Telegram Web Link
#መጀመር
ማንኛውም ነገር ካልጀመርነው ይከብዳል ስንጀምረው ተግዳሮት አለዉ ደጋግመን ስናደርገዉ ቀላል ነዉ።
ሳንጀምር ይከብዳል አንበል እንደሚከብድ በምን አወቅን?
1. እንጀምረው
2. እንቀጥለው
3. እንጨርሰው ።
#ሁሌ ከሁዋላ የሚሰበረው እስክንለምድ ነው!!!
©ሁንዴ

ይህን መልዕክት ለምትወዱአቸው #5 ታታሪ ጓደኞቻችሁ Forward አርጉልኝ !
#Join #Share
@psychoet
@psychoet
@psychoet
እንኳን ደስ አለን!
የ11 ዙር የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሊጀምር ነው!

ስለ ሳይኮሎጂ ለማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች።

📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖ለሕይወታችን ምን ይፈይደል?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
📖Counseling ምንድነው?
🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
🔖የ2015 ስኬታማ ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን


ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን ቅዳሜ ፣እሑድ በጠዋት ፣ በከሰአትና በማታ ፈረቃ እንዲሁም እሮብ ማታ መከታተል ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡
www.tg-me.com/psychoet

አድራሻ:-4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221

ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
One week left

Register now!
0912664084
#የስሜት_ብልሃትና_ተግባቦት
#Emotional_Intelligence& Communication
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE

ጥሩ የስሜት ብልሀት ያላቸው ሰዎች የተመሰገኑ ፣ በማንኛውም ሁኔታ የተረጋጉ ፣ የሩጫ ህይወት የማይመሩ ፣ የበለጠ ደስተኛና ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን የሚመሩ ናቸው ፡፡

በህይወታቸው በጣም ደስተኛና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ያለቸው የስሜት ብልሃት ( Emotional Intelligence ) ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሙያውና ችሎታው እያላቸው በባህሪ ምክንያት ይሰናበታሉ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሀሳብ እያላቸው ባላቸው ባህሪና በተግባቦት እጥረት ምክኒያት ሰሚ ያጡ ፣ ተቀባይነት ያጡ ሰዎች ብዙ ናቸው ፡፡

#ለዛሬ እነዚህ የተግባቦትና የስሜት ብልሃት አለመኖር በሕይወታችን የሚያመጡትን ችግር እንመልከት ፡፡

እኔ አንዱን ድግሪዬን በማኔጅመንት ስሰራ የመመረቂያ ጽሑፌ (Competency development in business areas ) የሚል ነበር ፡፡ በዚህ ጥናት ያገኘሁት አንዱ ግኝት ሰዎች ለቢዝነሳቸው መውደቅና አለማደቅ አንዱና ዋና ምክንያት ያላቸው አነስተኛ #የተግባቦትና #የስሜት_ብልሃት ነው ፡፡

#የስሜት_ብልሃትና_ጥሩ_ተግባቦት_የሌላቸው_ሰዎች_መገለጫዎች

★የራሳቸውን ስሜት አይቆጣጠሩም ( በቀላሉ ይናደዳሉ ፣ ይበሳጫሉ ፣ ከልክ ያለፈ ቁጣ ይታይባቸዋል )

★ከሰው ጋር ተግባቢ አይደሉም ፣ ፍርሀት ጭንቀት ይታይባቸዋል ፣ ስለ ራሳቸው አሉታዊ አመለካከት የላቸውም

★በትንሽ ነገር አብዝተው ያዝናሉ

★በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እና ስሜት ስለማይረዱ ፣ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር በሀሳብ ፣ በወሬ የመጋጨት ሁኔታ ይታይባቸዋል

★ሰው ስለነሱ ስላለው አስተሳሰብ አብዝተው ይጨነቃሉ ፣ ይረበሻሉ ፡፡

★ሃሳባቸውን በድፍረት አይገልፁም ፣ እየተጎዱ ከጉዳቱ መውጣት እየቻሉ ዝምታን ይመርጣሉ ፣

★ለውሳኔዎች ከተገቢው በላይ ይቸኩላሉ፣ በወሰኑት ነገር ለመጸጸት ደግሞ የመጀመሪያ ናቸው

ከላይ የዘረዘርኳቸው መገለጫዎች( የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት ክህሎት አለመኖር) የሚያመጣቸው ጉዳቶችና የባህሪ መገለጫዎች ናቸው ።

በእርግጥ ተግባቦትም ሆነ የስሜት ብልህነት ሳይንሳዊ የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ማሳደግ ይቻላል ፡፡ ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ችግሮች በራሳችሁ ላይ የምታዩ ሰዎች ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ በጥቂት ጊዜ ጥሩ የሆነ ተደጋጋሚ ተግባራዊ ልምምዶችን በማረግ መዉጣት ይቻላል ፡፡
___
#በዚህ ሳምንት መጨረሻ /ቅዳሜ መስከረም 21 እና እሑድ መስከረም 22 በሚጀምረው የሕይወት ክህሎት ስልጠና ላይ እነዚህን ጉዳዮች በስፋት የማነሳቸው ሲሆን በተጨማሪም በየቀኑ የሚሰሩ እነዚህን ክህሎት የሚያሳድጉ ልምምዶችን በተግባር እናያለን፡፡ ለመለወጥ የወሰናችሁ ሰዎች ካሉን ፈረቃዎች በተመቻችሁ መርጣችሁ +251912664084 በመደወል ተመዝገቡ የስልጠናው ሙሉ ማስታወቂያ ከዚህ በፊት ተለጥፏል ፡፡ የ 6 ሳምንት ስልጠናችንን ያልተመዘገባችሁ ባለን ጥቂት ቀሪ ቦታዎች ተመዝግባችሁ እንድትጀምሩ እናበረታታለን፡፡

ይህ ፅሁፍ ለሌሎችም እንዲደርስና ስልጠናው የሚያስፈልጋቸው እንዲያገኙት ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

@PSYCHOET
ብዙ ሰዎች ህመማቸውን መከፋታቸውን የሚያወሩለት ወዳጅ አጥተው ሶሻል ሚዲያ ላይ ነው ሚገልፁት። እንዲህ አይነት ፖስቶችና መልእክቶች ስታዩ ረጋ ብላችሁ ምላሽ ስጡ። ቀልድ ነው ብላችሁ በምታላግጡበት ሰአት ያ ሰው ወደሞት እየቀረበ ይሆናል።

በተለይ በአፍላው እድሜ በሚገኙ ወጣቶች ዘንድ ራስን ማጥፋት በጣም እየጨመረ ነው።

እባካችሁ ራሴን ላጠፋ ነው ወይም መሮኛል ብሎ ለፖሰተ ሰው ብታቁትም ባታውቁትም አብሮነታችሁን ድጋፋችሁን አሳዩ እንጂ ቀልድ አትቀልዱ። ለቀልድና ጨዋታ ብዙ የተሻለ ቦታ አለ።

በቅርብ የምናቃቸው ሰዎች መሞታቸው ሲገለፅ የአብዛኛው ጓደኞቻቸው ምላሽ "እኔ መች ጠረጠርኩ... ደብሮኛል እያለኝ.. " ምናምንም በሚሉ ፀፀቶች የተሞላ ነው።

በዙርያችሁ ላለ ሠው ሁሉ ትኩረት ስጡ!

ራስን ማጥፋት የቀልድ ርእስ አይደለም!
©Tesfa G Neda

--------------------------------------------------------------
በዓመት እስከ 800,000 ሰዎች ራሳቸውን እንደሚያጠፉ የWHO ሪፖርት ያመለክታል፡ ከዚህ ቁጥር በላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ራሳቸውን የማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ ።
እድሜያቸው ከ 15 እስከ 29 ዓመት በሆኑ ወጣቶች ሁለተኛው ከፍተኛ ሞት የሚመዘገብበት ችግር ነው ፡ እንዲሁም 79% ያህሉ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ላይ የሚስተዋል ነው ። ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት መርዝ መጠጣት መታነቅ ፣የጦር መሳሪያ መጠቀም፣ በዋናነት ይጠቀማሉ ።

አጋላጭ ሁኔታዎች
-----------------------------------------------------------------
የተለያዩ የአዕምሮ ህመሞች በተለይም ድባቴ (Depression) ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ ችግር ፣ከባድ አካላዊ ህመም ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ፣ ጭንቀት፣ ድንገተኛ ግጭትና ብቸኝነት ዋና ዋና በአጋላጭ ችግሮች ናቸው ። እንዲሁም ቀደም ባለ ጊዜ ያልተሳካ ራስን የማጥፋት ሙከራ ከነበረ ዋነኛ አጋላጭ ችግር ሊፈጥር ሊሆን ይችላል ።

መከላከያ መንገዶች
-----------------------------------------------------------------
ራስን የማጥፋት ችግር በሚገባ መከላከል ይቻላል
በተለይም ራስን ለማጥፋት የሚረዱ ምቹ ሁኔታዎችን መቀነስ፣ ተደጋጋሚ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን በመገናኛ ብዙሃን በመስጠት፣ ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ ማዕከል በማደራጀት ለመምህራን ለወላጆች እንዲሁም ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ በቂ የቅድመ ጥንቃቄ መረጃና ትምህርት መስጠት እንዲሁም ለተማሪዎች የማማከር አገልግሎት ማመቻቸት፣ የአልኮል መጠጥ አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ የአእምሮ ህመሞችን ቶሎ መለየትና በቂ ህክምና ማድረግ እንዲሁም ተገቢውን ክትትል ማድረግ፣በቂ የሱስ ማገገሚያ ማዕከላትን ማቋቋም።
================================
ማጣቀሻ ፡- WHO report
©ዮሴፍ ሳህለ

ባላችሁበት የቴሌግራም ግሩፖች #share አድርጉ @psychoet
የ11 ዙር የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዚህ ሳምንት ይጀምራል፡፡ በቀረን ቦታ ይመዝገቡ፡፡

ስለ ሳይኮሎጂ ለማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች።

📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖ለሕይወታችን ምን ይፈይደል?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
📖Counseling ምንድነው?
🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
🔖የ2015 ስኬታማ ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን


ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን ቅዳሜ ፣እሑድ በጠዋት ፣ በከሰአትና በማታ ፈረቃ እንዲሁም እሮብ ማታ መከታተል ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡
www.tg-me.com/psychoet

አድራሻ:-4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221

ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
የአለም የአእምሮ ጤና ቀን
መስከረም 30፣ 2015

የአእምሮ ጤንነትን የሚጠብቁና የሚያሳድጉ 5 ተግባራት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ)

የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡  ሰው እንደ ሰው ፣  ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በተለይም አሁን ያለንበት ጊዜ ደግሞ ይህ የአእምሮ ጤንነት በመንግስትም ሆነ በዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ከተለያዩ የሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡

አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር

አዳዲስ ክህሎቶችን መማር

ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ

ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት

አወንታዊ ነገሮችን ማሰብ

ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

ጽሑፉ ለናንተ ከጠቀማችሁ ሎችም እንዲጠቀሙበት #Share በማድረግ አካፍሉ! ማካፈል ከዚህ ይጀምራል፡፡
www.tg-me.com/psychoet
#መልካም_የጥቅምት_ወር_ይኹንላችሁ!

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በኹሉም አካባቢዎች ሰላምን የምንሰማበት ፣ ፍትህን የምናይበት ይሁንልን ፡፡

ከእረፍት በኀላ ተመልሰናል። ቆሞ የነበረው የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት የማሕበራዊ ሚዲያ ትምህርታችን ከዛሬ ጀምሮ በዐዲስ መልክ ይቀጥላል ፡፡

ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ።
Telegram : www.tg-me.com/psychoet
Facebook : fb.com/psychologyabc

መልዕክቱን #Share #Like በማረግ ለሌሎችም እናጋራ
ውሸት አሁን አሁን በማህበረሰባችን ዘንድ ኖርማል እየሆነ የሄደ መጥፎና ጎጂ ልማድ ነው፡፡ ስለ ውሸት ምን ታስባላችሁ?
👉ጠቃሚ ምክሮች👈

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

#መልካም_ቀን !
#Share #Like
@Psychoet
#ማስታወቂያ
የ11 ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠና ጀምሯል!

የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች እየተሰጠ ነው።

🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
🔖የ2015 ስኬታማ ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን
📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖ለሕይወታችን ምን ይፈይደል?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?

ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን
👉ቅዳሜ ከሰአት 8-11
ወይም
👉እሑድ ጠዋት 3-6
በመረጡት ፈረቃ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ለመመዝገብ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
t.m/psychoet

የስልጠና አድራሻ:-4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221

ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «#ማስታወቂያ የ11 ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠና ጀምሯል! የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች እየተሰጠ ነው። 🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት 🔖የ2015 ስኬታማ ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም 🔖የስሜት ብልህነት 🔖ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት 🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን 📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው? 📖ለሕይወታችን…»
ወዳጆቼ ኾይ፣ ከጠቀማችሁ ትንሽ ነገር ልበላችሁ

ኹላችንንም ወደዚህች ምድር የላከን ፈጣሪ ነው፡፡ አንዳችንም ወደን ፈቅደንና አስበንበት የመጣን የለንም፡፡ ታዲያ ለምን ይኾን ፈጣሪ ወደዚህች ምድር የላከን? በቃ በልተን ጠጥተን፣ ተምረን ሰርተን ፣ አግብተን ወልደን እንድንሞት ብቻ ነው? ወይስ ሌላ ምክኒያት ኖሮት ይኾን? ቆይ የሕይወት ሩጫችን የት ለመድረስ ነው? ከደረስንስ በኀላ?  የሕይወትስ ትልቁ ነገር ምንድነው?
#ራሳችንን_እንጠይቅ
@psychoet
📕መሸበርና መፍራት የነገን ችግር አያስወግድልንም ይልቁኑስ የዛሬን ደስታ ያሳጣናል።

📘ሕይወት፣ የመዘጋጃና የመኖሪያ ዕድሜ የሌላት፣ ከአፈር ለተሠራ ሰው የተሰጠች ስጦታ ነች ፡፡ የሰው ልጅም ከተፈጠረ ጀምሮ ሕይወትን በውስጡ ለማሰንበት በትግል የሚኖር፣ሲያጣትም እጅግ ጠሊቅ ሐዘን ውስጥ የሚገባ ፍጡር ነው፡፡

📗ሰዉ የራሱንና የሚወዳቸውን እስትንፋስ ለማቈየት፣ ከሰከንድ እስከ ሰዓታት ከዛሬው እየተበደረ ለማያውቀው ነገ ሲገብር፣ ለማያውቀው ነገ ደስታ ዛሬ ሲያለቅስ፣ ለማያውቀው ነገ ጥጋብ ዛሬ ሲራብ ሲታረዝ፣ ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር ነው…፡፡

📒በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡

📘 ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

📖ሜሎሪና መፅሀፍ የተወሰደ
📕📔📗📕📗📔📕📗📔📕📗
በውሳኔ መጽናት መቻል

አንድ ሰው ያለመው ቦታ እንዳይደርስ የሚያቆመው በውሳኔ መጽናት አለመቻል ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ብዙ ምክንያቶች አሉ ለምሳሌ ያህል፡

📌 የወሰንንበት ጉዳይ ያልገባን ከሆነ
📌 ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ
📌 በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ውሳኔያችንን የሚሸረሽሩ ነገሮች ደጋግመው ሲነግሩን ወዘተ ናቸው፡፡

ታዲያ ምን እናድርግ? መፍትሄ፡

🔑 ሁሌም በራሳችን እርግጠኛ መሆን መቻል
🔑 ከመወሰናችን በፊት ደጋግመን ማሰብ፣ አማራጮችን መመልከት
🔑 ምን ለውጦችንና ጥቅሞችን ልናገኝ እንደምንችል ማሰብ
🔑 ልክ እንደ ወሰንን ወደ ድርጊት መግባት፣ ጊዜ አለመውሰድ

©ተመስገን አብይ
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
መልዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ #Share ያድርጉት

(Sicial Rules ተብለው የተዘረዘሩ የማኅበራዊ ሕይወት ሕግጋትን ስመለከት ለኛስ አትጠቅምም ወይ ብዬ ነው ወዲህ ማምጣቴ)
==================
1. ይሰለቹሃል
አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' ነው
የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም
"... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል
አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው
ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።
============

6. አታቋርጥ
ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ
ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመሥግን
ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።
9. ያለስስት አድንቅ
ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ
ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።
===================

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ
ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ ስርዓት
ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም
ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ
ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ
ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።
==========================

16. ተቆጠብ
ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ
ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት
በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት
በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ
የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ
የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!

ሳይኮሎጂ ፔጅን #Like በማድረግ ቤተሰብ ኹኑ

@psychoet
©Abraham Tsehaye
……… በጣም ገራሚ ታሪክ

😍 ትንሿ ቆንጅዬ ልጅ ሁለት አፕል እንደያዘች እናቷ መጣች ።
እናትም " የኔ ጣፋጭ አንዱን ለኔ ለእናትሽ ትሰጪኛለሽ ?" ስትል በትህትና ትጠይቃታለች ።
ልጅም ትኩር ብላ ከተመለከተቻት በኋላ አንዱን አፕል ግምጥ አደረገችው ። ቀጠለችና ሁለተኛውንም ደገመችው 😳 እናት በልጇ ሁኔታ ደንግጣ ፍዝዝ ብላ ቀረች ።
ስሜቷን በቁጣ ልታሳያት ብትሞክርም ድንጋጤው ከለከላት ☺️እንዴት በእኔ በእናቷ ትጨክናለች …? ብላ አሰበች ።

በዚህ መሀከል ልጅ የገመጠችውን አንዱን ለእናቷ እያቀበለቻት "እንኪ ማሚ ይበልጥ የሚጣፍጠው ይሄኛው ነው ።" አለቻት ። እናት ያልጠበቀችውን ክስተት በማየቷ ልጇን አቅፋ ተንሰቅስቃ አለቀሰች 😍

መልካም አዳር 💕

@psychiet
2024/09/27 21:31:52
Back to Top
HTML Embed Code: