Telegram Web Link
#እጅግ_በጣም_ስኬታማ_የሆኑ_ሰዎች_7_ልምዶች
በጣም አስተማሪ መልዕክት ነው #SHARE
Telegram @psychoet

ከአስራ አምስት ሚሊዮን ቅጂ በላይ ተሽጧል፤ በሰላሳ ቋንቋዎች ተተርጉሞም ለንባብ በቅቷል፤ በእኛው አማሪኛ ቋንቋም ተተርጉሞ መታተሙንም አውቃለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ “The 7 Habits of Highly Effective people” ይባላል:: “እጅግ በጣም ስኬታማ የሆኑ ሰዎች 7 ልምዶች” ብለን ቃል በቃል እንተርጉመው፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ ይባላል፡፡ ይህ መጽሐፍ በግለሰብ ደረጃ ብልፅግናን (Personal development) ለመፍጠር እንዲረዱ ታስበው እስከ ዛሬ ድረስ ከተጻፉ መጽሐፍት መካከል ወደር የማይገኝለት ነው፡፡ ካላነበባችሁት እንድታነቡት እመክራለሁ፡፡ ያነበብነውም ደግመን ልናነበው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

የዚህ ድንቅ መጽሐፍ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ “ውስጣዊ ድል ከውጫዊ ድል ይበልጣል” ይላል፡፡ እዚህ ምድር ላይ ማግኘት የምንፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ ለማግኘት አስቀድመን ራሳችንን ማሸነፍ፤ የህይወታችን ሾፌር መሆን፤ ውስጣዊ ማንነታችንን መቆጣጠር ወዘተ አለብን ማለት ነው፡፡ “ከተማን ከሚመራ ሰው ይልቅ ራሱን የሚመራ ሰው ይበልጣል” ይላል ጠቢቡ ሰለሞን፡፡ ራስን ማሸነፍ ሌሎች ውጫዊ ነገሮችን የማሸነፊያ ቁልፍ ነው፡፡ በመቀጠል በቅደም ተከተል የምንመለከታቸው 7 ልምዶች ማንኛውም ሰው የግል ህይወቱ መሪ እንዲሆን በእጅጉ የሚያግዙ ናቸው፡፡ አሁን ቦታውን ለእነዚህ ልምዶች ለቀቅ እናድርግ እስኪ፡፡

1. ኃላፊነት ውሰዱ

ጅብ ከሄደ በኋላ የውሻ መጮህ ምንም ውጤት አያመጣም፤ ትርፉ ድካም ነው፡፡ ውጤት የሚያመጣው ጅቡ ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ በማነፍነፍ ድምጽ ማሰማት ነው፡፡ ሁኔታዎችን፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ዓለምን ወዘተ የሚወቅሱ ሰዎች በህይወታቸው የረባ ቁም ነገር አያከናውኑም፤ ሁልጊዜም ኃላፊነትን የሚያሸክሙት ከእነሱ ውጪ ላለ ሌላ አካል ነው፡፡ ኃላፊነትን መሸከም ስንችል ነው የህይወታችንን ጉዞ አቅጣጫ መወሰን የምንችለው፡፡ የተሸከርካሪውን መሪ ለሌላ አካል አሳልፈን ሰጥተን የምፈልገው ቦታ አይደለም የደረስኩት፤ በፈለኩት ፍጥነት አይደለም እየተጓዝኩ ያለሁት ወዘተ ልንል አንችልም፤ ብንልም ዋጋ የለውም፡፡ የጉዞውን አቅጣጫ፣ ፍጥነት እና አድራሻ የሚወስነው አሽከርካሪው ነው፡፡ ልምዳችን መውቀስ፣ ጣት መጠቆም፣ ራስን መከላከል ወዘተ ከሆነ እውነቱን ለመናገር የሚወቀስ ነገር ማግኘት አይከብድም፡፡ ዘወትር የእናቴ መቀነት አደናቅፎኝ ነው ማለት ህይወታችን ባለህበት እርገጥ እንዲሆን በር ወለል አድርጎ ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ለውጥ ለማምጣት፣ የራሳችን ሰዎች ለመሆን፣ ውስጣችንን ድል ለማድረግ ወዘተ ሁልጊዜም ለገዛ ራሳችን ህይወት ሙሉ ኃላፊነት እንውሰድ፡፡ ቃላችንን የምናከብር፤ በአልንበት ቦታ የምንገኝ፤ በገዛ ራሳችን ጥረት የምንፈልገውን ማንኛውንም ዓይነት ነገር እጃችን ለማስገባት መጓዝ ያለብንን ያህል ርቀት መጓዝ የምንችል ሰዎች እንሁን፡፡ “ስራ እኮ ጠፋ! እኔ ምን ላድርግ?!” ከማለታችን በፊት ስራ ለማግኘት የምንችለውን ድንጋይ በሙሉ መፈንቀላችንን እርግጠኛ እንሁን፤ ቀጣሪዎች የሚፈልጉትን ዕውቀት እና ክህሎት ይዘን ለመገኘት ጥረት እናድርግ፤ የተለመደውንም ያልተለመደውንም አማራጭ እንፈትሽ፡፡ ሳይኮሎጂስቶች “Life is 10 % what happens to us and 90 % how we react to it” ይላሉ፡፡ የህይወታችንን አብዛኛውን (90 %) ክፍል በምንፈልገው መልኩ መስራት እንችላለን ማለት ነው፡፡ የምናጭደው የዘራነውን ነው፡፡

2. የምትፈልጉትን ነገር አስቀድማችሁ እወቁ

ስቴቨን ኮቬይ “ነገሮች ሁለት ጊዜ ይፈጠራሉ” ይላል፡፡ የመጀመሪያው ፈጠራ የሚጠናቀቀው አእምሮአችን ውስጥ ነው፡፡ ከቤት ከመውጣታችን በፊት የምንሄድበትን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ከአንድ እና ሁለት፣ አምስት እና አስር ዓመት ወዘተ በኋላ ምንድን ነው ማግኘት፣ ማድረግ፣ መሆን ወዘተ የምንፈልገው? ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ መስጠት ነገሮቹ በተጨባጭም ወደ ህይወታችን የሚመጡበትን ዕድል ከፍ ያደርጋል፡፡ “We rise to the level of our expectations” ይባላል፡፡ የምናገኘው የምናስበውን ነው፤ የምንደርሰው እንደርሳለን ብለን የምናስበው ከፍታ ድረስ ነው፡፡ ግባችንን ማወቃችን ትኩረታችንን ለመሰብሰብ ይረዳናል፤ ከነፈሰው ጋር አንነፍስም፤ በፈተና መካከል ጸንተን እንቆማለን፡፡ ሳይኮሎጂስቶች የህይወታችንን ግብ በቅጡ ለመለየት የሚረዳን አንዱ ሁነኛ መንገድ “የቀብራችን ዕለት እንዲነበብ የምንፈልገውን የህይወት ታሪካችንን መወሰን ነው” ይላሉ፡፡ ቁጭ ብለን ልናስብበት ይገባል፡፡

3. ቅድሚያ ለሚገባቸው ነገሮች ቅድሚያ ስጡ

“ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት” ይባላል፡፡ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገሮች ቅድሚያ መስጠት አለብን፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም፡፡ ኮቬይ እንዲህ ይላል፡- “ራሳችሁን ከእነዚህ ሶስት አጉል ልምዶች በአንዱ መውቀስ ቢኖርባችሁ በየትኛው ነው የምትወቅሱት? (1) መስራት ያለብኝን ነገር በቅደም ተከተል መለየት አልችልም፤ (2) በአስቀመጥኩት ቅደም ተከተል መሰረት መስራት አልችልም፤ (3) በወሰንኩት ቅደም ተከተል መሰረት ለመስራት አስፈላጊው ቁርጠኝነት የለኝም፡፡ ብዙ ሰዎች ቁርጠኝነቱ የለኝም ነው የሚሉት፡፡ ጠለቅ ብለን ከመረመርነው ግን እውነቱ ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እውነቱ ቅደም ተከተሉ ውስጣችን በጥልቀት አለመስረጹ ነው፡፡ ልምድ 2ን ማለትም የህይወት ግባችንን አስቀድመን በሚገባ ለይተን በሚገባ ውስጣችንን መቅረጽ አለመቻላችን ነው”::

4. በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ ተመሩ

ከተቃራኒ ፆታ ጀምሮ እስከ የንግድ ስራ ግንኙነት ድረስ በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ መመራት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ “አዎ! በሚገባ አምንበታለሁ፡፡ በእኩል ተጠቃሚነት መርህ ነው ህይወቴን የምመራው፡፡” ትሉ ይሆናል፡፡ እንደምትሉት እንደምትኖሩ ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ለማሸነፍ ከመጣር ይልቅ እንዴት በጋራ እኩል ተጠቃሚ ለመሆን ጥረት አድርጉ፡፡ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ከሌላው ከፍ ብሎ ለመታየት፣ ልክ ሆኖ ለመገኘት ወዘተ ከመጨነቅ ይልቅ በጋራ እኩል እንዴት ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ማሰብ እና ይህንን መርህ በየትኛውም የግንኙነታችን መረብ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ይበልጥ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

5. መጀመሪያ ለመረዳት ጥረት አድርጉ

መጀመሪያ ስንረዳ የሚረዱንን እናገኛለን፡፡ ብዙ ጊዜ ግን በአንጻሩ ጊዜያችንን የምናጠፋው ሰዎች እንዲረዱን በመፍጨርጨር ነው፡፡ ቆም ብለን  “ምንድነው እስኪ እያሉ ያሉት? ልክ ይሆኑ ይሆን? በየትኛው ማዕዘን ነው እነሱ ጉዳዩን ያዩት?” ወዘተ ብሎ በቀናነት ማሰብ እና ሰዎችን ለመረዳት ጥረት ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ሰዎችን የመረዳት ችሎታችን ጥሩ ሲሆን የሚረዱንን ሰዎች ቁጥርም ይጨምራል፡፡

6. 1 + 1 = 3

“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ትልቅ መልዕክት ያለው አባባል ነው፡፡ በጋራ የሚሰሩ ስራዎች በግል ከሚሰሩ ስራዎች ይልቅ የላቀ ውጤት ያመጣሉ፡፡ አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብም፡፡ ሩጫን በመሰለ የግል ጥረትን በከፍተኛ ሁኔታ በሚጠይቅ የውድድር ዘርፍ እንኳን አትሌቶቻችን ሲተባበሩ የሚያስመዘግቡትን አንጸባራቂ ድል እናውቀዋለን፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ በጋራ የመስራትን መንፈስ ማዳበር ጠንካራ ያደርጋል፤ የበዛ ፍሬም ያፈራል፡፡ አብረን መብላት ብቻ ሳይሆን አብረን መስራትንም ባህላችን እናድርግ፡፡ ስቴቨን ኮቬይ እንደሚለው “አንድ
ሲደመር አንድ ከሁለት በላይ ነው”፡፡

7. መጋዛችሁን ሳሉ

ስቴቨን ኮቬይ መጽሐፉ ውስጥ ግሩም አፈ ታሪክ አለ፡፡ አንድ ተጓዥ መንገደኛ በአንድ ጫካ ውስጥ አቋርጦ ሲያልፍ አንድ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ላቡ ጠፍ እስከሚል ድረስ ያለምንም እረፍት እንጨት ሲቆርጥ ይመለከታል፡፡ ተጓዡ መንገደኛ ቆም ይልና የመጋዙን መደነዝ አስተውሎ ኑሮ “ወዳጄ! ለምን መጋዝህን ዕረፍት ወስድህ አትስለውም?” ይለዋል፡፡ ልፋ ያለው እንጨት ቆራጭ “አይ ለሱ እንኳን ጊዜ የለኝም” የሚል የዋህ ምላሽ ይሰጠዋል፡፡ ይኼ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ዕረፍት ወስዶ መጋዙን ቢስል በተሻለ ቅልጥፍና ብዙ እንጨት መቁረጥ እንደሚችል አልተረዳም፡፡

የተራ ቁጥር ሰባት ልምድ መልዕክት ቀላል እና ግልጽ ነው፡፡ በቂ ዕረፍት ምንጊዜም አድርጉ ነው፡፡ ከስራ በኋላ ራሳችሁን ዘና የማድረግ ልምምዱ ይኑራችሁ፡፡ መዝናናት ለጊዜው ከሚሰጠው ደስታ ባሻገር ለቀጣይ ስራ ያዘጋጃል፡፡ ሁልጊዜም እንደምለው ትልልቅ ኩባንያዎች ወጪ ችለው፣ ወርሃዊ ደሞዝ መክፈላቸውን ሳያቋርጡ ሰራተኞቻቸውን የሚያዝናኑት በጣም ቸር ስለሆኑ አይደለም፡፡ ይልቁንም የተዝናና ሰራተኛ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚሆን እና እነሱንም ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡

አንድ አንድ ሰዎች “እኔ መዝናናት አይሆንልኝም” ይላሉ፡፡ “መዝናናት ራሱን የቻለ ችሎታ ነው” ይላል አንድ ሌላ ወዳጄም፡፡ በመሆኑም “እንዴት እንዝናና?” የሚል ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች እነዚህን የመዝናኛ አማራጮች እንድትፈትlቸው እጋብዛለሁ፡- ዋና ዋኙ፤ ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር አስደሳች ጊዜ አሳልፉ፤ ዮጋ ስሩ፤ ዳንስ ደንሱ፤ ከከተማ ከተቻለም ከሀገርም ወጣ ብላችሁ ጎብኙ፤ ደስታ ይሰጠኛል ብላችሁ የምታስቡትን የትርፍ ጊዜ የመዝናኛ አማራጭን (Hobby) ሞክሩ፡፡

ቸር እንሰንብት!

(በነጋሽ አበበ)
©zepsychologist
#የጥሩ_እንቅልፍ_9_ጠቀሜታዎች
ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው

1. እንቅልፍ ልብዎን ጤናማ ያደርገዋል

እንቅልፍ ማጣት የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ(ስትሮክ) እንደሚያባብስ ተመራማሪዎች ይናገራሉ ይህም የሚሆነው የደም ግፊት እና ኮሌስትሮል መጠንን በመጨመር መሆኑን ይናገራሉ ፡፡በእያንዳንዱ ምሽት ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል እንቅልፍ ካገኙ የልብዎን ጤና የተጠበቀ ይሆናል ፡፡

2. እንቅልፍ ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል

ተመራማሪዎች ለብርሃን መጋለጥ የሜላቶኒንን መጠን እንደሚቀንስ ያምናሉ ፡፡ ሜላተንቲን የእንቅልፍ ና የመንቃትን ዑደትን የሚያስተካክል ሆርሞን ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ዕጢዎችን እብጠት በመቀነስ ካንሰርን ይከላከላል፡፡ ሰውነትዎ የሚፈልገውን ሜላቶኒንን ለማምረት እንዲረዳዎ መኝታዎ ጨለመ ባለ ስፍራ ያድርጉ እንዲሁም ከመኝታዎ በፊት ኤሌክትሮኒክስን ከመጠቀም ይቆጠቡ ፡፡

3. እንቅልፍ ውጥረትን ይቀንሳል

ሰውነትዎ እንቅልፍ እጥረት ሲኖርበት ወደ ውጥረት(ስተርስ) ሁናቴ ይሄዳል ፡፡ ይህም ውጥረት ወየንም ስተርስ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ የመያዝ እድልን ይጨምራል፡፡

4. በቂ እንቅልፍ ማግኘት የበለጠ ንቃትን ይሰጣል

ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ ንቃት እንዲሰማዎት እና በሚቀጥለው ቀን እንዲነቃቁ ይረዳዎታል ፣ በተጨማሪም ጥሩ ስሜት እነዲሰማዎት በማድረግ ሌላ ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ እድልዎተን ይጨምራል።

5. እንቅልፍ የማስታወስ ችሎታዎን ያሻሽላል

ተመራማሪዎች እስካሁኑ ሰዐት ድረስ ለምን እንደምንተኛ ሙሉ በሙሉ አልተረዱም ፣ ነገር ግን እንቅልፍ የማስታወስ ዐቅምን በማጠናር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ደርሰውበታል፡፡
በእንቅልፍ ጊዜ ሰውነትዎ አረፍ ሊል ይችላል ፣ነገር ግን አንጎልዎ ቀንዎን በማቀነባበር የተያዩ ግንኙነቶችን በማድረጉ ሥራ ላይ ነው ፡፡ እነዚሀም ግንኙነቶች በተያዩ ክስተቶች ፣ በስሜት ህዋሳት ፣ ስሜቶች እና ትውስታዎች መካከል ሲሆን በቂ እንቅልፍ ማግኘት ነገሮችን በተሻለ ለማስታወስ እና ለማስኬድ ይረዳዎታል ፡፡

6. እንቅልፍ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል

ተመራማሪዎቹ እንዳሳዩት በማታ ጥቂት ሰዓታት የሚተኙ ሰዎች ከመጠን በላይ ወፍራም ወይም ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው መሆናቸውን ነው ፡፡ የእንቅልፍ እጥረት በሰውነት የምግብ ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሆርሞኖችን መጠን ይጎዳል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት የምግብ ፍላጎትን የሚያስተካክሉ ሆርሞኖች ጋሬሊን እና ሌፕቲን በእንቅልፍ እጥረት ምክንያት ተስተጓጉለው ተገኝተዋል ፡፡ ክብደትን ለማቆየት ወይም ክብደት ለመቀነስ ከፈለጉ ፣ በመደበኛነት በቂ እንቅልፍ ማግኘት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አይርሱ።

7. ማቅለብ ብልጥ ያደርግልዎታል

በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ መውሰድ ለአጠቃላይ ጤናዎ ጥሩ ሲሆን በተጨማሪም የበለጠ ምርታማ እንዲሆኑ አዕምሮዎትን የሚያድስ አማራጭ ነው ፡፡ ጥናቶችእንደሚያሳዩት ከሆነ በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ የሚወስዱ ሰዎች የአዕምሮ ወይንም ኮግኒቲቭ ተግባር እና የ ስሜት መሻሻል ማሳየታቸውን ነው፡፡

8. እንቅልፍ የጭንቀት በሽታ አደጋዎን ይቀንሳል

ሴሮቶኒንን ጨምሮ እንቅልፍ በሰውነትዎ ውስጥ ያሉትን ብዙ ኬሚካሎች ይነካል። የ serotonin ጉድለት ያላቸው ሰዎች በጭንቀት በሽታ የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ትክክለኛውን የእንቅልፍ መጠን እያገኙ መሆኑን በማረጋገጥ ድብርትዎን ለመከላከል በየዕለቱ ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል የዕንቅልፍ ጊዜ ይውሰዱ፡፡

9. እንቅልፍ ሰውነቱን በራሱ እንዲጠገን ይረዳል

እንቅልፍ ዘና የማለት ጊዜ ነው ፤ ሰውነታችን በቀኑ ጊዜ፣ በአልትራቫዮሌት ጨረሮች እና በሌሎች ጎጂ ነገሮች ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ጠንክሮ የሚሠራበት ጊዜ ነው ፡፡ ተኝተው እያለ ሴሎችዎ የበለጠ ፕሮቲን ያመርታሉ ፡፡ እነዚህ የፕሮቲን ሞለኪውሎች የሰውነት ክፍሎችዎን በመገንባትና በማድስ ጉዳቱን ለመጠገን ያስችላቸዋል ፡፡

©በአቤል ታደሰ

ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው
መልካም አዳር
@Psychoet
😁😁😁😁😁😁ሳቅ ለስጋም ሆነ ለአእምሮ ጤና መልካም ነዉና ስትስቁ ዋሉልኝ ቤተሰቦቼ !
❖ሕይወት እንኳን ለመጨነቅና ለማዘን ለመደሰት ራሱ አጭር ናት ። መልካም የደስታና ሳቅ ቀን ይሁንልችሁ ።
❖ከተመቻችሁ ደግሞ #Share በማረግ ጓደኞቻችሁን አስቁ።
@psychoet
‹‹ በዚኽች ምድር በቢሊዮን የሚቈጠር ሰው አለ፤ ፈጣሪ አንዱንም ሰው ያለ ምክንያት አልፈጠረም፡፡ ኹሉም ሰው በዐላማ መልካም ሥራ እንዲሠራ በዚኽም ምድር ላይ ተደስቶ እንዲኖር ተፈጥሯል፡፡ ሕይወታችንም የሚለካው በኖርንበት ዐላማ እንጂ በኖርንበት ዕድሜ ብዛት አይደለም፡፡››

ሜሎሪና ቴሎስ
አንተ የአላማ ሰው ነህ!
አንቺ የአላማ ሰው ነሽ!
@psychoet

መልዕክቱን ቢያንስ ለ5 ጓደኞቻችን እናጋራ
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት

1. ጥሩ አድማጭ መሆን

ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡

2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን

በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡

3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ

የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡

4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ

ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡

5. አቀማመጥን ማስተካከል

ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡

6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት

እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡

7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ

ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡

8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡

9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር

በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡

ተግባቦት የብዙ ሰው ችግሮ ነውና #share በማረግ ለሌሎች እነዚህን ቁልፍ ነገሮች እናሳውቅ
ፔጃችንን #Like በማረግ በየቀኑ አዕምሮዎን በመልካም ሀሳብ ይመግቡ

(በዘመነ ቴዎድሮስ)
©zepsychologist

#ለሀገራችን ቸር ሳምንት ይሁንልን

Join My Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet
አንዳንዴ ፥ ይደክመኛል ተስፋ እቆርጣለሁ ፥ የሕይወት ትርጉም ይጠፋኛል ፡፡ ሕይወቴ ከደስታ ይልቅ በሀዘን ፣ ከብሩህ ተስፋ ይልቅ በፍርሃት ይሞላል ፡፡

ግን ግን ሁል ጊዜ መጓዜን አላቆምም ፡፡ ነገ በሕይቴ የበለጠ መከራ ወይንም ትልቅ ደስታ ቢመጣም መጓዜን አላቆምም ፡፡ በዚህች ምድር ሁለት ሕይወት የለም ፡፡ አንዴ ኑሬ ላልመለስ እሄዳለሁ ግን ግን በሕይወቴ ሁሉ የምጥረው ነገር ቢኖር ሌላ ሰውን ላለማሳዘን ፣ ላለማስከፋት በኔ ምክንያት ሕይወትን እንዳይጠላ ለማረግ ነው ፡፡

ወዳጆቼ ቆም ብለን እናስብ ! ለማይደግሞ ሕይወት ወደኀላ አንመልከት በቀና አስተሳሰብና ማንነት እንኑር እንጓዝ ፡፡ አንድ ቀን እኛም ታሪክ እንሆናለን ፡፡

እወዳችኀለሁ!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
አንድ ጊዜ አንድ ወጣት ልጅ ከሚወደው ፈረሱ ጋር በመሆን በመንገድ እየሄደ ለፈረሱ ምንም የሚታየኝ መንገድ ፊት ለፊት ላይ የለም አለው:: ፈረሱም ቀጣይ አንድ እርምጃ ይታይሀል ብሎ ጠየቀው:: አዎ ታየኛል ብሎ ልጁ መለሰለት:: ፈረሱም የምትደርስበትን ካወቅህ መላውን መንገድ ማወቅ አይጠበቅብህም በቀጣዩ አንድ እርምጃ ላይ ብቻ አተኩር አለው ይባላል::

ዛሬ መውሰድ ያለብህ አንድ እርምጃ (ስልክ መደወል: ፅሁፍ መፃፍ: ሰዎች ማማከር: ስራ መልቀቅ: ከቤት መውጣት: መለየት መለያየት?)....

ብዙዎቻችን መንገድ አይታየኝም: ሩቅ ነው: ጠመዝማዛ ነው: አስፈሪ ነው: ከባድ ነው ብለን የት መድረስ እንደሚገባን ብናውቅ እንኳን ጉዟችንን ለመቀጠል ፍቃደኛ አይደለንም:: ዋናው የት መድረስ እንዳለብህ ማወቅ እንጂ ሁሉ የመንገዱ ሁኔታ ሊያሳስብህ አይገባም:: ከፊት ለፊትህ ያለ አንድ እርምጃ ከታየህ እሱን ቀጥል::

መንሰላል የመጀመሪያውን መወጣጫ ረግጠህ የመጨረሻው ላይ እንደማታርፍ ነገር ግን እነዛን ትንንሽ መወጣጫ ተጠቅመህ ወደላይ እንደምትደርሰው እንደዛው የራዕይ ጉዞም በአንድ ግዜ ሁሉንም መንገድ የምትጏዘው ሳይሆን ከማይታዩህ: አስፈሪና ጠመዝማዛ ከመሰሉህ ረጃጅም መንገዶች ይልቅ ቀጣዩን አንድ እርምጃ የምትወስድበት ሂደት ነው::

ዛሬ መውሰድ ያለብህ አንድ እርምጃ (ስልክ መደወል: ፅሁፍ መፃፍ: ሰዎች ማማከር: ስራ መልቀቅ: ከቤት መውጣት: መለየት መለያየት?) የትኛው ነው???
መልካም ቀን!!

@psychoet
ቢያንስ ለ 5 ወዳጆች #Share እናርገው
ሰላም የቻናሉ ቤተሰቦች!
እነኾ የምሽት ጥያቄ

በሕይወታችሁ በጣም የተደሰታችሁባቸው 3 ቀናት የትኞቹ ናቸው?

ይሄን እያሰላሰላችሁ ተኙ፡፡
በራስ መተማመን የራስ እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy) ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም…….. ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣ አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው

https://youtu.be/X_DtOjIBQ4Q
👉ጠቃሚ ምክሮች👈

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

#መልካም_ቀን !
#Share #Like
በቴሌግራም ቤተሰብ ይኹኑ T.ME/Psychoet
የኑሮ ቀውስን ማሸነፍ |Overcoming Crisis|
በዶክተር ማይልስ ሞንሮ ተጽፎ በአማረኛ ተተርጉሞ የቀረበ

በአስቸጋሪ ጊዜ የማደግ ሚስጥር
📌ሕይወት ሲከፋ እንዴት እናመልጣለን?
📌በሌላ ሰው ስህተት ስንወድቅ ምን እናረጋለን?
📌በተለያዩ የሕይወት ቀውሶች ውስጥ ስንገባ እንዴት እናመልጣለን?

አስተማሪ የሰስነልቦናዊ ምክር ስለሆነ ጊዜ ሰታችሁ አድምጡት!
ክፍል 1 | Part 1
https://youtu.be/B7Q1GThhups

ክፍል 2 | Part 2
https://youtu.be/YmVEApdaeg8

ክፍል 3 (የመጨረሻው) | Part 3 ( Last )
https://youtu.be/fo3708Pyi5o
ነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 1
የምትችሉ እንድትመጡ ደራሲዋ ጋብዛችኀለች፡፡
#መጀመር
ማንኛውም ነገር ካልጀመርነው ይከብዳል ስንጀምረው ተግዳሮት አለዉ ደጋግመን ስናደርገዉ ቀላል ነዉ።
ሳንጀምር ይከብዳል አንበል እንደሚከብድ በምን አወቅን?
1. እንጀምረው
2. እንቀጥለው
3. እንጨርሰው ።
#ሁሌ ከሁዋላ የሚሰበረው እስክንለምድ ነው!!!
©ሁንዴ

ይህን መልዕክት ለምትወዱአቸው #5 ታታሪ ጓደኞቻችሁ Forward አርጉልኝ !
#Join #Share
@psychoet
@psychoet
@psychoet
👉ጠቃሚ ምክሮች👈

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

#መልካም_ቀን !
#Share #Like
በቴሌግራም ቤተሰብ ይኹኑ @Psychoet
2024/11/16 07:14:06
Back to Top
HTML Embed Code: