Telegram Web Link
አስገራሚው የLexus RZ ኤሌክትሪክ መኪና መሪ


Lexus RZ ላይ የ Yoke መሪ ሲሆን የምታገኙት ይሄ ቴስላም ሌሎች መኪኖችም ላይ ታገኛላችሁ :: እዚህ መኪና ላይ ለየት የሚለው ነገር መሪውን በአንድ ዙር ሙሉ ጎማውን ማዞር ትችላላችሁ :: ይሄም የሆነው ጎማው እና መሪው ምንም mechanical connection ሳይኖራቸው ወደ ጎማው electronic signal በመላክ ነው የሚሰራው :: በጣም ወድጄዋለሁ እናንተስ?
ስለዚህ መኪና አጭር ቪዲዮ ቲክቶክ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMY3RGpvd/

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Lexus #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
mg-comet.pdf
8 MB
ለህንድ ገበያ ላይ በርካሽ የቀረበ የኤሌክትሪክ መኪና

MG Comet EV

በአንድ ቻርጅ 230 ኪሎሜትር መጟዝ የሚችለው ይሄ የኤሌክትሪክ መኪና አራት ሰው የሚይዝ ሲሆን ሳይዙም ከ Kia Ray ጋር ተቀራራቢ ነው በቁመት :: ግን እዚህ ላይ ሁለት በር ነው የምታገኙት :: እንዲሁም ደግሞ ከጀርባም በጣም ጠባብ ቦታ ነው ያለው :: ዋጋውም 14,700 ዶላር ነው :: ተጨማሪ ነገሮችን ብሮሸሩን በማውረድ ሙሉ መረጃ ታገኛላችሁ ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#EV #MG
@OnlyAboutCarsEthiopia
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዋጋ ማስተካከያው ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም  የሚቆይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት፡ -

- ቤንዚን 👉 በሊትር 69 ብር ከ43 ሳንቲም ብር

- ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 71 ብር ከ08 ሳንቲም

- ኬሮሲን 👉 በሊትር 71 ብር ከ08 ሳንቲም

- የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 በሊትር 66 ብር ከ60 ሳንቲም 

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 57 ብር ከ84 ሳንቲም

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 56 ብር ከ50 ሳንቲም ተደርጓል።

መረጃው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍቢሲ ነው።

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Fuel #News
@OnlyAboutCarsEthiopia
2023 Toyota Corolla Cross Hulemekina Brochure.pdf
1.7 MB
Toyota Corolla Cross

ከ2020 ጀምሮ መመረት የጀመረ compact crossover suv ሲሆን በ Toyota CHR እና በ Toyota Rav4 መካከል የሚገኝ መኪና ነው :: በ Toyota TNGA PLATFORM ላይ የተሰራ መኪና ነው :: በነዳጅ እና በ hybrid የሚገኝ ሲሆን በ 1.8 litre ወይም በ 2 litre ባለ 4 cylinder ሞተር ይመጣል:: በሁለቱም በ FWD እንደ እስታንዳርድ እና በ AWD አማራጭ ማግኘት ይቻላል :: 6 trim level ሲኖረው L, LE, XLE ነዳጅ ብቻ ለሚጠቀሙት ለሀይብሪድ ሞዴሎቹ ደግሞ S, SE, XSE ትሪም ሌቭል ሲኖረው በቀላሉ የትኛው ትሪም ሌቭል እንደሆነ በቸርኬያቸው ማወቅ ይቻላል ::
ብሮሸሩ ላይ ሙሉውን መረጃ ታገኛላችሁ :: መኪናውን መግዛት ካሰባችሁ በ 0911663121 ላይ በመደወል ሙሉ መረጃ እንሰጣችሗለን ::

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#Toyota #Corolla
@OnlyAboutCarsEthiopia
ID.4 & ID.6 Simple Guide on OnlyAboutCarsEthiopia.pdf
1.8 MB
VW ID.4 እና ID.6 የገዛችሁ እና ለመግዛት የምታስቡ ሰዎች ይህ ጋይድ መኪናችሁ ላይ ምን ምን ነገሮች እንዳሉ እንዲሁም ደግሞ ምን ምን ምልክቶች እንደሆኑ የሚያብራራ አጠር ያለ PDF ነው :: ይህ መኪና ላላቸው ሰዎችም ሼር አድርጉላቸው :: እንዲሁም ደግሞ VW ID.4 እና ID.6 ከገበያው ባነሰ ዋጋ እኛ ጋር አለ የምትሉ አስመጪዎች መኪኖቹን የሚፈልጉ ደንበኞች ስላሉን በ 0911663121 ላይ ደውሉልን ::

ሞቅ ሞቅ ያለ ምሽት ተመኘን
#VW #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
The New Revised Excise Tax System on OnlyAboutCarsEthiopia.pdf
9.5 MB
አዲሱ ለመኪና የተሻሻለው የኤክሳይስ ታክስ ምን የተለየ ነገር አለው?

አዲሱ የተሻሻለው የመኪና የኤክሳይስ ታክስ ከትንንሽ የነዳጅ መኪኖች ጀምሮ እስከ ትልልቅ ነዳጅ የሚጠቀሙ መኪኖችን የታክስ ሲስተም ላይ ለውጥ አምጥቷል :: እሱ ብቻ ሳይሆን በተሻሻለው ላይ ክፍልፋዩን ያ ማለት በሞተራቸው CC የሚከፋፈሉበትን ከ 3 ወደ 4 አሳድገውታል :: ስለዚህ በአዲሱ ከ 1500 CC በታች, ከ 1500 CC እስከ 2500 CC, ከ 2500 CC እስከ 3000 CC እና ከ 3000 CC በላይ በሚል ተከፍለዋል :: ይህም ለትንንሽ መኪኖች ዋጋቸው እንዲጨምር እና ለትልልቅ መኪኖች ደግሞ የሚከፈለው ቀረጥ እንዲቀንስ ያደርገዋል :: ምንም እንኳን አሁን ላይ የነዳጅ መኪናን በፍራንኮቫሉታ (በተመላሽ) ማስገባት ነው የሚቻለው :: ፀድቆ ተግባር ላይ የዋለው ከባፈው ሳምንት ጀምሮ ሲሆን ሙሉ ዝርዝር መረጃውን ከላይ ባለው PDF ላይ ማግኘት ትችላላችሁ ::
ከበፊቱ የታክስ ሲስተም ጋር ማወዳደር ከፈለጋችሁ ከዚህ በፊት የሰራሁት የዩትዩብ ቪድዮ ከስር ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/Ib9S7B59Mhw

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Ethiopia #Tax
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለሞተር ስፖርት ቤተሰቦች በሙሉ

በኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት አሶሴሽን የሚዘጋጀው የራሊ መኪና ውድድር በነገው እለት ግንቦት 13/ 2015 ላይ በገላን ይደረጋል :: ቦታውን እና ተጨማሪ መረጃዎችን ዛሬ ማታ ወይም ነገ ጠዋት የምናሳውቅ ይሆናል ::

ግሩም ከሰአት ተመኘን
#Rally #Race
@OnlyAboutCarsEthiopia
የዛሬው በኢዮጵያ ሞተር ስፖርት አሶሴሽን የተዘጋጀው የራሊ ውድድር መነሻ ቦታው ገላን ኮንዶሚኒየም ሲሆን ካርታው ላይ እንደምታዩት እሱን ተከትለው የሚሄዱ ይሆናል :: 2:30 ላይ የሚጀምር ሲሆን እስከ ማታ 11:30 ይቆያል :: ለተወዳዳሪዎች መልካም እድል ተመኘን

#Rally #Race
@OnlyAboutCarsEthiopia
#MarathonTrading

መኪና ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ ማስመጣት ትፈልጋላችሁ?

እንግዲያውስ Marathon Trading ለእናንተ መፍትሄ ይዞ መቷል :: የኤሌክትሪክም የነዳጅም መኪኖችን ቀጥታ ከካምፓኒ እየወሰደ ለእናንተ የሚያቀርብ ድርጅት ነው :: አሁን በብዛት የሚገቡትን የ Toyota VW Audi BMW Honda መኪኖችን በብዛት እየላኩ ይገኛሉ :: ዋጋቸውም በካምፓኒ ዋጋ ነው የሚያቀርቡት :: በብዛትም በፍሬም መግዛት ትችላላችሁ :: ታዲያ እስከ ጅቡቲም እስከ ኢትዮጵያም ያመጣሉ :: ከእናንተ የሚጠበቀው ማዘዝ ብቻ ነው :: ተጨማሪ መረጃ ከስር በምታገኙት አድራሻ ማናገር ትችላላችሁ ::

WhatsApp እና telegram:
+86 185 6539 3229
ከ Tesla Model Y የሚሻል ኤሌክትሪክ መኪና

2023 Cadillac Lyriq

Lyriq የ Cadillac የመጀመሪያው ኤሌክትሪክ መኪና ነው :: በደንብ ከሚታወቀው ከ Cadillac Escalade ረዘም ያለ ነው :: ታዲያ ከ Tesla Model Y በምን ቢሻል ነው? በውጫዊ ዲዛይን ባለው ቴክኖሎጂ በውስጥ ስፋት እና ውስጥ ላይ ከ Google ጋር በመጣመር የሰሩት አስገራሚ ከርቭ እክሪን አለው :: የዛሬው የዩትዩብ ቪዲዮ እዚህ መኪና ላይ ያተኮረ ይሆናል :: ኢትዮጵያ ስለተላከ ሲመጣ ደግሞ ተጨማሪ ነገሮችን አብረን እናያለን :: ዩትዩብ ላይ ከወር በሗላ ስለተመለስን የእናንተ እገዛ እንፈልጋለን :: ስለዚህ እየገባችሁ በማየት እና ላይክ በማድረግ እንድትደግፉን እንጠይቃለን ::
የ Cadillac Lyriq መኪና ሪቪው
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/AP1OQ8WFPrI

መልካም ምሽት ተመኘን
#Lyriq #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024 Toyota Tacoma is the Ultimate Adventure Machine.pdf
1.2 MB
የ 2024 Toyota Tacoma ምን ምን አሻሽለው ነው ያቀረቡት?

የ 2024 Toyota Tacoma መኪና በአዲስ ዲዛይን ያቀረቡት ሲሆን ይሄም 4ኛው ጀነሬሽን ሞዴል ነው :: በ 8 የትሪም አማራጮች ማለትም ከ SR እስከ TRD Pro ያሉትን በአዲሱ ሞዴል ላይ የሀይብሪድ አማራጭም ይዘው ቀርበዋል :: የሞተር አማራጩ በ 2.4 ሊትር ብቻ የሚገኝ ሲሆን ከ 228 እስከ 326 የፈረስ ጉልበት አለው :: ሌላው ደግሞ የባሌስትራ ወይም የሊፍ ስፕሪንግ ወደ ኮይል እስፕሪንግ ቀይረውታል :: ስለዚህ የበለጠ ምቾት እንዲኖረው ያደርጋል :: ግን ከዛ በላይ ደግሞ ውስጡ ያምራል ::
በዛሬው የቲክቶክ ቪዲዮ ስለሱ በጥቂቱ ላስመልክታችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZM2N6SwKU/

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Toyota #Tacoma
@OnlyAboutCarsEthiopia
Volkswagen ID.6 Crozz Pro Review

ይህ የኤሌክትሪክ SUV መኪና በ VW ID ኤሌክትሪክ series ቻይና ውስጥ ብቻ የሚመረት መኪና ነው :: ቮልስዋገን ከ FAW ጋር እና ከ SAIC ጋር አንድ ላይ የሚሰሩት መኪና ሲሆን Pro X በ SAIC ጋር Crozz ደግሞ በ FAW ካምፓኒ ጋር ነው የሚሰሩት :: ስለዚህ ረዘም ያለ አሻም ቲቪ ላይ የተለቀቀ የ Crozz Pro ሞዴል ሪቪው አለ :: ከ Pro X ሞዴሉ ጋር ማወዳደር ከፈለጋችሁ የሁለቱንም ቪዲዮ ሊንካቸውን ከስር አስቀምጫለሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

Crozz Pro
https://youtu.be/TIomyFop47U

Pro X
https://youtu.be/DYacLXpdovs

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#VW #ID6 #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ፍጥነትን ከመቆጣጠር እስከ ራሱን በራሱ የሚነዳ ተሽከርካሪ | ክሩዝ ኮንትሮል ከምን ወደ ምን?

ክሩዝ ኮንትሮል አሁን ላይ አብዛኛዎቹ መክኖች ላይ ተገጥሞ ታገኙታላችሁ ::ግን ክሩዝ ኮንትሮል እንዴት ተፈጠረ? የፈጠረውም ቲቶር በምን አጋጣሚ ሊያስበው ቻለ? እንዴት እያደገ መጣ? አሁን ላይ የሰው አልባ ተሽከርካሪ እየተሰራ ነው? እና ወደፊትስ? በዛሬው ቪዲዮ ስለነዚህ ነገሮች በዝርዝር እንመለከታለን :: ከስር የምታገኙትን የዩትዩብ ሊንክ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/xRycVFv2ykY

ቅልል ያለ ምሽት ተመኘን
#CruiseControl #Selfdrivingcars
@OnlyAboutCarsEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው Porsche Taycan

Porsche Taycan 4S

Porsche Taycan የመጀመርያው የፖርሽ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን ለገበያ የወጣው በ 2019 ላይ ነበር :: ኢትዮጵያ ውስጥ በ 2021 ላይ እንደገባ ሳይ በጣም ነበር የገረመኝ :: በዛሬው ቪዲዮ ስለዚህ ኤሌክትሪክ መኪና በዝርዝር ስላሉት ነገሮች ስለውስጣዊ እና ውጫዊገፅታው ሬንጁ እና በመጨረሻም ስለዋጋው እንመለከታለን :: ከስር የምታገኙትን የዩትዩብ ሊንክ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/8_mZQhwQtvM

ልዩ ያለ ምሽት ተመኘን
#Prosche #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
አንዴ ነው አሉ አፄ ሀይለስላሴ (ጃንሆይ) መኪና እንዲሰራላቸው ለጃፓኑ ቶዮታ መኪና አምራች ካምፓኒ ትእዛዝ ይሰጣሉ ::
የቶዮታ ካምፓኒ ዋና ስራ አስኪያጅ ለክብሮ የሚመጥን ምን አይነት መኪና ይሰራልዎ ብሎ ጥያቄ ያቀርባል :: ጃንሆይም "ለአንድ ኩሩ ዘር" የሚሆን መኪና እንደሚፈልጉ ይነግሯቸዋል :: ከዛም መኪናው ከተሰራ ጀምሮ እስከአሁን "LandCruiser“ ተብሎ ይጠራል ይባላል :: 😁

ምንጭ - በእምነት አውቶሞቲቭ

በዛውም የዩትዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳትረሱ

Https://youtube.com/yonathandesta

ፈታ የምትሉበት ቀን ተመኘን
#LandCruiser
@OnlyAboutCarsEthiopia
አዲስ የቶዮታ እና ሌሎችም የነዳጅ መኪኖችን ገዝታችሁ ከሆነ 5 ማድረግ የሌለባችሁን ነገሮች እንይ

1. 320 ኪሎሜትር እስኪደርስ ድረስ በሀይል ፍሬኑን እፍን ማድረግ የለባችሁም ::
2. ሙሉ በሙሉ የነዳጅ ፔዳሉን ረግጣችሁ አትንዱ
3. 1600 ኪሎሜትር እስኪደርስ ከ 100 ኪሎሜትር በሰአት በላይ አታሽከርክሩ ::
4. Pickup ወይም SUV ከሆነ እስከ 800 ኪሎሜትር ድረስ ተጨማሪ እቃ እየጎተታችሁ መሄድ የለባችሁም
5. የመጨረሻው ልክ 1600 ኪሎሜትር ሲደርስ የመኪናችሁን የመጀመሪያውን ዘይት ቀይሩ ::
ዝርዝር ምክንያቶችን እንዲሁም ተጨማሪ ማድረግ የሌለባችሁን ነገሮች ዮትዩብ ላይ ለቅቂያለሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/BrUURbXfa1k

ግሩም ምሽት ተመኘን
#NewCars #Toyota
@OnlyAboutCarsEthiopia
Toyota FJ Cruiser እንዴት በጣም ተወዳጅነቱ እየጨመረ መጣ?

ቶዮታ FJ 40 ከ 60 አመት በላይ በጣም ተወዳጅ ሆኖ የቆየ መኪና ነው :: ቶዮታ FJ Cruiser ደግሞ ከ 2007 - 2014 በአሜሪካ እንዲሁም በሌሎች አህጉራት ማለትም በእስያ አሁንም ድረስ ዲዛይኑ ብዙ ሳይለወጥ የሚመረት መኪና ነው :: በጣም ግን ተወዳጅነቱ እንዴት ሊመጣ ቻለ? እንዴት መመረትስ ጀመረ? ዋጋው ለምን እየተወደደ መጣ? እና ጃንሆይ እና ላንድ ክሩዘር የሚያገናኛቸው ታሪክ እውነታው ምንድነው? የሚለውን በዛሬው የዩትዩብ ቪዲዮ እንመለከታለን :: ሊንኩን ከስር ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/_0wWb9NHknc

ብሩህ ምሽት ተመኘን
#Toyota #FJCruiser
@OnlyAboutCarsEthiopia
#MarathonTrading

መኪና ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ በተመጣጣኝ ዋጋ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ማስመጣት ትፈልጋላችሁ?

እንግዲያውስ Marathon Trading ለእናንተ መፍትሄ ይዞ መቷል :: የኤሌክትሪክም የነዳጅም መኪኖችን ቀጥታ ከካምፓኒ እየወሰደ በጥቂት ቀናት ውስጥ በመጫን ለእናንተ የሚያቀርብ ድርጅት ነው :: ዋጋቸውም በካምፓኒ ዋጋ ነው የሚያቀርቡት :: በብዛትም በፍሬም መግዛት ትችላላችሁ :: ታዲያ በትንሽ ጊዜ ውስጥ እስከ ጅቡቲም እስከ ኢትዮጵያም ያመጣሉ :: በየጊዜው እየላኩ ስለሆነ የሚደርስበት ጊዜ ይቆያል ብለው አይጨነቁም :: ከእናንተ የሚጠበቀው ማዘዝ ብቻ ነው :: ተጨማሪ መረጃ ከስር በምታገኙት አድራሻ ማናገር ትችላላችሁ ::

WhatsApp
+86 185 6539 3229
የቻይናው G-Wagon
Cybertank 300 ሪቪው

ብዙዎቻችን ቻይና ውስጥ ያሉ የመኪና አምራች ካምፓኒዎች ለየት ያሉ መኪኖችን የሚያመርቱ አይመስለንም :: ግን ይሄ እውነት አይደለም :: በተለይ ከ 2021 ጀምሮ በብዛት ለሀገር ውስጥም ለውጪ ሀገራትም ማለትም ለአውሮፓ እና ለአፍሪካ ይልካሉ :: ስለዚህ እሱን በማሰብ የ G-Wagen ዲዛይን ያለውን መኪና በሚገርም ዋጋ አንድ ካምፓኒ ለገበያ አቅርቧል ::
Cybertank 300 መኪና ከ Mercedes G-Wagon እና ከ Ford Bronco ጋር የሚመሳሰሉ ብዙ ነገሮች አሉት :: በዛሬው ቪዲዮ ይህንን Cybertank 300 ከእነሱ መኪኖች ጋር እያወዳደርኩ አሳያችሗለሁ :: ውጪውን አይታችሁ ተደማችሁ ሳትጨርሱ ውስጡን ደግሞ ሳሳያችሁ ይበልጥ ትገረማላችሁ ::
ሙሉ ቪዲዮውን ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/XgP15d_sGuQ

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Cybertank
@OnlyAboutCarsEthiopia
" ህጋዊ ፈቃድ ያለው መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ በጊዜያዊነት ወደ ሀገር እንዳይገባ ታግዷል " - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

ይህንን አይታችሁታል ብዬ አስባለሁ :: ግን እውነታው ምንድነው? እስከአሁን የገቡትስ በምን ፈቃድ ገቡ? እውነት መኪኖቹ ቴክኒካል ችግር ኖሯቸው ነው? ወይስ ሌላ ነው ምክንያቱ? ነገ ከምሽቱ 2 ሰአት ጀምሮ ቲክቶክ ላይቭ ላይ የምንወያይ ይሆናል :: ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁ እዚህ ላይ በማስቀመጥ እሱ ላይ የምንወያይበት ይሆናል ::
ነገ እንገናኝ

ልዩ ምሽት ተመኘን
#VW #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/24 08:37:42
Back to Top
HTML Embed Code: