ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷♂
እንደምን አላችሁ፣ በጣም የምትጠሉትን የሰው ባህሪ Comment ላይ ጻፉልን? ብዙ ሰው የጻፈው ባህሪ ላይ ሥነልቦናዊ ማብራሪያ እናቀርባለን፡፡
ከተሰጡት ከ 50 በላይ የኾኑ አስተያየቶች በብዙ ቤተሰቦች የተመረጡት 3 የሚጠሉ ባህሪዎች እነዚህ ናቸው፡፡
በነዚህ ርዕሶች በዚህና በቀጣዩ ሳምንት የተወሰነ ሥነልቦናዊ ማብራሪያ እናቀርባለን
1. የሚዋሽ (ውሸት)
2. የሚያስመስልና የሚለዋወጥ (ማስመሰልና መቀያየር)
3.ሰዎችን የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያረግ
@Psychoet

#ውሸት
#ክፍል_1
ለምን እንዋሻለን ???
በግል የምንዋሸው እንዳለ ኾኖ አሁን አሁን በትልልቅ ሚዲያዎች ሳይቀር ቀርቦ ውሸት መናገር እየተለመደ የመጣ መጥፎ ተግባር ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ውሸትን ለብዙ ነገራቸው አየተጠቀሙት ልምድ አርገውታል፡፡ ግን
ውሸት ምንድነው?
ባለሙያዎች ውሸትንና ውሸታሞችን እንዴት ያዮቸዋል? ከታች የቀረበው ጽሑፍ ብዙ ነገሮችን ያስዳስሰናል፡፡
ውሸትን የተለያዩ ምሁራን ትርጓሜና እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል በዚህም ነጋሪውን ለመጥቀም የታሰበ ሐሰታዊ የሆነ ግንኙነት የሚለው መጀመሪያው ሲሆን ይህም ብዙ ውዝግቦችን አስነስቶ ነበር፡፡ ምክንያቱም ነጋሪውን ብቻ ለመጥቀም ውሸት አይነገርም የሚሉ፣ ውሸት ሆን ተብሎ የሚደረግ እውነትን የመደበቅ ስራ ነው ብለው መልስ የሰጡ ብዙ ወገኖች ነበሩ፡፡ በሁለተኛው የውሸት ማብራሪያ ወይም ፍቺ መሰረትም ሰዎች ሳያውቁት የተሳሳተ መረጃ ከተናገሩ እንደ ውሸት አይቆጠርም ማለት ነው፡፡ በርገን እና ቡለር የተባሉ ሁለት ምሁራን ደግሞ ውሸት ማለት መልዕክት ላኪው ለመልዕክት (መረጃ) ተቀባዩ ሆን ብሎ የተሳሳተ መረጃ በማቀበል መልዕክት ተቀባዩን መጉዳት ነው ይሉናል፡፡ እኛ ደግሞ የእራሳችን የሆነ የውሸት ትርጉም ወይም ፍቺ ይኖረናል፡፡
ውሸት ብዙ ጊዜ በቃላት ብቻ የሚገለጽ አይደለም በድርጊትም ጭምር እንጂ ለምሳሌ ያልተጎዳ አትሌት እግሩን እንደተጎዳ አድርጎ እያነከሰ ከውድድር ወይም ከስልጠና ካቋረጠ ዋሽቷል ማለት ነው፡፡ መረጃን ሆን ብሎ መደበቅ ለምሳሌ የገቢን መጠን በመደበቅ ግብርን ለመቀነስ የሚደረግ ጥረትም ውሸት ነው፡፡ እኛ ሰዎች ውሸትን ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእራሳችንም እንዋሻለን ለአብነትም ማሳካት የፈለግነውን ነገር በራሳችን በሆነ ምክንያት ካላሳካን ችግሩን በውጪ ኣካል በማሳበብ (Externalize) ለራሳችን ውሸት እንነግራለን፡፡ እንደ ዲፓውሎ እና ሌሎችም ምሁራን መሰረት ሶስት የውሸት ዓይነቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው outright lie (falsification) ሲሆን በግርድፉ አማርኛ ፍጹም ውሸት የሚባለው ነው ይህም ውሸት ተናጋሪዎች ከእውነታው ፍጹም ተቃራኒ የሆነ መረጃን ወይም መልዕክት ይናገራሉ ወይም ያስተላልፋሉ፡፡ ሁለተኛው Exaggeration ወይም ማጋነን ሲሆን በዚህም ውሸት ተናጋሪዎች እውነታውን በማጋነን ያቀርባሉ ለምሳሌ ቀጠሮ ላይ አርፎዶ የሚመጣ ተቀጣሪ የመንገዱን መዘጋጋት ከዕውነታው በተጋነነ መልኩ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ሶስተኛው የውሸት ዓይነት subtle lie ሲሆን በዚህም የሚነገረው የውሸት ዓይነት ጥቂት ሆኖ ከብዙ እውነታዎች ጋር በማቅረብ ሰዎችን ለማማሳት የምንጠቀምበት ነው፡፡
ለምን እንዋሻለን ?
ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡– ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡
ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡
ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-
ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡
ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡
ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡
ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡
ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡
ቀጣዩ ክፍል ነገ ይቀጥላል ...... ያላችሁን ጥናቄና አስተያየት በ Comment አሳውቁን
©በቁምላቸው ደርሶ

#ክፍል_2
ውሸታም ሰዎችን እንዴት እናውቃለን?
ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን የሚለካ እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
#ስሜታዊነትን (emotional state)፣
#የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity) እና
#ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡
የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ያደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡
ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ………..
©(በቁምላቸው ደርሶ)

እንኳን ደስ አለን!
ሲጠበቅ የነበረው የክረምት የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሊጀምር ነው!
ስለ ሳይኮሎጂ ለማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ በተጋባዥ የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎችና ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች።
📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
📖ለሕይወታችን ምን ይፈይደል?
📖የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
📖Counseling ምንድነው?
🔖ችግር አፈታትና ውሳኔ አሰጣጥ
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖የሕይወት አላማ መረዳት
🔖በራስ መተማመን እና ሌሎችም
ለሰልጣኞቻችን የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!
ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን ቅዳሜና እሑድ አልያም ከሰኞ እሮብ አርብ በጠዋት ፣ በከሰአትና በማታ ፈረቃ መከታተል ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡
www.tg-me.com/psychoet

‹‹ትልቁ የጦርነት ሥፍራ አእምሮ ነው፤ ትልቁ ድል ደሞ ራስን ማሸነፍ ነው››
በሕይወታችሁ አሁን ምን ላይ ናችሁ? ወደፊትስ የት መድረስና ምን ማድረግ ትፈልጋላችሁ? የምትፈልጉት ቦታ እንዳትደርሱ ምን ያዛችሁ?
በሕይወታችን ትልቅ ጦርነት የምናደርገው ከራሳችን ጋር ነው ፣ እያንዳንዱ ውሳኔዎቻችን ከራሳችን ጋር በሚደረግ ትግልና ትንቅንቅ የሚወሰኑ ናቸው ፡፡ ትልቁ ጠላታችንም አስተሳሰባችን ፣ ልማዳችን ፣ ምከላችን ነው ፡፡ ኹሉም ግጭት ደግሞ አእምሮአችን ውስጥ ከራሳችን ጋር ይካሄዳል ፡፡
ራሳችንን ካሸነፍን በምንም አንሸነፍም፡፡ ትልቁ ጠላታችን የኛ ሌላኛው ማንነታችን ነው፡፡
ከተስማማችሁ #ላይክና #ሼር በማድረግ ለሌሎችም እናድርስ
የሕይወትና የአስተሳሰብ ለውጥ ላይ የሚያተኩረው ስልጠናችን ላይ ለመመዝገብ 0912664084 ይደውሉ፡፡

ስለ ዝምተኛ ሰዎች እውነታዎች /FACTS ABOUT QUIET PEOPLE
1. ዝም ያሉ ሰዎች በልባቸው ውስጥ ብዙ ያወራሉ፣ አንዳንዴ ብቻቸውን ያወራሉ።
(Quiet people talk a lot inside of their heart, sometimes they talk alone.)
2. አንዴ ካንተ ጋር ከተግባቡና ከተመቻቹህ በኋላ ግን እብዶች ይሆናሉ።
(Once they get comfortable with you they get crazy and wild.)
3. በሃሳብ እና በልብ ይናገራሉ።
( They speak in thoughts and heart.)
4. ዓይን አፋር ናቸው, የአይን ግንኙነትን ብዙ መጠበቅ አይችሉም.
( They are shy, they can't maintain eye contact a lot.)
5. በጣም ብዙ ንዴት አለባቸው አታናድዱአቸዉ። እና ቁጣቸውን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ ያውቃሉ.
( They have too much anger don't get them pissed off. And they know how to micromanage their anger issues.)
6. ጠንካራ እና በጣም ብልህ ናቸው.
(They are strong and very intelligent.)
7. በማህበራዊ ሚዲያ (አንዳንድ ጊዜ) በጣም ብርቱ ናቸው. ይፖስታሉ፣ ይፅፋሉ፣ ያደንቃሉ አስፈላጊ መስሎ ከታያቸውም ይተቻሉ
(They are very crazy on social media (sometimes))
8. በጣም አሪፍ ስብዕና አላቸው እና ከነርሱ ጋር አብረው መሆንም አስደሳች ነው።
(They have very cool personalities and are fun to be with.)
9. አእምሯቸው ሁል ጊዜ ያሰላል, ከመጠን በላይ ያስባሉ. መጥፎ ነገሮች እና ጥሩ ነገሮች. እንደዛ ነው የታዘብኩት። ( Their minds are always calculating, they are overthinking too much. Bad things and good things. That's how I have noticed. )
10. እነሱ ታማኝ ናቸው እና በግንኙነቶች ውስጥ በጣም ይወዳሉ. እንደዚህ ያሉ ሰዎች በግንኙነት ውስጥ ሲሆኑ በሙሉ ልባቸው ሠዉን ይወዳሉ። ጥልቅ ፍቅርም አሏቸው . እነሱ ካልወደዱህ ግን ፍቅራቸው በጣም ጠንካራ ስለሆነ ሙሉ ለሙሉ ይተውሃል።
(They are loyal and love the most in relationships. When quite people they are in a relationship they love you wholeheartedly. They love deep. But if they don't love you, they leave you completely due to their love is very strong. )
11. በውስጥ ስሜታቸው ቢጎዳና Sensitive ቢሆኑም እንኳን፤ሕመማቸውን ፈጽሞ አያሳዩም,
(They never show their pain, and they are emotional people. )
12. አንዳንዶቹ የተጨነቁ እና ብቸኛ ናቸው, ነገር ግን ምንም እንዳልሆኑ አስመስለው, በጥልቅ ብቻቸውን መሆን ይሰማቸዋል, ስሜታቸዉን ለመግለፅ አይደፍሩም ስለዚህም ድብቅ ሰዎች ናቸው.
(Some of them are depressed and alone but they pretend, deep down they feel like to be alone, they are introvert people. )
13. በጣም ቆንጆ ፈገግታ እና ያልተለመደ ሳቅ አላቸው ። (They've got the cutest smile and weirdest laughter. )
14. አብዛኞቻቸው እውነትን ይወዳሉ። እነርሱም ሐቀኞች ናቸው።
(Most of them they like facts, and they are honest. )
15. ጸጥ ያሉ ሰዎች ሚስጥራዊ ሊሆኑ ይችላሉ, እንዲሁም ብዙ ነገሮችን ይደብቃሉ, ነገር ግን ምቾት እንዲሰማቸው ወይም እንዳይረበሹ ማድረግ ከፈለጉ ያለ ምንም ፍርሃት እውነቱን ይናገራሉ.
(Quiet people are likely to be secretive, also they hidecholy they will tell the truth as it is without any fear. )
16. ጸጥ ያሉ ሰዎች ብቻቸውን በሚሆኑበት ጊዜ በእውነት ደስተኛ ይሆናሉ። በሚወዱት ነገር እስከተጠመዱ ድረስ። ችግር የለም.
(Quiet people are introverts they are actually happy when they are alone. As long as they are busy with what they love. It's okay. )
17. ጸጥ ያሉ ሰዎች, እና ውስጣዊ ሰዎች በአእምሮአቸው ውስጥ የራሳቸውን ትዕይንቶች ፈጥረው ያምናሉ.
( Quiet people, and introvert people create their own scenes in their mind and believe them. )
18. ዝምተኛ ሰዎች,ማንበብ ይወዳሉ። የሚወዷቸው መጽሃፍትን በተለይም ልብ ወለድ እና ልብ ወለድ ያልሆኑ መጽሃፎችን ነዉ። አንዳንድ ጊዜ አነቃቂ መጽሐፍት (የራስ አገዝ መጽሐፍትንም ማንበብ ያስደስታቸዋል ።
( Quiet people, and introverted people they love to read. Reading books, especially novels both fiction and nonfiction books. Sometimes inspirational books (self help books).)
👉ዝምተኛ ሠዎችና የዚህ ፔጅ አምድ ተከታዮችና አንባቢዎች ይህ ሙያዊ ትንታኔ ምን ያህል ስለእናንተ ወይም ስለምታውቋቸዉ ዝምተኛ ሰዎች ባህሪ እንደገለፀ ትዝብታችሁን Comment በማድረግ አጋሩን።
©#Inspirational #stories & #life #hacks
አነቃቂ ታሪኮችና የሕይወት ዘዴዎች
@Psychoet
የሕይወትና የአስተሳሰብ ለውጥ ላይ የሚያተኩረው ስልጠናችን ላይ ለመመዝገብ 0912664084 ይደውሉ፡፡ ቅዳሜ ሀምሌ 16 ይጀምራል፡፡ የበዛ ዝምታችሁን በስልጠናችን ማሸነፍ የምትፈልጉ መልካም ዕድል ነው፡፡

ማኅበራዊ ፍርሃት ማስወገድ
ይህን ጠቃሚ ትምህርት #Share እናድርገው
✍ማኅበራዊ ፍርሃት #ብዙ_ሰው_በተሰበሰበበት ቦታ ለመናገር ወይም አንድን ድርጊት ለመፈጸም በተዳጋጋሚ የሚፈጠር በብዙ ግለሰቦች ላይ የሚስተዋል #ምክኒያታዊ_ያልሆነ_ፍርሃት ነው፡፡ ይህ #የጭንቀት ዓይነት ያለባቸው ግለሰቦች ብዙ ጊዜ ንግግር ያለበት ተግባር አጥብቀው #ይሸሻሉ ምክኒያቱም አይደለም ንግግር አድርገው ገና ለማድረግ ሲያስቡ የሚሰማቸው #የፍርሃት ወይም #የጭንቀት_ስሜት ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ፡፡ ከህጻናት በስተቀር ማኅበራዊ ፍርሃት ያለባቸው ሰዎች ፍርሃታቸው ምክኒያታዊ እንዳልሆነ ይረዳሉ ምንም እንኳን ይህ ከፈርሃታቸው ባይታደጋቸውም፡፡
★እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ላይ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ምልክቶች ናቸው፡-
1.ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ አጥብቆ መፍራትና በትምህርት ገበታም ሆነ በስራ ቦታ የተዘጋጁትን በአግባቡ ማቅረብ አለመቻል
2.እንደ ካፌ፣ ሬስቶራንት፣ ቤተ-መጻሕፍትና ሌሌች ብዙ ሰዎች ባሉበት ቦታ ሰዎች እኔን እየተመለከቱኝ ነው ብሎ መሳቀቅ ፣ ከልክ በላይ አንገት አቀርቅሮ መጓዝ
3.ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ በሚያስቡበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ይተቹኛል ብሎ ማሰብ
4.ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ሲያደርጉ በላብ በጠመቅ ወይም ልዋረድ እችላለሁ ብሎ በፍርሃት ማሰብ
5.ብዙ ሰው ባለበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ የሆነ ያልሆነ ምክኒያት በመደርደር እራስን ማቀብ
6.አዲስ ሰው ጋር ለመገናኘት ተደጋጋሞ የሚከሰት ፍርሃት
7.ብዙ ሰው ባለበት ቦታ ምግብ በሚመገቡት ጊዜ ትንታ ወይም መታነቅ እንዲሁም ምግቡ ሊዝረከርክብኝ ይችላል ብሎ መፍራት
8.ከእነዚህ ጋር ተዛምዶ የሚከሰት እንደ የልብ ምት መጨመር፣ ላብ ላብ ማለት፣ የሰውነት መንቀጥቀጥና የመሳሰሉት ፍርሃት ወለድ አካላዊ ለውጦች ናቸው፡፡
፠፠፠ መፍትሄ ፠፠፠
1.የአስተሳሰብ ለውጥ፡-
ብዙ ጊዜ ማኅበራዊ ፍርሃት እንዲከሰት የሚያደርጉ ከበስተጀርባ ያሉ አሉታዊ አመለካከቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ለራስ የሚሰጥ ዝቅተኛ ግምት አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ለዚህ ፍርሃት መከሰት አስተዋጽኦ የሚያበረከቱ ምክኒያታዊ ያልሆኑ አሉታዊ አስተሳሰቦችን ነቅሶ በመለየትና በአዎንታዊ አመለካከት መተካት፡፡
2.መለማመድ፡-
ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ መናገር ስለሚያስፈራን ንግግር የምንሸሽ ከሆነ የፍርሃቱ መጠን እንዲጨምር መፍቀድ ነው፡፡ ከሸሻችሁት በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው መቼም ቢሆን ከዚህ ችግር እንደማትገላገሉ ነው፡፡ ስለዚህ እራስን ቀስ በቀስ ማለማመድ ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡
3.ስራ ላይ ማተኮር፡-
ብዙ ጊዜ የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ከሚሰሩት ስራ ይልቅ ሌሎች ሰዎች ስለሚሰጧቸው አስተያየትና ምላሽ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ እዚህ ላይ መታሰብ ያለበት ከስራው ይልቅ አድማጭ ተመልካች ላይ የምናተኩር ከሆነ መጀመሪያ በተገቢው ስራን መስራት እንችልም ምክኒያቱም ቀልባችን ሌሌች ሰዎች ላይ ነውና፡፡ ሲቀጥ ልሌሎች ሰዎች ላይ ስናተኩር የበለጠ ስለፍርሃት ስሜታችን ላይ እንድናተኩርና የበለጠ አሉታዊ ሃሳቦች እንዲፈጠሩ ይገፋፋል፡፡
4.ጡንቻን ማዝናናት መለማመድ፡-
ከውስጥ ከሆድ መተንፈስ በመለማመድ ጭንቀቱ የሚፈጥረውን የረብሻ ስሜት መቀነስ፡፡ ይህ በጣም ቀላልና የትም ቦታ ሊለማመዱት የሚችሉት ዘዴ ነው፡፡ ለተወሰነ ደቂቃ (እስከ 10 ሴኮንድ) ወደ ውስጥ በመተንፈስ ትንፋሽህን መያዝ ከዚያም መልቀቅ፡፡ እንደገና ወደ ውስጥ ትንፋሽን በመያዝ አሁንም ወደ ውጪ መተንፈስ፡፡በተደጋጋሚ ይህን በማድረግ የጭንቀት ስሜቱን ማቅለል ይቻላል፡፡ ይህን ዘዴ ጭንቀቱ ቀለል እሰከሚልድረስ መከወን ይቻላል፡፡
5.የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና መውስድ፡-
ዓይንን እየተመለከቱ ማውራት፣ ፈገግታ፣ የንግግር ፍሰትን መጠበቅና የመሰሳሰሉት ልምምዶች በንግግርና በሌሎች ማህበራዊ ተግባቦት ላይ ውጤታማነታችንን ሲለሚጨምሩ ለወደፊት የበለጠ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ መናገርና ሌሌች ተግባሮችን ለመፈጸም አወንታዊ ማበረታቻዎች ናቸው፡፡
★★★ከዚህ ጋር በተያያዘ ሥነልቡና ፔጅ የተዘጋጀውን የአንድ ወር ተግባራዊ ልምምድ ስልጠና ብትካፈሉ ብዙ የአመለካከትና የባሕሪ ለውጥ እንደምታመጡ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ ስልጠናው በዚህ ሳምንት ቅዳሜ ይጀምራል ፡፡ 0912664084
# ★★★
6.ሌላው presentation ሲኖርብን ከመስታወት ፊት በመቆም በደንብ መለማመድ ፣ ስናወራ ምን እንደምንመስል ማየትና ራሳችንን እያረምን ደጋግሞ መለማመድ ፡፡ በተጨማሪ ደፋር ሰዎች ራሱ ብንሆን አንዳንድ ያልተዘጋጀናቸውን ነገሮች ስናቀርብ / ባላሰብነው ሁኔታ ውስጥ ስንገኝ ፍርሀት ሊከሰት ስለሚችል ሁልጊዜ ጠንቃቃ መሆን ይጠበቅብናል ደግሞም ከልክ ያለፈ በራስ መተማመንም ማስወገድ መልካም ነው ፡፡
የፍርሃት ስሜት ወይም ጭንቀት የዕለት ተዕለት ህይዎታችን በደስታ እንዳንመራ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ማኅበራዊ ፍርሃትም እንደዚሁ በህይወታችን ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽኖ ይኖራል፡፡ ለችግሩ መፍትሄ ማፈላለግ እንጂ ለምን ይህ ተከሰተብኝ ብሎ እራስን መኮነንና ጥፋተኛ ማድረግ አይገባም ምክኒያቱም ምንጩ እኛ ሳንሆን አስተዳደጋችን ፣ አካባቢያችን ፣ አስተማሪዎቻችን ፣ ሊሆኑ ይችላሉና ፡፡ ስለዚህ በዚህ ፍረሀት ያላችሁ ሰዎች የጠቀስኳቸውን ነገሮች በደንብ ተግባራዊ አድርጉ ፡፡ ጥያቄ ካላችሁ ጻፉልኝ፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ ።
(በአሸናፊ ካሳሁን እና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist

‹‹... የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መጠኑና ስፋቱ ቢለያይም፣ ራሱ በሠራው አሊያም ሌሎች ባጠሩለት እስር ቤት ይኖራል፡፡ እንደ ራሱ አሳብና አመለካከት ግን ትልቅ እስር ቤት የሚኾንበት አንዳች ነገር የለም፡፡ ለካስ እስር ቤት ቦታ ብቻ ሳይኾን አስተሳሰብ ጭምር ነው፡፡...
በዚህች ምድር እጅግ ብዙ ሰው በአእምሮው እስር ቤት ውስጥ በአሉታዊ አስተሳሰብ ታስሮ፣ በከንቱና እንቶ ፈንቶ ፍርሀት ተይዞ ማንም እንዳይረዳው ኾኖ የእስር ቤት ቊልፉን ራሱ ደብቆ ይኖራል፡፡ ››
በአስተሳሰብ ዙሪያ የምንሰጠው ስልጠና ነገ ይጀምራል፡፡ በቀሩን ጥቂት ቦታዎች ለመመዝገብ 0912664084 ይደውሉልን፡፡

#የስሜት_ብልሃትና_ተግባቦት
#Emotional_Intelligence& Communication
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE
ጥሩ የስሜት ብልሀት ያላቸው ሰዎች የተመሰገኑ ፣ በማንኛውም ሁኔታ የተረጋጉ ፣ የሩጫ ህይወት የማይመሩ ፣ የበለጠ ደስተኛና ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን የሚመሩ ናቸው ፡፡
በህይወታቸው በጣም ደስተኛና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ያለቸው የስሜት ብልሃት ( Emotional Intelligence ) ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሙያውና ችሎታው እያላቸው በባህሪ ምክንያት ይሰናበታሉ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሀሳብ እያላቸው ባላቸው ባህሪና በተግባቦት እጥረት ምክኒያት ሰሚ ያጡ ፣ ተቀባይነት ያጡ ሰዎች ብዙ ናቸው ፡፡
#ለዛሬ እነዚህ የተግባቦትና የስሜት ብልሃት አለመኖር በሕይወታችን የሚያመጡትን ችግር እንመልከት ፡፡
እኔ አንዱን ድግሪዬን በማኔጅመንት ስሰራ የመመረቂያ ጽሑፌ (Competency development in business areas ) የሚል ነበር ፡፡ በዚህ ጥናት ያገኘሁት አንዱ ግኝት ሰዎች ለቢዝነሳቸው መውደቅና አለማደቅ አንዱና ዋና ምክንያት ያላቸው አነስተኛ #የተግባቦትና #የስሜት_ብልሃት ነው ፡፡
#የስሜት_ብልሃትና_ጥሩ_ተግባቦት_የሌላቸው_ሰዎች_መገለጫዎች
★የራሳቸውን ስሜት አይቆጣጠሩም ( በቀላሉ ይናደዳሉ ፣ ይበሳጫሉ ፣ ከልክ ያለፈ ቁጣ ይታይባቸዋል )
★ከሰው ጋር ተግባቢ አይደሉም ፣ ፍርሀት ጭንቀት ይታይባቸዋል ፣ ስለ ራሳቸው አሉታዊ አመለካከት የላቸውም
★በትንሽ ነገር አብዝተው ያዝናሉ
★በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እና ስሜት ስለማይረዱ ፣ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር በሀሳብ ፣ በወሬ የመጋጨት ሁኔታ ይታይባቸዋል
★ሰው ስለነሱ ስላለው አስተሳሰብ አብዝተው ይጨነቃሉ ፣ ይረበሻሉ ፡፡
★ሃሳባቸውን በድፍረት አይገልፁም ፣ እየተጎዱ ከጉዳቱ መውጣት እየቻሉ ዝምታን ይመርጣሉ ፣
★ለውሳኔዎች ከተገቢው በላይ ይቸኩላሉ፣ በወሰኑት ነገር ለመጸጸት ደግሞ የመጀመሪያ ናቸው
ከላይ የዘረዘርኳቸው መገለጫዎች( የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት ክህሎት አለመኖር) የሚያመጣቸው ጉዳቶችና የባህሪ መገለጫዎች ናቸው ።
በእርግጥ ተግባቦትም ሆነ የስሜት ብልህነት ሳይንሳዊ የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ማሳደግ ይቻላል ፡፡ ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ችግሮች በራሳችሁ ላይ የምታዩ ሰዎች ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ በጥቂት ጊዜ ጥሩ የሆነ ተደጋጋሚ ተግባራዊ ልምምዶችን በማረግ መዉጣት ይቻላል ፡፡
___
#በዚህ ሳምንት መጨረሻ /ቅዳሜ ሀምሌ 16 እና እሑድ ሀምሌ 17 በሚጀምረው የሕይወት ክህሎት ስልጠና ላይ እነዚህን ጉዳዮች በስፋት የማነሳቸው ሲሆን በተጨማሪም በየቀኑ የሚሰሩ እነዚህን ክህሎት የሚያሳድጉ ልምምዶችን በተግባር እናያለን፡፡ ለመለወጥ የወሰናችሁ ሰዎች ካሉን ፈረቃዎች በተመቻችሁ መርጣችሁ +251912664084 በመደወል ተመዝገቡ የስልጠናው ሙሉ ማስታወቂያ ከዚህ በፊት ተለጥፏል ፡፡ የ 6 ሳምንት ስልጠናችንን ያልተመዘገባችሁ ባለን ጥቂት ቀሪ ቦታዎች ነገ ተመዝግባችሁ እንድትጀምሩ እናበረታታለን፡፡
ይህ ፅሁፍ ለሌሎችም እንዲደርስና ስልጠናው የሚያስፈልጋቸው እንዲያገኙት ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛
@PSYCHOET

ስለ ይሉኝታ እንድጽፍ በጠየቃችሁት መሠረት ...
#ይሉኝታ
እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ይነበብ ለሌሎችም ይሉኝታ ለሚያጠቃቸው ጓደኞቻችሁ አጋሩ።
#ይሉኝታ_ምንድን_ነው?
የሰዎችን ደስታና ሃዘን መካፈል፤ ለሰዎች በችግራቸው ጊዜ ያአቅምን ማድረግ አብዛኞቻችን ያስደስተናል፤ እርካታም ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዴ ሰዎች በይሉኝታ ሲታሰሩና ከፍላጎታቸው እና ከአቅማቸው በላይ ጊዜያቸውን፤ ገንዘባቸውን፤ ሃሳባቸውን ለሌሎች ሰዎች ደስታ ሲያውሉ ይታያል፡፡ ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት፡፡
#የይሉኝታ_መንስኤዎች
✿ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት
✿በራስ መተማመን ማነስ
✿ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ
✿የውስጥ መረጋጋት ከሌለን
✿አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ
✿ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡- በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ
#ይሉኝታ_የሚያጠቃቸው_ሰዎች_መገለጫ_ባህሪያት
❀ከሌሎች ሰዎች ሃሳብ ጋር ሁሌም መስማማት እንዳለብን ሲሰማን
❀ሰዎችን ሊያስደስታቸውና ሊያስከፋቸው ይችላሉ ብለን የምናስባቸው ነገሮች ላይ በብዛት መጨነቅ
❀ሳናምንበትም እንኳ ቢሆን ስለሌሎች ሰዎች መጥፎ ነገር ሲወራ አብሮ ማማት
❀ሰዎች ስለኛ ምን ሊያስቡ እና ምን ሊናገሩ እንደሚችሉ ማሰብና መጨነቅ
❀የሃሰብ ልዩነቶችንና ግጭቶችን ተጋፍጦ በሃሳብ ከመርታት ይልቅ መሸሽ፤ ሃሳቦች ሳይብላሉ ማቋረጥ
❀ሰዎች በውይይት መሃል የተለየ ሃሳብ ሲያነሱ ከሃሳቡ ይልቅ ሰዎች ላይ ማተኮር
❀ሃሳባችን ከማንጸባረቅና ላመንበት ነገር ከመቆም ይልቅ ለቡድን ተጽእኖ እጅ መስጠት
❀ከደንብና መመሪያ መከበር ይልቅ በሰዎች ለመሞገስና ለመከበር ትኩረት መስጠት
❀የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍለንም ሌሎችን ላለመሳከፋትና ላለማበሳጨት መጣር
❀አይሆንም የማለት ድፍረት ማጣት፤ ለሁሉም ነገር እሺን ማስቀደም
➌ #ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች
✿ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት
✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?
✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ
✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ
✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ
✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር
✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር
✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል
©zepsychology

ለ ሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና ምዝገባ ላለፉችሁ በሙሉ
በሶስቱም ፈረቃ ጥቂት ቀሪ ቦታ ስላለን በሚመቻችሁ በአንዱ ቶሎ በመመዝገብ መጀመር ትችላላችሁ፡፡
⏰ሮብ ማታ12:00 - 2:00
⏰ቅዳሜ 3:00 - 6:00
⏰ቅዳሜ 8:00-11:00
ከዚህ ሳምንት በኀላ አዳዲስ ተመዝጋቢ አንቀበልም፡፡
👉ክፍያ :- ( የመመዝገቢያ፣ የሻይ ቡና ሰአት፣ የሰርተፊኬት ፣ የ18 ሰአት የስልጠና ጨምሮ ) - 1000 ብር ነው
👉አድራሻ :- 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ( ከቶታሉ ጀርባ) አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ - 219 እና 221
0912664084 ይደውሉልን

ለፔጁ ቤተሰቦች
www.tg-me.com/psychoet
fb.com/psychologyabc
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ አዳዲስ የሥነልቦና ትምህርቶችን በ FACEBOOK በTELEGRAM እንዲሁም በYouTube እጀምራለሁ ፡፡
ስለዚህ እስካሁን ያነሳኀቸው ነጥቦች ከጠቀማችሁ ወይም ጠቃሚ እንደሆኑ ካመናችሁ ጓደኞቻችሁን ወደዚህ ፔጅ እንድትጋብዙ እጠይቃለሁ ፡፡ ይህንንም መልእክት ደግሞ #Share እንድታረጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ ፡፡
በቅርቡ የምፅፋቸው ውስጥ
*የአሸናፊነት ስነልቡና
*የፍቅርና የጋብቻ ህይወትና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ
*ስለ ሁለንተናዊ የሕይወት ስኬት
*ስለ አዕምሮና አስተሳሰብ ጤንነት ወዘተ ...
መልካም ጊዜ !
ቴሌግራም ቻናሌ ፦ www.tg-me.com/psychoet
ዕውቀት ከአስተሳሰብ ጨለማ ነፃ ያወጣል ፡፡

Photo
የአሸናፊነት ሳይኮሎጂ (ክፍል 1/5)
በናሁሰናይ ፀዳሉ
አሸናፊነት በራሱ ባህሪይ ነው ለዛውም የምንለማመደውና የምናሳድገው ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እንጂ ከተግባር አይደለም ፡፡ በሀሳቡ ፣ በአዕምሮው የተሸነፈ ሰው በተግባር ቢያሸንፍም ውስጣዊ ደስታ እርካታ ድልን አያገኝም ፡፡ አሸናፊነት የሚለመድ የሚታይ ባህሪይ ነው ፡፡
10ሩ የአሸናፊዎች ባህሪ
1. Self Projection
ይህ ማለት ወደፊት ልንሆነው ፣ ልንደርስበት እና ሊኖረን ስለምንፈልገው ነገር ጥርት ያለ እይታ / አመለካከት መኖር ነው ፡፡ የመጨረሻ መዳረሻ ግባችንን አስበን ወደዛ ለመጓዝ የምናረገውን ሂደት በአይነ ሕሊናችን መሳል / መመልከት ነው ፡፡
2.Setting Goals
ይህ ደግሞ በአይነ ሕሊናች የሳልናቸው የመጨረሻ ውጤቶች ጋር ለመድረስ የምናበጀው ግብ ነው ፡፡ የምናዘጋጃቸው ግቦች ተግባራዊ የሚሆኑ ፣ በጊዜ የተወሰኑ ፣ ሊደረስባቸው የሚችሉ ፣ ሊለኩ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡ አለበለዚያ ግቡን ማሳካት አንችልም / እጅጉን ይከብደናል ፡፡
3.Focus positive side
ፍርሀት ጭንቀትንና ውጥረትን ይወልዳል ፡፡ ፍርሀት ደግሞ በአብዛኛው የሚመነጨው ከአሉታዊ አመለካከት ነው ይህ አመለካከት ደግሞ በሕይወታችን አሸናፊዎች እንዳንሆን ይይዘናል ፡፡ ስለዚህ አሸናፊዎች ሁልጊዜም ቀና / አወንታዊ አሳቢዎች ናቸው ፡፡
4.power of self determination
ቆራጥነት ሌላው የአሸናፊነት ሥነልቡና መነሻ ነው ፡፡ ብዙ ሰው ለሚሰራው ስራ ፣ ለሚወዳደረው ውድድር ፣ ለሚያጋጥመው ፍልሚያ ቆራጥ አይደለም ፡፡ የምንሰራውን ስራ የምንሰራው ግድ ስለሆነ ፣ ገንዘብ ለማግኛ ብቻ እንጂ በሕይወታችን ደስታን ለማግኚያ አይደለም ፡፡ ስለዚህ የአሸናፊነት ሥነልቡና ለማዳበር በስራችን ቋራጥና የምናረገውን ነገር ሁሉ ለሌላ ሰው ብለን ሳይሆን ለራሳችን ብለን ማድረግ አለብን ፡፡
5.Self Awareness
በዚህ ምድር አንድም ፍፁም ሰው የለም ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ ፍፁምነት / ሁሉን አዋቂነት ሳይሆን በምንወዳደርበት ነገር ተሽሎ (በልጦ) መገኘት ነው ፡፡ ለዚህ ደግሞ ራስን ማወቅ ( ደካማና ጠንካራ ጎናችንን) ወሳኝነት አለው፡፡
የሚቀጥሉትን 5 ባህሪያት ነገ እንመለከታለን ፡፡
👍 #Like ▶️ #Share በማረግ ሁላችንም ባለንበት ቦታ አሸናፊ እንሁን !
መልካም ቀን!
@psychoet