Telegram Web Link
#ዜና

ብዙ የመኪና አምራቾች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ከነበራቸው እቅድ እያፈገፈጉ ነው።


ብዙ የመኪና አምራቾች የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማምረት የነበራቸው እቅድ ላይ በጣም ጥመኞች የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ከዛ እቅድ ወደ ኋላ ብሎዋል። ይህ ማለትም ይበልጥ ሃይብሪድ እና ሌሎች የሃይል አምራቾጮችን የምጠቀሙ መኪኖች ላይ ትኩረታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

የMercedeሱ CEO አንዳለው ሙሉ በሙሉ የካርበን ልቀት ወደሌላቸው ተሽከርካሪዎች የሚደረገው ለውጥ ከተጠበቀው በላይ ጊዜ የሚወስድ ይሆናል። እናም የሃይብሪድ መኪኖች ላይ ፍላጎት እስካለ ድረስ እስከ 2030 ድረስ የምናመርታቸው ይሆናል።

የVolkswagenኑ CEO ደግሞ የፕለጊን ሃይብሪድ ቴክኖሎጂ ወደ ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ ወደ ሆኑ ተሽከርካሪዎች የምንሻገርበት ድልድይ ነው። እናም የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ፍላጎት በመገዛቀዙ Volkswagen ዋገን ይሄን መሻገሪያ የሆነ ቴክኖሎጂ መጠቀም ግድ ብሎታል ብለውዋል።

ይሄ በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ፍላጎት መገዛቀዝ ሰፊው ህዝብ የሚጠቀማቸው ተሽከርካሪውች ላይ ብቻ አይደለም። ቅንጡ እና በጣም ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ Rimac እንደተናገረው የሃይፐር መኪና ገዢዎች ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ የሆኑ መኪኖችን እየፈለጉ ይደለም።

በዚህ ምክንያት ምን አልባት አሁንም ብዙ በፒስተን ሃይል የሚሰሩ እና ትላልቅ አቅም ያላቸው ኢንጅኖች የያዙ Super Carዎችን ገበያው ላይ ተመልሰው ልንመለከት እንችላለን።

#Haybrid #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

ምን አልባት አደጋ መኪናዎ ላይ ቢደርስ.....


ለተለያዩ ሞዴል መኪኖች የሚሆኑ መስታወቶች ከ Omega Auto Glass ታገኛላችሁ ::

Omega Auto Glass የፋብሪካ ቲንትድ የፕራይቬሲ መስታወቶችን ለአዳዲስ መኪኖችንም ለቆዩትም ታገኛላችሁ ::
አድራሻ
ቁጥር 1 - ሀብተጊዮርጊስ ድልድል ወደ አሊያንስ በሚወስደው መንገድ ላይ ፓልሪየስ ጎን
ቁጥር 3 - ጎፋ መብራት ሀይል ታገኙናላችሁ ::
ስልክ 0911241153 ወይም
0911609080 ወይም
0925494095 ይደውሉ ::

#OmegaAutoGlass
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቻይና የመኪና ኤክስፖርት ወደ አዲስ ሪከርድ ወደ ማስመዝገብ እያቀና ነው።


ቻይና ገበያዋ ላይ ከሚያስፈልጋት በላይ የሆነውን ከፍተኛ የመኪና ምርት ወደ ባህር ማዶ እየላከች መሆኑ የሚታወቅ ነው። እንደ China Passenger Car Association ዘገባ በወርሃ April ላይ ቻይና የመኪና አምራች ካምፓኒዎቿ 417,000 መኪኖችን ወደተለያዩ ሃገራት በመላካቸው ትልቁን የኤክስፖርት ሪከርዷን  የያዘች ሲሆን ይህም ካለፈው አመት አንፃር በ38% ከፍ ያለ ነው።

ካምፓኒዎቹ አብዛኛውን ጊዜ መኪኖቹን ወደ ደቡብ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ እና ለሌሎች የእሲያ ሃገራት ነው የሚልኩት። 
የኤክስፖርት ሪከርዷ ከፍ እያለ ባለበት ተመሳሳይ ጊዜ የሃገር ውስጥ ሽያጯ ግን በተቃራኒው ቀንሶዋል። የመኪና አምራቾቹ ያለፈው ወር ላይ 1.5 ሚሊየን መኪኖችን የሃገር ውስጥ ገበያ ላይ የሸጡ ሲሆን ይህም ካለፈው አመት አንፃር በ6℅ ያነሰ ነው።
ሃገር ውስጥ ያለው ሽያጭ በመቀዛቀዙ ካምፓኒዎቹ ተጨማሪ መኪኖችን ወደ ባህር ማዶ እየላሉ ይገኛሉ።

#China #Export
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Cadillac ወደ Le Mans የF1 ውድድር ስለመመለሱ የሚያስቃኝ ዶክመንተሪ ሰራ።


የCadillac ለመኪና ውድድር አድናቂዎቹ ያለፈው አመት ላይ ወደ Le Mans ውድድር ስለመመለሱ እና ከውድድሩ በስተጀርባ ስለነበሩት ትዕይንቶች የሚያስቃኝ ዶክመንተሪ ፊልም ከ Samsung TV Plus ጋር በመተባበር የሰራ ሲሆን "No Perfect Formula" የሚል እርእስ ሰተውታል።

ዶክመንተሪው የCadillac የውድድር ቡድን ያለፈው አመት የነበረው የLe Mans ውድድር ላይ የV-Series. R የውድድር መኪናን ዲዛን ለማረግ፣ ለማበልፀግ፣ ለመገንባት ፣ለመሞከር ሲጥሩ እና ውድድር ሲያረጉ የነበረውን ውጣ ውረድ የሚያስቃኝ ይሆናል።

የ(1:30)አንድ ሰአት ተኩሉ ዶክመንተሪ ለመጀመሪያ ጊዜ May 31 በእለተ አርብ አየር ላይ የሚውል ሲሆን በSamsung Tv Plus App ላይ በሚገኘው Hagerty ቻናል ይሆናል።
ዶክመንተሪውም የዚኛው አመት Le Mans ውድድር እስኪጀመር ለተደጋጋሚ ጊዜ ቻናሉ ላይ የሚታይ ሲሆን የዚኛው አመት ውድድር June 15 ላይ የሚጀምር ይሆናል።

#Cadillac #Documentary #Le_Mans_F1_Race
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቻይና የሃገር ውስጥ የመኪና ሽያጯ ቀንሶ በምትኩ የኤክስፖርት ቁጥሯ ጨምሯል።


ቻይና ከሃገር ውስጥ ፍላጎቷ በላይ በጣም ብዙ የሆኑትን መኪኖች የአውቶ ኢንዱስትሪዋ ጤናማ ሆኖ እንዲቆይ በማሰብ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን መኪኖች ኤክስፖርት ማድረጓ ብዙ የአለም ሃገራት ስጋት እንዲገባቸው አድርጓል።

ያለፈው ወር ላይ የነበረው የሃገር ውስጥ የመኪና ሽያጯ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ5.7% ያነስ እና ከሱ ወር በፊት ከነበረው ወር ሽያጭ ጋር ሲነፃፀር ደግሞ በ9.7% የቀነሰ ነበር።

ከዚህ ፍፁም ተቃራኒ በሆነ መልኩ 417,000 መኪኖችን ለተለያዩ ሃገራት በመላክ የኤክስፖርት ንግዷ በ 38% አድጎዋል።

Mercedes እና stellantis የቻይና መኪኖች ላይ ያለው ታሪፍ ጭማሪ ይደረግበት በሚለው ሃሳብ የተስማሙ ባይሆንም የቻይና መኪኖች የአውሮፓ ጎዳናዎች ላይ እንዳይበራከቱ ለመከላከል ሲባል በአውሮፓ ህብረት መረር ያሉ ፖለቲካዊ አሻጥሮችን መመልከት እንጀምራለን።

#China #EU #CarExport
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የBYD Shark ፒክ አፕ መኪና የመጀመሪያው ኦፊሻል ፎቶ


ከላይ የምትመለኩቱት የBYD Shark የመጀመሪይው በግልፅ የሚታይ እና ኦፊሻል የሆነው ፎቶ ሲሆን ለBYD የመጀመሪያው ፒክ አፕ መኪናው ነው።

መኪናው ፕለጊን ሃይብሪድ የሆነ እና እስከ 480 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጭ ሲሆን Active Suspension ሲስተምም ተካቶለታል።
Gasgoo እንደዘገበው ከሆነ BYD Shark ዛሬ በሃገረ ሜክሲኮ ላይ ለገበያ መቅረብ ይጀምራል።

#BYD #Shark
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ የፋስት ቻርጂንግ ስቴሽኖቹን ለማስፋፋት ግማሽ ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት አደረገ።


ከጥቂት ሳምንታት በፊት የSuper ቻርጀር ቡድኑን በማሰናብት የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪውን አስገርሞ ነበር። ያኔ የቴስላ ባለቤት የሆነው Elon Musk "የፋስት ቻርጂንግ ኔትዎርካችንን ቀስ ብለን የምናስፋፋ ሲሆብ አሁን ላይ ትኩረታችን በስራ ላይ ያሉ የቻርጂንግ ስቴሽኖች ላይ የማስፋፊያ ስራ መስራት ነው።" ብሎ ነበር።

ነገር ግን ከዚህ ውሳኔው ወደ ኋላ ያለ ይመላል። ያለፈው አርብ የቀድሞው twitter የአሁኑ X ላይ "ቴስላ በዚህ አመት የSuper ቻርጂንግ ኔትዎርኩን ለማስፋፋት 500 ሚሊየን ዶላር መድቦዋል" ሲል መረጃውን አጋርቶዋል። 

ቴስላ የSuper ቻርጀር ቡድኑን መበትኑ በአሜሪካ ላይ ትልቁ የቻርጂንግ ኔትዎርክ እንደመሆኑ የባይደን አስተዳደር ሃገሪቷ ላይ የኤሌክትሪ መኪኖች ቻርጀርን ለማስፋፋት ያቀደው እቅድ ላይ እንደተሰነዘረ ጥቃት ታይቶ ነበር።

እንደ EVAdoption ምረጃ መሰረት ቴስላ በመጀመሪያው የእሩብ አመት አጋማሽ ላይ 1,500 የመኪና ቻርጀሮችን የገጠመ ሲሆን ከሱ ጋር የቅርብ ተፎካካሪ ናቸው ከሚባሉት ካምፓኒዎች በአራት እጥፍ የበለጠ ነው።

#Tesla #SuperChargers
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ያለፈው አመት ላይ ብዙ መኪናዎችን በመሸጥ ከላይ ከተቀመጡት 10 የመኪና አምራች ድርጅቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ።


የመኪናው ብራንድ - የሽያጭ ብዛት

1. Toyota - 10,300,000 መኪኖች

2. Volkswagen - 9,200,000 መኪኖች

3. Hyundai Group - 7,300,000 መኪኖች

4. Stellantis - 6,200,000 መኪኖች

5. General Motors - 6,100,000 መኪኖች

6. Ford - 4,400,000 መኪኖች

7. Honda - 4,100,000 መኪኖች

8. Nissan - 3,300,000 መኪኖች

9. BYD - 3,000,000 መኪኖች

10. BMW - 2,500,000 መኪኖች

#Top_10 #Sales
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volkswagen ስለሜሪካው ID Buzz አንዳንድ ስፔስፊኬሽኖችን አጋራ።


በዚህ አመት ወደ መጨረሻው ላይ የአሜሪካ ገበያ ላይ ስለሚውለው mini van፤ የአሜሪካው ቨርዥን ID Buzz አንዳንድ መረጃዎችን አግኝተናል።

በሶስት የTrim ሌቭሎች ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን 91kwh ባትሪ ፓክ አለው።  Rear wheel driveቩ ላይ አስከ 282 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጭ ሲሆን በAll Wheel Drive ቨርዥኑ እስ 335 የፈረስ ጉልበት ማመንጨት ይችላል።

ሁለት አይነት ቀለም ያላቸውን ጨምሮ በብዙ አይነት የቀለም አማራጮች የቀረበ ሲሆን ውስጥ ላይ ስታንዳርድ 12.9 ኢንፎቴመንት ስክሪን ፣ Driver assistant ቴክኖሎጂ፣ የCaptain ወንበሮች ፣ እና panaromic የመስታወት ጣራ አለው።

Volkswagen እንደተናገረው የኪሎሜትር ሬንጁን እና የመሸጫ ዋጋውን ለሽያጭ የሚውልበት ቀን ሲቃረብ ይፋ ይሆናል።

#VW #ID
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አሜሪካ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች(HouseHolds) መኪና ለመግዛት የተበደሩት የብድር እዳ 1.6 ትሪሊየን ዶላር ነው ተባለ።


የትኛው የቤተሰብ አይነት ነው አሜሪካ ውስጥ ብዙ መኪና በብድር እየገዛ ያለው?
የEquifax የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያሳየው በአመት ከ100,000 ዶላር እስከ 250,000 ዶላር ገቢ የሚያስገቡ ቤተሰቦች ለመኪና ብድር በመውሰድ ከፍተኛውን ቁጥር ይዘዋል። ብዛታቸው 9.3 ሚሊየን ቤተሰቦች ሲሆኑ በአማካይ 30,500 ዶላር ብድር ይወስዳሉ።

በሁለተኛነት በአመት ከ50,000 ዶላር እስከ 100,000 ዶላር ገቢ የሚያስገቡ ቤተሰቦች ሲሆኑ ብዛታቸው 5.3 ሚሊየን ነው። በአማካይ የሚወስዱት ብድርም 27,500 ዶላር ነው።

በሶስተኛነት በአመት ከ50,000 ዶላር ያነሰ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ሲሆኑ ብዛታቸው 1.6 ሚሊየን ነው። በአማካይ የሚወስዱት ብድር 25,800 ዶላር ነው።

በሚገምር ሁኔታ በአመት ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ የሚያስገቡ ቤተሰቦች አማካይ የብድር መጠናቸው 44,400 የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ከነሱ ውስጥ 71,000 ቤተሰቦች ብቻ ናቸው መኪና ለመግዛት ብድር የወሰዱት።

በአሜሪካ ላይ በጠቅላው አዲስም ሆነ ያገለገለ መኪና ለመግዛት የተወሰደው የብድር መጠን  1.6 ትሪሊየን ዶላር ደርሷል። የእኛስ ሀገር በግምት ስንት ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ? ግምታችሁን ኮሜንት ላይ እንጠብቃለን ::

#USA #Household_Car_Loans
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Ad

Yango ላይ መስራት ጀመርኩ፤

እርስዎም የትም ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው ከ 10 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተመዝግበው እንደኔ በመስራት ገቢዎትን በ ጉርሻ ብቻ እስከ 9200 ብር በሳምንት ተጨማሪ ገንዘብ ያግኙ።

አሽከርካሪዎች አፑን ለመጫን ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
bit.ly/4bEE8m8

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ገፃቸው
https://www.tg-me.com/YangoETH

እንዲሁም የፌስቡክ ገፃቸው
https://www.facebook.com/groups/1171500204006823
#Yango_pro #Earnings #Driving
#ዜና

Chevrolet Equnox በይፋ ለሽያጭ ቀረበ።


በመጨረሻም Chevrolet Equnox በአሜሪካ ገበያ ላይ ለሽያጭ ቀርቦዋል።
የbase ሞዴሉ የመነሻ ዋጋ የማድረሻውን ሳይጨምር ከ35,000 ዶላር ጀምሮ ሲሆን የአመቱ መገባደጃ ድረስ ገበያ ላይ አይውልም።

አሁን ገበያ ላይ የቀረበው የመነሻው ዋጋ ከ43,000 ዶላር ጀምሮ ነው። Chevrolet ለመጀመሪያ ጊዜ Equnox የኤሌክትሪክ መኪናን ሲያስተዋውቅ የመነሻ ዋጋው ከ 30,000 የአሜሪካ ዶላር ጀምሮ እንደሚሆን ቃል ገብቶ የነበር ቢሆንም ነገር ግን መኪናው የአሜሪካ የታክስ ህግ ላይ ያለውን የ7,500 የቀረጥ ክፍያ እንዲጣልበት የሚያረጉትን ቅድመ ሁኔታዎች ስለሚያሟላ ዋጋውን ወደ 27,500 ዶላር ዝቅ አድርጎታል።

#Chevrolet #Equnox
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አለም አቀፋዊ የቤንዚል ፍላጎት ኮቪድ 19 ከመቀስቀሱ በፊት እንደነበረው ሆነ።


በ2024 የኤሌክትሪክ መኪናዎች ዓለም አቀፋዊ የነዳጅ ዘይት ላይ ያለው ፍላጎት መቀነስን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚገልጹትን ከኮቪድ-ቀድሞ የነበሩ ትንበያዎችን ስናፈሱ ነበር።

ነገር ግን አስካሁን ያ አልሆነም። ምን አልባት ወደፊት...።
bloomburg በቅርቡ ይዞ የወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው ከሆነ በዚህ የበጋ ወቅት የአለም የቤንዚን ፍላጎት በ2019 ከነበረው ከፍ ያለ ይሆናል።

#Gasoline #Bloomburg
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

8 የመኪና አምራቾች በደንበኞቻቸው የግል መረጃ አያያዝ ላይ የተዛባ መረጃ ለደንበኞቻቸው በመስጠት ተወንጅለዋል።


የመኪና አምራቾች ሲዋሹ ተያዙ። 2014 ላይ 8 የመኪና አምራቾች ከPrivately ጋር ተያይዞ በፈቃደኝነት የደንበኞቻቸውን መረጃዎች ለመንግስት አካላት በፍርድ ቤት ትዛዝ ፍቃድ ተሰቶአቸው ሲመጡ ለማቅረብ ፈርመው ነበር።

መኪኖች ይበልጥ በዘመኑ እና የተለያዩ መረጃዎችን የመኪና አምራቾፅ መሰብሰብ በጀመሩ ቁጥር Privacy ጥያቄ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ሆኖዋል። የዲሞክራቶቹ ሴናተሮች Ed Markey ከMassachusetts ግዛት እና Ron Wyden ከOregon ግዛት 8 የመኪና አምራቾችን የደንበኞቻቸውን መኪኖች የGPS location ለፖሊስ ስለመስጠታቸው የተዛባ መረጃ በመስጠታቸው እና ግልፅ ባለማረጋቸው ከሰዋቸዋል።

የመኪና አምራቾቹ Toyota፣ Nissan፣ Subaru፣ Volkswagen፣ BMW፣ Mazda፣ Mercedes-Benz እና Kia ሲሆኑ ለህግ አውጪዎች ይደንበኞቻቸውን መረጃ ካለፍርድ ቤት ትዛዝ እና ፍቃድ ለፖሊስ ሲሰጡ እንደነበር ተናግረዋል።

ሴናተሮቹም የመኪና አምራቾቹ ይሄን ለደንበኞቻቸው ግልፅ ባለማረጋቸው የከሰሷቸው ሲሆን ለFederal Trade Commission ካምፓኒዎቹ ላይ ምርመራ እንዲያረ ሲሉ ደብዳቤ ፅፈዋል።

#AutoMakers #Privacy
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nio ቴስላን እንዲቀናቀን በማሰብ አዲስ የመኪና ብራንድ ይፋ አረገ።



የቻይናው የመኪና አምራች Nio በዋጋቸው ቀነስ ያሉ መኪኖች የሚያመርት Onvo የተሰኘ አዲስ ብራንድ ይፋ አድርጎዋል።  የብራንዱ የመጀመሪያ መኪና የሆነው L60 ሲሆን የቦዲ ስታይሉ Mid-Size Crossover የምንለው እና በቀጥታጣየቴስላውን ሞዴል Y አንዲቀናቀን ታስቦ የተሰራ ነው።

መኪናው ባለ 900- ቮልት አርክቴክቸር የሚጠቀም ሲሆን የሃይል አጠቃቀሙ በየ100Kmሩ 12.1 kilowatt hour ነው። ይሄም ከቴስላ ሞዴል Y በትንሹ ያነሰ ነው።

ሶስት የባትሪ ፓክ አማራጭ ያለው ሲሆን እነሱም ባለ 60፣ ባለ 90፣ እና ባለ 150 kilowatt hour ነው። እንደ ባትሪ ፓክ ሳይዙ ከ555 km ጀምሮ እስከ 1,000 km የሚደርስ የKm ሬንጅ አለው። 
Nio  እንዳለው እንዴሌሎቹ የNio መኪኖች ሁሉ L60ም የBattery swapping ፊውቸር ተካቶለታል።

አሁን ላይ L60ን ኦርደር ማረግ የተጀመረ ሲሆን የመነሻ ዋጋው ከ30,500 ዶላር ጀምሮ ነው። ይሄም ከቴስላ ሞዴል Y  አንፃር በ12% ቅናሽ አለው። በደንበኞች እጅ ላይም በሶስተኛው የሩብ አመት አጋማሽ ላይ የሚደርስ ይሆናል።

#Nio #Onvo #L60
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አሜሪካ የቻይና የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪዎች እና የባትሪ ክፍሎች ላይ ያለውn የቀረጥ ታሪፍ ከፍ አረገች።



ከትናንትና ወዲያ የወጣ ዘገባ በሃገረ ቻይና ተመርተው በBuick እና በLincoln አሜሪካ ላይ የሚሸጡ መኪኖች ላይ 100% የቀረጥ ታሪፍ ይኖርባቸዋል ይል ነበር። ነገር ግን ቀረጡ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ብቻ የሚመለከት በመሆኑ Buick እና Lincoln የሚጎዳቸው አይሆንም።

አሁን ላይ የቀረጥ ታሪፉ በቻይና የሚመረቱ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪዎች እና የባትሪ ክፍሎች ላይ የተጨመረ ሲሆን በፊት ላይ ከነበረበት 7.5% ወደ 25% ከፍ ብሎዋል። ይሄም ለኤሌክትሪክ መኪኖቻቸው ከቻይና ባትሪን ኢምፖርት የሚያረጉ ካምፓኒዎች ላይ ጫና ይኖረዋል።

ለምሳሌ እንደ አንዳንድ የMustang Mach E እና F-150 Lightning ያሉ የፎርድ መኪናዎች በቻይናው የባትሪ አምራች በሆነው CATL የሚመረቱ LFP ባትሪዎችን ይጠቀማሉ።
አሁን የተጣለው የ25% የቀረጥ( Tax) ክፍያ ለመኪና አምራቾች ከቻይና  LFP ባትሪዎችን በቅናሽ በማስገባት ያገኙት የነበረውም Advantage ሙሉ በሙሉ ያስቀረዋል።

#LFP_Batteries #USA #Tax
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አሜሪካ ላይ አዲስ መኪና ለመግዛት ካሰቡ ሰዎች ውስጥ 80% የሚሆኑት የኤሌክትሪክ መኪኖች የመግዛት ፍላጎት አላቸው።


ስለ ኤሌክትሪክ መኪኖች ሲነሳ ብዙ ጊዜ እንደ መሞገቻ ነጥብ ሰዎች ከሚያነሱት ውስጥ " ማንም አይፈልጋቸውም" የሚለው ሃሳብ ነው ። ነገር ግን እንደ Cox Automotive የዳሰሳ ጥናት መረጃ መሰረት 80% የሚሆኑ አዲስ መኪና ለመግዛት ያሰቡ አሜሪካዊያን የኤሌክትሪክ መኪኖችን ነው የሚፈልጉት። ብቸኛው ነገር መኪኖቹን አሁን ላይ አይደለም የሚፈልጓቸው። እንዳሉት በመጪው ከ3 እስከ 5 አመት ባለው ጊዜ ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ለመሸመት እና ለማሽከርከር ዝግጁ ይሆናሉ።


ይሄም ማለትም በ2030 ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጭ በጣም ይጨምራል። ከCox Automotive የዳሰሳ ጥናት ላይ የተገኙት ሁለት አበይት መረጃዎች
የመጀመሪያው አብዛኞቹ የመኪና ሸማቾች የኤሌክትሪክ መኪና በመጠቀማቸው የሚያገኟቸውን ጥቅማ ጥቅሞች አያውቁም። የመኪና አምራቾች በማስታወቂያዎቻቸው ውስጥ እነዚህን ጥቅማ ጥቅሞች አካተው ማሳየት ይኖርባቸዋል።

ሌላኛው ደግሞ አብዛኛው ሰው በቅርብ የሚያውቁት የኤሌክትሪክ መኪና የሚጠቀም ሰው ካለ አነሱም የመግዛት ፍላጎታቸው ይጨምራል።

#Electric_Cars #USA
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Renault: Rafaleን በፕለጊን ሃይብሪድ ቨርዥን ከፍ ባለጉልበት ሰራው።



Renault አዲስ መኪና ይፋ ያረገ ሲሆን መኪናው Rafale የተባለው ባለፈው አመት ላይ የወጣው የRenault አዲስ የSUV መኪና ስፖርት ቨርዥን በፕለጊን ሃይብሪድ የሃይል አማራጭ ነው።

መኪና Rafale E-Tech 4×4 300hp ሲሆን ከስሙ ተነስታቹ ምን ያህል የፈረስ ጉልበት እንዳለው መገመት አይከብድም።
ሴታፑ ቱርቦ ቻርጅድ የሆነ ባለ1.2 L 3ሲሊንደር ኢንጂን ከኤሌክትሪ ሞተር ጋር አጣምሮ የያዘ ሲሆን አንደኛው የፊተኛው Axle ላይ እና ሌላኛው ደሞ የኋለኛው ላይ የተገጠመ ነው።

200 የፈረስ ጉልበት ካለው ከስታንዳርዱ ፕለጊን ሃይብሪድ Rafale፤ Rafale E-Tech 4×4 300hp ሲነፃፀር ፍጥነቱ ከዜሮ እስከ 100 ለመድረስ ከ2 ሰከንድ የሚፈጥን ሲሆን በ6.4 ሰከንድ ውስጥ ፍጥነቱ 100Km/h ይገባል።የተገጠመለት 22 kilowatt hour ባትሪ ፓክ ተጨማሪ 100km በኤሌክትሪክ ሃይል እንዲጓዝ ያስችለዋል።

ስለ መሸጫ ዋጋው እስካሁም ምንም የተባለ ነገር ባይኖርም በመኸር ወር ለገበያ ይቀርባል።

#Renault #Rafale E-Tech 4×4 300hp #PHEV
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/22 12:18:19
Back to Top
HTML Embed Code: