Telegram Web Link
የ 2024 የመጀመሪያው City Circuit የመኪና ውድድር
(February 25,2024)

የነገው የመኪና ውድድር በ Kilinto Industrial Park ይካሄዳል :: እዛ መታችሁ መመልከት የምትፈልጉ ትኬት በር ላይ የምታገኙ ሲሆን ዋጋውም 100 ብር ነው :: የሚጀምረው 3 ሰአት ላይ ሲሆን Kilinto Industrial Park Location የምትፈልጉ ከሆነ ከስር ታገኙታላችሁ ::

https://maps.app.goo.gl/aZ32n8U7XpZ2uz96A?g_st=ic

@OnlyAboutCarsEthiopia
የትላንትናው የመኪና ውድድር ላይ መተው ነበር?
Anonymous Poll
14%
መጥቼ ነበር
86%
አልመጣሁም ነበር
#ዜና

አሜሪካ ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪኖች ብዙ ውድድሮች ላይ በጣም እያሸነፉ በመሆኑ ውድድር ላይ እንዳይሳተፉ ታገዱ

በ USA ላይ በሚካሄዱ ብዙ የመኪና ውድድሮች ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች እንዳይሳተፉ መታገዱ የተነገረው  የኤሌክትሪክ መኪኖች ከነዳጅ መኪኖች በተሻለ (instant torque) ማለትም በትንሽ ሰከንዶች ውስጥ የመኪናው ከፍተኛ ፍጥነት ላይ ስለሚደርሱ ሲሆን  እንደ drag race ያሉ ውድድሮች ላይ የተሻለ ብልጫ ስላላቸው Top Gear የቲቪ ሾው ላይ ባደረጉት ቴስት መሰረትም ቀጥታ መንገድ ላይ ብቻ ሳይሆን ጠመዝማዛ መንገዶችንም ጭምር በጥሩ ፍጥነት እና ቅልጥፍና መወጣት ይችላሉ ።

በጣም ፈጣን የሚባሉ (muscle car) አማራች ካምፓኒ የሆነው የ Dodge CEO በቅርቡ እንደተናገረው ከሆነ " የነዳጅ (internal combustion) መኪኖች የመጨረሻ የፍጥነት ገደባቸው ላይ ደርሰዋል! ከዚህ በላይ ወዴትም ሊሻሻሉ አይችልም" ብለዋል።

የእሁዱን የመኪና ውድድር የታደማችሁ የተወዳደራችሁ እንዲሁም ተወዳድራችሁ ያሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ :: በጣም ደስ የሚል ጊዜ ነበር :: ከዚህ በሗላ ቶሎ ቶሎ እንዲዘጋጅ እናደርጋለንም ብለዋል :: ኢንስታግራም ላይ የጠየቃችሁትን ጥያቄዎች ሰብሰብ አድርገን ተወዳዳሪዎችን ጠይቀናቸው ነበር :: ያልመጣም ብዙ ሰው ስለነበር ያመለጣችሁን ነገሮች ቀስ በቀስ የምንለቅ ይሆናል :: ይጠብቁን

መልካም ቀን ተመኘን
#electric #USA
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ ካምፓኒ አዲስ የጎማ መጠገኛ(tire repair kit) አበለፀገ።

ይሄን ቀላል የሚመስል እቃ ለማበልፀግ ረዥም ጊዜ የወሰደባቸው ሲሆን ከ 80 psi compressor ከሲላንት ጋር አብሮ  ነው የቀረበው:: በጎማችን ላይ ከ 6 ሚሊሜትር ያልበለጡ ቀዳዶችን በጊዜያዊነት ለመጠገን የምንጠቀምበት ሲሆን እንደ ቴስላ ካምፓኒ መረጃ መሰረት ከ 100 ኪሎሜትር የሆነን ጉዞ ልናረግበት አይገባም የድንገተኛ ጊዜ መገልገያ ብቻ ነው ብሎዋል።

ይሄም እቃ በ125 ዶላር አማዞን ላይ እየተሸጠ ይገኛል ::

መልካም ምሽት ተመኘን
#Tesla #Tire
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ሪቪው

በ2025 ለገበያ የሚቀርበው Renault 5 E-tech የተሰኘው የኤሌክትሪክ ሃች ባክ መኪና መሸጫ ዋጋው 27,000 ዶላር እንደሆነ ተገለፀ

አዲሱ Renault 5 በ 52 Kwh ባትሪ ፓክ እስከ 420 ኪሎሜትር የሚጓዝ ሲሆን ከ10-80%  ቻርጅ ለማድረግ በ100 Kilowatt DC ፈጣን ቻርጀር 30 ደቂቃ ብቻ ይፈጅበታል ።

110 Kilowatt ሞተር የተገጠመለት ሲሆን 147 የፈረስ ጉልበት ሲኖረው መላው  ክብደቱም 1300 ኪሎግራም ገደማ ሲሆን ለኤሌክትሪክ መኪና በጣም ቀላል እንደሆነ እየተነገረ ነው።

የውስጡን ዲዛይን እና ውጫዊ ገፅታው በጣም የሚያምር እና ብዙ ሰዎች ወደውት እንደ ቅሬታ ያቀረቡት ብቸኛው ነገር ዋጋውን ነው።

መልካም ምሽት ተመኘን
#Renault #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የ2024 subaru solterra ለገበያ ከመቅረቡ በፊት በስፔስፊኬሽኑ ተሻሽሎ በዋጋውም ላይ ትልቅ ቅናሽ ተደረገበት።

Subaru solterra ዋጋው ላይ 8000 ዶላር ያህል ቅናሽ ያደረገ ሲሆን  ይህን ያረገበት ምክንያትም በዋጋው ውድነት ($77,990)  ብዙ ሰው እየገዛው ስላልሆነ እና ከሱ ዋጋ በቅናሽ ተመሳሳይ መኪኖች ገበያው ላይ ሲኖሩ ለምሳሌ በ 20% በቅናሽ የ ቴስላ ሞዴል Y ዝቅተኛ ሞዴሉን በ FWD(Front Wheel Drive) ሆኖ ነገር ግን በተሻለ የሞተር አቅም ገበያ ላይ እናገኛለን ::

Subaru solterra ቤዝ ሞዴሉን ጨምሮ በዋጋ ቀነስ የሚለው ሞዴሉ  AWD( All Wheel Drive) ሲሆን ሁለቱም ላይ የተገጠመው ሞተር ባለ 160 Kilowatt ወደ 220 የሚጠጋ የፈረስ ጉልበት ሲያመነጭ በተገጠመለት 71 Kwh ባትሪ እስከ 410 ኪሎሜትር ይጓዛል።

አሁን ላይ በ 10% ቅናሽ አድርገው የባትሪ እና አንዳንድ ቴክ ፊቸሮችን አሻሽለው በ 69,990 ዶላር ለገበያ ያቀረቡት ሲሆን ዋጋው ከዚም መቀነስ እንዳለበት እና አሁን ቢሆን ውድ እንደሆነ እየተዘገበ ነው።

ውብ ቀን ተመኘን
#Subaru #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አዲሱ የቮልስ ዋገን መኪና Volkswagen ID.7 ቃል እንደገቡት በተሻለ  የድራይቪንግ ኪሎሜትር ሬንጅ ማለትም በአንድ ቻርጅ እስከ 700 ኪሎሜትር እንዲጓዝ ሆኖ ቀረበ።

አዲሱ ID.7 በተሻለ የድራይቪንግ ሬንጅ ባለው ባትሪ እና ቻት ጂፒቲ (Chat Gpt) የተሰኘው AI (Artificial Intelligence) ተካቶበት በአውሮፓ ገበያ ላይ የቀረበ ሲሆን ቤዝ ሞዴሉ በ 77 Kwh Pro ሞዴሉ ደግሞ 86 Kwh ባትሪ ፓክነው የተገጠመለት።

ባትሪውንም ከ10 - 80% ቻርጅ ለማድረግ 28 ደቂቃ ብቻ ሲወስድበት ሁለቱም ሞዴሎች ላይ RWD (Rear Wheel Drive)የሆነ 1 ባለ 240 Kilowatt እስከ 282 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጭ ሞተር ታገኛላቹ።

የእቃ መያዣው ተለቅ ያለ ስለሆነ ለቤተሰብ መኪናነት ለመገልገል ይበልጥ ተመራጭ የሆነ ይመስላል።

ውብ ምሽት ተመኘን
#VW #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የካርበን ልቀት መመርመሪያን የሚያታልል መሳሪያ በ BMW የናፍጣ መኪኖች ላይ በድብቅ ተገጥሞ ተገኘ።

ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ቶዮታ ካምፓኒ በመኪኖቹ ላይ የካርበን ልቀት መመርመሪያ መሳሪያዎችን የሚያታልል መሳሪያ በመኪኖቹ ላይ ገጥሞ ከጃፓን መንግስት ቁጣ ገጥሞት የነበር ሲሆን አሁን ደግሞ የጀርመን የመኪና አምራች ካምፓኒ የሆነው BMW በናፍጣ መኪኖቹ ላይ ይሄን መሳሪያ ገጥሞ ተገኝቶዋል ::

የጀርመን የትራንስፖርት ባለስልጣን (KBA) ባደረገው ምርመራ f-25 የተሰኘው የ BMW X3 ሁለተኛው ጀነሬሽን የሆነው የናፍጣ መኪናው ላይ ይሄንን መሳሪያ ያገኘ ሲሆን እስከአሁን የጀርመን መንግስትም ሆነ የአውሮፓ መንግስታት በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት እርምጃ አልወሰዱም።

በዚህ ህገወጥ ተግባር ላይ መንግስታቱ እርምጃ በሚወስዱበት ጊዜ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መኪኖች ወደ ካምፓኒው (recall) የሚጠሩ ይሆናል።

ውብ ምሽት ተመኘን
#BMW #Diesel
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ግዙፉ የመኪና አምራች ካምፓኒ Toyota ቢሊየን ዶላሮችን አዲስ አይነት ሞተር ለማበልፀግ ፈሰስ አርጎ እየሰራ ነው።

በአለም ደረጃ ብዙ ቁጥር ያላቸውን ከትናንሽ የቤት ተሽከርካሪዎች እስከ ትላልቅ የህዝብ ማመላለሻዎችን አምርቶ ለአለም ገበያ በማቅረብ የምናውቀው Toyota በመጪዎቹ አመታት ማለትም ወደፊት ገበያው ላይ ተፈላጊ ይሆናሉ ብሎ ያመነባቸውን በነዳጅ እና በሃይድሮች የሚንቀሳቀሱ ሞተሮችን(Engine) በተሻሻለ መንገድ ለማበልፀግ ትልቅ ገንዘብ በጅቶ እየሰራ ይገኛል።

ብዙ የመኪና አምራቾች ወደፊት ገበያው ላይ ተፈላጊ ይሆናሉ ብለው ያመኑባቸው የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቢሆንም Toyota ግን "ምን አይነት upgrade ቢደረግባቸው የድራይቪንግ ሬንጃቸው ቢጨመር በአለም ደረጃ 30% በላይ ፈላጊ የላቸውም" ሲል ይሞግታል።

ብዙ የመኪና አምራች እና የዘርፉ ምሁራን ይሄን ነገር የተቃወሙት ሲሆን ብዙ የሚባሉ ሃገራት እንደ ቻይና, አሜሪካ, እንግሊዝ, ካናዳ እና ብዙ የሚባሉ የአፍሪካ ሃገራት ከአየር ንብረት መበከል እና ለነዳጅ ከሚወጣው ትልቅ ወጪ አንፃር በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ለመቀነስ ትልቅ ታክስ እየጣሉባቸው ህዝባቸውን የኤሌክትሪክ መኪኖችን አንዲጠቀሙ እያበረታቱ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት ደግሞ በ2035 ሙሉ በሙሉ በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን እናግዳለን ብለዋል።

ፍክት ያለ ሀሙስ ተመኘን
#Toyota #Engine
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Apple የኤሌክትሪክ መኪኖች ለማምረት የጀመረውን ጉዞ አቋረጠ

ከ2014 ጀምሮ ለአስር አመታት self driving የሆኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች ለማምረት ብዙ ቢሊየን ዶላሮች በጅቶ ጥናት እና ምርምር እያደረገ የነበር ሲሆን አሁን ላይ ይህን በማቆም ከ2000 በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖቹን ለማበልፀግ ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞቹን ወደ ካምፓኒው (Generative AI) ፕሮጀክት ስራ ላይ አንዲዘዋወሩ አደረገ።

ለዚህም እንደ ምክንያት ያስቀመጡን እንደሚጠብቁት ትርፋቸውን ከፍ አያደርግልንም ገበያው ላይም ተፈላጊነት ላይኖረው የሚችል product ላይ ኢንቨስት አናደርግም ብለው ነው። ብዙዎች እንደተጨማሪ ምክንያት ያስቀመጡት የሌሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለ ፍላጎት መቀነስ ዋጋው ላይ ካለ ጦርነት ጋር ተደማምሮ ነው ሲሉ ተደምጧል።

ፍክት ያለ ሀሙስ ተመኘን
#Apple #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Aston martin የመጀመሪያ የኤሌክትሪክ መኪናውን ወደ ገበያ የሚያወጣበት ጊዜ አራዘመው ።

የእንግሊዝ ቅንጡ መኪኖችን አምራች ካምፓኒ የሆነው Aston Martin የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ መኪናውን የሚለቅበትን ቀን አዘገየው :: ለዚህም እንደ ምክንያት ያስቀመጠው የኤለክትሪክ መኪኖቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው በቂ ሸማቾችን ስላላገኘሁ ነው ብሎዋል።

በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ተስፋ ባይቆርጥም ይበልጥ በምትኩ ትኩረት ነዳጅን እና ኤሌክትሪክን አንድ ላይ የሚጠቀሙ (Hybrid) ተሽከርካሪዎችን ማምረት ላይ እንደሚያረግ አሳውቆል።

ፍክት ያለ ሀሙስ ተመኘን
#AstonMartin #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Honda fuel cell (ኬሚካል ኢነርጂን ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል የሚቀይር)  የኤሌክትሪክ CR-V አቸውን አስተዋወቁ።

Toyota Mirai የተባለው መኪናው ላይ ወደ 40,000 ዶላር ያህል መነሻ ዋጋ ሲኖረውየነበረውን 60% ቅናሽ በማድረግ 12,000 ዶላር እየሸጡ ሲሆን Honda በfuel cell ተንቀሳቃሽ የሆነውን CR-V ቨርዥናቸውን ለማስተዋወቅ ቆንጆ አጋጣሚ ሆኖላቸዋል ።

አሜሪካ ኦሃዬ ግዛት ውስጥ የሚመረተው ይሄ CR-V Honda እና GM በጋራ በመሆን ያበለፀጉትን የfuel cell ሲስተም ሲጠቀም 174 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጭ FWD(Front Wheel Drive) የሆነ ኤሌክትሪክ ሞተር ተገጥሞለታል።

ይሄንም ሞተር ለማንቀሳቀስ ከ Toyota Mirai አንፃር አነስ ያለ የባትሪ ፓክ እና የfuel cell ታንከር ሲኖረው የመያዝ አቅሙም 4.3 ኪሎግራም ነው።

በአጠቃላይ ይሄ ሲስተም ወደ 434 ኪሎሜትር ድራይቪንግ ሬንጅ ሲሰጠን 18 Kwh ባትሪ ፓኩ ከ 30-46 ኪሎሜትር ተጨማሪ ጉዞን እንዲያረግ ያስችለዋል ።

ይሄ መኪና በመጀመሪያ Summer ላይ ጃፓን ላይ ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን በመቀጠል አመቱ ከማለቁ በፊት የአሜሪካ ገበያ ላይ እንደሚቀርብ አስታውቀዋል ።


#Honda #FuelCell
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ጠቃሚ_መረጃ

እንዴት ነው የመኪናችንን ባትሪ ሲሞት በሌላ ባትሪ የምናስነሳው?

1. የሞተ ባትሪውን ፖዘቲቭ ላይ ኬብሉን መሰካት
2. ቻርጅ ያለው ባትሪ ፖዘቲቭ ላይ ኬብሉን መሰካት
3. ቻርጅ ያለው ባትሪ ኔጌቲቭ ላይ ኬብሉን መሰካት
4. የሞተ ባትሪውን ኔጌቲቭ ላይ ኬብሉን መሰካት
5. ባትሪው የሚሰራው መኪና ሞተሩን በማስነሳት በትንሹ ለ 3 ደቂቃ እንዲሰራ ማድረግ
6. ከዛ ባትሪው የሚሰራው መኪና ሞተሩን ማጥፋት
7. ባትሪ የሞተበትን ማስነሳት
8. ከዛ ከ 4 ወደ 1 በቅደም ተከተል ኬብሉን መንቀል

ይህንን የሰራነው ፖስት ለአፍሮ ሊንክ የመኪና መሸጫ ሲሆን እናንተም መሸጫ ኖሯችሁ መኪኖቻችሁን እንድናስተዋውቅ እንዲሁም ብራንዳችሁም በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲተዋወቅ ከፈለጋችሁ በ 0911663121 በመደወል እኛን ማናገር ትችላላችሁ ::

https://www.tg-me.com/afrolink_motor

Join በማድረግ የተለያዩ ከኤሌክትሪክ መኪና ጋር የተገናኙ ብዙ ለየት ለየት ያሉ አስተማሪ እና ጠቃሚ መረጃዎችን የምታገኙበት ቻናል ነው ::

@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Elon musk ቀጣይ አመት ላይ Tesla Roadster የተሰኘውን መኪናቸው ይለቀቃል አለ።

ቴስላ ይህ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚንቀሳቀሰውን የአለማችን ፈጣኑ መኪና ይሆናል ያሉትን tesla roadster የተሰኘውን Hyper Car በቀጣይ አመት ላይ ለገበያ እንደሚቀርብ የተናገሩ ሲሆን

የቴስላ መስራች እና ceo የሆነው elon musk እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ሃሳቦችን ተናግሮ ተግባር ላይ ያልዋሉ ቢሆንም እንደተናገረው ከሆነ" የሮድስተር ምርት ዲዛይን ያለቀ ሲሆን በዚህ አመት መጨረሻ ላይም ይፋ ይሆናል"

እናም "ይሄን የመሰለ መኪና አይኖርም ፣ ያው መኪና ብላቹ ልጠሩት ከደፈራቹ ጥሩት😂" ብሎዋል።

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#Tesla #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Huawei በ 1 ሰከንድ ቻርጅ አንድ ኪሎ ሜትር እንድንጓዝ የሚያስችለንን የመኪና ቻርጀር እያበለፀገ ነው

አሪፍ አሪፍ flagship ስልኮችን እና ለሰፊው ማህበረሰብ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ስልኮችን በማምረት የምናውቀው Huawei በኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይም ትልቅ ተፅኖ ያለው ካምፓኒ ነው።

አሁን ላይ እያበለፀጉት ያለው ሱፐር ፋስት የመኪና ቻርጀር በአምስት ደቂቃ ቻርጅ ብቻ እስከ 260 ኪሎሜትር ጉዞ እንድናደርግ የሚያስችለን ቻርጀር ሲሆን 600 Kilowatt ከ 600amps ጋር ነው

እነዚህን ቻርጀሮች ለማምረት ከፍተኛ ወጪ ያለው ቢሆንም Huawei በ Kwh (Kilowatt hour) ያለውን ክፍያ እንደሚቀንሱ ተናግረዋል።

ድንቅ ቀን ተመኘን
#Huawei #Charger
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/23 18:29:21
Back to Top
HTML Embed Code: