡ ልጄ መንገድ ሲያቋርጥ የሰዉ ልጆች ሁሉ ቆመዉ በአድናቆት ይመለከቱታል፡፡ እኔ ያዘልኩት ፅንስ ትኩረትን የሚስብ ነዉ፡፡ የያዝኩት ትንሽ ነገር ሳይሆን ሀያል የሆነ ዝሆን ነዉ ብላ መለሰች፡፡

#ትምህርት / Lesson

💠ሌሎች የራሳቸዉን ግብ በፍጥነት ሲመቱ የኔ አይሳካም ብለን ተስፋ አንቁረጥ በሌሎችም አንቅና ምክንያቱም
፩ . የኛ ስኬት የሚወሰነዉ በራሳችን ትጋት(ፅንስ) እንጂ በሌሎች ላይ ስላልሆነ
፪ . ጥሩ ነገር ሁሌ ግዜ ይወስዳል ( ትልቅ ነገር ለመስራት ብቻ ሳይሆን ለማሰብም ግዜ ይወስዳል ዉጤቱ ግን ታላቅ ነዉ )
፫ . ....
ይህንን ካነቡ አይቀር 👉በዉስጣቸዉ ትልቅ ነገር አለ ለምትሉት ጓደኛ/ዘመድ/ቤተሰብ ይህን #FORWARD #Share ያድርጉ፡፡
🙌🙌🙌

2013 ሀሳባችሁን የምታሳኩበት ዓመት ይኹንላችሁ !
ልብህ በብርሀን የተሞላ ከሆነ መንገዱ አይጨልምብህም!
ከ 19 ዓመት በፊት...
ሜሎሪና የዛሬውን ቀን እንዲህ ያስታውሰናል
ዐዲስ ዓመት እና 9/11 ጥቃት


መልካም ዐዲስ ዓመት!
🌻 ልዩ 🌻🌻የ 2🌼13🌻🌻
የአዲስ ዓመት የበዓል ዝግጅት
🌻#አዜክስ #ኢንተርቴመንት 🌻 2🌼13ዓ.ም🌻

✿የደስታ የጤና የብልጽግና ስኬታማ ምንሆንበት
✿ ሀገራችን ሰላሟ ተጠብቆ የምንኖርበት የበረከት ዘመን ያድርግልን

🌻🌻🌻 እንዲሁም የ ስኬት ዘመን እንዲሆንልን እንመኛለን

https://youtu.be/WEabjkEPiEQ
ለወዳጅዎ ዘመድዎ በማጋራት የመልካም ምኞት ሀሳቦን ይግለፁበት 🌹
🌼መልካም አዲስ አመት🌼
#ተሰሚነት
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ብዙዎቻችን የሚጎለን ክህሎት ስለሆነ ሌሎችም እንዲማሩ አንብበን #Share እናርገው

“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡ ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡

ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡

ቅለት

ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡

ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ

“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡

በራስ መተማመን

አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ ጉልበት አላቸው፡፡

በሌሎች ዓይን ማየት

ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣ ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ መቼም አይጠፋም፡፡

ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡

እጥረትን መፍጠር

ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣ የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣ በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡

ዝግጅት

ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመናችንንም ይገነባል፡፡

ለምሳሌ እነዚህን በሙሉ ክህሎቶች ዶ/ር ምህረት ላይ እናገኛለን ፡፡ የመሰማቱ አንዱ ሚስጢር ይሄ ነዉ ፡፡ ሲያስተምር አይታችሁ ከሆነ የሚያስተምረውን ነገር ቀለል አርጎ ፣ በራስ መተማመን ለአድማጭ በሚስብ መልኩ ያደርጋል ፡፡ ይህ በሁላችን አድማጮቹ ዘንድ ተሰሚነትን ፈጥሮለታል ፡፡ በሌላ በኩል አንድ ሰፈር /ስራ ቦታ የምናውቀውን ሳያቋርጥ የሚያወራ ፣ ንግግር የማያስጨርስ ሰው ስናስብ እንኳን ለመስማት ከሱ ጋር ለማውራት ይቀንቀናል ፡፡ እንግዲህ ሚስጥሩ ይሄው ነው ፡፡

በሰዎች ዘንድ ለመሰማት በዕውቀትና በጥበብ እናውራ !
(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
#Share & #Like oue page - fb.com/psychologyet
ሜሎሪና
❤️❤️❤️
መልካም ቀን!
@Psychoet
2024/09/29 21:36:25
Back to Top
HTML Embed Code: