Telegram Web Link
#ዜና

Alfa Romeo የአዲሱን CUV መኪናውን ስም ለመቀየር ተገደደ።


የጣሊያን መንግስት በ Alfa Romeo ፓረንት ካምፓኒ stellantis በጣም የተበሳጨ ሲሆን ለዚህም ምክንያት ሰሞኑን ባቀረብንላቹ ዜና መሰረት ካምፓኒው የAlfa Romeo Milano የተባለው መኪናውን ፖላንድ ሃገር ላይ እንዲመረት በመወሰኑ ነው።

ከዚህም በላይ የStellantis Ceo የሆነው Carlos Tavares መኪናው ከፖላንድ ይልቅ በጣሊያን ውስጥ የሚመረት ከሆነ ተጨማሪ 10,000 ዩሮ ያሶጣል ማለቱ ከፍተኛ ቁጣን የጫረባቸው ባለስልጣናቱ በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሃገሪቷ ላይ ከጣሊያን ውጪ ለተመረቱ ምርቶችን ጣሊያናዊ ስምን መስጠት እንዲከለከል የወጣውን ህግ አንስተው "Milano" የሚለውን ስም እንዲቀይር ካምፓኒውን ከሰውታል።

ካምፓኒውም የመኪናውን ስም ወደ Junior እንዲቀይር የተገደደ ሲሆን በሰጣ ገባው ምክንያት ለአዲሱ መኪና ነፃ ማስታወቂያ በማግኘቴ የጣሊያን መንግስትን ላመሰግን እወዳለው ብሎዋል።

#Alfa_Romeo #Junior
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቻይና ጀርመን ከምታመርተው የመኪኖች በላይ ኤክስፖርት ታረጋለች።


የቻይና የመኪና ኤክስፖርት ቢዝነስ በሚያስገርም ሁኔታ እያደገ ነው። እንደ China Association of Automobile Manufacturers መረጃ መሰረት በወርሃ March ቻይና 502,000 መኪኖችን ወደሌሎች ሃገራት ኤክስፖርት አርጋለች። ይህም ካለፈው አመት ሲነፃፀር በ38% እድገት አሳይቶዋል።

ኤክስፖርት የተደረጉትም ቀላል እና እና የንግድ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ 424,000 ቀላል ተሽከርካሪዎች የተቀሩት 78,000ዎቹ ደግሞ የንግድ ተሽከርካሪዎች ናቸው።

ቻይና በዚህ መጠን ኤክስፖርት ማረጓን ከቀጠለች በአንድ አመት ውስጥ ቁጥሩ ወደ 6 ሚሊየን ይደርሳል። ለንፅፅር ጀርመንን ብንመለከት ባለፈው አመት 4.1 ሚሊየን ተሽከርካሪዎችን አምርታለች።
ይህ ማለትም ጀርመን በአመት ውስጥ ከምታመርተው የተሽከርካሪዎች ቁጥር በ2 ሚሊየን ብልጫ ያላቸውን ተሽከርካሪዎችን ቻይና ኤክስፖርት ታረጋለች።

#Chinese_Car_Export
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BMW በኤሌክትሪክ መኪኖች ምርት እና ሽያጭን በጥሩ ሁኔታ ይዞታል።


BMW በቀላሉ እንደ Mercedes ፣ Audi ፣ Cadillac እና ሌሎች ልጠቅሷቸው የምችሏቸውን Legacy የቅንጦት ብራንዶችን በሽያጭ ረቷቸዋል።

Bloomberg እንደዘገበው እንደዚህ በጥሩ ሁኔታ ገበያውን ሊቆጣጠረው ከቻለባቸው ምክንያቶች መካከል ከዚህ በፊት ሽያጩ አሽቆልቁሎበት በነበረው i3 ክተሰኘው የኤሌክትሪክ መኪናው በከባዱ ስለተማረ ነው።

የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማምርት ሌላ አዲስ ማምረቻ በመገንባት ፋንታ የነዳጅ መኪኖችን በሚያመርትበት ተመሳሳይ ፕላትፎርም ላይ ተራ በተራ እያረገ እያመረተ ነው። አንዲሁም የራሱን የባትሪ ማምረቻ ገንብቶ ከማምረት ይልቅ እንደ የቻይናው CATL ካሉ የመኪና ባትሪ አምራቾች በመግዛት እራሱን ከቢሊየን ዶላሮች ከሚፈጅ የኢንቨስትመንት ወጪ አድኖዋል።

በቀጣይ አመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ "Neue Klasse"  ተብሎ የተሰየመውን የጣዩን የኤሌክትሪክ መኪና ጀነሬሽን ማምረት የሚጀምር ይሆናል። በጥሩ ሁኔታ የሚሸጡለት ከሆነ ትልቅ የሚባል ትርፍን ያስገኙለታል።

#BMW #Neue_Klasse
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ማሳሰቢያ

ይህ ዛሬ 22 መክሊት ህንፃ አከባቢ የደረሰ አደጋ ነው፡፡

እባክዎ! አሽከርካሪዎች በዝግታ፣ በማስተዋል እና በእርጋታ ያሽከርክሩ ራስዎንና ወገኖዎትን ከአስከፊው የትራፊክ አደጋ ይከላከሉ‼️
ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አዲስ አበባ ላይ ባለፉት 9 ወራት 286 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል :: እና በተቻለ አቅም አሽከርካሪዎች ፍጥነታችሁን ቀነስ አድርጋችሁ አሽከርክሩ :: እግረኞችም መሻገር ባሉባችሁ ቦታዎች እንዲሁም ዜብራ የሌለበት መንገድ ከሆነ አይተው በጥንቃቄ ይሻገሩ ::

ምንጭ - TMA

@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Boston Dynamics አዱሱን(Humanoid Robot) ሰው መሳይ ሮቦት ይፋ አደረገ።


አሁን ላይ ባለቤትነት በHyundai ስር የሆነው ሮቦቶች ላይ የሚሰራው የምርምር ተቋም Boston Dynamics ለ11 አመታት ያህል ሮቦትን እንዴት በተሻለ መንገድ መስራት እንደሚችል የተማረበትን Atlas የተባለውን ሮቦቱን ጡረታ አሶጣው።

ከተመረተበት 2013 ጀምሮ ከባድ የሚባል ኑሮን ያሳለፈው Atlas ከባድ እቃዎችን መወርወር ፣ መዝለል ፣ መገለባበጥ እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላል። አበልፃጊው ቡድኑ ብዙ ብዙ አይነት መሰናክሎችን እያበጁ ስለ ሮቦት መስራት የተማሩበት ሲሆን በእነዚህ ፈተናዎች ምክንያት የሮቦቱ ሰውነት ላይ የተለያዩ የግጭት እና የመጫጫር  ምልክቶች ይታዩበታል።

በመጨረሻም ጡረታ አሶጥተውት በምትኩ አዲስ 001 የተባለ ሰው መሳይ የሮቦት ቨርዥን ይፋ አድርገዋል።
አዲሱ ሮቦት እንደ Atlas የሃይድሮሊክ ሲስተም ከመጠቀም ይልቅ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ሲስተም ነው የሚሰራው።

#Hyundai #BostonDynamics
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

መኪናዎትን ቶሎ ለመሸጥ አስበዋል?

እንግዲያውስ የተለያዩ መኪኖቻችሁን በሁሌመኪና በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ
በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶዎችን) በመላክ 300 ብር ብቻ ቴሌብር ላይ ከላይ ባስቀመጥነው ስልክ ላይ በመክፈል መሸጥ እና ማከራየት ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

የንግድ ኤሌክትሪክ መኪናዎች አገልግሎት ለመስጠት ከነዳጅ መኪኖች ያነሰ ወጪ ያስወጣሉ?


ብሉምበርግ የአንድ Elite Home Care የተባለ Ford E-Transits መኪኖችን የሚጠቀም የጭነት አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ባለቤት አናግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል።
"የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለስራዬ መጠቀም ከጀመርኩ በሗላ ለጥገና እና ለቻርጅ የማወጣው ዋጋ በፊት የነዳጅ መኪኖችን ለመጠቀም ከነበረው ጊዜ ሲነፃፀር በአመት 6,500 ዶላር ወጪን አስቀርቶልኛል።"

ይሄ ጉዳይም የቤት የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጭ ላይ መቀዛቀዝ ቢኖርም የንግዶቹ የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ሽያጭ መጨመሩ አንዱ ምክንያት ነው።

የ Ford CEO Jim Farley አንዳለው E-Transit መኪናን በሚፈለገው ፍጥነት ማምረት አልቻልንም።
በመጀመሪያው እሩብ አመት 3,000 ገደማ የሚሆኑ መኪኖችን ሽጧል። ይሄ ማለትም በ147% እድገት አሳይቷል ነገር ግን እስካሁን በነዚህ መኪኖች ትርፍን እያገኘ አይደለም።

Ford Pro የተባለው የካምፓኒው የንግድ መኪኖች አምራች ክፍል በዚህ አመት ላይ ለFord ትልቁ የትርፍ ማዕከል ሆኖለታል።  በአመት ከ 8- 9 ቢሊየን ዶላሮች ትርፍን ሲያስገባለት ለዚህ ዋናው ቁልፍ ምክንያት የሆነውም ለጭነት አገልግሎት ሰጪ ደንበኞቹ የሚሰጠው የSubscription ሰርቪስ ነው።
ይሄ የSubscription ሰርቪስ በ2026 የFord Proን 20% ትርፍ ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል።

#Ford #electric # E-Transit
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Google Map ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ስቴሽን ቦታ ተካተተ።


Google የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮች ቦታን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለንን ፊቸር Goolge Map ላይ አካተተ። በመጪው ወር በAI( Artificial Intelligence) በመታገዝ ቻርጀሮቹ የሚገኙበትን ቦታ ዝርዝር መረጃ ማሳየት ይጀምራል።

መረጃው የተሰበሰበው እለት ተእለት ማፑ ላይ በሰዎች በሚሰጠው በሚሊየኖች የሚቆጠር አስተያየት ሲሆን ይሄም ትክክለኛ መረጃን እንዲይዝ እና በየጊዜው ከሚደረጉ ለውጦች ጋር አብሮ ማሻሻያ እንዲያደርግ ያደርገዋል።

Google ሌላ ተጨማሪ ፊቸርም ይዞ የመጣ ሲሆን ይሄም ቅርባችን ያለውን ቻርጀር ማሳየት፣ ምን ያህል አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ቻርጀሮች እንዳሉ እና የቻርጂንግ ፍጥነታቸውን ያሳያል። Google ይሄን ፊቸር የ Google ሲስተም ከተጫነባቸው መኪኖች ጀምሮ በአለም ዙሪያ ላሉ ተጠቃሚዎቹ በመጪው ወር ይፋ ያደርገዋል።

#GoogleMaps #ChargingStation
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አዲሱ Toyota Camry በሃይብሪድ አማራጭ ብቻ ነው የቀረበው


አዲሱ Toyota Camry በሃይብሪድ አማራጭ ብቻ የቀረበ ሲሆን የካምፓኒው 5ኛ ጀነሬሽን ሃይብሪድ  ሲስተም ነው የተገጠመለት። ይሄም 4 ባለ 2.5 L ሲሊደር Engine ከኤሌክትሪክ ሞተር ጋር የያዘ ሲሆን የሁለቱ ጥምረት Front wheel drive ሞዱ ላይ 225 የፈረስ ጉልበት ማመንጨት እንዲችል ያረገዋል።

አዲሱ የCamry All wheel drive ቨርዥኑ ላይ engineኑን ከኋላ ጎማዎቹ ጋር የሚያገኛኘውን የድሮው ሜካኒካል ሴታፕ በመተው የኤሌክትሪክ ሞተሩን ከኋላ Axleሉ ጋር አያይዞታል። ይሄም እስከ 232 የፈርስ ጉልበት እንዲያመነጭ ሲያስችለው አሁን ገበያ ላይ ካለው የCamry ሞዴል ሲነፃፀር በ30የፈረስ ጉልበት ብልጫ አለው።


Toyota Camry በሃይብሪድ አማራጭ ብቻ በመቅረቡ ምክንያት የሞተሩን ክብደት በመቀነስ ከlithium ion ባትሪው የሚመጣውን ሃይል ጨምረውለታል።  አዲሱ camry የነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ሞተሮቹ ተደምረው በሊትር 21kmዎች ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል።

ከToyota Prius ጋር ምን ያህል ልዩነት አላቸው ካላቹ Prius በFront wheel drive ቨርዥኑ በሊትር 24kmዎችን ይጓዛል። ነገር ግን  በall wheel drive ቨርዥን ላይ Camry ከPrius በሊትር 1.7km ብቻ ያነሰ ጉዞ ነው ሚያረገው።

ይሄም አዲሱ Camry የማድረሻ ዋጋውን ጨምሮ በ29,000 ዶላር ፀደይ ላይ ለገበያ ሲቀርብ የPriusን ገበያ ይቀማ ይሁን? የሚለውን መመልከት አጓጊ ያረገዋል።

#Toyota_Camry #Toyota_Prius #Hybrid
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ  ሁሉንም Cybertruck መኪኖቹን ወደ ካምፓኒው recall አደረገ።


ቴስላ ሁሉንም ያመረታቸውን cybertruck መኪኖች recall ያደረገ ሲሆን አንዴ ልሌላ ጊዜው በቀላል የሶፍትዌር update የሚስተካከል ችግር አይደለም።

The National Highway Traffic Safety Administration እንደተናገረው 3,878 Cybertrucks መኪኖቹ ወደ ካምፓኒው ለጥገና ተጠርተዋል።  እንዲጠሩበት ምክንያት የሆነውም ችግር የሃይል መስጫ(የነዳጅ ) ፔዳሉ በመላላት ቦታውን ለቆ ውስጥ ላይ ካለው የመኪና ክፍል ላይ ነክሶ ይቀራል።

NHTSA እንዳለው ነክሶ የቀረው ፔዳል የነዳጅ መስጫውንም ሆነ የፍሬን መያዣ መስመሩን በማቋረጥ ፍጥነት እንዳንጭምር ወይም መኪናውን ማቆም እንዳንችል በማረግ ለትራፊክ ለአደጋ ያጋልጣል።

ቴስላም የተለያዩ የመኪና ባለቤቶች ይሄች ችግር በምስል ቀርፀው የማህበራው የትስስር ገፆች ላይ ካጋሩ ቡሃላ የCybertruck መኪኖቹ ላይ ያለው ሽያጭ አቁሞዋል።

#Tesla #Cybertruck
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

ከ 600 ሺህ ብር ጀምሮ የሚሸጡ መኪኖች እንዲሁም የሳምንቱን ያገለገሉ እና አዳዲስ መኪኖች ዋጋ ማወቅ ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ ሁሌመኪና ላይ በመግባት የተለያዩ መኪኖችን ሙሉ መረጃቸውን ከነዋጋቸው ያገኛሉ :: እንዲሁም በሁሌመኪና በቀን በሺዎች ተመልካች ባለው ቻናላችን ላይ በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ :: ተጨማሪ መረጃ በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶዎችን) በመላክ 300 ብር ብቻ ቴሌብር ላይ ከላይ ባስቀመጥነው ስልክ ላይ በመክፈል መሸጥ እና ማከራየት ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

Toyota Highlander ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴል ሆነ።


Toyota የኤሌክትሪክ መኪኖችን መስራት ላይ ለዘብ ያለ ነው ተብሎ ሲተች የነበረ ቢሆንም ከዚህ ሃሳብ በተለየ አንዱን የመኪና ሞዴሉ ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አርጎታል። CarBuzz ዘገባ Toyota Highlander ወደ በኤሌክትሪክ ብቻ ወደ የሚገኝ የመኪና ሞዴል መለወጡን አረጋግጧል።

መኪናው በአሜሪካ Kentucky ግዛት ውስጥ በሚገኘው የቶዮታ ማምረቻ የሚመረት ሲሆን በሌክሰስ ዘርም ይኖረዋል።
ይሁን እንጂ አስከ 7 ሰው መያዝ የሚችለው Grand Highlander የነዳጅ ሆኖ የሚቀጥል ሲሆን የፕለግ-ኢን ሃይብሪድ አማራጭ ይጨመርለታል።

የኤሌክትሪኩ Highlander መቼ ለገበያ ይፋ እንደሚሆን የጊዜ ሰሌዳ የቀመጠለት ባይሆንም ቶዮታ አዳዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖችን 2026 ላይ በአሜሪካ  ገበያዎች ላይ ያወጣል።
በተጨማሪ CarBuzz ካሞፓኒው "BZ" የሚለውን የስየማ መንገዱን ይበልጥ አሳማኝ እና በሰው ዘንድ የተለመደ በሆነ የአሰያየም መንገድ ሊለውጠው እያሰበ እንዳለ ዘግቦዋል።

#Toyota #Highlander #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nissan የሽያጭ እና የትርፍ ቅድመ ትንበያው ዝቅ አደረገ።


Nissan በወርሃ March ለሚጠናቀቀው የሽያጭና የትርፍ የበጀት አመት ቅድመ ትንበያን ዝቅ አደረገ ።
የNissan CEO ንግግር ከመጠን በላይ አዎንታዊ የነበር ቢሆንም አሁን ላይ  3.44 ሚሊየን ተሽከርካሪዎች እንሸጣለን ብለው ይጠብቃሉ። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው ዒላማ በትንሹ ማለትም ከ100,000 ፍሬ ዝቅ የተደረገ ሲሆን ይህም ራሱ ከ3.7 ሚሊዮን ፍሬ  ተብሎ ከነበረ የቅድመ ትንበያ ዝቅ የተደረገ ነው። 

በእውነቱ Nissan ሽያጭ 2019 ላይ 5.5 ሚሊየን ተሽከርካሪዎች ከሸጠበት ጊዜ ጀምሮ ወጥ በሆነ መልኩ እየወረደ ነው የመጣው።
በተጨማሪም የሚጠበቀው የሽያጭ መቀነስ ገቢውን፣ የሥራ ትርፉንና የበጀት አመቱን አጠቃላይ ገቢውን ይቀንሳል። ከዚህም በላይ ኩባንያው ቀደም ሲል በኒሳን የሽያጭ ትንበያዎች ላይ ተመስርተው ኢንቨስት ላደረጉ አቅራቢዎች የገንዘብ እርዳታ ይከፍላል። ስለዚህ እነዚህ ወጪዎች በመጪው ገቢው ቁጥር ላይ ይንጸባረቃሉ ።

#Nissan
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኢንዱስትሪ ለCopper(ለመዳብ) ያለው ፍላጎት ጨምሮዋል።


የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለመስራት የሚያስፈልጉ እንደ lithium ያሉ ጥሬ እቃዎች ዋጋ ሲቀንስ የሌሎቹ ዋጋ ደሞ ጨምሮዋል። እንደ የሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ ላይ የሚሰራው Trafigura የተባለው ኩባኒያ ጥናት መሰረት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ምርት መስፋፋት ጋር ተያይዞ Copper (መዳብ) ላይ ያለው ፍላጎት በመጪው 10 አመታት ውስጥ በጣም እንደሚጨምር ይገመታል።

ኩባኒያው እንደተናገረው ከ10 ሚሊየን ቶን 1/3ኛው የመዳብ ፍላጎት ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራች ካምፓኒዎች ነው። አሁን ላይ የመዳብ ዋጋ በLondon Metal Exchange በቶን 10,000 ዶላር ገብቶዋል።

ለዚህም ምክንያት የሆነው አቅርቦት ላይ ባለው እጥረት እና ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ከአቅርቦቱ ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ ነው። የዘርፉ ተንታኖች የመዳብ ገበያው በዚህ አመት 26 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን እጥረት እንደሚያጋጥመው ገምተዋል።

#EV_Industries #Copper
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Ranger Rover Sport SV በካምፓኒው ታሪክ ትልቅ የተባለውን ፍሬን ተገጠመለት።


አዲሱ Ranger Rover Sport SV ካምፓኒው ከዚህ በፊት ተጠቅሞት ከሚያውቃቸው በላይ ትልቅ የሆነ ፍሬን ተገጥሞለታል። ግዙፍ ባለ 8 Piston የፊት Caliperዎች እና ከ400mm ወይም 17inch በላይ የሆነ የሴራሚክ ዲስክ አለው።

ይህ ማለትም ከአንዳንድ የመኪኖች ጎማ እራሱ ይሚበልጥ ሲሆን አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ላይ ትልቅ የሚባል ፍሬን ከሆነ ከLamborghini Urus መኪና ፍሬን ጋር ተመሳሳይነት አለው።

ፍሬኑ ከስታንዳርድ በቅይጥ ብረት ከሚዘጋጁት ፍሬኖች በ34 km ያነሰ ክብደት ያለው ሲሆን ቶሎ የሚያልቅ አይነትም አይደለም። Range Rover እንደተናገረው የመኪናው 4 ሞዴሎች 1,600 km ኖርማል መንገድ ላይ፣ 990 km ትራክ ላይ ተነድተው የፍሬን ጫማቸው ከአገልግሎት እድሚያቸው ላይ ገና 30% ያህል ይቀራቸዋል።

የ180,000 ዶላር መነሻ ዋጋ ያለውን መኪና ለሚገዛ ሰው የፍሬን ዋጋ ያን ያህል ቁብ ሚሰጠው ነገር ባይሆን ለመቀየር በሺ የሚቆጠሩ ዶላሮችን ያሶጡታል። ይሄ የፍሬን ሲስተምም የመኪናውን የመሸጫ ዋጋ በ15,000 ዶላር ከፍ እንደሚያረው ተገምቶዋል።

#Ranger_Rover_Sport_SV #ceramic_Breaking
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nissan አዲስ Qashqai SUV መኪና አውሮፓ ላይ ይፋ አረገ።


Nissan የተሻሻለውን የQashqai SUV መኪና ቨርዥኑን አውሮፓ ላይ ይፋ አድርጓል። ተሽከርካሪው  አዲስ የfront-end ዲዛይን ሲኖረው እንዲሁየኋላው ስታይል ላይም  ማሻሻያ ተደርጎበታል። በአውሮፓ ውስጥ የNissan የመጀመሪያው የGoogle ሲስተምን ያካተተ ተሽከርካሪ ነው። ተጨማሪ ማሻሻያዎች እንደ Around View Monitor፣ ለፓርኪንግ አገልግሎት የሚሆን bird's eye view (የወፍ በረር እይታ) የተደረጉበት ሲሆን ለተሻሻለው የDriving Assistance ፊውቸር ተስማሚ ነው።

Qashqai ሁለት የኃይል አማራጮችን ይዞ ቀርቦዋል። የመጀመሪያው Mild Hybrid ነው ሲሆን Nissan እስካሁን ዝርዝር መረጃዎችን አልሰጥበትም።

E-Power ብሎ የሰየመው ሁለተኛው የኃይል አማራጩ ግን ከሌሎች የE-Power ተሽከርካሪዎች በተለየ መልኩ ይሰራል። ለ140 kilowatt የኤሌክትሪክ ሞተሩ የኤሌክትሪክ ሃይልን ለማመንጨት  ባለ 3 ሲሊንደር ቱርቦ engine ይጠቀማል።
ትራንስሚሽን (gear box) የሌለው ሲሆን ሞተሩ ቀጥታ ከጎማው ጋር ነው የተያያዘው።

አዲሱ Qashqai እንግሊዝ በሚገኘው የNissan ማምረቻ ውስጥ መመረት የጀመረ ሲሆን በተጨማሪም  በካናዳ ገበያ ላይ መሸጥ የሚጀምር ይሆናል።

#Nissan #Qashqai
@OnlyAboutCarsEthiopiw
#ዜና

የTesla መኪኖች ከሁሉም የመኪና አይነቶች ዝቅተኛ የሆነ የጥገና ወጪ ነው ያላቸው።


የቴስላ መኪኖች በአሜሪካ ላይ ከየትኛውም የመኪና ብራንድ ያነሰ የጥገና ወጪ ነው ያላቸው። በቅርቡ Consumer Reports እንዳረገው የዳሰሳ ጥናት የራሱን አባላት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ መኪናቸውን ለማስጠገን ከኪሳቸው ያወጡትን ገንዘብ በመጠየቅ እና የየተለያዩ የመኪና ብራንዶች በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ለጥገና የሚያወጡት ወጪ ምን ያህል ሊሆን እንደሚች ሲያነፃፅር  በ4,000 የአሜሪካ ዶላር የጥገና ወጪ Teslaን ዝቅተኛው ሆኖ አግኝቶታል።
በ4,900 ዶላር የጥገና ወጪ Buick እና Toyotal ዝርዝሩ ላይ ቴስላን ተከትለውም ተቀምጠዋል።

ከዚ በጠቃራኒው ከፍተኛ የጥገና ወጪ የሚያወጡት የRange Rover መኪና ባለቤቶች ሲሆኑ በ10 አመት ጊዜ ውስጥ 19,250 የአሜሪካ ዶላር ይወጣሉ። ይሄም ከPorsche መኪና የጥገና ወጪ በ5,000 ዶላር ብልጫ ያለው ሲሆን Porsche የደረጃ ሰንጠረዡ ላይ 2ኛ ውዱ የጥገና ወጪ የሚጠይቅ የመኪና ብራንድ ሆኖ ተቀምጦዋል።

#Tesla #RangeRover #Repair_Cost
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Smart አስካሁን ካመረተው ትልቅ የሚባለው መኪና ይፋ አረገ።


በፓረንት ካምፓኒው Geely ስር የሚተዳደረው እና ትናንሽ መኪኖችን በማምረት የሚታወቀው Smart ተለቅ ባሉ የመኪና ሞዴሎች ለመምጣት ያሰበ ይመስላል። ያው ከብራንዱ መኪኖች አንፃር ተለቅ ያለ።

smart አዲስ #5 የተባለ የmid-size SUV መኪና  concept ይዞ የቀረበ ሲሆን በፓረት ካምፓኒው Geely SEA በተባለው ፕላትፎርም ነው የተሰራው። ፕላት ፎርሙ Smartን ጨምሮ እንደ Geely ፣ Volvo እና zeekr ባሉ የፓረንት ካምፓኒው የመኪና ብራንዶች በተለያየ ሳይዝ ላሉ መኪኖቻ የሚጠቀሙት ነው።

Smart አንዳለው መኪናው በ800 ቮልት አርክቴክቸር የተሰራ ሲሆን ትልቅ የሆነ ባለ 100 kilowatt hour ባትሪ ፓክ ነው የተገጠመለት። ይሄም በፍጥንት ቻርጅ መደረግን የሚያስችለው ሲሆን በአንድ ቻርጅ ከ550 km በላይ ይጓዛል።

ለገበያ መች እንደሚቀርብ ይፋ የሆነ ባይሆንም የ#5 የምርት ቨርዝኑን በያዝነው አመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ይፋ የሚሆን ይሆናል።

#Smart #Geely
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/26 23:17:29
Back to Top
HTML Embed Code: