Telegram Web Link
#ዜና

Volkswagen 4 አዲስ የ ID.7 ሞዴሎች አቀረበ።


Volkswagen የID.7 GTX፣ ID.7 GTX Tourer፣ ID.7 PRO S እና ID.7 Tourer Pro S ሽያጭ እንደአማራጭ በመጨመር የሞዴሎች ጥራት እያሻሻለ ነው።

ሁሉም አዳዲስ ሞዴሎች ከተለመደው 77kWh ባትሪ ወደ 86kWh አሳድጟቸዋል :: ID.7 GTX Tourer ፍጥነት መጨመር ላይ ያተኮረ ሲሆን ከ0-100 ኪሎሜትር በሰአት በ 5.4 ሴኮንድ ይደርሳል።  

ID.7 Pro S ደግሞ ርቀት መጨመር ላይ ያተኮረ በመሆኑ በአንድ ቻርጅ እስከ 709 ኪሎሜትር መሄድ ይችላል።

እነዚህ ሞዴሎች ለገበያው የቀረቡት በትላንትናው እለት ወይም June 6, 2024 ላይ ሲሆን ከ 58,985 ዩሮ ተነስቶ እስከ 63,955 ዩሮ በጀርመን ገበያ ላይ ሽያጭ ጀምሯል።

#volkswagen #ID7 #EV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BMW አዲሱን 1 Series ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቀቀ።


ቻንሲ በማሻሻል የBMW መኪናቸውን ከገበያው ላይ በጣም ተፎካካሪ ከሚባሉት ውስጥ አድርገዋል።

አዲሱ BMW 1 Series ነዳጅ ቆጣቢ ሞተር እና 48 volt ማይልድ ሀይብሪድ የሚጠቀም እና ሪሳይክል የተደረገ ማቴሪያል የሚጠቀም ነው።

በተጨማሪም የBMW አዲሱን የiDrive ሲስተም እና Quick-select ፊቸሮች ሲኖሩት የሚጠቀመውም BMW Operating System 9 ነው። 

ይህ መኪና ለብራንዱ የ20 የስኬት አመታት አዲስ ምእራፍ እንደሚሆን እና በLeipzig ፋብሪካም አዳዲስ ሞዴሎችን BMW እንደሚያስተዋውቅ ተናግሯል።

መኪናው በዚህ አመት መጨረሻ ወደ October አካባቢ በዋነኛው የጀርመን ገበያ ላይ ይቀርባል።

#BMW #BMW1Series  #BMWGroup
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota የCrown ሞዴሉን በCrown Signia አስፋፋው።


አዲሱ Crown በXLE እና በLimited Grade ሀያብሪድ ሆኖ በ All wheel-drive አማራጭ የቀረበ ነው።

በሊትር 16.15 ኪሎሜትር መሄድ ሲችል 240 የፈረስ ጉልበትም ይኖረዋል። በተጨማሪም 21 ኢነች ጎማ እና 2 ሜትር የሚሆን የካርጎ ቦታ ይኖረዋል።

ለፀጥታ ሲባል ውስጡ የተገጠመለት ሲስተም ሲኖረው ሌዘር መቀመጫና የወንበር ማሞቂያ ስታንዳርድ ሆኖ ይቀረባል።

12.5 ኢንች የስፒከር እና የመልቲሚድያ ሲስተም የተገጠመለት እና የToyotaን ሴፍቲ ሴንስ 3.0 ከPanoramic Sunroof ጋር በማሟላት ቀረቧል።

#Toyota #ToyotaCrown #Hybrid
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ZF LifeTech አዲስ የኤር ባግ ሲስተም ፈጠረ።


ZF ተብሎ የሚታወቀው ኩባንያ ስሙን ወደ ZF LifeTech ቀይሮ አዲስ የኤረ ባግ ሲስተም ለመኪና አምራቾች ማቅረብ ጀመረ።

ZF LifeTech በተለምዶ በመሪ መሀል ላይ የነበረውን የኤር ባግ ደህንነት ሲስተም መሪው ላይ በማድረግ የፈጠረውን ሲስተም አቀረበ።

የህ የሲስተም ለውጥ ለአምራቾች ደህንነትን ሳይቀንሱ የተሻለ የዲዛይን ነፃነት እነዲኖራቸው የተደረገ ነው።

በዝህ ሲስተም የመሪው መሀል እንደ ሬድዮ፣ መስኮቶችን እና AC የመሳሰሉትን ነገሮች መቆጣጠሪያ ቦታ መደረግ የሚቻል መሆኑን ZF LifeTech ተናግሯል። 

#ZF #ZFLifeTech #Airbag
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

SAIC-GM እራሱን በራሱ የሚነዳ መኪና መፈተኛ ፕላትፎረም ለቀቀ።


RoboTest በሚባል የተሰየመው አዲሱ የመፈተኛ ፕላትፎርም ጥራትን ከጉድለት በጥንቃቄ እና በፍጥነት ለይቶ መሻሻልና መቀየር ያበትን በቀላሉ አቅርቦ ያሳያል።

የህ ፕላትፎርም በጥንቃቄ በመስራቱ እራስን በራስ ለሚነዱ መኪኖች አካባቢን ለመረዳት የሚያስፈልጋቸውን ራዳር፣ ካሜራ፣ ሴንሰር እና የመሳሰሉትን ሲስተሞች ያሟላ ነው።

ፕላትፎረሙ ለመንገድ ላይ ደህንነት ካለው ጥቅም በተጨማሪ ለሪሰርች እና ማሻሻል የሚወስደውን ጊዜ በጣም ይቀንሳል።

ከዚያም በተረፈ በSAIC-GM 100% ሞዴሎች ላይ እነደሚሰራ ተነግሯል።

#SAIC #GM #autonomousdriving
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Ad

Yango Pro ላይ ለአሽከርካሪዎች ከማርች(march) እስከ ጁን(june) በሚያደርጓቸው ጉዞዎች እና ጥሪ ተቀብሎ በማጠናቀቅ ተመን (completion rate) ላይ ከፍተኛ መሻሻል ላሳዩ 10 ሹፌሮቻችንን ተጨማሪ አስገራሚ ሽልማቶችን ይዘን መተናል ።ለዚህ ወር ልዩ የሆነው ሽልማት፦ ከነ ቤተሰብዎ የሚዝናኑበት የኩሪፍቱ ወተር ፓርክ መግቢያ ትኬት ነው ::


አሽከርካሪዎች አፑን ለመጫን ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
bit.ly/4bEE8m8

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ገፃቸው
https://www.tg-me.com/YangoETH

እንዲሁም የፌስቡክ ገፃቸው
https://www.facebook.com/groups/1171500204006823
#Yango_pro #Earnings #Driving
#ዜና

Rivian የR1S እና የR1T ሞዴሎቹ ላይ ማሻሻያ አደረገ።


አዲሱ Rivian የመልክ ለውጥ ባይኖረውም የሀይልቁጠባ እና የጉልበት መጨመርያ ማሻሻያዎችን አግኝቷል።

በቀድሞ በ2 ሞተር ይቀርብ የነበረው R1 ከማሻሻል በተጨማሪ በአዲሱ ሞዴል በ3 እና በ4 ሞተር ማግኘት የምንችል መሆኑንም ተናግረዋል።

2 ሞተር የተገጠመለት R1 665 የፈረስጉልበት ሲኖረው ከ0 ወደ 100 ኪሎሜትር በሰአት በ3.4 ሴከንድ መድረስ ይችላል።

ባለ3 ሞተሩ ደግሞ 850 የፈረስጉልበት እና ከ0 ወደ 100 ኪሎሜትር በሰአት በ2.9 ሴከንድ የሚደርስ ፍጥነት አለው።

በመጨረሻም ባለ 4 ሞተሩ Rivian በ1025 የፈረስጉልበት እና ከ0 ወደ 100 ኪሎሜትር በሰአት በ2.5 ሴከንድ መድረስ ይችላል።

#Rivian #R1 #EV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Mercedes-Benz አዲሱን Zetros ክፍያ በአዲሱ Zetros 8x8 አጠናቀቀ።


በሚመጡት አመታት Zetros በ4፣ 6፣ እና በ8 wheel drive የሚቀርብ እና ለደህንነት ተጨማሪ ድገፋ የተደረገለት ጋቢና ይኖረዋል።

በአዲሱ Zetros, Mercedes-Benz ፖርትፎልዮ በማስፋፋት እና ለመከላከያ እገዛማድረግ ችሏል።

የሚጠቀመው የ510 የፈረስጉልበት እና 2300 Nm torque ያለው የ6 ሲሊንደር ናፍጣ ሞተር ነው።

Mercedes-Benz ይህን መኪና እና ሌላም የተለያዩ ለመከላከያ ሚሆኑ መኪኖችን June 17 2025 ላይ ያሳያል።

#Mercedes #Zetros #Military
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volvo የ13% የሽያጭ እድገት ማስመዝገቡን ተናገረ።


Volvo በMay ወር ውስጥ 68,034 መኪና በመሸጥ ባለፈው አመት በዚሁ ጊዜ ከሸጠው 60200 መኪና ማሻሻያ ማድረጉን ገለፀ።

ይህ የሽያጭ መጨመረ በአውሮፓ ሀገራትውስጥ ባሳዩት ጠንካራ የስራ አፈፃፀም ከመሆኑም በተጨማሪ ገበያው ላይ EX30 በማስገባታቸው የመጣ ነው።

በተጨማሪም የኤሌክትሪክ እና የሀይብሪድ መኪና ሽያጫቸውም የ37% ማሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል።

ከአመቱ መጀመሪያ እስከ May ወር ድረስ ወደ 320,000 ገደማ የሚሂኑ ሸያጮችን ማስመዘገባቸውንም አሳውቀዋል።

የVolvo ዳይሬክተር የሆኑት Björn Annwall “በዚህ ወር ያሳየነው ማሻሻል በአመቱ መጨረሻ ከአምና በ15% ለማሻሻል ያቀደወነውን እቅድ ያንፀባርቃል” ሲሉ ተናግረዋል።

#Volvo #sales
@OnltAboutCarsEthiopia
#ዜና

Ford በኤሌክትሪክ ላይ ልምዱ ያላቸውን 300 ሰዎች ይዞ በዋጋ ቀነስ ያለ ኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማምረት እየሞከረ ነው ::


ቴክ ክራንች ሊንክዲን ላይ አንዳንድ መረጃዎችን ለማግኘት በሰራው ማጣራት መሰረት በካሊፎርኒያ ከተለያዩ ካምፓኒዎች የተውጣጡ ማለትም ከቴስላ ከሪቪያን ከሉሲድ ከአፕል እና ከ F1 የመጡ ኤሮዳይናሚክስ ላይ የሚሰሩ ሰዎችም የተካተቱበት ነው ::

ከእነዚህም ውጪ ፎርድ በቅርቡ ከገዛው Automotive Power (AMP) 100 ሰዎችን ከዛ ውስጥም አካቷል ::
Ford Advanced EV የሚል ስያሜም ተሰቷቸዋል :: ይህም Ford የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ከዚህ በፊት ሲሰራ ከነበረው አሁን በፍጥነት እና በተሻለ መልኩ ወደፊት መራመድ ያስችለዋል ::

#Ford
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

46% የሚሆኑት የኤሌክትሪክ መኪና ተጠቃሚዎች ወደ ነዳጅ መኪና መመለስ እንደሚፈልጉ በአሜሪካ የተደረገ ጥናት አመለከተ


አሁን ላይ በብዛት አብዛኛው ሰው በአለም ዙርያ ከነዳጅ መኪኖች ወደ ሀይብሪድ እና ኤሌክትሪክ መኪኖች መኪኖቹን እየለወጠ ይገኛል :: ታዲያ በቅርቡ በሚኬንዚ በተደረገ ጥናት መሰረት 46% የሚሆኑ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙት የኤሌክትሪክ መኪና ተጠቃሚዎች ቀጣይ መኪና መግዛት ሲያስቡ ወደ ነዳጅ መኪኖች እንደሚመለሱ ነው ጥናቱ ያመላከተው ::

ታዲያ ለዚህም ዋነኛው ምክንያት የቻርጅ ማድረጊያ መሰረተ ልማቶች ደስተኛ ባለመሆናቸው እና መኪኖቹ የሚገዙበት ዋጋ ውድ መሆኑ ከነዳጅ መኪኖች ጋር ሲወዳደር እንዲሁም ረዥም ጉዞ መጟዝ አለመቻላቸው መሆኑ ተገልጿል ::

ምንም እንኳን 46% አሜሪካ ውስጥ ይሁን እንጂ በአለም አቀፍ ደረጃ 29% የሚሆኑት የኤሌክትሪክ መኪና ተጠቃሚዎች ወደ ነዳጅ መኪኖች መመለስ እንደሚፈልጉ ጥናቱ ያሳያል ::

9% የሚሆኑት የኤሌክትሪክ መኪና ተጠቃሚዎች በቂ የቻርጅ ማድረጊያ መሰረተ ልማቶች መኖራቸውን ሲገልፁ በአለም አቀፍ ደረጃ 21%  የሚሆኑ ሰዎች መቼም የኤሌክትሪክ መኪና እንደማይገዙ ገልጸዋል :: 38% ደግሞ የሚሆኑ ነዳጅ መኪኖችን የሚጠቀሙ ሰዎች ቀጣይ የሚገዙት ኤሌክትሪክ ወይም ሀይብሪድ እንደሆነ ተናግረዋል ::

#EV #ICE
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Alpine አዲስ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራ A290 የተባለ ከ Renault 5 ጋር የሚወዳደረውን መኪና ለእይታ አቀረበ ::


በ 2022 ላይ Renault Alpine ድጋሚ ወደ ገበያ በማሰብ Alpine A110 በብዙዎች ዘንድ በጣም ጥቂት የስፖርት መኪኖችን ብቻ የሚያመርት የመኪና አምራች ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር :: ግን Alpine ከሱም ያለፈ እቅድ ነበረው ::

እናም አሁን ላይ ሌላኛውን A290 የተባለው ሞዴል አውጥተዋል :: ይህም የ Hot Hatch ምድብ ውስጥ የሚካተት ሲሆን ከ Renault 5 ጋርም የሚቀናቀን ይሆናል ::

ሁለት አማራጮችን ያቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው 180 የፈረስ ጉልበት ሲኖረው ሁለተኛው ደግሞ 220 የፈረስ ጉልበት አለው :: ከ 0 እስከ 100 ኪሎሜትር በሰአት ለመድረስ 6.5 ሰከንዶች ይወስድበታል ::

ወደ ዋጋቸው ስንመጣ ቤዝ ሞዴሉ 41,000 የአሜሪካን ዶላር ሲሆን በ 52 KWh ባትሪ ፓክ ሲመጣ 380 ኪሎሜትር በአንድ ቻርጅም ይጟዛል ::

#Alpine #A290 #Renault
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

4 ለማደስ ብዙ ብር የሚያስወጧችሁ የመኪና ብራንዶች


አንዳንድ መኪኖች ከገዛችሗቸው በሗላ ምንም እንኳን አዲስ ቢሆኑም ጥገና ሊፈልጉ ይችላሉ :: ወይም ደግሞ ቶሎ የሚበላሽ ፓርት ሊኖራቸው ይችላል :: በአማካይ አንድ መኪና በአመት ወደ 900 ዶላር (~55,000 ብር) በ Consumer Affair ጥናት እንደሚያሳየው ያወጣል ::

ይህም ለመጀመሪያዎቹ አስር አመታት ሲሆን ይህም በአመት 2 ጊዜ ዘይት መቀየር, ጎማዎቹን ቦታ ማቀያየር, አዲስ የዝናብ መጥረጊያ, ፊልተሮቹን መቀየር, አላይመንት እና ፍሬን ሸራ መቀየርን ያካተተ ነው ::

በ Go Banking Rates መረጃ ከሆነ Porsche በ 2,207 ዶላር በአመት በማስወጣት ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ BMW በ 1,931 ዶላር የሁለተኛነትን Land Rover በ 1,856 ዶላር የሶስተኛነትን እና Jaguar በ 1,763 ዶላር የአራተኝነትን ቦታ ይዟል :: ሁለቱ የጀርመን ሁለቱ ደግሞ የእንግሊዝ መኪኖች ናቸው :: በእነዚህ ብራንድ ስር ያሉትን መኪኖች ስትገዙ አውቃችሁ ብትገዙ የተሻለ ነው በሚል ነው ::

#porsche #land_Rover #BMW #Jaguar
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ፈጣን ቻርጀሮች ባትሪውን ይጎዳል ብላችሁ ታስባላችሁ?


በቅርቡ የቴስላ መኪኖች ላይ በተደረገ ጥናት ወደ 13,000 መኪኖችን በመውሰድ የሞከሩት ሲሆን መኪኖቹ ላይ የተጋነነ ለውጥ እንዳላዩም በመረጃ አስደግፈው አቅርበዋል ::

በፈጣን ቻርጀር ቻርጅ የሚያደርጉት ከ 70% በላይ ከሆነ ያ ማለት በወር ውስጥ 10 ጊዜ ቻርጅ ቢያደርጉ እና ከ 7 በላይ ቻርጅ የሚያደርጉት በፈጣን ቻርጀር ከሆነ 30% ባትሪው ይቀንሳል :: ግን አብዛኛው ሰው እቤቱ ባለው ቻርጀር ነው በብዛት ቻርጅ የሚያደርገው ::

344 ሰዎች ናቸው ከ 70% በላይ መኪኖቻቸውን በቴስላ ፈጣን ቻርጀሮች ቻርጅ የሚያደርጉት :: የተሞከሩትም መኪኖች ከ 2012-2023 ድረስ ሲሆኑ 90% የሚሆኑት መኪኖች ግን ከ 2018 ወዲህ ያሉት ናቸው ::

#DC-Fast_Chargers #Ev
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አል-አድሃ(አረፋ) በዓል በሰላም በፍቅር በጤና አደረሳችሁ አደረሰን

መልካም በዓል ተመኘን 🙏
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

በ 2023 10 በብዛት የተሸጡ ሞዴል መኪኖች

1. Tesla Model Y (1,223,000 መኪኖች)
2. Toyota RAV4 (1,075,000 መኪኖች)
3. Honda CR-V (846,000 መኪኖች)
4. Toyota Corolla (803,000 መኪኖች)
5. Toyota Corolla Cross (715,000 መኪኖች)
6. Toyota Camry (650,000 መኪኖች)
7. Ford F-150 (623,000 መኪኖች)
8. Toyota Hilux (605,000 መኪኖች)
9. Nissan Sentra (534,000 መኪኖች)
10. Tesla Model 3 (508,000 መኪኖች)

ምንጭ - Jato Dynamics

ታዲያ እናንተም መኪናችሁን መሸጥ ከፈለጋችሁ ያለኮሚሽን 300 ብር ብቻ በመክፈል @hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ በመላክ ሁሌመኪና ላይ በማስተዋወቅ መሸጥ ትችላላችሁ ::
@hulemekina ላይ ከ 350 ሺህ ብር ጀምሮ የሚሸጡ መኪኖችም አሉ ::

@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Fiat Panda በሀይብሪድ እና ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ የሆኑ አማራጮችን አቀረበ።


Fiat Panda እነዚህን መኪኖች በአውሮፓ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ እንደሚያቀርቡት ተናግረዋል :: ከ Citroen C3 እና Vauxhall Frona ጋር ተመሳሳይ ፕላትፎርም ሲሆን ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው መኪናም ይሆናል ተብሏል :: የ Citroen C3 ሀይብሪድ በ 15,000 ዩሮ እና ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ ከ 30,000 ዩሮ ባነሰ ዋጋ እየተሸጡ ይገኛል ::

የ Fiat Panda የሞተር አማራጮቹም በ 1.2 ሊትር ቱርቦቻርጀር ያለው እና 48 Volt ኤሌክትሪክ ሞተር የተካተተበት DCT ሀይብሪድ ሲሆን ኤሌክትሪክ ሞዴሎቹ ደግሞ በ 44 Kwh  LFP (Lithium iron Phosphate) ባትሪ ላይ 83 Kw, 113 የፈረስ ጉልበት እና በአንድ ቻርጅ 300 ኪሎሜትር እና ተለቅ ያለው ባትሪ ላይ እስከ 400 ኪሎሜትር ይጟዛል ::

#Fiat #panda
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

50% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው መኪኖች ከጉብማውንት ኢምፖርት እና ኤክስፖርት

2024 Changan estar

በተመጣጣኝ ዋጋ የምታገኙት ሙሉ በሙሉ የሆነው ይህ መኪና ይበልጥ ለእናንተ ባላችሁ ገንዘብ መግዛት እንድትችሉ በማሰብ ጉብማውንት ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ድርጅት 50% ብቻ ከከፈላችሁ 50% የባንክ ብድሩን እኛ እናመቻቻለን እያሉ ነው ::
ባትሪው 32 Kwh በአንድ ቻርጅ የምትመለከቱት 310 ኪሎሜትር ይጟዛል ::
ምን አልባት ለግል ለቤት ወይም ደግሞ ለራይድም መጠቀም ካሰባችሁ ለሁሉም ይሆናል ::
መኪኖቹን በአካል ማየት ከፈለጋችሁ በ 0943703030 ላይ ጉብማውንት ኢምፖርት እና ኤክስፖርት በመደወል አዲሱ ገበያ መኪኖቹን መመልከት ትችላላችሁ ::

ሙሉ ሪቪው ከስር በምታገኙት ሊንክ ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/9gJNRRhPNb0

ግሩም ከሰአት ተመኘን
#Changan #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቶታል ኢነርጂስ ኢትዮጵያ የነዳጅ ማደያ ላይ የመጀመሪያውን ኤሌክትሪክ ቻርጀር ለኤሌክትሪክ መኪኖች በአዲስ አበባ ገጠመ

የኤሌክትሪክ መኪኖችን መብዛት ተመልክቶ ቶታል ኢነርጂስ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጀሮችን በነዳጅ ማደያቸው መግጠም ጀምረዋል :: ይህም ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ ያስመረቁ ሲሆን የተገጠመውም ቻርጀር ፈጣን ቻርጀር ሲሆን ምን ያህል እንደሚያስከፍሉ እስከአሁን የወጣ ነገር የለም ::

አሁን ላይ ከ 100,000 በላይ ኤሌክትሪክ መኪኖች በሀገራችን ሲገኙ ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች የሉም በሚባል ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው ያሉ ሲሆን በ 10 አመት ውስጥ 2,226 ቻርጀሮችን መግጠምን እንደእቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ::

ምንጭ - Shega

#EVCharger #TotalEnergies
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቻይና ውስጥ Mercedes 2,380 EQ Series ኤሌክትሪክ መኪኖችን እየተነዱ ሀይል ሊያጡ ስለሚችሉ በሚል ጠርቷቸዋል ::

የጀርመን ውድ መኪኖችን በማምረት የሚታወቀው Mercedes Benz ከ 2,000 የሚበልጡ ኤሌክትሪክ መኪኖችን ቻይና ውስጥ እንዲስተካከሉ ጠርቷል ::

በሶፍትዌር ችግር ምክንያት አንዳንድ መኪኖች ከ ትልቁ የመኪና ባትሪ ጋር ግንኙነትን ሊያቆሙ ስለሚችሉ ይህ ደግሞ እየተነዳ ሀይል ሊያጡ ስለሚያደርጋቸው ነው ::
መኪኖቹም 39 EQS SUV ከ November 28,2023 እስከ February 7,2024 ኢምፖርት የተደረጉ መኪኖች እና 2,341 EQE SUV ከ November 1,2023 እስከ April 25,2024 ቻይና ውስጥ የተመረቱት ናቸው ::

ይህ Mercedes ኤሌክትሪክ መኪኖችን ሲጠራ ለሁለተኛ ጊዜ ነው :: በሀገራችን እነዚህ መኪኖች በቁጥር ነው ያሉት :: ግን ያላቸው ሰዎችን የምታውቁ ይህንን መረጃ ሼር አድርጉላቸው ::

ምንጭ - CNEVPOST

#Mercedes #EV #China
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/06/27 09:07:25
Back to Top
HTML Embed Code: