Telegram Web Link
ማድረግ እየቻልክ አትመኝ
ምኞት የሰነፍ ሰው ህልም ነው።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
#SHARE አድርጉት ብዙ ሰው ያስተምራል
#Frustration / #ተስፋ_መቁረጥ_ከየት_ይመጣል ?
___

ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ሁነው ተስፋ የለኝም ፣ ተስፋዬ ተሟጧል ፣ የመሳሰሉትን ቃላት በቀን ተቀን ሕይወታቸው ይጠቀማሉ ፡፡

ተስፋ መቁረጥ ወደ ግባችን / ፍላጎቶቻችን እንዳንደርስ የሚያረገን ባህሪ ነው ፡፡ በሕይወቱ ብዙ ጊዜ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ወደግቡ/እቅዱ የመድረሱ እድል በጣም አነስተኛ ነው ፡፡ ወደ ጠቃሚ የሕይወት ግባችን አለመድረስ ደግሞ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት ፣ የበደለኝነት ስሜት ያመጣብናል ፡፡

ሳይኮሎጂ ችግር የመፍቻ ዋና መንገዱ የችግሩን ምክንያት መረዳት እንደሆነ ያትታል ፡፡ስለሆነም የተስፋ መቁረጥ ዋና ዋና ምክንያቶች እንመለከታለን፡፡
___
1
.Environmental Factor (አካባቢያዊ ምክንያት)

በአካባቢያችን ያሉ የተለያዩ ሁኔታዎችና ገጠመኞች ፍላጎቶቻችንንና እቅዳችንን እንዳናሳካ ይከለክሉናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ማድረግ የምንፈልገውን ነገሮች " አትችለውም ፣ ይከብድሀል ፣ ከዚህ በፊት አልተሞከረም ፣ ሰው ምን ይልሀል" በማለት ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ያደግንበት ባህል ፣ የምንኖርበት አካባቢ ለማድረግ ያቀድነውን ነገር እንዳናሳካ በራሱ ሊይዘን ይችላል ፡፡ ይሄ በሕይወታችን ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል ፡፡

2.Personal inadequency Factor (ግላዊ ብቃት/ክህሎት ማጠር )

ይህ ደግሞ ፍላጎቶቻችንን እንዳናደርግ የሚገድበን አለመሙላት (ብቃት አልባነት) ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድን እቃ በጣም ወደነው ለመግዛት ስንፈልግ ከተወደደብንና ያለን ገንዘብ አነስተኛ ከሆነ ተስፋ ቆርጠን ላንገዛ እንችላለን ፡፡ እዚህ ጋር ነገሩን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አለመኖር የራሳችን የሆነ ጉድለት ይሆናል፡፡ ሌላው አንድን ነገር ለመስራት አስበን የግል ችሎታ / ብቃት/ ክህሎት ሲያንሰን እሱ " በቃ አልችልም " በማለት ተስፋ ለመቁረጥ መንስኤ ይሆነናል ፡፡

3. Conflict of interest ( የፍላጎት ግጭት )
የመጨረሻው የግላዊ ፍላጎቶች/ ግቦች እርስ በእርስ ሲፃረሩ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችላል ፡፡ ተስፋ መቁረጡ የሚመጣዎ ሁለቱንም ግቦቻችንን ልናሳካ ባለመቻላችን ነው ፡፡ አንዱን ግብ ብናሳካ ራሱ ሌላውን ስላላሳካን የመወላወል ተስፋ የመቁረጥ ( የማዘን ) ስሜት ይሰማናል፡፡

ከነዚህ ሶስቱ ዎና ዎና ምክንያቶች እግጅ በጣም ብዙ ሰው የሚያጋጥመው የመጨረሻው (.Conflict of Motives / የፍላጎት ግጭት ) እንደሆነ ሳይኮሎጂ ይጠቁማል፡፡
__
እነዚ
ህ Conflict of motives ( የፍላጎት ግጭት ) ደግሞ በ አራት ይከፈላሉ ፡፡
__
ሀ.
Approach - Approach Conflict
(ፍላጎት ፥ ፍላጎት ግጭት)

ይህ ግጭት ሁለት ነገሮችን በእኩል ፈልገን ነገር ግን መምረጥ የምንችለው አንዱን ብቻ ሲሆን ማለት ነው ፡፡ ለምሳሌ :- ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኅላ Department ሲመርጡ ብዙ ተማሪዎች በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ የdepartment ምርጫዎች ይወጠራሉ ነገር ግን መምረጥ የሚችሉት የወደዱትን ሁሉ ሳይሆን አንዱን ብቻ ስለሚሆን ግጭት ውስጥ ይገባሉ ፡፡ ሌላው ገበያ ሂደን ሁለት ሱሪዎች በጣም ወደናቸው ነገር ግን መግዛት የምንችለው አንዱን ብቻ ከሆነ ይህ አይነት ግጭት ከራሳችን ጋር ይገጥመናል፡፡

ለ. Avoidance - Avoidance Conflict (የማስወገድ ፥ የማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ ከሁለት የማንፈልጋቸው ነገሮች የግድ አንዱን መምረጥ ግድ ሲለን ነው ፡፡
ለምሳሌ ፦ ልጃችን በሰዎች ታግቶ ብር ካልከፈላችሁ ይገደላል ቢሉን ፤ እዚህ ጋር ልጁ እንዲሞትም አንፈልግም ለአጋቾቹ ብር መክፈልም አንፈልግም ፡፡ ግን አንዱን መምረጥ ግድ ይለናል ፡፡ ሌላ ምሳሌ ፦

ሐ. Approach - Avoidance Conflict (የፍላጎትና ማስወገድ ግጭት)

ይህ ደግሞ በአንድ ግብ ላይ የፍላጎትም የማስወገድም ስሜት ሲሰማን ነው ፡፡

መ. Multiple Approach - Avoidance Conflict (ብዙ የፍላጎት ማስወገድ ግጭት)

ይህ ሁላችንም በሕይወት ቆይታችን የሚያጋጥመን የለት ተለት ግጭት ነው ፡፡ እያንዳንዱ የሚገጥመን ነገር #ብዙ_አወንታዊና_አሉታዊ ነገሮች ይይዝና እሱን #መምረጥና #አለመምረጥ ችግር ይሆናል ፡፡
ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው መልኩን ፣ ገቢውን ወደን ፀባዩ አመለካከቱ ካላማረን ይሆነኛል አይሆነኝም ብለን ከራሳችን እንጋጫለን ፡፡ሌላው አንድን ስራ ስንሰራ በዉስጡ ያሉ የተለያዩ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ስገፉን ሲስቡን እንደዚህ አይነት ግጭት ውስጥ እንገባለን ፡፡

፠፠__፠፠

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙
www.tg-me.com/Psychoet 👍

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠__፠፠
ሳምንት ሰው ይበለን!
@ሳይኮሎጂ
Like our page
ወርቃማ #አባባሎች! ሼር
ቴሌግራም - T.me/PSYCHOET
🌼🌼ለቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ መልካምና ውጤታማ 2016 ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡ 🙏

2016 በራሱ ይዞ የሚመጣው አንዳች ነገር የለውም ዋናው ጉዳይ እኛ ወደ 2016 ምን ይዘን መተናል ነው፡፡ 🌼🌼 ዓመቱ መልካም እቅዶችንና ስራዎችን የምንሰራበት ዓመት ይኹን!

🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼

በዚህ አዲስ አመት በፔጃችን የተለያዩ የስነልቦና ሀሳቦችን ማንሳታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይኾናል። በተጨማሪም ከእናንተ በሚነሱ ሀሳቦች ላይ ሙያዊ ገለጻ ማድረግ እንጀምራለን።

           አዲስዓመት
     መልካምአዲስዓመት
  መልካም        አዲስዓመት
መልካም           አዲስዓመት
መልካም             አዲስዓመት
መልካም             አዲስዓመት
                        አዲስዓመት
                       አዲስዓመት
                     አዲስዓመት
                   አዲስዓመት
                 አዲስዓመት
            አዲስዓመት
        አዲስዓመት
      አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመት                አዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመትአዲስዓመት

             አዲስዓመት
        መልካምአዲስዓመት
መልካምአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት
        መልካምአዲስዓመት
              አዲስዓመት

                  ዓመት
            አዲስዓመት
መልካምአዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
            አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመት አዲስዓመት
አዲስዓመትአዲስዓመት

        
አዲስዓመት
        መልካምአዲስዓመት
መልካምአዲስዓመትአዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት             
አዲስዓመት
አዲስዓመት
አዲስዓመትመልካምአዓመት
መልካምአዲስዓመትአዲትዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
አዲስዓመት              አዲስዓመት
መልካም አዲስዓመትአዲስዓመት
    መልካምአዲስዓመትስዓመት
          መልካምአዲስዓመት
                 አዲስዓመት


🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
🔆🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🔆
🔆🌼🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🌻🌻 መልካም 🌻🌻️🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🌻🌻  አዲስ    🌻🌻🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🌻🌻  ዓመት    🌻🌻️🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🌻️🌹🌾🌻💐🌹🌻🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊🔸🌼🔆
🔆🌼🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🌼🔆
🔆🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🔆

መልካም አዲስ ዓመት
@psychoet
እወዳችኋለሁ❤️
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂ pinned «🌼🌼ለቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ መልካምና ውጤታማ 2016 ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡ 🙏 2016 በራሱ ይዞ የሚመጣው አንዳች ነገር የለውም ዋናው ጉዳይ እኛ ወደ 2016 ምን ይዘን መተናል ነው፡፡ 🌼🌼 ዓመቱ መልካም እቅዶችንና ስራዎችን የምንሰራበት ዓመት ይኹን! 🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼 በዚህ አዲስ አመት በፔጃችን የተለያዩ የስነልቦና ሀሳቦችን ማንሳታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይኾናል። በተጨማሪም…»
ሰላም ቤተሰቦች
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በየሳምንቱ ለሁለት ቀን ቋሚ የኾነ ከእናንተ ከሚነሱና ወቅቱን ያገናዘቡ #የሳይኮሎጂ #የአመራርና ማህበራዊ #የስራ ፈጠራ ጉዳዮች ዙሪያ #እፅፋለሁ ስለሆነም በየትኛው ቀን እንዲሆን እንደምትፈልጉ ከታች ምረጡ?

#የተሰጠው ድምፅ #የሚቆጠረው እስከ #ቅዳሜ ማታ 6:00 ያለውን ነው ፡፡

በዛውም ወደ ቻናሉ ሰዎችን በመጋበዝ የሚፈልጉትን እንዲመርጡና እንዲማሩ እንርዳ ፡፡

✿ Vote : #በTelegram_ብቻ@psychoet
1️⃣ ሰኞ
2️⃣ ማክሰኞ
3️⃣ ረቡዕ
4️⃣ ሀሙስ
5️⃣ አርብ
6️⃣ ቅዳሜ
እንወያይበት!

1. ዕቅድ ማውጣት ተገቢ ነው ወይስ ህይወት ባመራችን እንጓዝ?

@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
አስገራሚ እውነታዎች ስለእንቅልፍ
*****

• የሰው ልጅ የዕድሜውን አንድ ሦስተኛ የሚያሳልፈው በእንቅልፍ ነው። ይህም በአማካኝ 25 ዓመት ይሆናል።

• በቀን ከ7 ሰዓት በታች መተኛት የሰዎችን አማካኝ የመኖሪያ ዕድሜ ይቀንሳል።

• አላርም (የሚያነቃ ሰዓት) ከመፈጠሩ በፊት እንግሊዝ እና አየርላንድ ውስጥ ሰዎችን ከእንቅልፍ በመቀስቀስ የሚተዳደሩ ሠራተኞች ነበሩ። ሠራተኞቹ ማልደው ተነስተው በር እያንኳኩ ደምበኞችን ከእንቅልፍ ያስነሱ ነበር።

• ቀንድ አውጣ ያለማቋረጥ ለ3 ዓመት መተኛት ይችላል።

• ድመቶች የዕድሜያቸውን 70 በመቶ የሚያሳልፉት በእንቅልፍ ነው። ድመቶች በቀን እስከ 16 ሰዓት ይተኛሉ።

• አሜሪካን ለ1 ቀን ብቻ ያስተዳደሩት ፕሬዝዳንት ዴቪድ አቹሰን፤ ከ24 ሰዓት የስልጣን ዘመናቸው ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፉት በእንቅልፍ ነበር። ጊዜውም እ.ኤ.አ መጋቢት 4 ቀን 1894 ነው።

• ማይግሬን (ከባድ የራስ ምታት)፣ ዝቅተኛ የደም ግፊት እና የእንቅልፍ መቆራረጥ፣ የቅዥት ዋነኛ መንስኤዎች ናቸው።

• በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ፓል ከርን የተባለ የሀንጋሪ ወታደር የፊት ግንባሩን በጥይት ተመቶ እንቅልፍ የሚቆጣጠረው የአይምሮው ክፍል ላይ ከባድ ጉዳት ይደርስበታል። በዚህም ወታደሩ ለ40 ዓመታት ያህል (ቀሪ ዕድሜውን) ያለ እንቅልፍ አሳልፏል።

• ቀጭኔዎች ንቁ ለመሆን በቀን ከ5 እስከ 30 ደቂቃ ብቻ መተኛት በቂያቸው ነው። ቀጭኔዎች በቀን በአማካኝ እስከ 5 ሰዓት ይተኛሉ።

• ሞርፊን የሚለው ቃል የመጣው ሞርፈስ ከተባለው የጥንት ግሪኮች የእንቅልፍ እና የህልም አምላክ ነው። ሞርፊን የከባድ በሽታዎች የህመም ማስታገሻ ሲሆን በታማሚዎች ላይም የእንቅልፍ ስሜት ይፈጥራል።

• ምሽት ላይ ካፌን ያላቸው እንደ ቡና ፤ ሻይ እና ኮካ ያሉ (የሚያነቃቁ) መጠጦችን መጠጣት ፤ አይምሯችን ሜላቶኒን የተባለውን የእንቅልፍ ሆርሞን የሚለቅበትን ጊዜ እንዲዘገይ ያደርገዋል። ይህም መደበኛውን የእንቅልፍ ስርዓት በአማክኝ እስከ 40 ደቂቃ ድረስ ያዛባል።

• የመተኛት ፍርሃት ሶምኒ ፎቢያ ይባላል።

• አብዛኛው ሰው አልጋ ላይ ከወጣ በኃላ በ7 ደቂቃ ውስጥ እንቅልፍ ይወስደዋል።

• ስራን በወቅቱ የማይሰሩ ሰዎች ለእንቅልፍ ችግር (ኢንሶምኒያ) የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው።

• በተደጋጋሚ በነውጥ (ሁከት) የተሞሉ ህልሞችን ማየት፤ እንደ ፓርኪንሰን (የሚያንቀጠቅጥ በሽታ) እና ድሜንሻ (የመርሳት በሽታ) ያሉ የአይምሮ ህመሞች ምልክት ሊሆን ይችላል።

• ህልም እያዩ ህልም መሆኑን መረዳት እና የህልሙን ትዕይንት በተወሰነ መልኩ መቆጣጠር መቻል ሉሲድ ድሪም ይባላል። በተለይ ቪዲዮ ጌም መጫወት የሚያዘወትሩ ሰዎች እንዲህ አይነት ህልሞችን በተደጋጋሚ ያያሉ።

• ከ80 በላይ በሳይንስ የተለዩ የእንቅልፍ ችግሮች አሉ።

• የዓለም ህዝብ ቁጥር አንድ የእንቅልፍ መስተጓጎል ምክንያት ኢንተርኔት ነው።

• ከመተኛታችን ከ2 ሰዓት በፊት ቴሌቭዥን ማየት እንዲሁም ስልክ እና ኮምፒዩተር መጠቀም እንቅልፍ ያስተጓጉላል።

• የሰው ልጅ በአማካኝ የዕድሜውን 6 ዓመት የሚያሳልፈው ህልም በማየት ነው።

• ዳክዬዎች የሚተኙት አንድ አይናቸው ሳይከደን ነው።

• ስሉዝ የተባሉት እንስሳቶች 80 በመቶ የሚሆነውን የዕድሜያቸውን ከፍል የሚያሳልፉት በእንቅልፍ ነው። ዓለም ላይ ቁጥር አንድ እንቅልፋም እና ዘገምተኛ እንስሳቶች ስሉዝዎች ናቸው።

• ከየብስ እንስሳቶች በሙሉ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ያላቸው ዝሆኖች ናቸው። ዝሆኖች በቀን እስከ 2 ሰዓት ብቻ ይተኛሉ።

• በእንቅልፍ ልብ የሚበሩ ወፎች አሉ። በተለይ ስደተኛ ወፎች (ወቅት እየጠበቁ ከሀገር ሀገር የሚጓዙ) አየር ላይ ለአጭር ጊዜ ያሸልባሉ።

በኢዮብ መንግሥቱ
2024/11/15 18:21:56
Back to Top
HTML Embed Code: