Telegram Web Link
ውሸት
#ክፍል_2
ለምን እንዋሻለን ??? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን???
ለምን እንዋሻለን ??

ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡–  ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡

ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡

ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች  በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና  እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ  (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው  ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-

ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡

ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን  ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡

ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡

ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡

ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡

ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
#ስሜታዊነትን (emotional state)፣
#የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity)  እና
#ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡

የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን  የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና  ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም  ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡

ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………..

(በቁምላቸው ደርሶ)
©Zepsychologist
@psychoet
<እብዱ> መጽሐፍ ትረካ
ጸሐፊ - ኅሩይ ሚናስ
/የብዕር ስም- አውግቸው ተረፈ /
ክፍል 1
https://youtu.be/W2hsg_560Zo
ክፍል 2
https://youtu.be/fpEKcAcBYTs
ክፍል 3 (የመጨረሻ ክፍል)
https://youtu.be/1JzswWFOOnk
አንድ ባለ ትዳር ፖሊስ ጣቢያ ደውሎ"ሚስቴ ጠፍታለች" ብሎ ያመለክታል፡፡

ፖሊስ ፡- "ከጠፋች ምን ያህል ግዜ ሆናት?"

ባል ፡- "አንድ ወር ሆኗታል"

ፖሊስ ፡- "ለምን እስከዛሬ አላመለከትክም?"

ባል ፡- እስከ ትናንት ድረስ መጥፋቷ ህልም ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዛ ምንም የታጠበ ልብስ እንደሌለኝ ሳይ መጥፋቷን አመንኩ፡፡

ጭብጥ፡- አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ናቸው፡፡ በህይወታቸው ውስጥ ምንም ቦታ የለክም፤ ነገር ግን ካንተ የሚፈልጉት ነገር ሲኖር መቃብር ድረስ ወርደውም ቢሆን ይፈልጉሀል፡፡

"የሰው ልጅ ያልተነበበ መፅሐፍ ነው" ወዳጄ ሁሌም ሰዎችን መርምራቸው፤ የዛኔ እውነተኛ ወዳጅህን እና ጠላትህን ነጋሪ ሳያስፈልግህ አንተው ትረዳዋለህ፡፡

©ከFB የተገኘ
@Psychoet
የምስራች ለአንባቢያንና ለወዳጆቼ

ሜሎሪና ክፍል ኹለት <<ሜሎሪና - ቴሎስ>> ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከአንባቢዎች እጅ ይደርሳል፡፡ መጽሐፉ፣ የሰው ልጅ በሕይወት ሲኖር ከሚጠይቃቸው ጥየያቄዎች አንዱና ዋነኛው የኾነውን "ወደዚኽ ምድር ለምን መጣኹ? የሕይወት አላማዬንስ እንዴት አገኛለሁ? >> የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚጥር #የሳይኮሎጂ_ልብወለድ መጽሐፍ ነው፡፡

በዚኽ መጽሐፍ ዝግጅት ወቅት በተለያየ መንገድ ስትረዱኝ ለነበራችሁ ወዳጆቼ በሙሉ ምስጋናዬ ካላችሁበት ይድረስልኝ፡፡ <<ሜሎሪና - ቴሎስ>> ከሰኞ ጀምሮ በኹሉም መጽሐፍ አከፋፋዮች ዘንድ ታገኙታላችኹ ። ሜሎሪና

መልዕክቱን #Share በማድረግ ላልሰሙ ታደርሱልኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ

@PSYCHOET
ስለ ዝምተኛ ሰዎች እውነታዎች /FACTS ABOUT QUIET PEOPLE

1. ዝም ያሉ ሰዎች በልባቸው ውስጥ ብዙ ያወራሉ፣ አንዳንዴ ብቻቸውን ያወራሉ።
(Quiet people talk a lot inside of their heart, sometimes they talk alone.)

2. አንዴ ካንተ ጋር ከተግባቡና ከተመቻቹህ በኋላ ግን እብዶች ይሆናሉ።
(Once they get comfortable with you they get crazy and wild.)

3. በሃሳብ እና በልብ ይናገራሉ።
( They speak in thoughts and heart.)

4. ዓይን አፋር ናቸው, የአይን ግንኙነትን ብዙ መጠበቅ አይችሉም.
( They are shy, they can't maintain eye contact a lot.)

5. በጣም ብዙ ንዴት አለባቸው አታናድዱአቸዉ። እና ቁጣቸውን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ ያውቃሉ.
( They have too much anger don't get them pissed off. And they know how to micromanage their anger issues.)

6. ጠንካራ እና በጣም ብልህ ናቸው.
(They are strong and very intelligent.)

7. በማህበራዊ ሚዲያ (አንዳንድ ጊዜ) በጣም ብርቱ ናቸው. ይፖስታሉ፣ ይፅፋሉ፣ ያደንቃሉ አስፈላጊ መስሎ ከታያቸውም ይተቻሉ
(They are very crazy on social media (sometimes))

8. በጣም አሪፍ ስብዕና አላቸው እና ከነርሱ ጋር አብረው መሆንም አስደሳች ነው።
(They have very cool personalities and are fun to be with.)

9. አእምሯቸው ሁል ጊዜ ያሰላል, ከመጠን በላይ ያስባሉ. መጥፎ ነገሮች እና ጥሩ ነገሮች. እንደዛ ነው የታዘብኩት። ( Their minds are always calculating, they are overthinking too much. Bad things and good things. That's how I have noticed. )

10. እነሱ ታማኝ ናቸው እና በግንኙነቶች ውስጥ በጣም ይወዳሉ. እንደዚህ ያሉ ሰዎች በግንኙነት ውስጥ ሲሆኑ በሙሉ ልባቸው ሠዉን ይወዳሉ። ጥልቅ ፍቅርም አሏቸው . እነሱ ካልወደዱህ ግን ፍቅራቸው በጣም ጠንካራ ስለሆነ ሙሉ ለሙሉ ይተውሃል።
(They are loyal and love the most in relationships. When quite people they are in a relationship they love you wholeheartedly. They love deep. But if they don't love you, they leave you completely due to their love is very strong. )

11. በውስጥ ስሜታቸው ቢጎዳና Sensitive ቢሆኑም እንኳን፤ሕመማቸውን ፈጽሞ አያሳዩም,
(They never show their pain, and they are emotional people. )

12. አንዳንዶቹ የተጨነቁ እና ብቸኛ ናቸው, ነገር ግን ምንም እንዳልሆኑ አስመስለው, በጥልቅ ብቻቸውን መሆን ይሰማቸዋል, ስሜታቸዉን ለመግለፅ አይደፍሩም ስለዚህም ድብቅ ሰዎች ናቸው.
(Some of them are depressed and alone but they pretend, deep down they feel like to be alone, they are introvert people. )

13. በጣም ቆንጆ ፈገግታ እና ያልተለመደ ሳቅ አላቸው ። (They've got the cutest smile and weirdest laughter. )

14. አብዛኞቻቸው እውነትን ይወዳሉ። እነርሱም ሐቀኞች ናቸው።
(Most of them they like facts, and they are honest. )

15. ጸጥ ያሉ ሰዎች ሚስጥራዊ ሊሆኑ ይችላሉ, እንዲሁም ብዙ ነገሮችን ይደብቃሉ, ነገር ግን ምቾት እንዲሰማቸው ወይም እንዳይረበሹ ማድረግ ከፈለጉ ያለ ምንም ፍርሃት እውነቱን ይናገራሉ.
(Quiet people are likely to be secretive, also they hidecholy they will tell the truth as it is without any fear. )

16. ጸጥ ያሉ ሰዎች ብቻቸውን በሚሆኑበት ጊዜ በእውነት ደስተኛ ይሆናሉ። በሚወዱት ነገር እስከተጠመዱ ድረስ። ችግር የለም.
(Quiet people are introverts they are actually happy when they are alone. As long as they are busy with what they love. It's okay. )

17. ጸጥ ያሉ ሰዎች, እና ውስጣዊ ሰዎች በአእምሮአቸው ውስጥ የራሳቸውን ትዕይንቶች ፈጥረው ያምናሉ.
( Quiet people, and introvert people create their own scenes in their mind and believe them. )

18. ዝምተኛ ሰዎች,ማንበብ ይወዳሉ። የሚወዷቸው መጽሃፍትን በተለይም ልብ ወለድ እና ልብ ወለድ ያልሆኑ መጽሃፎችን ነዉ። አንዳንድ ጊዜ አነቃቂ መጽሐፍት (የራስ አገዝ መጽሐፍትንም ማንበብ ያስደስታቸዋል ።
( Quiet people, and introverted people they love to read. Reading books, especially novels both fiction and nonfiction books. Sometimes inspirational books (self help books).)

👉ዝምተኛ ሠዎችና የዚህ ፔጅ አምድ ተከታዮችና አንባቢዎች ይህ ሙያዊ ትንታኔ ምን ያህል ስለእናንተ ወይም ስለምታውቋቸዉ ዝምተኛ ሰዎች ባህሪ እንደገለፀ ትዝብታችሁን Comment በማድረግ አጋሩን።

©#Inspirational #stories & #life #hacks
አነቃቂ ታሪኮችና የሕይወት ዘዴዎች
@Psychoet
ከኢትዮጵያ ውጭ ለምትኖሩ የቻናላችን ቤተሰቦች መልካም ዐዲስ አመት እንዲኾንላችሁ እመኛለኹ፡፡

🎊🎊🎊🎁2022🎁🎉🎉🎉

HAPPY NEW YEAR!
ምን ያህሎቻችሁ ትስማማላችኹ?
@psychoet
ሜሎሪና ክፍል ኹለት (ሜሎሪና - ቴሎስ) ለአንባቢዎች ቀርቧል፡፡

#በዐዲስ አበባ በ #ጃዕፈር #ሀሁ #እነሆ #ኮሜርስ መደብር እንዲኹም በሚቀርቧችኹ ቦታዎች ታገኙታላችኹ

መልካም ንባብ ይኹንላችኹ፡፡

‹‹በርግጥ ወደዚች ምድር የመጣነው እኛ ፈልገን ሳይኾን ምድር ስለፈለገችን ነው፡፡ እንዴት እንደምንኖር ግን እኛና አካባቢያችን እንወስናለን፡፡ ትልቁ መኖርም እኛ እንደፈለግን ሳይኾን፣ በምድር እንደተፈለግን መኖር ነው፡፡ በዚኽች ምድር በቢሊዮን የሚቈጠር ሰው አለ፤ ፈጣሪ አንዱንም ሰው ያለ ምክንያት አልፈጠረም፡፡ ኹሉም ሰው በዐላማ መልካም ሥራ እንዲሠራ በዚኽም ምድር ላይ ተደስቶ እንዲኖር ተፈጥሯል፡፡ ሕይወታችንም የሚለካው በኖርንበት ዐላማ እንጂ በኖርንበት ዕድሜ ብዛት አይደለም፡፡... ››
@psychoet
ሠላም ወዳጆች፣
ኑ! "ሜሎሪና - ቴሎስ" መጽሐፍን እንመርቅ፣

″ሜሎሪና ክፍል ፪ -ቴሎስ‶
የተሰኘው የናሁሰናይ ፀዳሉ ዐዲስ መጽሐፍ
ቅዳሜ፣ ጥር 21 ከ 7:30- 10:00
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡

በዕለቱ የአንጋፋ የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች ዲስኩር፣
የግጥም፣ የጃዝ ሙዚቃ ፕሮግራም እንዲኹም
በደራሲው መጽሐፍ የማስፈረም ሥነስርአት ይከናወናል፡፡ እርስዎም በዕለቱ ተገኝተው አብረውን እንዲመርቁ በክብር ተጋብዘዋል፡፡

‹‹ቴሎስ ማለት በግሪክ ፣ የአንድን አካል ‹ዐላማ፣› ‹ግብ› እና ‹ፍጻሜ› የሚወክል ቃል ነው፡፡

የምርቃት ቦታ ፦ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
ቀን፦ ያኹኑ ቅዳሜ ጥር 21 ቀን 2014.ዓ.ም.
ሰአት ከ 7:30 - 10:00

መግቢያ . . . . በነፃ፣
"ሜሎሪና" መጽሐፍን በዕለቱ በዐማርኛ እንዲኹም በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በአዳራሹ መግቢያ በር ላይ ያገኙታል

ኹላችሁም እንድትገኙ ተጋብዛችኋል፣ መልዕክቱን ለሌሎች ያጋሩ

@Psychoet
ነገ ቅዳሜ ጥር 21 ከ 7:30-10 ሰአት በብሔራዊ ቴአትር አይቀርም፡፡
ወዳጆቻችሁን እየጋበዛችሁ፡፡
ዛሬ አይቀርም!
ምን ያህሎቻችን ተግባቢና ተጫዋች ሰው መኾን እንሻለን https://youtu.be/givWWp8Q44Y
#ሰዎች_ሁልጊዜም_የሚሉት_ነገር_አያጡም
Telegram www.tg-me.com/psychoet

አባትና ልጅ ወደ አንድ አካባቢ ረጀም ጉዞ ለማድረግ አህያቸውን ጭነው ከቤታቸው ይወጣሉ፡፡ ጉዞውን እንደጀመሩ ልጅ በአህያው ላይ ቁጭ ብሎ አባት ደግሞ የአህያዋን ልጓም ይዘው በእግራቸው ይጓዙ ጀምር፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ ግን የልጅን በአህያ ላይ መቀመጥ የአባትን በእግር መጓዝ የተመለከቱ ሰዎች “አባቱ በእግሩ እየሄደ እንዴት ልጁ በአህያ ይሄዳል? ምን ዓይነት ስነ ምግባር የጎደለው ልጅ ነው?” በማለት ቅሬታቸውን እና ትችታቸውን ሰነዘሩ፡፡ ይህንን እንደ ሰሙ አባት እውነትም ስህተት የሰሩ መስሏቸው ልጃቸውን በእግሩ የአህያዋን ልጓም ይዞ እንዲሄድ አድርገው እሳቸው ደግሞ በአህያ ላይ ወጥተው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ አሁን ደግሞ ሰዎች አባት ላይ ትችታቸውን ማዥጎድጎድ ጀመሩ;፡፡ “ምን ዓይነት ጨካኝ አባት ነው? ልጁን በእግሩ እያዳከረ እሱ በአህያ እንዴት ይሄዳል” አሉ፡፡ በዚህም አባት ይደናገጡና ከአህያዋ ላይ በመውረድ እንግዲያውስ ሁለታችንም በእግራችን እንሂድ ተባብለው በእግራቸው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ወደ ሌላ መንደር ሲቃረቡ አሁንም አህያዋን ያለ ምንም ጭነት ተዝናንቶ መሄድ እና የአባትና ልጅን በእግር መጓዝ የተመለከቱ የመንደሩ ሰዎች ሌላ ትችት መሰንዘር ጀምሩ፡፡ “ድሮም ሃብት ያላቸው ሰዎች ችግራቸው ይኼ ነው! እንዴት ያላቸውን ነገር መጠቀም እንዳለባቸው አያውቁም” አሉ፡፡

አሁንም ሰውን ማስደስት እንዳልቻሉ እና ልክ እንዳልሆኑ የተሰማቸው አባት እና ልጅ የሚቀጥለው መንደር ሰው አፍ ላለመግባት ሁለቱም በአህያዋ ላይ ወጥተው መጓዛቸውን ቀጠሉ፡፡ ቀጣዩ መንደር እንደደረሱ ግን አባት እና ልጅ የገጠማቸው አሁንም ሌላ ትችት ነው፡፡ “ምን ዓይነት ጨካኝ ሰዎች ናቸው? አንደበት የላትም ብለው ነው? የእግዜር ፍጥረት ላይ ይታያችሁ እስኪ እንዴት ሁለት ሆነው ጀርባዋ ላይ ተዝናንተው ተቀምጠው ይሄዳሉ አንዳቸውን ከተሸከመች አንሶ ነው” አሉ፡፡ አባት እና ልጅ ተደናግጠው ሁለቱም ከአህያዋ ጀርባ ላይ አፍታ እንኳን ሳይቆዩ ወረዱ፡፡ በየደረሱበት ትችት የገጠማቸው አባት እና ልጅም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ከተመካከሩ በኋላ ቢያንስ ከዚህ በኋላ የምናገኛቸውን ሰዎች ማስደሰት ይኖርብናል ብለው በማሰብ አህያዋን ተጋግዘው ለሁለት ተሸክመው ጉዟቸውን አሁንም ይቀጥላሉ፡፡ አህያዋን በመሸከማቸው ምክንያት እጅግ ተዳክመው ወደ ሚቀጥለው መንድር ይደርሳሉ፡፡ አህያ የተሸከሙትን የከተማዋን ሰዎች የተመለከቱት ሰዎች ወገባቸውን ይዘው መሳቅ ጀመሩ፡፡ ምን ዓይነት ጅል ሰዎች ናቸው አህያዋ ላይ ተቀምጠው እንደመሄድ እንዴት አህያ ተሸክመው ይጓዛሉ በማለት ተሳለቁባቸው፡፡ አባትና ልጅም ምንም ነገር ቢያደርጉ ከሰው ትችት ማምለጥ እንደማይችሉ እና ሁልጊዜም ቢሆን ሰዎች የሚተቹት ነገር ፈልገው እንደማያጡ ተረድተው ጉዟቸውን እነሱ ባሻቸው መንገድ ቀጠሉ፡፡

እውነትም ሰዎች ምንጊዜም ቢሆን የሚሉት አንድ ነገር አያጡም፡፡ የምታደርጉትን ነገር ቢወዱትም ባይወዱትም፤ ልክ ነው ብለው ቢያስቡም ባያስቡም ፤ ቢመለከታቸውም ባይመለከታቸውም አንድ የሚሉት ነገር አያጡም፡፡ መፍትሄው የገዛ ራስን ህይወት በራስ ፍላጎት መምራት ነው፡፡ የአንተ/የአንቺ ህይወት የተባለበትም ምክንያት ይኼ ነው፤ አንተ/አንቺ በአሻችሁ መንገድ ትመሩት ዘንድ ነው፡፡

ስለዚህ የትኛውም ጥሩ ነው፣ ዋጋ አለው፣ ይበጀኛል ወዘተ ብላችሁ ከልባችሁ እስካመናችሁ ድረስ ሰዎች ምንም ይበሉ ምን ከማድረግ ወደ ኋላ አትበሉ፡፡

(በኤባ ተስፋዬ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
Forwarded from Ask Anything Ethiopia
#education

ኸረ ሰዎች ጭንቀት ይዞኛል! ለምን መሰላችሁ ሜሎሪና የሚለዉን መፅሐፍ አንብቤ ነበር ነገር ግን መፅሀፉ ያለቀዉ በጣም ልብ አንጠልጣይ የሆነ ቦታ ላይ ነዉ እና የያሬድ እና የታቤል መጨረሻውን ማወቅ እፈልጋለሁ እባካችሁ ቴሎስ(ሜሎሪና 2 መሰለኝ) የሚለዉን መፅሐፍ ካላችሁ?

By: MAYT 👨
Ask Anything Ethiopia
ምን ያህሎቻችን ለወዳጅ ቤተሰቦቻችን መጽሐፍ በስጦታ መልክ እንሰጣለን?

ለጀማሪና እንዲኹም ለነባር አንባቢ ጓደኞቻችሁ "ሜሎሪና" እና "ቴሎስ"ን በስጦታ እንድትሰጡ እጠይቃለሁ? 🙏 ራሳችንንና ሕይወትን የምንፈልግበትና መጽሐፍ ነው፡፡
@psychoet
2024/09/28 11:26:14
Back to Top
HTML Embed Code: