Telegram Web Link
ትራፊክ እስቲከራችሁን እያስላጠ እየቀጣ ምርር አድርጟችሗል?

Omega Auto Glass የፋብሪካ ቲንትድ የፕራይቬሲ መስታወቶችን ለአዳዲስ መኪኖችንም ለቆዩትም ታገኛላችሁ ::
አድራሻ ሀብተጊዮርጊስ ድልድል ወደ አሊያንስ በሚወስደው መንገድ ላይ ፓልሪየስ ጎን ታገኙናላችሁ ::
ስልክ 0911241153 ወይም
0911609080 ወይም
0925494095 ይደውሉ ::

ውብ ቀን ተመኘን
#OmegaAutoGlass
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ታዋቂው የነዳጅ አቅራቢ shell አሜሪካ ላይ ያሉትን የሃይድሮጅን ነዳጅ ማደያዎቹን ሙሉ በሙሉ ዘጋቸው።


በቶዮታ ካምፓኒ በመጪዎቹ አመታት ገበያውን ይቆጣጠራሉ ብሎ ባመነባቸው የሃይድሮጅን ተሽከርካሪዎቹ ተነስቶ ከ Shell ማደያ ጋር በሽርክ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ አንዲከፈቱ ያደረጋቸውን የሃይድሮጅን ነዳጅ ማደያዎች ተጠቃሚ በማጣታቸው ምክንያት በኪሳራ ተዘጉ።
የሃይድሮጅን መኪኖችን ማበልፀግ ከተጀመረ 35 አመታት ቢቆጠሩም ዋጋቸው ውድ በመሆኑ እና እንደ ነዳጅ የሚጠቀሙት የሃይድሮጅን መሙያ ዋጋው ከፍተኛ በመሆኑ እንዲሁም መልሶ የመሸጫ ዋጋ (resale value) በጣም የወረደ መሆኑን አስከትሎ ገበያውን ሰብረው መግባት ባለመቻሉ ነው።

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Shell #Toyota #Hydrogen
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ሪቪው

ከ 30,000 ዶላር በታች የምታገኙት ኤሌክትሪክ ፒክአፕ ትራክ

Geely Radar RD6


በአለማችን ላይ ብዙ ሀገሮች ላይ ኤሌክትሪክ መኪኖችን ማግኘት አትችሉም :: ብታገኙም የምታገኙትም በአሜሪካ ውስጥ ነው :: እነሱም በጣት የሚቆጠሩ ሞዴሎችን ነው :: በብዛት ስለማይገኙ ዋጋቸው ውድ ነው :: ታዲያ Geely ይህንን በማሰብ የተሻለ የኪሎሜትር ሬንጅ ያለውን መኪና ለገበያ አቅርቧል :: ለገበያ ያቀረቡትም የተለያዩ አህጉራት ላይ ለመሸጥ ነው :: ምን አልባት ከባዱን የአውሮፓ ገበያ ውስጥም ሊገባ ይችላል ተብሏል ::

መሸጥ የጀመረው ነሀሴ 2015 ላይ ሲሆን አሁን ግን አሻሽለውት 2 ሞተር እና የ AWD(All Wheel Drive) አማራጭም አካተውበታል :: በተጨማሪም የተሻለ የመጎተት አቅም እና የተሻለ የእቃ ማስቀመጫ ቦታ እንዲኖረው አድርገዋል :: በፊት የሚይዘው 430 ኪሎግራም ብቻ ነበር :: አሁን ግን ከ 860 ኪሎግራም በላይ መሸከም ይችላል :: በእጥፍ አሳድገውታል :: እሱ ብቻ ሳይሆን መጎተት የሚችለውንም በፊት ከነበረው ከ 2.5 ቶን ወደ 3 ቶን ከፍ አድርገውታል :: ስለዚህ ይህንን በብዙ ሀገሮች የሚሸጠው የመጀመሪያው ኤሌክትሪክ ፒክአፕ ትራክ ይሆናል ::

ምክንያቱም ዋጋው በጣም አሪፍ ስለሆነ ነው :: መነሻ ዋጋው ቻይና ውስጥ ከ 30,000 ዶላር ያነሰ ነው :: 3 አይነት የባትሪ አማራጭ ሲኖረው በ 63 በ 86 እና በ 100 KWh ባትሪ ፓክ የሚገኝ ሲሆን በ CATL የባትሪ አምራች የተመረቱ Lithium Ion phosphate የተገጠመላቸው ናቸው :: በ 410 ኪሎሜትር በ 550 ኪሎሜትር እና በ 632 የ ኪሎሜትር አማራጮች ነው የሚገኙት ::

Maxus T90 EV መኪና ቻይና እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ላይ እየተሸ ያለ ግን እሱ ከ Internal Combustion engine ወይም ከነዳጅ ወደ ኤሌክትሪክ የቀየሩት ስለሆነ ብዙም አሪፍ አልነበረም ::አሁን ግን ኤሌክትሪክ እየሰሩ ነው ከ Radar RD6 የተሻለ:: የ Mg Sub Brand ነው Maxus እሱ ሲወጣ የምናየው ይሆናል ::

Radar RD6 0-100 ኪሎሜትር በሰአት ለመድረስ 4 ሰከንዶች ይፈጁበታል :: 400 KW ከፊት እና ከሗላ ሞተሮች ላይ ሲኖረው 600 የፈረስ ጉልበት ያለው መኪና ነው :: እስከ 6 Kw የሆነ ማንኛውንም እቃ ማንቀሳቀስ ይችላል :: እና ሌላም መኪና ቻርጅ ማድረግም ይችላል :: በአጠቃላይ 61.5% ማርኬት ሼር ሲኖራቸው አሁንም እያደገ እየመጣ ነው ::

እኛ ሀገር ቢመጣ አሪፍ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?
እስኪ ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

ልዩ ምሽት ተመኘን
#EV #Geely
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BMW ኤሌክትሪክ ሞዴላቸው ላይ ለባትሪ ቅያሪ እየጠየቁ ያሉት ገንዘብ ብዙ ስለሆነ ባለንብረቶች ቁጣቸውን አሰሙ።

Bmw ኤሌክትሪክ መኪና ተጠቃሚዎች በ BMW ካምፓኒ በኩል ለባትሪ ጥገና እና ለመቀየር እንደ መኪናው ሞዴል እና አይነት ቢለያይም BMW i3 ሞዴላቸው ላይ እየተጠየቁ ባለው ከ 30 ሺህ እስከ 70 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ ቁጣቸውን አሰሙ።

እንደሚታወቀው የባትሪ ፓክ ዋጋ በፊት በነበረበት ቅናሽ እያሳየ ነው፡ ባለፈው አመት ብቻ በ 40% ያህል ባትሪ ላይ ቅናሽ አሳይቷል። ነገር ግን የመኪና አምራች ካምፓኒዎች ባትሪዎቹን ከባትሪ አምራች ካምፓኒዎች በርካሽ እያገኙ ቢሆንም ለጠተቃሚዎች ባትሪ ጥገና እና ለቅያሪ እየጠሩት ያለው ዋጋ በጣም የተጋነነ ነው ብለዋል።

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#BMW #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Kia አዲሱን Stinger መኪናቸውን ወደ ኤሌክትሪክ ቀይረውታል ::

በ2025 ለገበያ እንደሚቀርብ የተነገረለት የ kia (muscle car) kia stinger ከዚህ በፊት እንደነበረው የነዳጅ ተጠቃሚ መሆኑ ቀርቶ ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ ተቀይሮዋል።

አዲሱ kia stinger ላይ በዋጋው ቀነስ ያለ እና የተሻለ ፐርፎርማንስ ያለው የሊቲየም አየን ባትሪ እንደሚገጠምላቸው የተነገረ ሲሆን በአንድ ቻርጅ እስከ 700 ኪሎሜትርም ይጓዛሉ።

ከፊት ባለ 200 kilowatt ሞተር ከኋላ ደግሞ ባለ 250 Kilowatt በድምሩ 450 Kilowatt ሞተር ሲሆን የተገጠመላቸው ወደ 603 የፈረስ ጉልበት ያመነጫሉ ::

ውብ ከሰአት ተመኘን
#Kia #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BYD ዝቅተኛ የሚባለው የኤሌክትሪክ መኪናውን በደቡብ አሜሪካ ገበያ በ 20,000 ዶላር አቀረበው።

Byd ባለፈ አመት May ላይ ያወጣው ሲጉል የሚባለውን ሀችባክ መኪናው በሽያጭ ከካምፓኒው ሞዴሎች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን ታዋቂ የሆኑትን Dolphin እና Yuan plusን በመብለጥ ባለፈው አመት በቻይና ገበያ ላይ ብቻ ከ280,000 በላይ መኪኖች  ሽጠዋል ።

ሲጉል ቻይና ላይ በሁለት አማራጮች የቀረበ ሲሆን, base ሞዴሉ በ 30 kwh ባትሪ ፓክ እስከ 305 ኪሎሜትር መሄድ ሲችል ሌላኛው ደግሞ በ 38kwh ባትሪ ፓክ አስከ 405 ኪሎሜትር መጟዝ ይችላል።

ኢትዮጵያ ውስጥም ከገቡ ጥቂት ጊዜ ቢሆንም ግን ደግሞ ተፈላጊ ናቸው :: ስለእነዚህ መኪኖች ቪዲዮ መስራት ስለምንፈልግ ያላችሁ በ 305 ኪሎሜትር እና በ 405 ኪሎሜትር የሚሄዱት መኪኖች ያላችሁ በ @MacMono የቴሌግራም አካውንት ላይ ቴክስት ላኩልን ::

ድንቅ ቀን ተመኘን
#BYD #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ጠቃሚ_መረጃ

Ceramic Coating ምንድነው?

ውሀ የሚመስል ፈሳሽ ግን ደግሞ ከመኪናችን ቀለም ጋር በመዋሀድ የመኪናው ቀለም በዋናነት ተጨማሪ Layer በመሆን ከፀሀይ ይከላከልልናል ::

ጥቅሙ ምንድነው ?

መኪናው ላይ ከ ፀሀይ ከ UV Ray ከ ወፍ ኩስ ከዛፍ ላይ ከሚወርዱ ትንንሽ እንጨቶች ወይም ቅጠሎች እና ከትንንሽ ጭረቶች የሚመጡትን ነገሮች የመኪናውን ቀለም እንዳይጎዱት በደንብ ይጠብቃል ::

Ceramic Coat መኪናችሁ ላይ ሲደረግ shine የማድረግ እና Smooth የሆነ surface እንዲኖረው ስለሚያደርግ መኪናችሁን ለማፅዳትም ቀላል ያደርገዋል :: ብዙ Ceramic Coating የሚሸጡ ካምፓኒዎች ሲያስተዋውቁ በደንብ የሚያስተዋውቁት ውሀ እንዲሁም ቆሻሻ ወይም ጭቃ የመኪናው ቀለም ላይ ይዞ እንደማይቆይ ነው :: አንዴ ተጠቅመነው ከ ሁለት እስከ አምስት አመት ድረስ ይቆያሉ :: እንዳያያዛችን የአመቱን ጊዜ ማስረዘምም ማሳጠርም እንችላለን :: ከ PPF ጋር ያለው ልዩነት ምን ይመስላችሗል?

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#CeramicCoating
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ያሉ ሁሉም ከተሞች አዲስ ነዳጅ ማደያ እንይገነባ ፍቃድ ከለከሉ

የወርቃማ ግዛቷ ዋና ከተማ የሆነችው Sacramento ለነዳጅ ማደያ ፍቃድ የከለከች የመጀመሪያዋ ከተማ ስትሆን ክልከላው በስራ ላይ ያሉትም ማደያዎች አዲስ የነዳጅ ዲፖ እንዳይገጥሙ እና እንዳያስፋፉ ጭምር ያገደ ነው።

ይሄንን ፍቃድ ግን በአንድ ቅድመ ሁኔታ ማግኘት እንደሚቻል የገለፁ ሲሆን ቅድመ ሁኔታውም አንድ የነዳጅ ፓምብ በተከሉ ቁጥር አብረው አንድ ባለ 50 Kilowatt DC ፈጣን ቻርጀር አብረው መትከል ይጠበቅባቸዋል።

የዚህ ህግ መውጣቱ ዋና አላማው በታዳሽ ሃይል የሚንቀሳቀሱ እና eco-friendly የሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ስቴሽን እንዲገነባ እና በመጪው አመታት ላይ ለሚመጡ የፍላጎት እና የአቅርቦት አለመመጣጠን እልባት ለመስጠት ታስቦ ነው ብለዋል።

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#GasStation
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በጃፓን የመኪና አምራች ካምፓኒዎች ላይ እየወጣ ያለ የሀሰት መረጃ

እንደ ቶዮታ፣ማዝዳ፣ኒሳን እና ሱባሩ ጨምሮ ሁሉም የጃፓን የመኪና አምራቾች ባለፈው 12 ወራት ውስጥ በኤሌክትሪክ መኪኖች ካስገቡት ገቢ ተነስተው ሶሊድ ስቴት ባትሪ ወደሚጠቀሙ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደማምረት 100% ሺፍት ለማድረግ በጣም ትልቅ የሚባል በጀት በጅተዋል :: ምክንያቱም በመጪው 5 አመታት ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪኖች ፍላጎት በከፍተኛ ቁጥር ስለሚጨምር ነው ተብሎ እየተዘዋወረ ያለው መረጃ ከእውነታው የራቀ ነው ::


የኤሌክትሪክ መኪኖችን ማምረት ላይ ኢንቨስት እያደረጉ ቢሆንም እንዲህ አይነት ትልቅ ለውጥ ቀርቶ አንዳቸውም እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ በ50% እራሱ ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች ሺፍት የማድረግ ሃሳብ የላቸውም።

የእረፍት ቀን ተመኘን
#Japan #EV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በአሜሪካ እየተሸጡ ያሉ የ ቶዮታ፣ ሌክሰስ እንዲሁም የ ሱባሩ ኤሌክትሪክ መኪኖች ያገለገሉ መኪኖች ዋጋቸው በጣም እየቀነሰ ነው

እንደ Toyota BZ4X እና Lexus RZ450E ያሉ መኪኖች አሜሪካ ውስጥ 5,000 እስከ 10,000 ኪሎሜትር ከተነዱ በሗላ መልሶ ለመሸጥ እስከ 40% የዋጋ ልዩነት እያሳዩ ነው :: ይህ መሆኑ ሰዎች አዳዲስ መኪኖቻቸውን ከመግዛት እየተቆጠቡ ነው ብለዋል ::

ምንም እንኳን ባለፉት 3 አመታት ብቻ አሜሪካ ውስጥ 356% የኤሌክትሪክ መኪና ሽያጭ ጭማሪ ቢያሳያም ግን ደግሞ መልሰው ሲሸጡ አንዳንድ ሞዴሎች ዋጋቸው በጣም እየቀነሰ ይገኛል :: የ Subaru Soltera ሞዴል መኪና የተሻለ መልሶ የሚሸጥበት ዋጋ ቢኖረውም ግን እሱም ዋጋው ላይ ቅናሽ እንደሚያሳይ ገልጸዋል ::

ወደ ሀገራችን ስንመጣ የኤሌክትሪክ መኪና ላይ መልሶ የመሸጫ ዋጋው ከነዳጅ መኪኖች ሲወዳደር ይቀንሳል :: ይህ ጥሩ ነው ብለን እናስባለን :: እናንተስ ምን ታስባላችሁ? ወደፊት ያገለገሉት ኤሌክትሪክ መኪኖች መልሶ የመሸጥ ዋጋቸው በ% ከአሁኑ የሚጨምር ወይስ የሚቀንስ ይመስላችሗል?

የተለየ ሰኞ ምሽት ተመኘን
#Japan #EV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ ሞዴል 2 ጀርመን በርሊን ውስጥ በሚገኘው የቴስላ ካምፓኒ ማምረቻ በሆነው ቅጥር ግቢ ውስጥ ታየ


በቴስላ ካምፓኒ በቀጣይ አመት ላይ ኪስ በማይጎዳ ዋጋ ለገበያ ይወጣል ተብሎ ተነግሮ የነበረው እና ስለ ሞዴሉ በሚስጥር ተይዞ የነበረው መኪና ቴስላ ሞዴል 2 ሳይሆን አልቀረም እየተባለ ነው።

ሞዴል 2 ባለፉት 2 አመታት ውስጥ ቻይና በሚገኘው የቴስላ ዲዛይን ቲም አማካኝነት ዲዛይን ሲደረግ የነበረ እና ከሞዴል Y ጋር ትንሽ መመሳሰል ያለው ወደ ምርት ያልገባ ሃች ባክ መኪናቸው ነው።

ድንቅ ከሰአት ተመኘን
#Tesla #EV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Porsche, Bentley እና audi ቻይና ውስጥ ለሚያመርቷቸው የመኪኖቻቸው ክፍሎች የሰራተኞችን ጉልበት አለአግባብ በመበዝበዛቸው አሜሪካ ውስጥ እገዳ ተጣለባቸው

የአሜሪካው መንግስት እንደገለፀው ከሆነው የቮልስ ዋገን ግሩፕ የሆኑት እነዚህ መኪኖች ቻይና ላይ ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ከአስር አመታት በላይ ሰራተኞችን ካምፕ ውስጥ አስረው ያለ ፍላጎታቸው እያሰሩ ጉልበታቸውን ሲበዘብዙ ነበር ብሎዋል።

ካምፓኒው ህግ እንዳልጣሰ እና ይሄ ነገር ሃሰት ነው ብሎ ቢሞግትም ትላልቅ ሚዲያዎች ግን አሁንም ስለ እውነትነቱ እየዘገቡ ነው።

በ ቮልስ ዋገን ግሩፕ ስር የሚመረቱት እነዚህ ቅንጡ መኪኖች በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ስማቸው ሲነሳ የመጀመሪያው ባይሆንም የአሁኑ ግን ጠንከር ያለ እና ክስም እንደሚመሰረትባቸው ተነግሯል።

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#VW #China
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

4 የአሜሪካ የመኪና አምራች ካምፓኒዎች ትልቅ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል

መኪኖቻቸውም በየመሸጫዎቹ ተቀምጠው አቧራ እየጠጡ ነው

Ram, Jeep, Chrysler እና Dodge የተባሉት እና በአንድ ካምፓኒ ውስጥ የታቀፉት የመኪና አምራቾች ባለፉት አመታት ውስጥ በከፍተኛ ቁጥር መኪኖችን በማምረት የሚታወቁ ሲሆን ከኮቪድ 19 በሗላ ከአየር ንብረት ጋር ተያይዞ በወጡ ህጎች በዋጋቸው ውድነት ጋር ተደማምሮ የፈላጊያቸው ቁጥር እጅጉን አሽቆልቁሏል።

በአሜሪካ ብቻ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የነዚህ ካምፓኒ መኪኖች ቆመው አቧራ እየጠጡ ሲሆን ይሄም በቢሊየን ዶላሮች የሚገመት ኪሳራ ውስጥ እንደሚከታቸው ተነግሯል።

አጋጣሚው ለሸማቾች ጥሩ እድል የከፈተ ሲሆን በየሳምንቱ እነዚህ መኪኖች ላይ የ 1% ቅናሽ እየተደረገ ነው።

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Jeep #Dodge
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nio በቀን 90,199 የኤሌክትሪክ መኪኖችን ባትሪ ቀየረ ::

እንደምታስቡት ተበላሽቶ ሳይሆን መኪኖቹን ከገዛችሁ በሗላ ቻርጅ ለማድረግ ብዙ ሰአት እንዳትጠብቁ በማሰብ ነው :: Nio የቻይና ኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች ካምፓኒ ባትሪዎችን እንደሚቀይር ይታወቃል :: በጣም በተጨናነቀበት ቀን በአንድ ቀን 90,199 ሰርቪስ እንደሰጠ ተናግሯል :: በአንድ እስቴሽን ደግሞ በቀን እስከ 195 ሰርቪሶችን እንደሰጠም ተዘግቧል ::

ከ ፌብራሪ 8-18 ብቻ 871,477 ባትሪዎችን ቀይረዋል :: ይህም ሀሳብ ወደ ሀገራችን መቶ ተግባራዊ ቢሆን የተሻለ ይመስለኛል :: ምን ታስባላችሁ?

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Nio #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቢልጌት በአለማችን ትልቁ የመርከቦች መናሃሪያ በሆነው ቦታ ላይ በኒኩለር ሃይል የሚንቀሳቀስ መርከብ መገንባት ጀመረ።

የቢልጌት ካምፓኒ የሆነው Terra Power ከአለማችን ትልቁ የመርከብ አምራች ካምፓኒ ከሆነው HD Korea shipbuilding & offshore engineering(KSOE)  ጋር በጋራ በመሆን በኒኩለር ሃይል የሚንቀሳቀሱ መርከቦችን በመገንባት ላይ ነው።

ይሄም ግንባታ አልቆ እውን በሚሆንበት ጊዜ በነዳጅ እና በድንጋይ ከሰል የሚንቀሳቀሱ መርከቦችን ያስቀራል ተብሎ የሚታመን ሲሆን አሁን ላይ ካሉት መርከቦች አንፃር በጣም ረዥም ጉዞዎችን  በአንዴ ማካሄድ የሚችል ሲሆን በጉልበትም ሆነ በፍጥነት በጣም የተሻለ ነው። ከአየር ንብረት አንፃርም ወደ ከባቢ አየር የሚለቀው ምንም አይነት ነገር ስለሌለ ተመራጭ ያደርገዋል ።

ውብ ቀን ተመኘን
#Billgate #Nuclear
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቴስላ ካምፓኒ ኢንጅነሮች የቴስላ መኪኖች ላይ ብዙ ቅሬታ ሲቀርብበት የነበረውን ችግር በማስተካከል ላይ እንደሆኑ ገለፁ።

የቴስላ መኪኖች መስታወት መጥረጊያ ማኑዋል ሞድ ላይ በትክክል ስራውን የሚሰራ ቢሆንም auto ላይ በምናደርግበት ወቅት በፀሃያማ ቀናቶች ጨምሮ እራሱን activate እያደረገ መስራቱ ለአመታት ብዙ ሰዎች ቅሬታ ሲያቀርቡበት የነበረ እክል ሲሆን የቴስላ ካምፓኒ  ለዚህ ችግር እልባት እንዳበጀ የገለፀ ሲሆን በጣም በቅርቡ software update እንደሚለቅ አስታውቆዋል።

ውብ ቀን ተመኘን
#Tesla #Ev
@OnlyAboutCarsEthiopia
የ 2024 የመጀመሪያው የ City Circuit የመኪና ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

ቦታው - Kilinto Industrial Park ውስጥ ነው የሚሆነው ::
ትኬት በር ላይ ይሸጣል
ሊፍት መስጠት የምትችሉ ሰዎች ኮሜንት ላይ አውርታችሁ አንድ ላይ መምጣት ትችላላችሁ :: ለትውውቅም አሪፍ እድል ይሆንላችሗል ::
በተለይ ደግሞ እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ላይ ተወዳዳሪዎቹን በምታቀርቧቸው እስፔር ፓርት ማገዝ እንዲሁም እስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ በ 0911663121 ላይ ይደውሉልን ::

እሁድ እዛው እንገናኝ

ግሩም ምሽት ተመኘን
#CarRace #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Elon musk እና የtesla ኢንጂነሮች የቴስላ ሳይበር ትራክ እየዛገ አይደለም ብለው አስተባበሉ።

ሰሞኑን ብዙ ትላልቅ ሚዲያዎች ሲቀባበሉት የነበረው በ stainless steel የተሰራው የቴስላ ሳይበር ትራክ ቦዲ ላይ በተፈጠረው ዝገት መሳይ ብርቱካናማ ነገር የ ቴስላ ካምፓኒ ባለቤት የሆነው elon musk እና የቴስላ ኢንጂነሮች መልስ ሰጡ።

ባለፈው አመት ኖቬምበር ላይ ለገበያ የወጣው ሳይበር ትራክ እንደ መኪና በዝናብ እና በውሃ ለመበላሸት በጣም አጭር ጊዜ እና በተሰራበት ማቴሪያል stainlessness steel(የማይዝ ብረት) አማካኝነት ዝገት መሳይ ነገር መፈጠሩ ብዙ ተጠቃሚዎቹን ያስቆጣ የነበር ቢሆንም እንጂነሮቹ እንደገለፁት ከሆነ ይሄ surface contamination ማለትም ከመኪናው ቦዲ በላይ በተከማቸ metalic dust ነው እንጂ እራሱ መኪናው ዝጎ አይደለም ብለው ከገለፁ በሗላ አንድ ዩቱበር ይሄን ለማረጋገጥ እቤት ውስጥ ኪችን ላይ በምንጠቀማቸው የፅዳት ሳሙናዎች እና በፎጣ ብቻ ዝገት መሳይ ነገሩን ሲያፀዳ እና የተባለው እውነት መሆኑን በቪዲዮ አጋርቶናል

ከዛም በተጨማሪ ከዚህ በፊት በግሬ ጥቁር እና ነጭ የቀለም አማራጮች ሲቀርቡ የነበረ ሲሆን ከሱ በተጨማሪ 3 የቀለም አማራጮችን ማለትም በወርቃማ በሰማያዊ እና በሌላ አይነት ግሬ ቀለም አቅርበዋል :: እነዚህን ለማድረግ ግን ተጨማሪ 6,000 የአሜሪካን ዶላር እንደሚጠይቁ አስቀምጠዋል ::

ልዩ ቀን ተመኘን
#Tesla #Cybertruck
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/27 09:32:56
Back to Top
HTML Embed Code: