Telegram Web Link
ቶዮታ ከ 88 አመታት በሗላ 300 ሚሊየን መኪና ምርቱን አውጥቷል ::

ቶዮታ በጣም ትልቅ እና አንጋፋ የመኪና አምራች ካምፓኒ ነው :: ያው ቁጥሩም የሚያሳየው ይህንኑ ነው :: ከ 1935 ጀምሮ እስከ ሴፕቴምበር 2023 መጨረሻ ድረስ የመኪኖቹን ምርት 300 ሚሊየን ለማድረስ የፈጀ ሲሆን 88 አመት ከ 2 ወር ፈጅቷል:: ከ 300 ሚሊየን መኪኖች ውስጥ 180.52 ሚሊየኖቹ ጃፓን እና የተቀሩት 119.6 ሚሊየኖቹ ደግሞ የልተለያየ ሀገር ተመርተዋል :: የመጀመሪያው መኪና G1 ትራክ ሲሆን በብዛት ደግሞ የተሸጠው መኪና ቶዮታ ኮሮላ ነው :: ከተሸጡትም መኪኖች ከ 1/6 በላይ የተሸጡት እነዚህ የኮሮላ ሞዴል መኪኖች ሲሆኑ አጠቃላይ 53.399 ሚሊየን መኪኖች ናቸው :: እናንተስ የምትወዱት የቶዮታ ሞዴል የቱ ነው?
ስለቶዮታ ከየት ወዴት የሚለውን አስገራሚ ታሪክ ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/TLAo-eTDkiw

ውብ ቀን ተመኘን
#CarFacts #Toyota
@OnlyAboutCarsEthiopia
ጥቁር ቲንትድ መስታወቶችን ለ ሱዚኪ መኪኖች ማስገጠም ትፈልጋላችሁ?

እንግዲያው ኦሜጋ ለመኪኖቻችሁ በትራፊክ የማያስቀጡ ቲንትድ መስታወቶችን አቅርቦላችሗል :: በብዛት ሀገራችን ላይ የሚገኙት የሱዙኪ መኪና ሞዴል Dzire, Alto, Celario እና Swift ያላችሁ ለመኪናችሁ መስታወት ከፈለጋችሁ Omega Auto Glass በመምጣት ወይም በመደወል በጥቁርም ቲንትድ እንዲሁም በነጭም መስታወት ጭምር ታገኛላችሁ
አድራሻ ሀብተጊዮርጊስ ድልድል ወደ አሊያንስ በሚወስደው መንገድ ላይ ፓልሪየስ ጎን ታገኙናላችሁ ::
ስልክ 0911241153 ወይም
0911609080 ወይም
0925494095 ይደውሉ ::

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
#OmegaAutoGlass
@OnlyAboutCarsEthiopia
ባለሥልጣኑ አሮጌ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች አስቀድመው መፍትሄ እንዲያዘጋጁ አሳሰበ

የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ድዳ ድሪባ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤የመኪና ጭስ ስታንዳር እየተዘጋጀ ነው። በዚህም እያንዳንዱ መኪና የሚያስወጣው ጪስ የሚለካ ይሆናል።

መኪናው ከተቀመጠው መለኪያ በላይ ጪስ የሚያመነጭ ከሆነ አገልግሎት እንዳይሰጥ ይደረጋል ብለዋል።

አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ ተሽከርካሪዎች ከተመረቱ 23 ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ናቸው ያሉት ኃላፊው፤ ስለዚህ አሮጌ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች ከአሁኑ መፍትሄ ሊያዘጋጁ ይገባል ብለዋል።

በመዲናዋ አሮጌና ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ በርካታ መኪኖች መኖራቸውን በመጥቀስ፤ መኪናዎቹን በአንድ ጊዜ ሥራ እንዲያቆሙ ማድረግ እንደማይቻል አመላክተዋል፡፡

ሆኖም ቦሎ የሚሰጡ፣ መኪናዎችን የሚቆጣጠሩና መኪና የሚገዙ አካላት ባለሥልጣኑ የሚያወጣውን የጭስ ስታንዳርድ መሠረት እንዲያደርጉ አቶ ድዳ አሳስበዋል።

አገልግሎት የሰጡ መኪናዎች እንደበፊቱ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ቢደረግ ኖሮ አዳዲስ መኪናዎች ወደ ከተማዋ አይገቡም ነበር ያሉት አቶ ድዳ፤ እየተዘጋጀ ያለው የመኪና ጭስ ስታንዳርድ ለአየር መበከል አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ጋዞችና ብናኞች ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጤና ችግሮችን ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል።

በመዲናዋ የአየር ጥራት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ 10 ዘመናዊ መሣሪያዎች የተገጠሙ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ከመኪና የሚወጣውን ጭስ መቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የአየር ጥራት መረጃ በተለይ በተገቢው ጊዜና ቦታ መረጃ መስጠት የአየር ብክለትን ተጋላጭነትን ለመቀነስ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል።

(ኢፕድ)

ምን ታስባላችሁ?

@OnlyAboutCarsEthiopia
ምልክቱን ከዚህ በፊት በሰራነው ቪዲዮ ላይ አሳይተን ነበር :: ታዲያ ምልክቱ ምንን ለመግለፅ ይመስላችሗል?

AC ማብሪያ ማጥፊያ ነው የምትሉ በ “❤️” ምልክት
Auto Start Stop መጥፋቱን የምትሉ ደግሞ በ "👍🏽" ምልክት ግለፁልን ::
መጨመር የምትፈልጉት ሀሳብ ካለ ኮሜንት ላይ አስፍሩልን ::

ፅድት ያለ ምሽት ተመኘን
#CarTech
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለአዳዲስ መኪኖች ቲንትድ መስታወት

ቲንትድ የፕራይቬሲ መስታወቶችን ለ Toyota BZ4X እና ለሌሎችም አዳዲስ መኪኖችን ከ Omega Auto Glass ታገኛላችሁ ::
አድራሻ ሀብተጊዮርጊስ ድልድል ወደ አሊያንስ በሚወስደው መንገድ ላይ ፓልሪየስ ጎን ታገኙናላችሁ ::
ስልክ 0911241153 ወይም
0911609080 ወይም
0925494095 ይደውሉ ::

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
#OmegaAutoGlass
@OnlyAboutCarsEthiopia
2023 Nissan Patrol Vs 2023 Toyota LandCruiser 300 Series
Only About Cars Ethiopia
2023 Nissan Patrol Vs 2023 Toyota LandCruiser 300 Series
ከላይ ከምታዩት መኪኖች የእናንተ ምርጫ የቱ ነው?
Anonymous Poll
57%
2023 Toyota LandCruiser 300 Series
43%
2023 Nissan Patrol
2023 Nissan Patrol ወይስ 2023 Toyota LandCruiser የቱ ይሻላል?

ከ 1951 ጀምሮ Nissan Patrol እና Toyota Land Cruiser ሁለቱም ሲፎካከሩ እስከአሁን የቆዩ ሲሆን አስገራሚ የoff-road አቅም, የቅንጦት featuresፊቸሮች እና ጉልበት ያላቸው ሞተሮች ይዘው በመቅረባቸው ነው :: ታዲያ በዛሬው ቪዲዮ ያላቸውን ልዩነት የትኛው መኪና ለየትኛው መንገድ እንዲሁም የትኛው የተሻለ ነው የሚለውን እናያለን ::
የዩትዩብ ሊንኩን
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/2CWkT51O4y4

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Nissan #Toyota #SUV
@OnlyAboutCarsEthiopia
2023 Toyota BZ4X 2WD Vs AWD

የቶዮታ የመጀመሪያው ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን ቻይና ውስጥ በ GAC እና FAW የመኪና ድርጅቶች የሚሰራ ነው :: 4 አይነት የትሪም አማራጭ ሲኖረው በ 2 አይነት የሞተር እና የባትሪ አማራጭ ይገኛል :: ታዲያ በዛሬው ቪዲዮ ያላቸውን ልዩነት የትኛው መኪና የተሻለ የኪሎሜትር ሬንጅ እንዳለው እንዲሁም የትኛው የተሻለ ቴክኖዎሎጂ አለው የሚለውን እናያለን ::
የዩትዩብ ሊንኩን
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/Of4WhGt-Mas

ውብ ቀን ተመኘን
#EV #Toyota #SUV
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለመኪኖቻችሁ ቲንትድ መስታወት

ቲንትድ የፕራይቬሲ መስታወቶችን ለአዳዲስ መኪኖችንም ለቆዩትም ከ Omega Auto Glass ታገኛላችሁ ::
አድራሻ ሀብተጊዮርጊስ ድልድል ወደ አሊያንስ በሚወስደው መንገድ ላይ ፓልሪየስ ጎን ታገኙናላችሁ ::
ስልክ 0911241153 ወይም
0911609080 ወይም
0925494095 ይደውሉ ::

ውብ ቀን ተመኘን
#OmegaAutoGlass
@OnlyAboutCarsEthiopia
5 አውቶማቲክ መኪናችሁ ላይ ማድረግ የሌለባችሁ ነገሮች

አሁን ላይ በመኪናው ኢንዱስትሪ ውስጥ ከአስርት አመታት በላይ አውቶማቲክ ትራንስሚሽን ገበያውን በመቆጣጠር ቆይቷል :: ይህም የሆነው ከ ማንዋል ትራንስሚሽን የተሻለ ለመንዳት ቀላል ስለሆነ ነው :: ታዲያ ምንም ቀላል ቢሆንም በሹፌሩ አነዳድ ችግሮች መኪናው በየጊዜው ጋራዥ ሊገባ ይችላል :: ይህ እንዳይፈጠር መደረግ የሌለባቸውን 5 ነገሮች እንይ
1. መኪናችሁ እየተንቀሳቀሰ ከ Drive(D) ወደ Reverse(R) ወይም ወደ Park(P) መደረግ የለበትም ::
2. መኪናችሁን ካቆማችሁት በሗላ Drive(D) ላይ አድርጋችሁ ማቆየት የለባችሁም ::
3. ነዳጅ ፔዳሉን ገና ስትነሱ ሙሉ በሙሉ መርገጥ የለባችሁም ::
4. ምስሉ ላይ የምትመለከቱትን የ Check Engine ሲበራ ዝም ብላችሁ አይታችሁ ማለፍ የለባችሁም ::
5. መኪናችሁን ስታቆሙ ወደ Neutral(N) ማርሽ ማድረግ የለባችሁም :: Neutral(N) የምትጠቀሙት ለ Emergency ብቻ ነው መሆን ያለበት ::
ተጨማሪ ነገሮችን ከዩትዩብ ቪዲዮ ላይ ከስር ባለው ሊንክ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MhpxNxv4kAw?si=7oZX3VZhPa4IXZSj

ልዩ ቀን ተመኘን
#Automatic
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪናዎትን በማኪያቶ ዋጋ ይሽጡ
በቅርብ ቀን

@Hulemekina
የ 2024 Toyota BZ4X በምን ይለያል?

Toyota company bz4x በሚል ስም ሲያመርተው የነበረው የኤሌክትሪክ መኪናው በ 2024 ሞዴል ላይ 4x ወደተባለ አዲስ እና የተሻለ version ቀይሮታል ::

አዲሱ version 4x ከbz4x የተለየ ገፅታ ሲኖረው  ከsuv ወይም ከCrossover መኪኖችም ትንሽ ለየት ያለ መልክ ነው ያለው ::

Toyota እንዳሳወቀው ከሆነ 4x ከሌሎች የተሻለ የbattery አቅም, የተሻለ የኪሎሜትር ሬንጅ ማለትም እስከ 615ኪሜ በአንድ ቻርጅ ይጓዛል ።

ከቀድሞው ሞዴሉ bz4x ሳይዝ አንፃር 10% ያህል የሚተልቅ ሲሆን የተገጠመለት motorም ከበፊቱ ጋር ተመሳሳይ ነው ::

ልዩ ቀን ተመኘን
#Electric #bz4x
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ ጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ
በዓሉ የሰላም እና የደስታ በዓል ይሁንላቹ

መልካም የገና
በዓል 🎁

@OnlyAboutCarsEthiopia
Hyundai Kona 2024 ሞዴል እሳት ፈጥሯል

ባለ 1.6 ሊትር ቱርቦ ሞተር የሆነው የ2024ቱ Hyundai kona በግጭት ሙከራ (crush testing) 3ት ጊዜ እሳት ፈጠረ።

እሳቱ የተነሳበት ምክንያትም 12 Volt ባትሪው የ +ቭ cable ከengine control module(ECU) ማቀፊያው ጋር ፍትጊያ በመፍጠሩ እና ሾርት በማድረጉ ነው።

ይሄ ችግር እንዳለበት የታወቀውም Insurance Institute for Highway Safety (IIHS) ባደረገው የግጭት ሙከራ ላይ ነው።

Hyundaiም ይሄን እክል ለመቅረፍ ሲል በ አሜሪካ 10,984 መኪኖችን recall አርገዋል።

ብዙ ሰው ከነዳጅ መኪኖች በበለጠ የኤሌክትሪክ መኪኖች እሳት የመፍጠር አቅም አላቸው ብለው ያስባሉ :: እናንተስ ምን ታስባላችሁ ?

ግሩም ቀን ተመኘን
#News #HyunaiKona
@OnlyAboutCarsEthiopia
Tesla Model 3 ቻይና የሚመረተው አሜሪካ ከሚመረተው በምን ይለያል?

በ አሜሪካ ፍሬሞንት ፋብሪካ ውስጥ የሚመረተው ቴስላ ሞዴል 3 ቻይን ከሚመረተው አንፃር ተጨማሪ ፓርቶች አንዳሉት ተናግረዋል ።

Hardware 4 የሚባለው የsefety ፊቸር ሲኖረው የቻይናው hardware 3.5ን ይጠቀማል፡: በተጨማሪ የ አሜሪካው ራዳር እና የፊትለፊት መጋጫው ላይ የሳይበር ትራክ ካሜራ ተገጥሞለታል።

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Tesla #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
በ2023 አለም ላይ በብዛት የተሸጡ 10 ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የትኞቹ ናቸው?

1. Tesla Model Y - 747,000 ፍሬ በመሸጥ
2. Tesla Model 3 - 482,000 ፍሬ በመሸጥ
3. Wuling Hongguang Mini EV - 443,000 ፍሬ በመሸጥ
4. BYD Dolphin - 200,000 ፍሬ በመሸጥ
5. Volkswagen ID.4 - 150,000 ፍሬ በመሸጥ
6. Hyundai Kona Electric - 100,000 ፍሬ በመሸጥ
7. Ford Mustang Mach-E - 90,000 ፍሬ በመሸጥ
8. Kia Niro EV - 80,000 ፍሬ በመሸጥ
9. Volkswagen ID.3 - 77,900 ፍሬ በመሸጥ
10. Fiat 500 - 75,000 ፍሬ በመሸጥ

እዚህ ላይ ከተዘረዘሩት መኪኖች አንዳንዶቹ ኢትዮጵያ ውስጥም በብዛት የተሸጡ መኪኖች ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ በሀገራችን ያልገቡ መኪኖች ናቸው ::

ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት ተሽጧል ብላችሁ የምታስቡት መኪና የቱን ነው?

ፍክት ያለ ቀን ተመኘን
#Top10 #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
በ2023 አውሮፓ ውስጥ በብዛት የተሸጡ 10 ተሽከርካሪዎች የትኞቹ ናቸው?

በ 2023 አውሮፓ ላይ በብዛት የተሸጡ 10 መኪኖች
1. Tesla Model Y - 209,503
2. Dacia Sandero - 196,121
3. Volkswagen T-Roc - 175,169
4. Peugeot 208 - 163,182
5. Renault Clio - 161,576
6. Opel/Vauxhall Corsa - 161,576
7. Volkswagen Golf - 156,193
8. Toyota Yaris - 154,847
9. Skoda Octavia - 153,446
10. Volkswagen Polo - 140,176 መኪኖችን ሽጠዋል::

እዚህ ላይ ከተዘረዘሩት መኪኖች አንዳንዶቹ ኢትዮጵያ ውስጥም ገብተው ለመሸጥ አስቸጋሪ ሆነው አይተናል :: ለሱ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ግን ደግሞ የአውሮፓ መኪና ሲባል ሰዉ ላይ ያለው ምልከታ ከፍ ያለ ነው ::

ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን በብዛት አይሸጡም? ምክንያቱ ምንድነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

ልዩ ቀን ተመኘን
#Top10 #Europe
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም በፍቅር በጤና አደረሳችሁ አደረሰን መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ!

መልካም በዓል ተመኘን 🙏
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/23 20:18:11
Back to Top
HTML Embed Code: