Telegram Web Link
#ዜና

Elon musk ቀጣይ አመት ላይ Tesla Roadster የተሰኘውን መኪናቸው ይለቀቃል አለ።

ቴስላ ይህ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚንቀሳቀሰውን የአለማችን ፈጣኑ መኪና ይሆናል ያሉትን tesla roadster የተሰኘውን Hyper Car በቀጣይ አመት ላይ ለገበያ እንደሚቀርብ የተናገሩ ሲሆን

የቴስላ መስራች እና ceo የሆነው elon musk እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ሃሳቦችን ተናግሮ ተግባር ላይ ያልዋሉ ቢሆንም እንደተናገረው ከሆነ" የሮድስተር ምርት ዲዛይን ያለቀ ሲሆን በዚህ አመት መጨረሻ ላይም ይፋ ይሆናል"

እናም "ይሄን የመሰለ መኪና አይኖርም ፣ ያው መኪና ብላቹ ልጠሩት ከደፈራቹ ጥሩት😂" ብሎዋል።

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#Tesla #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Huawei በ 1 ሰከንድ ቻርጅ አንድ ኪሎ ሜትር እንድንጓዝ የሚያስችለንን የመኪና ቻርጀር እያበለፀገ ነው

አሪፍ አሪፍ flagship ስልኮችን እና ለሰፊው ማህበረሰብ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ስልኮችን በማምረት የምናውቀው Huawei በኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይም ትልቅ ተፅኖ ያለው ካምፓኒ ነው።

አሁን ላይ እያበለፀጉት ያለው ሱፐር ፋስት የመኪና ቻርጀር በአምስት ደቂቃ ቻርጅ ብቻ እስከ 260 ኪሎሜትር ጉዞ እንድናደርግ የሚያስችለን ቻርጀር ሲሆን 600 Kilowatt ከ 600amps ጋር ነው

እነዚህን ቻርጀሮች ለማምረት ከፍተኛ ወጪ ያለው ቢሆንም Huawei በ Kwh (Kilowatt hour) ያለውን ክፍያ እንደሚቀንሱ ተናግረዋል።

ድንቅ ቀን ተመኘን
#Huawei #Charger
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቻይና የአውቶሞቲቪ ኢንዱስትሪ ላይ አንዳንድ መንገጫገጮች እየታዩ ነው

ከሰሞኑ ወደ ቻይና እየተሰማ ያለው ዜና አንዳንድ የመኪና አምራች ካምፓኒዎች ትንሽ ከበድ ያለ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ያሳያል። Neta Auto የተባለው የመኪና አምራች በቅርቡ ለአመራሮቹ ይሰጥ የነበረውን ቦነስ ያዘገየ ሲሆን Hi-Phi የተባለው የመኪና አማራች ካምፓኒ ደግሞ ለ 6 ወር ያህል ማምረቱን ሊያቆም ነው።

ይህም ክስተት ካምፓኒዎች ግልፅ የሆነ የካሽ እጥረት ያገጠማቸው እንደሆነ ሲያሳይ የቻይና ሚዲያዎች እየዘገቡት እንዳለውም Changan Hi-Phi ሊገዛው ይችላል ።

(ቺግ ዳ) የተባለችው የሃይፋይ ካምፓኒ (research & development center)መቀመጫ የሆነችው ከተማ እና saudi arabia sovereign wealth እዚህ ሽያጭ ላይ ተጫራቾች እንደሚሆኑም ተዘግቧል።

ድንቅ ቀን ተመኘን
#China #Hiphi
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የተባበሩት የአውቶሞቲቭ ሰራተኞች ህብረት(UAW) የmercedes ሰራተኞች የህብረቱ አካል መሆን እንደሚፈልጉ ተናገረ

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአሜሪካ ቴነሲ ግዛት ውስጥ የሚገኘው የ Volkswagen ማምረቻ ውስጥ 50% የሚሆኑት ሰራተኞች የUAW አባል መሆን እንፈልጋለን ብለው ድምፅ የሰጡ ሲሆን አሁን ላይ (Alabama) ግዛት ውስጥ የሚገኘው የ Mercedes ማምረቻ ሰራተኞች ተመሳሳይ የድምፅ ቁጥር ላይ ደርሰዋል።

በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በአሜሪካ (UAW) የህብረቱ አካል ያልሆኑ ሰራተኞችን ወደህብረቱ ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ያለ ሲሆን የመኪና አምራች ካምፓኒዎችም 70% ያህል ሰራተኞቻቸው የዚህ ህብረት አባል ለመሆን ድምፅ ከሰጡ ህብረቱ ከካምፓኒው እውቅናን የሚጠይቅ ሲሆን ሰራተኞቹ ድምፅ እንዳይሰጡ የሚከለክል አምራች ካምፓኒ ላይ የሃገሪቱ የሰራተኛ ጉዳዮች ቦርድ እርምጃ ይወስዳል።

አሁን ላይ ባለው አሰራር ብዙ የመኪና አምራች ሰራተኞች ተገቢውን ደሞዝ እና የስራ እድገት እያገኙ እንዳልሆነ ቅሬታ ይሰማል።

#Mercedes #UAW
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የአውሮፓ የመኪና አምራቾች ህብረት በአውሮፓ(EU) ህብረት የወጣውን (ICE ban) የነዳጅ መኪኖች እገዳን አንቃወምም አለ

ባለፈው ሳምንት ሲዘገብ እንደነበረው የአሜሪካ የመኪና አምራች ካምፓኒዎች  በጆ ባይደን አገዛዝ የወጣውን የኤሌክትሪክ መኪኖች ምርትን የሚያበረታታውን (ICE ban) የነዳጅ መኪኖች ላይ የተጣለውን እገዳ ይነሳል በማለት መንግስትን እየሞገቱ ሲሆን

በአንፃሩ ደግሞ በአውሮፓ የሚገኙ የመኪና አምራቾች በአውሮፓ ህብረት በ2035 ሙሉ በሙሉ የነዳጅ መኪኖች ገበያ ላይ እንዳይውሉ የሚያግደውን ህግ አንቃወምም ቀድሞውንም ወደ ኤለክትሪክ መኪናዎች ምርት ለመግባት ብዙ ቢሊየን ዶላሮችን መድበን እየሰራን እንገኛለን ህጉ እንዲሻሻል ማድረጋችንም አይጠቅመንም ሲሉ ተደምጠዋል።

#EU #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቻይና የመኪና አምራች ካምፓኒ የሆነው BYD ሜክሲኮ ላይ ያለው ማምረቻው ወደ አሜሪካ መኪኖችን ኤክስፖርት እንደማያደርግ ተናገረ።

የአሜሪካ ፓለቲከኞች የቻይና መኪኖች በሜክሲኮ በኩል ኤክስፖርት እየተደረጉ የመኪና ገበያውን እንዳይቀላቀሉ ስጋት ያደረባቸው ሲሆን ሜክሲኮ ላይ ማምረቻ ያለው BYD ግን ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ ምንም አይነት መኪና ኤክስፖርት የማድረግ እቅድ እንደሌለው ተናግሯል።

የBYD ceo እንደተናገሩት ከሆነ "በአሜሪካ እና በቻይና መካከል ባለው ፖለቲካዊ ቁርሾ የቻይና መኪና አምራቾች ላይ ጫና በመኖሩ እና የኤሌክትሪክ መኪና ላይ ያለው ፍላጎት በመቀነሱ ገበያው ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ ገብቶዋል"

BYD ይሄን ይበል እንጂ ብዙዎች "ቻይና ላይ ለማምረት በጣም ምቹ የሆነ ነገር እያለ የረዥም ጊዜ እቅዳቸው ወደ አሜሪካ ገበያ ላይ መግባት ካልሆነ ለምን ሜክሲኮ ላይ ማምረቻ ገነቡ?" የሚለውን ጥያቄ ያነሳሉ። ምን እንደሚፈጠር ማየት ነው ::

#BYD #Mexico
@OnlyAboutCarsEthiopia
የአሜሪካ Massachusetts ግዛት ዋና ከተማ የሆነችው Boston የመንገድ ዳር የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮችን ልትገጥም ነው።

የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ብዙ ጊዜ የሚነሳው ቅሬታ እንደ አፓርትመንት እና ኮንዶሚኒየም ባሉ የጋራ መኖሪያዎች መሰረተ ልማት ባልተሟላበት ቦታ ላይ እንዴት ቻርጅ እናረጋቸዋለን የሚለው ጥያቄ የነበር ሲሆን
የቦስተን ከተማ ያመጣው ሃሳብ ግን ለዚ ቆንጆ መፍትሄ ይመስላል።

Electric & Green Spot ከሚባሉ ካምፓኒዎች ጋር ስምምነትን በመፍጠር የህንፃ ባለቤቶቹ ከሁለቱ ካምፓኒዎች ጋር በመሆን ከህንፃው ስር የህንፃውን የኤሌክትሪክ መስመር በመጠቀም (level two) የኤሌክትሪክ ቻርጀሮችን ሲገጥሙ ከሚያገኙት ትርፍ ላይም የህንፃ ባለቤቶቹ እና ካምፓኒዎቹ ይከፋፈላሉ።

በ መጪው 2 አመታት ውስጥ ወደ 250 የሚጠጉ የመንገድ ዳር ቻርጀሮችን ለመትከል ያሰቡ ሲሆን ቻርጀሮቹን ለየት የሚያረጋቸው እላያቸው ላይ የጠገጠመ የቻርጅ ገመድ የሌላቸው ሲሆን በምትኩ ለሁሉም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባለቤቶች ከተማ ውስጥ ያሉ ማንኛውም ቻርጀሮች ላይ ሰክተው መጠቀም የሚያስችላቸውን ተንቀሳቃሽ የቻርጅ ገመዶችን ያቀርቡላቸዋል።

በዚህ ሲስተምም የቦስተን ከተማ ለግንባታው ምን አይነት ወጪም ማውጣትም ሆነ ለቻርጀሮቹ አዲስ የኤሌክትሪክ መስመር በጀት አይጠበቅበትም።
#ዜና

የመኪና አምራቹ Honda ቨርቹዋል ሪአሊቲን ከእንቅስቃሴ በማድረግ በቨርቷል የምንመለከተው አለም የምር experience እያደረግነው ያለ እንዲመስለን የሚያረግን ዊልቼር መሳይ መቀመጫ አበለፀገ።

ሆንዳ UNI-ONE ሲል የሰየመው ይሄ ከ vertual reality መነፅር ጋር አንድ ላይ የምንጠቀመው ተንቀሳቃሽ መቀመጫ በ VR እየተጫወትነው ያለውን የGame experience አሻሽሎ የምር እንደሆነ ፣ የጨዋታው አካል እንደሆነ ያህል እንዲሰማን የሚያረገን ሲሆን

ጨዋታው ላይ እየበረርንም ሆነ እየተንሸራተትን ያለውን እንቅስቃሴ እንዲሰማን ሲል በአራቱን አቅጣጫ ሰውነታችን ባላንስ ወዳደረገበት በመንቀሳቀስ እና በመሄድ computer generated የሆነውን አለም በቆንጆ ሁኔታ experience እንድናደርገው የሚያስችለን መሳሪያ ነው።

#Honda #Wheelchair
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ሪቪው

የ Xiaomi የመጀመሪያው ኤሌክትሪክ መኪና


የመጀመሪያው መኪና Xiaomi SU7 በሁለት አይነት አማራጭ የቀረበ ሲሆን

SU7 (RWD)
- 73.6 Kwh ባትሪ ፓክ
- የ BYD ብሌድ ባትሪ
- በ 295 የፈረስ ጉልበት እና
- በ 688 የኪሎሜትር ሬንጅ ታገኛላችሁ ::

SU7 Max (AWD) ሞዴል
- 101 Kwh ባትሪ ፓክ
- በ CATL ባትሪ
- 664 የፈረስ ጉልበት እና
- በ 800 የኪሎሜትር ሬንጅ ይመጣሉ ::

ዲዛይኑን ከ Porsche Taycan 4S ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን አድርገው የሰሩት መኪና ነው :: ከ 0-100 ኪሎሜትር በሰአት ለመድረስ 2.78 ሰከንድ ብቻ ሲፈጅበት
ከ 100 ኪሎሜትር በሰአት ወደ ዜሮ 33.3 ሜትር ብቻ ነው ለመቆም የሚወስድበት :: ይህም የሆነው የተጠቀሙት በደንብ የሚታወቀውን የ Brembo ፍሬን ነው :: April ላይ የሚያቀርቡ ሲሆን መጀመሪያ ላይ 2,000 መኪኖችን ለሽያጭ እንደሚያቀርቡት ገልጸዋል ::

#Xiaomi #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BMW አዳዲስ የመኪና ውስጥ የentertainment ፊቸሮችን በመኪኖቹ ላይ መጠቀም እንዲቻል አደረገ

በጀርመን እና በፈረንሳይ ሃገር ለሚገኙ የBMW መኪና ተጠቃሚዎች መኪናቸው ውስጥ ሆነው ከፊት ላሉ ተሳፋሪዎች ከመኪናቸው ውስጥ በቀጥታ video stream እንደማድረግ፣ wifi hotspot መጠቀም እንዲችሉ እና ከኋላ ወንበር ላይ የ ቲያትር እስክሪን ላላቸው የመኪና ሞዴሎች ባለቤቶች ደግሞ ተከታታይ እና ወጥ ፊልሞችን ማየት የሚያስችላቸውን  amazon fire tv unlock ማድረግ እንዲችሉ አድርጎ አቀረበ።

እነዚህን ፊቸሮች ለመክፈት መኪናችን operating system 8 እና ከዛ በላይ የሚጠቀም መሆን ያለበት ሲሆን (MyBMW) በሚባለው የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ወርሃዊ 10 ዩሮ የsubscription እየከፈሉ unlimited የሆነን ዳታ መጠቀም ይችላሉ።


ብዙ የመኪና አምራቾች እንደዚህ አይነት የsubscription ፊቸሮችን በማዘጋጀት ብዙ ቢሊየን ዶላሮችን ወደ ኪሳቸው ማስገባት እንደሚችሉ ቢናገሩም እስከአሁን ሰው መኪና ውስጥ በ subscription ከፍሎ ለመጠቀም የሚፈልገው ፊቸር ምን እንደሆነ ግን አልደረሱበትም።

#BMW
@OnlyAboutCarsEthiopia
በአለም አቀፍ ደረጃ የትኛው የመኪና የሞተር አይነት ከዚህ በሗላ እየበዛ ይመጣል ብላችሁ ታስባላችሁ?
Anonymous Poll
6%
የነዳጅ ሞተር ያለው መኪና
42%
ሀይብሪድ ሲስተም የሚጠቀም መኪና ወይስ
52%
ኤሌክትሪክ መኪና
#ዜና

ቅንጡ የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ Polestar በእግሩ ለመቆም 950 ሚሊየን ዶላር ብድር ወሰደ።

ባለፈው ወር ላይ Volvo በስሩ ያለውን polestar ከተባለው የኤሌክትሪክ መኪና ብራንዱ ላይ ያለውን አብዛኛውን ድርሻ ለራሱ Parent ካምፓኒ ለ Geely የሸጠለት ሲሆን ለዚህም ምክንያት የሆነውም የመኪና ብራንዱን በገንዘብ እጥረት ምክንያት ማስቀጠል ስለከበደው ነው።

Polestar እንደተናገረው ከሆነ የ2025ቱን እቅዱን ለማሳካት እና ምርቱን ቀጥ አርጎ ለማስቀጠል 1.3 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው የተናገረ ሲሆን አሁን ላይ ከ 12 አለም አቀፍ ባንኮች የ950 ሚሊየን ዶላር ብድር እንዳገኘ ተገልጿል።

Polestar በዚህ አመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ Polestar 3 እና Polestar 4 የሚባሉት መኪኖቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ሲገቡ ትልቅ ለውጥን የሚጠብቅ ሲሆን በአመቱ መጨረሻ ላይም የሁለት አሃዝ የእድገት ትርፍ ላይ እደርሳለው ብሎ አቅዶዋል።

#Polestar
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በጣም ቅንጡ የሆኑ መኪኖችን በማምረት የሚታወቀው Rolls Royce ትእዛዝ ወስዶ እየሰራው የነበረውን አንድ custom መኪና ለመጨረስ 4 አመት ወሰደበት።


"እውነተኛ የእጅ ጥበብ ስራዎች ጊዜ ይወስዳሉ" አንድ መኪናውን በትእዛዝ ማሰራት በፈለገ customer  ላይም የተፈጠረው ይሄ ነው።

ይሄ archedia droptail ተብሎ የተሰየመውን በእጅ ውስብስብ እና ጊዜ በሚወስድ መልኩ ልቅም ተደርገው ከሚሰሩ (coachbuilt cars) ተብለው ከሚጠሩ የመኪና አይነቶች ውስጥ የሚመደበውን መኪና ሰርተው ለማስረከብ ድፍን 4 አመታት የፈጀባቸው ሲሆን ውስጥ ላይ የተጠቀሟቸውን የእንጨት ውጤቶች ለየትኛውም የአየር ሁኔታ ተስማሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ሲሉ እና ከመሰነጣጠቅ እንዲጠብቃቸው ሲሉ የእንጨት መልካቸውን ሳይለቁ የካርበን ፋይበር ልባስ አበጅተው የሸፈኗቸው ሲሆን ይሄ ስራ ብቻ ከ 8,000 ሰአታት በላይ ወስዶባቸዋል።

ለዚህም የጥበብ ስራቸው 30 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላሮችን ተቀብለዋል።

#RollsRoyce
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Bugatti ታዋቂ የነበረበት የ W16 ሞተር ትቶ ወደ PHEV(Plug-in Hybrid) V16 ሞተር መጠቀም ጀመረ።


የፈረንሳዩ በጣም ፈጣን እና ቅንጡ የሆኑ Hyper Cars አምራች የሆነው Bugatti 2005 ላይ Bugatti Veyron በሚል የሞዴል ስም በ 16 ሲሊንደር ሞተር ከ 4 ቱርቦ ቻርጀሮች ጋር ፣በ 1001 የፈርስ ጉልበት፣ እስከ 431 ኪሎሜትር በሰአት በሚደርስ ፍጥነት፣ በ1.2 ሚሊየን ዶላር ለገበያ ቀርቦ አለምን ጉድ ያስባለው መኪናው ላይ ፤

ቀጥሎም 2019 በሰአት እስከ 490 ኪሎሜትር በሚደርስ ስፒድ የአለማችን ፈጣኑ መኪና ተብሎ የብዙዎችን አፍ ያስከፈተው  Bugatti Chiron የተሰኘው ሞዴሉ ላይ ይጠቀም የነበረውን ዝነኛውን W16 ሞተሩን ትቶ አሁን ላይ ወደ V16 ሞተር ከሃይብሪድ ሲስተም ጋር ወደሚጠቀም ሞተር ምርቱን የለወጠ ሲሆን አዲሱ ሞተሩ ላይ በከፍተኛ መጠን carbon fiber ተጠቅሞዋል።

#Bugatti
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የነበረው ፍላጎት መቀነስ ለ Fiat Panda አዲስ ጅማሬን ፈጠረለት።

Panda ከ1980 ጀምሮ እስካሁን በጣሊያኑ የመኪና አምራች Fiat ከዘመን ዘመን እየተሻሻለ ከ40 አመታት በላይ ገበያ ላይ የቆየ ሃች ባክ ቦዲ ስታይል ያለው መኪና ነው ::

አሁን ላይም በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ላለው ፍላጎት እየቀነሰ በመምጣቱ fiat የቀድሞ ሞዴል መኪናውን ወቅቱን ያማከለ ማሻሻል አድርጎበት pandina በሚል ስም ለገበያ ያቀረበው ሲሆን እንደ ፊያት ካምፓኒ ገለፃ ከሆነ ጣሊያን ውስጥ ቢያንስ እስከ 2027 ድረስ panda የተሰኘው ሞዴል መኪናው መመረቱን ይቀጥላል።

#Fiat
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ታዋቂው የመኪና አምራች Ford ለመኪኖቹ የ 800 ቮልት ባትሪ ሲስተም እያበለፀገ ነው


ከ4 አመት በፊት (multi voltage system) ብለው የሰየሙትን እንደ ኤሌክትሪኩ ሃመር ያሉ ትልቅ ባትሪ ፓክ ያላቸው መኪኖች ቻርጅ ለማድረግ የሚወስዱትን ጊዜ ለማሳጠር የሚጠቅመውን የ 800 ቮልት ባትሪ ሲስተም ፈጠራቸውን ፓተንት የወሰዱ ሲሆን ከ ጀነራል ሞተርስ አልቲየም ፓክ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ቢሆንም የ GM ቤዝ ሲስተም ግን ባለ 400v ነው ::

የሲስተሙ አሰራር ትላልቅ ባትሪ ፓክ ያላቸው መኪኖች ሁለት ባለ 400 ቮልት ፓክ ሲኖራቸው ቻርጅ በሚደረጉበት ወቅት ቶሎ ቻርጅ እንዲያረጉ ሲባል ሁለቱን ወደ አንድ 800 ቮልት ፓክ የሚቀይር ነው።

#GM #Ford
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

ያለ ኮሚሽን መኪናዎትን በቀላሉ ይሽጡ

መኪናዎትን ለመሸጥ እና ለማከራየት በቀላሉ የመኪናዎትን ፎቶ እና ቪዲዮ ወደእኛ በመላክ አስተዋውቀው መሸጥ እንዲሁም ማከራየት ይችላሉ ::

ፎቶ ብቻ - 300 ብር (ኢንስታግራም,ቲክቶክ እና ቴሌግራም ላይ ፎቶዎቹን እንለቃለን)
ፎቶ እና ቪዲዮ - 1000 ብር (ኢንስታግራም,ቲክቶክ እና ቴሌግራም ላይ ፎቶዎቹንም ቪዲዮውንም እንለቃለን የቪዲዮ ድምፅ ግን በዮናታን ደስታ የምንሰራ ይሆናል)

ክፍያውን በቴሌብር ብቻ የምንቀበል ሲሆን የሚከፈለውም በ 0911663121 ስልክ ላይ ነው :: ድርጅቶችም ከእኛ ጋር መስራት ይችላሉ ደረሰኝ ስለሚያገኙ ::

የመኪናዎትን ፎርሙን የሚሞሉበትን ሊስት እንድንልክሎ እና ለተጨማሪ መረጃ በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም በ @hulemekinaadmin መልእክት ይላኩልን ::

@hulemekina
አዲስ_መኪኖችን_ከመግዛታችሁ_በፊት_በቀላሉ_ቼክ_ማድረጊያ_ቼክሊስት.pdf
887.2 KB
#ጠቃሚ_መረጃ

አዲስ መኪና ስትገዙ በቀላሉ ቼክ ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች የያዘ ቼክሊስት ነው :: ፕሪንት አድርጋችሁ ለመጠቀም አመቺ አርገን ነው የሰራነው PDF ነው :: በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የነበረ ስለሆነ በድጋሚ የለቀቅነው ::
እንዴት መጠቀም እንደምትችሉ ሙሉ ቪድዮ ዩትዩብ ላይ ተለቋል ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/rt63O2HVi-4

#NewCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ጥያቄ

እነዚህ የመኪና ቀለሞች ኢትዮጵያ በሚገኙ መኪኖች ምን ያህል ፐርሰንት ይኖራሉ ብላችሁ ታስባላችሁ?

መልሳችሁን ከታች ባለው ምርጫ ላይ ያስቀምጡ ::

ይህንን ፖስት የሰራነው ለአፍሮሊንክ ፔጅ ነበር :: ነገር ግን የእናንተንም ሀሳብ ማወቅ ስለፈለግን ነው ::
ምን አልባት ስለ ኤሌክትሪክ መኪኖች እንዲሁም ስለመኪና እኛ የምንሰራቸውን ቪዲዮዎች እነሱ ገጽ ላይ ታገኛላችሁ :: የቴሌግራም ገጻቸው
👇🏽👇🏽👇🏽
@afrolink_motor

እናንተም ከመኪና ጋር የተገናኙ ካምፓኒ ማለትም (መኪና አስመጪ፣እስፔር ፓርት አስመጪ፣ጋራዥ እና የመሳስሉት) ኖሯችሁ ሶሻል ሚዲያችሁን እኛ ማኔጅ እንድናደርግ የምትፈልጉ ከሆነ በ 0911663121 ላይ በመደወል እኛን ማግኘት ትችላላችሁ ::

@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/27 09:23:00
Back to Top
HTML Embed Code: